940 subscribers
241 photos
46 videos
288 links
Vulnerable, thought-provoking conversations among Ethiopian women on the Gospel, the mission of the Church, and the life of a Christian

Contact us @SelahContactBot

Follow us on Facebook, Instagram, Pinterest and Twitter
https://selahethiopia.org/follow
Download Telegram
በዚህ ጥቅስ ውስጥ ምን ትረጂያለሽ? በፀጋ ባገኘነው ህይወት ስንኖር እንደሚገባ መመላለስ ከእኛ ይጠበቃል። ይህንን ሀሳብ ለማጉላት አብዛኛውን ጊዜ ጳውሎስ ስፓርታዊ ልምምዶችን እና የጨዋታ ህጎችን ለምሳሌነት ሲጠቀም ይስተዋላል። የጨዋታውን ድል ለመቀዳጀት በጨዋታው ሜዳ ከመሳተፍ ባለፈ የምንጫወትበት መንገድ ትልቅ ዋጋ አለው!

What stands out to you in this verse? We are expected to walk properly in our Christian life. To illustrate this point, Paul often uses sporting practices and "rules of the game" as examples. To "win" the game, he's saying, the way we play is more important than just being on the field!

@SelahEthiopia
እግዚአብሔር ከአፋችን ለሚወጡት ቃላት ግድ እንደሚለው ብናውቅም፣ አንዳንድ ጊዜ የምንናገራቸውን ግድየለሽ ነገሮችን ለመሸፈን በቀልድ ወይም በግማሽ ልብ ወዳጅነት እንሸሸጋለን። እግዚአብሔር ሁሉንም ያያል፣ ሁሉንም ይሰማል። ልባችንን እና አንደበታችንን በአምሳሉ ለፈጠራቸው ሰዎች እንዲያለዝብልን እግዚአብሔርን እንለምነው። የአንደበት ለውጥ ብቻ ሳይሆን ከልብ የሆነ መቀደስም ይሁንልን።

Even when we know God cares about the words that come out of our mouths, sometimes we hide behind humor or half-hearted friendliness to cover for the painful things we say. God sees it all, and He hears it all. Praying for our hearts and our mouths to be kind to those He made in His image.

@SelahEthiopia
ዳያና እና ሐና ወደ ሴላ ፎከስ ተመልሰዋል! በእውነት የተኖረ ህይወት ምን ማለት እንደሆነ ለመወያየት፣ ከራሳቸውም ተሞክሮ በዚህ ሐሳብ ላይ ሊነጋገሩ መጥተዋል።... ይህ ሐሳብ ለአንቺ ምን ማለት እንደሆነ በኮመንት ውስጥ ንገሪን!

Diana and Hanna return to Selah Focus to discuss what it means to live a life truly lived... Tell us in the comments how this video affected you!

@SelahEthiopia

https://www.youtube.com/watch?v=3iNmn2yCf4w
በዚህ መዝሙር ውስጥ ከዳዊት የነፍስ ፀሎት ምን መማር እንችላለን? በጥቂት ጊዜ በተገደበ የምድር ቆይታችን አንዳንዶቻችን ባልተገቡ ሁኔታዎች ሌሎቻችን ደግሞ መልካም በሆኑ የህይወት ሃላፊነቶች ተወጥረን ሁሉ የሚያልፍ በማይመስል ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን እናገኘዋለን። ሆኖም ግን የተጠራንለት ህይወት ከዚህ አለም ያለፈ ፋይዳ ስላለው ዛሬ ቆም ብለን እግዚአብሔር በእለተ ተዕለት ህይወታችን ማስተዋል እንዲሰጠን እንፀልይ።

What can we learn from David's prayer in this Psalm? During our limited time on earth, some of us may find ourselves in compromising situations, and the rest of us are too busy with life's honorable responsibilities. However, the life we are called to is far more important than this world and all the good things in it; let us take time today and pray that God will give us a heart for eternity and His eternal Kingdom.

@SelahEthiopia
የምታስቢው ሀሳብ በህይወትሽ ውስጥ ያለውን ተፅዕኖ አጢነሽ ታውቂያለሽ? የምናስበው ሀሳብ እና የትኩረት አቅጣጫችን በህይወታችን ለምንተገብራቸው ተግባራት እና ሆነው ለምናያቸው ለውጦች መንስኤዎች እና መነሻዎች ናቸው። ለዚህም ነው ውጤት ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ ትኩረታችንን፣ ልባችንን እና ሀሳባችንን እንድንመዝን መፅሐፍ ቅዱስ የሚመክረን።

Have you ever considered the impact of your thoughts on your life? Our thoughts and our focus are the driving force of the actions we take in our lives and the changes we see. That is why the Bible always advises us to evaluate our focus, our heart, and our thoughts instead of focusing simply on desired outcomes.

@SelahEthiopia
ለሌሎች እውነተኛ እና ከልብ የሆነ ፍቅር ማሳየት ብዙውን ጊዜ መስዋዕትነትን ይጠይቃል። ከምቾታችን ያስወጣናል። ፕሮግራማችንን፣ ገንዘብ አያያዛችንን፣ ጊዜአችንን፣ ጉልበታችንን፣ ስሜታችንን... መስዋዕትነቱ ሁሉን የሚያካትት ነው። ነገር ግን ክርስቶስ እኛን የወደደበት ፍቅር እንደዚህ አይነት ነው፣ ስለዚህም ይህን ፍቅር ለሌሎች መስጠት እንደሚቻል እርግጠኛ መሆን እንችላለን። ክርስቶስ እንዳደረገው ሌሎችን የመውደድ ኃይል እንዲኖራችሁ ዛሬ ስለእናንተ እጸልያለሁ - በተግባር እና በእውነት እንደወደደን መንፈስ ቅዱስ እኛም ሌሎችን በዚሁ አይነት ፍቅር እንድንወድ ይርዳን።

Showing true and genuine love to others usually requires sacrifice. It takes us out of our comfort zone. It affects your schedule, your finances, our time, our energy... It is all-encompassing. But such is the love with which Christ loves us and because of that, we can be sure giving this love to others is possible. Praying for you today that you are empowered to love others as Christ did— in action and in truth.

@SelahEthiopia
አዲስ ዓመት ነው፣ እና ሁላችንም ከባለፈው የተሻለ ማድረግ እና የበለጠ ማሳካት እንዳለብን ሊሰማን ይችላል። ለአፍታ ቆም ብለን የዘንድሮ ራዕያችን ምን መሆን እንዳለበት እናስብ።

It's a new year, and we all feel that we need to do and achieve more. Let's stop for a moment and consider what our vision should be for this year.

@SelahEthiopia

https://youtu.be/7W7_toWuedQ
መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጊዜያዊ በሆነ  አለም እንደ ምፅዐተኛ እንድንኖር ይመክረናል። ታዲያ በዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምፅዐት እንደ ሞኝነት በሚቆጠርበት አለም በእለት ተዕለት ኑሯችን ያለኝ ይበቃኛል በማለት ከዚህ ምድር ላለፈ ሀሳብ መኖር እንዴት እንችላለን?

The Bible advises us to live as strangers in this temporary world. So, in this world where the coming of our Lord Jesus Christ is considered foolish, how can we have contentment?

@SelahEthiopia

https://youtu.be/rwB6aXFfI0o
እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
— 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7

በህይወታችን ውስጥ በሚያጋጥሙን፣ እያጋጠሙን ባሉ ወይም ደግሞ ሊያጋጥሙን ይችላሉ ብለን በምናስባቸው ሁኔታዎች ሳቢያ ጭንቀትን እናስተናግዳለን። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ጥቂት በማይባል ደረጃ እንዳንጨነቅ ይመክረናል። እግዚአብሔር በቃሉ አትጨነቁ ሲልም የሚያስጨንቅ ነገር እንደሌለ በመንገር ሳይሆን ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነው እግዚአብሔር ስለ እኛ አሳቢ መሆኑን በመግለጥ ነው። ስለዚህም እግዚአብሔር ላይ መደገፍ እንደምንችል አውቀን እንድንበረታ፣ ስለችሎታው እና ስለአሳቢነቱ እንድናከብረው ነው።

There is so much in this world that can rightly concern us, worry us, or even cause us stress. Then why does the Word of God repeatedly tell us not to worry? When God tells us not to worry, it is not by telling us that there is nothing to worry about, but by revealing that God, who is the greatest of all, knows and cares about the things that worry us— and that He can be trusted to help us in and through them.

@SelahEthiopia
መንገዴን ቃኘሁ፤ አካሄዴንም ወደ ምስክርህ አቀናሁ።
— መዝሙር 119፥59

እለት እለት ስለመንገዳችን ማጤን እና የህይወታችን አቅጣጫ መፈተሽ እንደ ክርስቲያን ከእኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው። የአካሄዳችንን ልክነት የምንመዝነው ደግሞ  የእግዚአብሔርን ቃል መሰረት በማድረግ ነው። ሁል ጊዜ በማስተዋል፣ መንገዳችንን በመፈተሽ እንደ ቃሉ ለመኖር የሚያስችለውን ፀጋ እግዚአብሔር ያብዛልን።

Daily reflection on our chosen path and checking the direction of our life is something we should regularly do as Christians. We measure the validity of our actions and choices based on the Word of God. May God give us the grace to live according to His Word by always discerning and examining our ways.

@SelahEthiopia
ከማንበብ ያለፈ የጠለቀ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እግዚአብሄርን፣ የእግዚአብሄርን ቃል፣ እንዲሁም ራሳችንን ሌሎችን እንድንረዳ ይረዳናል። በዚህ ቪዲዮ መሰረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ ዘዴዎችን እናያለን።

Creating a rich habit of diving deeper into Scripture helps us understand God, Scripture, and ourselves better. Here are some tools to help you get past just reading the Word and move on to studying and living the Word.

https://www.youtube.com/watch?v=Mp0Nze7wQ44

@SelahEthiopia
እንዲሁም ጌታን ደስ የሚያሰኘውን ፈልጉ።
— ኤፌሶን 5፥10

ከጨለማው አለም በክርስቶስ በተሰራው ስራ ወደ ብርሃን የተጠራን እኛ በዚህ በሚያልፈው አለም ስንኖር እንደ ስጋ ፈቃዳችን ሳይሆን ጌታን ደስ የሚያሰኘውን እየፈተሽን ልንኖር ይገባል። ለእዚህም መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳን እንጸልይ።

We have been called out of the darkness into the light through the work of Christ. When we live in this world, we should not live according to our temporary desires, but to test what pleases the Lord. Let’s pray the Holy Spirit guides us in these daily choices.

@SelahEthiopia
ቃሉ የሚናገረውን አድርጉ እንጂ ሰሚዎች ብቻ ሆናችሁ ራሳችሁን አታታልሉ።
— ያዕቆብ 1፥22

ታዛዥነት ትዕዛዝን ከመስማት ያለፈ እርምጃን ይጠይቃል። ታዛዥነት ጥበብን ይጠይቃል። የእግዚአብሔርን ቃል ሁል ጊዜ ማዳመጥ እና ማወቅ ተገቢ የሆነ ድርጊት ሲሆን በተግባር ማዋል ደግሞ ፍሬ አልባ ከሆነ ህይወት ያተርፈናል።

Obedience is so much more than hearing and knowing the order. Obedience shapes our response to what we know; obedience is wisdom. The Word of God is always worth hearing, and putting it into practice will make us fruitful in this life and the next.
ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት መንገድ ለእኛ ያለውን የፍቅር ልክ ያሳየናል። በዚህ ምድር በተመላለሰበት ጊዜም በሁሉም ተግባሩ ፍቅርን ሲሰብክ ኖሯል። በመጨረሻው ፀሎቱም  ከአባቱ ጋር ባላቸው ፍቅር ልክ እኛ እንድንዋደድ ፀልዮልናል። የመጨረሻ ትዕዛዙም የፍቅር ትዕዛዝ ነው። ታዲያ ይህን ትዕዛዝ በማክበር እንዴት እንኑር?

The way Jesus Christ came to earth shows us His love for us. When He walked on this earth, He preached love through all His actions. Also, in His last prayer, He prayed for us to love each one another as He loved His Father. His last commandment, His parting words, were the commandment of love. How can we live in obedience to this commandment?

https://youtu.be/2ckR2Q1SBOA

@SelahEthiopia
“እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ።”
— ማቴዎስ 11፥28 (አዲሱ መ.ት)

ኢየሱስ ከሀጢአት በስተቀር የሰው ልጅ የሆነውን በመሆን ፍቅሩን ያሳየ አምላክ በመሆኑ በህይወታችን የምናልፍበት መከራ እና ሸክም የሆነብንን ችግር ሁሉ ሊረዳ እና ሊያሳርፈን ቃል ገብቶልናል። ዛሬ በዚህ ቃል ላይ ልባችንን እናሳርፍ! የከበደንንም ሸክም ወደ እርሱ እናቅርብ። እንደ ቃሉ ሊያሳርፈን የታመነ ነውና!

Jesus showed His love by becoming man, tempted in every way just as we are yet without sin. Because of this, we know that He empathizes with us as we go through life’s ups and downs. Let's rest our hearts on this Word today! Let us bring our heavy burdens to Him.

@SelahEthiopia
ድህረ ዘመናዊው አለም ግለኝነት እና እኔነትን እንደ ጥንካሬ ይሰብከዋል። በተቃራኒው ደግሞ መፅሀፍ ቅዱሳችን ከህብረት መራቅ የእግዚአብሔር ሀሳብ እንዳልሆነ እና አንዳችን ለሌላችን አስፈላጊ እንደሆንን ያስተምረናል። ሶሬቲ እና ኢየሩሳሌም ዛሬ ስለ ክርስቲያናዊ ህብረት ጠቃሚ ውይይት ይዘውልን መጥተዋል፤ እናዳምጣቸው!

The postmodern world preaches individualism and egoism as strengths. On the contrary, the Bible teaches us it is not God's will to turn our backs on fellowship, it insists that we are a body and that we are critical for the well-being of one another. Soreti and Eyerusalem brought discuss this important topic of Christian fellowship. Take a few minutes to have a listen!

https://youtu.be/QDG0xpNdHMA
“አሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊ ነገር ላይ አይሁን።”
— ቆላስይስ 3፥2 (አዲሱ መ.ት)

ሀሳብ የተግባራችን ምንጩ ነው! ሰው በሚያስበው ሀሳብ የሚመራ በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሀሳብ በተለያየ መንገድ ይመክረናል። ታዲያ ሀሳባችን ተግባራችንን ከወሰነ በዚህ ጊዜያዊ በሆነው በምድር ቆይታችን የሀሳባችን ትኩረት ከምድሩ ባለፈው እና ዘላለማዊ በሆነው ላይ እንዲሆን ይገባዋል። መልካም ሳምንት።

Actions are born from our thoughts and from what our mind meditates on! Since we are guided by our thoughts, the Bible emphasizes the need to be mindful of what we entertain. So, if our thoughts determine our actions, then during this short life here on earth, the focus of our thoughts should be on what is eternal and spiritually valuable. Have a wonderful week.

@SelahEthiopia
ለአንድ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ የህይወት ቀዳሚ መርህ በመሆኑ መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማወቅ እንድንመላለስ ይመክረናል። የእግዚአብሔር የተገለጠ ፈቃዱ በክርስቶስ ኢየሱስ የታየ እንዲሁም በቃሉ ውስጥ አማኞች በህይወታቸው ይመላለሱበት ዘንድ በግልፅ የተቀመጠ ነው!

For a Christian, knowing God's will is the primary principle of life. The Bible directs us to walk knowing God's will. God's revealed will is shown through Jesus and is clearly stated through His Word so that believers can apply His will in their lives!

https://youtu.be/hFLtu36Puz4
የክርስቶስ መምጫ በቀረበበት በዚህ ጊዜ ንቁ እና ትጉህ መሆን ይጠበቅብናል። ትጋት ከትላንት ይልቅ ለመጨመር የሚገባን መሰረታዊ እሴት ነው። ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትጋት ያለውን ሀሳብ እና እንደ ክርስቲያን ትጋትን በየእለት ተዕለት ህይወታችን የምንለማመድበትን መንገድ ከ ዳያና እና ሩት ጋር እናያለን።

With the knowledge of the coming Christ, we are expected to live alert and diligent lives. Diligence is foundational, and should be developed in each of our lives. Today Diana and Ruth discuss the concept of diligence in light of the Bible, and how Christians can practice diligence in their daily lives.

https://youtu.be/7bB2kXuqq3U
“እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፣ በፍጹም ልባችሁም ከፈለጋችሁኝ ታገኙኛላችሁ፤”
— ኤርምያስ 29፥13 (አዲሱ መ.ት)

ሀያሉ እና ትልቅ የሆነው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሆነላቸው ማንነቶቹ አንደኛው ራሱን መግለጡ ነው። የሰው ልጆች በልፋት እና በአቅማቸው ሊያውቁት የማይችሉት እግዚአብሔር በዘመናት መካከል ለሰዎች መገኘት ችሏል። በአዲሱ ኪዳንም በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔር ራሱን ገልጧል። ይህ ባህሪ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር እና በጎነት የሚያሳይ ነው።

One of the greatest gifts from God to mankind is God revealing himself. God has been with His people since time immemorial, and it was not because of any effort from our part. But God goes even further, He revealed Himself to us in His Son Jesus Christ to show us His love and kindness.

@SelahEthiopia
“የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፤ በእሽታ መንፈስም ደግፈህ ያዘኝ።”
— መዝሙር 51፥12 (አዲሱ መ.ት)

ዳዊት በህይወቱ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ፈቀቅ በማለት አምላኩን ሲያሳዝን ራሱን በማዋረድ ረድኤትን እና የመነሳት አቅምን የሚጠብቀው ከ ራሱ ከእግዚአብሔር ነው። በህይወት ያዛለንን ድካም በማመን በእግዚአብሔር ፊት በመቅረብ የእሽታ መንፈስ ደግፎ እንዲያነሳን እንጠይቀው።

When David displeased God, he humbled himself and waited for help from God Himself. Holding our weaknessed in our hands, let us come before God and ask Him to give us a spirit of willingness, let us ask Him to help us love Him better.

@SelahEthiopia