Scripture union addis ababa
103 subscribers
607 photos
13 videos
29 files
14 links
Download Telegram
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በህይወትህ መንገድ ላይ ውጊያው ቢበዛም፣ ህመም ቢኖረውም፣ ትስፋህ ቢመነምንም፣ ግን አይዞህ እግዚአብሄር አለ በርታ፣ ህመምህን ሚረዳ አለ በርታ፣ እንባሽን የሚያይ አለ በርቺ።

ባበቃው ነገርህ ላይ ህይወትን ይዘራል፣ በጨለመብህ ነገር ላይ ብርሀንን ያበራል አይዞሽ እግዚአብሄርን ብቻ ፈልጊው እርሱን ብቻ ጥሪው በእርሱም ብቻ ታመኝ ፤ ለሁሉ ነገር መልስ ያለው እርሱው ነውና ።
በዚህ ቀን ጌታን እፈልግሀለሁ የምትልበት ቀን ይሁንልህ፣ ቀኑ ሙሉ ጌታ ሆይ እፈልግሀለሁ እያልክ ቀኑ አሳልፍ።

ያኔ ያዛለህ ነገር ከላይህ ይነሳል፣ ላጥያቄሽ መልስ ባታገኝም እንኳን ግን በርትተሽ ትውያለሽ እርሱ ከመልስሽ በላይ ነውና።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በእያንዳዱ ጥዋት ሁለት ወሳኝ ምርጫ አለህ በውስጥህ ካለው ህልም ጋር በአልጋህ ላይ መተኛት ወይም ተነስተህ ህልምህን ማሳደድ!!!

“መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በዐልጋው ላይ ይገላበጣል።”
— ምሳሌ 26፥14 (አዲሱ መ.ት)

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ህይውት የአንተን ጥንካሬ የምትፈትንበት ጊዜ ብዙ ነው። ብዙ ተስፋ አስቆራጭ፣ አድካሚ፣ አሰልቺ፣ ለምን እታገላለሁ የሚያስብል ብዙ ውጣ ውረዶች አሉአት፤ በውስጥህ ያለውን አቅም ሁሉ ሙጥጥ የሚልበትም ጊዜም ብዙ ነው።

ነገር ግን በምንም ውስጥ ብታልፍ የውስጥ ጥንካሬህን አትጣል ሲደክምህ ጊዜ ወስደህ አስብ፣ እረፍት አድርግ፣ የጀመርከውን ሩጫ ለምን እንደጀመርከው ረጋ ብለህ አስብ፣ ይህ እንደገና ጉልበት እንድታገኝ ይረዳሀል።

አዞህ በርታ ያሰብክበት ትደርሳለህ ካለምከው ከተመኘህው ህልምህ ጋር ትገናኛለህ።

ነገር ግን ይህ ፈተና አንተ ብቻ እንዳለፍክበት አታስብ ሁሉም ስኬታማ ሰው በእንደዚህ አይነት መንገድ አልፎ ነው ከህልሙ ጋር የተገናኘው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በዙሪያህ ያሉት ሰዎች ምን አይነት ናቸው። የአንተ ማንነት፣ አኗኗርህ፣ ስኬትና ውድቀት፣ ህልምህን ማግኘትህና ማጣትህ ሁሉ አጠገብህ ባሉት ሰዎች ይወሰናል።

በህይወትህ ዘመን ከህልምህ ጋር እንድትገናኝ ሊረዱህ የሚችሉ የግድ በህይወትህ ሊኖሩ የሚገባቸው ሰዎች አሉ። ደግሞ ህይወትህን መልካም መስለው ሊያበላሹ ከህልም ፈጽመው ሊያለያዮህ የሚችሉ አሉ። መልካም እውነተኛ መስለው የሚገሉህ አሉ።

ዙሪያህን በከፍታም በዝቅታም ከአንተ የማይለዮ፣ ህልምህን እንድትሻ በሚያግዙህ ሰዎች ክበብ።

ማስወገድ ያለብህን ሰዎችም ደግሞ አስወግድ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
ያንተ ስኬት በደገፈህ ወይም በተቃወመህ ሰው ብዛት አይደለም የአላማህ መሳካት አለመሳካት የሚወሰነው ባጨበጨቡልህ ሰዎች ብዛት ሳይሆን በራስህና በአላማህ ላይ ባለህ እምነት ነው። እናም ደግሞ በሰጠህው ትኩረት ይህም ሲሆን ከሌሎች ሰዎች ተፅዕኖ መውጣት ትችላለህ። አስተውል ያደነቀህ ሁሉ ነገ ያንቋሽሽህ ይሆናል ያጨበጭብልህ ነገ አንተ ላይ ጣቱን ቀስሮ ይዝትብህ ይሆናል የተከተለህ ሁሉ አብሮህ ይቀጥላል ማለት አይደለም ካንተ የተሻለ ሲያገኝ መንገድ መቀየሩ አይቀርም ስለዚህ አብረውህ ያሉት ላይ ሳይሆን አላማህ ላይ አተኩር።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ራስህን ተመልከት
ራስህን የምትመለከትበት ጊዜ ይኑርህ፤ ሰው ነህና መድከም መታከት ጉልበት ማጣት በህይወት ሊገጥምህ ስለሚችል ቆም ብለህ ራስህን መመልከቻ፣ ውሳኔህን መገምገሚያ ህይወትህን ለማሻሻል ማሰብያና ማቀጃ ጊዜ ይኑርህ።

የህይወት ጉዞ ሲታክትህ ከእለት ተግባሮችህ ራቅ በልና ተረጋግተህ አስብ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ውጫዊ ትኩረት
ዘመኑ ሰዎችን እጅግ በጣም በውጫዊ ነገሮች ላይ ብቻ ትኩረት እንድናደርግ በሚገፉ ነገሮች የሞላ ነው።
ውበት በሚለበስ ልብስ በሚደረግ ጫማ በሚቀባ ሽቶ፣ ሜክአፕ፣ በሚነዳ መኪና በሚኖርበት ቤት በምንዝናናበት ቦታ የሚመዘን ሆኗል።

ሴት ልጅ እጅግ ድንቅ የሆነ ማንነት ያላት ናት ነገር ግን ያን ማንነት ላይ በመስራት ውስጣዊ ማንነቷ ከማሳደግ ይልቅ በውጫዊው ላይ ብቻ በማተኮር የተፈጠረችበትን አላማ ሳታሳካ ታልፋለች ወንድ ልጅም እንደዚሁ ስለ ውጫዊው ሲያስብ ስብእናውን ግን ሳይገነባ ለቤተሰቡም ለሀገርም ለህዝብ ሳይሆን ያልፋል።

አለም ፈጽሞ ከተሰራሽበት አላማ ልታወጣሽ ስለምትሻ ውጫዊው ላይ ብቻ እንድታተኩሪ ታደርግሻለች ይህን ስል ግን ራስሽን ተይ ጣይ እያልኩ አይደለም።

ነገር ግን ዘላቂውና ዘላለማዊው ነገር የውስጥ ውበት ነውና በውስጥ ማንነትሽ ላይ ስሪ፣ ያንን አንቺ ነትሽን ለማሳደግ ትጊ። ለዚህ ደግሞ በየቀኑ በእግዚአብሄር ቃል እና በጸሎት መትጋት ራስሽንም በቃሉ ማስዋብ ዋናው መፍትሄ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ባልገባህና ባልተረዳኸው ነገር በቁጣ አትገንፍል። የተፈጠረውንና በዙሪያህ ያለውን ሁኔታ በትኩረት ለማጤን ለመረዳት ጊዜ ወስድህ አስተውል አስብ ገና ጠልቀህ ባላወክው ነገር ላይ ብዙ ውሳኔዎችን ከመወሰን ተቆጠብ የማትፀፀትበትን ውሳኔ ለመወሰን ተረጋግተህ አስብ።ሳታስተውል ያደረከውን አስተውሎ ለማስተካከል ጊዜ ይፈጃልና።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አውቀህሞ ሆነ ሳታውቅ ጥፋትን ታጠፋለህ እግዚአብሔርንም በዙሪያህ የሚገኙትን ስዎችንም ታስከፋለህ ታሳዝናለህም ነገር ግን ያጠፋህውን ጥፋት የሰራህውን ሀጢያት ዳግመኛ ላለመድገም ለሌሎችን ስዎች መንገር ምን ይሉኛል ያውቁብኛል ብለህ አትሳቀቅ በግልጽ የደከምክበትን ነገር ነገራቸው በህብረት እንድትፀልዪበት እርስበርሳቹ ድካማችሁን ተነጋገሩ ያንዳችሁ ውድቀት ሌላው መማሪያ ይሆናል።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አንዳንድ ጊዜ ለኔ ሊከፍሉትየሚገባ እዳ አለባቸው ያረኩላቸውን መርሳት የለባቸውም ብለህ የምታስባቸው ብዙ ሰዎችን መጥቀስ ትችላለህ አንተ ለሰዎች አደርጊያለው ብለህ የምታስበው ውለታ ብቻ ሳይሆን እነሱ ላንተ ያደረጉልለህን ታስታውሳለህ ወይ? የከፈሉልህን ዋጋ እሱን አስብ። ላደረጉልህ አመስጋኝ ሁን አላደረጉልኝም ለምትላቸው ግን አላረጉልኝም ብለህ አንተ መልካም ማድረግህን አታቋርጥ።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በእያንዳድዱ በምታልፍባችውሁኔታውስጥ አንዱን ለማንሳት አልያም ለመያዝ ሌላውን መልቀቅ የግድ ይልሀል የሚያስፈልግህን ያዝ የማያስፈልግህን ልቀቅ። መልቀቅ የነበረብህን ይዘህ ስታስቆየው ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል በጊዜው የምትፈልገውን ሁሉ ሳይሆን በሰአቱ የሚያስፈልግህን ብቻ ያዝ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus

መልካም ቀን
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በትላንትና ውድቀት፣ አለመሳካት፣ ግራ መጋባት ከመያዝ ለመውጣት ከርችሞ ከያዘህ አመለካከት፣ አስተሳሰብ፣ አኗኗር፣ ጓደኝነት ጥሎ መሄድ አስፈላጊ ነው።

ይህን ጥሎ የመሄድ ጥበብ ያልተለማመደ ሰው ህይወቱን እንደሚገባ ሳይኖር የትላንት እስረኛ እንደሆነ ያልፋል።

ስለዚህም ወደፊት ለመሄድ ካሰረህ የፍቅር፣ የጓደኝነት ግንኙነት ራስህን አፋተህ ፤ ጥለህ መሄድ ይኖርብሀል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ህልምህ ላይ አተኩር
የህይወትህ ማንቀሳቀሻ ከሆኑ ነገሮች መሀል የያዝከው ህልም አንዱ ነው። ህይወትህ ትርጉም ሚኖረው፣ ነገን ተስፋ የምታደርገው፣ ደስተኛም የምትሆነው ለያዝከው ህልም ስትኖር ነው።

ህልምህ ምንድን ነው፣ የምትኖርለትስ ነገር አለህ? እግዚአብሄር አምላክ በአላማ ነው የፈጠረህ በስተመጨረሻ በህይወትህ ማብቂያ ምን ሰራሁ በማለት ከመጨነቅ ከመቆጨት፣ ከመተከዝ ራስህን በቅድሚያ የምትኖርለት ህልም ስጠው።

ህልምህን ለማወቅ በቅድሚያ ራስህን እውቅ ምትወደውን፣ ምትጠላውን፣ ደስ የሚያሰኝህን ለይተህ እወቅ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አስተውለህ ምረጥ

ህይወት ምርጫ ናት ስትኖር መምረጥ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ይሆናል። ስለዚህም አስተውለህ መምረጥ የአንተ ትልቁ ድርሻና ሀላፊነት ነው።

ሳታስተዉል የምታደርገው ምርጫ ብዙ መዘዝ ይዞ ይመጣብሀልና በአስተውሎ መምረጥ ሀላፊነትህ ብቻ ሳይሆን ግዴታህም ጭምር ነው።

የአንተ ምርጫ አንተ ብቻ ሳይሆን በዙሪያህ ያሉትንም ስለሚነካ ጥንቃቄ ያሻዋል።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ለካ ለውጥ ከራስ ነው
ከመምከርህ፣ ከማስተማርህ፣ ጣት ከመቀሳሰርህ በፊት ውስጥህን በሚገባ መፈተሽ፣ እኔ እንዴት ነኝ? ኑሮዬ? አወጣጥ፣ አገባቤ፣ ከስው ጋርስ እንዴት ነኝ? ብለህ ራስህን በሚገባ መርምር። መጽሀፍ ቅዱስ ሁሌም ወደ ውስጥ እንድንመለከት ውስጣችን ላይ እንድንሰራ ይመክረናል።

"ማቴዎስ 7 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ “በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ ሳትመለከት፣ በወንድምህ ዐይን ያለውን ጕድፍ ለምን ታያለህ?
⁴ በዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ ወንድምህን፣ ‘ዐይንህ ውስጥ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ’ ማለት እንዴት ትችላለህ?
⁵ አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።"

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ሰውን ችግር ሲገጥማችሁ ህይወት ሲከብዳችሁ መፍትሄ እንዲሰጣችሁ እንዲያማክራችሁ በችግራችሁ ሰአት በዙሪያችሁ ሰው እንዲኖር ትፈልጉ ይሆናል ግን እንደዛ አይደለም ሰው ቢመጣ አይዞአችሁ ብሎ ይሄዳል። አንዱ ሲመጣ ሌላው ይተካ ይሆናል። ግን አስታውስ መቼም እንዳትረሳ ስታዝን አብሮህ የሚያዝን ሁሌም አጠገብህ ያለ የሚያጽናና፣ ስትደሰት አብሮህ የሚደሰት ስታጠፍ የሚታዘብ ብቻ ሳይሆን የሚገስጽህ አጽናኝና አበርቺ መንፈስ ቅዱስ እንዳለህ አትርሳ።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
🎄🎄🎄ገና ለኔ🎄🎄🎄
ሁለተኛ እድል! ሌላ አይደለም እንደገና የመኖር፣ እንደገና ተስፋ የማድረጊያ፣ የተበላሸውን የማስተካከያ፣ የጠለሸውን የማጽጃ፣ የተሰበረውን መጠገኛ፣ ተስፋው፣ ህይወቱ በቀጭን ገመድ ላይ ለተንጠለጠለው የረዳት እጅ መዘርጊያ፣ ያበቃለትን እንደ ገና ማስቀጠያ፣ ተስፋ በመቁረጥ በጨለማ ለተቀመጡ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ የብርሀን ወጋገን። በተስፋ እጦት፣ በሀጥያት እስራት፣ ለመውጣት አዳጋች በሆነ እስር ቤት፣ ለተከረቸሙ እንደገና መፈታት፣ እንደገና ነጻ መውጣት ለእኔ ገና ይህ ነው።
ሀለተኛ እድል!
እንደገና!
እንደ አዲስ!


🙏ክብር ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን አሜን! 🙏

መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ

🎄🎄🎄መልካም በአል🎄🎄🎄
🎄🎄🎄ሳሙኤል ከበደ🎄🎄🎄

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Have Yourself A Merry Little Christmas (Deluxe Ed
Lauren Daigle
🎤🎤🎤Lauren daigle 🎤🎤🎤

🎄🎄Merry Christmas 🎄🎄

Youthfocus music

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ከትላንት ምን ተማርክ?

ህይወት በክፍል ውስጥ ተቀምጦ እንደ መማር ነው። በየእለቱ የምናልፍበት አዲስ የሆነ ልምምድ ብዙ ያስተምረናል በዚህ ልምድ ውስጥ ስናልፍ ስህተት ልንሰራ፣ ጥፋት ልናጠፍ እንችላለን ነገር ግን ከዛ በሓላ ያን ስህተት መድገም ተምሮ እንዳልተማረ አውቆ እንዳላወቀ መሆን ነው።

ከትላንት አለመማር፣ ከባለፈው ውድቀቴ ቀለምን አለመቅሰም፣ ለነገ የሚሆን እውቀትን አለመጨበጥ ደግሞ ደጋግሞ ያንኑ ስህተት መስራት ላለመለወጥ መፈለግን ያሳያል ለዚህም ይመስላል "ታሪክ ራሱን ይደግማል" የሚባለው።

ከትላንት መማር ጥበብ ነው ከስህተታችን፣ ከታሪክ መማር ተመሳሳይ ስህተት እየሰሩ ከመኖር ያስመልጠናል።
ትላንት የያደረግካቸውን ስህተቶች ያመጡብህን መዘዝ አስተውለህ ከትላንት ስህተት ለዛሬ የሚሆን ስንቅ ያዝ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ለነገ ቀጠሮ አትስጥ

ትላንት ታሪክ ነው፣ ነገ ሚስጥር፣ ዛሬ ደግሞ ስጦታ ነው። ባደጉት ሀገራት፣ ባላደጉት ሀገራት፣ ውጤታማ በሆኑት ሰዎችና በስንፍና ሙቀት ተደላድለው በአልጋ ላይ ባሉት የደረጃ ተማሪ በሆኑትና ኩረጃን ብቸኛ ተስፋ ባደረጉት መካከል ያለው ልዩነት የትጋት ጉዳይ ነው ታታሪ ተግቶ ሀገሩን፣ ህዝቡን፣ ትውልዱን፣ ሲቀይር ሰነፍ ደግሞ በምቾት ሙቀት ምኞትን ሲያልም ያድራል ።

የሰነፍ ትልቁ ተግባሩ ስራንና ሀላፊነትን ለነገ ማስቀመጥ ነው። የዛሬን ለዛሬ ካልሰራን ነገ ደግሞ የራሱ የራሱ የሆነ ስራ ይዞ ይመጣል በአንዱ ላይ አንዱ ሲደራረብ የቱንም ሳንሰራ ዘመናችን ያልፋል። ለነገ ቀጠሮ አትስጥ ዛሬ ስጦታ ነውና የምትችለውን ሀሉ አድርግ

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ታሪክ እንደ ወንዝ
ጠቢብ በህይወት ዘመኑ ሊሰራ ያሰበው፣ ለትውልድ ጥሎ ለመሄድ ያቀደው ነገር፣ ከእለታቱ በአንዱ ቀን እንደሚሆን አይጠብቅም፤ ነገር ግን ሰው ታሪክ በተባለ ወንዝ ውስጥ በአንዱ ወቅት ገብቶ የሚዋኝ ከዛም ደግሞ መዳረሻው ሲደርስ እንደሚወርድ የሚገነዘብ ነው።

ይህንንም ተገንዝቦ በውሀ ውስጥ የሚኖረው ቆይታ ሳያበቃ ስራውን ቶሎ ቶሎ የሚሰራ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus