Scripture union addis ababa
103 subscribers
607 photos
13 videos
29 files
14 links
Download Telegram
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ህይወት እና ትግል

በምድር ላይ እስካለን ድረስ በብዙ ትግል መኖራችን እሙን ነው። በምንኖርበት በእያንዳንዱ ቀን እልህ አስጨራሽ፤ ተስፋ አስቆራጭ የህይወት ፈተናዎች ይገጥሙናል። አንተ ብቻ ላይ አንዱን ስትጨርስ ሌላውን የሚወረውር ሰው እንዳለ አታስብ። ይልቅስ በእንደዚህ አይነት ከባድ የህይወት እውነት የምትኖረው አንተ ብቻ ሳትሆን 7ቢሊዬን ህዝብ እንዳለም አትርሳ።

መፍትሄን ስትፈልግ ችግርህ ላይ በማተኮር መፍትሄ እንደማይመጣ ጠንቅቀህ ተረዳ። ይልቅስ የባሰ ውዝግብ እንጂ ለችግርህ መፍትሄ ማግኘት ከፈለግክ ግን ችግሩ ላይ ሳይሆን መፍትሄው ላይ አተኩር የችግሩን ምንጭ ከስሩ ለመረዳት ባለህ ሀይል ሁሉ ጣር ምንጩን ካወቅክ መፍትሄው ቀላል ስለሆነ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
"Those heights by great men, won and kept, were not achieved by sudden flight. But they, while their companions slept, were toiling upward in the night."

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
እሴት ጨምርበት
ኢትዮጲያ ህዝቦቿም እጅግ ከሚታወቁባቸው ነገሮች መሀል ለቡና ያለን ስፍራ ትልቁን ቦታ ይይዛል በእያንዳንዱ የህይወት ጉዟችን ውስጥ ቡና ትልቁን ስፍራ ይይዛል ከዛም ባለፈ ትልቁም የገቢ ምንጫችን ነው። በፈረንጆቹ 2018 አም ወደ ውጪ በላከችው ጥሬ ቡና 800 ሚሊዮን ዶላር አስገብታለች። ነገር ግን የአሜሪካው ስታር በክስ የብና ካፌ በዚሁ አመት 4.5 ቢሊየን ዶላር እንዳስገባ ጥናቶች ይጠቁማሉ የዚህ ሁለት የገንዘብ ልዮነቶች ምክንያት እሴት የመጨመርና እሴትን ያለመጨመር ልዮነቶች ናቸው።

ዛሬ በእጅህ ላይ ያለው ጥሬ የምትለው ነገር ምንድን ነው ጥቂት የምትለው በዛ ትንሽ ነው ባልከው ነገር ላይ እሴትን ጨምርበት ያኔ ካሰብከው በላይ የስኬት ማማ ላይ ትገኛለህ ካንተ ሚጠበቅው ማንነትህ ላይ አእምሮህ ላይ ስራህ ላይ እሴትን መጨመር ነው። ጊዜህን አቅምህን ሁሉ አሟጠህ ባለህ ነገር ላይ እሴትን ጨምርበት

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
From 2010 leaders training for reminder
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የገጠመህን ችግር በብዙ ህመምና ችግር አልፈህ ከዚህ በሓላ እረፍት ነው የምፈልገው፣ ምንም አይነት ነገር እንደማይገጥምህ አታስብ፤ ህይወት ሁል ጊዜ አንዱን ስታልፍ ባልጠበቅከው በሌላ ችግር ትገናኝሀለች፣

ስለዚህም ልታረግ የምትችለው አንድ ነገር ቢኖር በርትተህ መራመድ ብቻ ነው።
አንዱን ስታልፍ ሌላው አንዱን ስትሻገር ደግሞ ሌላ እንደሚገጥምህ እወቅ ነገር ግን ሁሌም ከአምላክህ ጋር ተጣበቅ ከእርሱ ጋር ከሆንክ ሁሉንም በድል ያሻግርሀል።

🖋አዞህ ልብህንም በአምላክህ አበርታ🖋

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጉልበቴ
እጅግ አታካችና አድካሚ በሆነው በዚህ አለም ውስጥ ስትኖር በየእለቱ ጉልበትህን የሚያዝሉ፣ ሀይልህን የሚቀሙ፣ ተስፋህን ለማጥፋት የሚጥሩ፣ ውስጥ ግን የሚበሉ ብዙ የህይወት ትግሎች አሉ ታዲያ ይህን ለመቋቋም እንዴት ይቻል ይሆን?መልሱ ቀላል ነው ብርታትህ ጉልበትህ፣ በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብትሄድ ክፋን እንዳትፈራ ኃይልን የሚሰጥህ ከአምላክህ ጋር የምታደርገው የሁል ጊዜ የጥሞ ጊዜ ነው።

የገጠመህን፣ የምታልፍበትን፣ ውጣ ውረዱንም ሁሉ ለማለፍ ታላቅ ብርታትህ ከአምላክህ ጋር በጸሎት በዝማሬ፣ በአምልኮ፣ በቃሉ በኩል የምታደርገው ህብረት ነው። ሁሉን የሚያስችልህ ክርስቶስ ነው ከእሱ ጋር ሆነህ ደግሞ ሁሉን ትችላለህ ብቻ አንተ ከእሱ ጋር አብዝተህ ተጣበቅ በሁሉም ሁኔታ ከእሱ አትለይ አትራቅ በተገፋህና በተቸገርከው ልክ አብዝተህ ወደ እሱ ተጠጋ። ያኔ በህይወት የሚገጥሙህን ፈተናዎች በድል ትወጣለህ።
ከእሱ ስትርቅ ብቸኛ ተስፋህን እየገፋህ እና እየሸሸህ እንደሆነ አስተውል!!!

“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አንዱን ስታነሳ
ታላቁ መጽሀፍ መጽሀፍ ቅዱስ ገንዘብንም ጌታንም መውደድ እንደማይቻል ያስተምረናል ሁለት መውደድ ለሁለቱም መገዛት እንደማይቻልም ይነግረናል በህይወት ስትኖር በብዙ የምርጫ ውጥረት ውስጥ ታልፋለህ በከበረውና በተዋረደው፣ በሚጠቅመውና በማይጠቅመው፣ በአንገብጋቢውና አንገብጋቢ በሆነው ነገር መሀል በምርጫ ውጥረት ህይወትን እንገፋለን። ለሁሉም መገዛት አንችልም ስለዚህ ስትመርጥ ከህይወትህ አላማ ጋር በሚሄድ ወደታች በሚያወርድህ ከከፍታህ ከምትሰራው ታላቅ ስራ የሚያስተጓጉልህን ና እንጫወት ስራው ይደርሳል ፣ ፈታ በል፣ በሗላ ትሰራዋለህ የሚሉትን አትቀበል፤ ይልቅስ የያዝከውን ታላቅ ስራ የሚያበረታታህንና የሚያጠናክርህን ነገር ምረጥ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
“ኀይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13 (አዲሱ መ.ት)

በራስህ አትችልም

ህይወት እጅግ ከባድ ነው፣ ኑሮም ትግል ነው በዚህ ከባድ ህይወት ውስጥ እየኖርክ የየቀኑን ከባድ እውነታዎች መጋፈጥም እጅግ ከባድ ነው።

ይህን አስቸጋሪ ህይወት በድል ልትጨርሰው፣ ከትግሉ በሗላ በአሸናፊነት ምትወጣው ከጌታ በምታገኘው ብርታትና ጉልበት ብቻ ነው።

ለዚህም ነው በየቀኑ ልትጋፈጠው ከምትወጣው የህይወት ጦርነቶች አስቀድመህ በማለዳ ኃይልን ከጌታ መቀበል መቻል ያለብህ። ድምጹን መስማት መንፈሱንም መሞላት ቃሉንም በልብህ እያሰላሰልህ መዋል ለህይወትህ ደስታን ለትግልህም ድልን ማግኛ የጥበብ መንገድ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ወደ ላይ ተመልከት
ምን አይነት ነገር ውስጥ ነው ያለህው? ምን አይነት ነገርስ እያስሽጨነቀሕ ነው ያለው? ምንስ ግራ አጋባህ? በህመም ላይ ህመም የሆነብህ ነገርስ ምንድን ነው?
ተስፋ ሊያስቆርጥህ ያለው ነገር ምንድን ነው? ምንም ነገር ቢከብህ ከተራራህ በላይ ታላቅ የሆነ ጌታ አለ! እርሱ አለ! በምንም ውስጥ እለፍ፣ ምንም ይግጠምህ፣ የስሜት መለዋወጥም ይኑር ወደላይ ማየት አታቁም እያመመህም መጸለይን አትተው።

ጉዳዮ ህይዉትህን እስኪናወጥ ድረስ ያደረሰ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በጽኑ አለት ላይ ተደገፍ እርሱ አቅም ለሌላቸው ብርታት መጠጊያም፣ መሸሸጊያም ነውና።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በሁሉም ነገር ውስጥ አይሀለሁ

ከማለዳው የጽሀይ ወጋገን እስከ ምሽት ጨረቃ ድረስ፣ ባለፍኩበት መንገድ ሁሉ፣ በተራራውም፣ በሸለቆውም፣ በህመሙም፣ በደስታውም፣ በጨለማውም በብርሀኑም ውስጥ።

በግራ መጋባትም፣ በመጨነቅም፣ በተስፋ መቁረጥም ጊዜ ውስጥ ጌታ ሆይ አንተን አይሀለሁ። ስታግዘኝ አይሀለሁ፣ በገጠመኝ ሁሉ ውስጥ ሳልፍ አብሮነትህን አየዋለሁ ስታግዘኝ አይሀለሁ፣ ስትመራኝ፣ ስታበረታኝ፣ ስታጽናናኝ አይሀለሁ።

መልካምነትህን መልካም ባልሆነ ነገር ውስጥም አየዋለሁ ስገፋህም እንኳ ከእኔ ሳትለይ ቆመህ በህይወት ዘመኔ ሁሉ አንተን አይሀለሁ።
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
በትምህርታችሁ civil engineering , cotm, arcitecture, hydraluics engineering የምትማሩ ልጆች ይህ ቻናል ለተማሪዎችም ምህንድስናን practice ለሚያረጉ መሀንዲሶች የሚጠቅሙ ማቴሪያሎች አሉበት ተቀላቀሉት ለምታውቋቸው መሀንዲሶችም አጋሩ።

@ethcivileng
@ethcivileng
@ethcivileng
@ethcivileng
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
Illasha A. Fekadu - ስሜ ነው - Sime New.webm
5.8 MB
🌼🌼ስሜ ነው 🌼🌼
😊😊😊😊😊😊
🎙🎙🎙🎙🎙🎙
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ከአሰተሳሰብህ ጀምር

ሁልጊዜ አዲስ አመት በመጣ ቁጥር ብዙ ነገሮችን ለመለወጥ ለመቀየርም እናስባለን እናቅዳለን አዲስ ደብተር አዲስ ቦርሳ አዲስ የቤት እቃ፣ አዲስ ቤት፣ አዲስ ሰፈር፣ አዲስ ሀገር እንቀይራለን እንደ ትላንት ላለመኖር ጥረትን እናደርጋለን።

ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ በመረጥነው የለውጥ መንገድ እንራመድና ወዲያው ወደ ትላንቱ እንመለሳለን አዲስ አመት ቢመጣም ወቅት ቢቀየርም ሀገር ብንቀይርም፣ በትምህርት ደረጃችን እየጨመርን ብንመጣም እኛ ግን በተለወጠ ዘመንና አመት ላይ እንደዛው እንደትላንት አንዳንዴም በባሰ ሁኔታ እንገኛል።

ለዚህ የሽንፈትና ውድቀት ድግግሞሽ ምክንያቱ ዘመን፣ ሀገር፣ ቤት፣ ሰፈር፣ ትምህርት ቤት፣ መለወጥ አለመለወጥ ሳይሆን፤ እኛ መለወጥን የፈለግንበት መንገድ ነው። መለወጥን ከፈለግክ ከአስተሳሰብህ ጀምር ያኔ እውነተኛ ለውጥን ታገኛለህ ትላንትን መደጋገም የማትፈልግ ከሆነ ትላንት የኖርክበትን የተበላሸ አመለካከት ለውጥ ሀገር ከመቀየር ለነገሩ ያለህን እይታ አስተካከል፤ ሁሉም ነገር ከአስተሳሰብ ይጀምራል

እይታክም እንኳ የአስተሳሰብህ ውጤት ነውና ምንም ነገር ለመለወጥ ከማቀድህ ቀደም ብለህ አስተሳሰብህን መርምር፣ በጥልቀት ቁጭ ብለህ አስብ ለራስህ ጊዜን ስጠው ያኔ የችግርህን ስር አስተሳሰብህ ሆኖ ታገኘዋለህ ያን አስተሳሰብ ነቅለህ አውጣ ያኔ እንዳትራመድ ካገደህ ሰንሰለት እና ትብታብ ትፈታለህ።

ነጸነትህ፣ የምትናፍቀውም ለውጥ የሚገኘው በአንተው እጅ ውስጥ ነው። ለውጥን ከውጪ አትፈልገው ቦታ በመለወጥ፣ ሀገር በመቀየር ዘላቂ ለውጥ አይመጣም ዘላቂ ለውጥን ምትሻ ከሆነ አስተሳሰብህን በመመርመርና በመለወጥ ጀምር።


🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ🌼


🌼🌼🌼መልካም በአል🌼🌼🌼
🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼🌼
🌼🌼🌼መልካም ቀን ተመኘሁ🌼🌼🌼

🌼🌼መስከረም 1/ 2014🌼🌼
ሳሙኤል ከበደ

🌼🌼🌼@youthfocus🌼🌼🌼
🌼🌼🌼@youthfocus🌼🌼🌼
🌼🌼🌼@youthfocus🌼🌼🌼
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
🌼🌼በ2014 አዲስ ልብወለድ🌼🌼
በyouthfocus channal
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
Illasha Fekadu - እውነት - Ewnet.webm
5.4 MB
🎧🎧🎧illasha Fekadu 🎧🎧🎧 🎼🎼🎼Ewnet እውነት 🎼🎼🎼 Amezing song cant stop hearing it!!!

@youthfocus @youthfocus @youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በማስተዋል ተመላለስ
ምሳሌ ፪
በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ጥበብንና ማስተዋልን አብዝተህ ፈልግ ከምንም ነገር አስቀድመህ እርሷን እሻት ከከበረው ሀብት በላይ ውድ ከሆነው እንቁ በላይ ጥበብን አብዝተህ ፈልጋት ከክፋት ከአደገኛም ወጥመድ እርሷ ትጠብቅሀለች።
ውብ፣ ምትማርክ ሆና መንገድዋ ግን ወደ ሞት ከምትወስደው እርሷ ትጠብቅሀለች፣ ዘመንህን በጸጸትና ሀዘን ከመምራት ታስመልጥሀለች።
ከምንም ነገር በፊት አስቀድመህ ጥበብን ፈልጋት።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ሁሌም

በህይወት ስትኖር ብዙ ውድቀት አለመሳካት ስህተቶች ትሰራለህ ከዚህም የተነሳ ልብህ ይሰበራል ተስፋም ትቆርጣለህ በእንደዚህ አይነት መንገድ ማለፍ ከባድ ነው። ለሰውም ልናስረዳው የምንችለው ነገር አይደለም ስለ ሁሉም ነገር ተስፋ መቁረጥና ጨለማ ብቻ ይታየናል። ስሜታችንን አብዝተን የምንሰማ ከሆነ እስከሞት ድረስ የስሜት መለዋወጦቹ ሊያደርሱን ይችላሉ

በእንደዚህ አይነት ግራ አጋቢና ተስፋ አስቆራጭ መንገድ ስትጓዝ አንድ ነገር ግን ማስተዋል አለብህ ሁል ጊዜም ሁለተኛ እድል አለ።
በምንም አይነት የውድቀት ጎዳናላይ ሁን የገነባሗው የትኛውም ነገር ይፍረስ ሁለተኛ እድል እንዳለ ግን አትርሳ።

ከአንተ የባሰ ብዙ እጣ ደርሶአቸው መልሰው ራሳቸውን ከወደቁበት አንስተው የፈረሰውን ነገር እንደገና ገንብተው፣ በብርታት በክፍታ ላይ መቆም የቻሉ እንዳሉ እወቅ።

የፍቅር ህይወትህ፣ ትምህርትህ፣ ስራህ፣ ቢዝነስህ.... የትኛው ነገር ተበላሸብህ? የትኛውስ ነገር ከመጠገን በላይ ፈራረሰብህ አይዞህ ስሜትህን አድምጠህ ማዘንህም ግራ መጋባትህም ትክክል ነው ነገር ግን ደግሞ ቆም ብለህ ሁሌም እድል እንዳለ ነገ አዲስ ቀን እንደሆነ ቁስልህ እንደሚፈወስ፣ ተስፋህም እንደሚመለስ አስተውል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የምርጫ ውዝግብ
በህይወትህ ከልጅነት ዘመን ወደ ብስለት ወይም እድገት ስትመጣ ብዙ ግራ ሚያጋቡ፣ እንቅልፍ የሚነሱ፣ የሚያሳስቡ የሚያስጨንቁ ምርጫዎች፣ አጣብቂኝ ውስጥ ትገባለህ። ብዙ ምርጫ ባለበት አለም ውስጥ እየኖርክ በየቀኑ ቀላል የማይባሉ ምርጫዎች ይቀርቡልሀል ታዲያ ከእንደዚህ አይነት ውዝግብ እንዴት ታመልጣለህ? እውነታው ከሁሉም መሸሽ አትችልም ነገር ግን ለመወሰን ግን ነገሮችን የበለጠ ግልጽ እንዲሆንልህ ልታረጋቸው የምትችላቸው ነገሮች ልጥቀስልህ
፩ በብስለት ማደግ
ብስለት ከተፈጥሮ፣ ከልምድ፣ ከንባብ፣ ከስህተቶች ልታገኝ ትችላለህ በተለይ ደግሞ ብዙ ከማንበብ ቀድመህ በብዙ ርእሶች ላይ በንባብ ራስህን ማሳደግ እጅግ ጠቃሚ ስልት ነው።

፪ ጊዜያዊውን ሳይሆን ዘላቂውን ማሰብ ወይም መመልከት
የምትወስነው ውሳኔ ነገህ ላይ የራሱ የሆነ ተጽእኖ አለው ታዲያ ስትወስን የዛሬን ደስታና ምቾት ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት በአንተ ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖ አስበህ ውስን

፫ ከራእይህ አንጻር ምረጥ
ከራእይህ ጋር የማይሄድን ነገር አትምረጥ ምንም ያህል ብትወደውም ብትፈልገውም ምርጫህ ከራእይህ አንጻር ይሁን ምክንያቱም ከምትኖርለት ነገር እንዳይለይህ ዋጋ ከምትከፋልለት ነገር እንዳያርቅህ። ስትመርጥ ከራእይህ አንጻር ምርት

፬ ምን ጊዜም ለመወሰንም ለመምረጥም አትቸኩል
በችኮላ የምታረገው ነገር ዋጋ ያስከፍልሀል ለውሳኔ አትሩጥ የሚያቻኩል ነገር ቢኖርም እንኳ በነገሩ ላይ እደርበት። ዛሬ የቀረበልህን ምርጫ አድረህ ስታስበው እንደ ትላንቱ ላይሆን ስለሚችል ዛሬ ለውሳኔ አትቸኩል ራስህንም ሌሎችንም ግራ ከማጋበት ትድናለህ።
**** በተቻኮልክ ቁጥር ስህተት እንደሚበዛ እወቅ የማትጸጸትበት ምርጫ በጥልቅ አስበህበት የምትመርጠው ምርጫ ነው።

፭ በአንደኛነትና በዋናነት ፈጽመህ ፈጽመህ መጸለይን እንዳታቆም ግራ ስትጋባም እንደውም መጽለይህን ቀጥል ጌታ ዝም ያለህ ቢመስልህም መጸለይህን ግን በምንም አይነት መንገድ እንዳታቆም።
ስትጸለይ ነገሮች ይበልጥ እየጠሩ ይመጣሉ፣ እይታህም እየተቀየረ ይመጣል።
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ሁሉም ነገር ያልፋል
ዛሬ የገጠመህ ህመም ያልፋል፣ ያልተጠበቀው ገጠመኝንም አልፈህው እንደ ታሪክ ታየዋለህ ዛሬ እንዲህ ህመም ውስጥ ስልክህ ነገም እንዲሁ ይሆናል ማለት አይደለም ዛሬ ነገ አይደለምና ይህንም ታልፈዋለህ። አይዞህ ምታልፈበት ከባድ ነው። ቀላል ነገር አልገጠመህም፣ በእለት ኑሮህ ስቃዩ ላስተዋለው ከባድ ሲቃ ነው። ግን ይህ ህመም ለዛሬ ብቻ ነው መሽቶ ሲነጋ አዲስ ቀን ሲመጣ ይህ ሁሉ ያልፋል እስኪ እስከ ዛሬ የመጣህበትን መንገድ ተመልከት አላልፈውም ያልከውን ሁሉ እርሱ አላሻገረህም፣ አላሳለፈህም አሁንም ጠንክር በርታ አይዞህ ከባዱን ስቃይህን፣ መገፋትህን የሚያይ በላይ በሰማይ አምላክ አለ። ይረዳሀል ታልፈዋለህ ትወጣዋለህ።

በተሰማህ ህመም ምክንያት በራስህ ላይ መጥፎ እርምጃን ውሳኔንም አትውሰድ ለሚያልፋ ቀን የማያልፍን ህመም በራስህ አትጨምር በተሰማህ ከባድ ህመም የባሰ ራስህ እንዳትጎዳ።

አይዞህ በርታ እግዚአብሔር አለልህ

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus