Sest Computer School
78 subscribers
16 photos
2 files
41 links
💻 Welcome to the world of computers
🖥️ From basics to advanced
⚙️ Tips, tricks, tutorials & real skills
@sestcom_bot ለፈጣን ምላሽና ማብራሪያ
Download Telegram
✳️ MotherBoard:

◽️Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡

◽️ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ (Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡


@sest_computer
ቴሌግራም ላይ ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ maximum security እና privacy level

1. Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ።
ይህን ለማስተካካል
Settings - privacy and security - passcode

2. 2-step verification ተጠቀሙ።
2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት።
ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ።

3. ከ2 በላይ device ላይ አትጠቀሙ። Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል።
ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate secc ቀንሷቸው።

4. በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ።

5. ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ።

6. የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ።

7. ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው ካያቸው በኋላ የሚጠፉ) ሚሴጆችን ላኩ።

8. የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት።

9. በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ።
Phone number - Nobody
Last seen & online - My contacts
Profile photos - My contacts
Forwarded message - Nobody
Calls - My contacts
Group & channels - My contacts

@sest_computer
✅ በአለማችን ላይ ያሉ ምርጥ የ Adobe ሶፍትዌሮች ጥቅማቸውን እንመልከት!

- በጣም ተወዳጅነትን ያተረፋና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን የሚሰጡ ሰባት የ Adobe SoftWare:

🔺Adobe Light Room

- ይህ የ Adobe ሶፍትዌር አንደኛው ክፍል ሲሆን የሚጠቅመን የተለያዩ ፎቶዎችን ብርሀን Brightness ለማስተካከል ነው። አብዛኛው ፎቶ ግራፈር (CameraMan) የሚጠቀምበት ሶፍትዌር ነው።

🔺Adobe After Effect

- ይህ ደግሞ የተለያዩ Animation Videos ለመስራት የምንጠቀምበት ሶፍትዌር ነው።

🔺Adobe Flash Professional

- ይህ የተለያዩ 2D ጌሞች ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመስራት የሚጠቅመን የ Adobe ሌላኛው ክፍል ነው።

🔺Adobe Spark

- የተለያዩ Graphics Design ለመስራት ፅሁፎችን ወደ ተለያዩ ፎቶዎች ለመቀየር የምንጠቀምበት ሶፍትዌር ነው።

🔺Adobe Media Encoder

- በ PR እና AE የሠራናቸው ስራዎች ወደ ቪዲዮ ስንቀይር የተለያዩ ዲቫይሶች ላይ እንዲሠራልን Encode የምናደርግበት ሶፍትዌር ነው።

🔺Adobe Audition

- ይህ Record Mix Edit ለማድረግ የሚጠቅመን የ Adobe አንደኛው ክፍል ነው።

🔺Adobe Premiere Pro

- የአለማችን ቁጥር አንድ የቪዲዮ መስሪያ  ሶፍትዌር ነው። ቪዲዮዎች፣ፎቶዎችን፣ አኒሜሽኖችን ወ.ዘ.ተ የምንፈጥርበት ፕሮፌሽናል የቪዲዮ ማቀነባበርያ ሶፍትዌር ነው።


ከኛጋር ይማሯቸው።
GRAPHICS DESIGN IN SEST COMPUTER SCHOOL.

@sest_computer
10 በጣም ጠቃሚ ድረገፆች

1. themarkup.org/series/blacklight = Real Time website privacy inspector. ማንኛውንም ድረገፅ ከመክፈታችሁ በፊት ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ይጠቅማችኋል።
2. codingame.com = ጌም እየተጫወታችሁ ኮዲንግ የምትለማመዱበት
3. Remotists.com = በአለም አቀፍ ደረጃ remote ስራዎችን search የምታደርጉበት
4. hacksplaining.com = Hacking ቀላል በሆነ መንገድ የምትማሩበት
5 Typelit.io = የተለያዩ ፅሁፎችን Type እያደረጋችሁ የምትለማመዱበት
6. coveryourtracks.eff.org = የምትጥቀሙት browser ምን አይነት መረጃ አሳልፎ እንደሚሰጥና track ያደርግ እንደሆነ check የምታደርጉበት
7. www.startrek.com/ የቴክ ዜናዎች ዶክመንተሪዎችና ታሪኮች በፅሁፍ የምታገኙበት
8. musclewiki.com = የሰውነት እንቅስቃሴ በምናደርግበት ጊዜ ምን አይነት ስፖርት መስራት እንዳለብንና የትኛውን የሰውነታችን ክፍል ለማዳበር እንደሚጠቅመን ስዕላዊ በሆነ መንገድ የሚያሳየን
9. codepen.io = የተለያዩ ኮዲንግ ፕሮጀችቶችን የምታገኙበት እንዲሁም ድረገፁ ላይ ኮድ ፅፋችሁ run  ታደርጉበታላችሁ።
10. litsolutions.org = የተለያዩ መፅህፍትን ጥያቄዎች መልስ የምታገኙበት

ጥንቃቄ ለራስ ነው።
@sest_computer
​​✳️ ውድ የቻናሉ ተከታታዮች ዛሬ ኮምፒዉተር በራሱ የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበትን ምክንያቶች በጥቂቱ እናያለን።

🔺የሀርድዌር መቃረን፡ ለWindows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware  መቃረን ነው፡፡  እያንዳንዱ Hardware  ክፍሎች ለመግባባት IRQ (interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው።

🔺እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆነ IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊፈጥር ይችላል፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡

🔺የተበላሸ ራም፡ የሚያሳየው  መልእክት (Fatal Exception Error) á‹¨áˆšáˆ ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል። በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡

🔺መጋል፡ በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ ያደርጋል።


#Tech_Tips
#Join

@sest_computer
​​✳️ ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች!

◽️ ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶወች (ዋልፔፐር) አይጠቀሙ፡፡

◽️ ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡

◽️ አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡

◽️ የማይጠቀሙበት አፕሊኬሽን ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት።

◽️ ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡

◽️ ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ።

◽️ Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
◽️ ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
◽️ ብዙ አፕሊኬሽን ባንዴ አይክፈቱ::

#Tech_Tips
#Join
@sest_computer
​​✳️ Cloud Storage ምንድነው❓

🔺 ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡

🔺በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዩ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት Microsoft, Google, and Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋሉ፡፡

🔺መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጅ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን ማግኘት እንችላለን።

🔺ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡ 

🔺በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን እና ብዛት ነው፡፡

#Share
#Tech_Tips

@sest_computer
✳️ የስልካችንን DATA ስናበራ የሚመጡት G, E, 3G, H/H+, 4G, 5G እነዚህ ምልክቶች ምንድናቸው?

🔺G : Feature ስልኮች (Keypad) ላይ ሳይቀር ስልኩ ከኢንተርኔት ጋር ሲገናኝ ይህንን ምልክት እናያለን። ትርጉሙም GPRS (Global Packet Radio Service) ማለት ነው።

🔺E : Edge -በመባል የሚታወቀው ይህ Network የስልካችን ኔትወርክ Enhanced GPRS የሚባለውን መጠቀም ሲጀምር ይህንን እናያለን። የታወቀው ፍጥነት ደግሞ 0.4mb/s ነው።

🔺3G : ብዙዎቻችን እናቀዋለን የ3rd Generation Network ሲሆን በGSM Network ላይ የሚሰራ Network ነው። 3G በአማካኝ እስከ 2mb/s ፍጥነት ይኖረዋል።

🔺H/H+ : HSDPA (High speed Downlink packet access) ማለት ሲሆን ብዙ ስማርት ስልኮች ላይ H ከሆነ እስከ 7 mb/s ድረስ ይሄዳል። H+ ሲሆን ደግሞ እስከ 21mb/s ድረስ ይሄዳል።

🔺4G/LTE : ይህ 4ኛው ትውልድ ኔትወርክ 5G ከመምጣቱ በፊት ምርጥ Network ነበር። ፍጥነቱም እስከ 150mb/s ነው። ብዙ ጊዜ ከwi-fi በበለጠ ፍጥነት ይኖረዋል።

🔺5G : የ5ኛው Generation ሲሆን ከ4G በ1000 እጥፍ የDownload ፍጥነት ሊኖረው ይችላል።


#Tech_Tips
#Join #share

@sest_computer
✳️ ብንጠቀምባቸው ስራን የሚያቀሉልን ጠቃሚ ዌብሳቶች!

1. የተለያዩ ነገሮችን ለማወዳደር
  versus.com

2. ለተለያየ አገልግሎት ጊዚያዊ ኢሜል ካስፈለገዎ :
10minutemail.com  ወይም yopmail.com

3. ማንኛውንም ትልልቅ ሶፍትዌሮች ከነ ሲሪያል ኪ ዳውንሎድ ለማድረግ
Getintopc.com

4. የዋይፋይ (ኢንተርኔት) ፍጥነት ለማወቅ Speedtest.net   ወይም fast.com ን ይጠቀሙ

5. በቀን ና ሰአት ላይ የተለያዩ ቀመሮችን መስራት ከፈለጉ :
timeanddate.com ን ቢጠቀሙ ጊዜ ይቆጥባሉ።

6. ጠንከር ያለ ና በቀላሉ የማይሰበር የይለፍ ቃል
/password ከፈለጉ
Passwordsgenerator.net ይጠቀሙ

7. ከጎበኙት ድረገፅ የወደዱትን ፔጅ ቢፈልጉ በፕሪንት ወይም pdf አልያም በኢሜይል ማስቀረት ካሰቡ :
Printfriendly.com ይጠቀሙ።

8. የተለያዮ የውጪ ቋንቋዎችን ለመማር
Duolingo.com ን ይጎብኙ

9. አልከፍት ያሎትን ድረገፅ አልሰራ ያለው ለእርሶ ብቻ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ
downforeveryoneorjustme.com  ወይም isitdownrightnow.com ዌብሳይቶቾ ጠቃሚ ናቸው።

10. ኮምፒውተራችን ላይ መጫን ሳያስፈልገን የMicrosoft office ን ምርቶች ኦንላይን ለመጠቀም
office.com ላይ በመግባትና የmicrosoft ን ኢሜል በማስገባት መጠቀም ይችላሉ።

@sest_computer
በጣም ጠቃሚ ትምህርታዊ ነፃ AI Tools

▪️ Humata AI Document summarizer and review
▪️ Textero AI Essay Writer
▪️ WolframAlpha Help on mathematics and science
▪️ MathGPTpro Helps on Mathimatics
▪️ Quizgecko ዶክመንት ሰጥታችሁት ጥያቄ የሚያወጣ
▪️ Prepsup በተለያዩ ዘርፎች ለፈተና የሚያዘጋጃችሁ
▪️ LearnGPT ማንኛውንም የትምህርት አይነት በቀላሉ የሚያስረዳ
▪️ Codeamigo Code assistant
▪️ gptionary Conversation with an AI on a specific topic
▪️ Gradgpt ኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ለመቀላቀል Statement of Purpose, Letter of recommendation, SOP Review
ለመፃፍ ያግዛል።

Bonus
BrandScript Generator content and story generator ለማድረግ

መሰል ትምህርቶችን ይማሩ!!!!!
@sest_computer
✳️ የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች ድረገፆች❗️

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ www.aau.edu.et
መቀሌ ዩኒቨርስቲ  www.mu.edu.et
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ www.astu.edu.et
አክሱም ዩኒቨርስቲ www.axu.edu.et
አምቦ ዩኒቨርስቲ www.ambou.edu.et
አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ www.amu.edu.et
ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ www.bdu.edu.et
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ www.dbu.edu.et
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ www.dmu.edu.et
ዲላ ዩኒቨርሰቲ  www.du.edu.et
ጎንደር ዩኒቨርስቲ www.gu.edu.et
ጂማ ዩኒቨርስቲ www.ju.edu.et
ሃረማያ ዩኒቨርስቲ www.haramaya.edu.et
ሃዋሳ ዩኒቨርስቲ www.hu.edu.et
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ www.wsu.edu.et
ወለጋ ዩኒቨርስቲ www.wu.edu.et
ድሬ ዳዋ ዩኒቨርስቲ  www.ddu.edu.et
ወሎ ዩኒቨርስቲ www.wou.edu.et
ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ www.jgu.edu.et
መዲ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ www.mwu.edu.et
ሚዛን ቲፒ ዩኒቨርሲቲ www.mtu.edu.et
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ www.su.edu.et
ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ www.kuc.edu.et
አአ ሾል.& ቴክ ዩኒቨርሲቲ www.aastu.edu.et
አዲግራት ዩኒቨርሲቲ  www.adu.edu.et
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  www.asu.edu.et
ቡሌ ሁራ ዩኒቨርስቲ www.bhu.edu.et
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ www.dbtu.edu.et
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ www.wcu.edu.et
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ  www.wku.edu.et
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ  www.wdu.edu.et
አርሲ ዩኒቨርሲቲ www.aru.edu.et
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ www.gmu.edu.et
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ www.obu.edu.et


#Join
@sest_computer
✳️ እስከ 100 GB + ነፃ ኦንላይን ማንኛውም File ማስቀመጫ ምርጥ ሳይቶች❗️

🔺Sign up at Ozibox.com to get 100GB of free storage.

🔺Sign up at SurDoc.com to get 100GB of free storage.

🔺Sign up at Shared.com to get 100GB of free storage.

🔺Sign up at Adrive.com to get 50GB of free storage

🔺Sign up at Mega.co.nz to get 50GB of free storage.

🔺Sign up at Hubic.com to get 25GB of free storage.

🔺Sign up at Firedrive.com to get 20GB of free storage.

🔺Sign up at Onedrive.live.com to get 15GB of free storage.

🔺Sign up at Copy.com to get 15GB of free storage.

🔺Sign up at Mediafire.com to get 10GB of free storage. (40GB more available with other activities)

🔺Sign up at Pcloud.com to get 10GB of free storage (10GB more available with other activities)

🔺Sign up at Box.com to get 10GB of free storage.

Tera box is my best but the ads.....

@sest_computer
✳️ ብዙ ጊዜ ኮምፒውተራችን ላይ Delete አልሆን ያሉ ፎልደሮችን እንዴት እንደምናጠፋ እናያለን❗️

Step 1. Folder/File ጋር Right Click አድርገን Properties የሚለውን ይምረጡ።

Step 2. ከዛም Security የሚለው ላይ Advanced የሚለውን ይንኩት።

Step 3. Administration ከሚለው አጠገብ Change  የምትለዋን ይጫኑ።

Step 4. ከዛም Advanced የሚለውን ይጫኑ።

Step 5. ከዛም Find Now የሚለውን ተጭነው ከሚመጡት ዝርዝር ውስጥ የኮምፒውተርዎን User Name ይምረጡ።

Step 6. መቀየሩን ካረጋገጡ በኋላ ሳጥኖቹ ላይ ራይት ( ✅) ያድርጉ።

Step 7. Apply የሚለውን መምረጥ

Step 8. Messages box ያመጣል ከዛም yes ይበሉ።

Step 9. Permission ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ OK ይበሉት።

Step 10. OK ብለው ሁሉንም window ፕሮግራሞችን ይዝጉት።

Step 11. መጨረሻ Delete ማድረግ የፈለጋችሁትን ፎልደር ማጥፋት ትችላላችሁ።


@sest_computer
✳️ ምርጥ የኮምፒዉተር ሶፍትዌር ማዉረጃ ሳይቶች❗️

1.
download.cnet.com

ይህ ሳይት የኮምፒዉተር ሶፍትዌሮችን ከማዉረጃ ሳይቶች ቀደምት ሲሆን ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተመሰረተ ነዉ፡፡ የዚህ ሳይት ባለቤት በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ገናና ስም ያለዉ CNet ነዉ፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም የሞባይል አፕሊኬሽኖችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከ 100,000 በላይ ፕሮዳከቶችን አካቷል፡፡ ሶፍትዌሮቹ በ ኤዲተሮች ተገምግመዉ እና ደረጃ ተሰጥቷቸዉ ተቀምጠዋል፡፡ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ግምገማዎችን መፃፍ እና ለ ሶፍትዌሮቹ ደረጃ መስጠት ይችላሉ፡፡

2.
filehippo.com

🔺ይህ ሳይት በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ነዉ፡፡ FileHippo Update Checker የሚል ፕሮግራም ያካተተ ሲሆን ይህም በኮምፒዉተራችን ላይ የጫንናቸዉን ሶፍትዌሮች scan በማድረግ አዲስ የተሻሻለ ምርት ካላቸዉ ይጠቁመናል፡፡ ይህም ኮምፒዉተርን ከሚያጠቁ ቫይረሶች ለመከላከል እጅጉን ይጠቅማል፡፡

3.
www.softpedia.com

🔺Softpedia የሮማኒያ ዌብሳይት ሲሆን ሶፍትዌሮችን ዳዉንሎድ ማድረግ እና ስለ ሶፍትዌሮቹ ማብራሪያ መረጃዎችን ማግኘት ያስችለናል፡፡ ከ ሶፍትዌሮቹም በተጨማሪ የ ቴክኖሎጂ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና መዝናኛ ዜናዎችን ያገኙበታል፡፡ ሶፍትዌሮችን በ ካታጎሪ ተቀምጠዉ ማግኘት ስለምንችል ስራችንን ያቀልልናል፡፡ ተጠቃሚዎችም በሚፈልጉት መስፈርት መፈለግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በተሻሻሉበት ቀን፣ በተጠቃሚ ብዛት፣ ሬቲንግ እና በመሳሰሉት፡፡

4.
www.tucows.com/downloads

🔺ስሙ ምህጻረ ቃል ሲሆን ይህም The Ultimate Collection Of Winsock Software ማለት ነዉ፡፡ ለ Windows, Linux እንዲሁም ለድሮዎቹ የ Windows ቨርዢኖች የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡

5.
www.freewarefiles.com

🔺ነፃ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በብዛት የምናገኝበት ሳይት ሲሆን ከ 15,800 በላይ ነፃ ሶፍትዌሮችን አካቷል፡፡ እነዚህን ሶፍትዌሮችንም በ ካታጎሪ ስለተቀመጡ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡

6.
m.majorgeeks.com

🔺ይህ ሳይት በፊት TweakFiles በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፋይሎች አሪፍ ኢንተርፌስ ያላቸዉ እና ለተጠቃሚዎች በቀላሉ የተገለፁ ናቸዉ፡፡ ፋይሎቹ ዌብሳይቱ ላይ ከመለጠፉ በፊት ጥራታቸዉ ይረጋገጣል ይህም ብዙዎችን ከሚያሰለቸዉ የዉሸት ሶፍትዎሮች እንዲሁም ቫይረሶች ይጠብቅዎታል፡፡ በተጨማሪም አሪፍ ኢንተርፌስ ኮሚዩኒቲ ያለዉ ሲሆን ስለ ኮምፒዉተር ያሉንን ጥያቄዎች ይመልሱልናል፡፡

7.
www.bytesin.com

🔺FileCluster አሁን ላይ ከተመሰረቱ አዳዲስ ዌብሳይቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ተጠቃሚዎቹም አዲስ እና የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የ WordPress Themes፣ ዜናዎችን እና ሶፍትዌር ካምፓኒዎችንም ማግኘት ይችላሉ፡፡

8.
www.soft32.com

🔺በ 2003 የተመሰረተ ሲሆን የ ሶፍትዌር ዳይሬክተሪዉን ቶሎ ቶሎ update በማድረግ ይታወቃል፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux እንዲሁም ለ ሞባይል የሚሆኑ ሶፍትዌሮች ሲኖሩት ለ iPhone ተጠቃሚዎች ብቻ ራሱን የቻለ ክፍል አዘጋጅቷል፡፡ ከ 85,000 በላይ ሶፍትዌሮች ሲይዝ ጥያቄዎቻችንን መጠየቅ የምንችልበት ፎረምም አለዉ፡፡


@sest_computer
All possible ways to start Microsoft Word on Windows 💻📝

1. From the Start Menu

Click Start
Type Word
Click Microsoft Word

2. Using Windows Search

Press Windows key
Type Word
Press Enter

3. Desktop Shortcut

Double-click the Microsoft Word icon on the desktop (if available)

4. Taskbar Icon

Click the Word icon on the taskbar (if it’s pinned)

5. Run Command

Press Windows + R
Type winword
Press Enter

6. File Explorer

Open File Explorer
Go to:C:\Program Files\Microsoft Office\
or C:\Program Files (x86)\Microsoft Office\ Open the Office folder
Double-click WINWORD.EXE

7. From a Word Document

Double-click any file with .doc or .docx
Microsoft Word opens automatically

8. Right-Click Menu (if enabled)

Right-click on the desktop
Choose New → Microsoft Word Document
Double-click the new file

9. Task Manager

Press Ctrl + Shift + Esc
Click File → Run new task
Type winword
Click OK

10. Command Prompt

Open Command Prompt
Type winword
Press Enter

11. PowerShell

Open PowerShell
Type winword
Press Enter

12. Start Menu → All Apps

Click Start
Open All apps
Scroll to Microsoft Office
Click Microsoft Word

@sest_computer
✳️ Server (ሰርቨር) ምንድን ነው?

🔺ሰርቨር ማለት በሁለት ይከፈላል እነሱም Hardware Server and Software Server ይባላሉ።

🔺ሰርቨር ማለት ከስሙ እንደምንረዳው አገልጋይ ማለት ሲሆን ለ Client Devices አገልግሎት የሚሰጥ ማለት ነው። በዚህም የሶፍትዌር ሰርቨር የምንላቸው ዌብ ሰርቨር፣ ዶሜን ኔም ሰርቨር፣ ሜይል ሰርቨር በጥቂቱ መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም ስርቨር የሆኑ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጥቀስ ይቻላል ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ሰርቨር፣ ኡቡንቱ ጥቂቶች ናቸው።

🔺Hardware Server የምንለው የኮምፒውተር አይነት ሲሆን መረጃን ለመያዝ የሚያገለግልና በክሊያንት ኮምፒውተሮች መረጃውን እንዲደርስና ዋና መረጃው የሚቀመጥበት ማለት ነው። ሰርቨር ኮምፒውተር በጣም ከፍተኛ የሆነ መረጃን የመያዝ አቅም ያለው፣ መረጃን ፕሮሰስ የማድረግ አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመስራት አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ በዋጋ፣ በአካላዊ ከመደበኛው ኮምፒውተር የሚተልቅ እቃ ነው።

🔺በአንድ ሰርቨር ኮምፒውተር ለብዙ ክሊያንት ኮምፒውቲንግ እቃዎች(ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ ደስክቶፕ፣ ካሜራ፣ ፕሪንተር ወዘተ...) በአንድ ላይ ኔትወርክ በመጠቀም እርስ በራሳቸው እንዲተዋወቁ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ መረጃውን እንዲጋሩ ያደርጋል።

🔺Client Devices የምንለው ማንኛውም የኮምፒውቲንግ እቃዎች ከሰርቨሩ ጋር በመግናኘት መረጃዎችን አሳሾችን (Browsers) በመጠቀም መረጃን የምንጠቀምበት እቃዎችን ያካትታል። ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቱቭ ስንጠቀም መረጃውን ከሰርቨር ኮምፒውተር ላይ ኔትወርክ በመጠቀም የሚያመጣልንና ነው። በአጠቃላይ ሰርቨር ኮምፒውተር ማለት በጣም ብዙ መረጃዎችን አምቆ የያዘ ለተጠቃሚዎች በክሊያንት ኮምፒውተር አማካኝነት በመጠቀም መረጃን ከሰርቨር ኮምፒውተር በማምጣት ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ነው።

🔺ክሊያንትና ሰርቨር ኮምፒውተር የሚገናኙበት ፕሮቶኮል TCP/IP ይባላል። TCP/IP በዋናነት መልእክቶች ከሰርቨር ኮምፒውተር ወደ ክሊያንት ኮምፒውተር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ ሲሆን በLAN Local Area Network ወይም በWAN Wide Area Network ክሊያንት ኮምፒውተሮችን ከሰርቨር ኮምፒውተሮች ጋር በማስተሳሰር መረጃን መለዋወጥ ያስችላል።

@sest_computer
✳️ ለተማሪዎች የሚጠቅሙ 4 የአንድሮይድ አፕሊኬሽኖች❗️


🔺ተማሪዎች በትምህርት ወቅት ጫና ሳይፈጠርባቸው ትምህርታቸውን በአግባቡ በመከታተል በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ የሚረዱ አፕሊኬሽኖች ናቸው፡፡ ዓለም ዓቀፍ እውቅናም የተሰጣቸው አፕልኬሽኖች ናቸው።

1.School Planner Application

🔺ይህ አፕልኬሽን የቤት ስራዎችን፣ የግሩፕና የግል አሳይመንቶችን፣ ፕሮጀክቶችን፣ የእያንዳንዱን ክላስ ሰዓትና ቀን ማንኛውም ትምህርት ነክ አክቲቪቲዎቻችሁን ኦርጋናይዝ ያደርግላችኋል፡፡ ፕሮግራም ያወጣላችኋል።

🔺ይህ አፕሊኬሽን በየቀኑ በፕሮግራማችሁ መሰረት በየቀኑ መስራት ያለባችሁን ለምሳሌ ጥናት ወይም የቤት ስራ፣የግሩፕ አሳይመንት፣ የላብራቶሪ ሙከራ ባጠቃላይ ጠዋት ምን ማድረግ እነዳለባችሁ፡፡ ከሰዓት ምን መስራት እንዳለባችሁ ማታ ምን መፃፍ እንዳለባችሁ ያስታውሳችኋል።
-የምታስረክቡት አሳይመንት ወይም ፕሮጀክት ካለባችሁ የምታስረኩብበት ቀን "በዚህ ቀን ነው፡፡ ቀኑ እየደረሰ ነው…" እያለ ያስታውሳችኋል፡፡

2.Brilliant

🔺ይህ አፕልኬሽን ደሞ በተለይ በሂሳብ፣ በሳይንስና በኮምፒውተር ጥሩ ውጤት ለማምጣት በጣም የሚጠቅም አፕ ነው፡፡
ይህ አፕሊኬሽን እየሸመደዳችሁ እንዳታጠኑና በተለይ ረጃጅም ቃላት የሚበዙባቸው የትምህርት አይነቶችን ዘርዘር ያሉ ገለፃዎችን በመጠቀም ሳትሰለቹ  ትምህርቶቹን በቀላሉ እንድታጠኗቸውና እንዲገባችሁ ይረዳል ።

3.Grammarly

🔺ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ያሳድጋል፡፡
የተለያዩ በእንግሊዘኛ ስትፅፉ  የግራመር ስህተታችሁን ያርማል፣ ትክክለኛ ቃላት እንድትመርጡ ያደርጋል፡፡ ረጃጅም አረፍተ ነገሮችን ስትፅፉ የሲንታክስ ስህተታችሁን ያርማል፡፡ በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ቀስበቀስ ያሳድጋል፡፡

4.Mendeley

🔺Research በምትሰሩበት ግዜ ለጥናታችሁ  የሚሆኑ የተለያዩ ሪሶርሶች እንዴት እንደምታገኙ ይረዳችሃል፡፡ ለጥናታችሁ ወይም ለሪሰርች የሚጠቅሙ መፅሃፎችን፣ጥናታዊ ፅሁፎችን፣ ምክረ ሃሳቦችን እንዴት እንደምታዘጋጁ ያስተምራቸኋል፡፡

🔺ለሪሰርቻችሁ የተጠቀማችሁባቸውን የተለያዩ የጥናታዊ ፁሁፎች ፃሃፊዎችን፣የመፅሐፍት ደራስያን ፣ምሁራንን ስማቸውን በመጥቀስ ጥናታችሁ ላይ በማካተት እንዴት ወይም ክሬዲት እንደምትሰጧቸው ያስተምራችኋል፡፡

❗️አፕልኬሽኖቹን ፕለይስቶር ላይ Search አድርጋችሁ በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።


@sest_computer
💻የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?

➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው  ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ይዘዋል፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን። ይሁን እንጂ አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም function (FN) የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት ሊኖርብን ይችላል::

           የF1 ጥቅሞች
► Win + F1 = Display help menu
►Ctrl +F1 Show/hide menu options in Excell and Word
►F1 in chrome  Open Chrome support

       የF2 ጥቅሞች
► Alt + Ctrl + F2 = opens Document Library in Microsoft Office
► Allows you to edit the selected folder or file name in Windows Explorer
►Rename a file in Windows Explorer
►Edit the active cell in Microsoft Excel
►Ctrl + F2 Shows a print preview in Word
►Alt + Ctrl + F2 Open the document library in Microsoft Office.

       የF3 ጥቅሞች
► Opens search feature in Windows Explorer
► Shift + F3 = change from lowercase to uppercase in Word
► Opens find feature in Firefox and Chrome

       የF4 ጥቅሞች
► Alt + F4 closes window
► Places the cursor in the address bar in Explorer

       የF5 ጥቅሞች
► Starts slide show in Power Point
► Refreshes Internet browser pages
► Opens Find and Replace in Office
► Refresh the browser, also clearing the cache memory.

       የF6 ጥቅሞች
► Goes to the next page in a split screen in Microsoft Word
► Ctrl + F6 = easily switch between Word documents.
►Places the cursor in the browser’s address bar

       የF7 ጥቅሞች
► Alt + F7 does a spelling and grammar check in Microsoft Word
► Shift + F7 open Thesaurus in Microsoft Word

       የF8 ጥቅሞች
► In Excel, enables extend mode for arrow keys
► Select text in Word
► Enables safe mode in Windows

       የF9 ጥቅሞች
► Ctrl + F9 inserts empty fields into Word
► Updates fields in Word
► Send or receive e-mails in Outlook
► Recalculate formulas in Excel

       የF10 ጥቅሞች
► Opens menu bar
► Ctrl + F10 maximizes window in Word
► Shift + F10 does the same thing as a right click

       የF11 ጥቅሞች
► Exits and enter full screen mode in browsers
► Shift + F11 adds a new spreadsheet in Excel

       የF12 ጥቅሞች
► Opens Save As in Word
► Shift + F12 saves Word document
► Ctrl + F12 opens Word document

በዚህ አጋጣሚ ማስተዋል ያለብን ከላይ የዘረዘርናቸው አጠቃላይ ጥቅማቸውን እንጂ እንደምንከፍተው የሶፍትዌር አይነት ጥቅማቸውም ሊለያይ ይችላል። ለምሳሌ ጌም ስንጫወት ወይም pdf document ስንከፍት

@sest_computer
​​✳️ ውድ ተማሪዎቻችን የሁላችንንም ስልክ የሚያንቀሳቅሰው Android ምን እንደሆነ እንንገራችሁ

🔺Android ምንድን ነው?

◽️ Android Open Source የሆነ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ሲሆን በብዛት ለስማርት ስልኮች ያገለግላል።

◽️ ጉግል በ 2003 አንድሮድን ያገኘ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ለተንቀሳቃሽ ስልኮች በጣም ታዋቂው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ሊሆን ችሏል።

🔺Android ስራው ምንድን ነው?

◽️ አንድሮድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ስለሆነ ዓላማው ተጠቃሚውን እና መሣሪያውን ማገናኘት ወይም ማግባባት ነው።

🔺ለምሳሌ ፣ አንድ ተጠቃሚ Text መላክ በሚፈልግበት ጊዜ አንድሮይድ ለተጠቃሚው የመፃፊያ Keyboard ይሰጣል። ፅፎ ሲጨርስ ደግሞ ተጠቃሚው መላኪያውን በሚነካበት ጊዜ Android መልእክቱ እንዲልክ ስልኩን ይመራዋል።

◽️ Google በየአመቱ ለAndroid System Update ይለቃል። ምንም እንኳን Google ለAndroid እድገት ትልቅ ሚና ቢጫወትም ጉግል የAndroid ኦፐሬቲንግ ሲስተምን ለሞባይል አምራቾች በነፃ ይሰጣል።

◽️ Electric ፣ Samsung ፣ LG ፣ Huawei ፣ Lenevo  እና Sony Androidን በሚያመርቷቸው ስልኮች ላይ ከሚጭኑ አምራቾች ጥቂቶቹ ናቸው።

🔺Android vs. iOS?

◽️ የAndroid ዋና ተፎካካሪ የሆነው ISO በአይፎን ስልኮች ላይ የሚሰራ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ነው። በAndroid እና iOS የሚያመሳስሉም የሚያለያዩም ነገሮች አሉ። ወደ እሱ ሲመጣ ሁለቱም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ከ Wi-Fi ጋር መገናኘት ፣ አፖችን ማሰራት ፣ Text መላክ እና ፎቶ ማንሳት ያሉ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። ሆኖም ግን በመልክ እና በአሰራር ረገድ ዋና ዋና ልዩነቶች አሉ።

🔺የAndroid ጥቅሞች

◽️ የAndroid ዋነኛው ጠቀሜታ ተጠቃሚው ብዙ አማራጮች ያሉት መሆኑ ነው። Androidን እንደ ኦፐሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ መሣሪያዎች አሉ። በሌላ በኩል IOSን የሚፈልጉ ከሆነ አይፎን መግዛት ይኖርቦታል።

◽️Android በ2000 ዎቹ መጀመሪያ ከነበሩት ቀናት በጣም ረዥም መንገድ መጥቷል። ራሱንም በማዘመን ተደራሽ ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀላል መሆንም ችሏል።
ለsocial media ፖስት ቪዲዮ edit ስታደርጉ የሚጠቅሟችሁ icons, illustrations, 3D ሞዴሎችና ፎቶዎችን Download ለማድረግ የሚጠቅሟችሁ ድረገፆች

https://iconmonstr.com/
https://icons8.com/
https://www.vecteezy.com/
https://www.flaticon.com/
https://www.freepik.com/
https://undraw.co/
https://www.pexels.com/
https://pixabay.com/
https://gratisography.com/
https://unsplash.com/

@sest_computer
​✳️ ኮምፒውተራችሁን ፍጥነት ለመጨመር እነዚህን ዘዴዎች ይጠቀሙ❗️

🔺Power option

◽️ Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ።

🔺Defragmentation and optimize

◽️ Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ።

🔺Delete unnecessary temporary file

◽️ Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን %temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

🔺Clean up Memory

◽️ This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ የሚመጣውን የ warning box OK ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት።

🔺Visual effects

◽️ Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ። ቀጥሎ ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ።

@sest_computer