Scripture union addis ababa
103 subscribers
607 photos
13 videos
29 files
14 links
Download Telegram
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አንዱን ስታነሳ
ታላቁ መጽሀፍ መጽሀፍ ቅዱስ ገንዘብንም ጌታንም መውደድ እንደማይቻል ያስተምረናል ሁለት መውደድ ለሁለቱም መገዛት እንደማይቻልም ይነግረናል በህይወት ስትኖር በብዙ የምርጫ ውጥረት ውስጥ ታልፋለህ በከበረውና በተዋረደው፣ በሚጠቅመውና በማይጠቅመው፣ በአንገብጋቢውና አንገብጋቢ በሆነው ነገር መሀል በምርጫ ውጥረት ህይወትን እንገፋለን። ለሁሉም መገዛት አንችልም ስለዚህ ስትመርጥ ከህይወትህ አላማ ጋር በሚሄድ ወደታች በሚያወርድህ ከከፍታህ ከምትሰራው ታላቅ ስራ የሚያስተጓጉልህን ና እንጫወት ስራው ይደርሳል ፣ ፈታ በል፣ በሗላ ትሰራዋለህ የሚሉትን አትቀበል፤ ይልቅስ የያዝከውን ታላቅ ስራ የሚያበረታታህንና የሚያጠናክርህን ነገር ምረጥ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
“ኀይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13 (አዲሱ መ.ት)

በራስህ አትችልም

ህይወት እጅግ ከባድ ነው፣ ኑሮም ትግል ነው በዚህ ከባድ ህይወት ውስጥ እየኖርክ የየቀኑን ከባድ እውነታዎች መጋፈጥም እጅግ ከባድ ነው።

ይህን አስቸጋሪ ህይወት በድል ልትጨርሰው፣ ከትግሉ በሗላ በአሸናፊነት ምትወጣው ከጌታ በምታገኘው ብርታትና ጉልበት ብቻ ነው።

ለዚህም ነው በየቀኑ ልትጋፈጠው ከምትወጣው የህይወት ጦርነቶች አስቀድመህ በማለዳ ኃይልን ከጌታ መቀበል መቻል ያለብህ። ድምጹን መስማት መንፈሱንም መሞላት ቃሉንም በልብህ እያሰላሰልህ መዋል ለህይወትህ ደስታን ለትግልህም ድልን ማግኛ የጥበብ መንገድ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ወደ ላይ ተመልከት
ምን አይነት ነገር ውስጥ ነው ያለህው? ምን አይነት ነገርስ እያስሽጨነቀሕ ነው ያለው? ምንስ ግራ አጋባህ? በህመም ላይ ህመም የሆነብህ ነገርስ ምንድን ነው?
ተስፋ ሊያስቆርጥህ ያለው ነገር ምንድን ነው? ምንም ነገር ቢከብህ ከተራራህ በላይ ታላቅ የሆነ ጌታ አለ! እርሱ አለ! በምንም ውስጥ እለፍ፣ ምንም ይግጠምህ፣ የስሜት መለዋወጥም ይኑር ወደላይ ማየት አታቁም እያመመህም መጸለይን አትተው።

ጉዳዮ ህይዉትህን እስኪናወጥ ድረስ ያደረሰ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በጽኑ አለት ላይ ተደገፍ እርሱ አቅም ለሌላቸው ብርታት መጠጊያም፣ መሸሸጊያም ነውና።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በሁሉም ነገር ውስጥ አይሀለሁ

ከማለዳው የጽሀይ ወጋገን እስከ ምሽት ጨረቃ ድረስ፣ ባለፍኩበት መንገድ ሁሉ፣ በተራራውም፣ በሸለቆውም፣ በህመሙም፣ በደስታውም፣ በጨለማውም በብርሀኑም ውስጥ።

በግራ መጋባትም፣ በመጨነቅም፣ በተስፋ መቁረጥም ጊዜ ውስጥ ጌታ ሆይ አንተን አይሀለሁ። ስታግዘኝ አይሀለሁ፣ በገጠመኝ ሁሉ ውስጥ ሳልፍ አብሮነትህን አየዋለሁ ስታግዘኝ አይሀለሁ፣ ስትመራኝ፣ ስታበረታኝ፣ ስታጽናናኝ አይሀለሁ።

መልካምነትህን መልካም ባልሆነ ነገር ውስጥም አየዋለሁ ስገፋህም እንኳ ከእኔ ሳትለይ ቆመህ በህይወት ዘመኔ ሁሉ አንተን አይሀለሁ።
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
በትምህርታችሁ civil engineering , cotm, arcitecture, hydraluics engineering የምትማሩ ልጆች ይህ ቻናል ለተማሪዎችም ምህንድስናን practice ለሚያረጉ መሀንዲሶች የሚጠቅሙ ማቴሪያሎች አሉበት ተቀላቀሉት ለምታውቋቸው መሀንዲሶችም አጋሩ።

@ethcivileng
@ethcivileng
@ethcivileng
@ethcivileng
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
Illasha A. Fekadu - ስሜ ነው - Sime New.webm
5.8 MB
🌼🌼ስሜ ነው 🌼🌼
😊😊😊😊😊😊
🎙🎙🎙🎙🎙🎙
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ከአሰተሳሰብህ ጀምር

ሁልጊዜ አዲስ አመት በመጣ ቁጥር ብዙ ነገሮችን ለመለወጥ ለመቀየርም እናስባለን እናቅዳለን አዲስ ደብተር አዲስ ቦርሳ አዲስ የቤት እቃ፣ አዲስ ቤት፣ አዲስ ሰፈር፣ አዲስ ሀገር እንቀይራለን እንደ ትላንት ላለመኖር ጥረትን እናደርጋለን።

ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ በመረጥነው የለውጥ መንገድ እንራመድና ወዲያው ወደ ትላንቱ እንመለሳለን አዲስ አመት ቢመጣም ወቅት ቢቀየርም ሀገር ብንቀይርም፣ በትምህርት ደረጃችን እየጨመርን ብንመጣም እኛ ግን በተለወጠ ዘመንና አመት ላይ እንደዛው እንደትላንት አንዳንዴም በባሰ ሁኔታ እንገኛል።

ለዚህ የሽንፈትና ውድቀት ድግግሞሽ ምክንያቱ ዘመን፣ ሀገር፣ ቤት፣ ሰፈር፣ ትምህርት ቤት፣ መለወጥ አለመለወጥ ሳይሆን፤ እኛ መለወጥን የፈለግንበት መንገድ ነው። መለወጥን ከፈለግክ ከአስተሳሰብህ ጀምር ያኔ እውነተኛ ለውጥን ታገኛለህ ትላንትን መደጋገም የማትፈልግ ከሆነ ትላንት የኖርክበትን የተበላሸ አመለካከት ለውጥ ሀገር ከመቀየር ለነገሩ ያለህን እይታ አስተካከል፤ ሁሉም ነገር ከአስተሳሰብ ይጀምራል

እይታክም እንኳ የአስተሳሰብህ ውጤት ነውና ምንም ነገር ለመለወጥ ከማቀድህ ቀደም ብለህ አስተሳሰብህን መርምር፣ በጥልቀት ቁጭ ብለህ አስብ ለራስህ ጊዜን ስጠው ያኔ የችግርህን ስር አስተሳሰብህ ሆኖ ታገኘዋለህ ያን አስተሳሰብ ነቅለህ አውጣ ያኔ እንዳትራመድ ካገደህ ሰንሰለት እና ትብታብ ትፈታለህ።

ነጸነትህ፣ የምትናፍቀውም ለውጥ የሚገኘው በአንተው እጅ ውስጥ ነው። ለውጥን ከውጪ አትፈልገው ቦታ በመለወጥ፣ ሀገር በመቀየር ዘላቂ ለውጥ አይመጣም ዘላቂ ለውጥን ምትሻ ከሆነ አስተሳሰብህን በመመርመርና በመለወጥ ጀምር።


🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ🌼


🌼🌼🌼መልካም በአል🌼🌼🌼
🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼🌼
🌼🌼🌼መልካም ቀን ተመኘሁ🌼🌼🌼

🌼🌼መስከረም 1/ 2014🌼🌼
ሳሙኤል ከበደ

🌼🌼🌼@youthfocus🌼🌼🌼
🌼🌼🌼@youthfocus🌼🌼🌼
🌼🌼🌼@youthfocus🌼🌼🌼
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
🌼🌼በ2014 አዲስ ልብወለድ🌼🌼
በyouthfocus channal
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
Illasha Fekadu - እውነት - Ewnet.webm
5.4 MB
🎧🎧🎧illasha Fekadu 🎧🎧🎧 🎼🎼🎼Ewnet እውነት 🎼🎼🎼 Amezing song cant stop hearing it!!!

@youthfocus @youthfocus @youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በማስተዋል ተመላለስ
ምሳሌ ፪
በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ጥበብንና ማስተዋልን አብዝተህ ፈልግ ከምንም ነገር አስቀድመህ እርሷን እሻት ከከበረው ሀብት በላይ ውድ ከሆነው እንቁ በላይ ጥበብን አብዝተህ ፈልጋት ከክፋት ከአደገኛም ወጥመድ እርሷ ትጠብቅሀለች።
ውብ፣ ምትማርክ ሆና መንገድዋ ግን ወደ ሞት ከምትወስደው እርሷ ትጠብቅሀለች፣ ዘመንህን በጸጸትና ሀዘን ከመምራት ታስመልጥሀለች።
ከምንም ነገር በፊት አስቀድመህ ጥበብን ፈልጋት።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ሁሌም

በህይወት ስትኖር ብዙ ውድቀት አለመሳካት ስህተቶች ትሰራለህ ከዚህም የተነሳ ልብህ ይሰበራል ተስፋም ትቆርጣለህ በእንደዚህ አይነት መንገድ ማለፍ ከባድ ነው። ለሰውም ልናስረዳው የምንችለው ነገር አይደለም ስለ ሁሉም ነገር ተስፋ መቁረጥና ጨለማ ብቻ ይታየናል። ስሜታችንን አብዝተን የምንሰማ ከሆነ እስከሞት ድረስ የስሜት መለዋወጦቹ ሊያደርሱን ይችላሉ

በእንደዚህ አይነት ግራ አጋቢና ተስፋ አስቆራጭ መንገድ ስትጓዝ አንድ ነገር ግን ማስተዋል አለብህ ሁል ጊዜም ሁለተኛ እድል አለ።
በምንም አይነት የውድቀት ጎዳናላይ ሁን የገነባሗው የትኛውም ነገር ይፍረስ ሁለተኛ እድል እንዳለ ግን አትርሳ።

ከአንተ የባሰ ብዙ እጣ ደርሶአቸው መልሰው ራሳቸውን ከወደቁበት አንስተው የፈረሰውን ነገር እንደገና ገንብተው፣ በብርታት በክፍታ ላይ መቆም የቻሉ እንዳሉ እወቅ።

የፍቅር ህይወትህ፣ ትምህርትህ፣ ስራህ፣ ቢዝነስህ.... የትኛው ነገር ተበላሸብህ? የትኛውስ ነገር ከመጠገን በላይ ፈራረሰብህ አይዞህ ስሜትህን አድምጠህ ማዘንህም ግራ መጋባትህም ትክክል ነው ነገር ግን ደግሞ ቆም ብለህ ሁሌም እድል እንዳለ ነገ አዲስ ቀን እንደሆነ ቁስልህ እንደሚፈወስ፣ ተስፋህም እንደሚመለስ አስተውል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የምርጫ ውዝግብ
በህይወትህ ከልጅነት ዘመን ወደ ብስለት ወይም እድገት ስትመጣ ብዙ ግራ ሚያጋቡ፣ እንቅልፍ የሚነሱ፣ የሚያሳስቡ የሚያስጨንቁ ምርጫዎች፣ አጣብቂኝ ውስጥ ትገባለህ። ብዙ ምርጫ ባለበት አለም ውስጥ እየኖርክ በየቀኑ ቀላል የማይባሉ ምርጫዎች ይቀርቡልሀል ታዲያ ከእንደዚህ አይነት ውዝግብ እንዴት ታመልጣለህ? እውነታው ከሁሉም መሸሽ አትችልም ነገር ግን ለመወሰን ግን ነገሮችን የበለጠ ግልጽ እንዲሆንልህ ልታረጋቸው የምትችላቸው ነገሮች ልጥቀስልህ
፩ በብስለት ማደግ
ብስለት ከተፈጥሮ፣ ከልምድ፣ ከንባብ፣ ከስህተቶች ልታገኝ ትችላለህ በተለይ ደግሞ ብዙ ከማንበብ ቀድመህ በብዙ ርእሶች ላይ በንባብ ራስህን ማሳደግ እጅግ ጠቃሚ ስልት ነው።

፪ ጊዜያዊውን ሳይሆን ዘላቂውን ማሰብ ወይም መመልከት
የምትወስነው ውሳኔ ነገህ ላይ የራሱ የሆነ ተጽእኖ አለው ታዲያ ስትወስን የዛሬን ደስታና ምቾት ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት በአንተ ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖ አስበህ ውስን

፫ ከራእይህ አንጻር ምረጥ
ከራእይህ ጋር የማይሄድን ነገር አትምረጥ ምንም ያህል ብትወደውም ብትፈልገውም ምርጫህ ከራእይህ አንጻር ይሁን ምክንያቱም ከምትኖርለት ነገር እንዳይለይህ ዋጋ ከምትከፋልለት ነገር እንዳያርቅህ። ስትመርጥ ከራእይህ አንጻር ምርት

፬ ምን ጊዜም ለመወሰንም ለመምረጥም አትቸኩል
በችኮላ የምታረገው ነገር ዋጋ ያስከፍልሀል ለውሳኔ አትሩጥ የሚያቻኩል ነገር ቢኖርም እንኳ በነገሩ ላይ እደርበት። ዛሬ የቀረበልህን ምርጫ አድረህ ስታስበው እንደ ትላንቱ ላይሆን ስለሚችል ዛሬ ለውሳኔ አትቸኩል ራስህንም ሌሎችንም ግራ ከማጋበት ትድናለህ።
**** በተቻኮልክ ቁጥር ስህተት እንደሚበዛ እወቅ የማትጸጸትበት ምርጫ በጥልቅ አስበህበት የምትመርጠው ምርጫ ነው።

፭ በአንደኛነትና በዋናነት ፈጽመህ ፈጽመህ መጸለይን እንዳታቆም ግራ ስትጋባም እንደውም መጽለይህን ቀጥል ጌታ ዝም ያለህ ቢመስልህም መጸለይህን ግን በምንም አይነት መንገድ እንዳታቆም።
ስትጸለይ ነገሮች ይበልጥ እየጠሩ ይመጣሉ፣ እይታህም እየተቀየረ ይመጣል።
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ሁሉም ነገር ያልፋል
ዛሬ የገጠመህ ህመም ያልፋል፣ ያልተጠበቀው ገጠመኝንም አልፈህው እንደ ታሪክ ታየዋለህ ዛሬ እንዲህ ህመም ውስጥ ስልክህ ነገም እንዲሁ ይሆናል ማለት አይደለም ዛሬ ነገ አይደለምና ይህንም ታልፈዋለህ። አይዞህ ምታልፈበት ከባድ ነው። ቀላል ነገር አልገጠመህም፣ በእለት ኑሮህ ስቃዩ ላስተዋለው ከባድ ሲቃ ነው። ግን ይህ ህመም ለዛሬ ብቻ ነው መሽቶ ሲነጋ አዲስ ቀን ሲመጣ ይህ ሁሉ ያልፋል እስኪ እስከ ዛሬ የመጣህበትን መንገድ ተመልከት አላልፈውም ያልከውን ሁሉ እርሱ አላሻገረህም፣ አላሳለፈህም አሁንም ጠንክር በርታ አይዞህ ከባዱን ስቃይህን፣ መገፋትህን የሚያይ በላይ በሰማይ አምላክ አለ። ይረዳሀል ታልፈዋለህ ትወጣዋለህ።

በተሰማህ ህመም ምክንያት በራስህ ላይ መጥፎ እርምጃን ውሳኔንም አትውሰድ ለሚያልፋ ቀን የማያልፍን ህመም በራስህ አትጨምር በተሰማህ ከባድ ህመም የባሰ ራስህ እንዳትጎዳ።

አይዞህ በርታ እግዚአብሔር አለልህ

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጥቅመኝነት ወዳጅነት
ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ያለው ጌታ ሰውን ለሌላኛው ሰው ሰጥቷል። በምድር ላይ ለሰው ልጅ እጅግ ከባዱ ነገር ብቸኝነት ነው። ይህን ብቸኝነት ለማስወገድ ሰው ሰውን ይፈልጋል፣ ለሰው መድሀኒቱ ሰው ነውና! እውነታው ግን ጓደኝነት፣ ወዳጅነት ጥቅመኝነት ከሆነ ሰነባብቷል። በብቸኝነትህ በችግርህ ግራ በተጋባህበት ወቅት እንኳን ሰው ሊደርስልህ ሰውን ፈልገህ ላውራህ/ሽ እፈልግሀለሁ/ሽ ብለን እንኳ ሰው አይገኝም። ነገር ግን የሆነ ነገር አንተ ጋር ካለ ወይም የተሻለ እጣ እንደገጠመህ ሲያውቁ ግን ፈልገው አፈላልገው ይመጣሉ።

በተቸገርክ ሰአት ማን አገዘህ ማን ቆመልህ? አንድ ሰው ካገኘህ እጅግ እድለኛ ነህ። ቆይ ለመሆኑ
የወዳጅ፣ የጓደኛ ትርጉም ምን ይሆን? ጥቅመኝነት ወይስ አኑአሪነት? በጠራራ ጽሀይ በመብራት ይዞ ከተማዋን ሲዞር ለነበረው ፈላስፍ ምን ተፉጠረ? ምን ሆነህ ነው እንደዚህ ግራ ገብቶህ በከተማ ምትዞረው ሲባል መልሱ እጅግ ሚገርም ግራም ሚያጋባ ነው " ሰውን እየፈለኩ ነው" ያለው እኛም ሰውን ፍለጋ እንደዛ በጠራራ ጽሀይ መብራት አብርተን በከተማ ለመዞር ምንም አልቀረንም።

ሰዎች ግን ምን ነክቶናል እንዴት እንደዚህ ራስ ወዳድ ሆንን? እንዴት ለጎረቤታችን መሆን አቃተን? እንዴት ለተቸገረው፣ ግራ ለገባው የራሳችንን ነገር ጎዶሎአችንን፣ ህመማችንን ቻል አርገን ለሌላው መሆን አቃተን?? ሰው መሆን ታዲያ ምን ይሆን? ለሌላው ካልቆም ለወዳጅ ዋጋ ካልከፈልን?

ይህ ዘመን ግን ከየትኛውም ጊዜ በባሰ ሰው የጠፋበት ዘመን ሆኗል እውነተኛ ሰው የት ይሆን የሚገኝ? የራስን ሳይሆን የሌላን መልካም የሚመኝ፣ ከራስ በፊት ወዳጁን የሚያስቀድም፣ እየተቆረሰ የሚኖር፣ በቅናትን በተንኮል የሚኖር ሳይሆን ስለ ሌላው መልካም የሚደሰት።
ንጉስ ዳዊት ልጁን ሰለሞንን በህይወት መጨረሻ ከአባቶቹ ጋር ከማሸለቡ በፊት የመከረው ምክር ልጄ ሆይ ሰው ሁን ነው ያለው።
ሰው መሆን ለሌላው ሰው መገኘት ለሌላው መቆረስ ለሌላው መኖር።
እስቲ ዛሬ ይህች ቀን ሌላን ሰው የምናስቀድምበት ሌላን የምናስበት ቀን ይሁንልን የራሳችንን ትተን የሌላን።
ሰው ሆይ የት ነህ? የሰው ሁሉ ጥያቄ ይህ ነው
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጡት ከመጥባት የሚጀምረው የ ህይወት ሂደት አጥንት እስከመጋጥ ይደርሳል ።ጡት ያልጠባ እና ጥርሱ ያልጠነከረ ልጅ አጥንት የመጋጥ አቅም እንደሌለው ሁሉ ።መማር ባለባቸው ጊዜ ሲያስተምሩ መቀበል ሲኖርባቸው ካቅማቸው በላይ ሲሰጡ ።ማስቀደም ያለባቸውን ባለማስቀደማቸው ለከፍተኛ የስሜት መጎዳት እና ለማንነት ቀውስ የተጋለጡትን ቤት ይቁጠራቸው ።





ችግሩ ካላወቅን መፍትሄው እንደሚርቅ ችግሩን በጥልቀት መረዳት ለመፍትሄው ያቀርበናል እና አለም ያዘባችውን priority ትክክል ነው ብላ የነገረችን ሀሳባች አጥብቀን በመቃወም እንዲሁም ሀሳብን በሀሳብ በመመከት ሀሳቧን ከንቱ ማረግ እንችላለን ።


አብዛኖቻችን እ/ር ከልብ መውደድ ባለብን ሰአት ስዎችን በመውደድ እ/ር ይቀድማል ካለን ይልቅ የመሰለንን በ መምረጣችን ጉዳት ላይ ወደቀናል ።አንደኛ ማረግ ያለብንን ነገሮች ከየት ማግኘት እንዳለብን እንኳን ሳናውቅ አለም የሰጠችን ቅደም ተከተል አሜን ብለን ተቀብለን ከታች ወደ ላይ እንደ መጀመር ሆኖብን ህይወት ትርጉም እስከማይሰጠን ድረስ ያለንን ሁሉ ከፈልን ። በ አለም ቅደም ተከተል ተማምነን እ/ር በእኛ የሚያሳድገውን አላማ ገደልን ።


"ከሞተልን ይልቅ ሌሎችን አቀረብን !!" ቀዳሚ ማረግ ያለብን ሗላ አረገን ብዙ ተጎድተናል።



የእ/ር ቃል በሉቃስ ፲:፪፯ ፣ማር ፩፪: ፫፫ እንደሚነግረን ወደ ላይ እና ወደ ጎን እንደሆነ ነው።አንድ ወንድም ክርስትና XY plane ነው ብሎ ነበር ።ይህ ማለት ደግሞ እ/ር በቅድሚያ ከሁሉም በፊት እርሱን እንድንወድ እና ለእርሱ የታመንን ወዳጃች እንድንሆን ይፈልጋል ።ይህን ያደረገ አንድ አማኝ ወንድሙን ለመውደድ ችግር አይገጥመውም ! ለዛውም በእውነተኛ ፍቅር ❤️ነገር ግን አንድ እ/ር የማይታዘዝ እና ማይወድ ሰው አብሮት ያለውን ሰው ይወዳል ማለት ያዳግታል ።




ስለዚህ እ/ር ምንንም እና ማንንም ከመውደዳቸው በፊት እርሱን በርህይወታችን እንድናስቀድም መንግስቱ በ ህይወታችን እንዲታይ ይፈልጋል ።ብዙዎቻችን የሳትነው ሀሳብም ይሄው ነው !!! አዎ ከምንም እና ከማንም በፊት የ እ/ር ህይወታችን ውስጥ መቅደም ይኖርበታል።





አለም ስኬት ፣እውቀት ፣ሀብት ይቀድማል ብትለንም የ ሚቀድመው ግን የ እ/ ር ሀሳብ እና ፅድቁ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል ።




"የ አለም ኮተት ስንከተል እየኳተን ከሆንን ከታች ወደ ላይ ለመጀመር እየሞከርን ስለሆነ ስብራቱ ከባድ በመሆኑ ወደ ትክክለኛው የህይወት መርህ በ መመለስ እራሳችን ላይ ከሚመጡት አስጊ ጉዳቶች እንከላከል ይህንንም እውነታ ለ አንድ ሰው በማጋራት ሀላፊነታችንን እንወጣ ።
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የ ዛሬው መልክቴ ነው !!



✍️ሊዲያ ቴዎድሮስ
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የሰው ውስጥ ነው ውበቱ
በዚህ ውጫዎ ማንነት ላይ ወይንም ማቴሪያል ላይ በሚያተኩር ዘመን ሰው ሁሉ ትኩረቱ በሰው ዘንድ ተወዳጅነትን፣ ተቀባይነትን ለማግኘት ውስን ማስዋብ ላይ ብቻ የተወሰነ ይመስላል። የሰው ልጅ ለውበት ትልቅ ቦታ ስላለው ውስጥም ሳይሆን አስቀድሞ ውጫዊ ውበትን እንመለከታለን። ሰውን በሰውነቱ ከመቀበልና ከማክበር ይልቅ ውጫዎ ማንነቱ ላይ ብቻ እንወሰናለን።

የሚገርመው ግን የሚያኖረን ውበት ሳይሆን ማንነት እንደሆነ አልተረዳንም በውጪ ተውበንና አምሮብን ውስጣችን ግን መጥፎ ነገር የተሞላን በውጭ ስንታይ የምናብረቀርቅ ውስጣችን ግን ለሰው የሚሆን አንዳች ነገር የሌለን ሰዎች አብዛኛውን ጊዜያችንን አለም መለኪያ አርጋ ባስቀመጠችው የውጪ ውበትና ማራኪነት ላይ ብቻ አተኩረን ዘመናችንን ሁሉ እሱን እያስዋብን እያሽሞነሞንን የውስጥ ማንነታችን ላይ አንዳችም ነገር ስላልጨመርን ነው። ከውጪ ይልቅ የውስጥ ማንነታቸው ላይ ጊዜያቸውንና ዘመናቸውን ያጠፋ ጥቂት ብርቅ አእምሮና ማንነት የተጎናጸፋ ጥቂት ወንድና ሴት ልጆች አሉ እንደአለም መለኪያ ሳይሆን እንደ እግዚአብሄር ቃል ራሳቸውን በቃሉ እና በእግዚአብሄር መንፈስ ሙላት ያስጌጡ እንደአብጊያ ታላቅ አእምሮ ያላቸው ለሚኖሩበት ማህበረሰብም ሆነ ላላቸው የፍቅር የትዳር አጋር በረከት የሆኑ ጥቂት የሚባሉ ናቸው።

እውነተኛ ውበት የውስጥ ማንነት ነው፤ የሚያኖረን ማንነት ውብ የሆነ ማንነት ነው። ፊትን ቁመናን አለባበስን ብቻ ተመልክቶ መፍረድም ሆነ ውበትን ብቻ መፈለግ ውስጡ ሌላ ውጪው ሌላ ሆኖ ላልተጠበቀ ቀውስ ሊዳርግ ይችላል። ይህንን ስል ልናስተውል የሚገባው ነገር ለውበት ቦታ መስጠት አያስፈልግም እያልኩ ሳይሆን ግን ሰውን በማንነቱ እንጂ ባለውና በሌለው መመዘን ትክክል አለመሆኑን ለመጠቆም ነው። ውበትም ደምግባትም ከንቱ ነው ዛሬ ታይቶ ነገ የማይገኝ ነው ማንነት ግን በየእለቱ እድሜ ሲጨምር እየጨመረ ሚሄድ እንጂ ሚጠፋ አይደለም። ( እንደ ምክር ቢጤ ጣል ላድርግ የነገ ትዳርህን መልካም ማድረግ ከፈለግክ ባላስህን ጠብቀህ ምረጥ ውበት ላይ ብቻ አትመርኮዙ እሱ ዘላቂ ያልሆነ ስላልሆነ ይልቅ የሚያኖርህ/ሽ መልክ ሳይሆን ማንነት ስለሆን ውብ ማንነት ያለውን ምረጪ/ጥ አንተም አንቺም ከምንም በላይ ውስጥ ማንነት ላይ እንስራ ነገ ለምናገኘው የህይወት ዘመን አጋር መልካም ሰው ምን ሆነው ያኔ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አሁን ያለህበት ህመም፣ ችግር፣ ግራ መጋባት፣ ለዛሬ ብቻ ነው ነገ አዲስ ቀን ነው ለጥቂት ጊዜ በዚህ መንገድ ታልፋለህ ነገ ጸሀይ ስትወጣ ሁሉም አዲስ ይሆናል!

አይዞህ በርታ አይዞሽ በርቺ
እግዚአብሄር አለልን እርሱ ይበቃናል

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ህይወት
ህይወት ልክ እንደዚህ የልብ ምትን ማንበቢያ ማሽ ናት አንዳንዴ ከፍታ፣ አንዳንዴ ዝቅታ ፣ ግራ መጋባት፣ ጨለማ፣ ብርሀን የነዚህ ነገሮች ሁሉ ድምር ናት መኖራችን ሚታወቀው ልክ ይህ ማሽን የልብ ምትን እንደሚረዳበት ነው ሰው በከፍታ ይኖራል ደግሞም በዝቅታ ያልፋል በአንዱ ማለትም በከፍታ ወይም በዝቅታ ብቻ አይኖርም የሁለቱም ድምር ውጤት ነው። መሽቶብሀል አይዞህ ይነጋልሀል፣ ግራ ገብቶሀል አይዞህ እርሱ እንደሰማዩ ቀለም ጥርት ያረግልሀል ብቻ ጸንተህ ጠብቀው በምታልፍበት መንገዱ ሁሉ እርሱን አጥብቀህ ያዝ፣ ምንም ያህል ነገሩ ቢከብድ በጌታህ ተስፋ አትቁረጥ መጸለይህን ቀጥል።
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
1ኛ ጴጥሮስ 3 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን፤
⁴ ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን።

እግዚአብሄርን ምትፈራ ሴትን ማን ያገኛታል? ላገኛትም ሰው እጅግ ማረፊያ በረከትም ናት። ውበት ጠፊ ነው። ውጫዊው ነገር ሁሉ ዛሬ ታይቶ በጊዜ ሂደት ሚደበዝዝ ነው። ራሷን እግዚአብሄርን በመፍራት መኖር ያለማመደች ሴት ግን ዘመናት ቢያፋ ወቅት ቢፈራረቅ እየደመቀች ትሄዳለች ላገኛት ሰውም በረከት እና ማረፊያ ናት።

ቃሉ እንደሚል ከውጪ ይልቅ ውስጥሽን በቃሉ እና በመንፈሱ አስውቢ። ጥበብን ከእርሱ ተቀበይ ያኔ ቤትሽ ዙሪያሽ ያሉ ሁሉ በአንቺ ምክንያት ማረፊያ ትሆኛለሽ

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በግንባታ ላይ
ህይወት ዝብርቅርቅ ብሎብህ ይሆናል፤ ነገሮች ሁሉ ግራ እያሃቡህም ይሆናል፣ ምን ማድረግ እንዳለብህ ላታውቅም ትችላለህ የግንባታ ቦታዎችን ተመልክተህ ከሆነ ዝብርቅርቅ ያሉ ግራ ሚያጋቡ ስፍራዎች ናቸው የግንባታ እቃዎች በየቦታው ተበታትኖ፣ ሰራተኞች በየፊናቸው ደፋ ቀና ሲሉ በውጭ ተለጥፎ በምስል ተውቦና አምሮ የምታየው የህንጻው ምስል እና በመሬት ላይ የሚገነባው በግንባታው ሂደት ወቅት ለየቅል የሆነ እንደሆነ ትታዘባለህ ነገር ግን በቀኑ መጨረሻ ያየህው ምስል እና የተገነባው ህንጻው ቁጭ አንድ አይነት ይሆናሉ። ያንተም ህይወትህ እንዲሁ በግንባታ ላይ እንደሆነና ተስርተህ እንዳላለቅክ ማወቅ ይኖርብሀል ለዚህም ነው መዘበራረቁ ግንባታ ሂደት ነው ትእግስት ይፈልጋል ጊዜ ይፈልጋል አይዞህ በርታ ጥቂት ጊዜ ነው። በሂደቱ ውስጥ እያለህ ህይወትን ባለህበት ደረጃ ለማጣጣም ሞክር።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus