Sest Computer School
78 subscribers
16 photos
2 files
41 links
💻 Welcome to the world of computers
🖥️ From basics to advanced
⚙️ Tips, tricks, tutorials & real skills
@sestcom_bot ለፈጣን ምላሽና ማብራሪያ
Download Telegram
እነዚህን ጠቃሚ AI ዌብሳይቶች ሞክሯቸው።
Voice.ai  convert spoken language into written text.
Beautiful.ai create stunning presentations with its intuitive design features and intelligent layout suggestions.
Krisp.ai eliminates background noise from audio in real-time.
Designs.ai is a comprehensive AI tool that simplifies the design process, empowering users to create stunning visuals effortlessly.
namelix.com/ generate a short, brandable business name using artificial intelligence
autodraw.com/ It enables users to quickly transform their rough doodles into professional-looking illustrations.
kickresume.com/ You can create amazing CV and resumes.

SEST COMOUTER SCHOOL
የአንዳንድ Programming Languagesን ዕውቀት የምንቀስምባቸው ድረገጾች፦

ለHTML 👉 w3schools.com

ለCSS 👉 css-tricks.com

ለJavaScript 👉  javascript.info

ለPython 👉 realpython.com

ለTypeScript 👉 codecademy.com

ለJava 👉 javatpoint.com

ለRuby 👉 rubyguides.com

ለC 👉 tutorialspoint.com

ለC++ 👉 learncpp.com

ለC# 👉 csharp.net

ለPHP 👉 php.net

ለSwift 👉 hackingwithswift.com

ለKotlin 👉 kotlinlang.org

ለRust 👉 rust-lang.org

ለDart 👉 dart.dev

ለR 👉 r-project.org

ለPerl 👉 perl.org

ለScala 👉 scala-lang.org

ለHaskell 👉 haskell.org

ለJulia 👉 julialang.org

ለElixir 👉 elixir-lang.org

ከእኛ ጋር የትኛውን መማር ይፈልጋሉ?
ከኛ ጋር Skill ያዳብሩ። ለነገ ስኬትዎ ይስሩ።

@sest_computer
​​​​​​​​✳️ Arduino Programming

◽️ Banzi በ2005 እ.ፈ.አ የተጀመረው Arduino (ሲነበብ አርድዊኖ) የኤሌክትሮኒክስ ፕሮጀክቶች ለመስራት የምንገለገልበት የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።

◽️ አርድዊኖ ፕሮግራማብል (Program ከጻፍን በኋላ ምንጭንበት) ሰርኪውት ቦርድና (Circuit Board) IDE (Integrated Development Environment, ኮድ ወይም ፕሮግራም ምንጽፍበት ሶፍትዌር) ያካትታል።

◽️ C/C++ የፕሮግራም መጻፍያ ቋንቋ (programming language) ላይብረሪዎች በመጠቀም ስራውን ሚከውነው አርድዊኖ, ኮምፒተራችንን በመጠቀም IDEው ላይ የጻፍነውን ኮድ በUSB ኬብል በመጠቀም ሰርኲት ቦርዱ ላይ የምንጭንበት ነው።

◽️ የአርድዊኖ ቦርድ ማይክሮ ኮንትሮለር ስር የሚካተት ሲሆን ከማይክሮ ፕሮሰሰርስ (microprocessors, እንደነ RaspberryPi, የአርድዊኖ ዓይነት ፕሮግራማብል ቦርድ) ካሉት የሚለየው የራሱ Firmwareና Operating System ስለሌለው ነው።

◽️ አርድዊኖ በምንጽፈው ኮድ ተመስርቶ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን  ለምሳሌ -የሰዎችና ስፒከሮች ድምጽ (Voice Sensor), -የመብራትና የጸሀይ ብርሃን (Light sensor), -የሰዎች እንቅስቃሴ (Movement Sensor) _ወይም ጽህፎች (Text Inputs) እንደ ግብአት በመጠቀም ሌላ ውጤት (Output) መፍጠር ይችላል!

◽️ የአርድዊኖ ፕሮግራም ለመጻፍ/ለመጠቀም የአርድዊኖ ሰርኲት ቦርድ (ምስሉ ላይ ያለው ለምሳሌ, አርድዊኖ ኡኖ, 39$ ይሸጣል።

◽️ በአርድዊኖ ከተሰሩ ስራዎች ለመጥቀስ ያክል የጣት አሻራ, የርቀት መለክያ እቃዎችና የህጻናት ማጫዎቻ ሮቦት አሻንጉሊቶች ይገኙበታል።

@sest_computer
ሙሉ ለሙሉ ነፃ የትምህርት ስኮላርሽፕ የሚሰጡ ዩኒቨርስቲዎች ከነ አድራሻቸው እነሆ!

📌1. Simon Fraser University Scholarships In Canada
https://lnkd.in/dkNEy39J
📌2. Orange Knowledge Programme In Netherlands
https://lnkd.in/dvvN5pAE
📌3. Boston University Scholarships In USA
https://lnkd.in/dx4Xn7Z
📌4. British Council STEM Scholarships In UK
https://lnkd.in/dn77K7dm
📌5. Deakin University Scholarship in Australia
https://lnkd.in/dUrKBJbe
📌6. LOCALINTERNational Summer Paid Internship in Turkey
https://lnkd.in/dPBySrM8
📌7. 300 University of South Australia Scholarships
https://lnkd.in/dRKFAtQ8
📌8. University of Miami Stamps Scholarship In USA
https://lnkd.in/dZQ_sKnR
📌9. DAAD Helmut Schmidt Germany Scholarship
https://lnkd.in/dbw36D8n
📌10. Hokkaido University MEXT Japan Government Scholarship
https://lnkd.in/d6MNJz7i
📌11. University of Manitoba Scholarship In Canada
https://lnkd.in/dEkcYbA
📌12. Aalto University Scholarship In Finland
https://lnkd.in/d4WtQ6AN

@sest_computer
1
✳️ Power Supply Unit:

◽️Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው።


@sest_computer
✳️ Hard Drive:

◽️Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ ሙዚቃዎችን፤ ምስሎችን፤ ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡

◽️Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት (operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች (operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡


@sest_computer
✳️ Central Processing Unit (CPU):

◽️ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ (processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡

◽️ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡

◽️ የማቀናበር ሃይል (processingpower) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡ ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡


@sest_computer
✳️ MotherBoard:

◽️Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡

◽️ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ (Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡


@sest_computer
ቴሌግራም ላይ ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ maximum security እና privacy level

1. Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ።
ይህን ለማስተካካል
Settings - privacy and security - passcode

2. 2-step verification ተጠቀሙ።
2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት።
ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ።

3. ከ2 በላይ device ላይ አትጠቀሙ። Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል።
ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate secc ቀንሷቸው።

4. በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ።

5. ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ።

6. የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ።

7. ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው ካያቸው በኋላ የሚጠፉ) ሚሴጆችን ላኩ።

8. የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት።

9. በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ።
Phone number - Nobody
Last seen & online - My contacts
Profile photos - My contacts
Forwarded message - Nobody
Calls - My contacts
Group & channels - My contacts

@sest_computer
በአለማችን ላይ ያሉ ምርጥ የ Adobe ሶፍትዌሮች ጥቅማቸውን እንመልከት!

- በጣም ተወዳጅነትን ያተረፋና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን የሚሰጡ ሰባት የ Adobe SoftWare:

🔺Adobe Light Room

- ይህ የ Adobe ሶፍትዌር አንደኛው ክፍል ሲሆን የሚጠቅመን የተለያዩ ፎቶዎችን ብርሀን Brightness ለማስተካከል ነው። አብዛኛው ፎቶ ግራፈር (CameraMan) የሚጠቀምበት ሶፍትዌር ነው።

🔺Adobe After Effect

- ይህ ደግሞ የተለያዩ Animation Videos ለመስራት የምንጠቀምበት ሶፍትዌር ነው።

🔺Adobe Flash Professional

- ይህ የተለያዩ 2D ጌሞች ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመስራት የሚጠቅመን የ Adobe ሌላኛው ክፍል ነው።

🔺Adobe Spark

- የተለያዩ Graphics Design ለመስራት ፅሁፎችን ወደ ተለያዩ ፎቶዎች ለመቀየር የምንጠቀምበት ሶፍትዌር ነው።

🔺Adobe Media Encoder

- በ PR እና AE የሠራናቸው ስራዎች ወደ ቪዲዮ ስንቀይር የተለያዩ ዲቫይሶች ላይ እንዲሠራልን Encode የምናደርግበት ሶፍትዌር ነው።

🔺Adobe Audition

- ይህ Record Mix Edit ለማድረግ የሚጠቅመን የ Adobe አንደኛው ክፍል ነው።

🔺Adobe Premiere Pro

- የአለማችን ቁጥር አንድ የቪዲዮ መስሪያ  ሶፍትዌር ነው። ቪዲዮዎች፣ፎቶዎችን፣ አኒሜሽኖችን ወ.ዘ.ተ የምንፈጥርበት ፕሮፌሽናል የቪዲዮ ማቀነባበርያ ሶፍትዌር ነው።


ከኛጋር ይማሯቸው።
GRAPHICS DESIGN IN SEST COMPUTER SCHOOL.

@sest_computer
10 በጣም ጠቃሚ ድረገፆች

1. themarkup.org/series/blacklight = Real Time website privacy inspector. ማንኛውንም ድረገፅ ከመክፈታችሁ በፊት ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ይጠቅማችኋል።
2. codingame.com = ጌም እየተጫወታችሁ ኮዲንግ የምትለማመዱበት
3. Remotists.com = በአለም አቀፍ ደረጃ remote ስራዎችን search የምታደርጉበት
4. hacksplaining.com = Hacking ቀላል በሆነ መንገድ የምትማሩበት
5 Typelit.io = የተለያዩ ፅሁፎችን Type እያደረጋችሁ የምትለማመዱበት
6. coveryourtracks.eff.org = የምትጥቀሙት browser ምን አይነት መረጃ አሳልፎ እንደሚሰጥና track ያደርግ እንደሆነ check የምታደርጉበት
7. www.startrek.com/ የቴክ ዜናዎች ዶክመንተሪዎችና ታሪኮች በፅሁፍ የምታገኙበት
8. musclewiki.com = የሰውነት እንቅስቃሴ በምናደርግበት ጊዜ ምን አይነት ስፖርት መስራት እንዳለብንና የትኛውን የሰውነታችን ክፍል ለማዳበር እንደሚጠቅመን ስዕላዊ በሆነ መንገድ የሚያሳየን
9. codepen.io = የተለያዩ ኮዲንግ ፕሮጀችቶችን የምታገኙበት እንዲሁም ድረገፁ ላይ ኮድ ፅፋችሁ run  ታደርጉበታላችሁ።
10. litsolutions.org = የተለያዩ መፅህፍትን ጥያቄዎች መልስ የምታገኙበት

ጥንቃቄ ለራስ ነው።
@sest_computer
​​✳️ ውድ የቻናሉ ተከታታዮች ዛሬ ኮምፒዉተር በራሱ የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበትን ምክንያቶች በጥቂቱ እናያለን።

🔺የሀርድዌር መቃረን፡ ለWindows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware  መቃረን ነው፡፡  እያንዳንዱ Hardware  ክፍሎች ለመግባባት IRQ (interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው።

🔺እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆነ IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊፈጥር ይችላል፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡

🔺የተበላሸ ራም፡ የሚያሳየው  መልእክት (Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል። በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡

🔺መጋል፡ በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ ያደርጋል።


#Tech_Tips
#Join

@sest_computer
​​✳️ ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች!

◽️ ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶወች (ዋልፔፐር) አይጠቀሙ፡፡

◽️ ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡

◽️ አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡

◽️ የማይጠቀሙበት አፕሊኬሽን ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት።

◽️ ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡

◽️ ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ።

◽️ Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
◽️ ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
◽️ ብዙ አፕሊኬሽን ባንዴ አይክፈቱ::

#Tech_Tips
#Join
@sest_computer
​​✳️ Cloud Storage ምንድነው

🔺 ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡

🔺በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዩ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት Microsoft, Google, and Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋሉ፡፡

🔺መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጅ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን ማግኘት እንችላለን።

🔺ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡ 

🔺በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን እና ብዛት ነው፡፡

#Share
#Tech_Tips

@sest_computer
✳️ የስልካችንን DATA ስናበራ የሚመጡት G, E, 3G, H/H+, 4G, 5G እነዚህ ምልክቶች ምንድናቸው?

🔺G : Feature ስልኮች (Keypad) ላይ ሳይቀር ስልኩ ከኢንተርኔት ጋር ሲገናኝ ይህንን ምልክት እናያለን። ትርጉሙም GPRS (Global Packet Radio Service) ማለት ነው።

🔺E : Edge -በመባል የሚታወቀው ይህ Network የስልካችን ኔትወርክ Enhanced GPRS የሚባለውን መጠቀም ሲጀምር ይህንን እናያለን። የታወቀው ፍጥነት ደግሞ 0.4mb/s ነው።

🔺3G : ብዙዎቻችን እናቀዋለን የ3rd Generation Network ሲሆን በGSM Network ላይ የሚሰራ Network ነው። 3G በአማካኝ እስከ 2mb/s ፍጥነት ይኖረዋል።

🔺H/H+ : HSDPA (High speed Downlink packet access) ማለት ሲሆን ብዙ ስማርት ስልኮች ላይ H ከሆነ እስከ 7 mb/s ድረስ ይሄዳል። H+ ሲሆን ደግሞ እስከ 21mb/s ድረስ ይሄዳል።

🔺4G/LTE : ይህ 4ኛው ትውልድ ኔትወርክ 5G ከመምጣቱ በፊት ምርጥ Network ነበር። ፍጥነቱም እስከ 150mb/s ነው። ብዙ ጊዜ ከwi-fi በበለጠ ፍጥነት ይኖረዋል።

🔺5G : የ5ኛው Generation ሲሆን ከ4G በ1000 እጥፍ የDownload ፍጥነት ሊኖረው ይችላል።


#Tech_Tips
#Join #share

@sest_computer
✳️ ብንጠቀምባቸው ስራን የሚያቀሉልን ጠቃሚ ዌብሳቶች!

1. የተለያዩ ነገሮችን ለማወዳደር
  versus.com

2. ለተለያየ አገልግሎት ጊዚያዊ ኢሜል ካስፈለገዎ :
10minutemail.com  ወይም yopmail.com

3. ማንኛውንም ትልልቅ ሶፍትዌሮች ከነ ሲሪያል ኪ ዳውንሎድ ለማድረግ
Getintopc.com

4. የዋይፋይ (ኢንተርኔት) ፍጥነት ለማወቅ Speedtest.net   ወይም fast.com ን ይጠቀሙ

5. በቀን ና ሰአት ላይ የተለያዩ ቀመሮችን መስራት ከፈለጉ :
timeanddate.com ን ቢጠቀሙ ጊዜ ይቆጥባሉ።

6. ጠንከር ያለ ና በቀላሉ የማይሰበር የይለፍ ቃል
/password ከፈለጉ
Passwordsgenerator.net ይጠቀሙ

7. ከጎበኙት ድረገፅ የወደዱትን ፔጅ ቢፈልጉ በፕሪንት ወይም pdf አልያም በኢሜይል ማስቀረት ካሰቡ :
Printfriendly.com ይጠቀሙ።

8. የተለያዮ የውጪ ቋንቋዎችን ለመማር
Duolingo.com ን ይጎብኙ

9. አልከፍት ያሎትን ድረገፅ አልሰራ ያለው ለእርሶ ብቻ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ
downforeveryoneorjustme.com  ወይም isitdownrightnow.com ዌብሳይቶቾ ጠቃሚ ናቸው።

10. ኮምፒውተራችን ላይ መጫን ሳያስፈልገን የMicrosoft office ን ምርቶች ኦንላይን ለመጠቀም
office.com ላይ በመግባትና የmicrosoft ን ኢሜል በማስገባት መጠቀም ይችላሉ።

@sest_computer
በጣም ጠቃሚ ትምህርታዊ ነፃ AI Tools

▪️ Humata AI Document summarizer and review
▪️ Textero AI Essay Writer
▪️ WolframAlpha Help on mathematics and science
▪️ MathGPTpro Helps on Mathimatics
▪️ Quizgecko ዶክመንት ሰጥታችሁት ጥያቄ የሚያወጣ
▪️ Prepsup በተለያዩ ዘርፎች ለፈተና የሚያዘጋጃችሁ
▪️ LearnGPT ማንኛውንም የትምህርት አይነት በቀላሉ የሚያስረዳ
▪️ Codeamigo Code assistant
▪️ gptionary Conversation with an AI on a specific topic
▪️ Gradgpt ኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ለመቀላቀል Statement of Purpose, Letter of recommendation, SOP Review
ለመፃፍ ያግዛል።

Bonus
BrandScript Generator content and story generator ለማድረግ

መሰል ትምህርቶችን ይማሩ!!!!!
@sest_computer
✳️ የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች ድረገፆች❗️

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ www.aau.edu.et
መቀሌ ዩኒቨርስቲ  www.mu.edu.et
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ www.astu.edu.et
አክሱም ዩኒቨርስቲ www.axu.edu.et
አምቦ ዩኒቨርስቲ www.ambou.edu.et
አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ www.amu.edu.et
ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ www.bdu.edu.et
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ www.dbu.edu.et
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ www.dmu.edu.et
ዲላ ዩኒቨርሰቲ  www.du.edu.et
ጎንደር ዩኒቨርስቲ www.gu.edu.et
ጂማ ዩኒቨርስቲ www.ju.edu.et
ሃረማያ ዩኒቨርስቲ www.haramaya.edu.et
ሃዋሳ ዩኒቨርስቲ www.hu.edu.et
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ www.wsu.edu.et
ወለጋ ዩኒቨርስቲ www.wu.edu.et
ድሬ ዳዋ ዩኒቨርስቲ  www.ddu.edu.et
ወሎ ዩኒቨርስቲ www.wou.edu.et
ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ www.jgu.edu.et
መዲ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ www.mwu.edu.et
ሚዛን ቲፒ ዩኒቨርሲቲ www.mtu.edu.et
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ www.su.edu.et
ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ www.kuc.edu.et
አአ ሾል.& ቴክ ዩኒቨርሲቲ www.aastu.edu.et
አዲግራት ዩኒቨርሲቲ  www.adu.edu.et
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  www.asu.edu.et
ቡሌ ሁራ ዩኒቨርስቲ www.bhu.edu.et
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ www.dbtu.edu.et
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ www.wcu.edu.et
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ  www.wku.edu.et
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ  www.wdu.edu.et
አርሲ ዩኒቨርሲቲ www.aru.edu.et
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ www.gmu.edu.et
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ www.obu.edu.et


#Join
@sest_computer
✳️ እስከ 100 GB + ነፃ ኦንላይን ማንኛውም File ማስቀመጫ ምርጥ ሳይቶች❗️

🔺Sign up at Ozibox.com to get 100GB of free storage.

🔺Sign up at SurDoc.com to get 100GB of free storage.

🔺Sign up at Shared.com to get 100GB of free storage.

🔺Sign up at Adrive.com to get 50GB of free storage

🔺Sign up at Mega.co.nz to get 50GB of free storage.

🔺Sign up at Hubic.com to get 25GB of free storage.

🔺Sign up at Firedrive.com to get 20GB of free storage.

🔺Sign up at Onedrive.live.com to get 15GB of free storage.

🔺Sign up at Copy.com to get 15GB of free storage.

🔺Sign up at Mediafire.com to get 10GB of free storage. (40GB more available with other activities)

🔺Sign up at Pcloud.com to get 10GB of free storage (10GB more available with other activities)

🔺Sign up at Box.com to get 10GB of free storage.

Tera box is my best but the ads.....

@sest_computer
✳️ ብዙ ጊዜ ኮምፒውተራችን ላይ Delete አልሆን ያሉ ፎልደሮችን እንዴት እንደምናጠፋ እናያለን❗️

Step 1. Folder/File ጋር Right Click አድርገን Properties የሚለውን ይምረጡ።

Step 2. ከዛም Security የሚለው ላይ Advanced የሚለውን ይንኩት።

Step 3. Administration ከሚለው አጠገብ Change  የምትለዋን ይጫኑ።

Step 4. ከዛም Advanced የሚለውን ይጫኑ።

Step 5. ከዛም Find Now የሚለውን ተጭነው ከሚመጡት ዝርዝር ውስጥ የኮምፒውተርዎን User Name ይምረጡ።

Step 6. መቀየሩን ካረጋገጡ በኋላ ሳጥኖቹ ላይ ራይት ( ) ያድርጉ።

Step 7. Apply የሚለውን መምረጥ

Step 8. Messages box ያመጣል ከዛም yes ይበሉ።

Step 9. Permission ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ OK ይበሉት።

Step 10. OK ብለው ሁሉንም window ፕሮግራሞችን ይዝጉት።

Step 11. መጨረሻ Delete ማድረግ የፈለጋችሁትን ፎልደር ማጥፋት ትችላላችሁ።


@sest_computer
✳️ ምርጥ የኮምፒዉተር ሶፍትዌር ማዉረጃ ሳይቶች❗️

1.
download.cnet.com

ይህ ሳይት የኮምፒዉተር ሶፍትዌሮችን ከማዉረጃ ሳይቶች ቀደምት ሲሆን ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተመሰረተ ነዉ፡፡ የዚህ ሳይት ባለቤት በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ገናና ስም ያለዉ CNet ነዉ፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም የሞባይል አፕሊኬሽኖችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከ 100,000 በላይ ፕሮዳከቶችን አካቷል፡፡ ሶፍትዌሮቹ በ ኤዲተሮች ተገምግመዉ እና ደረጃ ተሰጥቷቸዉ ተቀምጠዋል፡፡ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ግምገማዎችን መፃፍ እና ለ ሶፍትዌሮቹ ደረጃ መስጠት ይችላሉ፡፡

2.
filehippo.com

🔺ይህ ሳይት በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ነዉ፡፡ FileHippo Update Checker የሚል ፕሮግራም ያካተተ ሲሆን ይህም በኮምፒዉተራችን ላይ የጫንናቸዉን ሶፍትዌሮች scan በማድረግ አዲስ የተሻሻለ ምርት ካላቸዉ ይጠቁመናል፡፡ ይህም ኮምፒዉተርን ከሚያጠቁ ቫይረሶች ለመከላከል እጅጉን ይጠቅማል፡፡

3.
www.softpedia.com

🔺Softpedia የሮማኒያ ዌብሳይት ሲሆን ሶፍትዌሮችን ዳዉንሎድ ማድረግ እና ስለ ሶፍትዌሮቹ ማብራሪያ መረጃዎችን ማግኘት ያስችለናል፡፡ ከ ሶፍትዌሮቹም በተጨማሪ የ ቴክኖሎጂ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና መዝናኛ ዜናዎችን ያገኙበታል፡፡ ሶፍትዌሮችን በ ካታጎሪ ተቀምጠዉ ማግኘት ስለምንችል ስራችንን ያቀልልናል፡፡ ተጠቃሚዎችም በሚፈልጉት መስፈርት መፈለግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በተሻሻሉበት ቀን፣ በተጠቃሚ ብዛት፣ ሬቲንግ እና በመሳሰሉት፡፡

4.
www.tucows.com/downloads

🔺ስሙ ምህጻረ ቃል ሲሆን ይህም The Ultimate Collection Of Winsock Software ማለት ነዉ፡፡ ለ Windows, Linux እንዲሁም ለድሮዎቹ የ Windows ቨርዢኖች የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡

5.
www.freewarefiles.com

🔺ነፃ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በብዛት የምናገኝበት ሳይት ሲሆን ከ 15,800 በላይ ነፃ ሶፍትዌሮችን አካቷል፡፡ እነዚህን ሶፍትዌሮችንም በ ካታጎሪ ስለተቀመጡ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡

6.
m.majorgeeks.com

🔺ይህ ሳይት በፊት TweakFiles በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፋይሎች አሪፍ ኢንተርፌስ ያላቸዉ እና ለተጠቃሚዎች በቀላሉ የተገለፁ ናቸዉ፡፡ ፋይሎቹ ዌብሳይቱ ላይ ከመለጠፉ በፊት ጥራታቸዉ ይረጋገጣል ይህም ብዙዎችን ከሚያሰለቸዉ የዉሸት ሶፍትዎሮች እንዲሁም ቫይረሶች ይጠብቅዎታል፡፡ በተጨማሪም አሪፍ ኢንተርፌስ ኮሚዩኒቲ ያለዉ ሲሆን ስለ ኮምፒዉተር ያሉንን ጥያቄዎች ይመልሱልናል፡፡

7.
www.bytesin.com

🔺FileCluster አሁን ላይ ከተመሰረቱ አዳዲስ ዌብሳይቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ተጠቃሚዎቹም አዲስ እና የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የ WordPress Themes፣ ዜናዎችን እና ሶፍትዌር ካምፓኒዎችንም ማግኘት ይችላሉ፡፡

8.
www.soft32.com

🔺በ 2003 የተመሰረተ ሲሆን የ ሶፍትዌር ዳይሬክተሪዉን ቶሎ ቶሎ update በማድረግ ይታወቃል፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux እንዲሁም ለ ሞባይል የሚሆኑ ሶፍትዌሮች ሲኖሩት ለ iPhone ተጠቃሚዎች ብቻ ራሱን የቻለ ክፍል አዘጋጅቷል፡፡ ከ 85,000 በላይ ሶፍትዌሮች ሲይዝ ጥያቄዎቻችንን መጠየቅ የምንችልበት ፎረምም አለዉ፡፡


@sest_computer