ሰንፔር ሚዲያ Sapphire Media
434 subscribers
297 photos
4 videos
8 files
109 links
መንፈሳዊ መጣጥፎችን ግጥሞችን ወጎችን አጫጭር ልቦለዶች አስደናቂ ታሪኮችን ትምህርታዊ ፅሁፎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን።

"ትውልድ ሆይ ወደ እግዚአብሔር ቃልና ወደ ተሰቀለው ክርስቶስ ተመልከቱ!!!"


https://youtu.be/KRKo3x7iYNw

http://Instagram.com/sapphiremedia4god

tiktok.com/@sapphiremedia1
Download Telegram
ዛሬ ይጀምራል 🙏
ዛሬም ይቀጥላል
The Renewal We Expect - Hawassa_240214_103442.pdf
289.5 KB
@ኮንፍረንስ ሪቫይቫል፦ የሚናፈቀው ተሃድሶ

(Revival:- The Renewal We Need or Expect)
ዛሬም ይቀጥላል
ይምጡና ይካፈሉ
“ትልልቆችን” በመያዝ ትልቅ የሚኾን ክርስትና የለንም!

ዘመኑ የውድድር ዘመን ስለመሆኑ በብዙ መልኩ ይነገራል፡፡ “ቀድሞ መገኘት ነው!” የሚል አስቀዳዳሚ ማስታወቂያ የትም የሚሰማ ነው፡፡ በዚህ ዘመን ሁሉም ነገር ውድድር መስሏል፤ ሁሉም ነገር ስል ሃይማኖትንም ይጨምራል፡፡ እንደውም ሃይማኖታዊ እሽድምድም ከብዙው ነገር ይልቅ ከፍተኛውን ቦታ ሳይዝ አይቀርም፡፡

የእኔ ሃይማኖት በላጭ ነው የሚለውን ለማስረገጥም ይሁን የእኔ አገልግሎት የተሻለ ነው ለማለት የሃይማኖት ሰዎች በእነርሱ ዙሪያ ያሉትን ታዋቂ ሰዎች እንደ ሰንደቅ ዓላማ ከፊት ከፍ አድርገው ያሰልፋሉ፡፡ ኦ#ርቶዶክሱ ተመለስኩ የሚለውን “መጋቢውን” ይዞ የእምነቱን ትልቅነት ሊለፍፍ ይሞክራል፤ ጴንጤው ሼሁን እና ቄሱን ይዞ ግዳይ እንደጣለ ሊፎክር ይዳዳዋል፤ እ#ስላሙ ቄሱን ወይ መጋቢውን ይይዝና ወደ እውነተኛይቱ ኑ የሚል ጥሪውን ያስተጋባል፡፡ ያው እነ ታዋቂ እና ተደናቂ እገሌዎች የሃይማኖቱ እውነተኝነት መለኪያ ማስረጃ መሆናቸው ነው፡፡ አሳዛኙ ነገር በዚህ መልኩ ታላቅ የሚሆን ሃይማኖት አለመኖሩ ነው፡፡

በሌላ ጎኑ ደግሞ ከዓለም አካባቢ ወደ ሃይማኖት ቤት የሚመጡ ታዋቂ ሰዎች ወይ ዘፋኞች አልያም ከአርትጋ ተያይዞ በየሚዲያው የገነኑ ሰዎች ናቸው፡፡ መቸም እንዲህ ያሉ ሰዎች ወደየእምነታችን ሲመጡ ደስ ማሰኘቱ አይቀሬ ነው፤ በአንድም በሌላም በዓለም ሳሉ የሚያደንቋቸው ሰዎችም የእነሱን መንገድ ለመከተል ይወሰወሱ ይሆናል (ይህንን እንደ በጎ አጋጣሚ መቁጠር ይቻልም ይሆናል)፡፡ ሆኖም ግን የእነዚህ ሰዎች ወደ ሆነ የእምነት ክፍል መምጣት የአንድን ሃይማኖት ትልቅነት አስረጋጭ ሊሆን አይችልም፤ ብዙዎቹ ታዋቂነታቸውን እንጂ ዐዋቂነታቸውን እርግጠኛ መሆን አይቻልምና፡፡ በተለይ የክርስትና እምነት በተከታዮቹ ሳቢያ ትልቅ ሊሆን የሚችል እምነት አይደለም፡፡

ክርስትና ከመሠረቱ እግዚአብሔር አምላክ የዓለምን የሆነውን ነገር ለማሳፈር ያልሆነው ነገር የተመረጠበት እምነት ነው፡፡ የክርስትና ጀማሪ እና ሐዋሪያ የሆነው ጌታችን የክርስትና እምነት አስቀጣይ የሆኑት ሐዋርያቱን ሲጠራ የሄደበት መንደር፣ ሄዶም የጠራቸው ሰዎች በእውነት የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ በቃ አንዳች ትምክህት ሊኖር አይችልም! ነገር ሁሉም ከጠሪው እንጂ ከተጠሪዎች አይደለም፡፡

በክርስትና እምነት ውስጥ ለታላቅነቱ ፍጻሜ የሌለው አንድ ትልቅ ብቻ አለ፤ ክርስትናችንም ከእርሱው የተነሳ ትልቅ ነው፡፡ እምነታችንን በእርሱው እንጂ በእነእከሌ ለማስተዋወቅ መሞከር መኮሰስ ነው፡፡ ሸንበቆ የሆነ ስጋ ለባሽ ማንም ቢኾን ተሰባሪ ነው፡፡ ማንም ከእዚህ ወደ እዚያ እየተመመ የእውነት አምድ መሆን አይችልም፡፡ እገሌ መጣ፤ እገሊት ሄደች የሚለው ሃይማኖታዊ ብሽሽቅ ራስ ከሆነው ከማራቅ በስተቀር ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡

ክርስትና በደም የጸና እምነት ነው፡፡ በሞተው እና በተነሳው፤ እራሱ በቀጠረው ቀንም በሚመጣው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተመሥርቷል፡፡ ማንንም ወደ ክርስትና ለመጥራት ክርስቶስ በቂና ከበቂ በላይ ነው፡፡ በእምነታችን ያለን ትምክህት ሁሉ ከእርሱ እንጂ ከሌላ ሊመነጭ አይገባም፡፡ እንደ ውሃ ከሚዋልሉ ሰዎች ላይ እምነታችንን እናንሳ፤ በጸናው በእርሱ ላይ ልባችንን እናጽና!!!

Sintayehu Bekele 🙏🙏🙏
He knew what we were before conversion...wicked, guilty, and defiled; yet He loved us. He knows what we will be after conversion...weak, erring, and frail; yet He loves us.

-J.C. Ryle
ከእምነታችሁ ጋር ስትታገሉ፣ ነፍሳችሁ በአስጨናቂ ጨለማ ስትዋጥ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ባላችሁ ግንኙነት ግራ ስትጋቡ፣ ወደ ቅዱሳት መጽሐፍ ሽሹ! እግዚአብሔር መንፈሰ ቅዱስ የሚናገራችሁ፣ ነፍሳችሁን የሚያገለግለውና አስቀድሞ የሰጣችሁን እምነት የሚያጠናክረው በእነዚህ ገጾች አማካኝነት ነው።

RC Sproul
ወርሃዊው መንፈሳዊ የስነፅሁፍ ምሽታችን ቅዳሜ ይደረጋል። መጥተው ይካፈሉ።
“ክርስቲያን፥ የሆነውን ሁሉ ከመሆኑ በላይ ክርስቲያን ነው። ባለ እምነት ፣ ባለ መፅሐፍ እና ባለ ተልዕኮ ነው። ብልህ ክርስቲያን ይህን የወቅት “ልታይ ልታይ” ባይነት አባብሎና ገስፆ ፥ ወቅቱን በዘላለሙ ዋና ውቅር ላይ ያስቀምጣል። ተገቢው ቦታውንና ቅርፁን ይሰጠዋል። ይህን የሚያደርገው ለወቅትም ለዘላለምም ሲል  ነው።
ክርስቲያንነት ወቅታዊነትን በዘላለም አንፃር ዛሬን ማየት ነው። ዛሬን መተርጎም መቻል ነው። ለዛሬ ጥያቄ የሚደመጥ ዘላለማዊ መልስ መስጠት ነው።” 


ንጉሴ ቡልቻ፤ ወቅታዊ_ዘላለማዊ ገፅ ፬
ነገ እንገናኝ 🙏
"እኔ ላይ የተላከው ሰይጣን ረቂቁ ሳይሆን መሃይሙና ጨቋኙ ይመስለኛል"
                           * * *

ከጉራጌ ገጠር የተገኘ ነው።  ቤተሰቦቹ የተፈሩ ባለውቃቢ ነበሩ። ይህ ብቻ ሳይሆን ገና የሰባት አመት ልጅ ሳለ የወደፊቱ ታላቅ ባለውቃቢ እንደሚሆን ተነግሮለታል። 

"የትልቁ ውቃቢ ተሸካሚ የሆኑት ባለውቃቢ  ሲሞቱ መንፈሱ እርሱ ላይ ያርፍና ታላቅ ባለውቃቢ ይሆናል" ተብሎለታል። በዚህም ሰበብ ገና ጨቅላ ሳለ ጀምሮ 'ወሰድ መለስ' የሚያደርገው 'ወፈፌ' ሊሆን ችሏል።

ህፃን ሳለ በባዕድ አምልኮ የታሰሩ ወደ ባዕድ አምልኮ ስፍራ ሲመጡ እርሱ ብርቱ አገልጋይ ሆኖ ይሰለፋል። እንጨት ይፈልጣል፥ ወንዝ ወርዶ ውሃ ይቀዳል፥ በማምለኪያ ግቢው ከሚገገኘው የጫት ዛፍ ጫት ቀንጥሶ ያቀርባል፥ በርከክ ብሎ 'የአምላኪዎቹን' እግር ያጥባል፥ ቡና አፍልቶ ለተሳታፊው በማደል ስራ ይሰማራል።

በብርቱ መታተር ውቃቢውን ቢያገልግም በውቃቢው የሚመሰገን አይደለም። ሲመሻሽ የጭንቅ ለሊት ይጀምራል። በብዙ  ይሰቃያል፥ ያውጓል፥ ደግሞም ይቃዣል።
"ታዛዥ አገልጋይ ሆኖ ሳለ እንዲህ መሰቃየቱ ለምን ሆነ?" የሚል ጥያቄ በቤተሰቡ አእምሮ ቢፈጠርም ልጃቸውን ለማፅናናት የሚሆን ቃል አያጡም። "ትልቅ ሰው እየሆንክ ስለሆነ ውቃቢው ሊዋረስህ ነው፥ ስቃይህ በዚህ የተነሳ ነውና ታገስ" ይሉታል።

ከቀናት በአንዱ ፥ እንደማንኛውም አዳጊ ልጅ አጎቶቹ ዘንድ ተልኮ  ሲሄድ ለየት ያለች ሴት ተመለከተ።

ሴቲቱ ጭንቅላቷ አነስተኛ፥ አንገቷ አጭርና ወፍራም ፥ከትከሻ እስከዳሌዋ ወፍራምና ቅርፅ አልባ ነች። ከቀኝ ትኬሻዋ ወደ ግራ ዳሌዋ አሮጌ ጨርቅን አሸርጣለች። ማንኛውም ሰው ሲራመድ በእጆቹ አየር ይቀዝፋል። ይቺ ግን እጆቿ አይንቀሳቀሱም። መላ ነገሯ ያልተለመደ ነው። ታዳጊው ሴትየዋን በአስተውሎ ከተመከተ በኋላ ተሸበረ። በፍርሃት ወደመጣበት ሊመለስ እያሰበ ሳለ ሴቲቱ ድንገት ተሰወረች።

ደግሞ ሌላ ቀን፥

ከእኩያ ጓደኞቹ ጋር ከብት ሊያግድ ተሰማራ። ይሄኔ ለሱ ብቻ አንድ ሰው ታየው።
ሰውዬው ለመግለፅ በሚከብድ ልክ ቀጫጫ ሲሆን ወንዝ መሃል ሹል  ድንጋይ ላይ ተቀምጦ ሰውነቱን እያከከ ይታጠባል። በነገሩ ግራ የተጋባው ብላቴና የተመለከተውን ለጓደኞቹ ሊያሳይ ዘወር ከማለቱ  ሰውዬው ተሰወረ።

በተደጋጋሚ የሚሆነው ክስተት ቤተሰቡን በማስጨነቁ መፍትሔ ተፈለገ። መላ ለማበጀትም በአባቱ መኖሪያ ካለ ወንዝ እንዲወሰድ ተወሰነ።

ዘወትር ረቡዕ ከለሊቱ 11 ሰኣት ሲሆን ማንም ወንዙን ሳይሻገር ወደ ወንዙ ይደርሳሉ።
ታዳጊው ልጅ አንዴ ወደ ወንዙ ከተነከረ በኋላ ወደ ዳር ይወጣና በአሻዋ ሰውነቱ ይታሻል። ከአሸዋ መታሸት ቀጥሎ ድጋሚ ይነከራል፥ መልሶም  በአሸዋ ይታሻል። ለሦስት ዙሮች በውሃው እየተነከረ በአሸዋ ከታሸ በኋላ በውሃ ይለቀለቃል። ይህ ሲሆን ከአሸዋው ጋር የሚቀላቀሉ ጥቃቅን ሹል ድንጋዮች የታዳጊውን ገላ እየሸነታተሩ ቁስል የሚፈጥሩ ሲሆን ወደ ውሃው በተነከረ ቁጥር ለከፍተኛ ስቃይ ይዳረጋል።

ድርጊቱ የአንድ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ጊዜ የሚደረግ አይደለም!  ለ 49 ተካታታይ  ሳምንታት ሳይታጎል ይቀጥላል።
49 ሳምንታት በውሃ መነከርና በአሸዋ መታሸቱ ከተከወነ በኋላ በ50ኛው ሳምንት የመደምደሚያ ስርኣት ተከወነ።

በ50ኛው ረቡዕ ዥንጉርጉር ነብር መሳይ ፍየል ተፈልጎ ከተገኘ በኋላ የ10 አመቱ ብላቴና ፍየሉን ተሸክሞ ወደ ወንዝ ወረደ። ቀጥሎ የፍየሉን ደም ስር በጥሶ እንዲያደማ ታዘዘ። የፍሉን ደም ስር ለመበጠስ ስለት መጠቀም አይፈቀድለትም፥  መበጠስ ያለበት ጥርሱ ነው።

በበርቱ ትግል ፍየሉን ማድማት ተሳካለት።

ፍየሉ እንዲታረድ ከተደረገ በኋላ በአሸዋ የመታጠብና በውሃ የመነከር  ትርዒቱ ቀጠለ። ከአሸዋና ውሃ መነከር ድርጊት ቀጥሎ በፍየሉ ደምና ፈርስ ታጠበ።

ከጠቦቱ ስጋ አንዳች አልቀመስም። የዚህ ሰበቡ መናፍስታዊ እምነት ነበር። ፍየሉ የብላቴናውን ልክፍት ስለወሰደለት ስጋዋን ቢበላ ልክፍቱ ዳግመኛ ያገኘዋል በሚል እምነት ነበር ከመብል የተከለከለው።

ታዳጊው ልጅ ከገደል ራሱን ወርውሮ ስለመግደል ያሰበበት ወቅት ነበር። ሆኖም ከገደሉ ከወደቀ በኋላ ሳይሞት ቢቀር ለዘመናት በአካል ጉዳተኝነት ሊሰቃይ እንደሚችል በማመን ሃሳቡን ሰርዞታል።

ከሐገር ቤት ወደ አዲስ አበባ ካቀና በኋላ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል። በሰው ቤት በአሽከርነት በሚሰራበት ወቅት ተደብድቧል፥ ደግሞም የላቡን ውጤት ተከልክሎ ያውቃል።

ይህ ብላቴና ከአመታት በኋላ ይህን ሁሉ  ውጣ ውረድ አልፎ ታላቅ የወንጌላውያን አገልጋይ ሆኗል። ያለፈ ስቃዩን ሲያስታውስ "ልጅ ሳለሁ ለኔ የተመደበው ሰይጣን ረቂቁ ሳይሆን ጨቋኙና አምባገነኑ ይመስለኛል" እያለ ይቀልዳል።

ይህ ታሪክ የስመ ጥሩው አገልጋይ ፓስተር ታምራት ሃይሌ የልጅነት ህይወት ነው!

ማጣቀሻ መፅሐፍ ፥ ፓስተር ታምራት ሃይሌ "የታምራት አምላክ ታምረኛ"


© ተስፈኣብ ተሾመ