Forwarded from አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ሰው ወደ ኃጢአት በተራመደ መጠን ሃሳቡ ደካማ ይሆናል። ወደ ኃጢአትም ያዘነብላል። በውስጡም ለኃጢአት ሥፍራ ያዘጋጃል። ተጨማሪ እርምጃ በተራመደ ቁጥር በልቡ ውስጥ የነበረው ፍቅረ እግዚአብሔር ይቀንሳል። መውደቁም ግልጽ እየሆነ ይሄዳል። ስለዚህም በመጽሐፍ _"አንች ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው "ተብሎአል። [መዝ 136*8_9] የባቢሎን ልጅ [የምርኮ ሀገር) የተባለ ኃጢአት ነው። ልጆች የተባሉት ፈቃዳተ ኃጢአት ናቸው። እነዚህን ልጆች የተባሉ ፈቃዳተ ኃጢአት የሚፈጠፍጣቸው ዓለት የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። [1ቆሮ 10*4] ስለዚህ ኃጢአትንና ፈቃዳቱን ሁሉ በክርስቶስ አጋዥነት የሚቋቋምና በአእምሮው ሲታሰብ ጀምሮ ኃጢአትን የሚጠላ ሰው ብፁዕ ነው።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@pope_shenouda
@pope_shenouda
Forwarded from አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
"ኃጢአትን ባትሰራ መልካም ነው ፤ ኃጢአት ከሠራህ ሳትቆይ ንስሐ ብትገባ መልካም ነው። ንስሐ ከገባህ ዳግመኛ ወደ ኃጢአት ባትመለስ መልካም ነው። ወደ ኃጢአት ካልተመለስክ ይህ በእግዚአብሔር ዕርዳታና ቸርነት መሆኑን ብታውቅ መልካም ነው። ይህንን ካወቅህ ስለአለህበት ሁኔታ እግዚአብሔርን ብታመሰግን መልካም ነው። "[ቅዱሱ ሰብ ባስልዮስ ]

@pope_shenouda
@pope_shenouda
✟....."#ፍቅር_የሚመነጨው፤ ከሙሉ ልብ ከሚወጣ #ጸሎት ነው። እውነቴን ነው የምላችሁ፥ ንጹሕና ጥልቅ ጸሎት ከጸለይን፤ ምኞታችን ሁሉ እግዚአብሔርን ማስደሰት ብቻ ነው።

ይህም ለሌሎች የተቀደሱ ምግባራት ያዘጋጀናል፣
#ይጋብዘናል። ሌሎችን ይበልጥ እየወደድን ስንመጣ፥ #እንዳንጎዳቸው_እንሳሳላቸዋለን

ይበልጥ በለገስን ቁጥር ለራሴ የሚለው ሐሳብ
#ይጠፋልናል። በዚህ ልምምዳችን ውስጥ እግዚአብሔርም ጸጋችንን እያበዛልንና ፍቅርን እየጨመረ #ያተጋናል

ነገር ግን ይህ ጸጋ
#ጎበዞች#ጠንካሮች#ኀይለኞች#ብልጦች ስለሆንን ሳይሆን፥ #በረድኤተ_እግዚአብሔር_ብቻ_ይገኛል።"....✟

✥እናታችን እማሆይ ጣማፍ ኄራኒ✥
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 19 days, that account will self-destruct and this channel will no longer have an owner.
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 10 days, that account will self-destruct and this channel will no longer have an owner.