Sest Computer School
78 subscribers
16 photos
2 files
41 links
💻 Welcome to the world of computers
🖥️ From basics to advanced
⚙️ Tips, tricks, tutorials & real skills
@sestcom_bot ለፈጣን ምላሽና ማብራሪያ
Download Telegram
✳️ የስልካችንን DATA ስናበራ የሚመጡት G, E, 3G, H/H+, 4G, 5G እነዚህ ምልክቶች ምንድናቸው?

🔺G : Feature ስልኮች (Keypad) ላይ ሳይቀር ስልኩ ከኢንተርኔት ጋር ሲገናኝ ይህንን ምልክት እናያለን። ትርጉሙም GPRS (Global Packet Radio Service) ማለት ነው።

🔺E : Edge -በመባል የሚታወቀው ይህ Network የስልካችን ኔትወርክ Enhanced GPRS የሚባለውን መጠቀም ሲጀምር ይህንን እናያለን። የታወቀው ፍጥነት ደግሞ 0.4mb/s ነው።

🔺3G : ብዙዎቻችን እናቀዋለን የ3rd Generation Network ሲሆን በGSM Network ላይ የሚሰራ Network ነው። 3G በአማካኝ እስከ 2mb/s ፍጥነት ይኖረዋል።

🔺H/H+ : HSDPA (High speed Downlink packet access) ማለት ሲሆን ብዙ ስማርት ስልኮች ላይ H ከሆነ እስከ 7 mb/s ድረስ ይሄዳል። H+ ሲሆን ደግሞ እስከ 21mb/s ድረስ ይሄዳል።

🔺4G/LTE : ይህ 4ኛው ትውልድ ኔትወርክ 5G ከመምጣቱ በፊት ምርጥ Network ነበር። ፍጥነቱም እስከ 150mb/s ነው። ብዙ ጊዜ ከwi-fi በበለጠ ፍጥነት ይኖረዋል።

🔺5G : የ5ኛው Generation ሲሆን ከ4G በ1000 እጥፍ የDownload ፍጥነት ሊኖረው ይችላል።


#Tech_Tips
#Join #share

@sest_computer
✳️ ብንጠቀምባቸው ስራን የሚያቀሉልን ጠቃሚ ዌብሳቶች!

1. የተለያዩ ነገሮችን ለማወዳደር
  versus.com

2. ለተለያየ አገልግሎት ጊዚያዊ ኢሜል ካስፈለገዎ :
10minutemail.com  ወይም yopmail.com

3. ማንኛውንም ትልልቅ ሶፍትዌሮች ከነ ሲሪያል ኪ ዳውንሎድ ለማድረግ
Getintopc.com

4. የዋይፋይ (ኢንተርኔት) ፍጥነት ለማወቅ Speedtest.net   ወይም fast.com ን ይጠቀሙ

5. በቀን ና ሰአት ላይ የተለያዩ ቀመሮችን መስራት ከፈለጉ :
timeanddate.com ን ቢጠቀሙ ጊዜ ይቆጥባሉ።

6. ጠንከር ያለ ና በቀላሉ የማይሰበር የይለፍ ቃል
/password ከፈለጉ
Passwordsgenerator.net ይጠቀሙ

7. ከጎበኙት ድረገፅ የወደዱትን ፔጅ ቢፈልጉ በፕሪንት ወይም pdf አልያም በኢሜይል ማስቀረት ካሰቡ :
Printfriendly.com ይጠቀሙ።

8. የተለያዮ የውጪ ቋንቋዎችን ለመማር
Duolingo.com ን ይጎብኙ

9. አልከፍት ያሎትን ድረገፅ አልሰራ ያለው ለእርሶ ብቻ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ
downforeveryoneorjustme.com  ወይም isitdownrightnow.com ዌብሳይቶቾ ጠቃሚ ናቸው።

10. ኮምፒውተራችን ላይ መጫን ሳያስፈልገን የMicrosoft office ን ምርቶች ኦንላይን ለመጠቀም
office.com ላይ በመግባትና የmicrosoft ን ኢሜል በማስገባት መጠቀም ይችላሉ።

@sest_computer
በጣም ጠቃሚ ትምህርታዊ ነፃ AI Tools

▪️ Humata AI Document summarizer and review
▪️ Textero AI Essay Writer
▪️ WolframAlpha Help on mathematics and science
▪️ MathGPTpro Helps on Mathimatics
▪️ Quizgecko ዶክመንት ሰጥታችሁት ጥያቄ የሚያወጣ
▪️ Prepsup በተለያዩ ዘርፎች ለፈተና የሚያዘጋጃችሁ
▪️ LearnGPT ማንኛውንም የትምህርት አይነት በቀላሉ የሚያስረዳ
▪️ Codeamigo Code assistant
▪️ gptionary Conversation with an AI on a specific topic
▪️ Gradgpt ኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ለመቀላቀል Statement of Purpose, Letter of recommendation, SOP Review
ለመፃፍ ያግዛል።

Bonus
BrandScript Generator content and story generator ለማድረግ

መሰል ትምህርቶችን ይማሩ!!!!!
@sest_computer
✳️ የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች ድረገፆች❗️

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ www.aau.edu.et
መቀሌ ዩኒቨርስቲ  www.mu.edu.et
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ www.astu.edu.et
አክሱም ዩኒቨርስቲ www.axu.edu.et
አምቦ ዩኒቨርስቲ www.ambou.edu.et
አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ www.amu.edu.et
ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ www.bdu.edu.et
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ www.dbu.edu.et
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ www.dmu.edu.et
ዲላ ዩኒቨርሰቲ  www.du.edu.et
ጎንደር ዩኒቨርስቲ www.gu.edu.et
ጂማ ዩኒቨርስቲ www.ju.edu.et
ሃረማያ ዩኒቨርስቲ www.haramaya.edu.et
ሃዋሳ ዩኒቨርስቲ www.hu.edu.et
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ www.wsu.edu.et
ወለጋ ዩኒቨርስቲ www.wu.edu.et
ድሬ ዳዋ ዩኒቨርስቲ  www.ddu.edu.et
ወሎ ዩኒቨርስቲ www.wou.edu.et
ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ www.jgu.edu.et
መዲ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ www.mwu.edu.et
ሚዛን ቲፒ ዩኒቨርሲቲ www.mtu.edu.et
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ www.su.edu.et
ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ www.kuc.edu.et
አአ ሾል.& ቴክ ዩኒቨርሲቲ www.aastu.edu.et
አዲግራት ዩኒቨርሲቲ  www.adu.edu.et
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  www.asu.edu.et
ቡሌ ሁራ ዩኒቨርስቲ www.bhu.edu.et
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ www.dbtu.edu.et
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ www.wcu.edu.et
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ  www.wku.edu.et
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ  www.wdu.edu.et
አርሲ ዩኒቨርሲቲ www.aru.edu.et
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ www.gmu.edu.et
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ www.obu.edu.et


#Join
@sest_computer
✳️ እስከ 100 GB + ነፃ ኦንላይን ማንኛውም File ማስቀመጫ ምርጥ ሳይቶች❗️

🔺Sign up at Ozibox.com to get 100GB of free storage.

🔺Sign up at SurDoc.com to get 100GB of free storage.

🔺Sign up at Shared.com to get 100GB of free storage.

🔺Sign up at Adrive.com to get 50GB of free storage

🔺Sign up at Mega.co.nz to get 50GB of free storage.

🔺Sign up at Hubic.com to get 25GB of free storage.

🔺Sign up at Firedrive.com to get 20GB of free storage.

🔺Sign up at Onedrive.live.com to get 15GB of free storage.

🔺Sign up at Copy.com to get 15GB of free storage.

🔺Sign up at Mediafire.com to get 10GB of free storage. (40GB more available with other activities)

🔺Sign up at Pcloud.com to get 10GB of free storage (10GB more available with other activities)

🔺Sign up at Box.com to get 10GB of free storage.

Tera box is my best but the ads.....

@sest_computer
✳️ ብዙ ጊዜ ኮምፒውተራችን ላይ Delete አልሆን ያሉ ፎልደሮችን እንዴት እንደምናጠፋ እናያለን❗️

Step 1. Folder/File ጋር Right Click አድርገን Properties የሚለውን ይምረጡ።

Step 2. ከዛም Security የሚለው ላይ Advanced የሚለውን ይንኩት።

Step 3. Administration ከሚለው አጠገብ Change  የምትለዋን ይጫኑ።

Step 4. ከዛም Advanced የሚለውን ይጫኑ።

Step 5. ከዛም Find Now የሚለውን ተጭነው ከሚመጡት ዝርዝር ውስጥ የኮምፒውተርዎን User Name ይምረጡ።

Step 6. መቀየሩን ካረጋገጡ በኋላ ሳጥኖቹ ላይ ራይት ( ) ያድርጉ።

Step 7. Apply የሚለውን መምረጥ

Step 8. Messages box ያመጣል ከዛም yes ይበሉ።

Step 9. Permission ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ OK ይበሉት።

Step 10. OK ብለው ሁሉንም window ፕሮግራሞችን ይዝጉት።

Step 11. መጨረሻ Delete ማድረግ የፈለጋችሁትን ፎልደር ማጥፋት ትችላላችሁ።


@sest_computer
✳️ ምርጥ የኮምፒዉተር ሶፍትዌር ማዉረጃ ሳይቶች❗️

1.
download.cnet.com

ይህ ሳይት የኮምፒዉተር ሶፍትዌሮችን ከማዉረጃ ሳይቶች ቀደምት ሲሆን ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተመሰረተ ነዉ፡፡ የዚህ ሳይት ባለቤት በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ገናና ስም ያለዉ CNet ነዉ፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም የሞባይል አፕሊኬሽኖችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከ 100,000 በላይ ፕሮዳከቶችን አካቷል፡፡ ሶፍትዌሮቹ በ ኤዲተሮች ተገምግመዉ እና ደረጃ ተሰጥቷቸዉ ተቀምጠዋል፡፡ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ግምገማዎችን መፃፍ እና ለ ሶፍትዌሮቹ ደረጃ መስጠት ይችላሉ፡፡

2.
filehippo.com

🔺ይህ ሳይት በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ነዉ፡፡ FileHippo Update Checker የሚል ፕሮግራም ያካተተ ሲሆን ይህም በኮምፒዉተራችን ላይ የጫንናቸዉን ሶፍትዌሮች scan በማድረግ አዲስ የተሻሻለ ምርት ካላቸዉ ይጠቁመናል፡፡ ይህም ኮምፒዉተርን ከሚያጠቁ ቫይረሶች ለመከላከል እጅጉን ይጠቅማል፡፡

3.
www.softpedia.com

🔺Softpedia የሮማኒያ ዌብሳይት ሲሆን ሶፍትዌሮችን ዳዉንሎድ ማድረግ እና ስለ ሶፍትዌሮቹ ማብራሪያ መረጃዎችን ማግኘት ያስችለናል፡፡ ከ ሶፍትዌሮቹም በተጨማሪ የ ቴክኖሎጂ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና መዝናኛ ዜናዎችን ያገኙበታል፡፡ ሶፍትዌሮችን በ ካታጎሪ ተቀምጠዉ ማግኘት ስለምንችል ስራችንን ያቀልልናል፡፡ ተጠቃሚዎችም በሚፈልጉት መስፈርት መፈለግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በተሻሻሉበት ቀን፣ በተጠቃሚ ብዛት፣ ሬቲንግ እና በመሳሰሉት፡፡

4.
www.tucows.com/downloads

🔺ስሙ ምህጻረ ቃል ሲሆን ይህም The Ultimate Collection Of Winsock Software ማለት ነዉ፡፡ ለ Windows, Linux እንዲሁም ለድሮዎቹ የ Windows ቨርዢኖች የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡

5.
www.freewarefiles.com

🔺ነፃ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በብዛት የምናገኝበት ሳይት ሲሆን ከ 15,800 በላይ ነፃ ሶፍትዌሮችን አካቷል፡፡ እነዚህን ሶፍትዌሮችንም በ ካታጎሪ ስለተቀመጡ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡

6.
m.majorgeeks.com

🔺ይህ ሳይት በፊት TweakFiles በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፋይሎች አሪፍ ኢንተርፌስ ያላቸዉ እና ለተጠቃሚዎች በቀላሉ የተገለፁ ናቸዉ፡፡ ፋይሎቹ ዌብሳይቱ ላይ ከመለጠፉ በፊት ጥራታቸዉ ይረጋገጣል ይህም ብዙዎችን ከሚያሰለቸዉ የዉሸት ሶፍትዎሮች እንዲሁም ቫይረሶች ይጠብቅዎታል፡፡ በተጨማሪም አሪፍ ኢንተርፌስ ኮሚዩኒቲ ያለዉ ሲሆን ስለ ኮምፒዉተር ያሉንን ጥያቄዎች ይመልሱልናል፡፡

7.
www.bytesin.com

🔺FileCluster አሁን ላይ ከተመሰረቱ አዳዲስ ዌብሳይቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ተጠቃሚዎቹም አዲስ እና የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የ WordPress Themes፣ ዜናዎችን እና ሶፍትዌር ካምፓኒዎችንም ማግኘት ይችላሉ፡፡

8.
www.soft32.com

🔺በ 2003 የተመሰረተ ሲሆን የ ሶፍትዌር ዳይሬክተሪዉን ቶሎ ቶሎ update በማድረግ ይታወቃል፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux እንዲሁም ለ ሞባይል የሚሆኑ ሶፍትዌሮች ሲኖሩት ለ iPhone ተጠቃሚዎች ብቻ ራሱን የቻለ ክፍል አዘጋጅቷል፡፡ ከ 85,000 በላይ ሶፍትዌሮች ሲይዝ ጥያቄዎቻችንን መጠየቅ የምንችልበት ፎረምም አለዉ፡፡


@sest_computer
All possible ways to start Microsoft Word on Windows 💻📝

1. From the Start Menu

Click Start
Type Word
Click Microsoft Word

2. Using Windows Search

Press Windows key
Type Word
Press Enter

3. Desktop Shortcut

Double-click the Microsoft Word icon on the desktop (if available)

4. Taskbar Icon

Click the Word icon on the taskbar (if it’s pinned)

5. Run Command

Press Windows + R
Type winword
Press Enter

6. File Explorer

Open File Explorer
Go to:C:\Program Files\Microsoft Office\
or C:\Program Files (x86)\Microsoft Office\ Open the Office folder
Double-click WINWORD.EXE

7. From a Word Document

Double-click any file with .doc or .docx
Microsoft Word opens automatically

8. Right-Click Menu (if enabled)

Right-click on the desktop
Choose New → Microsoft Word Document
Double-click the new file

9. Task Manager

Press Ctrl + Shift + Esc
Click File → Run new task
Type winword
Click OK

10. Command Prompt

Open Command Prompt
Type winword
Press Enter

11. PowerShell

Open PowerShell
Type winword
Press Enter

12. Start Menu → All Apps

Click Start
Open All apps
Scroll to Microsoft Office
Click Microsoft Word

@sest_computer
✳️ Server (ሰርቨር) ምንድን ነው?

🔺ሰርቨር ማለት በሁለት ይከፈላል እነሱም Hardware Server and Software Server ይባላሉ

🔺ሰርቨር ማለት ከስሙ እንደምንረዳው አገልጋይ ማለት ሲሆን ለ Client Devices አገልግሎት የሚሰጥ ማለት ነው። በዚህም የሶፍትዌር ሰርቨር የምንላቸው ዌብ ሰርቨር፣ ዶሜን ኔም ሰርቨር፣ ሜይል ሰርቨር በጥቂቱ መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም ስርቨር የሆኑ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጥቀስ ይቻላል ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ሰርቨር፣ ኡቡንቱ ጥቂቶች ናቸው።

🔺Hardware Server የምንለው የኮምፒውተር አይነት ሲሆን መረጃን ለመያዝ የሚያገለግልና በክሊያንት ኮምፒውተሮች መረጃውን እንዲደርስና ዋና መረጃው የሚቀመጥበት ማለት ነው። ሰርቨር ኮምፒውተር በጣም ከፍተኛ የሆነ መረጃን የመያዝ አቅም ያለው፣ መረጃን ፕሮሰስ የማድረግ አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመስራት አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ በዋጋ፣ በአካላዊ ከመደበኛው ኮምፒውተር የሚተልቅ እቃ ነው።

🔺በአንድ ሰርቨር ኮምፒውተር ለብዙ ክሊያንት ኮምፒውቲንግ እቃዎች(ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ ደስክቶፕ፣ ካሜራ፣ ፕሪንተር ወዘተ...) በአንድ ላይ ኔትወርክ በመጠቀም እርስ በራሳቸው እንዲተዋወቁ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ መረጃውን እንዲጋሩ ያደርጋል።

🔺Client Devices የምንለው ማንኛውም የኮምፒውቲንግ እቃዎች ከሰርቨሩ ጋር በመግናኘት መረጃዎችን አሳሾችን (Browsers) በመጠቀም መረጃን የምንጠቀምበት እቃዎችን ያካትታል። ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቱቭ ስንጠቀም መረጃውን ከሰርቨር ኮምፒውተር ላይ ኔትወርክ በመጠቀም የሚያመጣልንና ነው። በአጠቃላይ ሰርቨር ኮምፒውተር ማለት በጣም ብዙ መረጃዎችን አምቆ የያዘ ለተጠቃሚዎች በክሊያንት ኮምፒውተር አማካኝነት በመጠቀም መረጃን ከሰርቨር ኮምፒውተር በማምጣት ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ነው።

🔺ክሊያንትና ሰርቨር ኮምፒውተር የሚገናኙበት ፕሮቶኮል TCP/IP ይባላል። TCP/IP በዋናነት መልእክቶች ከሰርቨር ኮምፒውተር ወደ ክሊያንት ኮምፒውተር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ ሲሆን በLAN Local Area Network ወይም በWAN Wide Area Network ክሊያንት ኮምፒውተሮችን ከሰርቨር ኮምፒውተሮች ጋር በማስተሳሰር መረጃን መለዋወጥ ያስችላል።

@sest_computer
✳️ ለተማሪዎች የሚጠቅሙ 4 የአንድሮይድ አፕሊኬሽኖች❗️


🔺ተማሪዎች በትምህርት ወቅት ጫና ሳይፈጠርባቸው ትምህርታቸውን በአግባቡ በመከታተል በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ የሚረዱ አፕሊኬሽኖች ናቸው፡፡ ዓለም ዓቀፍ እውቅናም የተሰጣቸው አፕልኬሽኖች ናቸው።

1.School Planner Application

🔺ይህ አፕልኬሽን የቤት ስራዎችን፣ የግሩፕና የግል አሳይመንቶችን፣ ፕሮጀክቶችን፣ የእያንዳንዱን ክላስ ሰዓትና ቀን ማንኛውም ትምህርት ነክ አክቲቪቲዎቻችሁን ኦርጋናይዝ ያደርግላችኋል፡፡ ፕሮግራም ያወጣላችኋል።

🔺ይህ አፕሊኬሽን በየቀኑ በፕሮግራማችሁ መሰረት በየቀኑ መስራት ያለባችሁን ለምሳሌ ጥናት ወይም የቤት ስራ፣የግሩፕ አሳይመንት፣ የላብራቶሪ ሙከራ ባጠቃላይ ጠዋት ምን ማድረግ እነዳለባችሁ፡፡ ከሰዓት ምን መስራት እንዳለባችሁ ማታ ምን መፃፍ እንዳለባችሁ ያስታውሳችኋል።
-የምታስረክቡት አሳይመንት ወይም ፕሮጀክት ካለባችሁ የምታስረኩብበት ቀን "በዚህ ቀን ነው፡፡ ቀኑ እየደረሰ ነው…" እያለ ያስታውሳችኋል፡፡

2.Brilliant

🔺ይህ አፕልኬሽን ደሞ በተለይ በሂሳብ፣ በሳይንስና በኮምፒውተር ጥሩ ውጤት ለማምጣት በጣም የሚጠቅም አፕ ነው፡፡
ይህ አፕሊኬሽን እየሸመደዳችሁ እንዳታጠኑና በተለይ ረጃጅም ቃላት የሚበዙባቸው የትምህርት አይነቶችን ዘርዘር ያሉ ገለፃዎችን በመጠቀም ሳትሰለቹ  ትምህርቶቹን በቀላሉ እንድታጠኗቸውና እንዲገባችሁ ይረዳል ።

3.Grammarly

🔺ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ያሳድጋል፡፡
የተለያዩ በእንግሊዘኛ ስትፅፉ  የግራመር ስህተታችሁን ያርማል፣ ትክክለኛ ቃላት እንድትመርጡ ያደርጋል፡፡ ረጃጅም አረፍተ ነገሮችን ስትፅፉ የሲንታክስ ስህተታችሁን ያርማል፡፡ በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ቀስበቀስ ያሳድጋል፡፡

4.Mendeley

🔺Research በምትሰሩበት ግዜ ለጥናታችሁ  የሚሆኑ የተለያዩ ሪሶርሶች እንዴት እንደምታገኙ ይረዳችሃል፡፡ ለጥናታችሁ ወይም ለሪሰርች የሚጠቅሙ መፅሃፎችን፣ጥናታዊ ፅሁፎችን፣ ምክረ ሃሳቦችን እንዴት እንደምታዘጋጁ ያስተምራቸኋል፡፡

🔺ለሪሰርቻችሁ የተጠቀማችሁባቸውን የተለያዩ የጥናታዊ ፁሁፎች ፃሃፊዎችን፣የመፅሐፍት ደራስያን ፣ምሁራንን ስማቸውን በመጥቀስ ጥናታችሁ ላይ በማካተት እንዴት ወይም ክሬዲት እንደምትሰጧቸው ያስተምራችኋል፡፡

❗️አፕልኬሽኖቹን ፕለይስቶር ላይ Search አድርጋችሁ በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።


@sest_computer
💻የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?

➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው  ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ይዘዋል፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን። ይሁን እንጂ አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም function (FN) የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት ሊኖርብን ይችላል::

           የF1 ጥቅሞች
► Win + F1 = Display help menu
►Ctrl +F1 Show/hide menu options in Excell and Word
►F1 in chrome  Open Chrome support

       የF2 ጥቅሞች
► Alt + Ctrl + F2 = opens Document Library in Microsoft Office
► Allows you to edit the selected folder or file name in Windows Explorer
►Rename a file in Windows Explorer
►Edit the active cell in Microsoft Excel
►Ctrl + F2 Shows a print preview in Word
►Alt + Ctrl + F2 Open the document library in Microsoft Office.

       የF3 ጥቅሞች
► Opens search feature in Windows Explorer
► Shift + F3 = change from lowercase to uppercase in Word
► Opens find feature in Firefox and Chrome

       የF4 ጥቅሞች
► Alt + F4 closes window
► Places the cursor in the address bar in Explorer

       የF5 ጥቅሞች
► Starts slide show in Power Point
► Refreshes Internet browser pages
► Opens Find and Replace in Office
► Refresh the browser, also clearing the cache memory.

       የF6 ጥቅሞች
► Goes to the next page in a split screen in Microsoft Word
► Ctrl + F6 = easily switch between Word documents.
►Places the cursor in the browser’s address bar

       የF7 ጥቅሞች
► Alt + F7 does a spelling and grammar check in Microsoft Word
► Shift + F7 open Thesaurus in Microsoft Word

       የF8 ጥቅሞች
► In Excel, enables extend mode for arrow keys
► Select text in Word
► Enables safe mode in Windows

       የF9 ጥቅሞች
► Ctrl + F9 inserts empty fields into Word
► Updates fields in Word
► Send or receive e-mails in Outlook
► Recalculate formulas in Excel

       የF10 ጥቅሞች
► Opens menu bar
► Ctrl + F10 maximizes window in Word
► Shift + F10 does the same thing as a right click

       የF11 ጥቅሞች
► Exits and enter full screen mode in browsers
► Shift + F11 adds a new spreadsheet in Excel

       የF12 ጥቅሞች
► Opens Save As in Word
► Shift + F12 saves Word document
► Ctrl + F12 opens Word document

በዚህ አጋጣሚ ማስተዋል ያለብን ከላይ የዘረዘርናቸው አጠቃላይ ጥቅማቸውን እንጂ እንደምንከፍተው የሶፍትዌር አይነት ጥቅማቸውም ሊለያይ ይችላል። ለምሳሌ ጌም ስንጫወት ወይም pdf document ስንከፍት

@sest_computer
✳️ ውድ ተማሪዎቻችን የሁላችንንም ስልክ የሚያንቀሳቅሰው Android ምን እንደሆነ እንንገራችሁ

🔺Android ምንድን ነው?

◽️ Android Open Source የሆነ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ሲሆን በብዛት ለስማርት ስልኮች ያገለግላል።

◽️ ጉግል በ 2003 አንድሮድን ያገኘ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ለተንቀሳቃሽ ስልኮች በጣም ታዋቂው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ሊሆን ችሏል።

🔺Android ስራው ምንድን ነው?

◽️ አንድሮድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ስለሆነ ዓላማው ተጠቃሚውን እና መሣሪያውን ማገናኘት ወይም ማግባባት ነው።

🔺ለምሳሌ ፣ አንድ ተጠቃሚ Text መላክ በሚፈልግበት ጊዜ አንድሮይድ ለተጠቃሚው የመፃፊያ Keyboard ይሰጣል። ፅፎ ሲጨርስ ደግሞ ተጠቃሚው መላኪያውን በሚነካበት ጊዜ Android መልእክቱ እንዲልክ ስልኩን ይመራዋል።

◽️ Google በየአመቱ ለAndroid System Update ይለቃል። ምንም እንኳን Google ለAndroid እድገት ትልቅ ሚና ቢጫወትም ጉግል የAndroid ኦፐሬቲንግ ሲስተምን ለሞባይል አምራቾች በነፃ ይሰጣል።

◽️ Electric ፣ Samsung ፣ LG ፣ Huawei ፣ Lenevo  እና Sony Androidን በሚያመርቷቸው ስልኮች ላይ ከሚጭኑ አምራቾች ጥቂቶቹ ናቸው።

🔺Android vs. iOS?

◽️ የAndroid ዋና ተፎካካሪ የሆነው ISO በአይፎን ስልኮች ላይ የሚሰራ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ነው። በAndroid እና iOS የሚያመሳስሉም የሚያለያዩም ነገሮች አሉ። ወደ እሱ ሲመጣ ሁለቱም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ከ Wi-Fi ጋር መገናኘት ፣ አፖችን ማሰራት ፣ Text መላክ እና ፎቶ ማንሳት ያሉ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። ሆኖም ግን በመልክ እና በአሰራር ረገድ ዋና ዋና ልዩነቶች አሉ።

🔺የAndroid ጥቅሞች

◽️ የAndroid ዋነኛው ጠቀሜታ ተጠቃሚው ብዙ አማራጮች ያሉት መሆኑ ነው። Androidን እንደ ኦፐሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ መሣሪያዎች አሉ። በሌላ በኩል IOSን የሚፈልጉ ከሆነ አይፎን መግዛት ይኖርቦታል።

◽️Android በ2000 ዎቹ መጀመሪያ ከነበሩት ቀናት በጣም ረዥም መንገድ መጥቷል። ራሱንም በማዘመን ተደራሽ ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀላል መሆንም ችሏል።
ለsocial media ፖስት ቪዲዮ edit ስታደርጉ የሚጠቅሟችሁ icons, illustrations, 3D ሞዴሎችና ፎቶዎችን Download ለማድረግ የሚጠቅሟችሁ ድረገፆች

https://iconmonstr.com/
https://icons8.com/
https://www.vecteezy.com/
https://www.flaticon.com/
https://www.freepik.com/
https://undraw.co/
https://www.pexels.com/
https://pixabay.com/
https://gratisography.com/
https://unsplash.com/

@sest_computer
✳️ ኮምፒውተራችሁን ፍጥነት ለመጨመር እነዚህን ዘዴዎች ይጠቀሙ❗️

🔺Power option

◽️ Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ።

🔺Defragmentation and optimize

◽️ Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ።

🔺Delete unnecessary temporary file

◽️ Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን %temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

🔺Clean up Memory

◽️ This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ የሚመጣውን የ warning box OK ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት።

🔺Visual effects

◽️ Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ። ቀጥሎ ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ።

@sest_computer
🔥 Ai Tools

በቀላሉ ቃላቶችን በመጠቀም ብቻ የተለያዩ ምስሎችን የምንፈጥርባቸው ጠቃሚ ዌብሳይቶች
❗️

🔺Microsoft Copilot:
     🔗 https://copilot.microsoft.com/

🔺 MonsterAPI Playground:
     🔗 https://monsterapi.ai/playground/sdxl-base

🔺 Imagine Art Generator:
      🔗 https://www.imagine.art/

🔺Freepik AI Image Editor:
     🔗 https://www.freepik.com/ai/image-editor

🔺 Canva AI Image Generator:
    🔗 https://www.canva.com/ai-image-generator/

🔺Lensgo AI:
   🔗https://lensgo.ai/

🤩 Unleash your creativity with these powerful AI platforms!

ሌሎች ጠቃሚና አስተማሪ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ለማግኘት ===>ሴስት ኮምፒውተር
Sest Computer School pinned «💻የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል? ➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው  ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ይዘዋል፡፡ እና ምንም ማስተካከል…»
የትኛውን መማር ይፈልጋሉ ?
💸 1. Content Creation & Social Media

TikTok / YouTube Shorts – Create videos about tech, motivation, or tutorials. Monetize through ads, affiliate links, or brand deals.

YouTube Channel – Make educational or entertainment videos, then earn from ads.

Instagram Reels / Threads – Grow a page and sell shoutouts or promote your own products.

Podcasting – Use your phone mic to start; grow your audience and get sponsors.

Live streaming (TikTok / Twitch) – Earn from gifts, subscriptions, or sponsors.



---

🛍️ 2. Online Selling & Services

Freelancing – Offer skills like design, writing, translation, or teaching on Fiverr or Upwork.

Sell digital products – E-books, courses, designs, or templates (once made, they keep earning).

Print-on-demand – Sell t-shirts, mugs, or phone cases with your designs.

Dropshipping – Sell products without keeping stock.

Offer tutoring / coaching online – You can teach computers or English directly via Zoom or Telegram.



---

🔗 3. Affiliate & Referral Marketing

Affiliate links – Share product links (Amazon, ClickBank, Digistore24) and earn a commission when people buy.

App referrals – Many apps (like Binance, Payoneer, or Fiverr) pay you to refer users.

Influencer marketing – Promote other brands to your audience and get paid.



---

📱 4. Using Mobile Apps

Survey apps / GPT sites – Apps like Swagbucks, TimeBucks, or ySense pay small amounts for surveys and tasks.

Microtasking apps – Like Remotasks or UHRS where you label images or transcribe short clips.

Sell your photos – Apps like Foap let you sell photos taken on your phone.



---

🧠 5. Skill-Based Opportunities

Learn coding / web design – Create websites or apps for clients.

Graphic design / Canva work – Make posters, thumbnails, and logos for others.

Video editing – Offer editing services for TikTokers or YouTubers.

Social media management – Help others grow and manage their pages.



---

💰 6. Local + Online Combo

Promote local businesses online – Help shops or cafes in your area with social media and get paid monthly.

Buy & sell phones / gadgets online – Use Telegram, Facebook Marketplace, or WhatsApp groups.

Create Telegram channels – Grow it, and later monetize through ads or products.

የትኛውንም አይነት ኮርስ መማር ሲፈልጉ sest Computer ጋር ይምጡ.....

@sest_computer
1000+ Subscriber ያለው

የቴሌግራም ቻናል ካላችሁ ማስታወቂያ እየሰራችሁ ገንዘብ ልትሰሩበት የምትችሉበት አንድ platform አለ።

Telega.io ይባላል።
ማስታወቂያ አስነጋሪዎችን፡ የቻናልና የቦት ባለቤቶችን የሚያገናኝ platform ነው።

አካውንት ከፍታችሁ ያላችሁን ቻናል ወይም ቦት ካስመዘገባችሁ በኋላ የሚመጣላችሁን ማስታወቂያ ቻናል ወይም ቦታችሁ ላይ በመለጠፍ ገንዘብ ማግኘት ትችላላችሁ። ክፍያውን በUSDT (TRC 20 network) መቀበል ትችላላችሁ።

የቴሌግራም ቦት አለው። @telega_adv_bot

እገዛ ከፈለጋችሁ @sest_computer
🔥1
ፓስዎርድ ለምትረሱ ሁሉ...

Google Password Manager

በGoogle manager ተጠቀሙ።

Google Password manager በChrome, በAndroidና በGoogle Drive ፕላትፎርሞች ላይ integrate የተደረገ ሲሆን ማንኛውም ተጠቃሚ save ያደረገውን password በቀላሉ store, access, updateና delete ማድረግ ይችላል።

Password generation: Google Password Manager suggests strong, unique passwords when saving them to a Google Account.

Password storage: Users can save passwords in their Google Account or on their device.

Password auto-fill: Users can automatically fill in passwords on sites and apps.

Password protection: Google Password Manager protects saved passwords with built-in security.

Password notifications: Users can receive notifications if their passwords are compromised or part of a data breach.

Password checkup: Google Password Manager can perform a Password Checkup to flag weak, reused, or compromised passwords

Password sharing: Users can share logins with friends and family.

Two-factor authentication: Users can enable two-factor authentication

Master password: Users can create a master password.

በchrome browser በቀላሉ access ማድረግ የምትችሉ ሲሆን ሌሎች ብርዘሮች ላይ በPasskey sign in ማድረግ ይጠበቅባችኋል።

@sest_computer
Content creator መሆን እንዴት ቀላል እንደሆነ ላሳያችሁ።

ከዚህ በታች የዘረዘርሁላችሁ ድረገፆች ነጻ የAi ቱሎችን የያዙ ናቸው። እያንዳንዱን website ብትከፍቱት በውስጡ ለብዙ አይነት ስራ የሚያገለግሉ በጣም ብዙ ቱሎች ተዘርዝረው ታገኛላችሁ።

ከዛ ውስጥ እየሞከራችሁ የሰሩላችሁንና ለሰው ይጠቅማሉ ብላችሁ ያሰባችኋቸውን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በቪዲዮ ወይም በtext አዘጋጅታችሁ post አድርጉ። ይህን ተግባር ለተወሰነ ጊዜ ከደጋገማችሁት content creator ሆናችሁ ማለት አይደል? Simple!!🤷‍♂️

Best websites to get list of AI tools
1. https://www.futurepedia.io/
2. https://aitools.fyi/
3. https://www.futuretools.io/
4. https://topai.tools/
5. https://www.superaitools.io/
6. https://huggingface.co/spaces
7. https://aitoolsdirectory.com/
8. https://theresanaiforthat.com/

ይህን ለማድረግ ማሰብ ያለባችሁ ነገሮች
የገባችሁን ብቻ ስሩ።
በጣም ቀለል አድርጉት አታወሳስቡት።
እንደቀላል አትዩት ምናልባት በዚች ውሳኔ ህይወታችሁ ሊቀየር ይችላል።
ለመሳሳት አትፍሩ

@sest_computer
📨ልታውቁቸው የሚገቡ ጠቃሚ የቴሌግራም ቦቶች📥

1. @freelanceethiobot : የተለያዩ ፍሪላንስ ስራዎችን የሚያገናኝ  ሃገርኛ ቦት 
2. @BOA_ATM_bot : የአቢሲንያ ባንክ ATM የት አካባቢ እንደምታገኙ የሚያመለክት ሃገርኛ ቦት
3. @GameBot : የተለያዩ ጌሞችን single player ወይም multi player ለመጫወት
4. @getmediabot : ከዩትዩብ ትዊተር ኢንስታግራምና ፌስቡክ ሙዚቃ ቪደዮና ላይሪክስ ዳውንሎድ ለማድረግ
5. @GmailBot ፡ email ሲላክላችሁ ቼክ የማድረግ ችግር ካለባችሁ በቴሌግራም በዚህ ቦት አማካኝነት ማየት ትችላላችሁ ።
6. @Stickerdownloadbot : ማንኛውንም sticker ወደ ፎቶ ወይም gif ቀይሮ ዳውንሎድ ለማድረግ
7. @RandTalkNew_bot : ከተለያዩ ሰዎች ጋ ማንነታችሁ ሳይታዎቅ chat የምታደርጉበት (ተመሳሳይ ሌሎች ቦቶችን በቅርቡ post አድርግልችኋለሁ)
8. @DrWebBot : የተለያዩ ፋይሎችና ሊንኮች virus መያዛቸውን አለማያዛቸውን ቼክ የምናደርግበት 
9. @AndyRobot : ከዚህ ቦት ጋ chat እያደረጋችሁ እንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታችሁን ማዳበር ትችላላችሁ።
10. @gamee :  የተለያዩ ጌሞችን single player ወይም multi player ለመጫወት


Join this channe: @sest_computer