Scripture union addis ababa
103 subscribers
607 photos
13 videos
29 files
14 links
Download Telegram
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
"የምትሞትለት ነገር ከሌለህ ምትኖርለት ነገር አይኖርህም "

እስከ መጨረሻው ዋጋ ልትከፍልለት የተነሳህለት ጉዳይ ምንድን ነው? የተፈጠርኩት ይህን አድርጌ እንዳልፍ ነው የምትለው ራእይ አለህ? ነገን ስታስብ በህይወት ከሚገጥምህ ከጭጋጋማው ደመና በሗላ፣ ከከፍታውና ዝቅታው በሗላ እደርስበታለሁ የምትለው ህልም አለህ?

እንደዚህ ዋጋ ልትከፍልለት የተዘጋጀህለት የህይወት ጉዳይ፣ አላማና፣ ራእይ ያስፈልግሀል አለበለዚያ በህይወትህ ሳትደሰትና ሳትረካ ታልፋለህ።

አጥብቀህ የምትሞትለትን ጉዳይ ፈልግ ያኔ የምትኖርለትን ምክንያት ታገኛለህ!!

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
የመጨረሻ | Kalkidan Nigussie
ተወዳጁ የደስታዬ እልልታ
የመጨረሻ. ቃልኪዳን ንጉስ
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍. 😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የምትኖረው ህይወት የአስተሳሰብህን ያህል ነው ደግመህ ደጋግመህ ምታስበው ምንድን ነው? አይቻልምን ደግመህ ደጋግመህ ካሰብክ እንግዲያውስ ህይወትህም በአይቻልም ይይዛል ይቻላልን ምታስብ ከሆነ የትኛውንም ነገር ማድረግ ትችላለህ።

አስተሳሰብህ ቀይር ያኔ ህይወትህም ይቀየራል!!!!
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (rahel)
ሀሳብ እና አላማህን ለማሳካት በምታደርገው ጉዞ ውስጥ አስቀድመህ ያቀድከውን በአግባቡ ማከናወን እናም መጨረስ ስትችል ነው ውጤታማ የምትሆነው እንጂ የምትሰራውን ነገር በማብዛት አልያም በአንዱ ላይ ሌላ ሀሳብ እና ስራ እየጨመርክ እራስህን ስለወጠርክ አይደለም። ውጤታማነትህን እናም አቅምህን ማስተዋል እንድትችል አስቀድመህ የጀመርከውን በጥሩ ሁኔታ አጠናቀው ያኔ በጣርከው ልክ ውጤትን ታገኛለህ።
በ ራሄል ካሳሁን
መልካም ቀን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ህይወት እና ትግል

በምድር ላይ እስካለን ድረስ በብዙ ትግል መኖራችን እሙን ነው። በምንኖርበት በእያንዳንዱ ቀን እልህ አስጨራሽ፤ ተስፋ አስቆራጭ የህይወት ፈተናዎች ይገጥሙናል። አንተ ብቻ ላይ አንዱን ስትጨርስ ሌላውን የሚወረውር ሰው እንዳለ አታስብ። ይልቅስ በእንደዚህ አይነት ከባድ የህይወት እውነት የምትኖረው አንተ ብቻ ሳትሆን 7ቢሊዬን ህዝብ እንዳለም አትርሳ።

መፍትሄን ስትፈልግ ችግርህ ላይ በማተኮር መፍትሄ እንደማይመጣ ጠንቅቀህ ተረዳ። ይልቅስ የባሰ ውዝግብ እንጂ ለችግርህ መፍትሄ ማግኘት ከፈለግክ ግን ችግሩ ላይ ሳይሆን መፍትሄው ላይ አተኩር የችግሩን ምንጭ ከስሩ ለመረዳት ባለህ ሀይል ሁሉ ጣር ምንጩን ካወቅክ መፍትሄው ቀላል ስለሆነ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
"Those heights by great men, won and kept, were not achieved by sudden flight. But they, while their companions slept, were toiling upward in the night."

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
እሴት ጨምርበት
ኢትዮጲያ ህዝቦቿም እጅግ ከሚታወቁባቸው ነገሮች መሀል ለቡና ያለን ስፍራ ትልቁን ቦታ ይይዛል በእያንዳንዱ የህይወት ጉዟችን ውስጥ ቡና ትልቁን ስፍራ ይይዛል ከዛም ባለፈ ትልቁም የገቢ ምንጫችን ነው። በፈረንጆቹ 2018 አም ወደ ውጪ በላከችው ጥሬ ቡና 800 ሚሊዮን ዶላር አስገብታለች። ነገር ግን የአሜሪካው ስታር በክስ የብና ካፌ በዚሁ አመት 4.5 ቢሊየን ዶላር እንዳስገባ ጥናቶች ይጠቁማሉ የዚህ ሁለት የገንዘብ ልዮነቶች ምክንያት እሴት የመጨመርና እሴትን ያለመጨመር ልዮነቶች ናቸው።

ዛሬ በእጅህ ላይ ያለው ጥሬ የምትለው ነገር ምንድን ነው ጥቂት የምትለው በዛ ትንሽ ነው ባልከው ነገር ላይ እሴትን ጨምርበት ያኔ ካሰብከው በላይ የስኬት ማማ ላይ ትገኛለህ ካንተ ሚጠበቅው ማንነትህ ላይ አእምሮህ ላይ ስራህ ላይ እሴትን መጨመር ነው። ጊዜህን አቅምህን ሁሉ አሟጠህ ባለህ ነገር ላይ እሴትን ጨምርበት

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
From 2010 leaders training for reminder
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የገጠመህን ችግር በብዙ ህመምና ችግር አልፈህ ከዚህ በሓላ እረፍት ነው የምፈልገው፣ ምንም አይነት ነገር እንደማይገጥምህ አታስብ፤ ህይወት ሁል ጊዜ አንዱን ስታልፍ ባልጠበቅከው በሌላ ችግር ትገናኝሀለች፣

ስለዚህም ልታረግ የምትችለው አንድ ነገር ቢኖር በርትተህ መራመድ ብቻ ነው።
አንዱን ስታልፍ ሌላው አንዱን ስትሻገር ደግሞ ሌላ እንደሚገጥምህ እወቅ ነገር ግን ሁሌም ከአምላክህ ጋር ተጣበቅ ከእርሱ ጋር ከሆንክ ሁሉንም በድል ያሻግርሀል።

🖋አዞህ ልብህንም በአምላክህ አበርታ🖋

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጉልበቴ
እጅግ አታካችና አድካሚ በሆነው በዚህ አለም ውስጥ ስትኖር በየእለቱ ጉልበትህን የሚያዝሉ፣ ሀይልህን የሚቀሙ፣ ተስፋህን ለማጥፋት የሚጥሩ፣ ውስጥ ግን የሚበሉ ብዙ የህይወት ትግሎች አሉ ታዲያ ይህን ለመቋቋም እንዴት ይቻል ይሆን?መልሱ ቀላል ነው ብርታትህ ጉልበትህ፣ በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብትሄድ ክፋን እንዳትፈራ ኃይልን የሚሰጥህ ከአምላክህ ጋር የምታደርገው የሁል ጊዜ የጥሞ ጊዜ ነው።

የገጠመህን፣ የምታልፍበትን፣ ውጣ ውረዱንም ሁሉ ለማለፍ ታላቅ ብርታትህ ከአምላክህ ጋር በጸሎት በዝማሬ፣ በአምልኮ፣ በቃሉ በኩል የምታደርገው ህብረት ነው። ሁሉን የሚያስችልህ ክርስቶስ ነው ከእሱ ጋር ሆነህ ደግሞ ሁሉን ትችላለህ ብቻ አንተ ከእሱ ጋር አብዝተህ ተጣበቅ በሁሉም ሁኔታ ከእሱ አትለይ አትራቅ በተገፋህና በተቸገርከው ልክ አብዝተህ ወደ እሱ ተጠጋ። ያኔ በህይወት የሚገጥሙህን ፈተናዎች በድል ትወጣለህ።
ከእሱ ስትርቅ ብቸኛ ተስፋህን እየገፋህ እና እየሸሸህ እንደሆነ አስተውል!!!

“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አንዱን ስታነሳ
ታላቁ መጽሀፍ መጽሀፍ ቅዱስ ገንዘብንም ጌታንም መውደድ እንደማይቻል ያስተምረናል ሁለት መውደድ ለሁለቱም መገዛት እንደማይቻልም ይነግረናል በህይወት ስትኖር በብዙ የምርጫ ውጥረት ውስጥ ታልፋለህ በከበረውና በተዋረደው፣ በሚጠቅመውና በማይጠቅመው፣ በአንገብጋቢውና አንገብጋቢ በሆነው ነገር መሀል በምርጫ ውጥረት ህይወትን እንገፋለን። ለሁሉም መገዛት አንችልም ስለዚህ ስትመርጥ ከህይወትህ አላማ ጋር በሚሄድ ወደታች በሚያወርድህ ከከፍታህ ከምትሰራው ታላቅ ስራ የሚያስተጓጉልህን ና እንጫወት ስራው ይደርሳል ፣ ፈታ በል፣ በሗላ ትሰራዋለህ የሚሉትን አትቀበል፤ ይልቅስ የያዝከውን ታላቅ ስራ የሚያበረታታህንና የሚያጠናክርህን ነገር ምረጥ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
“ኀይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13 (አዲሱ መ.ት)

በራስህ አትችልም

ህይወት እጅግ ከባድ ነው፣ ኑሮም ትግል ነው በዚህ ከባድ ህይወት ውስጥ እየኖርክ የየቀኑን ከባድ እውነታዎች መጋፈጥም እጅግ ከባድ ነው።

ይህን አስቸጋሪ ህይወት በድል ልትጨርሰው፣ ከትግሉ በሗላ በአሸናፊነት ምትወጣው ከጌታ በምታገኘው ብርታትና ጉልበት ብቻ ነው።

ለዚህም ነው በየቀኑ ልትጋፈጠው ከምትወጣው የህይወት ጦርነቶች አስቀድመህ በማለዳ ኃይልን ከጌታ መቀበል መቻል ያለብህ። ድምጹን መስማት መንፈሱንም መሞላት ቃሉንም በልብህ እያሰላሰልህ መዋል ለህይወትህ ደስታን ለትግልህም ድልን ማግኛ የጥበብ መንገድ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ወደ ላይ ተመልከት
ምን አይነት ነገር ውስጥ ነው ያለህው? ምን አይነት ነገርስ እያስሽጨነቀሕ ነው ያለው? ምንስ ግራ አጋባህ? በህመም ላይ ህመም የሆነብህ ነገርስ ምንድን ነው?
ተስፋ ሊያስቆርጥህ ያለው ነገር ምንድን ነው? ምንም ነገር ቢከብህ ከተራራህ በላይ ታላቅ የሆነ ጌታ አለ! እርሱ አለ! በምንም ውስጥ እለፍ፣ ምንም ይግጠምህ፣ የስሜት መለዋወጥም ይኑር ወደላይ ማየት አታቁም እያመመህም መጸለይን አትተው።

ጉዳዮ ህይዉትህን እስኪናወጥ ድረስ ያደረሰ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በጽኑ አለት ላይ ተደገፍ እርሱ አቅም ለሌላቸው ብርታት መጠጊያም፣ መሸሸጊያም ነውና።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በሁሉም ነገር ውስጥ አይሀለሁ

ከማለዳው የጽሀይ ወጋገን እስከ ምሽት ጨረቃ ድረስ፣ ባለፍኩበት መንገድ ሁሉ፣ በተራራውም፣ በሸለቆውም፣ በህመሙም፣ በደስታውም፣ በጨለማውም በብርሀኑም ውስጥ።

በግራ መጋባትም፣ በመጨነቅም፣ በተስፋ መቁረጥም ጊዜ ውስጥ ጌታ ሆይ አንተን አይሀለሁ። ስታግዘኝ አይሀለሁ፣ በገጠመኝ ሁሉ ውስጥ ሳልፍ አብሮነትህን አየዋለሁ ስታግዘኝ አይሀለሁ፣ ስትመራኝ፣ ስታበረታኝ፣ ስታጽናናኝ አይሀለሁ።

መልካምነትህን መልካም ባልሆነ ነገር ውስጥም አየዋለሁ ስገፋህም እንኳ ከእኔ ሳትለይ ቆመህ በህይወት ዘመኔ ሁሉ አንተን አይሀለሁ።
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
በትምህርታችሁ civil engineering , cotm, arcitecture, hydraluics engineering የምትማሩ ልጆች ይህ ቻናል ለተማሪዎችም ምህንድስናን practice ለሚያረጉ መሀንዲሶች የሚጠቅሙ ማቴሪያሎች አሉበት ተቀላቀሉት ለምታውቋቸው መሀንዲሶችም አጋሩ።

@ethcivileng
@ethcivileng
@ethcivileng
@ethcivileng
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
Illasha A. Fekadu - ስሜ ነው - Sime New.webm
5.8 MB
🌼🌼ስሜ ነው 🌼🌼
😊😊😊😊😊😊
🎙🎙🎙🎙🎙🎙
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ከአሰተሳሰብህ ጀምር

ሁልጊዜ አዲስ አመት በመጣ ቁጥር ብዙ ነገሮችን ለመለወጥ ለመቀየርም እናስባለን እናቅዳለን አዲስ ደብተር አዲስ ቦርሳ አዲስ የቤት እቃ፣ አዲስ ቤት፣ አዲስ ሰፈር፣ አዲስ ሀገር እንቀይራለን እንደ ትላንት ላለመኖር ጥረትን እናደርጋለን።

ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ በመረጥነው የለውጥ መንገድ እንራመድና ወዲያው ወደ ትላንቱ እንመለሳለን አዲስ አመት ቢመጣም ወቅት ቢቀየርም ሀገር ብንቀይርም፣ በትምህርት ደረጃችን እየጨመርን ብንመጣም እኛ ግን በተለወጠ ዘመንና አመት ላይ እንደዛው እንደትላንት አንዳንዴም በባሰ ሁኔታ እንገኛል።

ለዚህ የሽንፈትና ውድቀት ድግግሞሽ ምክንያቱ ዘመን፣ ሀገር፣ ቤት፣ ሰፈር፣ ትምህርት ቤት፣ መለወጥ አለመለወጥ ሳይሆን፤ እኛ መለወጥን የፈለግንበት መንገድ ነው። መለወጥን ከፈለግክ ከአስተሳሰብህ ጀምር ያኔ እውነተኛ ለውጥን ታገኛለህ ትላንትን መደጋገም የማትፈልግ ከሆነ ትላንት የኖርክበትን የተበላሸ አመለካከት ለውጥ ሀገር ከመቀየር ለነገሩ ያለህን እይታ አስተካከል፤ ሁሉም ነገር ከአስተሳሰብ ይጀምራል

እይታክም እንኳ የአስተሳሰብህ ውጤት ነውና ምንም ነገር ለመለወጥ ከማቀድህ ቀደም ብለህ አስተሳሰብህን መርምር፣ በጥልቀት ቁጭ ብለህ አስብ ለራስህ ጊዜን ስጠው ያኔ የችግርህን ስር አስተሳሰብህ ሆኖ ታገኘዋለህ ያን አስተሳሰብ ነቅለህ አውጣ ያኔ እንዳትራመድ ካገደህ ሰንሰለት እና ትብታብ ትፈታለህ።

ነጸነትህ፣ የምትናፍቀውም ለውጥ የሚገኘው በአንተው እጅ ውስጥ ነው። ለውጥን ከውጪ አትፈልገው ቦታ በመለወጥ፣ ሀገር በመቀየር ዘላቂ ለውጥ አይመጣም ዘላቂ ለውጥን ምትሻ ከሆነ አስተሳሰብህን በመመርመርና በመለወጥ ጀምር።


🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ🌼


🌼🌼🌼መልካም በአል🌼🌼🌼
🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼🌼
🌼🌼🌼መልካም ቀን ተመኘሁ🌼🌼🌼

🌼🌼መስከረም 1/ 2014🌼🌼
ሳሙኤል ከበደ

🌼🌼🌼@youthfocus🌼🌼🌼
🌼🌼🌼@youthfocus🌼🌼🌼
🌼🌼🌼@youthfocus🌼🌼🌼
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
🌼🌼በ2014 አዲስ ልብወለድ🌼🌼
በyouthfocus channal
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
Illasha Fekadu - እውነት - Ewnet.webm
5.4 MB
🎧🎧🎧illasha Fekadu 🎧🎧🎧 🎼🎼🎼Ewnet እውነት 🎼🎼🎼 Amezing song cant stop hearing it!!!

@youthfocus @youthfocus @youthfocus