Ethiopian vacancy
85.9K subscribers
7.2K photos
8 videos
136 files
6.47K links
💢Find your next career move with unique Telegram job alerts. We link top talent with amazing opportunities, seamlessly.
ማስታወቂያዎትን በእኛ ቻናል ለማስተዋወቅ ከፈለጉ፣ @meneyahel ላይ ያግኙን።
https://fb.me/ultimatevacancy1
#Ethiopianvacancy
#ethiojob #ethiojobvacancy#career
Download Telegram
👍1👏1
ለስራ ፈላጊዎች የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ
(ሲቲ ባስ፤ ሃምሌ21/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ያለበትን የሾፌርና የአገልግሎት ክፍያ ተቀባይ እጥረት ለማሟላት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በታተመዉ መሰረት በሁሉም ቅርንጫፎች በአካል ቀርቦ መመዝገብ እንደሚቻል የተቋሙ የሰዉ ሃብት ዳይሬክቶሬት አሳዉቋል ፡፡



በተጨማሪም የአ/አ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ለተቋሙና ለ cop 32 የአዉቶቡስ ካፒቴን ቅጥር ለማሟላት ያስችለዉ ዘንድ " በልምድ " እና " 0 " ዓመት እንዲሁም " በኮንትራት " በመቅጠር ላይ ሲሆን አያይዞም የአገልግሎት ክፍያ ተቀባይ በ "ልምድ " እና በ " 0 " ዓመት በስፋት ለመቅጠር በጋዜጣ ያወጣውን ማስታወቂያ ከሐምሌ 21/ 2018 እስክ ሐምሌ 28 /2018 ድረስ በየቅርንጫፉ በሰው ኃብት ልማት ቡድኖች ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡



ምዝገባዉን ተከትሎ ተመዝጋቢውን በስፋት ማግኘት እንዲቻል ሕዝብ በስፋት በሚገኝባቸው ተርሚናሎች ፤ መናሃሪያዎች ፤ ክፍያ የሚፈፀምባቸው የማስታወቂያ ቦርዶች ፤መረጃ ህብረተሰቡ የሚያገኝባቸው የሰልፍ ቦታዎች ፤በየቅርንጫፍ እና በአካባቢዉ ካፒቴን፤ ትኬተር፤ እንዲሁም ማንኛውም ሰራተኛ አውቆ በተለያዩ አማራጮች ተጠቅሞ የቅጥር ዜናዉ ተላልፎ ምዝገባው በስፋትና በጥራት እንዲከናወን ሁሉም ርብርብ በማድረግ ሀገራዊ እና ተቋማዊ ተልእኮው አንዲሳካ የአዲስ አበባ ከተማ አዉቶቡስ ድርጅት ጥሪዉን ያስተላልፋል፡፡
3🔥1
የቅጥር ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ለኮልፌ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን በቋሚነትና በኮንትራት አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም

1. ለኮንትራት ቅጥር ፈላጊዎች Contract Position የሚለውን ሊንክ በመጫን እንዲሁም
2. ለቋሚ ቅጥር ፈላጊዎች Permanent Position የሚለውን ሊንክ በመጫን በስራቸው የተዘረዘሩ የስራ መደቦች ላይ በመመዝገብ ማመልከት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

* [Contract Position](https://forms.gle/sphHtPyHE9qmuxhz5) (ለጊዜያዊ የስራ መደብ ) https://forms.gle/sphHtPyHE9qmuxhz5
* [Permanent Position](https://forms.gle/J1AaXJtRrVMoaFSu9) (ለቋሚ የስራ መደብ ) https://forms.gle/J1AaXJtRrVMoaFSu9

ማሳሰቢያ፡-
* ለጊዜያዊ የስራ መደብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሀምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ እንዲሁም

* ለቋሚ የስራ መደብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሀምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ሆኖ ከጠዋቱ 2.30 እስከ ማታ 11.30 ብቻ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
* “Submit” የሚለውን የሚጫኑት መጨረሻ ላይ መረጃ ከሞሉና ፋይሎትን ካያያዙ በኋላ ነው::
* በአንድ ኢሜል አድራሻ አንድ ጊዜ ብቻ ነው መመዝገብ የሚቻለው፡፡

https://forms.gle/eNbU1f5HbPiPsDUQA
3