Scripture union addis ababa
103 subscribers
607 photos
13 videos
29 files
14 links
Download Telegram
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጸሎት

ህይወት በብዙ ፈተናዎችና ትግሎች የተሞላች ነች አንዱን ታግለህ ሳትጨርስ ሌላው ይከተላል፣ እሱንም ሳታገባድድ ደግሞ ሌላው ይመጣብሀል እጅግ አታካችና አስቸጋሪ መንገድ ነች ህይወት። ታዲያ እነዚህን ውጣ ውረዶች በሙሉ በራስህም ሆነ ይረዱኛል በምትላቸው ሰዎች በኩል በመታገል፣ የበላይ ሆነ መጨረስ የማይታሰብ ነው። ሁለም ሰው የራሱ ችግር ስላለበት ላንተ ሊደርስልህ አይችልም

ነገር ግን ወደ ሰማዩ አባትህ አይንህን ብታነሳ፤ እርዳኝ ብለህ ብትጮህ፣ በጸሎት ብቻ አሸናፊ ትሆናለህ። በፊቱ በመንበርከክ ሀይልን ትቀበላለህ የገጠመህን ተራራም የመሻገሪያ አቅም ይጨመርልሀል።

በጸሎት ልብህን ትጠብቃለህ፣ ከአባትህም ጋር ህብረትን ታደርጋለህ፣ ህይወትህ ከወንዝ ዳር እንዳለ ተክል ያብባል ድርቅ ቢመጣም እንኳ አይጠወልግም። ከራስህም አልፈህ ለብዙዎች መፍትሄ ትሆናለህ፣ መዝሙረኛው ዳዎት እንዳለው" በጠዋትም በቀትርም በማታም" ፊቱን በጸሎት አብዝተክ መፈለግ ይሁንልህ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ስብራትህን ይዘህ

ህይወት ትእይንት ናት ብዙ ገጠመኝ የተሞላች ትእይንት መኖር ስትቀጥል የምትታዘበው ነገር ይህንኑ እውነታ ነው።

ብዙ ህመም፣ ብዙ ግራ መጋባት፣ ብዙ ትግል በዚህ መሀል የህይወት ስብራቶችም ይገጥሙሀል ለማገገም ለመፈወስም ጊዜ የሚፈልጉ፣ ቶሎ የማይሽሩ ህመሞች ሲያልፋም ጠባሳ ጥለው የሚያልፋ የህይወት ስብከቶች አሉ በእነዚህ ስብራቶች ውስጥ ሆኖ ወደፊት መሄድን ማሰብ ይከብዳል ተስፋ ይመነምናል ህይወት ትርጉም ያጣል።

ወደፊት መሄድ ለወጣት የማይቻል ተራራ ይሆናል ወደፊት ካልሄድን ወደሗላ እየሄድ ነውና ያገኘሀቸው ለውጦችን በሙሉ ማጣትህ ነው።

ስለዚህም ያለህ አማራጭ ህመምህን፣ ግራ መጋባትህንም፣ ስብራትህን ይዘህ በፊቱ በጸሎት ሁን እርሱን እሻው እየወጋ፣ እየጠዘጠዝህ ካለው ህመምህ ጋር በፊቱ ሁን እርሱ ፈዋሽህ፣ መድሀኒትህ እግዚአብሄር ነውና።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የእግር ኳስ ነገር
በአለማችን ላይ የሰውን ልብ እጅግ ከገዙ፣ ህይወቱንም እንኳ እስከመስጠት እንዲደርስ ምክንያት ከሆኑ የስፓርት ውድድሮች ሁሉ እግር ኳስ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

በኳስ ምክንያት የተጣሉ፣ የተገዳደሉ፣ የተታረቁ፣ ድንበር ሳይበግራቸው አንድነትን ያሳዩ፣ ብዙ ሰዎች አሉ። እኔ ከሚገርመኝ የእግር ኳስ ስልቶች ውስጥ የ12ቱ ተጫዋቾች ነገር ነው። የሁሉም ድል የሚወሰነው እያንዳንዳቸው በሚያደርጉት ጥረትና ትጋት ላይ ነው ሁሉም ለቡድኑ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል አይደለም፣ የአንዱ ተጫዋች ድካም በሙሉ ቡድኑ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ቀላል አይደለም።

"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንደሚባለው የእያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ዜጋም ህይወት እንደ እግር ኳሱ ሁሉ ነው።
የእያንዳንዱ ሰው ሀላፊነቱን እንደሚገባ መወጣት ወይም ቸልተኛ መሆን በድምሩ በሀገር ላይ የሚያስከትለው የድል ወይም የኪሳራ ውጤት ቀላል አይደለም።

የአንዱ ጥንካሬ፣ ትጋት ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሀገሩ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጾ አለው።
ስለዚህም በተሰማራህበት ስፍራ በር ትተህ ስራ የአንተ ብርታ ለመላ ሀገሪቱ አስተዋጾ ቀላል ስላልሆነ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጠንክረህ ስራ

ህልምህን፣ ራእይህን፣ እውን ማድረግ የምትሻ፣ የምትመኝ ከሆነ ምኞትህንና ፍላጎትህን በጠንካራ የስራ ባህል ልትደግፈው ይገባሀል።

ህይወት ያለ ስራ ትርጉም የላትም። በህይወት ደስ እየተሰኘህ እንድትኖር ከሚያደርጉህ ነገሮች መሀል በላብህ፣ በድካምህ፣ ለፍተህ የምታገኘው ፍሬ ነው።

ከስራ የሚገኝ ውስጣዌ እርካታ አለ፣
ጠንክሮ መስራት በውስጥህ ልዮ የውጤታማነትን ስሜት ይፉጥርልሀል፣ ብዙ እንድታፈራም በር ይከፍትልሀል

ስራ ፈት መሆን ራስህ፣ አእምሮህን፣ ቤተሰብህን፣ ሀገርህንም በብድርና በችግር ውስጥ በማስማቀቅ ለከፋ ድህነት ከማጋረጥ ያለፈ ነገር በውስጡ አያስገኝህም።

ለብዙዎች መትረፋን የምታስብ ከሆነ ራስህን በጠንካራ የስራ ባህል አስታጥቅ። ያኔ በብዙ ፍሬ ትባረካለህ።
በምን ላይ ነው የተሰማራሕው በትምህርት? በስራ? ጠንክረህ ስራ፣ አትድከም፣ አትሰልች በመጨረሻ ሙልካሙን የድካምህን ፍሬ ታጭዳለህ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ተስፋ አለ
ምን እየተሰማህ ነው? ውስጥህ ምን እየጎዳህ ነው? ተስፋ አርገህ አጣህ? እንዳሰብከው ሳይሆን ቀረ? አይዞህ አሁንም ተስፋ አለ ተስፋን የሚሰጥ ስላለ እርሱ አሁንም በዙፋኑ ላይ ጸንቶ ስለሚኖር አሁንም ተስፋ።

ቀን ሲጨልምብህ፣ ግራ ሲገባ በእርሱ ታምነህ፣ ነገ ብርሀን ይሆናል ብለህ ጉዞህን ቀጥል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አስረክበው
በህይወትህ እጅግ ልታገኘው የምትፈልገው ነገር ይኖራል። ብዙም ታግለህ፣ ሮጠህም ይሆናል ነገር ግን ምንም ለውጥ አላየህበትም።

ብዙ ብትለፋም የተቀየረ ነገር የለውም በእንደዚህ አይነት ጊዜ ልታረግ የምትችለው ነገርህን በሙሉ ለእግዚአብሄር ማስረከብ፣ ለጌታ አደራ አሳልፈህ ስጠው በቃ ልብህንም በእርሱ ላይ ጣለው እርሱ መንገድህን ቀያሽ ህይዉትህንም በእጁ የያዘ ጌታ ነው።

እርሱን ታምነኽው ተጓዝ የሚያሳስብህን ግር የሚልህን ሁሉ ለእርሱ ሰጥተኽው መንገድህን ቀጥል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ሰልፍ ዲሲፕሊን
ሰው በህይወት ዘመኑ ሁሉ ውጤታማና ስኬታማ የሆነን ህይወት ለመምራት የሚሻ ከሆነ ራሱን የመምራት ጥበብ ማዳበር ይኖርበታል።

ሰልፍ ዲሲፕሊን ማለት አንድን ተግባር ከግብ ለማድረስ ራሳችንን በመቆጣጠር፣ ስርአት በማስያዝ፣ መከፈል ያለበትን ዋጋ ሁሉ በመክፈል የምንኖርበት ስልት ነው።

ወደ አላማህ እንዳትደርስ፣ ከግብህ ጋር እንዳትገናኝ መሰናክል ከሚሆንብህ ነገር ትልቁና ዋናው ያው ራስህ ነህ ፤ ያማለት ስንፍና፣ እንቅልፍ ማብዛት፣ ወሬ፣ ሀሜት፣ ስራን አለመውደድ እነዚህ ሀሉ ከራስህ የሚመነጭ ተግዳሮት፣ መሰናክል ናቸው።

ማሸነፊያ መንገዱ አንድ ነው ራስን የማስተዳደር ( የመግዛት፣ የመምራት) ጥበብ ማዳበር፤ ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ መስጠይ፣ ዋና መሆን ላለበት ጉዳይ ዋና ማድረግ፣ የጊዜ አጠቃቀምን ማስተካከል፣ ወዘተ....... ራሳችንን የማስተዳደሪያ መንገዶች ናቸው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በምትሰራቸው ስራዎች አለመሳካት እየገጠመክ እየወደክ እየተነሳህ ህይወት ትቀጥላለች። ለማደግ ለመለወጥ ብለህ ብዙ ነገር ሞክረክ ሳይሳካ ይቀራል። ግን ፍላጎትህ እውነት ካለው ካንተ የሚጠበቀው ተስፍ ሳትቆርጥ ደጋግሞ መሞከር ነው። አይሳካም አይሆንም ወይም አሁንም ይበላሻል ብለህ ሙከራህን አታቁም።ሁሉም ያደገው ከአንድ እንጂ ከመቶ አይደለም አንተም ከስኬትህ ሳይሆን ከውድቀትህ ጀምር።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በአመት አንዴ!!

ፋሲካ በአመት አንዴ አክብረን የምናልፈው በዓል አይደለም። ፋሲካ ምግብና መጠጥም አይደለም። ፍሲካችን ኢየሱስ ነው።
“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5

እለት እለት ኢየሱስን በማወቅ ማደግ ይሁንልን!
ኢየሱስ ህይወት፣ ህይወትም ኢየሱስ ነው።
ከፍርዕዖን ግዛት ሳይሆን ከሰይጣን ሀሳብ ( ከዘላለም ሞት) ነብሳችን ያዳናት ጌታ ኢየሱስ ይባረክልን።
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ፈጣሪህን እና በዙሪያህ የሚገኙ ሰዎችን ለማመስገን የግድ ትልቅ ነገርን እስኪያደርጉልህ አትጠብቅ አምላክህን ለማመስገን ግዴታ ከትልቅ አደጋ እስኪያስመልጥህ አትጠብቅ ምክንያቱም በሰላም ወጥተህ መግባትህ ውስጥ አንተ ያላስተዋልካቸው እርሱ ግን አስቀድሞ የተከላከለልህ እጅጉን ከብዙ አደጋዎች አድኖሃል ሰዎችም ቢሆኑ የሚታይ ነገር ስላደረጉልህ ሳይሆን ምንም ባያደርጉ እንኳን ስሜትህን መጋራታቸውን አስተውል ።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በገጠመህ ትልቅ በሚመስል ትንሽ ችግር ምክንያት በችኮላ ተስፋ አትቁረጥ ውሳኔዎችህ ካለፉ በኋላ የማትቀይራቸው ሊሆኑ ይችላሉ ያንተ በህይወትህ ላይ ተስፋ ማጣት ብዙዎች መኖራቸውን ተርጉም እንዲያጣ እስከዛሬ ላንተ የከፈሉትን ሁሉ ዋጋቢስ ታደርገዋለህ አንዳንዶች አልወደዱኝም እያልክ የሚወዱህን አታስከፋ ህይወት መረረኝ ስትል የሚያጣፈጡልህንም እንዳታጣ ተጠንቀቅ።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
መዘናጋት
ከዋናው የህይወትህ አላማ፣ ካየህበት ስፍራ እንዳትደርስ መሰናክል የሚሆንብህ ትልቁ ተግዳሮትህ መዘናጋት ይባላል። ለጥቂት ጊዜ ፈታ ልበል ትንሽ ዘና ልበል በማለት ፋት ልትሰጠው ከማይገባህ የህይወት አላማህ እንድትዘናጋ ትኩረትህን ፈቅ እንድታደርግ ያደርግሀል።

ከመዘናጋት ህይወት ለማምለጥ አላማህን አጥብቀህ መያዝን ፈጽመህ አትርሳ። ዝም ብሎ ያለማቋሩጥ የሚፈሰው ውሀ ድንጋዮን አብዝቶ እንደሚሸረሽረው እንዲሁ ደግሞ አንተም በትኩረት ስትሰራ ስራህ እንዲሁ ብርቱ ውጤትን ያስገኝሀል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
እጅህን ለነገ ስጠው
በህይወት መንገድ ስትጓዝ በሚገጥምህ ከባድ ገጠመኞች ምክንያት የህይወት ግራጫ መልክ የያዝከው ተስፋ መንምኖ ነገን ማየት፣ በመንገድህ ስትጓዝም ሌላ እድል እንዳለም ማስተዋል እስካትችል ሊያጨልምብህ ይችላል የትላንት የልብ ላይ ህመም እድል እንደሌለህ፣ ምንም ብታረግ ህይወትህ ትርጉም እንደሌለው አርጎ ሊያሳይህ ይችላል።

ትላንት በሆነው ነገር ከፊት ያለው ዘመንህ ሊታሰርብህ፣ ልትዋጀው፣ ልትሰራበት፣ ልትጠቀምበት ሲገባህ የእርሻ ማሳላይ አረም ሊበቅልበት፣ ጓተራህም በድርቅ ሊመታብህ፣ ቤትህም ጾሙን ሊያድር ይችላል።

በትላንትና እስራት ስር መሆን ዘመንህን በአንበጣ ማስበላት ነው። ወደፊት ከመሄድ ተገትተህ በቆምክበት ጊዜ ልክ ኪሳራህም እየበዛ ይሄዳል ለዚህም ነው ሐዋሪያው ጳውሎስ "የሗላዬን እየተውኩ የፊቴን ለመያዝ እዘረጋለሁ" ብሎ ያስተማረው።

በተቻለህ አቅምና ፍጥነት የትላንት ህመምን፣ ጉዳትን፣ ችግርን፣ ከአእምሮህ ውስጥ አውጣው። አለበለዚያ በአደጉኛው ወይንቤቱ ከርችሞ ሊያስቀርህ ይችላል።

ከዚህ እስር ቤት ለመውጣት ከፈለግክህ እጅህን ለነገ ስጠው። በሙሉ ሀይልህ ነገን ብቻ ተመልከት ያኔ ከትላንት እስራት ነጻ ትወጣለህ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ራስህን እርዳ

አሁን በዚህ ሰአት ካለህበት ስፍራ ሊያወጣህ፣ ወደስኬት ጎዳናም ሊያሻግር ችግሮችህ በሙሉ አሸንፎ ውጤታማ ሊያደርግህ የሚችል ማን ይሆን?

አንተን የተሻለ ሰው ሊያደርግ የሚችል፣ ህልምህን፣ ራእይህን፣ የተፈጠርክለትን አላማ አከናውነህ እንድታልፍ ትልቁን ሚና የሚጫወተው ማን ይመስልሀ?

በህይወትህ የምትናፍቀውን ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ማን እንደሆን ታውቃለህ?

አንተ ራስህ ነህ!!!

ሌላ ማንም የለም ለአንተ ህይወት ለውጥ ዋናው ድርሻ የሚይዘው አንተ ራስህ ነው።

አንተ ወስነህ ካልተንቀሳቀስክ ማንም አይንቀሳቀስልህም፣ ማንም በህይወትህ የሚመጣውን ለውጥ አያስቀጥልልህም።

ስለዚህም ራስህን እርዳ ቆርጠህ ተነሳና ወደፊት ተራመድ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አደራ

ሰው ሰውን ሲያምነው፣ እንደራሱ ሲቆጥረው፣ ሲወደው፣ የሚወደውን ነገር በአደራነት በዚያ ሰው ዘንድ ሊያስቀምጥ ይችላል።

በማህበራዊ ህይወታችንም ይህንን ነገር ብዙውን ጊዜ እንታዘባለን። በአደራነት የተሰጠ ልጅ፣ ቤት፣ መኪና፣ ገንዘብ፣ ወዘተ አደራን ከሌላ ነገር የሚለየው ሰጪ አንድ ቀን ከእኛ ስለሚቀበል ነው። ማለትም ለጊዜው የተሰጠ እንጂ የእኛ ንብረት አይለመሆኑ ነው።

አንተ የአምላክህንና የብዙ ሰዎችንአደራ ተቀብለሀል ታዲያ ይህን አደራ ምን እያረከው፤ እንዴትስ እየተወጣከው ነው።

በቤተክርስቲያን የተሰጠህን አደራ እንዴት እያረክ ነው ባለህበት የአገልግሎት አቅጣጫ ሀላፊነትህን እንደሚገባ እየተወጣክ ነው? ወይስ?

በቤት የተሰጠህን አደራ እናት አናትህን ወንድም እህትህን ፣ ባለቤትህን፣ ልጆችህን እንዴት እየተንከባከብ ነው?

በማህበረሰብ ውስጥ የተሰጠህን አደራስ እንዴት እየተወጣክ ነው?

አደራ ሲሰጥህ ምን ያህል ታማኝ ተደርገህ እንደተቆጠርክ፣ ምን ያህል ትጋትና መሰጠት እንደሚጠበቅብህ ልታስብ ይገባሀል።

ተግተህም የተሰጠህን አደራ እንደ ራስ ልትይዝ፣ ልትንከባከብ ይገባል።


መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጽዳትና ጸሎት
በህይወት ስንኖር የእለት ተግባራችን ከሚሆኑ ነገሮች ውስጥ ትልቁን ስፍራ የሚይዘው ጽዳት ነው። ራሳችንን፣ አካባቢያችንን፣ ስራ ቦታችንን... እናጸዳለን ቆሻሻ ሲከማች ያንን ቦታ የማበላሸትና በሽታ የማምጣት አቅሙ ትልቅ ስለሆነ ህይወትና ጽዳት የተለያዮ ጉዳዮች አይደሉም።

የጥርስ ቆሻሻ ቶሎ ካልጽዳ ጥርስን ከጥቅም ውጪ እንደሚያደርገው፣ አካባቢ ካልጸዳ፣ ልብስ፣ ሰውነት ካልታጠበ ጀርምና በሽታ አምጪ ተዋሲያን እንደሚከማቹት ሁሉ ሰውም በጽሎት ማስወገድ ያለበትን ማንነት ካላስወገደ እንዲሁ ባልተወገደው አላስፈላጊ ማንነት ህይወታችን ስለሚበላሽ በጽሎት የሚደረገውን ጽዳት አጠናክሮ መቀጠል ቸል የማይባል ጉዳይ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አካፍል

ከውልደትህ ጀምሮ ራስህን በብዙ ነገር እያስተማርክና እያሳደግክ መጥተህ ይሆናል ብዙ መጽሀፍትን አንብበህ በውጪ ሀገር ትምህርትን ተከታትለህ ይሆናል፤ ይህ ሁሉ እውቀት፣ ይህ ሁሉ ግብአት ለሌሎች ማካፈል ከሌለበት ከንቱ ድካም ነው።

ምክንያቱም የተሰጠህ ነገር ሁሉ ከአንተ ስለሚያልፍ ለብዙዎች የህይወት ለውጥ ስለሚሆን፤ የሰበሰብከው ነገር ሁሉ ይዘህው አትሄድምና ለወንድምህ ማካፈልን አሁን መለማመድ ጀምር።

መጻፍ ካለብህ ጻፍ፣ ማስተማር ካለብህ አስተምር፣ መስጠት ካለብህ ስጥ ፣ ራስህን ብቻ የምታስተዳድርና ምትመራ አትሁን ወንድምህንም ማገዝን ዛሬ ጀምር።

የተሰጠህ ነገር ከአንተም ይበልጣልና አሁኑኑ ማካፈል ጀንር ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

🥇Happy anniversary🥇
🥇Happy anniversary🥇
🥇Happy anniversary🥇
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
👨‍💼👨‍💼የእውነተኛ ወንድ ባህሪያት👨‍💼👨‍💼

📖📖 ተከታታይ ትምህርት 📖📖

ክፍል ፩

መግቢያ

🔹የምንሙለከታቸው ፊልሞች፣ የምናነባቸው መጽሄቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያው፣ ማስታወቂያው ሁሉ የሚሰጡን "የወንድ" ትርጓሜ
እውነተኛ ወንድ ጠንካራ
እውነተኛ ወንድ ተደባዳቢ
እውነተኛ ወንድ ገንዘብ ያለው
እውነተኛ ወንድ በራሱና በራሱ ብቻ ሚመካ
እውነተኛ ወንድ ለአንድ የታመነ ሳይሆን ብዙ ሴቶች ሚያፈራርቅ
እውነተኛ ወንድ ጠጪ፣ አጫሽ፣ድራግ ተጠቃሚ
እውነተኛ ወንድ ከአእምሮ በላይ በጡንቻ የሚያምን
እውነተኛ ወንድ ትሁት ሳይሆን ከእኔ በላይ የሚል እንደሆነ ያስተምሩናል።

🔹አለም ምን ጊዜም ቢሆን እውነትን ሳይሆን በብልጭልጭ የተሸፈነ ውሸትን ነው ምታቀርብልን። እውነትን በሀሰት ብቻ ሳይሆን በብልጭልጭ ውበትም ሸሽጋ ነው ምታቀርበው።
ይህ ደግሞ የሰው ልጅ ከእውነት እንዲርቅ በሀሰት ውበት እንዲያዝ ማታለያ መንገድ ነው።

🔹እውነተኛ ወንድ ባህሪያቶቹን የሚያገኘው ከአምላኩ ከፈጣሪው ብቻ ነው ነገር ግን ሰይጣን የዚህን ክቡር ፍጥሩ መንፈሳዊ ህይወት፣ ባህሪ፣ እውነተኛነት ለማበላሸት ከጽሎት መሰዊያውና ከቃሉ ማእድ እንዳራቀው እንታዘባለን።

🔹ለማሳያነትም በ2016 እኤአ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየውም
47% ወንዶች ብቻ ናቸው በየለቱ ሚጽልዩት
30% ወንድሞች ብቻ ናቸው በየእለቱ ቃሉን የሚያነቡት።
28% ወንዶች ብቻ ናቸው ለህይወት መንፈሳዊ ምሪት ያስፈልጋል ብለው የሚያምኑት።

ይህ ታዲያ ምን ያህል የእውነተኛ ወንድ ባህሪያት እንደ ጠፋ በዚህም ምክንያት እውነተኛ ወንድ መጥፋቱን ማሳያዎች ናቸው። ከዚህም የተነሳ ያለንበት ዘመን ከመቼውም ጊዜ በላይ እውነተኛ ወንድ የሚያስፈልግበት ዘመን ነው።

ይህን እውነተኛ ወንድ ሁሉ ይፈልገዋል። ፈላጊው ማን ነው የተባለ እንደሆን

🔹በመጀመሪያ ፈጣሪው አምላኩ እግዚአብሄር እውነተኛ ወንድ ይፈልጋል።
ጥሪውን ተሸክሞ አምላኩን እየፈራ የተሰጠውን የመሪነት ሀላፊነት ሚወጣን ወንድ እግዚአብሄር ይፈልጋል

🤱እናቶች እውነተኛ ልጅ ታዛዥ እና ደጋፊ የሆነ እናት አባቱን የሚያከብር መሳቀቂያ ሳይሆን ማረፊያ የሚሆንን እውነተኛ ወንድ ይፈልጋሉ።

🙍‍♀እህቶች እውነተኛ ወንድም፣ፍቅረኛ፣ ባል
የሚረዳ፣ የሚደግፍ፣ ሚንከባከብ፣ ከራሱ በላ እነሱን ሚያስቀድም፣ ህመምን ሳይሆን እረፍትን የሚያመጣን እውነተኛ ወንድ ይፈልጋሉ።

🔹ሀገር ካለችበት ውጥንቅጥ የሚያወጣ፣ ለጥሪው በጽናት የቆመን፣ ሀላፊነትም በሚገባ ሚወጣን ወንድ ሀገር ትፈልጋለች ይፈልጋል።

ይህ ወንድ ማን ነው?

ቀጣይ ሳምንት ይቀጥላል

አዘጋጅ:- ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጽናት

በምድር ላይ ተሳካላቸው ምትላቸው ሰዎች ሁሉ በአንድ ቀን የተከናወነላቸው እንዳይመስል ብዙ አመታትን በዝቅታ ህይወት የተጓዙ፣ በርሀብ በጥማት፣ በማጣት፣ በችግር፣ በግራ መጋባት፣ በመገፋት፣ የኖሩ ናቸው።

ዛሬ የትልልቅ ድርጅቶች ባለቤት የሆኑ የብዙ ሚሊዬን እና ቢልየን ብር ካፒታል የሚያንቀሳቅሱ ትላንት ላይ በእግር ብዙ መንገድ የተጓዙ፣ በብዙ የከሰሩ፣ በተደጋጋሚ ሽንፈት የገጠማቸው፣ የተራቡ፣ ነገር ግን ወደፊት ከመቀጠል ራሳቸውን ያልገቱ ናቸው።

የእግዚአብሄር ሰዎችንም ብንመለከት ይህንኑ እውነት እንታዘባለን ሙሴ ሙሴን ለመሆን 40 አመታትን የበግ ጠባቂ ነበር።

ዮሴፍ ለመንገስ ብዙ ዘመናትን በባርነትና በእስር አሳልፏል።

አብርሃም ልጅን ለማግኘት 25 አመታትን ጠብቋል።.........

እነዚህን እና ሌሎችንም የእምነት አባቶችና እናቶች ብንመለከት የስኬታቸው ሚስጢር "ጽንአት" ይባላል

ሰው ጸንቶ ነው የተገባለት ስፍራ የሚደርሰው ስለዚህም በህይወትህ በሚገጥምህ መውደቅና መነሳት ተስፋ ፈጽሞ አትቁረጥ ነገር ግን በጽንአት ወደፊት ተራመድ ያንተ ተአምር ከፊት ይጠብቅሀል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus