Scripture union addis ababa
103 subscribers
607 photos
13 videos
29 files
14 links
Download Telegram
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ፍርሀት
"ጀግንነት ማለት የፍርሀት አለመኖር ሳይሆን በፍርሀት ላይ ማሸነፍ እንደሆነ ተምሬአለሁ። ጎበዝ ሰው ማለት የማይፈራ ሰው አይደለም፣ ፍርሀቱን የሚያሸንፍ እንጂ" ኔልሰን ማንዴላ

ፍርሀት የአእምሮ ገዳይ ነው በጊዜ ካልተወገደ ሓይልንም ያደክማል፣ የፈጠራ ችሎታህን ያጠፋል።

ፍርሀት ህልምህን እንዳትኖር፣ እድሎችንም እንዳትጠቀም አስሮ የሚያስቀር ወደፊት መራመድንም የሚከለክል እስር ቤት ነው።
እስከ ዛሬ በፍርሀት ያመለጡክ ብዙ ድንቅ እድሎች አሉ ዛሬ ግን ይህን አትፍቀድላቸው ጨክነህ ፍርሀትህን ገፍተህ በመውጣት ላንተ የተሰጠኽን እድል ተጠቀምበት።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ያልተሰሩ ጭንቅላቶች
" ያልተሰሩ ጭንቅላቶች የተሰሩ ከተሞችን ሲያፈርሱ የተሰሩ ጭንቅላቶች የፈረሱ ከተሞችን ይገነባሉ።" ቤንጃሚን ፍራንክሊን

ሰውነትህና ጭንቅላትህ ተመሳሳይ ባህርያት አሏቸው ፤ እሱም ልታፋፋቸው ልታቀጭጫቸውም ስለምትችል ነው።

በቂ፣ ተመጣጣኝና ጤናማ ምግብ ከመገብካቸው ሊወፍሩ ሊፋፉ ይችላሉ አእምሮ ግን በእውቀት፣ ትምህርት ካልመገብከው፣ በተገቢው መንገድ ካልሰራህበት አረም ሊያበቅል ይችላል ለማንም የማይጠቅም ገንቢ ሳይሆን አፍራሽ መሳሪያ ሊሆን ይችላል ተገቢውን ነገር ስይመግበው ደግሞ ገንቢ የሆነ ሀሳብ አመንጪ ሆኖ ለብዙዎች ፍቱን መፍትሄ ልታረገው ትችላለህ

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ወደፊት ተጓዝ
" መሮጥ ቢያቅትህ ተራመድ፣ መራመድ ቢያቅትህ ዳዴበል ነገር ግን በፍጹም እንድትቆም"
ማርቲን ሉተር

ህይወት አሰልቺ፣ አድካሚ፣ ተስፋ አስቆራጭ የሆነ መንገድ አላት ታዲያ በእንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ በምናልፍበት ጊዜ ብዙዎቻችን ሁሉን እርግፍ አድርገን ትተን መሄድን እንመርጣለን አስተውለህ አይተህ ከሆነ ግን በአንዴው የተከናወነለት ሰው በምድር እንደሌለ ትመለከታለህ ስኬት በመውደቅ መነሳት የሚገኝ ድል እንጂ በአንድ ቀን የሚደረስበት ስላልሆነ።

ስለዚህ ህይወት ምንም አይነት ነገር ብትወረውርብህ ወደፊት ከመራመድ እንዳትገታ በሩጫው ሜዳ በስተመጨረሻ ሽልማት ይጠብቅሀልና ጨክነህ ተጓዝ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ሚዛናዎነት
በዚህ ምርጫ በበዛበት፣ ባተሌነት(busy) በተሞላበት ዘመን ውስጥ እርጋታና እርካታ እንደጠፋ ትታዘባለህ፤ ሰው በስራው ተጠምዶ ቅድሚያ ሊሰጠው የተገባውን የቤተሰቡን ህይወት ረስቷል።

ራሱንም ቤተሰቡን ሰርቶ መለወጥ ሲገባው ደግሞ በጨዋታና መዝናናት ከአላማው ተንሸራቶ ወድቋል።

መማር ሲገባው በማይጠቅም ጉዳይ ጊዜውን ሲያቃጥል እንመለከታለን። ብቻ ህይወትን ስትመለከት በውጥንቅጥ የተሞላች እንደሆነ ትታዘባለህ። ታዲያ ለዚህ ሁሉ ችግር መፍትሄው ምን ይሆን??

ሚዛናዊነት
ሰው ሚዛናዊነት ካልጠበቀ በአንድ አቅጣጫ ተጣሞ እንዳደገ ተክል ሚዛናዊነት ያልጠበቅ ህይወትን ይመራል። ይህ ደግሞ በአንድ አቅጣ ጫ ብቻ ውጤታማ እንዲሆንና በሌላው አቅጣጫ ግን ያገደለ እንዲሆን በማድረግ ሁለንተናዊ እድገትን ይከለክለዋል።

ስትኖር የግል፣ የቤተሰብ፣ የማህበረሰብ፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ህይወትህን አመዛዝነህ መኑርን ተለማመድ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ዝምታን ተለማመድ

ማርክ ትዌይን "የምትናገረው ነገር ከሌለህ ምንም ነገር አትናገር፡፡"

በህይወትህ በምታደርጋቸው ተግባቦቶች ከብዙ ሰዎች ጋር ትገናኛለህ፣ ታወራለህ፣ ትግባባለህ ነገር ግን በሁሉም ጉዳይ ላይ ሙሉ እውቀት ስለማይኖርህ ሁሉንም ነገር ለመተቸትም ሆነ ለማሞገስ አትቸኩል አንዳንዴም ዝምታን ተለማመድ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
👨‍💼👨‍💼የእውነተኛ ወንድ ባህሪያት 👨‍💼👨‍💼
ክፍል 2
1.ራሱን ለአምላኩ ፈቃድና ሀሳብ የሚያስገዛ ነው
የእውነት መሪ ሊሆን የሚችል ወንድ ራሱ ጥሩ ተመሪ የሆነ ሲሆን ነው። ራሱን ለአምላክ ያስገዛ ወንድ፣ ከራሱ በላይ ለአምላክ ፈቃድ ሚኖር፣ ከራሱ አጀንዳ በፊት የጌታውን ሚያስቀድም ነው ማለት ነው። ይህ ወንድ መሪ ሲሆን ነገ የራሱ ቤተሰብ ሲያስተዳድር ከራሱ በላይ ለሌሎች ይራራል ይጠነቀቃል ያሰባል።
2. ሀላፊነትን ይወስዳል
ከብረት ዝገት ከሰው ስህተት አይታጣም እንደሚሉ ስህተት መስራት ሰው የመሆናችን አንዱ መገለጫ ነው። ታዲያ በሚሰራው ስህተት ሀላፊነትን ይወስዳል። በሌላ ላይ ጣቱ በመቀሰር ለመካድ አይሞክርም ይልቅ ያንን ስህተት ከተቻለ ለመለወጥ ካልሆነም ይቅርታን ጠይቆ የሚመጣውን ሀላፊነት ለመቀበል ዝግጁ ነው።
3.የልቡን ንጽህና ለመጠበቅ ይተጋል
በአለም ስንኖር ህይወታችንን ከትክክለኛው መንገድ በማውጣት ለማይረባና ለማይጠቅም ማንነት ሊሰጡ የሚፈልጉ የሚችሉም ብዙ ነገሮች አሉ። ከማለዳው ጀምሮ ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ የሀጢያት ፈተና በየልባችን ደጅ ያደባል፤ እውነተኛ የወንድ ባህሪ ያለው ግን በሀጢያት ላይ ይነግስባታል። የልቡንም ንጽሕና ለመጠበቅ ይተጋል
4.ራእይ አለው።
ራእይ የሌለው ህዝብ መረን ነው እንደሚል ቅዱስ ቃሉ። ራእይ የሌለው ወንድ የሚሄድበትን የተነሳበትን የሚሞትለትንም ነገር አያቅም። ለምን እንደሚኖር የማያውቅ ወንድ ዝም ብሎ በማይረባና በማይጠቅም ነገር ላይ እድሜውን ይጨርሳል። ፍሬ፣ ውጤት የሌለው ህይወትን ይመራል። ከአመት አመት ያለምንም ለውጥ ለራሱም ለሌላው ሳይሆን ይኖራል። ራሱን መምራት በፍጹም አይችልም ራሱን ለመምራት ብቁ ያልሆነ ደግሞ ሌላን ሰው ለመሸከም አቅሙም ችሎታውም አይኖረውም።

አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ህልም አለህ? የምትኖርለት፣ የምትሮጥለት፣ ነገር አለህ? ካለክ በርትተህ ስራ ከሌለህ ሌላ ሰው በህይወትህ ጨምረህ ግራ ከማጋባትህ በፊት ከአንተ የሚበልጥ የሚሰፋ ራእይን ለማግኘት ህልምህን ፍለጋ ጀምር።

እህቴ አንቺም በቅድሚያ ልትጠይቂው የሚገባሽ ነገር የሚኖርለት ራእይ መኖር አለመኖሩን ነው። ራእይ ከሌለው ሸክም እንጅ መፍትሄ አይሆንም

አዘጋጅ ሳሙኤል ከበደ
@samkb

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ሰው መሆን
መወለድ ማደግ ምቾት ችግር መታመም መዳን ማልቀስ መሳቅ ተስፋ መቁረጥ ተስፋ ማግኘት መወዛገብ መረጋጋት ፍቅርን ማግኘት ፍቅርን ማጣት የልብ ቁስል የልብ ፈውስ መፍለቅለቅ መንሰቅሰቅ አንገት ሰበር አንገት ቀና እንደሰከረ ሰው አዙሪት መሽከርከር ደግሞም እንደገና ከአዙሪቱ ለመውጣት መሞከር ግና ደግሞ እዛው አሁንም መሽከርከር መሽከርከር መሽከርከር ከዚህ ሁሉ በሗላ አድማስን ተሻግሮ ወደማይመለሱበት መሰናበት አቤት ሰው የመሆን ጣጣው አንዱ ሲባል ሌላው ሌላው ሲባል ደግሞ ሌላው አንዱ ባንዱ ላይ ሲደረብ ሲደራረብ ሆምጣጤ የጠጣ ያህል መንገፍገፍ ፣ መመረር እውነታው፣ ሀቁም፣ ገሀድ የሚታየው እውነት ይህ ነው ህይወት ማለት መራር ህይወት ማለት ህመም ህይወት ማለት ሲቃ ህይወት ማለት ጥረት ህይወት ማለት ጭንቀት ህይወት ማለት ደስታ ህይወት ማለት እረፍት ህይወት ማለት እርካታ ህይወት ማለት ለሌላው መቆረስ ለሌላው መኖር የራስን ትቶ የሌላውን መሸከም.........
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
መርዛማ ግንኙነት

ሰው ማህበራዎ ፍጥረት እንደመሆኑ ከሰው ውጭ ለብቻው መኖር አይችልም በየእለቱ ጊዜውን ህይወቱንም በማካፈል አብሮአቸው የሚኖር ወዳጆች ጎረቤቶች ቤተሰብ አሉት።

መልካም የሆነ ግንኙነት እንዳለው ሁሉ መርዛማ ግንኙነትም ደግሞ አለ። አንተነትህን እስክትረሳ ድረስ ህልምህን ራእይህን እስክትጥል ድረስ፣ ጌታ እግዚአብሔር በውስጥህ የገነባውን መልካም ነገር ሁሉ እስኪፈርስ ሊያደርስ የሚችል ወዳጅነት፣ ጓደኝነት፣ የፍቅር አጋር አለ።

ከነሱ ጋር አብረህ በመሆንህ ደስተኛ ልትሆን፣ እጅግም ልትወዳቸው ትችላለህ ነገር ግን በዛ ግኑኝነት ውስጥ ራስህን እያጣህ መሆኑ ላታስተውል ትችላለህ አውቀሗውም እነሱን ላለማጣት ስትል የራስህን ህይወት ልትሰዋ ትችላለህ። እጅግ መርዛማ ከመሆኑም የተነሳ አንተ ከአምላክህ ፈቃድ ውጪ ሊያስወጣህ፣ ትላንት የማትደራደርበት የህይወት ጉዳ ዛሬ ግን ሲበላሽ፣ ሲበረዝ፣ ሲቆሽሽ ምንም ላይመስልህ ይችላል።

ከእንደዚህ አይነት መርዛማ ወዳጅነት ራስህ ጠብቅ ቢከብድህም ዛሬ ይህ ማለዳ ቆርጠህ ምትወጣበት ይሁንልህ። ቶሎ ግን ይህን ግንኙነት የማትቆርጠው ከሆነ የምታጣው ነገር በየቀኑ እየጨመረ እንደሚሄድ በሗላ ለመመለስ ከባድ ሊያደርግብህ እንደሚችል እወቅ።

ምንም እንኳ እንተ ግንኙነቱን እጅግ ብትፈልገውም የሚያደርስብህ ኪሳራ ቀላል አይደለም ለመገንባት ዘመናት የወሰደብህን ነገር በሰአታት ውስጥ ሊያወድም ይችላል። ራስህን ለማንም ሳትጠቅም፣ በህይወትህ ምንም ፋይዳ ሳታመጣ ከምትጠፋ አቅምህን ሁሉ አሰባስበህ ቶሎ መለየትን ምረጥ።



መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ፍቅር ማለት?

ፍቅር መቆረስ ነው፣ ለሌላው መኖር፣ ከራስ በላይ ሌላን ማስቀደም፣ የሚኖሩለትን ብቻ ሳይሆን የሚሞቱለትን ሰው ማግኘት፣ ራስን ሳይሳሱ መስጠት፣ ፍቅር ለራስ ሳይሆን ለሌላ ራስን መስዋት፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ማቅረብ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
"የምትሞትለት ነገር ከሌለህ ምትኖርለት ነገር አይኖርህም "

እስከ መጨረሻው ዋጋ ልትከፍልለት የተነሳህለት ጉዳይ ምንድን ነው? የተፈጠርኩት ይህን አድርጌ እንዳልፍ ነው የምትለው ራእይ አለህ? ነገን ስታስብ በህይወት ከሚገጥምህ ከጭጋጋማው ደመና በሗላ፣ ከከፍታውና ዝቅታው በሗላ እደርስበታለሁ የምትለው ህልም አለህ?

እንደዚህ ዋጋ ልትከፍልለት የተዘጋጀህለት የህይወት ጉዳይ፣ አላማና፣ ራእይ ያስፈልግሀል አለበለዚያ በህይወትህ ሳትደሰትና ሳትረካ ታልፋለህ።

አጥብቀህ የምትሞትለትን ጉዳይ ፈልግ ያኔ የምትኖርለትን ምክንያት ታገኛለህ!!

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
የመጨረሻ | Kalkidan Nigussie
ተወዳጁ የደስታዬ እልልታ
የመጨረሻ. ቃልኪዳን ንጉስ
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍. 😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የምትኖረው ህይወት የአስተሳሰብህን ያህል ነው ደግመህ ደጋግመህ ምታስበው ምንድን ነው? አይቻልምን ደግመህ ደጋግመህ ካሰብክ እንግዲያውስ ህይወትህም በአይቻልም ይይዛል ይቻላልን ምታስብ ከሆነ የትኛውንም ነገር ማድረግ ትችላለህ።

አስተሳሰብህ ቀይር ያኔ ህይወትህም ይቀየራል!!!!
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (rahel)
ሀሳብ እና አላማህን ለማሳካት በምታደርገው ጉዞ ውስጥ አስቀድመህ ያቀድከውን በአግባቡ ማከናወን እናም መጨረስ ስትችል ነው ውጤታማ የምትሆነው እንጂ የምትሰራውን ነገር በማብዛት አልያም በአንዱ ላይ ሌላ ሀሳብ እና ስራ እየጨመርክ እራስህን ስለወጠርክ አይደለም። ውጤታማነትህን እናም አቅምህን ማስተዋል እንድትችል አስቀድመህ የጀመርከውን በጥሩ ሁኔታ አጠናቀው ያኔ በጣርከው ልክ ውጤትን ታገኛለህ።
በ ራሄል ካሳሁን
መልካም ቀን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ህይወት እና ትግል

በምድር ላይ እስካለን ድረስ በብዙ ትግል መኖራችን እሙን ነው። በምንኖርበት በእያንዳንዱ ቀን እልህ አስጨራሽ፤ ተስፋ አስቆራጭ የህይወት ፈተናዎች ይገጥሙናል። አንተ ብቻ ላይ አንዱን ስትጨርስ ሌላውን የሚወረውር ሰው እንዳለ አታስብ። ይልቅስ በእንደዚህ አይነት ከባድ የህይወት እውነት የምትኖረው አንተ ብቻ ሳትሆን 7ቢሊዬን ህዝብ እንዳለም አትርሳ።

መፍትሄን ስትፈልግ ችግርህ ላይ በማተኮር መፍትሄ እንደማይመጣ ጠንቅቀህ ተረዳ። ይልቅስ የባሰ ውዝግብ እንጂ ለችግርህ መፍትሄ ማግኘት ከፈለግክ ግን ችግሩ ላይ ሳይሆን መፍትሄው ላይ አተኩር የችግሩን ምንጭ ከስሩ ለመረዳት ባለህ ሀይል ሁሉ ጣር ምንጩን ካወቅክ መፍትሄው ቀላል ስለሆነ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
"Those heights by great men, won and kept, were not achieved by sudden flight. But they, while their companions slept, were toiling upward in the night."

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
እሴት ጨምርበት
ኢትዮጲያ ህዝቦቿም እጅግ ከሚታወቁባቸው ነገሮች መሀል ለቡና ያለን ስፍራ ትልቁን ቦታ ይይዛል በእያንዳንዱ የህይወት ጉዟችን ውስጥ ቡና ትልቁን ስፍራ ይይዛል ከዛም ባለፈ ትልቁም የገቢ ምንጫችን ነው። በፈረንጆቹ 2018 አም ወደ ውጪ በላከችው ጥሬ ቡና 800 ሚሊዮን ዶላር አስገብታለች። ነገር ግን የአሜሪካው ስታር በክስ የብና ካፌ በዚሁ አመት 4.5 ቢሊየን ዶላር እንዳስገባ ጥናቶች ይጠቁማሉ የዚህ ሁለት የገንዘብ ልዮነቶች ምክንያት እሴት የመጨመርና እሴትን ያለመጨመር ልዮነቶች ናቸው።

ዛሬ በእጅህ ላይ ያለው ጥሬ የምትለው ነገር ምንድን ነው ጥቂት የምትለው በዛ ትንሽ ነው ባልከው ነገር ላይ እሴትን ጨምርበት ያኔ ካሰብከው በላይ የስኬት ማማ ላይ ትገኛለህ ካንተ ሚጠበቅው ማንነትህ ላይ አእምሮህ ላይ ስራህ ላይ እሴትን መጨመር ነው። ጊዜህን አቅምህን ሁሉ አሟጠህ ባለህ ነገር ላይ እሴትን ጨምርበት

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
From 2010 leaders training for reminder
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የገጠመህን ችግር በብዙ ህመምና ችግር አልፈህ ከዚህ በሓላ እረፍት ነው የምፈልገው፣ ምንም አይነት ነገር እንደማይገጥምህ አታስብ፤ ህይወት ሁል ጊዜ አንዱን ስታልፍ ባልጠበቅከው በሌላ ችግር ትገናኝሀለች፣

ስለዚህም ልታረግ የምትችለው አንድ ነገር ቢኖር በርትተህ መራመድ ብቻ ነው።
አንዱን ስታልፍ ሌላው አንዱን ስትሻገር ደግሞ ሌላ እንደሚገጥምህ እወቅ ነገር ግን ሁሌም ከአምላክህ ጋር ተጣበቅ ከእርሱ ጋር ከሆንክ ሁሉንም በድል ያሻግርሀል።

🖋አዞህ ልብህንም በአምላክህ አበርታ🖋

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጉልበቴ
እጅግ አታካችና አድካሚ በሆነው በዚህ አለም ውስጥ ስትኖር በየእለቱ ጉልበትህን የሚያዝሉ፣ ሀይልህን የሚቀሙ፣ ተስፋህን ለማጥፋት የሚጥሩ፣ ውስጥ ግን የሚበሉ ብዙ የህይወት ትግሎች አሉ ታዲያ ይህን ለመቋቋም እንዴት ይቻል ይሆን?መልሱ ቀላል ነው ብርታትህ ጉልበትህ፣ በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብትሄድ ክፋን እንዳትፈራ ኃይልን የሚሰጥህ ከአምላክህ ጋር የምታደርገው የሁል ጊዜ የጥሞ ጊዜ ነው።

የገጠመህን፣ የምታልፍበትን፣ ውጣ ውረዱንም ሁሉ ለማለፍ ታላቅ ብርታትህ ከአምላክህ ጋር በጸሎት በዝማሬ፣ በአምልኮ፣ በቃሉ በኩል የምታደርገው ህብረት ነው። ሁሉን የሚያስችልህ ክርስቶስ ነው ከእሱ ጋር ሆነህ ደግሞ ሁሉን ትችላለህ ብቻ አንተ ከእሱ ጋር አብዝተህ ተጣበቅ በሁሉም ሁኔታ ከእሱ አትለይ አትራቅ በተገፋህና በተቸገርከው ልክ አብዝተህ ወደ እሱ ተጠጋ። ያኔ በህይወት የሚገጥሙህን ፈተናዎች በድል ትወጣለህ።
ከእሱ ስትርቅ ብቸኛ ተስፋህን እየገፋህ እና እየሸሸህ እንደሆነ አስተውል!!!

“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አንዱን ስታነሳ
ታላቁ መጽሀፍ መጽሀፍ ቅዱስ ገንዘብንም ጌታንም መውደድ እንደማይቻል ያስተምረናል ሁለት መውደድ ለሁለቱም መገዛት እንደማይቻልም ይነግረናል በህይወት ስትኖር በብዙ የምርጫ ውጥረት ውስጥ ታልፋለህ በከበረውና በተዋረደው፣ በሚጠቅመውና በማይጠቅመው፣ በአንገብጋቢውና አንገብጋቢ በሆነው ነገር መሀል በምርጫ ውጥረት ህይወትን እንገፋለን። ለሁሉም መገዛት አንችልም ስለዚህ ስትመርጥ ከህይወትህ አላማ ጋር በሚሄድ ወደታች በሚያወርድህ ከከፍታህ ከምትሰራው ታላቅ ስራ የሚያስተጓጉልህን ና እንጫወት ስራው ይደርሳል ፣ ፈታ በል፣ በሗላ ትሰራዋለህ የሚሉትን አትቀበል፤ ይልቅስ የያዝከውን ታላቅ ስራ የሚያበረታታህንና የሚያጠናክርህን ነገር ምረጥ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus