መጸሃፍስ ምን ይላል?
1.18K subscribers
1 file
በዚህ ቻናል የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጸሃፍትን እናጠናለን።
Download Telegram
መልእክተ ይሁዳ ጥናታችን ልንጀምር ነው ተዘጋጃችሁ? 😁
🔥62❤17⚡3💯2☃1👍1
Audio
በይሁዳ መልእክት ውስጥ የሃሰት አስተማሪዎች የሚታወቁባቸው14 መሰረታዊ መለኪያዎቻቸውና የተፈጥሮ ባህሪዎቻቸው….

1 ፍርዳቸው አስቀድሞ የተጻፈ ነው።
2 ከመጀመሪያውም እውነተኛ አማኞች ያልሆኑ፣ የእግዚአብሄር መንፈስ የሌላቸው በእውነተኛ አማኞች ማህበር ውስጥ ሾልከው የገቡ የክርስቶስ ጠላቶች ናቸው።
3 ሲናገሩ እውነተኛ ክርስቲያን ቢመስሉም በተግባራቸው ግን ከሃዲያዊያን የሆኑ አፋዊ ክርስቲያን ናቸው።
4 ከእግዚአብሄር ዘንድ የተገለጠውን እውነተኛውን ሃይማኖት ለራሳቸው ምኞት እንዲሆን አድርገው የሚለውጡ ለዋጮች ናቸው።
5 እግዚአብሄር የመሰረተውን stable የሆነውን ተቋም disorder የሚያደርጉ ናቸው።
6 በእግዚአብሄርና የእግዚአብሄር በሆኑ ነገሮች ላይ ሲናገሩ ደፋሮችና እቡያን ናቸው።
7 በተፈጥሮ እውቀት ብቻ የሚመላለሱ rationality የጎደላቸው ደመ ነፍሳዊ ፍጥረታት ናቸው።
8 በእግዚአብሄር ህብረት ውስጥ መከፋፈልን የሚፈጥሩ የገዛ ምኞታቸውን pursue የሚያደርጉ የቆሬ ልጆች ናቸው።
9 ከላይ ሲታዩ ያለነቀፋ እንደሆኑ የሚመስሉ ነገር ግን የእግዚአብሄር ማህበር የሆነችውን መርከብ የሚገለብጡ የተሰወሩ አለቶች ናቸው።
10 ገንዘብን የሚወዱ፣ ለስማቸው የሚጨነቁ፣ በእግዚአብሄር ላይ የሚያንጎራጉሩ ናቸው።
11 የተናገሩት ሆነ የሚያደርጉት ሁሉ ፍሬ የሌለው ባዶ ተስፋ ያዘሉ ናቸው።
12 በእግዚአብሄር መገለጥ ሳይሆን በራሳቸው ህልምና ቅዠት የሚመሩ ናቸው።
13 ይበቃኛል ማለትን የማያውቁ የማይረኩ ገደብ የለሽ ተንከራታች ፍጥረታት ናቸው።
14 የራሳቸውን ጥቅም ለማግኘት ሲሉ በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ አድሎ favoritism የሚያደርጉ ናቸው።
@scriptural_chronicles
❤16👍1🥰1