Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ተመለስ
የሯጭ ህይወት እጅግ በብዙ ጥንቃቄ፣ ራስን መግዛት፣ ትጋት፣ ጥረት፣ አላማ ተኮርነት፣ የተሞላ ህይወት ነው። ብዙ አድካሚ የሆነ የልምምድ ጊዜያቶችንም ያሳልፋል በልምምድ ቦታም በውድድር ስፍራም ግን ፍጹም ሊዘነጋ የማይገባው ህግ አለ፤ እርሱም ከመሮጫ መስመር አለመውጣቱ ነው።
የክርስትናም ህይወት ይህው ነው ከተሰመረው መስመር ያለ መውጣት፤ ነገር ግን ሰው ነንና ከፈቃዱ መውጣር ፣ ወደ ሗላ መመለስ፣ መድከምና መዛል በህይወታችንን የምናየው ድካሞቻችን ናቸው።
ነገር ግን በዛ የድካም ህይወት ውስጥ ሆነን የምንቀጥል ከሆነ መጨረሻው የህይወት ራስ ከሆነው ጌታ መኮብለል ነውና ጊዜው ሳያልፍ ወደ ቤትህ ወደ አባትህ ጉያ ቶሎ ተመለስ።
መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus

ቴክኖሎጂ ና ትኩረት .pdf
1.2 MB
🖋🖋 ቴክኖሎጂ ና ትኩረት🖋🖋
በሳሙኤል ከበደ
ሰላም ሰላም እንደምን አላችሁ ይች ጽሁፍ ከተለቀቀች ትንሽ ቆይታለች ነገር ግን ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው ይህው ዳግመኛ አንብባችሁ አስተያየታችሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
በሳሙኤል ከበደ
ሰላም ሰላም እንደምን አላችሁ ይች ጽሁፍ ከተለቀቀች ትንሽ ቆይታለች ነገር ግን ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው ይህው ዳግመኛ አንብባችሁ አስተያየታችሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በኑሮህ ውስጥ ሁሉንም ነገር ያጣህ ከመሰለህ አንድ ነገር አስተውል የአንዳንድ ችገሮች መጨረሻ የሌሎች አዲስ ነገሮች መጀመሪያ ሊሆን ይችላል በህይወትህ ውስጥ የሚገጥምህ እያንዳንዱ ነገር ለበጎ ነው። አንድ ቀን ሁሉም ነገር ይስተካከላል ከአንተ የሚጠበቀው ነገሮችን በትግስት መጠበቅ ነው።
መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ራስን መምራት
በህይወትህ ዘመን ሁሉ ሌሎችን ለመምራት፣ መንገድ ለማሳየት፣ አቅጣጫ ለማሳየት ከመነሳትህ በፊት በመጀመሪያ ደረጃ ፈጽመህ ልትጎብዝበት የሚገባህ ነገር ራስህን መምራት ላይ ነው።
ራስህን በብቃት መምራት ስትችል፣ ራስህን እንደሚገባ ስታስተዳድር ያኔ ለሌላ ሀላፉነትም ትታጫለህ። በእያንዳንዱ የህይወት መስክ በቤተሰብ፣ በትምህርትህ፣ በመንፈሳዊው ህይወትህ፣..... ራስህን እንደሚገባ ስትመራ ያኔ አለምን ከሚያስተዳድር ሰው በላይ ጥበበኛ ና ብርቱ እንደሆንክ መገንዘብ አለብህ።

ለውሳኔና ፍርድ አትቸኩል
በየእለቱ በምንኖረው ህይወት ካሰብነው ውጭ የሚገጥሙን ብዙ ያልተጠበቁ ገጠመኞች አሉ። ነገሮችን ተመልክተን ያን ኛውን ወገን ሳንጠይቅ ወዲያው ወደ ውሳኔና ፍርድ የምንገባ አይነት መሆን የለበትም አንድ ነገር ሊከሰት የሚችልበትን ብዙ አማራጮች ሳንመለከት ወዲያው ነገሩ እንዲህ ነው ማለት ስህተት ነው እኛንም ከእውነታው በራቀ ድምዳሜ ምክንያት የራሴ የምንለውን ሰው ልናጣ እንችላለን። ስለዚህም በቀን ውሎህ የሚገጥምህን የትኛውንም ገጠመኝ በመጀመሪያ ነገሩ እንዲህ ሄኖ ቢሆንስ ብለህ ሳትመረምር ወደ ፍርድ አትፍጠን።

ሌላ አለ
የተመኘህው፣ የፈለከውን ነገር አጣሕው፣ ተወሰደብህ፣ አልተሳካልህም አይዞህ ለአንተ ሌላ አለ። ያልተሳካው ያንተ ባይሆን ነው ለአንተ ግን አምላክ ያዘጋጀልህ የትላንቱን የሚያስረሳ ሌላ አለ፤ ሌላ እድል ሌላ መንገድ ሌላ በር።
ትላንት ባለፈው፣ ትላንት ባልተሳካው ልብህ አይሰበር ለአንተ ሌላ አለህ የአንቺ ሌላ አለ።
አላስተዋልን ይሆን እንጂ ህይወትህን የሚመራው መንገድህንም ሚቀይሰው የሰማይ አምላክ ነው። ስለዚህም ነገርህን ሁሉ ትተህ ወደፊት ተራመድ።

እምነትና በጎ ህሊና ይኑርህ
በህይወትህ ዘመን ሁሉ ከእግዚአብሔር የተሰጠህን መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ እነዚህ ሁለቱ ያስፈልጉሀል እምነትና በጎ ህሊና ጳውሎስ ለእምነት ልጁ የመከረው ምክርም ይህ ነው።
ለእኛም የሚያሻን ይህው ነው በክርስትና ህይወት ውስጥ ድል ማድረግ ካስፈለገ እምነትና በጎ ህሊና መያዝ ያስፈልጋል
እግዚአብሄርን ማመን ደግሞም ህሊናችንን ከክፋት ማንጻት፣ በንጽህናም መኖር ያስፈልጋል።

በህይወትህ ውስጥ እያሳለፍካቸው ያለኸው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሚታለፉ የማይመስሉ ፈተናዎች በመብዛታቸው አንተላይ የተለየ ነገር እየሆነ እንደሆነ እያሰብክ አትጨነቅ ምክንያቱም የችግሩ ትልቅነት ትልቅ መፍትሔ እንድታስብ ያደርግሃል። የተወሳሰበ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አትፋራ የተወሳሰበ መሆኑ ብዙነገር ያስተምራል በብዙ አቅጣጫ እንድታስተውል እና መፍትሔዎችን እንድታስብ ያደርግሃል። በሚያጋጥሙህ ችግሮች ውሰጥ ተምረህ ማለፍ ያለብህ ብዙ አዳዲስ ነገሮች ይኖራሉ። እናም በሚያጋጥምህ ነገር አትደናገጥ።
መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አንተ ሌሎች (የተናገሩልህን) የተናገሩህን አይደለህም አንተ ለራስህ የነገርከውን ግን ነህ! ሌሎች እሱ በጣም ጎበዝ ነው ማድረግ ይችላል እያሉ ቢያወሩም አንተ ማድረግ እንደምትችል በራስህ ካልተማመንክ የእነሱ ምስክርነት ካለህበት ፈቀቅም አያደርግህም ። ግን እንደምትችል አቅም እንዳለህ እራስህን ማሳመን ከቻልክ እናም በሚያስፈልግህ ነገር እራስህን ማዳበር ከቻልክ ሌሎች ስላንተ ሳይናገሩልህ አንተ ራስህን ማሳየት ትችላለህ ።
መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
መጨረሻ መጀመሪያ
ህይወት የአንድ እስፍንጥር ጉዞ፣ ሳትሆን ልክ እንደ ማራቶን ረዥም ጉዞ ናት። ይህ ጉዞ ታዲያ በውስጡ አድካሚ፣ ጉልበት የሚያዝል፣ አሰልቺ፣ ድልም፤ ሽንፈትም ይዞ ያለ ነው። የእያንዳንዳችን የምንሮጥበት መስክ የተለያየ ቢሆንም ግን ሩጫው የማያቋርጥ የተለያዩ ደረጃዎች ያሉት ነው።
የአንዱ መጨረሻ የሌላው ጅማሬ ነው የኬጂ ትምህርት ሲያበቃ የአንደኛ ደረጃ ይከተላል፣ እሱ ሲያበቃ ሁለተኛ ደረጃ እጅግ በመማረር መች ነው ይህ ትምህርት የሚያበቃው እንደው ማትሪክን ጨርሼ እፎይ...., ብለን ሳንጨርስ የግቢ ወይም ኮሌጅ እጣ ፈንታ ይከተለናል እያለ እያለ ህይወት አንዱን ስንጨርስ ሌላውን እያቀበለች ወደ ምንመለስበት ትመራናለች።
ሞትም ያው ነው ማብቅያ ሳይሆን የሌላ አዲስ ህይወት መጀመሪያም ጭምር።
ይህንን አስተውል አንዱን በድል ስትጨርስ ሌላው እንደሚከተል ከዚያ ውጪ ምንም እንደማይገጥምህ በማሰብ እንዳትኖር ነገ ሌላ አዲስ እድል እንዳለም አርቀህ ተመልከት።

አጥብቀህ ቅድስናህን ጠብቅ
በወደቀ አለም በወደቀ ስርአት ውስጥ እየኖርን፣ እየተመላለስንም ቢሆንም ግና የጠራን አምላክ እንድንቀደስ፣ ለቅድስናም ጠርቶናል።
መቀደስ ማለት ለአንድ ነገር ራስን መለየት ማለት ነው። ቅድስናን እንደ ሜኝነት በምትቆጥር አለም እየኖርን ራሳችንን መለየት ቀላል አይሆንም በስውር፣ በጨለማ በስውር የሚደረገው ጉዳይ ገሀድ በወጣበት በዚህ ወቅት ሀጢያትን እንደ ቆሻሻ መጽየፍ አቅቶናል።
አቅሙን አሰባስቦ፣ ለቅድስና ዋጋ ከፍሎ ራሱን ከዚህ አለም እድፍ የሚጠብቅ አምላክን የሚፈራ፣ ለእርሱም ዋጋ የሚከፍል፣ የቅድስና ትርጉምና ዋጋ የተረዳ ብቻ ነው።
ከጋብቻ በፊት በማይሆን ትስስር ውስጥ ገብተን በጋብቻችን እለት የምንሰጣጠውን ውድና ክቡር ስጦታ ያለጊዜውና ቦታ ፈጽመን አምላክንም አሳዝነን ነፍስና መንፈሳችንንም አሳድፈን ክቡሩን ነገር አቃልለን ከህይወት መንገድ ርቀን ተገኘን።
"ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹህ ነው።" እንደሚል ቅዱስ ቃሉ በቅድስና መንገድ ብቻ ነው የአምላክን ፍጹም በረከት ልናገኝ ልናጣጥም የምንችለው። ስውር ውሀ ቢጣፍጥም በቀኑ መጨረሻ ዋጋ ማስከፈሉ፣ አፍላ እድሜአችንን ለማይራራው መገበራችን አይቀርም።
ቅድስና ዝም ብሎ ቃል ብቻ ሳይሆን በውስጡ ሀይልና ጉልበት ነው ለብዙዎች ድካም፣ ልፍስፍስነት ቢመስልም፤ የአምላክ ነገር ደካማ ሲሉት ሀያል፣ የተናቀ ሲሉት የማእዘን ድንጋይ ዋና ምሰሶ ነውና አለምን ፈጽመህ አትስማ።
ለአምላክህ ራስህን ለይ! ስጋህንም፣ ህሊናህንም፣ መንፈስህንም፣ ህይወትህንም በቅድስና ውሀ በየእለቱ እያጠብህ ንጽህናዋን ጠብቅ።
በህይወትህ መንገድ ሁሉ ራስህን ከሚያሳድፍ መንፈስህን፣ ስጋህንም ከሚያረክስ ነገር አርቅ
ያለ ቅድስና እርሱን ማየት አትችልምና ስትቀደስ እርሱን ማየት ክብሩን ሀይሉንም መመልከት ትችላለህና። የምግብን ጣእም የሚያውቅ በተመገበ ብቻ እንደሆነ ሁሉ የቅድስናን ዋጋ የሚረዳ የተቀደሰ ብቻ ነው።

ህይወትና እንቆቅልሽ
ህይወት ከእንቆቅልሽ ተለይታ አታውቅም በየአንዳንዱ ቀን ከተለያዩ የህይወት እንቆቅልሾች ጋር መጋጠምህ አይቀርም፤ በቀላሉ መፍትሄ የማታገኝለት፣ ነገሩን ዝም ብለህ ስትመለከተው ምንም ትርጉም የሌለው፣ ልትረዳው የማትችለው በየእለቱ የሚያሳስብህ፣ የሚያስጨንቅህ፤ ተጨንቀህም አስበህም መፍትሄ የማታገኝለት የህይወት እንቆቅልሽ፤ በየእያንዳንዱ የመንገድህ ፌርማታ ላይ ሊጠብቅህ ይችል ይሆናል።
ዙሪያህን መመልከት ትተህ ወደ ላይ ብትመለከት የእንቆቅልሾችን ሁሉ መፍትሄ የሆነውን ጌታ በዙፋኑ ትመለከታለህ፣ እርሱ ያንተን የተተበተበ የህይወት ጥያቄና ግራም የሚያጋባህን ነገሮች ሁሉ ሊፈታ መፍትሄንም ሊሰጥህ ከባድ የሚባል ነገርን ለማያውቀው ጌታ፣ ለእርሱ ይህ ቀላል ነው።
አንተ ብቻ ጩህ ነገርህንም ይዘህ በፊቱ ቁም።

ምንድን ነው ምትሰራው?
አሁን በዚህ ወቅት ምን እየሰራህ ነው?
የምትሮጠው ሩጫ ምን ላይ ነው? ለምትወደው፣ ህልም፣ ራእይህ፣ ለሆነው ወይስ በተቃራኒው?
በውስጥህ የመኖርን ምክንያት ለሚሰጥህ፣ ባይከፈልህም በደስታ ለምታረገው ነገር፣ ስራህን ስታስብ የበለጠ መሰጠት፣ ጠንክሮ መስራትን በውስጥ መነቃቃትንና ግለትን ለሚሰጥህ ነገር ካልሆነ እንዲሁ በዝለት መቼ ጨርሼው በተገላገልኩ፤ እያልክ ህይወትህ ደስታን ሳያገኝ እንዲሁ ትኖራለህ
ጉልበትህንም ሀልህንም ለአንተ የውስጥ ፍላጎትህ ላለበት ነገር አውለው ያኔ ትበረታለህ፣ ያኔ እንዲሁ ምንም ሳታበረከት በከንቱ አታልፍም

🙏🙏ሰላም ሰላም የ አባቴ ልጆች እንዴት አላችሁልን🙌🙌🖐
ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ፡ በጣም በጉጉት የሚጠበቀው የ ENTOTO AMBA JIDIDIAH FELLOWSHIP የ ተራራ ፀሎት ፕሮግራማችን ከ final exam በኋላ ሚያዚያ 2 ቅዳሜ ቀን ይሆናል ጌታም በክብር ይገናኘናል🙌🙌 መቅረት አይቻልም
ተባረኩ!!!!
@entotoambafellowship
@entotoambafellowship
ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ፡ በጣም በጉጉት የሚጠበቀው የ ENTOTO AMBA JIDIDIAH FELLOWSHIP የ ተራራ ፀሎት ፕሮግራማችን ከ final exam በኋላ ሚያዚያ 2 ቅዳሜ ቀን ይሆናል ጌታም በክብር ይገናኘናል🙌🙌 መቅረት አይቻልም
ተባረኩ!!!!
@entotoambafellowship
@entotoambafellowship
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ትኩረት
ህይወት በብዙ ሀላፊነቶችና ግዴታዎች የተሞላች ነች እነዚህንም ስራዎች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመወጣት በአንድ ነገር ላይ አተኩሮ የመስራት ስልትን ማዳበር ይጠይቅሀል። እጅህ ላይ ያለውን ሁሉ ለማከናውን የምትሮጥ ከሆነ ጊዜህን፣ ጉልበትህን፣ ሀይልህን እንዲሁ በከንቱ ትጨርሰዋለህ።
ብዙ ስራ ቢኖርም በቅደም ተከተል፣ አንድ በአንድ በነገሮች ላይ የመስራት ስልትን መጠቀም ይኖርብሀል፤ አለበለዚያ ሁሉን ለማድረግ ስትሞክር አንዱንም ሳትተገብር ምንም ውጤት ሳታስመዘግብ እንዲሁ ታልፋለህ።
የተበታተነ ህይወት ምን ጊዜም ውጤቱ ከንቱ ልፋት ብቻ ነው። የጎላ ፍሬ ማየት ከፈለግክ ዋና የምትለውን የህይወትህን ተግባር መርጠህ በዛ ላይ አድምተህ ስራ ያኔ የሚያጎመራ ውጤትን ታገኛለህ።
ብዙ የሮጠ ምንም አያገኝም ይልቅስ የሚፈልገውን ለይቶ አውቆና መርጦ በጥበብ የሚሮጥ ስኬትን ያጣጥማል።

ጸሎት
ህይወት በብዙ ፈተናዎችና ትግሎች የተሞላች ነች አንዱን ታግለህ ሳትጨርስ ሌላው ይከተላል፣ እሱንም ሳታገባድድ ደግሞ ሌላው ይመጣብሀል እጅግ አታካችና አስቸጋሪ መንገድ ነች ህይወት። ታዲያ እነዚህን ውጣ ውረዶች በሙሉ በራስህም ሆነ ይረዱኛል በምትላቸው ሰዎች በኩል በመታገል፣ የበላይ ሆነ መጨረስ የማይታሰብ ነው። ሁለም ሰው የራሱ ችግር ስላለበት ላንተ ሊደርስልህ አይችልም
ነገር ግን ወደ ሰማዩ አባትህ አይንህን ብታነሳ፤ እርዳኝ ብለህ ብትጮህ፣ በጸሎት ብቻ አሸናፊ ትሆናለህ። በፊቱ በመንበርከክ ሀይልን ትቀበላለህ የገጠመህን ተራራም የመሻገሪያ አቅም ይጨመርልሀል።
በጸሎት ልብህን ትጠብቃለህ፣ ከአባትህም ጋር ህብረትን ታደርጋለህ፣ ህይወትህ ከወንዝ ዳር እንዳለ ተክል ያብባል ድርቅ ቢመጣም እንኳ አይጠወልግም። ከራስህም አልፈህ ለብዙዎች መፍትሄ ትሆናለህ፣ መዝሙረኛው ዳዎት እንዳለው" በጠዋትም በቀትርም በማታም" ፊቱን በጸሎት አብዝተክ መፈለግ ይሁንልህ።

ስብራትህን ይዘህ
ህይወት ትእይንት ናት ብዙ ገጠመኝ የተሞላች ትእይንት መኖር ስትቀጥል የምትታዘበው ነገር ይህንኑ እውነታ ነው።
ብዙ ህመም፣ ብዙ ግራ መጋባት፣ ብዙ ትግል በዚህ መሀል የህይወት ስብራቶችም ይገጥሙሀል ለማገገም ለመፈወስም ጊዜ የሚፈልጉ፣ ቶሎ የማይሽሩ ህመሞች ሲያልፋም ጠባሳ ጥለው የሚያልፋ የህይወት ስብከቶች አሉ በእነዚህ ስብራቶች ውስጥ ሆኖ ወደፊት መሄድን ማሰብ ይከብዳል ተስፋ ይመነምናል ህይወት ትርጉም ያጣል።
ወደፊት መሄድ ለወጣት የማይቻል ተራራ ይሆናል ወደፊት ካልሄድን ወደሗላ እየሄድ ነውና ያገኘሀቸው ለውጦችን በሙሉ ማጣትህ ነው።
ስለዚህም ያለህ አማራጭ ህመምህን፣ ግራ መጋባትህንም፣ ስብራትህን ይዘህ በፊቱ በጸሎት ሁን እርሱን እሻው እየወጋ፣ እየጠዘጠዝህ ካለው ህመምህ ጋር በፊቱ ሁን እርሱ ፈዋሽህ፣ መድሀኒትህ እግዚአብሄር ነውና።

የእግር ኳስ ነገር
በአለማችን ላይ የሰውን ልብ እጅግ ከገዙ፣ ህይወቱንም እንኳ እስከመስጠት እንዲደርስ ምክንያት ከሆኑ የስፓርት ውድድሮች ሁሉ እግር ኳስ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።
በኳስ ምክንያት የተጣሉ፣ የተገዳደሉ፣ የተታረቁ፣ ድንበር ሳይበግራቸው አንድነትን ያሳዩ፣ ብዙ ሰዎች አሉ። እኔ ከሚገርመኝ የእግር ኳስ ስልቶች ውስጥ የ12ቱ ተጫዋቾች ነገር ነው። የሁሉም ድል የሚወሰነው እያንዳንዳቸው በሚያደርጉት ጥረትና ትጋት ላይ ነው ሁሉም ለቡድኑ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል አይደለም፣ የአንዱ ተጫዋች ድካም በሙሉ ቡድኑ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ቀላል አይደለም።
"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንደሚባለው የእያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ዜጋም ህይወት እንደ እግር ኳሱ ሁሉ ነው።
የእያንዳንዱ ሰው ሀላፊነቱን እንደሚገባ መወጣት ወይም ቸልተኛ መሆን በድምሩ በሀገር ላይ የሚያስከትለው የድል ወይም የኪሳራ ውጤት ቀላል አይደለም።
የአንዱ ጥንካሬ፣ ትጋት ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሀገሩ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጾ አለው።
ስለዚህም በተሰማራህበት ስፍራ በር ትተህ ስራ የአንተ ብርታ ለመላ ሀገሪቱ አስተዋጾ ቀላል ስላልሆነ።

ጠንክረህ ስራ
ህልምህን፣ ራእይህን፣ እውን ማድረግ የምትሻ፣ የምትመኝ ከሆነ ምኞትህንና ፍላጎትህን በጠንካራ የስራ ባህል ልትደግፈው ይገባሀል።
ህይወት ያለ ስራ ትርጉም የላትም። በህይወት ደስ እየተሰኘህ እንድትኖር ከሚያደርጉህ ነገሮች መሀል በላብህ፣ በድካምህ፣ ለፍተህ የምታገኘው ፍሬ ነው።
ከስራ የሚገኝ ውስጣዌ እርካታ አለ፣
ጠንክሮ መስራት በውስጥህ ልዮ የውጤታማነትን ስሜት ይፉጥርልሀል፣ ብዙ እንድታፈራም በር ይከፍትልሀል
ስራ ፈት መሆን ራስህ፣ አእምሮህን፣ ቤተሰብህን፣ ሀገርህንም በብድርና በችግር ውስጥ በማስማቀቅ ለከፋ ድህነት ከማጋረጥ ያለፈ ነገር በውስጡ አያስገኝህም።
ለብዙዎች መትረፋን የምታስብ ከሆነ ራስህን በጠንካራ የስራ ባህል አስታጥቅ። ያኔ በብዙ ፍሬ ትባረካለህ።
በምን ላይ ነው የተሰማራሕው በትምህርት? በስራ? ጠንክረህ ስራ፣ አትድከም፣ አትሰልች በመጨረሻ ሙልካሙን የድካምህን ፍሬ ታጭዳለህ።