የሰለፍያ ደዕዋ በቻግኒالدعوة السلفية فى مدينة الشاغنى
681 subscribers
652 photos
56 videos
165 files
1.98K links
ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot

ይፃፉልን። ይላኩልን።
Download Telegram
أرجو عدم السرعة في القراءة بالله أقرأوا بكل تأني وتأمل ودقة
( وصية الله لرسله )
ሳትፈጥኑ በመረጋጋትና በማሰተንተን እንደምታነቡት ተስፋ አደርጋላሁ።
# የአሏህ ምክር /ትእዛዝ) ለመልክተኞቹ
( عليهم الصلاة والسلام)
* أوصى الله عيسى بالصلاة وهو في المهد صبيًا.
لكم أن تتخيلوا وليدًا في مهده يقول: (وأوصاني بالصلاة)!
አሏህ ኢሳን ( አለይሂ አስሰላም) በአንቀልባ ላይ ሁኖ በሶላት አዘዘው።
አስተዉሉት በአንቀልባ ያለ ልጅ
" በሶላት አዘዘኝ"
ይላል።
انها الصلاة
* ምክንያቱም ጉዳዮዋ ሶላት ነች።!!!
* لما نهى شعيبٌ – عليه السلام– قومه عن الشرك وعن الفساد الاقتصادي
ነብዮሏህ ሹአይብ
(አለይሂ አስሰላም) ህዝቦቹን ከሺርክና ከኢኮኖሚያዊ ውድመት ሲከለክላቸው:
(قَالُوا يَا شُعَيْبُ أَصَلَاتُكَ تَأْمُرُكَ أَن نَّتْرُكَ مَا يَعْبُدُ آبَاؤُنَا أَوْ أَن نَّفْعَلَ فِي أَمْوَالِنَا مَا نَشَاءُ ۖ )
(«ሹዐይብ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚገዙትን ጣዖታት እንድንተው ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መሥራትን (እንድንተው) ታዝሃለችን!)»
* أرأيت بمَ يُعرف المصلحون؟
وماذا يعظِّمون؟!
አስተካካዮች/መካሪዎች/ በምን እንደሚታወቁና ምንን እንደሚያከብሩ ተመለከትክን?!
انها الصلاة!!!
* ምክንያቱም ጉዳዮዋ ሶላት ነች።!!!
* يترك إبراهيمُ عليه السلام أهله في صحراء قاحلة،
ኢብራሂም (አለይሂ አስሰላም) ደረቅ በሆነ በረሀ ቤተሰቡን ትቶ
ثم يقول:
("ربنا إني أسكنت من ذريتي بواد غير ذي زرع عند بيتك المحرم ربنا ليقيموا الصلاة"!)
(«ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤትክ (በካዕባ) አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ፡፡ ጌታችን ሆይ! ሶላትን ያቋቁሙ ዘንድ (አስቀመጥኳቸው»)
ይላል።
انها الصلاة
* ምክንያቱም ጉዳዮዋ ሶላት ነች።!!!
* يأتي موسى لموعدٍ لا تتخيل العقولُ عظمته، فيتلقى أعظمَ أمرين:
ሙሳ ከበሬታው በአዕምሮ ሊቀረፅ የማይችል የሆነ ታላቅ ወደ ሆነው ቀጠሮ ሲሄድ፣ ሁለት ታላላቅ ጉዳዮችን ለመቀበል ሲሄድ:
قال الله تعالىٰ
(إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي)
«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡»
انها الصلاة!
* ምክንያቱም ጉዳዮዋ ሶላት ነች።!!!
* ما أجلَّ هذا الوحي!
ይህን ወህይ ምን የላቀ አደረገው!!
("وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ وَأَخِيهِ أَن تَبَوَّآ لِقَوْمِكُمَا بِمِصْرَ بُيُوتًا وَاجْعَلُوا بُيُوتَكُمْ قِبْلَةً وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ ۗ ")
("ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡- «ለሕዝቦቻችሁ በምስር (በግብፅ) ቤቶችን ሥሩ፡፡ ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ፡፡ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡")
انها الصلاة!
* ምክንያቱም ጉዳዮዋ ሶላት ነች።!!!
* سليمان–عليه السلام– يضربُ أعناقَ خيله وسوقَها؛ لأنها أشغلته عن صلاة العصر
"حتى توارت بالحجاب"!
ሱለይማን (አለይሂ አስሰላም) ከአሱር ሶላት ቢዚ ስላደረጉት፣ፈረሶችን አንገት አንገታቸውንና እግር እግራቸውን ይመታቸው ነበር።
"ፀሀይ በግርዶ እስከ ተደበቀች ድረስ"
انها الصلاة!
* ምክንያቱም ጉዳዮዋ ሶላት ነች።!!!
* بالله عليك!
ما حالي وحالك عند فوات الصلاة؟!
በአሏህ ይሁንብህ እኔና አንተ ሶላት ሲያልፈን እንዴት ነው ባህሪያችን?!
أين جاءت بشرى الولد لزكريا بعد أن بلغ من الكبر عتيّا؟!
"فنادته الملائكة وهو قائمٌ (يصلي) في المحراب"
قائمٌ يصلي!
ለዘከርያ የእድሜ ጣራ ላይ ሁኖ የልጅ ብስራት የመጣለት የት ሆኖ ነው?!
" እሱ በሚህራቡ ውስጥ ቁሞ እየሰገደ ሳለ መላኢኮች ጠሩት"
* አስተውል "ቁሞ እየሰገደ"!!
انها الصلاة!
* ምክንያቱም ጉዳዮዋ ሶላት ነች።!!!
* يُشغل الكفارُ رسول الله ﷺ عن صلاة العصر؛ فيدعو عليهم دعاءً مرعبًا!
"ملأ الله قبورهم وبيوتهم نارًا كما شغلونا عن الصلاة"!
……ከሀዲያኖች ረሱልን ﷺ ከአሱር ሶላት ቢዚ ሲያደርጎቸው፣ አስፈሪ ዱአ/ እርግማን/ አደረጉባቸው።!
" ከሶላቷ (ከአሱር) እንዳዘናጉን/ቢዚ/ እንዳደረጉን ቀብሮቻቸውንና ቤቶቻቸውን አሏህ እሳት ይሙላው !
انها الصلاة!
* ምክንያቱም ጉዳዮዋ ሶላት ነች።!!!
* ما قُرِنت عبادةٌ في القرآن بعبادات متنوعة كالصلاة، فإنها قرينة الزكاة، والصبر، والنسك، والجهاد، وغير ذلك!
በተለያዮ ኢባዳዎች እንደሶላት የተቆራኘች ኢባዳ የለችም።
እሷ(ሶላት):ከዘካ፣ከሶብር፣ከሀጅ፣ከጂሀድ እና ከሌሎችም ኢባዳዎች ጋር ተቋራኝታለች።
…… انها الصلاة الصلاة الصلاة..
ምክንያቱም እሷ
ሶላት ሶላት ሶላት ነች!!
لو علمت عن أول سؤال سيأتيك فى الامتحان لاجتهدت فى حفظه
فلماذا لا تحافظ على صلاتك
وأنت تعلم أنها أول ما ستسأل عنه يوم القيامة‎
ፈተና ላይ መጀመሪያ የምትጠየቀውን ብታውቅ ያንን በመሸምደድ ላይ ጥረት ባደረክ ነበር።!
በሶላትህ ላይ ለምን አትጠባበቅም!
የቂያማ ቀን መጀመሪያ ስለ ሶላት እንደምትጠየቅ እያወቅክ!!
#في جهنم ثلاثة وديـان :
1 وادي غي
2 وادي ويل
3 وادي سقر
ጀሀነም ውስጥ (3)ሶስት ሸለቆዎች አሉ:
1, ሸለቆ ገغይ
2, ሸለቆ ወይል
3، ሸለቆ ሰቀር
— وادي غي / هو وادي لمن يجمع الصلوات في صلاة واحدة
قال تعالى في سورة مريم
{ فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ ۖ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا (59)
—ሸለቆ ገغይ :–
ሶላቶችን በአንድ ጊዜ ጠቅልሎ ለሚሰግድ።
አሏህ እንዲህ አለ:—
(" ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡)
وهذا الوادي تستعيذ منه جهنم كل يوم ، من شدة حرارته ، فهل يتحمله’ بـشر !؟
ይህ የጀሀነም ሸለቆ ከአቃጣይነቱ የተነሳ ጀሀነም ከእሱ በየእለቱ ትጠበቃለች፣ የሰው ልጅ ሊሸከመው ይችላልን ! !?
— وادي ويل /
وادي للذي يـؤخر الصلوات بدون عذر
قال تعالى في سورة الماعـون :
{ فَوَيْلٌ لِلْمُصَلِّينَ الَّذِينَ هُمْ عَنْ صَلاتِهِمْ سَاهُونَ} .
— ሸለቆ ወይል:
ያለ ሸሪአዊ ምክንያት ሶላትን ለሚያዘገይ
አሏህ እንዲህ አለ:—
("ለሰጋጆች ወዮላቸው(ወይል የጀሀነም ሸለቆ አለባቸው) እነዚያ እነሱ ከሶላታቸው ዝንጉ የሆኑት")
— وادي سقر /
وهو وادي لتارك الصلاه
حيث قال تعـالى :
{ مَا سَلَكَكُمۡ فِی سَقَرَ ۝٤٢ قَالُوا۟ لَمۡ نَكُ مِنَ ٱلۡمُصَلِّینَ }
ሸለቆ ሰቀር:—
ሶላት ለተወ ሰው የጀሀነም ሸለቆ ነው።
አሏህ እንዲህ ስላለ:—
("ሰቀረ ጀሀነም ውስጥ ምን አስገባችሁ!? (እነሱም)አሉ ከሰገጆች አልነበርንም")
" اللهم لا تجعل الدنيا أكبر همنا ولا مبلغ علمنا، اللهم ردنا إليك رداً جميلاً.
አሏህ ሆይ! ዱንያን ትልቅ ሃሳባችን፣ትኩረታችንና የእውቀታችን ጫፍ፣አለማ አታድርግብን።
አሏህ ሆይ! መልካም የሆነ መመለስን ወደ አንተ መልሰን።

📝 አቡ ጃቢር ሙሐመድ

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni

አስተያየታችሁን 👇ወይም 👇እርማታችሁን👇
t.me/selefiyadawabechagnibot
🍂 آداب الجماع 🍃

👈قال ابن قدامة رحمه الله: ويستحب أن يلاعب امرأته قبل الجماع لتنهض شهوتها، فتنال من لذة الجماع مثل ما ناله.

👈قلت : تقبلها وتغمزها وتلمزها، فإذا رأيت أنه قد جاءها مثل ما جاءك واقعتها فإن فرغ قبلها كره له النزع حتى تفرغ،

⬅️👈لما روى أنس بن مالك، قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: ( إذا جامع الرجل أهله فليقصدها ثم إذا قضى حاجته فلا يعجلها حتى تقضي حاجتها )، ولان في ذلك ضررا عليها دفعا لها من قضاء شهوتها.

⬅️وينبغي للزوج إذا عزم على الاجتماع بأهله أن يتحرز بما يفعله بعض العوام، وهو منهي عنه، وهو أن يأتي زوجته على غفلة، بل حتى يلاعبها ويمازحها بما هو مباح مثل الجسة والقبلة، وما شاكل ذلك، حتى إذا رأى أنها قد جاءت شهوتها فحينئذ يأتيها، وذلك أن المرأة تحب من الرجل ما يحب منها، فإذا أتاها على غفلة قد يقضي هو حاجته وتبقى هي، فقد يؤذيها ذلك.

👈ويراعي الآداب الآتية في الجماع:

👈1. أن لا يجامع زوجته وهي في ثيابها، بل حتى تنزعها كلها، وتدخل معه في لحاف واحد، وللرجل أيضا أن يتجرد من ثيابه بشكل عادي وبصورة تدريجية كي لا تفاجأ المرأة.

👈ولا شك أن التجرد من الثياب فوائده منها أن فيه راحة البدن من حرارة النهار، ومنها سهولة التقلب يمينا وشمالا، ومنها ادخال السرور على الأهل وزيادة التمتع. وقال ابن مأمون في قصيدته:

👈واحذر من الجماع في الثيـاب فهو من الجهل بلا ارتياب، بل كل ما عليها صاح ينــزع وكن ملاعبا لها لا تفزع

👈2. ينبغي لمن يدخل بزوجته البكر أن لا يعزل عنها كما يفعل بعض الناس، ( والعزل هو أن يخرج عضو الذكورة قرب الإنزال فينزل المني بالخارج)، وعليه ألا ينزع إلا بعد الإنزال، وذلك كي يسارع ماؤه إلى رحمها، لعل الله يجعل له من ذلك ذرية ينفعه بها.

👈3. ثم إذا أنزل الرجل قبل زوجته فعليه أن لا ينزع بل عليه أن يتمهل حتى تنزل هي.

👈4. ليس هناك عدد محتوم في مرات الجماع للرجل والمرأة على السواء ولكنه يخضع كثرة أو قلة للمزاج والقدرة والضرورة والظروف الصحية والنفسية والاجتماعية.

👈5. يكره للزوج أن يأتي امرأته من غير أن تطيب نفسها بذلك، وكذلك أن يأتيها على غفلة، لأن ذلك يفسد عليها دينها وعقلها.

👈7. يحرم على الزوج أن يأتي زوجته جاعلا بين عينيه غيرها، لأن ذلك نوع من أنواع الزنا، وكذلك يحرم عليها.

👈8. الجماع جائز في كل الشهور والاوقات والأيام، وفي كل ساعة من الليل أو النهار إلا في فترات الحيض والنفاس والإحرام والصيام.

👈9. يستحب للزوجين أن يغسلا أسنانهما ثم يطيب الفم بطيب فائح لأن ذلك أدعى إلى الالتصاق والعناق ويؤدي إلى المحبة.

👈10. إذا أتى الرجل زوجته، ثم أراد أن يعاود الجماع فعليه بالوضوء ، لقوله صلى الله عليه وسلم: (إذا أتي احدكم أهله ثم أراد أن يعود فليتوضا وضوءه للصلاة، فإنه أنشط للعود).

👈11. إذا أرادا النوم وهما جنبان فعليهما بالوضوء أيضا فعن عائشة رضي الله عنها قالت: ( كان رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا أراد أن يأكل وينام، وهو جنب غسل فرجه وتوضأ وضوءه للصلاة).

👈12. يجب الاغتسال من الجماع قبل الصلاة والاغتسال قبل النوم أفضل لحديث عبدالله بن قيش رضي اله عنه سألت عائشة قلت: كيف كان صلى الله عليه وسلم يصنع في الجنابة؟ أكان يغتسل قبل أن ينام، أم ينام قبل أن يغتسل؟ قالت: كل ذلك كان يفعل ربما اغتسل فنام وربما توضأ فنام قلت: الحمد لله الذي جعل في الأمر سعة.

👈13. يجوز للعروسين أن يغتسلا في مكان واحد، ولو رأى منها ورأت منه ، فعن عائشة رضي الله عنها قالت: كنت أغتسل أنا ورسول الله صلى الله عليه وسلم في إناء واحد بيني وبينه، تختلف أيدينا فيه، فيبادرني حتى أقول: دع لي..دع لي. قالت: وهما جنب وقبل كل ذلك لا تنسوا الدعاء عند بدايه الجماع بسم الله الله جنبنا الشيطان وجنب الشيطان ما رزقتنا

نسأل الله أن ينفع بها المسلمين عامة
👉 ሺዓዎችና ዓሹራእ

ዓሹራእ ሲታወስ በዋነኝነት የሚታወሰው የሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ከርበላእ ላይ መገደል ነው ። ሑሰይን ከርበላእ ላይ የተገደለው ሙሐረም 10/61ኛው አመተ ሂጅሪያ ላይ ነበር ።
የሑሴይን መገደል መንስኤ የነበረው ለየዚድ ኢብኑ ሙዓዊያ ኢብኑ አቡ ሱፍያን ሙባየዓ አላደርግም ማለቱ ነበር ። በኢስላም ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው የሐሰን ኢብኑ ዐልይ ለሙዓዊያ የመሪነቱን ቦታ መልቀቁ ( ተናዙል ) ማድረጉ ነው ። ዑስማን ኢብኑ ዐፋን በዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አል የሁዲይ የተንኮል መረብ ከተገደለ በኋላ ዐልይ የኸሊፋነቱን ቦታ በሶሓቦች ግፊትና ውትወታ ተረክቦ ሁኔታዎችን ለማረጋጋት እየሰራ ባለበት ወቅት ሙዓዊያ የሻም ዋሊ ( አስተዳደር ) ነበርና ለዐልይ የዑስማን ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥያቄ ያቀርባል ። ዐልይም መጀመሪያ ሙባየዓ ማድረግ እንዳለበትና ሁኔታዎች ከተረጋጉና ገዳዮቹ በህዝብ ውስጥ ተደብቀው ስላሉ መለየት በሚቻልበት ወቅት ለፍርድ እንደሚቀርቡ ይገልፅለታል ። ሙዓዊያም ምናልባት መዲና ያለው ሁኔታ ካልተረጋጋና አቅም ከሌለው ሀላፊነቱን ለሱ እንዲሰጠውና እሱ ገዳዮቹን ለፍርድ ሊያቀርብ በሚችልበት አቅምና አቋም ላይ መኖሩን በመግለፅ ይህ ሳይሆን ሙባየዓ እንደማያደርግ ለዐልይ ይገልፅለታል ። ይህ አለመግባባት ሳይፈታ ዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ ዐብዱራሕማን ኢብኑ ሙልጂም በሚባል ኻሪጂ ይገደላል ። በቦታው ሐሰን ኢብኑ ዐልይ ሙባየዓ ተደረገለት ኸሊፋም ሆነ ። ነገር ግን ከሙዓዊያ ጋር የነበረው አለመግባባት በቀላሉ የሚፈታ አልነበረምና ሐሰን ለሙዓዊያ መሪነቱን አስረከበ ።
ይህ የሐሰን ተግባር ለሑሰይን አላስደሰተውም ። ነገር ግን ታላቁ ነውና ምንም ማድረግ አልቻለም ለሙዓዊያ ሙባየዓ አደረግ ። በዚህም ሀገር ሰላም ሆነ ሙስሊሞች ኡፈይ አሉ ። በዚህ ሁኔታ ነገሮች እየሄዱ እያሉ ሙዓዊያ መሪነቱን ለልጁ የዚድ አሳልፎ ሰጠ ። የዊላያት መሪዎችና የጦር አዛዦች እንዲሁም ታዋቂ ሶሓባዎች ለልጁ ሙባየዓ እንዲያደርጉ ጠየቀ ። ሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ለየዚድ ሙባየዓ እንደማያደርግ ግልፅ አደረገ ። በዚህን ጊዜ የዚድ ለመዲናው አስተዳዳሪ ከሑሰይን ሙባየዓ እንዲቀበልለት ትእዛዝ አስተላለፈ ። ሑሰይንም ሁኔታው ስላላማረው መዲናን ትቶ ወደ መካ ተሰደደ ። የዚህን ጊዜ ኢራቅ ያሉ የሙዓዊያ ተቋዋሚ ፋርሳዊያን ( ሺዓዎች ) ሑሰይንን ወደ እነርሱ እንዲመጣና መሪያቸው እንዲሆን መወትወት ጀመሩ ። ሑሰይንም ለመውጣት አሰበ የኩፋ ሰዎች በየቀኑ ወደ ሑሰይን ይልካሉ ። ይህ ሁኔታ ያላማረው የዚድ የሑሰይንን እንቅስቃሴ መከታተል ጀመረ ።
ሑሰይንም የአጎቱን ልጅ ሙስሊም ኢብኑ ዓቂልን ወደ ኩፋ ሄዶ ነገሮችን እንዲያጣራ ላከው ። ሙስሊም ኩፋ እንደደረሰ በጣም ጥሩ አቀባበል ተደረገለት ለሑሰይን ሙባየዓ አደረጉ ። የዚህን ጊዜ ለሑሰይን መምጣት እንዳለበትና ሙባየዓ እንደተደረገለት ገልፆ ላከለት ።
የዚድ የሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ኩፋ መግባትና ሰዎች ( ሺዓዎች ) ለሑሰይን ሙባየዓ እያደረጉ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድን የበስራና የኩፋ መሪ አድርጎ በመሾም ወደ ኩፋ እንዲሄድና የሆነውን ነገር አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ላከው ። ወደ መዲናና መካ የሚገኙ ትላልቅ ሶሓቦችም ሑሰይንን ወደ ኩፋ እንዳይወጣ እንዲመክሩትና ሙባየዓ እንዲያደርግ እንዲነግሩት መልእክት ላከ ።
ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ወደ ኩፋ እንደመጣ ለወታደሮች በጣም ከፍተኛ ስጦታ ሰጠ ። ታዋቂ ሰዎችን አስጠርቶ ከሱ ጋር እንዲሆኑ የፈለጉት ነገር እንደሚያደርግላቸው ካልሆነ ግን አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣቸው ገለፀላቸው ። ማንኛውም ሰው አዲስ ሰው እንዳያስጠጋ አስጠግቶ የተገኘ እርምጃ እንደሚወስድበት ተናገረ ። ቀጥሎ በስራና ኩፋ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ አዘዘ ። ማንኛውም አዲስ ሰው ከተገኘ ወደርሱ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ ። ቀጥሎ አሉ የተባሉ ታዋቂ ሰዎችን በተለያየ ጥቅማጥቅም በመያዝ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት እንዲያደርሱትና ከሱ ጎን የቆሙ ሰዎችን እንዲለዩለት አደረገ ።
ወዲያውኑ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት ቦታ ጦቀሙት ። ወደ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ጉዞ ቀጠለ ደረሰበትም ። ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል የተከሰተው ነገር ሲያይ ማመን አቃተው እነዚያ ቃል የገቡና ሑሰይንን እንዲያስመጣ ያዘዙት ሺዓዎች ክደውታል ። ዑበይዱላህ እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው አላደረገውም ተገደለ ። የሚቀጥለው ስራ የሑሰይንን መምጣት መጠበቅ ነው ። በተለያዩ መንገዶች ጠባቂ አደረገ ። ስለሙስሊም መገደል እንዳይደርሰው አደረገ ።
ሑሰይን ከመካ ወደ ኩፋ እንቅስቃሴ ጀመረ ። ትላልቅ ሶሓቦች እንዳይሄድ ከለከሉት ። ከእነዚህ ውስጥ : –
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር
– ጃቢር ኢብኑ ዐብዱላሂ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዙበይር
– አቡ ሰዒድ አል ኹድርይ
እና ሌሎችም ግን አልተሳካም ።
የሑሰይን መንቀሳቀስ ተሰማ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ 1000 ፈረሰኛ እሱን ለመጠባበቅ ላከ ። ሌላ ጦር ደግሞ ዑመር ኢብኑ ሰዕድን መሪ አድርጎ ላከ ። ለዚህ ጦር እጅ ከሰጠ ይዘው እንዲያቀርቡት ካልሆነ እንዲገሉት ትእዛዝ ሰጠ ። ሑሰይን ወደ ኩፋ በቀረበ ጊዜ የአጎቱ ልጅ መገደል ፣ የኩፋ ሰዎች ከዑበይዱላህ ኢብኑ የዚድ ጎን መቆማቸውንና የአጎቱን ልጅና እሱንም እንደካዱዋቸው የሙስሊም ኢብኑ ዑቅባ ደጋፊዎች ሀኒእ ኢብኑ ዑርዋን ጨምሮ ሁሉም መገደላቸውን ሰማ ። ብዙም ሳይቆይ ከዑመር ኢብኑ ሰዕድ ጦር ጋር ተገናኘ ። እነዚያ ወትውተው ከመካ ያስወጡት ሺዓዎች አዘጋጅተው ለጅብ ሰጥተውታል ።
የዚህን ጊዜ ከሱ ጋር ያሉትን ማስጨረስ አልፈለገም ሙሉ በሙሉ ሀሳቡን ቀይሮ ሶስት አማራጭ ለዑመር ኢብኑ ሰዕድ አቀረበለት ። አማራጮቹ የሚከተሉት ነበሩ : –
– እንዲተውትና ወደ መካ እንዲመለስ
– ወደ ድንበር ሄዶ እንደማንኛውም ሙስሊም ድንበር እንዲጠብቅ ( ሀገር ጠባቂ ወታደር እንዲሆን )
– ወደ ሻም ሄዶ ከየዚድ ጋር ተነጋግሮ እንዲግባባ የሚል ነበር ።
ዑመር ይህን ሲሰማ በጣም ደስ ብሎት ለዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ላከለት ። ይሁን እንጂ በሙስሊሞች ደም የሚታጠበው ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ እጅ ካልሰጠ እንዲገድለው አዘዘ ። ዑመር ለሑሰይን እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው ሑሰይንም አይደረግም አለ ። በሙሐረም 10 ኛ ቀን በ61ኛው አመተ ሂጅሪያ ሺዓዎች ከመካ መሪያችን ሁን ብለው አውጥተው ከርበላእ ላይ እንዲገደል አደረጉት ።
ይህን ቀን ነው ሺዓዎች ከርበላእ ላይ ራቁታቸውን ሆነው ራሳቸው እየገረፉ ለሑሰይን ሞት ሐዘን እያሉ ያ ሑሰይን ብለው የሚጮኹት ።

https://t.me/bahruteka
Forwarded from አብራር አወል ( Abu ubeyda) (Medresetu bilal ibni rebah የሱና ብርሐን መፍለቂያ https://t.me/bilalibnu https://t.me/AbraribnAwal)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☆ تلاوات الشيخ خالد الجليل ☆

‏﴿إِنَّ اللهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾

🎙القارئ : #خالد_الجليل

📖الأحزاب ۝ ٥٦
የጁምዓ ቀን ሱናዎች

❶ኛ ገላን መታጠብ።
➋ኛ ሽቶን መቀባባት እና መዋብ።
❸ኛ ሲዋክን /መፋቂያን መጠቀም።
❹ኛ የክት ልብስ መልበስ።
❺ኛ በጊዜ መስጂድ መጓዝ።
❻ኛ በእግር እየተጓዙ ወደ መስጅድ መሄድ።
❼ኛ መስጂድ ከደረሱ በኋላ የሰዎችን ትከሻ በመረማመድ ሰዉን አለማስቸገር።
❽ኛ ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ተህየቱ መስጂድ መስገድ።
❾ኛ ኹጥባ ወደ የሚያደርገው ኢማም መዞርና እሱን እያዩ ኹጥባ ማድመጥ።
❿ኛ ኹጥባ በሚደረግበት ሰዓት ፀጥታን መላበስ።
⓫ኛ ሰደቃን ማብዛት።
⓬ኛ ከሀሙስ ማታ ጀምሮ እሰከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱ ከሕፍ መቅራት።
⓭ኛ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሰዓትን መጠባበቅ።
⓮ኛ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን በብዛት ማውረድ።

https://t.me/AbraribnAwal
https://t.me/AbraribnAwal
Audio
خطبة الجمعة. خطورة الشرك باالله. أبو جبير.m4a

10 محر (١٠) ١٤٤٥. 21/11/2015
خطبة الجمعة
ب« عنوان» "خطورة الشرك باالله."
የጁመዐ ኹጥባ:
ርዕስ:—
" በአሏህ የማጋራት አደገኚነት"

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 6.9MB

እርዝመት :—29:28

በአቡ ጁበይር.

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni
#ቀጥ_በል_አደራ!!!
【————————】

በአላህ ትዕዛዝ በሰለፎች ፋና
በማይቀየረው በተውሒድ በሱና
ፈተናውን ታገስ በሀቅ ላይ ፅና
☑️☑️☑️☑️
መከራው ቢበዛም በስቃይ መታሸት
መለየቱ አይቀርም እውነትና ውሸት
ፍርዱን ታገኛለህ ስትቆሙ አላህ ፊት

https://t.me/AbuImranAselefy/7208
Audio
🟢 የተውሂድ ጀግኖቹ የደዕዋ ገድል 1⃣

👉ሙሳ እና ወንድማቸው ሃሩን (ዐለይመሰላም)
سورة الشعراء:
ከቁጥር 10 እስከ 68

👉ቲላዋ ከአጭር ማብራሪያ ጋር


ቲላዋውን ለማዳመጥ⤵️
https://t.me/Alkuraan_Wasuneh/6951

ይቀጥላል ⚫️🔘🔘
https://t.me/Alkuraan_Wasuneh
༘ ⃝ི⃕

قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله :

‏خُذ من حياتك الآن ما دمت حيًّا لموتك لأنك سوف تبقى أزمانًا طويلة بعد الموت لا تستطيع أن تعمل، لكن ما دمت حيًّا فاعمَل

[شرح البلوغ]

⃝༘⃕ ➥ https://t.me/Effectgood

انشر تؤجر فالدال على الخير كفاعله........

قناتنا علـ/يوتيوب ↲ https://youtube.com/@user-ol1dj3fs9d
🚫 ከሰጋጆች ስህተቶች
❨¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯❩


ብዙ አባቶችና ወንድሞች ላይ ከሶላት ጋር የተገናኙ መስጂድ ሲገባ ጀምሮ በጀማዓም ይሁን በግል በሚሰገድበት ጊዜ የሚስተዋሉ ስህተቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ዱዓቶችና ኡስታዞችም ጭምሮ የሚሰሩዋቸው ይገኙበታልትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ግን ትኩረት ያጡ ሆነው ይስተዋላሉ። ከእነዚህ ሶላት ውስጥ ከሚታዩና ልናስተካክላቸው ከሚገቡ ስህተቶች ውስጥ፦
❶ኛ በሶላት ውስጥ አለመረጋጋት
♻️ ይህ የሶላት ሩክን ሆኖ ሳለ ብዙዎች ጋር የሚታይ ስህተት ነው። ሩኩዕ ላይ፣ ከሩኩዕ ቀና በሚባልበት ጊዜ (ኢዕቲዳል) ላይ፣ ስጁድ ላይ፣ በስጁድ መካከል መቀመጥ ላይና የመሳሰሉ ቦታወች ላይ መረጋጋት ግዴታ ነው። ካልሆነ ሶላት ያበላሻል።

❷ኛ እንቅስቃሴ ማብዛት
↪️ ይህ ኹሹዕ ከማጣት የሚመጣ ከሶላቱ ጋር በሚገናኝ ጉዳይና ሸሪዓዊ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በጣም የተጠላ ነው።

❸ኛ ኢማምን መሽቀዳደም
♻️ ኢማምን መከተል ግዴታ ሲሆን እሱን መሽቀዳደምና ቀድሞ መነሳት፣ ሩኩዕ ማድረግ፣ ከሩኩዕ ቀና ማለትና ከስጁድ መነሳት የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ሶላት ያበላሻሉ።

❹ኛ ኢማሙ የሁለተኛውን ተስሊም ሳይጨርስ ያመለጠን ለሞሙላት መነሳት

❺ኛ በንያ ድምፅ አውጥቶ መናገር
ንያ ቦታው ቀልብ ስለሆነ ድምፅ አውጥቶ መናገር አያስፈልግም

❻ኛ መስጂድ ገብቶ ኢቃም እስከሚባል ቆሞ መጠበቅ
♻️ አዛን ከተባለ በኋላ መስጂድ የገባ ሰው ወዲያውኑ ሁለት ረካዓ መስገድ ይኖርበታል። ነብዩ ﷺ በሁለት አዛኖች (በአዛንና ኢቃም መካከል ሶላት አለ) ስላሉ ቆሞ መጠበቅ አያስፈልግም። ቀብልያ ያለው ሶላት ሆነም አልሆነም ለተሒየቲል መስጂድ ለሱነተል ውዱእና ለሱናውም ይሆንለታል።

❼ኛ መስጂድ ገብቶ ኢማሙ ስጁድ ላይ ወይም ተሸሁድ ላይ ከሆነ ቆሞ መጠበቅ
ይህም በጣም ስህተት ነው። ኢማሙ ባለበት ሁኔታ ተከትሎ ያመለጠውን ኢማሙ ሲጨርስ ሞሙላት ነው ያለበት።

❽ኛ በስጁድና ሩኩዕ ላይ ቁርኣን መቅራት

ኛ አይንን ግራና ቀኝ ወይም ወደ ሰማይ ማድረግ
↪️ ሶላት በምንስግድበት ጊዜ ወደ ስጁድ ማድረጊያ ቦታ ማየት ነው የሚያስፈልገው። ሸይጣን ሶላታችንን እንዳይሰርቀን!

❿ኛ በሁለት እግሮች ተረከዝ ላይ ቁጭ ብሎ ስጁድ ላይ ሁለት እጆችን እስከ ክርን መሬት ላይ መዘርጋት

⓫ኛ በሚሰግድ ሰው ፊት ለፊት ማለፍ (ሶላት ማቋረጥ)

⓬ኛ ኢማሙ ሩኩዕ ላይ ሆኖ ደርሶ ተክቢረተል ኢሕራም ሳያደርጉ ጎንበስ ማለት
⓭ኛ ሶላት ላይ ዐይኖችን መጨፈን
⓮ኛ በስጁድ ላይ የእግር ጣቶችን ማንሳት
⓯ኛ ስጁድ ሲያደርግ መሬቱን መሳም
⓰ኛ ሶላት ላይ ሲቆም ቀኝ እጅ በግራ ላይ አድርጎ አንገት ስር ማውጣት
⓱ ስጁድ ሲወረድና ከስጁድ ቀና ሲል ሁለት እጆችን ማንሳት
⓲ኛ በግንባር፣ በሁለት መዳፎችና፣ በሁለት ጉልበቶችና በሁለት አውራ ጣቶች (በሰባት አካላት) ስጁድ አለመውረድ
ሴቶች ሽቶ ተቀብተው መስጂድ መምጣት
ሴቶች በሚሰግዱበት ጊዜ እግራቸውን አለመሸፈን

♻️ እነዚህ ከብዙ ስህተቶች ጥቂቶቹ ናኛቸው ራሴንና አማኞችን ለማስታወስ እነዚህን ጠቀስኩ። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን።

https://t.me/bahruteka
ሙብተዲዕን ያዳመጠ የአላህ ጥበቃ ይነሳበታል ።

قال محمد بن النضر الحارثي – رحمه الله – :

" من أصغى سمعه إلى صاحب بدعة، وهو يعلم أنه صاحب بدعة، نزعت منه العصمة، ووكل إلى نفسه ".

الإبانة (471)

🔹መሐመድ ኢብኑ ነድር አል ሓሪሲ – ረሒመሁላሁ – የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –

" ወደ ቢዳዓ ባለቤት የቢዳዓ ባልተቤት መሆኑን እያወቀ ጆሮውን ሰጥቶ ያዳመጠ የአላህ ጥበቃ ከሱ ላይ ይነሳል ። ወደራሱም ይጠጋል "።

↪️ አብዛኛዎች ሰለፍዮች ከቢዳዓ ባልተቤቶች መራቅ ሲባል በአካል አለመገናኘት ብቻ ይመስላቸዋል ። ይህ ትልቅ ስህተት ነው ። ከሙብተዲዕ መራቅ ሲባል በአካል መራቅን ፣ ትምህርቶቹን በማንኛውም መንገድ አለማዳመጥን ፣ ፁሑፎቹን አለማንበብን ፣ ከግሩፑም ይሁን ከቻናሉ መራቅን ያካትታል ።
ይሁን እንጂ ብዙ ሰለፍዮች የቢዳዓ ባልተቤቶች ናቸው ብለው የሀገራችን ዑለሞች ያስጠነቀቁዋቸውን ሰዎች ቻናል ተቀላቅለው የተለያዩ ፁሑፎችን ሲያነቡና ድምፆችንም ሲሰሙ ይታያል ለምን ሲባሉ ምን እንደሚል ለመስማት ነው ይላሉ !!!!!! ። ይህ ፍፁም የተሳሳተ ሀሳብ ነው ። ምክንያቱም ሀገራችን ውስጥ ያሉ ሙኻሊፎች የሚያሰራጩዋቸው ሹብሀዎች እራሳቸው ከትክክለኛ አቋም እንዲንሸራተቱ ያደረጉዋቸው ሹብሀዎች ናቸው ። በመሆኑም በፍፁም ለእንደዚህ አይነት የሸይጣን ጉትጎታ መንገድ መክፈት አያስፈልግም ። በመረጃ ያወቅነውን ዐቂዳና ሚንሀጃችን ካፒታላችን ነውና እንጠብቀው ።

https://t.me/bahruteka
Forwarded from سلفيَّة المنهج 🇸🇦
فإذا أعجبك عملٌ من الأعمال الصَّالحة الَّتي قمت بها تذكَّر هذه الأمور الثلاثة:
* الأول: تذكر ذنوبك الَّتي اقترفتها ومعاصيك التي ارتكبتها
عن مطرف بن عبد الله بن الشخير رحمه الله قال : «لأن أبيت نائمًا وأصبح نادما، أحب إليَّ من أن أبيت قائما فأصبح معجبا» رواه ابن المبارك في الزهد.

الثاني: تذكَّر أنَّك مقصِّرٌ حتَّى في هذا العمل الَّذي أنت معجبٌ به
قال الله عز وجل في وصف المؤمنين الكُمَّل: {وَالَّذِينَ يُؤْتُونَ مَا آتَوْا وَقُلُوبُهُمْ وَجِلَةٌ أَنَّهُمْ إِلَى رَبِّهِمْ رَاجِعُونَ}[المؤمنون

الثالث: تذكَّر أنَّ نِعَمَ الله سبحانه وتعالى عليك لا تُعدُّ ولا تُحصى
يوضِّح ذلك ما جاء في «الصَّحيحين» من حديث أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: ((لَنْ يُنْجِيَ أَحَدًا مِنْكُمْ عَمَلُهُ))، قالوا: ولا أنت يا رسولَ الله؟! قال: ((وَلَا أَنَا إِلَّا أَنْ يَتَغَمَّدَنِيَ اللهُ بِرَحْمَةٍ))، فهو صلوات الله وسلامه عليه أخشى النَّاس وأكملُهم عبوديَّةً له سبحانه وتعالى يقول هذا، فكيف بغيره؟!


الشيخ عبد الرزاق البدر
🪴
قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله :

فليس بين الله وبين خلقه صلة إلا بالتقوى ، فمن كان لله أتقى كان من الله أقرب، وكان عند الله أكرم؛ إذا لا تفتخر بمالك، ولا بجمالك، ولا ببدنك، ولا بأولادك، ولا بقصورك، ولا سياراتك، ولا بشيء من هذه الدنيا أبدا إنما إذا وفقك الله للتقوى فهذا من فضل الله عليك فأحمد الله عليه .

#رياض_الصالحين  ( 1 ، 61 )

https://t.me/mmmkkjjk
Audio
محضرة جديدة
አዲስ ሙሀደራ
ما أوجبه الله علينا من أخذ التوحيد والسنة.
ተውሂድን እና ሱናን በመያዝ አሏህ በእኛ ላይ ግድ ያደረገብን ነገር።

የተጠቀሱ ነጥቦች:–
— የላኢላሀ ኢለሏህ እና ሙሀመዱን ረሱሉሏህ ትርጉም
— ሱናን መከተልን ማነሳሳት
— ቢድአ እና ባለቤቶችም መራቅ፣ማስጠንቀቅ
— የቢደአ አደገኝነትና ከባባድ ጥፋቶች
— ሰለፎች ከቢድአና ከባለቤቶቹ ያስጠነቅቁ እንደመበር
— ከጥመት ሰዎች ማስጠንቀቅ የተጀመረው በረሱል
( صلى الله عليه وسلم) ስለመሆኑ
— እና የመሳሰሉ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 11.4MB

እርዝመት :—48:54

በአቡ ጁበይር.

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni
ሰዎችን በጭፍን አትከተል!!
—————
ሰዎች በሐቅ ይመዘናሉ እንጂ ሐቅ በሰዎች አይመዘንም!! የሀቅ እንጂ የሰዎች ጭፍን ተከታይ አትሁን!። ምክንያቱም የታዘዝከው ሐቅን እንጂ ሰዎችን እንድትከተል አይደለም!። በጭፍን ውዴታ ጥግ መድረስ አደጋ አለው። ጭፍን ተከታይ መሆን ሐቅ ከመቀበል ያውርሃልና ተጠንቀቅ!። በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም። አላህ ይጠብቀንና በጭፍን የተከተልከው ሰው ከተንሸራተተ አለያም ድንበር አላፊ ከሆነ አንተም አብረሀው ገደል ልትገባ ትችላለህና ጭፍን ተከታይ አትሁን!!።
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) “በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም” ብለዋል። በመሆኑም የሰዎች ጭፍን ተከታይ መሆንን ተጠንቀቅ። ወደ ቁል ቁል ሲወርዱ እንዳያወርዱህ፣ ድንበር ሲያልፉም በጭፍን ተከትለሃቸው እንዳታልፍ። የሰዎች ንግግር ትክክል ካልሆነ ተመላሽ ነው። ፍፁም የሆነውና ሊመለስ የማይችለው የመልእክተኛው ንግግርና ተግባር ብቻና ብቻ ነው።

ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ማለታቸውን አትዘንጋ:- "ሁላችንም ተመላሾችና የተናገርነውም የሚመለስ ነው የዚህ ቀብር ባለ ቤት ሲቀር።" አሉ። የቀብሩ ባለ ቤት በማለታቸው የፈለጉበት መልአክተኛውን ነው።
ሐቅን እወቅ! ከዚያም ሰዎችን በሀቅ ትመዝናቸዋለህ። የሀቅ ሰዎችንም ታውቃለህ። ሰዎችን አውቀህ በጭፍን የምትከተላቸው ከሆነ ግን የሐቅ መመዘኛ መሰረትህ ትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተገነባ ሳይሆን የሰዎች ጭፍን ውዴታና ጭፍን ተከታይነት ይሆንና ሲገለባበጡም አብሮ መገለባበጥ ይሆናል።

ቆም ብለህ አስተውል! ቡድንተኝነትና ጭፍን ውዴታ አያውርህ!። ነገ አላህ ፊት ወዳጅህ ጠላት ሊሆንብህ ይችላል። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ

«ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» አዝ-ዙኽሩፍ 67

ታዲያ ስትወድም ሆነ ስትጠላ በጭፍን አይሁን!። የወደድከው አቅጣጫ ከሳተና ለየት ያሉ ነገሮችን ካስተዋልክበት ቆም በል። በጭፍን መውደድም መጥላትም አደጋው የከፋ ነውና ተጠንቀቅ!!። ሳታስበው በሰለፊያ መንሀጅ ስም በተመሰረተ ልዩ በሆነ ቡድንተኝነትና ዘመናዊ ሙሪድነት አዘቅጥ ውስጥ እንዳትዘፈቅ!!። በጭፍን በውዴታው የከነፍከለት አካል መንገድ ከሳተ ተከትለሀው መሳትህ አይጠቅምህም! ከባድ አደጋ ነው። የሚጠቅምህ በየትኛውም ወቅት ሀቅን አጥብቀህ መያዝህ ነው!!።

በተለይ በፊትና ጊዜ ምንም ያህል በአንዳንድ መልካም ስራዎቹ የምትወደው በዳዒነት የገነነ ነገር ግን እውቀቱ እዚህ ግባ የማይባል የምትወደው ሰው ቢኖር እንኳ ጠንካራ ነጥቦች ሲነሱ፣ የሆነ ጊዜ "እኔ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን አንስቼ ለመናገር እውቀቴ አይፈቅድልኝም" እያለ በሌላ ጊዜ ደግሞ የእውቀት ደረጃው በማይፈቅደው አጀንዳ ውስጥ ገብቶ ሲዘባርቅ እያየሀው ስለ ወደድከው ብቻ በጭፍን መከተል የለብህም!።

በየትኛውም ወቅት የጠንካራ እውቀት ባለ ቤቶችን እና በዳዒነት የገነኑ ያለ እውቀት ደረጃቸው ተከታይ ስላላቸው ብቻ በድፍረት የሚናገሩና ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደፈለጉበት አቅጣጫ የሚዋዥቁ ያለ እውቀት ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ሐቅ በጋጋታና ከተለያየ አቅጣጫ በሚጮሁ በተደራጁ ቲፎዞዎች ጩሀት አይለካም!። እውነትን ቆም ብሎ በማስረጃ መለየት ነው እንጂ ጭፍን ተከታይ መሆን አደጋው የከፋ ነው!። ትላንት በጥሩ አቋምና በትክክለኛው መንሀጅ እያለ ጠላቶቹ የነበሩ ኢኽዋንን ጨምሮ "አይንህ ላፈር" የሚሉት ሰዎች ዛሬ እንዴት ወዳጆቹ ሊሆኑና እሱን ሊያደንቁ፣ ሊያሞግሱ እንደቻሉ? ቆም ብለህ ፈትሽ!!። እሱ ተለሳልሶ ከአቋሙ ሸርተት ብሎ ነው ወይስ እነሱ ወደ ትክክለኛው አቋምና መንሀጅ ተመልሰው ነው? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ያለፉ ሂደቶችንና በወቅቱ ያሉ ሂደቶችንም በተረጋጋና በገለልተኝነት መንፈስ ቃኝ!። እውነት ጭፍን ተከታይነትና ቡድንተኝነት ሳያውረው ከልቡ ለፈለጋት ሰው ግልፅ ትሆናለች!።

ታላቁ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ: -
ወላሂ! በጌታዬ ይሁንብኝ አላህ ዘንድ እገሌና አገሌ አይጠቅሙህም!። የሚጠቅምህማ በሀቅ ላይ መቆምህና ለሀቅና ለተከታዮቹ ረዳት መሆንህ ነው።” ረዱል ጀዋብ 54

»» ሐቅን ተከተል!። ለሸይኽ አሕመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) ድንቅ ንግግር ትኩረት ስጠው!። ወገንተኝነት አያጥቃህ፣ ለሀቅ ብቻ ወግን! ሀቁ በበቂና በትክክለኛ ማስረጃ ከተነገረህ አንተም ሆንክ የምትወደው ዳዒ አለያም ከጎንህ ያሉ ወዳጆችህ መንገድ ስህተት እስከሆነ ወደ ሀቁ ለመመለስ አታንገራግር!! የተነገረህ እውነት እሰከሆነ ለመቀበል ቆራጥ አቋም ይኑርህ!። ምክንያቱም ወገንተኛ የምትሆንለት አካል ከአላህና ከመልእክተኛው በላይ የለምና ለአላህ እና ለመልእክተኛው እና ለሐቅ ብቻ ወገንተኛ ሁን!!። ሐቅ ከየትም ይምጣ ከማንም ሐቅ እስከሆነ መቀበል ነው። ሀቁ ካልተገለጠልህ ደግሞ እስኪገለጥልህ ከቡድንተኝነትና ጭፍን ተከታይነት ገለልተኛ ሆነህ በአደብ ፈልገው፣ በንፁህ ኒያ እስከፈለግከው ኢንሻአላህ ቢዘገይ እንኳ ፍንትው ብሎ ይታይሃል!!።
ግን ግን አደራ ምን ጊዜም ለግለሰቦች ከወገንተኝነት፣ ከጭፍን ተከታይነትና ከቡድንተኝነት ራስህን አርቅ!!። ምን ጊዜም ወገንተኝነታችሁ ለሐቅ ከሆነ ሐቅን የሚከተልን ትወዱታላችሁ ታከብሩታላችሁ እንጂ ጭፍን ተከታይ አትሆኑለትም!!።
አላህ ሐቁ ለተደበቀበት ግልፅ ያድርግለት!! የሀቅ ተከታዮችና በሐቅ ላይ ከሚፀኑ ባሮቹም ያድርገን!!

✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

#join ⤵️
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
የምን ፕራንክ ነው!? እንዴ!!!
መሰልጠን እና መሰይጠን ለዩ

       ❪„„„„„„„„„„„„„„„„„❫

ባለንበት የተደበላለቀ ዘመን የጠራ እውቀት ላይ ሆኖ ዲኑን እና ክብሩን የጠበቀ ታድሏል።

♻️ በአሁኑ ሰዓት አብዛኛውን ሰው busy ካደረጉት የምዕራባውያን ኮተቶች መካከል “ፕራንክ” ❮prank❯ የሚሉት ነው።
➲ Prank ማለት ራሳቸው ምዕራባውያን እንደሚከተለው ይተረጉሙታል፦
«Prank is a mischievous trick or practical joke.»
ፕራንክ ማለት የተሳሳተ ተንኮል ወይም ተግባራዊ ቀልድ ነው።


ይህ የተሳሳተ ተንኮል ሰዎች ባለወቁበት መልኩ የሚያስደነግጥ ነገር ይተገበርባቸዋል። ከደነገጡ ብሎም ካለቀሱ በኋላ prank ይባላሉ። በዚህ ተግባር በርካታ አላስፈላጊ ኮተቶች አሉ።

↪️ ሙስሊሞች በዚህ ተግባር መሳተፍ የለባቸውም በፍፁም አንዳንድ ሙስሊሞች ተሳትፈውበታል። የድሮ ፍቅረኛዬ ምናምን እያሉ ወንጀላቸውን በሚዲያ የበተኑ ሙስሊም ሴቶችን  አስተውያለሁ። ካፊር ሴት እያቀፈ የሚጃጃል ወንድም ተመልክቻለሁ። ሌሎችም

ስለዚህ ከዚህ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አስፈላጊ ነው። የዚህን መሰል ፈሳድ ካፊሮች ሲያመጡ መከተል እነሱን ከመወዳጀት  ነው። ይህ ደግሞ አደጋ መሆኑ ግለሰፅ ነው።

«وَمَنْ يَتَوَلَّهُمْ مِنْكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ»
[المائدة: 51]
ከእናንተ የተወደጃቸው ሁሉ እርሱ ከእነርሱ ነው❞

♻️ ነብዩ ﷺ ይህን አይነት መመሳሰል በግልጽ ማውገዛቸው ከማናችንም የሚሰወር አይመስለኝም።

عَنِ ابْنِ عُمَرَ قَالَ:- قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:- "مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ".
(صحيح أبي داود)
حسنه الألباني (3401)


ኢብኑ ዑመር  ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፏል፦
“ከሆኑ ሰዎች ጋር የተመሳሰለ ከነሱው ነው”
[ሶሂህ አቡ ዳውድ]

ፕራንክ የምዕራባውያን ፍብርክ መሆኑ ግልፅ ነው። በዚህ ተግባር መሰለፍ ከእነሱ መመሳሰል ነው። ሲጀመር በውስጡ ያሉ ፈሳዶች ❪ጥፋቶች❫ ፕራንክ መራቅ ካሉብን ተግባራት መሆኑን ይጠቁሙናል።

ሌላ አንድ ሀዲስ እንጨምር፦
«عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:- ((لَتَتْبَعُنَّ سَنَنَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ شِبْرًا شِبْرًا وَذِرَاعًا بِذِرَاعٍ، حَتَّى لَوْ دَخَلُوا جُحْرَ ضَبٍّ تَبِعْتُمُوهُمْ)). قُلْنَا يَا رَسُولَ اللَّهِ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى قَالَ:- ((فَمَنْ)).»
رواه البخار ٧٣٢٠

↪️ አብደላህ ብን ኹድሪይ እንዳስተላለፈው ነብዩ ﷺ የሚከተለውንብለዋል፦
“ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የአርጃኖ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቦጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!”
  [ቡኻሪ፡ 7320]

ከዚህ ሀዲስ አንፃር የት ነን!? በፕራንክ ጉዳይ busy የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ሀዲስ ልትገሰፁ ይገባል። እስከመቼ ይሁዳ እና ነሷራ ተከትለን እንጓዛለን!? ደግሞ ሙሉዕ የሆነ ዲን እያለን!!! እስልምና ያጓደለው ምንም የለም።  እስልምና ያላስተማረው ካለና ከሰራነው በትክክል ጥመት ነው። በጥመት ተግባር መሳተፋችንንም ማወቅ አለብን። ነገሮችን ቀለል ማድረግ ትተን ከፕራንክ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አለብን።

↪️ በነገራችን ላይ በዚህ ፕራንክ በሚሉት ኮተት ብዙ ጊዜ የሚከሰቱበት ሁለት ተግባሮች አሉ እነሱም፦
❶ኛ ሰዎችን ማሸበር ወይም ማስደንገጥ እና
❷ኛ በውሸት ቅንብር ማሳቅ ነው።


☑️ እነዚህ ሁለት ተግባራት ደግሞ በእስልምና የተከለከሉ ናቸው። ማስረጃዎችን እንመልከት፦

የመጀመሪያውን በተመለከተ ሙስሊም ሌላ ሙስሊምን ማስጨነቅ ወይም ማሸበር አይፈቅድም፦

عن عبدالرحمن بن أبي ليلى قال:-  قال رسول الله ﷺ "لا يحلُّ لمسلمٍ أن يروِّعَ مسلمًا"
       صححه الإمام  الألباني 
         سنن أبي داود


አብዱረህማን ኢብኑ አቢ ሌይላ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
"አንድ ሙስሊም ሙስሊምን ማሸበር አይፈቀድለትም"
ሱነን አቢ ዳውድ
ኢማም አልባኒ ሶሂህ ብለውታል


ሁለተኛው ደግሞ ሰዎችን ለማሳቅ በሚል ውሸት እየፈጠሩ መናገር በኢስላም አይፈቀድም። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-

وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ»

"ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!"

አቡነ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይ
ሸይኹል አልባኒይ “ሐሰን” ብለውታል፡፡


በሌላ በኩል ደግሞ የሚከተለውን ሀዲስ እናገኛለን፦
عن أبي أمامة رضي الله عنه قال:- قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم:-
"أنا زعيم ببيت في ربض الجنة لمن ترك المراء وإن كان محقا، وببيت في وسط الجنة لمن ترك الكذب وإن كان مازحا، وببيت في أعلى الجنة لمن حسن خلقه".
 سنن أبي داود
وحسنه الألباني.


♻️ አቡ ኡማማህ ረዲየሏሁ ዐንሁም እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፡-
"እኔ እውነተኛ ቢሆን እንኳን ክርክርን ለተወ ሰው በጀነት ዙሪያ ወይም ዳርቻ ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ስነ ምግባሩ ላማረለት ደግሞ በጀነት የላይኛው ክፍል ውስጥ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።"
ሱነን አቢ ዳውድ
አል-አልባኒ ሀሰን ብለውታል።


➲ በዚህ ሀዲስ ❸ ነጥቦች ጎልተው ተጠቅሰዋል።
❶ኛ ክርክር
❷ኛ ውሸት
❸ኛ ስነ-ምግባር


ውዱ ነብይ ﷺቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።❞ በማለት በቀልዳችን መዋሸት እንደሌለብን አስረድተዋል። ስለዚህ ውድ እህት ወንድሞች በፕራንክ ቀልድ የሚደረጉ ውሸቶች ትክክል አይደሉም። እኛም ተጠንቅቀን ሌሎችንም ልናስጠነቅቅ ይገባል።

📝 አቡ ዒምራን ሙሐመድ መኮንን

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
#የወንድ ሀያዕ!
~  ~
     #ወንድ ልጅ  በተፈጥሮው ሀያዕ ያላትን ሴት ይፈራል! ያፍራልም! ሰተር ያልሽና ቁጥብ ከሆንሽ ሊላከፍሽ ይቅርና ቀና ብሎ አንቺን ለማየት አይደፍርም ።

    #ራስሽን ካከበርሽ ወንድ ልጅ ያከብርሻል ለራስሽ ክብር ከሌለሽ ደግሞ ወንድ ልጅ ሊያከብርሽ አይችልም ።

      #ክብርሽን ስትጠብቂ ከነ_ክብረሽ ሊወስድሽ ወላጆችሽን ይማፀናል!

      #ራስሽን ስታረክሺ ግን ጊዜ ለማሳለፊያ እንጂ ለቁም ነገር አይፈልግሽም ።

    #ሴት ልጅ ራሷን ሰብሰብ አድርጋ ስትኖር ወንድ ሊያት ያፍራል በጎኑ እንኳን ብታልፍ ቀና ብሎ አያይም ።

    #የወንድ ልጅ ሀያዕው ሴት በጎኑ ስታልፍ አይኑን ሰበር ማድርግ ነው አንቺ ሰተር ብለሽ ስትመጪ ደሞ ማየትን አይሻም ።

     #ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ
ራስሽን ሰትር አድርጊ እንቁ ትሆኛለሽ ውዷዬ !

https://t.me/umusaymen
Forwarded from «ሰለፎችን እንከተል» channel (abdurahman(አቡ ፉዶይል))
ወንድም እህቶቼ

🔶መስጅድ ስንገባ ጫማችንን በፔስታል ይዘን እንገባለን ወይም የሚጠብቅ ካለ እንሰጣለን፣......... ይሄ ሁሉ ጥንቃቄ ጫማችን በሌባ እንዳይሰረቅ ነው!!! ጡሩ።
አቂዳችንና መንሃጃችንስ እንዳይሰረቅ ምን እያደረግን ነው
እኔ ከታዘብኩት ላካፍላችሁ፦
⛔️ምኑንም የማያውቁትን ሰው ፣ በሚድያ ብቻ ድምፁን ሰምተው ወደውት አቂዳና መንሃጃቸውን አሳልፈው የሰጡ ብዙ ሰወች አሉ‼️ በቃ ዓሊም ይሁን መሃይም ይሁን ምኑንም ሳያውቁ ሚድያ ላይ የዘለለንና የጮኸን እንደጅራት የሚከተሉ በጣም ብዙ ናቸው‼️ በተለይ በተለይ ውጭ ሃገሩ ያሉ እህቶቻችን (ሁሉም)አይደሉም ግን አብዛኞቹን በሚባል ደረጃ ምንም አያውቁም 👉 ኪታብ አይደለም ቁርአን ያልጀመሩ ግን በአፈቅቤ ወንዶች ተሸውደው የሱን ጀልባ ተሳፍረው እየነጎዱ ነው።

ዓላመቱ ሷሊህ አል'ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንድህ ይላሉ፦

#አንተ

አንተ ሸቀጣሸቀጥ ለመግዛት ስትፈልግ ፤ መኪና ለመግዛት ስትፈልግ ወይም ሌላ ትንሽ ነገር ለመግዛት ፈልገህ ሰለዛ እቃ ምንም እውቀት ከሌለህ #ተሳስተህ_የማይሆን ነገር እንዳትገዛ #ፈርተህ ስለዛ እቃ #ወደሚያወቅ_ሰው_ሄደህ_ትጠይቃለህ!!!👈ይሄ በዱኒያዊ ጉዳይ ነው። 👉 #በድንህ_ጉዳይ #ለምንድነው አዋቂወችን፣ አላህን የሚፈሩትን ፣የእውቀት ባለቤቶችን #የማትጠይቀው

#ለዱኒያህ_እየመረመርክ_ለድንህ_ለምድነው_የማትመረምረው»

ምንጭ፦ሚን አዳቢ አል'ሙፍቲ
ወአል'ሙስተፍቲ

⛔️ በቃ የወደዱትን ሰው ሌላ ሰው በመረጃ ጥፋቱን ቢናገርም በቃ ተናጋሪው ማንም ይሁን‼️ ለምን ዓሊም፣ ሸይኽ አይሆንም አውርደው ከመፈጥፈጥ ወደሗላ አይሉም‼️ ምን ያክል ተዓሱብ እንዳሰከራቸው በግልጽ እያየነው ያለ ጉዳይ ነው። ደግሞ ወደሰለፊያ (የውሸት)መጠጋታቸው ነገሩን ይበልጥ አስጠሊታ ያደርገዋል። ለምን ካላችሁ ሙሪድነት ሰለፊያ ላይ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ስለሆነ ነው።

⛔️ ከወንዶች ደግሞ እዚህ ሚድያ ላይ የታዘብኩት👉 ፉላን የነቃ ነው ፣ እሱ ትንሽ እውቀት አለው ፣ አስተዋይና በሳል ነው፣........ ብለን የምናስባቸው የተመዩዕ ፊትና ስትመጣ ብጥስጥሳቸው ወጥቶ ፣ ሹቡሃ ጠራርጎ ወሰዳቸው። በዚህም አልበቃቸውም ሰለፊያን ከጠላቶቿ ጎን ቆመው መዋጋት ጀመሩ‼️
ለካ ተሳስተን ነበር ብለናል።


وَتَحْسَبُهُمْ أَيْقَاظًا وَهُمْ رُقُودٌ ۚ

እነሱም የተኙ ሆነው ሳሉ (ዓይኖቻቸው በመከፈታቸው) ንቁዎች ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ፡፡

ሱራ አል'ካህፍ:18

↪️ ይሄን ያክል ርቀት የተጓዛችሁለት ሰው የሰለፊያን የማይቀማ ሰርቲፊኬት ማነው የሰጠው አወ በፊት ሰለፊይ ሊሆን ይችላል!!! ታድያስ በህይወት ያለ ሰውኮ ፊትና አይታመንለትም!!! ሊጠም ይችላል በል እንዳውም ከሃድም ሊሆን ይችላል‼️ ታድያስ ማነው ግለሰብ ላይ ተጣበቁ ያላችሁ

🔰ዓበደላህ ኢብኑ መስዑድ ረድየላሁ ዓንሁ እንድህ ብለዋል፦

«ሰዎችን መከተል የፈለገ የሞቱትን ይከተል፡፡ በህይወት ያለው ፈተና ላይ ላለመውደቁ ዋስትና የለም፡፡ እነዚያ የሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰሐቦች ከዚህ ኡማ በላጭ ህዝብ ነበሩ፡፡ ቅን ልቦና ያላቸው፣ እውቀታቸው የጠለቀ፣ መፈላፈል የማያበዙ ነበሩ፡፡ አላህ የሱን ነብይ እንዲጎዳኙ፣ ዲኑን እንዲያቃኑ የመረጣቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ደረጃቸውን እወቁላቸው፡፡ ትውፊቶቻቸውን ተከተሉ፡፡ በተቻላችሁ ስነ-ምግባራቸውንና ዲናቸውን አጥብቃችሁ ያዙ፡፡ ምክኒያቱም እነሱ ቀጥ ያለው ጎዳና ላይ ነበሩና፡፡»

📚 [(ጃሚዑል በያን፡ 2/97) ሊ ኢብኒ ዐብዱልበር]

ሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ እንድህ ብለዋል፦

« ሸይኽን ወይም ዓሊምን እሱ የሚለውንና የሚሰራውን በሙሉ በመከተል የያዘ ሁሉ ከረሡል ዓለይሂ ሶላት ወሰላም ውጭ ከእሱ(ከሸይኹ ወይም ዓሊሙ) #ጋር_የተስማማን_የሚወዳጅ_ከሆነ‼️‼️‼️#ከሱ_ጋር_የማይስማማን_ጠላት_የሚያደር_ከሆነ‼️‼️‼️#እሱ_ሙብተድዕ_ጠማማ_ነው👉ከኪታብና(ከቁርአን) ከሱና ያፈነገጠ ነው»

📚ጃሚዑ አልመሳኢል:7/464

#በህይወት_ያለ_ሰው_ፈተና_አይታመንለትም

ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ እንድህ ብለዋል፦
↪️ « #በፊት_በትክክለኛው_አቂዳ ቀጥ ብለው #በሗላ_ግን_የሚፈተን ስንትና ስንት ሰው አለ?
#ይሄን ጊዜ #ቀጥ_ብሎ_በነበረበት ሁኔታ #ተከትለኸው ፣ እሱ በሄደበት ሄደህ፣ #መሪ_አድርገህ_ይዘኸው!!! #አንተ_በእሱ ላይ #እምነት_አሳድረህ #አንተ_ሳታውቅ_ሊያፈነግጥ_ይችላል‼️ይሄን ጊዜ #አብረኸው_ትከስራለህ‼️በህይወት ያለ ሰው ፊትና አይታመንለትም»

📖ሸርሁ አል'ዓቂደቱ አል'ተድሙሪያ:20


https://t.me/nu_selefochin_enketel
ዝምድና የመቀጠል ጥቅሞች!
=======>


❶ኛ ዝምድናን መቀጠል ወንጀል ለማስማር ምክንያት ይሆናል፡፡
🍥 عن ابن عمر رضي الله عنه قال:أتى النبي صلى الله عليه وسلم رجل فقال : إني أذنبت ذنبا عظيما ، فهل لي من توبة ؟ فقال : النبي صلى الله عليه وسلم " : هل لك من أم؟"قال:لا . قال " فهل لك من خالة ؟ " قال : نعم . قال " : فبرها"

🍥
ኢብን ዑመር የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡- አንድ ሰው ወደ ነብዩ ﷺ በመምጣት “ታላቅ ወንጀል ፈጽሜያለሁ ፤ ጸጸት (ተውበት) ይኖረኝ ይሆን? አላቸው፡፡ “እናት አለችህ?” አሉት፡፡ “የለኝም” አለ፤ “አክስት አለችህ?” አሉት፤ “አዎ” አለ፡፡ “ለእርሷ በጎ ስራ” አሉት፡፡
📚ቲርሚዚይ

❷ኛ ዝምድና መቀጠል ሲሳይ ለመስፋት፤ እድሜ ለመርዘም ምክንያት ይሆናል፡፡
👈 عن علي بن أبي طالب رضي الله عنه ، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال" :من سره أن يمد له في عمره ، ويوسع له في رزقه ، ويدفع عنه ميتة السوء ، فليتق الله ، وليصل رحمه "
📚 رواه الحاكم والبزار بسند جيد.

👉 ዓልይ ብን አቢ ጧሊብ 4 የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡- “የእድሜው መጨመር፤ የሲሳዩ መስፋት፤ ከእርሱ ላይ መጥፎ ፍጻሜ መወገዱ የሚያስደስተው ሰው አላህን ይፍራ፤ ዝምድናን ይቀጥል፡፡”

وعن أنس رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال" :من أحب أن يبسط له في رزقه ، وينسأ له في أثره ، فليصل رحمه"
📚 رواه البخاري ومسلم.
አነስ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
“ሲሳዩ እንዲሰፋለት፤ እድሜው እንዲረዝምለት የሚፈልግ ሰው ዝምድናን ይቀጥል፡፡”
📚ቡኻሪና ሙስሊም

ዝምድናን መቀጠል ከአላህ ዘንድ ተወዳጅ ከሆኑ ተግባራት አንዱ ነው፡፡ ረሡል ﷺ ከሶሃቦች ጋር እያሉ ከኸይሰም ጎሳዎች አንድ ሰው መጣ፡፡ “ረሡል ነኝ የምትለው አንተ ነህ እንዴ?” አልኳቸው ይላል፡፡ እርሳቸውም “አዎ” አሉ፡፡ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ወደአላህ ተወዳጅ የሆነው ስራ የቱ ነው?” አልኳቸው፡፡ “በአላህ ማመን” አሉኝ ፡፡ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከዚያስ” አልኳቸው፤ “ዝምድናን መቀጠል ነው” አሉኝ፡፡ “የአላህ መልክተኛ ሆይ!ከአላህ ዘንድ የሚያስቆጣ ተግባር ምንድን ነው?” አልኳቸው ፤ “በአላህ ማጋራት” አሉኝ፡፡ ከዚየም “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከዚያስ?” አልኳቸው፡፡ “ዝምድናን መቁረጥ ነው” አሉኝ፡፡ አቡ የዕላ ፊሙስነዲሂ፡ ጀይድ ጥሩ በሆነ ሰነድ አውርቶታል፡፡ዝምድናን መቀጠል ጀነት ለመግባት ከእሳት ለመዳን ምክንያት ይሆናል፡፡

☑️ አቡ አዩብ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡- “አንድ የገጠር ሰው በሰፈር ድንገት ከረሡል ﷺ ጋር ተገናኘና የግመላቸውን ልጓም በመያዝ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! - ሙሀመድ ሆይ!- ወደ ጀነት የሚያቀርበኝ፤ ከእሳት የሚያርቀኝን ስራ ንገሩኝ” አላቸው፤ ረሡል ﷺ መልስ ከመስጠት ተቆጠቡና ሶሃቦችን መመልከት ጀመሩ፤ ከዚያም “በእርግጥ ተገጠመ ወይም በርግጥ ተመራ” አሉ፡፡ “ምን አልክ?” በማለት ረሡል ﷺ በድጋሜ ግለሰቡን ጠየቁት፤ እርሱም በድጋሜ ነገራቸው፤ ከዚያም ነብዩ ﷺ የሚከተለውን ተናገሩ፡- “አንድንም በእርሱ ሳታጋራ አላህን ልትገዛ ነው፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቀህ ልትስግድ፤ ዘካ ልታወጣ፤ ዝምድናን ልትቀጥል፤ ግመሏን ተዋት (ልቀቃት)፡፡” በሌላ ዘገባ “የዝምድናን ባለቤት ልትቀጥል” ነው፡፡ ሰውየው ጠይቆ ከሄደ በኋላ “ይህ ሰው ባዘዝኩት መሰረት አጥብቆ ከያዘ ጀነት ገባ” በማለት የአላህ መልክተኛ ተናገሩ፡፡
📚ቡኻሪና ሙስሊም

↪️ ዝምድና መቀጠል ውለታን በመመለስ አይደለም ዝምድና ከተቀጠለ ብቻ የሚቀጥል፤ ከቆረጡ ደግሞ የሚቆርጥ ሰው አለ፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሰው ውለታን መላሽ እንጅ ዝምድናን ቀጣይ አይባልም፡፡

እንዲህ አይነቱ ተግባር ለቅርብም ይሁን ለሩቁ ሊሆን የሚችል ነው፡፡ ውለታን መመለስ በቅርብ ዘመድ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ ትክክለኛው ዝምድናን ቀጣይ ቆረጡም ቀጠሉም ዘመዶችን ለአላህ ብሎ የሚቀጥል ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ረሡል ﷺ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"ليس الواصل بالمكافئ ، ولكن الواصل الذي إذا قطعت رحمه وصلها"
📚رواه البخاري ومسلم
“ውለታ መላሽ ዝምድናን ቀጣይ አይባልም፤ ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል ነው፡፡”
📚 (ቡኻሪ፡ 5991)

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
Audio
«ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺍﻟﻨﺼﻴﺤﺔ»
«ዲን ምክክር ነው»
ክፍል አንድ:—①

ቦታ :— ቻግኒ

መጠን :– 2.2MB

እርዝመት :—9:15

በአቡ ጁበይር.

ወደ ቻናሉ👇 ለመቀላቀል 👇ከፈለጉ👇
t.me/selefiyadawabechagni