905 subscribers
235 photos
42 videos
276 links
Vulnerable, thought-provoking conversations among Ethiopian women on the Gospel, the mission of the Church, and the life of a Christian

Contact us @SelahContactBot

Follow us on Facebook, Instagram, Pinterest and Twitter
https://selahethiopia.org/follow
Download Telegram
ዛሬ ዳያና እና ሐና ጸሎት ለእነሱ ምን ማለት እንደሆነ፣ እና በዕለት ተዕለት ህይወታቸው ውስጥ የጸሎትን ልምምድ እንዴት እንደሚያሳድጉ ይነጋገራሉ። በጸሎት አልባ ወቅቶች ውስጥ ስለሚያደርጉት ትግል እርስ በርስ ይካፈላሉ እና ከጸሎት አልባነት አዙሪት ለማምለጥ የሚረዱ መንገዶችን ይመረምራሉ። አብራችሁን ቆዩ።

Today on Selah Focus, Diana and Hanna talk about what prayer means to them and how they cultivate a practice of prayer in their daily. They share in on each other's struggle of prayerless seasons and explore ways to escape the cycle of prayerlessness.

Watch on YouTube: https://youtu.be/VPT2KpS7MjU
In Corinth among the Christians, there were not many wise according to the flesh, not many mighty according to the flesh, not many noble according to the flesh. Much like those of us here in Ethiopia. But the people of Corinth were beginning to think highly of themselves because of God's work in them. Paul reminds them, like he reminds us today, they were not chosen because they themselves were so great, but because God was gracious and great.

@SelahEthiopia
ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ቃል ትጉ እና ታታሪ እንድንሆን ቢያበረታታም ስለ እርካታ እና ባለንበት ቦታ አመስጋኝ መሆንን በተመለከተ ብዙ ይናገራል። በዚህ ዙሪያ ሩት ሃሳቧን ታካፍለናለች።⁠

Although the Word of God encourages us to be diligent and hard workers, it also says a lot about contentment and about having gratitude exactly where we are. Ruth shares with us here thoughts on this.⁠

Watch on YouTUbe:
https://youtu.be/UJ2Fg4oLx9g
ምን መጸለይ እንዳለብኝ በማላውቅበት ጊዜ ዳዊት የእኔ ጥልቅ የመነፅናናት ምንጭ ነው። በእነዚህ ሁለት ጥቅሶች ውስጥ ብቻ እንኳ፣ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከራው ጊዜ ከሁሉ የላቀ ታማኝ ጓደኛው እናም ታላቅ ምንጩ አድርጎ ሲመለከተው እንመለከታለን። የጌታን ቸርነት እና ከምድራዊ ሀብት በላይ የሆነውን የእግዚአብሔርን አቅርቦት ያስታውሳል። ዛሬ ለእግዚአብሔር የምትናገሪውን እንደ እኔ ያጣሽ ከሆነ፣ እኔም አንቺም ከዳዊት ቃላትን እንዋስ። ታማኙ፣ ቅርቡ አምላካችን እርሱን እንደሰማው እኛንም ይሰማናል።

David is my deepest source of inspiration when I don't know what to pray. In just these two verses alone, we see David considering God to be his greatest confidant in his time of suffering and His greatest source. He reminds himself of the goodness of the Lord, and the provision of God that is beyond earthly possessions. If you don't know what to say to God today, consider borrowing David's words as I do.

@SelahEthiopia
ሰውነታችንን እንደ መንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ማክበር አንዳንድ ጊዜ በዕለት ተዕለት ህይወት በተለይም በፍቅር ግንኙነቶች አውድ ውስጥ ለመወጣት ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ለዚያም ነው በዚህ ሳምንት ስለ ግንኙነቶች፣ ስለ ትውውቅ ጊዜ እና ስለ ዓወስቦ ንጽህና ጉዳዮችን ለመወያየት በጣም የጓጓነው። አንቺ ሰውነትሽን እንደ መልካም እና ሕያው መስዋዕት ይዘሽ እንድትቀርቢ ነው ጸሎታችን። በዚህ ጉዳይ ላይ አዲስ ቪዲዮ በዚህ ሳምንት!

Respecting our bodies as a sanctuary for the Holy Spirit can sometimes be challenging to walk out in real life especially in the context of romantic relationships. That's why we're so excited to discuss matters of relationships, dating, and purity this week to help equip you in obeying God's commands for your body. A new video on this topic coming this week!

@SelahEthiopia
እናትነት ለሴት ልጅ አስደናቂ እንዲሁም ፈታኝ ጊዜ እንደሆነ እናውቃለን። ሃና ከጌታ ልጅን ስለመጠበቅ የራሷን ልምድ እንዲሁም የጸሎት እና የታማኝነት ሚናዎች ታካፍለናለች። ጌታ በእነዚህ የእናትነት የመጀመሪያ ወራት ውስጥ እያስተማራት ያለውን ነገር ታጫውተናለች።

We know that motherhood is both a wonderful and a trying time for a woman. Hana shares her own experience about waiting on the Lord for a child, the lessons of prayerfulness and faithfulness, as well as what the Lord has been teaching her in these early months of motherhood.

https://youtu.be/H2Y7eF9v3EY
ባለፈው እሁድ በቤተክርስቲያን ሁላችንም ከዚህ በፊት የሰማነውን መልእክት ሰማሁ። እኛ መውጣት እና ያልተደረሰውን መድረስ አለብን ምክንያቱም ያ ስራ ተሰጥቶናል። ግን፣ ምሥራቹን ሰምተው ለማያውቁት ምን ያህሎቻችን እውነተኛ የልብ ስብራት እንደሚሰማን አስባለሁ። ስንቶቻችን ነን ጌታን የማያውቁትን ጎረቤቶቻችንን፣ ጓደኞቻችንን፣ የቤተሰባችን አባላትን የምንቆጥር እና በዚህ ከልብ የምናዝን? ከሀዘናችን እርምጃ የምንወስድስ? ጌታን ስለምናውቀው ብዙ ጊዜ ለየት ያልን መስሎ ሊሰማን ይችላል። የወንጌል እውነተኛ ልብ ግን የጌታ ልብ ነው፣ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ይኖሩ ለነበሩት ጥልቅ ርኅራኄ ያለው የጌታ ልብ ነው። ይህ ትህትና እና የልብ ስብራት ለሁላችንም ይሁንልን። እንውጣ፣ እንድረስ።

This last Sunday in church, I heard the message we've all heard before. We must go out and reach the unreached because that mandate has now been given to us. But, I wonder how many of us feel true heartbreak for those who have never heard the good news. How many of us consider our neighbors, our friends, our family members who don't know the Lord, and feel grieved by this? But the true heart of the Gospel is the heart of the Lord, the heart of the Lord that felt deep compassion for those who were living like sheep without a shepherd.

@SelahEthiopia
የእግዚአብሔር ቃል ሁሉንም ነገር ለጌታ ክብር ​​እንድናደርግ ይነግረናል። ታዲያ ይህ ለፍቅር ህይወታችን እና ለግንኙነታችን ምን ማለት ነው? አምላክን ለማክበር እና ለማስከበር ለጋብቻና ለተቃራኒ ጾታ ያለንን አመለካከት መቅረጽ የሚኖርብን እንዴት ነው? ዛሬ ከጽዮን ጋር

The Word of God tells us to do everything to the glory of the Lord. So what does that mean for our dating life and our relationships? How should we shape our view of marriage and the opposite sex to glorify God?

https://youtu.be/Ks-yLeCM1ro
የምናደርገው ነገር ሁሉ አንድን ነገር ወይም አንድን ሰው ያከብራል። ሁሉም ተግባሮቻችን በልባችን ፍላጎት እና ተድላ ስለሚመሩ በልባችን ዙፋን ላይ ስለተቀመጠው አንድ ነገር ይናገራሉ። እግዚአብሔር ትንሹን ነገርን እንኳ ለስሙ ክብር እንድናደርግ ይጠራናል። ይህ ጥሪ ባህሪያችንን ብቻ እንድናስተካክል ነው? አይደለም! ይህ ጥሪ ጌታን በልባችን ዙፋን ላይ እንድናስቀምጥ ነው። ይህ በእኛ በፈጠረው አዲስ ፍጥረት እሱን እንድናከብረው የቀረበ ጥሪ ነው።

ጌታ ይርዳን።

Everything we do glorifies something or someone. Because all of our actions are driven by the desires and pleasures of our hearts, they say something about who is sitting on the throne of our hearts. God calls us to do every little thing to the glory of His name. Is this a call to just modify our behavior? No. This is a call to place the Lord on the throne of our hearts. This is a call to glorify Him through the new creation He makes of us.

May the Lord help us.

@SelahEthiopia
የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን ጽድቅ እንድንፈልግ ያለማቋረጥ ያሳስበናል። ግን ይህ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ ምን ማለት ነው? የእግዚአብሔርን ጽድቅ በመፈለግ ላይ ከእግዚአብሄር ቃል ልንመረምራቸው የምንችላቸው አንዳንድ መርሆዎች ምንድን ናቸው? ዛሬ ከሩት ጋር!

The Word of God continually urges us to seek the righteousness of God. But what does that mean in our day-to-day life? What are some specific principles we can glean from the Word of God on seeking the righteousness of God? Today with Ruth!

Watch on YouTube: https://youtu.be/yWuAspjlX_0
ጳውሎስ የክርስቶስን ትሕትና ይዘን እንድንገኝ እየጠየቀን ነው። ከራስ ወዳድነት ፍላጎት ወይም ከንቱ ትምክህት የተነሳ ምንም እንዳናደርግ ያዘናል፤ ይልቁንም ልክ ክርስቶስ እራሱን ዝቅ እንዳደረገ እኛም ከራሳችን በላይ ለሌሎች እንድናስብ ይነግረናል፣ ይህም ከክርስቶስ አስተሳሰብ ጋር መካፈል እንደሆነ ያስተምረናል።

ዛሬ ለራሳችን ፍላጎት እንድንሞት እና ልጆቹን በደስታ እንድናገለግል እግዚአብሔር እንዲረዳን እለምናለሁ።

Paul here asks us to imitate Christ's humility. He asks of us to do nothing out of selfish ambition or vain conceit; but to consider others more important than ourselves just like Christ considered us to be more important.

I pray the Lord teaches you and me to die to ourselves today, and serve his sons and daughters with joy.

@SelahEthiopia
የወንጌልን ክብደት ማሰብ አለብን፤ የክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ለዚህ ወንጌል ዋናነት መሆን ለማሰብ ከዚህ ሳምንት የተሻለ ጊዜ የለም። እርሱ ተስፋችን ነው፣ እርሱ መዳናችን ነው፣ እርሱም ሕይወታችን ነው ምክንያቱም እርሱ ስለ እኛ መሞቱ ብቻ ሳይሆን ተነሥቷልም። እርሱ የሚናገረውን ሁሉ እናምናለን ምክንያቱም እርሱ ተነሥቷል፣ ዘለዐለም ሕያው ሆኖአልና።

We must think of the heaviness of the Gospel; and no better time than this week to consider the centrality of Christ's death and resurrection to this Gospel. He is our hope, He is our salvation, and He is our life because not only did He die for us, but also rose again. We can believe everything He says because He rose again and He lives.

@SelahEthiopia
ኢየሱስ ደሙን የሚያቀርበው አሮጌው ኪዳን በደም እንደታተመ በደም የታተመ አዲስ ኪዳን የመመሥረት ሥልጣን ያለው እርሱ ብቻ ስለሆነ ነው። ደሙንም ለእኛ አፈሰሰ። "እውነት እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት አዲሱን የወይን ፍሬ እስከምጠጣበት እስከዚያች ቀን ድረስ ዳግም ይህን አልጠጣም።” ሲልም ይናገራል፤ ይህም ኢየሱስ ገና በሰማይ የፋሲካን በዓል እንደገና አላከበረም ማለት ነው። አሁንም ሕዝቡ ሁሉ ወደ እርሱ እስኪሰበሰቡ ድረስ ይጠብቃል ከዚያም ታላቅ እራት ይሆናል፤ የበጉ ሰርግ እራት (ራዕይ 19፡9)።

እየሱስ የከፈለው ዋጋ የማይሻር ዘለዐለማዊ ዋጋ ነው። ወደ ታላቁ እራት እያየን፣ እየተጠባበቅን የፈሰሰውን ደሙን እንደ ተስፋ እንያዝ። ስለ አንቺ የፈሰሰ ሀያል የአዲስ ኪዳን ደም አለ።

Jesus offers His blood as only He has the authority to establish a new covenant, sealed with blood, even as the old covenant was sealed with blood (Exodus 24:8).

@SelahEthiopia
እግዚአብሔር ፍትሃዊ ባይሆን ኖሮ ልጁ እንዲሰቃይና እንዲሞት ባላስፈለገው ነበር። እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ባይሆን ኖሮ ልጁ እንዲሰቃይ እና እንዲሞት ባልፈቀደ ነበር። እግዚአብሔር ግን ፍትሃዊ እና አፍቃሪ ነው። ስለዚህ ፍቅሩ የፍትህ መስፈርትንሁሉ ለማሟላት ፈቃደኛ ሆነ።

ፍቅሩን አናቅልለው። የኃጢአታችንን ክብደትና በእኛ ላይ የነበረውን የቁጣውን ትክክለኛነት እስካልተረዳን ድረስ በእግዚአብሔር ፍቅር እና መወደድ አንገረምም። ነገር ግን በጸጋው ወደ አለመብቃታችን ስንነቃ የክርስቶስን መከራና ሞት ተመልክተን እንዲህ እንላለን: "ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው።" (1ኛ ዮሐንስ 4:10)

@SelahEthiopia
ኢየሱስ ከተሰቀለ እና ከተገደለ በኋላ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ምን ያህል አሳዛኝ እና ተስፋ ቢስ መስለው ነገሮች እንደተሰሟቸው መገመት እንችላለን። ስለ እርሱ የተነገረውን ትንቢት ቢሰሙም፣ ተአምር ሠሪ መሆኑን ቢያውቁም፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ቢናዘዙም፣ ሞቱ በእርግጥ ጨለማን አመጣላቸው።
ሕይወት አንዳንድ ጊዜ አዳኝ የሌላት፤ በጨለማ ውስጥ ያለች መስሎ ሊሰማን ይችላል።
እምነት ማለት ግን ዓይኖቻችን የማያዩትን ማመን ነው። እርሱ ከሞት ተነስቷል፤ ተስፋ እንዲኖረን፣ ለማመን በሚከብድበት ጊዜ እንኳን እንድናምን ሞትን አሸንፏል።

@SelahEthiopia
ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም እስከ አሁን ድረስ ከነኀጢ አታችሁ አላችሁ ማለት ነው። እንዲህም ከሆነ፣ በክርስቶስ ያንቀላፉት ጠፍተዋል ማለት ነው። ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለዚህች ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን። ነገር ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵራት ሆኖ በርግጥ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደ መጣ፣ የሙታንም ትንሣኤ በአንድ ሰው በኩል ሆኖአልና። ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤
1 ቆሮንቶስ 15:17 - 22

ሕያው ሆኖ ሕያው አርጎናል! ስሙ ይባረክ!
ተነስቷል!

@SelahEthiopia
ክርስቶስ በጥልቅ የጭንቀት ጊዜው ውስጥ በጸሎት ውስጥ ንቁነትን አፅንዖት ሰጥቶ በዚያ ውስጥ ህብረትን ምሳሌ አድርጎ ያሳያል። ይህ የአንቺን የሀዘን ጊዜያት እና የደስታ ጊዜያት እንዴት ይቀርፃል?

Christ, in His time of deepest anguish, emphasizes alertness in prayer and exemplifies community. How does this shape your moments of sorrow and your moments of joy?

@SelahEthiopia
ሌሎች ሰዎች ስለእኛ ስላላቸው ግንዛቤ ስንል በምናደርገው የሐሰተኛ አምልኮ ጩኸት ወይም ለታይታ የሚደረግ የእምነት ማሳያ ሳይሆን በቅን ልብ እና በእውነተኛ ተነሳሽነት ነው የአባታችንን ትኩረት የሚስበው ጥሪ የሚገኘው። ለዚህ ለሁላችንም የተጋላጭነት እና እውነተኛነት መንፈስ በጌታችን ፊት እንዲኖረን እጸልያለሁ።

Not with counterfeit cries of worship or displays of deep faith that we do for the sake of others' perception of us, but with a sincere heart and motivation. That's the call that gets the attention of our Father. Praying for this posture of vulnerability and truthfulness for all of us today.

@SelahEthiopia
ሁላችንንም ያየናል። ሁላችንንም ይይዘናል። ሁላችንንም ይጠብቀን። እግዚአብሔር ሁላችንንም እናቶች ይባርክ።

መልካም የእናቶች ቀን።

@SelahEthiopia
አንድ ክርስቲያን ለክርስቶስ ካላት እውነተኛ እና የዕድሜ ልክ ቃል ኪዳን ምን መጠበቅ ትችላለች? አንድ ክርስቲያን በጌታ የሕይወትን መንገድ ማወቅ ትችላለች። ነገር ግን ከምንም ነገር በላይ፣ አንድ ክርስቲያን እጅግ ጥልቅ የሆነ ደስታን፣ በራሱ በጌታ ወደር የለሽ እርካታን ማግኘት ትችላለች። እርሱ ከሁሉም ይበልጣል።

What can a Christian expect from a genuine and lifelong commitment to Christ? A Christian can expect to be shown the path of life. But above all else, a Christian can expect to experience the most profound pleasure, an unrivaled satisfaction in the Lord Himself.

@SelahEthiopia