Scripture union addis ababa
103 subscribers
607 photos
13 videos
29 files
14 links
Download Telegram
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ባለህ ተደሰት
ህይወትህ ዝም ብሎ ሩጫ፣ ባለህ ሳትደሰትና ሳታጣጥም እንዲሁ የምታሳልፈው እንዳይሆን እያንዳንዱን ቀን በምስጋና ኑር የሌለህን ለማግኘት ስትሮጥ በእጅህ ስላለው ሳታመሰግን ባለህ ሳትደሰት የምድር ኑሮህን የቆጡን አወርድ አይነት ህይወት እንዳይሆን አስተውል።

አምላክህን ስለሰጠህ ነገሮች በሙሉ አብዝተህ አመስግን ስለሰጠህ ብሩህና ግሩም ህይወት።

“ማጣትን ዐውቀዋለሁ፤ ማግኘትንም ዐውቀዋለሁ። ብጠግብም ሆነ ብራብም፣ ባገኝም ሆነ ባጣ በማንኛውም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ ያለኝ ይበቃኛል የማለትን ምስጢር ተምሬአለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥12 (አዲሱ መ.ት)

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ቃልህ የከበረ ሀብት ነው።
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (rahel)
#መሄድ አናቁም

አንድ ቀን አንድ ልጅ አንድ ፊኛ ወደላይ ሲወጣ ያይ እና አባቱን አባቴ ይህን ፊኛ ወደላይ እንዲወጣ የሚያደረገው ነገር ምንድንነው ብሎ ይጠይቀዋል ?

አባትየውም ገመድ ነው ልጅዬ ልጅ ይለዋል ። ግን ልጁ እንዴት አባቴ ? እንደውም ከዚህ በላይ ከፍ እንዳይ እንቅፋት እየሆነበት ነው አለው ።

አባትየውም ለምን አላሳየውም ብሎ ገመድን ፈታ እና ፊኛውን ለቀቀው ከዛም ትንሽ ከፍ አለ እና ተመልሶ ወደቀ።
ከዛም ልጁ አባቱን ጠየቀ እንዴት? አባትም አለው ልጄ የፊኛው ከፍ የማለት ሚስጥር የገመድ ወደታች መጎት ነው አለው ።

እኛም በአሁኑ ጊዜ የሚጎትቱን ነገሮች እንድንሄድ ያረጎናል ። ለችግሮቻችን እጅ አንስጥ ። ችግሮቻችንም ለምን መጡ አንበል ምክንያቱም የመሄዳችን ማሳያዎች ስለሆኑ።

አንድ ሰው ካልሄደ እንቅፋት አይመታውም ። እንቅፋቶቻችን እንደምንሄድ ማሳያዎች ናቸው። ምክንያቱም ቁጭ ያለሰው እንዴት እንቅፋት ይመታዋል አይመታውም ።

ስለዚህ የትኛውም አስቸጋሪ ሁኖታ አንጥላው። እንደውም እንዴት እንደምናልፈው እናስብ እንጂ ።


Join and share
👇👇👇👇👇
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
☝️☝️☝️☝️
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ፈጣሪ ከስፍራክ ከምቾትህ ከተደላደልክበት ነገር ሲያወጣህ፣ በቃ አለቀልኝ በምትልበት መንገድ ሲያሳልፍህ፤ አትታክት የነበረህን ስታጣ የተማርከውን አስብ። ያለውን ለውጥ አስተውል። ሁሌም ከላይ ያለው ሲወድቅ ከስር ያለው ዘላለሙን ያገኛል።

አስተውል የተጠራህው የክርስቶስ ህይወት እንዲገለጥልህ ብቻ ሳይሆን፤ ክርስቶስ ባንተ እንዲገለጥም ጭምር ነው።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
Shoot for the moon, even if you miss, you will land among the stars.

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
እይታ
ሰው ከሰው ጋር ላለው አለመስማማትና ግጭት ትልቁ መንስኤ በነገሮች ላይ ያለን አተያይና አመለካከት ነው።

ካለን የተለያየ እይታ የተነሳ አንዱ "ይህ እንደዚህ ነው ሲል ሌላው ደግሞ "አይ እንዲህ ነው ይላል" በዚህም አለመግባባት ይፈጠርን ወደ ከረረ ጥል ሊያመራ ይችላል።

አንተ እንዳየሓው ሌላው አያየውምና ከሰው ጋር በሚኖርህ አለመግባባት ቶሎ ወደ ቁጣና ብስጭት ጥልም አትግባ ይልቅስ ያሰው እንዳየው ለመመልከት ሞክር ያኔ ግጭት ሳይሆን ልዩ የሆነ አዲስ እይታን ታገኛለህ

እይታችን የተለያየ መሆኑን መረዳትና በመነጋገር ነገሮችን ለመፍታት መጣር ትክክለኛው መፍትሄ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በልብህ ይኑር
ወጣትነት እጅግ ጥሩም ከባድም ጊዜ የምናሳልፍበት ጊዜ ነው። ለብዙ ነገሮች የምንጋለጥበት፣ ራሳችንንም ትክክል ባልሆነ ምርጫ ውስጥ የምናገኝበት ጊዜ ነው።
ታዲያ ይህን ከባድ ዘመን እንዴት ነው የምናልፈው? ትክክለኛውንስ ምርጫ የምንመርጠው እንዴት ነው?

የእግዚአብሄር ቃል በልብህ ይኑር ያን ጊዜ እርሱ በመንገድህ ሁሉ ይመራሀል፣ ሕይወትህንም ያለ ግራ መጋባት ትኖራለህ፣ በምርጫህም ደስተኛ ሆነህ ትኖራለህ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
Do your best to present yourself to God as one approved, a worker who does not need to be ashamed and who correctly handles the word of truth. (2nd Timothy 2:15)

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ለውጥ (change)!!!

ለውጥ ከማይቀር የህይወት እውነታዎች መካከል አንዱ ነው። ዛሬ ከትላንት አስተዋልነውም አላስተዋልነውም በትልቅ የለውጥ ሂደት ውስጥ እያለፈ ነገሮችም እየተቀየሩ ከትላንት በተለየ አቋምና ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው።

ሰው ግን በተፈጥሮ ለውጥን በቀላሉ መቀበል ይከብደዋል፤ ጊዜ ካመጣው የተለየ አኗኗር፣ አመለካከት፣ የህይወት ዘይቤ ጋር ቶሎ መስማማት ይከብደዋል።

ከሀይስኩል ፕሪፓራቶሪ መግባት ለውጥ ነው፣ 12 ተፈትኖ ግቢ መግባት፣ ግቢ ጨርሶ ስራ መያዝ፣ ከብቸኝነት ህይወት ወጥቶ ማግባት ለውጥ ነው( ይህን ለውጥ ብዙዎች ይፈሩታል ምክንያቱም ከትላንት ነጻነት መለየት ስለማይፈልጉ ነገር ግን ያልተገነዘቡት አንድ ነገር ቢኖር ያለውጥ ይዞላቸው የመጣውን እድል ነው።) ትልቁ ጥበብ ግን ከነዚህ ለውጦች ጋር ራስን እያስማሙ መራመድ ትክክለኛው የመጣውን ለውጥ እድል ለመጠቀም ሁነኛ መፍትሄ ነው።

ካለበለዚያ በትላንት ነገር ተይዘን ዛሬ ያመጣልንን እድል ሳንጠቀምበት ህይወታችንም ኑሮአችን ሳይቀየር፣ ትውልዳችን ላይም ለውጥ ሳናመጣ እናልፋለን።

ስለዚህም በየቀኑ አንድን ነገር ተገንዘብ ህይወት ያለ ለውጥ አይታሰብም ስለዚህም ራስህን ከነዚህ ለውጦች ጋር ቶሎ አስማምተህ ተራመድ።

ለውጥን መፍራት አንዱ ከትላንት ጋር ያለመለያየት ምልክት ነውና የለውጥ ፍርሀትን ከህይወትህ አስወግድ፤ በዙሪያህ ለውጥ ያመጣልህ እድል እንዳያመልጥህ ተጠቀምበት።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በምንም አይነት ነገር ውስጥ ብታልፍ ምንም ችግር ሞክረህ ባይሳካልህ፣ ወጥነህ ባይሆንልህ፣ በዛሬ አለመሳካት በዛሬ ጭጋጋማ ቀን፤ በነገ ላይ ግን ተስፋ አትቁረጥ።

ደጋግመህ ሞክር! አሸናፊነት የሚገኘው በአንዴ ሙከራ ውስጥ ሳይሆን ደጋግሞ በመሞከር ውስጥ ነው። ለዚህም ቶማስ ኤድስን፣ ራይት ብራዘርስ...... ምስክሮች ናቸው።

ስለህይወት ያለህን አመለካከትም ከጨለምተኝነት ወደ ተስፈኝነት ቀይር ከአንተ በባሰ ነገር ውስጥ ሆነው በማመስገንና በአምላካቸው በመታመን የአሸናፊነት ህይወት የሚኖሩ ብዙ ናቸውና።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በህይወትህ መንገድ ላይ ውጊያው ቢበዛም፣ ህመም ቢኖረውም፣ ትስፋህ ቢመነምንም፣ ግን አይዞህ እግዚአብሄር አለ በርታ፣ ህመምህን ሚረዳ አለ በርታ፣ እንባሽን የሚያይ አለ በርቺ።

ባበቃው ነገርህ ላይ ህይወትን ይዘራል፣ በጨለመብህ ነገር ላይ ብርሀንን ያበራል አይዞሽ እግዚአብሄርን ብቻ ፈልጊው እርሱን ብቻ ጥሪው በእርሱም ብቻ ታመኝ ፤ ለሁሉ ነገር መልስ ያለው እርሱው ነውና ።
በዚህ ቀን ጌታን እፈልግሀለሁ የምትልበት ቀን ይሁንልህ፣ ቀኑ ሙሉ ጌታ ሆይ እፈልግሀለሁ እያልክ ቀኑ አሳልፍ።

ያኔ ያዛለህ ነገር ከላይህ ይነሳል፣ ላጥያቄሽ መልስ ባታገኝም እንኳን ግን በርትተሽ ትውያለሽ እርሱ ከመልስሽ በላይ ነውና።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በእያንዳዱ ጥዋት ሁለት ወሳኝ ምርጫ አለህ በውስጥህ ካለው ህልም ጋር በአልጋህ ላይ መተኛት ወይም ተነስተህ ህልምህን ማሳደድ!!!

“መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በዐልጋው ላይ ይገላበጣል።”
— ምሳሌ 26፥14 (አዲሱ መ.ት)

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ህይውት የአንተን ጥንካሬ የምትፈትንበት ጊዜ ብዙ ነው። ብዙ ተስፋ አስቆራጭ፣ አድካሚ፣ አሰልቺ፣ ለምን እታገላለሁ የሚያስብል ብዙ ውጣ ውረዶች አሉአት፤ በውስጥህ ያለውን አቅም ሁሉ ሙጥጥ የሚልበትም ጊዜም ብዙ ነው።

ነገር ግን በምንም ውስጥ ብታልፍ የውስጥ ጥንካሬህን አትጣል ሲደክምህ ጊዜ ወስደህ አስብ፣ እረፍት አድርግ፣ የጀመርከውን ሩጫ ለምን እንደጀመርከው ረጋ ብለህ አስብ፣ ይህ እንደገና ጉልበት እንድታገኝ ይረዳሀል።

አዞህ በርታ ያሰብክበት ትደርሳለህ ካለምከው ከተመኘህው ህልምህ ጋር ትገናኛለህ።

ነገር ግን ይህ ፈተና አንተ ብቻ እንዳለፍክበት አታስብ ሁሉም ስኬታማ ሰው በእንደዚህ አይነት መንገድ አልፎ ነው ከህልሙ ጋር የተገናኘው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በዙሪያህ ያሉት ሰዎች ምን አይነት ናቸው። የአንተ ማንነት፣ አኗኗርህ፣ ስኬትና ውድቀት፣ ህልምህን ማግኘትህና ማጣትህ ሁሉ አጠገብህ ባሉት ሰዎች ይወሰናል።

በህይወትህ ዘመን ከህልምህ ጋር እንድትገናኝ ሊረዱህ የሚችሉ የግድ በህይወትህ ሊኖሩ የሚገባቸው ሰዎች አሉ። ደግሞ ህይወትህን መልካም መስለው ሊያበላሹ ከህልም ፈጽመው ሊያለያዮህ የሚችሉ አሉ። መልካም እውነተኛ መስለው የሚገሉህ አሉ።

ዙሪያህን በከፍታም በዝቅታም ከአንተ የማይለዮ፣ ህልምህን እንድትሻ በሚያግዙህ ሰዎች ክበብ።

ማስወገድ ያለብህን ሰዎችም ደግሞ አስወግድ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
ያንተ ስኬት በደገፈህ ወይም በተቃወመህ ሰው ብዛት አይደለም የአላማህ መሳካት አለመሳካት የሚወሰነው ባጨበጨቡልህ ሰዎች ብዛት ሳይሆን በራስህና በአላማህ ላይ ባለህ እምነት ነው። እናም ደግሞ በሰጠህው ትኩረት ይህም ሲሆን ከሌሎች ሰዎች ተፅዕኖ መውጣት ትችላለህ። አስተውል ያደነቀህ ሁሉ ነገ ያንቋሽሽህ ይሆናል ያጨበጭብልህ ነገ አንተ ላይ ጣቱን ቀስሮ ይዝትብህ ይሆናል የተከተለህ ሁሉ አብሮህ ይቀጥላል ማለት አይደለም ካንተ የተሻለ ሲያገኝ መንገድ መቀየሩ አይቀርም ስለዚህ አብረውህ ያሉት ላይ ሳይሆን አላማህ ላይ አተኩር።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ራስህን ተመልከት
ራስህን የምትመለከትበት ጊዜ ይኑርህ፤ ሰው ነህና መድከም መታከት ጉልበት ማጣት በህይወት ሊገጥምህ ስለሚችል ቆም ብለህ ራስህን መመልከቻ፣ ውሳኔህን መገምገሚያ ህይወትህን ለማሻሻል ማሰብያና ማቀጃ ጊዜ ይኑርህ።

የህይወት ጉዞ ሲታክትህ ከእለት ተግባሮችህ ራቅ በልና ተረጋግተህ አስብ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ውጫዊ ትኩረት
ዘመኑ ሰዎችን እጅግ በጣም በውጫዊ ነገሮች ላይ ብቻ ትኩረት እንድናደርግ በሚገፉ ነገሮች የሞላ ነው።
ውበት በሚለበስ ልብስ በሚደረግ ጫማ በሚቀባ ሽቶ፣ ሜክአፕ፣ በሚነዳ መኪና በሚኖርበት ቤት በምንዝናናበት ቦታ የሚመዘን ሆኗል።

ሴት ልጅ እጅግ ድንቅ የሆነ ማንነት ያላት ናት ነገር ግን ያን ማንነት ላይ በመስራት ውስጣዊ ማንነቷ ከማሳደግ ይልቅ በውጫዊው ላይ ብቻ በማተኮር የተፈጠረችበትን አላማ ሳታሳካ ታልፋለች ወንድ ልጅም እንደዚሁ ስለ ውጫዊው ሲያስብ ስብእናውን ግን ሳይገነባ ለቤተሰቡም ለሀገርም ለህዝብ ሳይሆን ያልፋል።

አለም ፈጽሞ ከተሰራሽበት አላማ ልታወጣሽ ስለምትሻ ውጫዊው ላይ ብቻ እንድታተኩሪ ታደርግሻለች ይህን ስል ግን ራስሽን ተይ ጣይ እያልኩ አይደለም።

ነገር ግን ዘላቂውና ዘላለማዊው ነገር የውስጥ ውበት ነውና በውስጥ ማንነትሽ ላይ ስሪ፣ ያንን አንቺ ነትሽን ለማሳደግ ትጊ። ለዚህ ደግሞ በየቀኑ በእግዚአብሄር ቃል እና በጸሎት መትጋት ራስሽንም በቃሉ ማስዋብ ዋናው መፍትሄ ነው።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
ባልገባህና ባልተረዳኸው ነገር በቁጣ አትገንፍል። የተፈጠረውንና በዙሪያህ ያለውን ሁኔታ በትኩረት ለማጤን ለመረዳት ጊዜ ወስድህ አስተውል አስብ ገና ጠልቀህ ባላወክው ነገር ላይ ብዙ ውሳኔዎችን ከመወሰን ተቆጠብ የማትፀፀትበትን ውሳኔ ለመወሰን ተረጋግተህ አስብ።ሳታስተውል ያደረከውን አስተውሎ ለማስተካከል ጊዜ ይፈጃልና።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አውቀህሞ ሆነ ሳታውቅ ጥፋትን ታጠፋለህ እግዚአብሔርንም በዙሪያህ የሚገኙትን ስዎችንም ታስከፋለህ ታሳዝናለህም ነገር ግን ያጠፋህውን ጥፋት የሰራህውን ሀጢያት ዳግመኛ ላለመድገም ለሌሎችን ስዎች መንገር ምን ይሉኛል ያውቁብኛል ብለህ አትሳቀቅ በግልጽ የደከምክበትን ነገር ነገራቸው በህብረት እንድትፀልዪበት እርስበርሳቹ ድካማችሁን ተነጋገሩ ያንዳችሁ ውድቀት ሌላው መማሪያ ይሆናል።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
አንዳንድ ጊዜ ለኔ ሊከፍሉትየሚገባ እዳ አለባቸው ያረኩላቸውን መርሳት የለባቸውም ብለህ የምታስባቸው ብዙ ሰዎችን መጥቀስ ትችላለህ አንተ ለሰዎች አደርጊያለው ብለህ የምታስበው ውለታ ብቻ ሳይሆን እነሱ ላንተ ያደረጉልለህን ታስታውሳለህ ወይ? የከፈሉልህን ዋጋ እሱን አስብ። ላደረጉልህ አመስጋኝ ሁን አላደረጉልኝም ለምትላቸው ግን አላረጉልኝም ብለህ አንተ መልካም ማድረግህን አታቋርጥ።

መልካም ቀን
ራሄል ካሳሁን
@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus
Forwarded from Youth focus (Sam Kb)
በእያንዳድዱ በምታልፍባችውሁኔታውስጥ አንዱን ለማንሳት አልያም ለመያዝ ሌላውን መልቀቅ የግድ ይልሀል የሚያስፈልግህን ያዝ የማያስፈልግህን ልቀቅ። መልቀቅ የነበረብህን ይዘህ ስታስቆየው ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል በጊዜው የምትፈልገውን ሁሉ ሳይሆን በሰአቱ የሚያስፈልግህን ብቻ ያዝ።

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus

መልካም ቀን