የሰለፍያ ደዕዋ በቻግኒالدعوة السلفية فى مدينة الشاغنى
693 subscribers
656 photos
56 videos
166 files
2.02K links
ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot

ይፃፉልን። ይላኩልን።
Download Telegram
Forwarded from «ሰለፎችን እንከተል» channel (abdurahman(አቡ ፉዶይል))
ወንድም እህቶቼ

🔶መስጅድ ስንገባ ጫማችንን በፔስታል ይዘን እንገባለን ወይም የሚጠብቅ ካለ እንሰጣለን፣......... ይሄ ሁሉ ጥንቃቄ ጫማችን በሌባ እንዳይሰረቅ ነው!!! ጡሩ።
አቂዳችንና መንሃጃችንስ እንዳይሰረቅ ምን እያደረግን ነው
እኔ ከታዘብኩት ላካፍላችሁ፦
⛔️ምኑንም የማያውቁትን ሰው ፣ በሚድያ ብቻ ድምፁን ሰምተው ወደውት አቂዳና መንሃጃቸውን አሳልፈው የሰጡ ብዙ ሰወች አሉ‼️ በቃ ዓሊም ይሁን መሃይም ይሁን ምኑንም ሳያውቁ ሚድያ ላይ የዘለለንና የጮኸን እንደጅራት የሚከተሉ በጣም ብዙ ናቸው‼️ በተለይ በተለይ ውጭ ሃገሩ ያሉ እህቶቻችን (ሁሉም)አይደሉም ግን አብዛኞቹን በሚባል ደረጃ ምንም አያውቁም 👉 ኪታብ አይደለም ቁርአን ያልጀመሩ ግን በአፈቅቤ ወንዶች ተሸውደው የሱን ጀልባ ተሳፍረው እየነጎዱ ነው።

ዓላመቱ ሷሊህ አል'ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንድህ ይላሉ፦

#አንተ

አንተ ሸቀጣሸቀጥ ለመግዛት ስትፈልግ ፤ መኪና ለመግዛት ስትፈልግ ወይም ሌላ ትንሽ ነገር ለመግዛት ፈልገህ ሰለዛ እቃ ምንም እውቀት ከሌለህ #ተሳስተህ_የማይሆን ነገር እንዳትገዛ #ፈርተህ ስለዛ እቃ #ወደሚያወቅ_ሰው_ሄደህ_ትጠይቃለህ!!!👈ይሄ በዱኒያዊ ጉዳይ ነው። 👉 #በድንህ_ጉዳይ #ለምንድነው አዋቂወችን፣ አላህን የሚፈሩትን ፣የእውቀት ባለቤቶችን #የማትጠይቀው

#ለዱኒያህ_እየመረመርክ_ለድንህ_ለምድነው_የማትመረምረው»

ምንጭ፦ሚን አዳቢ አል'ሙፍቲ
ወአል'ሙስተፍቲ

⛔️ በቃ የወደዱትን ሰው ሌላ ሰው በመረጃ ጥፋቱን ቢናገርም በቃ ተናጋሪው ማንም ይሁን‼️ ለምን ዓሊም፣ ሸይኽ አይሆንም አውርደው ከመፈጥፈጥ ወደሗላ አይሉም‼️ ምን ያክል ተዓሱብ እንዳሰከራቸው በግልጽ እያየነው ያለ ጉዳይ ነው። ደግሞ ወደሰለፊያ (የውሸት)መጠጋታቸው ነገሩን ይበልጥ አስጠሊታ ያደርገዋል። ለምን ካላችሁ ሙሪድነት ሰለፊያ ላይ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ስለሆነ ነው።

⛔️ ከወንዶች ደግሞ እዚህ ሚድያ ላይ የታዘብኩት👉 ፉላን የነቃ ነው ፣ እሱ ትንሽ እውቀት አለው ፣ አስተዋይና በሳል ነው፣........ ብለን የምናስባቸው የተመዩዕ ፊትና ስትመጣ ብጥስጥሳቸው ወጥቶ ፣ ሹቡሃ ጠራርጎ ወሰዳቸው። በዚህም አልበቃቸውም ሰለፊያን ከጠላቶቿ ጎን ቆመው መዋጋት ጀመሩ‼️
ለካ ተሳስተን ነበር ብለናል።


وَتَحْسَبُهُمْ أَيْقَاظًا وَهُمْ رُقُودٌ ۚ

እነሱም የተኙ ሆነው ሳሉ (ዓይኖቻቸው በመከፈታቸው) ንቁዎች ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ፡፡

ሱራ አል'ካህፍ:18

↪️ ይሄን ያክል ርቀት የተጓዛችሁለት ሰው የሰለፊያን የማይቀማ ሰርቲፊኬት ማነው የሰጠው አወ በፊት ሰለፊይ ሊሆን ይችላል!!! ታድያስ በህይወት ያለ ሰውኮ ፊትና አይታመንለትም!!! ሊጠም ይችላል በል እንዳውም ከሃድም ሊሆን ይችላል‼️ ታድያስ ማነው ግለሰብ ላይ ተጣበቁ ያላችሁ

🔰ዓበደላህ ኢብኑ መስዑድ ረድየላሁ ዓንሁ እንድህ ብለዋል፦

«ሰዎችን መከተል የፈለገ የሞቱትን ይከተል፡፡ በህይወት ያለው ፈተና ላይ ላለመውደቁ ዋስትና የለም፡፡ እነዚያ የሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰሐቦች ከዚህ ኡማ በላጭ ህዝብ ነበሩ፡፡ ቅን ልቦና ያላቸው፣ እውቀታቸው የጠለቀ፣ መፈላፈል የማያበዙ ነበሩ፡፡ አላህ የሱን ነብይ እንዲጎዳኙ፣ ዲኑን እንዲያቃኑ የመረጣቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ደረጃቸውን እወቁላቸው፡፡ ትውፊቶቻቸውን ተከተሉ፡፡ በተቻላችሁ ስነ-ምግባራቸውንና ዲናቸውን አጥብቃችሁ ያዙ፡፡ ምክኒያቱም እነሱ ቀጥ ያለው ጎዳና ላይ ነበሩና፡፡»

📚 [(ጃሚዑል በያን፡ 2/97) ሊ ኢብኒ ዐብዱልበር]

ሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ እንድህ ብለዋል፦

« ሸይኽን ወይም ዓሊምን እሱ የሚለውንና የሚሰራውን በሙሉ በመከተል የያዘ ሁሉ ከረሡል ዓለይሂ ሶላት ወሰላም ውጭ ከእሱ(ከሸይኹ ወይም ዓሊሙ) #ጋር_የተስማማን_የሚወዳጅ_ከሆነ‼️‼️‼️#ከሱ_ጋር_የማይስማማን_ጠላት_የሚያደር_ከሆነ‼️‼️‼️#እሱ_ሙብተድዕ_ጠማማ_ነው👉ከኪታብና(ከቁርአን) ከሱና ያፈነገጠ ነው»

📚ጃሚዑ አልመሳኢል:7/464

#በህይወት_ያለ_ሰው_ፈተና_አይታመንለትም

ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ እንድህ ብለዋል፦
↪️ « #በፊት_በትክክለኛው_አቂዳ ቀጥ ብለው #በሗላ_ግን_የሚፈተን ስንትና ስንት ሰው አለ?
#ይሄን ጊዜ #ቀጥ_ብሎ_በነበረበት ሁኔታ #ተከትለኸው ፣ እሱ በሄደበት ሄደህ#መሪ_አድርገህ_ይዘኸው!!! #አንተ_በእሱ ላይ #እምነት_አሳድረህ #አንተ_ሳታውቅ_ሊያፈነግጥ_ይችላል‼️ይሄን ጊዜ #አብረኸው_ትከስራለህ‼️በህይወት ያለ ሰው ፊትና አይታመንለትም»

📖ሸርሁ አል'ዓቂደቱ አል'ተድሙሪያ:20


https://t.me/nu_selefochin_enketel