ዋልድባን እንታደግ - Save Waldba
169 subscribers
133 photos
17 videos
4 files
151 links
ዋልድባን እንታደግ ከ2004 ዓም ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሥኳር ፋብሪካን ለመገንባት ቅዱሱን ገዳም አፍርሰው ስኳር ለማምረት መሞከራቸው በዓለም ዙሪያ በርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች ተቃውሟቸውን በማሰማት ለኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በማሳወቅ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ዋልድባ ገዳምን ለመታደግ የተቋቋመ ማኅበር ነው፡፡
Download Telegram
👉👉👉የአቦምሳ አስተዳደርና ካብኔው አሳፋሪ ተግባር ከተለያዩ ቀበሌ እና ወረዳ ነፍሳቸውን ሊያዱን የመጡ ኦርቶዶክሳዊያንን ከተማችንን አጣበባችሁብን በአፋጣኝ ለቃችሁ ውጡልን ብለው ውሳኒያቸውን አሳወቁ ~
👉ወገን ይሄ ሕዝብ ወዴት ይሂድ ???
*********
በምሥራቅ አርሲ ጉና ወረዳ ረኤ አርባ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጦሴ በሚባል ቦታ በ24/10/2018 ዓ.ም ለ25/10/2018 ዓ.ም ሁለት ኦርቶዶክሳውያን የተገ*ደሉ ሲሆን አንዱ መ/ር በጥይት ተመ*ቶ አምልጦ ሆስፒታል ገብቷል ሦስት( 3) ኦርቶዶክሳውያን ታግተው ተወስደዋል።
1).ሟች መ/ር ተስፋዬ ተሾመ አጋ እድሜ 42
2). ሟች ሚሚ ግርማ እድሜ 24 እና ባለሁለት ልጆች እናት

በጥ*ይት ተመቶ ሆስፒታል የገባው መምህር ብርሃኑ ለማ ይባላል የ52ዓመት እድሜ

የቀበሌ አመራሮች አሁንም ቢሆን ሕዝቡ ሸሽቶ እንዳያመልጥ እየከለከሉት ነው።
ሌላ ቦታም በምሥራቅ አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ ፈረንቀሳ ጃዊ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሳጉሬ ቀርሳ የሚባል አከባቢ 24/10/2018 ዓ.ም ለ 25/10/2018ዓ.ም አጥቢያ አቶ አባይ ታደሰ የሚባል ኦርቶዶክሳዊ በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች ተ*ገድ*ሏል። ታጣቂዎቹ የቀሲስ ደምሰው ሰለሞንን ሴት ልጃቸው ምሕረት ደምሰውን ፣ግርማ ገረሱ እና ሀና ገዛኸኝ የምትባል እናት ያለ አባት ያሳደገቸው የ12 ዓመት ወንድ ልጇን አግተው ወስደውባታል፣እንዲሁም አቶ ካሣሁን ጃንካ የሚባል ሰው ኩብቶቹን በሙሉ ወስደውበታል

በዚህ ወረዳ ሞለሜ ቀበሌ ከሦስት ቀን በፊት አንድ ኦርቶዶክሳዊ በአሰቃቂ ሁኔታ መ*ገደ*ሉ*ንና በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት መኖሩን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል
እንደዚህ ዓይነት ጥቃት እየተፈጸመ ባለበት ሁኔታ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ከሊል ገናና እና ከቢኔዎቻቸው በአቦምሳ ከተማ ተጠልለው ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን ከተማችንን እያጣበባችሁብን ነውና ወደ መጣችሁበት ተመለሱ እያሉ በማስገደድ ላይ ናቸው።
ሁላችሁም #ሼር #ላይክ በማድረግ ድምጽ እንሁናቸው ድምጽ የሚሰማ አካል ካለ
◈ለተጨማሪ መረጃ
🀄️🀄️👇
https://t.me/Orthotewa7