Scripture union addis ababa
103 subscribers
607 photos
13 videos
29 files
14 links
Download Telegram
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አንተ ሌሎች (የተናገሩልህን) የተናገሩህን አይደለህም አንተ ለራስህ የነገርከውን ግን ነህ! ሌሎች እሱ በጣም ጎበዝ ነው ማድረግ ይችላል እያሉ ቢያወሩም አንተ ማድረግ እንደምትችል በራስህ ካልተማመንክ የእነሱ ምስክርነት ካለህበት ፈቀቅም አያደርግህም ። ግን እንደምትችል አቅም እንዳለህ እራስህን ማሳመን ከቻልክ እናም በሚያስፈልግህ ነገር እራስህን ማዳበር ከቻልክ ሌሎች ስላንተ ሳይናገሩልህ አንተ ራስህን ማሳየት ትችላለህ ።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
መጨረሻ መጀመሪያ
ህይወት የአንድ እስፍንጥር ጉዞ፣ ሳትሆን ልክ እንደ ማራቶን ረዥም ጉዞ ናት። ይህ ጉዞ ታዲያ በውስጡ አድካሚ፣ ጉልበት የሚያዝል፣ አሰልቺ፣ ድልም፤ ሽንፈትም ይዞ ያለ ነው። የእያንዳንዳችን የምንሮጥበት መስክ የተለያየ ቢሆንም ግን ሩጫው የማያቋርጥ የተለያዩ ደረጃዎች ያሉት ነው።
የአንዱ መጨረሻ የሌላው ጅማሬ ነው የኬጂ ትምህርት ሲያበቃ የአንደኛ ደረጃ ይከተላል፣ እሱ ሲያበቃ ሁለተኛ ደረጃ እጅግ በመማረር መች ነው ይህ ትምህርት የሚያበቃው እንደው ማትሪክን ጨርሼ እፎይ...., ብለን ሳንጨርስ የግቢ ወይም ኮሌጅ እጣ ፈንታ ይከተለናል እያለ እያለ ህይወት አንዱን ስንጨርስ ሌላውን እያቀበለች ወደ ምንመለስበት ትመራናለች።

ሞትም ያው ነው ማብቅያ ሳይሆን የሌላ አዲስ ህይወት መጀመሪያም ጭምር።
ይህንን አስተውል አንዱን በድል ስትጨርስ ሌላው እንደሚከተል ከዚያ ውጪ ምንም እንደማይገጥምህ በማሰብ እንዳትኖር ነገ ሌላ አዲስ እድል እንዳለም አርቀህ ተመልከት።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
አጥብቀህ ቅድስናህን ጠብቅ
በወደቀ አለም በወደቀ ስርአት ውስጥ እየኖርን፣ እየተመላለስንም ቢሆንም ግና የጠራን አምላክ እንድንቀደስ፣ ለቅድስናም ጠርቶናል።

መቀደስ ማለት ለአንድ ነገር ራስን መለየት ማለት ነው። ቅድስናን እንደ ሜኝነት በምትቆጥር አለም እየኖርን ራሳችንን መለየት ቀላል አይሆንም በስውር፣ በጨለማ በስውር የሚደረገው ጉዳይ ገሀድ በወጣበት በዚህ ወቅት ሀጢያትን እንደ ቆሻሻ መጽየፍ አቅቶናል።

አቅሙን አሰባስቦ፣ ለቅድስና ዋጋ ከፍሎ ራሱን ከዚህ አለም እድፍ የሚጠብቅ አምላክን የሚፈራ፣ ለእርሱም ዋጋ የሚከፍል፣ የቅድስና ትርጉምና ዋጋ የተረዳ ብቻ ነው።

ከጋብቻ በፊት በማይሆን ትስስር ውስጥ ገብተን በጋብቻችን እለት የምንሰጣጠውን ውድና ክቡር ስጦታ ያለጊዜውና ቦታ ፈጽመን አምላክንም አሳዝነን ነፍስና መንፈሳችንንም አሳድፈን ክቡሩን ነገር አቃልለን ከህይወት መንገድ ርቀን ተገኘን።

"ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹህ ነው።" እንደሚል ቅዱስ ቃሉ በቅድስና መንገድ ብቻ ነው የአምላክን ፍጹም በረከት ልናገኝ ልናጣጥም የምንችለው። ስውር ውሀ ቢጣፍጥም በቀኑ መጨረሻ ዋጋ ማስከፈሉ፣ አፍላ እድሜአችንን ለማይራራው መገበራችን አይቀርም።

ቅድስና ዝም ብሎ ቃል ብቻ ሳይሆን በውስጡ ሀይልና ጉልበት ነው ለብዙዎች ድካም፣ ልፍስፍስነት ቢመስልም፤ የአምላክ ነገር ደካማ ሲሉት ሀያል፣ የተናቀ ሲሉት የማእዘን ድንጋይ ዋና ምሰሶ ነውና አለምን ፈጽመህ አትስማ።

ለአምላክህ ራስህን ለይ! ስጋህንም፣ ህሊናህንም፣ መንፈስህንም፣ ህይወትህንም በቅድስና ውሀ በየእለቱ እያጠብህ ንጽህናዋን ጠብቅ።

በህይወትህ መንገድ ሁሉ ራስህን ከሚያሳድፍ መንፈስህን፣ ስጋህንም ከሚያረክስ ነገር አርቅ

ያለ ቅድስና እርሱን ማየት አትችልምና ስትቀደስ እርሱን ማየት ክብሩን ሀይሉንም መመልከት ትችላለህና። የምግብን ጣእም የሚያውቅ በተመገበ ብቻ እንደሆነ ሁሉ የቅድስናን ዋጋ የሚረዳ የተቀደሰ ብቻ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ህይወትና እንቆቅልሽ
ህይወት ከእንቆቅልሽ ተለይታ አታውቅም በየአንዳንዱ ቀን ከተለያዩ የህይወት እንቆቅልሾች ጋር መጋጠምህ አይቀርም፤ በቀላሉ መፍትሄ የማታገኝለት፣ ነገሩን ዝም ብለህ ስትመለከተው ምንም ትርጉም የሌለው፣ ልትረዳው የማትችለው በየእለቱ የሚያሳስብህ፣ የሚያስጨንቅህ፤ ተጨንቀህም አስበህም መፍትሄ የማታገኝለት የህይወት እንቆቅልሽ፤ በየእያንዳንዱ የመንገድህ ፌርማታ ላይ ሊጠብቅህ ይችል ይሆናል።

ዙሪያህን መመልከት ትተህ ወደ ላይ ብትመለከት የእንቆቅልሾችን ሁሉ መፍትሄ የሆነውን ጌታ በዙፋኑ ትመለከታለህ፣ እርሱ ያንተን የተተበተበ የህይወት ጥያቄና ግራም የሚያጋባህን ነገሮች ሁሉ ሊፈታ መፍትሄንም ሊሰጥህ ከባድ የሚባል ነገርን ለማያውቀው ጌታ፣ ለእርሱ ይህ ቀላል ነው።

አንተ ብቻ ጩህ ነገርህንም ይዘህ በፊቱ ቁም።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ምንድን ነው ምትሰራው?

አሁን በዚህ ወቅት ምን እየሰራህ ነው?
የምትሮጠው ሩጫ ምን ላይ ነው? ለምትወደው፣ ህልም፣ ራእይህ፣ ለሆነው ወይስ በተቃራኒው?

በውስጥህ የመኖርን ምክንያት ለሚሰጥህ፣ ባይከፈልህም በደስታ ለምታረገው ነገር፣ ስራህን ስታስብ የበለጠ መሰጠት፣ ጠንክሮ መስራትን በውስጥ መነቃቃትንና ግለትን ለሚሰጥህ ነገር ካልሆነ እንዲሁ በዝለት መቼ ጨርሼው በተገላገልኩ፤ እያልክ ህይወትህ ደስታን ሳያገኝ እንዲሁ ትኖራለህ

ጉልበትህንም ሀልህንም ለአንተ የውስጥ ፍላጎትህ ላለበት ነገር አውለው ያኔ ትበረታለህ፣ ያኔ እንዲሁ ምንም ሳታበረከት በከንቱ አታልፍም

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
🙏🙏ሰላም ሰላም የ አባቴ ልጆች እንዴት አላችሁልን🙌🙌🖐

ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ፡ በጣም በጉጉት የሚጠበቀው የ ENTOTO AMBA JIDIDIAH FELLOWSHIP የ ተራራ ፀሎት ፕሮግራማችን ከ final exam በኋላ ሚያዚያ 2 ቅዳሜ ቀን ይሆናል ጌታም በክብር ይገናኘናል🙌🙌 መቅረት አይቻልም

ተባረኩ!!!!
@entotoambafellowship
@entotoambafellowship
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ትኩረት
ህይወት በብዙ ሀላፊነቶችና ግዴታዎች የተሞላች ነች እነዚህንም ስራዎች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመወጣት በአንድ ነገር ላይ አተኩሮ የመስራት ስልትን ማዳበር ይጠይቅሀል። እጅህ ላይ ያለውን ሁሉ ለማከናውን የምትሮጥ ከሆነ ጊዜህን፣ ጉልበትህን፣ ሀይልህን እንዲሁ በከንቱ ትጨርሰዋለህ።

ብዙ ስራ ቢኖርም በቅደም ተከተል፣ አንድ በአንድ በነገሮች ላይ የመስራት ስልትን መጠቀም ይኖርብሀል፤ አለበለዚያ ሁሉን ለማድረግ ስትሞክር አንዱንም ሳትተገብር ምንም ውጤት ሳታስመዘግብ እንዲሁ ታልፋለህ።

የተበታተነ ህይወት ምን ጊዜም ውጤቱ ከንቱ ልፋት ብቻ ነው። የጎላ ፍሬ ማየት ከፈለግክ ዋና የምትለውን የህይወትህን ተግባር መርጠህ በዛ ላይ አድምተህ ስራ ያኔ የሚያጎመራ ውጤትን ታገኛለህ።

ብዙ የሮጠ ምንም አያገኝም ይልቅስ የሚፈልገውን ለይቶ አውቆና መርጦ በጥበብ የሚሮጥ ስኬትን ያጣጥማል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጸሎት

ህይወት በብዙ ፈተናዎችና ትግሎች የተሞላች ነች አንዱን ታግለህ ሳትጨርስ ሌላው ይከተላል፣ እሱንም ሳታገባድድ ደግሞ ሌላው ይመጣብሀል እጅግ አታካችና አስቸጋሪ መንገድ ነች ህይወት። ታዲያ እነዚህን ውጣ ውረዶች በሙሉ በራስህም ሆነ ይረዱኛል በምትላቸው ሰዎች በኩል በመታገል፣ የበላይ ሆነ መጨረስ የማይታሰብ ነው። ሁለም ሰው የራሱ ችግር ስላለበት ላንተ ሊደርስልህ አይችልም

ነገር ግን ወደ ሰማዩ አባትህ አይንህን ብታነሳ፤ እርዳኝ ብለህ ብትጮህ፣ በጸሎት ብቻ አሸናፊ ትሆናለህ። በፊቱ በመንበርከክ ሀይልን ትቀበላለህ የገጠመህን ተራራም የመሻገሪያ አቅም ይጨመርልሀል።

በጸሎት ልብህን ትጠብቃለህ፣ ከአባትህም ጋር ህብረትን ታደርጋለህ፣ ህይወትህ ከወንዝ ዳር እንዳለ ተክል ያብባል ድርቅ ቢመጣም እንኳ አይጠወልግም። ከራስህም አልፈህ ለብዙዎች መፍትሄ ትሆናለህ፣ መዝሙረኛው ዳዎት እንዳለው" በጠዋትም በቀትርም በማታም" ፊቱን በጸሎት አብዝተክ መፈለግ ይሁንልህ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ስብራትህን ይዘህ

ህይወት ትእይንት ናት ብዙ ገጠመኝ የተሞላች ትእይንት መኖር ስትቀጥል የምትታዘበው ነገር ይህንኑ እውነታ ነው።

ብዙ ህመም፣ ብዙ ግራ መጋባት፣ ብዙ ትግል በዚህ መሀል የህይወት ስብራቶችም ይገጥሙሀል ለማገገም ለመፈወስም ጊዜ የሚፈልጉ፣ ቶሎ የማይሽሩ ህመሞች ሲያልፋም ጠባሳ ጥለው የሚያልፋ የህይወት ስብከቶች አሉ በእነዚህ ስብራቶች ውስጥ ሆኖ ወደፊት መሄድን ማሰብ ይከብዳል ተስፋ ይመነምናል ህይወት ትርጉም ያጣል።

ወደፊት መሄድ ለወጣት የማይቻል ተራራ ይሆናል ወደፊት ካልሄድን ወደሗላ እየሄድ ነውና ያገኘሀቸው ለውጦችን በሙሉ ማጣትህ ነው።

ስለዚህም ያለህ አማራጭ ህመምህን፣ ግራ መጋባትህንም፣ ስብራትህን ይዘህ በፊቱ በጸሎት ሁን እርሱን እሻው እየወጋ፣ እየጠዘጠዝህ ካለው ህመምህ ጋር በፊቱ ሁን እርሱ ፈዋሽህ፣ መድሀኒትህ እግዚአብሄር ነውና።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
የእግር ኳስ ነገር
በአለማችን ላይ የሰውን ልብ እጅግ ከገዙ፣ ህይወቱንም እንኳ እስከመስጠት እንዲደርስ ምክንያት ከሆኑ የስፓርት ውድድሮች ሁሉ እግር ኳስ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

በኳስ ምክንያት የተጣሉ፣ የተገዳደሉ፣ የተታረቁ፣ ድንበር ሳይበግራቸው አንድነትን ያሳዩ፣ ብዙ ሰዎች አሉ። እኔ ከሚገርመኝ የእግር ኳስ ስልቶች ውስጥ የ12ቱ ተጫዋቾች ነገር ነው። የሁሉም ድል የሚወሰነው እያንዳንዳቸው በሚያደርጉት ጥረትና ትጋት ላይ ነው ሁሉም ለቡድኑ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል አይደለም፣ የአንዱ ተጫዋች ድካም በሙሉ ቡድኑ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ቀላል አይደለም።

"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንደሚባለው የእያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ዜጋም ህይወት እንደ እግር ኳሱ ሁሉ ነው።
የእያንዳንዱ ሰው ሀላፊነቱን እንደሚገባ መወጣት ወይም ቸልተኛ መሆን በድምሩ በሀገር ላይ የሚያስከትለው የድል ወይም የኪሳራ ውጤት ቀላል አይደለም።

የአንዱ ጥንካሬ፣ ትጋት ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሀገሩ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጾ አለው።
ስለዚህም በተሰማራህበት ስፍራ በር ትተህ ስራ የአንተ ብርታ ለመላ ሀገሪቱ አስተዋጾ ቀላል ስላልሆነ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ጠንክረህ ስራ

ህልምህን፣ ራእይህን፣ እውን ማድረግ የምትሻ፣ የምትመኝ ከሆነ ምኞትህንና ፍላጎትህን በጠንካራ የስራ ባህል ልትደግፈው ይገባሀል።

ህይወት ያለ ስራ ትርጉም የላትም። በህይወት ደስ እየተሰኘህ እንድትኖር ከሚያደርጉህ ነገሮች መሀል በላብህ፣ በድካምህ፣ ለፍተህ የምታገኘው ፍሬ ነው።

ከስራ የሚገኝ ውስጣዌ እርካታ አለ፣
ጠንክሮ መስራት በውስጥህ ልዮ የውጤታማነትን ስሜት ይፉጥርልሀል፣ ብዙ እንድታፈራም በር ይከፍትልሀል

ስራ ፈት መሆን ራስህ፣ አእምሮህን፣ ቤተሰብህን፣ ሀገርህንም በብድርና በችግር ውስጥ በማስማቀቅ ለከፋ ድህነት ከማጋረጥ ያለፈ ነገር በውስጡ አያስገኝህም።

ለብዙዎች መትረፋን የምታስብ ከሆነ ራስህን በጠንካራ የስራ ባህል አስታጥቅ። ያኔ በብዙ ፍሬ ትባረካለህ።
በምን ላይ ነው የተሰማራሕው በትምህርት? በስራ? ጠንክረህ ስራ፣ አትድከም፣ አትሰልች በመጨረሻ ሙልካሙን የድካምህን ፍሬ ታጭዳለህ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ተስፋ አለ
ምን እየተሰማህ ነው? ውስጥህ ምን እየጎዳህ ነው? ተስፋ አርገህ አጣህ? እንዳሰብከው ሳይሆን ቀረ? አይዞህ አሁንም ተስፋ አለ ተስፋን የሚሰጥ ስላለ እርሱ አሁንም በዙፋኑ ላይ ጸንቶ ስለሚኖር አሁንም ተስፋ።

ቀን ሲጨልምብህ፣ ግራ ሲገባ በእርሱ ታምነህ፣ ነገ ብርሀን ይሆናል ብለህ ጉዞህን ቀጥል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አስረክበው
በህይወትህ እጅግ ልታገኘው የምትፈልገው ነገር ይኖራል። ብዙም ታግለህ፣ ሮጠህም ይሆናል ነገር ግን ምንም ለውጥ አላየህበትም።

ብዙ ብትለፋም የተቀየረ ነገር የለውም በእንደዚህ አይነት ጊዜ ልታረግ የምትችለው ነገርህን በሙሉ ለእግዚአብሄር ማስረከብ፣ ለጌታ አደራ አሳልፈህ ስጠው በቃ ልብህንም በእርሱ ላይ ጣለው እርሱ መንገድህን ቀያሽ ህይዉትህንም በእጁ የያዘ ጌታ ነው።

እርሱን ታምነኽው ተጓዝ የሚያሳስብህን ግር የሚልህን ሁሉ ለእርሱ ሰጥተኽው መንገድህን ቀጥል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ሰልፍ ዲሲፕሊን
ሰው በህይወት ዘመኑ ሁሉ ውጤታማና ስኬታማ የሆነን ህይወት ለመምራት የሚሻ ከሆነ ራሱን የመምራት ጥበብ ማዳበር ይኖርበታል።

ሰልፍ ዲሲፕሊን ማለት አንድን ተግባር ከግብ ለማድረስ ራሳችንን በመቆጣጠር፣ ስርአት በማስያዝ፣ መከፈል ያለበትን ዋጋ ሁሉ በመክፈል የምንኖርበት ስልት ነው።

ወደ አላማህ እንዳትደርስ፣ ከግብህ ጋር እንዳትገናኝ መሰናክል ከሚሆንብህ ነገር ትልቁና ዋናው ያው ራስህ ነህ ፤ ያማለት ስንፍና፣ እንቅልፍ ማብዛት፣ ወሬ፣ ሀሜት፣ ስራን አለመውደድ እነዚህ ሀሉ ከራስህ የሚመነጭ ተግዳሮት፣ መሰናክል ናቸው።

ማሸነፊያ መንገዱ አንድ ነው ራስን የማስተዳደር ( የመግዛት፣ የመምራት) ጥበብ ማዳበር፤ ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ መስጠይ፣ ዋና መሆን ላለበት ጉዳይ ዋና ማድረግ፣ የጊዜ አጠቃቀምን ማስተካከል፣ ወዘተ....... ራሳችንን የማስተዳደሪያ መንገዶች ናቸው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በምትሰራቸው ስራዎች አለመሳካት እየገጠመክ እየወደክ እየተነሳህ ህይወት ትቀጥላለች። ለማደግ ለመለወጥ ብለህ ብዙ ነገር ሞክረክ ሳይሳካ ይቀራል። ግን ፍላጎትህ እውነት ካለው ካንተ የሚጠበቀው ተስፍ ሳትቆርጥ ደጋግሞ መሞከር ነው። አይሳካም አይሆንም ወይም አሁንም ይበላሻል ብለህ ሙከራህን አታቁም።ሁሉም ያደገው ከአንድ እንጂ ከመቶ አይደለም አንተም ከስኬትህ ሳይሆን ከውድቀትህ ጀምር።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በአመት አንዴ!!

ፋሲካ በአመት አንዴ አክብረን የምናልፈው በዓል አይደለም። ፋሲካ ምግብና መጠጥም አይደለም። ፍሲካችን ኢየሱስ ነው።
“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5

እለት እለት ኢየሱስን በማወቅ ማደግ ይሁንልን!
ኢየሱስ ህይወት፣ ህይወትም ኢየሱስ ነው።
ከፍርዕዖን ግዛት ሳይሆን ከሰይጣን ሀሳብ ( ከዘላለም ሞት) ነብሳችን ያዳናት ጌታ ኢየሱስ ይባረክልን።
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ፈጣሪህን እና በዙሪያህ የሚገኙ ሰዎችን ለማመስገን የግድ ትልቅ ነገርን እስኪያደርጉልህ አትጠብቅ አምላክህን ለማመስገን ግዴታ ከትልቅ አደጋ እስኪያስመልጥህ አትጠብቅ ምክንያቱም በሰላም ወጥተህ መግባትህ ውስጥ አንተ ያላስተዋልካቸው እርሱ ግን አስቀድሞ የተከላከለልህ እጅጉን ከብዙ አደጋዎች አድኖሃል ሰዎችም ቢሆኑ የሚታይ ነገር ስላደረጉልህ ሳይሆን ምንም ባያደርጉ እንኳን ስሜትህን መጋራታቸውን አስተውል ።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በገጠመህ ትልቅ በሚመስል ትንሽ ችግር ምክንያት በችኮላ ተስፋ አትቁረጥ ውሳኔዎችህ ካለፉ በኋላ የማትቀይራቸው ሊሆኑ ይችላሉ ያንተ በህይወትህ ላይ ተስፋ ማጣት ብዙዎች መኖራቸውን ተርጉም እንዲያጣ እስከዛሬ ላንተ የከፈሉትን ሁሉ ዋጋቢስ ታደርገዋለህ አንዳንዶች አልወደዱኝም እያልክ የሚወዱህን አታስከፋ ህይወት መረረኝ ስትል የሚያጣፈጡልህንም እንዳታጣ ተጠንቀቅ።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
መዘናጋት
ከዋናው የህይወትህ አላማ፣ ካየህበት ስፍራ እንዳትደርስ መሰናክል የሚሆንብህ ትልቁ ተግዳሮትህ መዘናጋት ይባላል። ለጥቂት ጊዜ ፈታ ልበል ትንሽ ዘና ልበል በማለት ፋት ልትሰጠው ከማይገባህ የህይወት አላማህ እንድትዘናጋ ትኩረትህን ፈቅ እንድታደርግ ያደርግሀል።

ከመዘናጋት ህይወት ለማምለጥ አላማህን አጥብቀህ መያዝን ፈጽመህ አትርሳ። ዝም ብሎ ያለማቋሩጥ የሚፈሰው ውሀ ድንጋዮን አብዝቶ እንደሚሸረሽረው እንዲሁ ደግሞ አንተም በትኩረት ስትሰራ ስራህ እንዲሁ ብርቱ ውጤትን ያስገኝሀል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus