Forwarded from በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw
የመኖርን ትክክለኛ ትርጉም በሕይወታቸው ያሳዩ፣ በቅኔ በትርጓሜ ከሁለት እልፍ በላይ ሊቃውንትን ያስተማሩ አራት ዐይናው የኔታ ይባቤ በላይ በዛሬው ዕለት በርካታ ሊቃውንትና ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል። ሞት ለሰው ሁሉ የተሠራ ነው። ትልቁ ቁም ነገር በፈጣሪ ዘንድ ትርጉም ያለው ሥራን መሥራት ነው። የኔታ የጀመሯቸውን መንፈሳዊ ተግባራት የሚያስቀጥሉ በርካታ ሊቃውንትን አፍርተውልን አልፈዋል።
እንደእርስዎ ሕይወታችንን ሁሉ ለታላቅ ቁምነገር አውለን እናልፍ ዘንድ አምላክ ይፍቀድልን። በረከትዎ ይደርብን።
እንደእርስዎ ሕይወታችንን ሁሉ ለታላቅ ቁምነገር አውለን እናልፍ ዘንድ አምላክ ይፍቀድልን። በረከትዎ ይደርብን።