6: "እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል : በደላችንን ይቅር በለን"
ጌታ ሆይ እንበድላለን:: ይህም እውን ስለሆነ መፍትሄውን ሰጥተኸናል:: አንተን ከነገሮች በላይ ማስቀደም አቅቶን እንበድልሃለን:: እንደ አምላክነትህ የሚገባህን ስፍራ ሳንሰጥህ:- በቃልህ (ዘዳ 6:4-6) እንዳዘዝከው አምላካችን ልትሆን የሚገባህ ብቻህን መሆን ሲገባ... ሳናስተውል አምላክ የሆኑብን ብዙ መሰጠትና ፍቅራችንን የሚሻሙን ጣኦቶች ሞልተውናል:: ላንተ ያለንን ፍፁምና እውነተኛ የሆነውን ፍቅር የምንገልጥበት አምልኮና መታዘዛችንም ይጏደላል:: "ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ" ወይም "ብትወዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ" ብለሃል: አቤቱ ፈቃስህን በሚቃወመው የየለት ሃሳብና ድርጊት የበደልነውን ይቅር በለን::
ጌታ ሆይ ከአንተ የምንሻውና ያገኘነውን ለሰዎች እንድንሰጥ ግዴታ ነው:: ሰዎችን በሚገባው መንገድ እውነት በሆነው መንገድ አንተ ባሳየኸን መንገድ መውደድ ስለሚሳነን ይቅር በለን:: "ፍቅራችን በጥልቅ እውቀትና በማስተዋል በዝቶ እንዲትረፈረፍ ስላልቻለ " ምህረት ያሻናል:: ከአንደበት በዘለለ በእውነትና በትግባር መዋደድ ባቃተን ይቅርበለን::
ከሁሉ በላቀ እኛ ያገኘነውን ይቅርታ ሌሎች እኛን በጥቂቱ የበደሉንን ይቅር ማለት ተስኖናል:: እባክህ ዛሬ ይቅር እንድትለን : ዛሬ ይቅር እንድንል አድርገን!
እውነተኛ ንስሃ ምንድን ነው? ይቀጥላል...
Share, join or invite 🙏👉🏿@samitadele

"በደላችንን ይቅር በለን" የቀጠለ...
እውነተኛ ንሰሃ (መዝ 51 ዓ.መ.ት)....
1) መሰረት የሚያደርገው የእግዚአብሄርን ስፊ ፍቅርና ምህረት ነው::
ንሰሃ ዋጋ የሚኖረው ምን ያህል የንስሃ ዝርዝር ንግግሮች ይዘን በመቅረባችን ሳይሆን እግዚአብሄር መሃሪ ስለሆነ ነው::
"...እንደ ቸርነትህ መጠን ...እንደ ርህራሄህም ብዛት..." ማረኝ መተላለፌንም ደምስስ (51:1)
ምሳሌ:- ሉቃ 15 የጠፋው ልጅ ወደ አባቱ መመለስን ሲያስብ አባቴን እንዲህ እለዋለው ያለው የንሰሃ ንግግር ሳይሆን አባቱ ገና ከሩቅ አይቶት ንግግሩን ሳይሰማ ሊቀበለው እየሮጠ መሄዱን አሰላስሉ::
2: ለእውነተኛ ንሰሃ በደልን ማወቅና በግልፅ መናዘዝ ያሻል::
"እኔ መተላለፌን አውቃለሁ...አንተን በእርግጥ አንተን ብቻ በደልኩ... እነሆ እውነትን ከሰው ልብ ትሻለህ..." (3-6 አንብቡ)
በደልን ማወቅ ሃጢያትን እርሱ እንደሚያየው ማየትና እውነተኛ የልብ ሃዘንን ይጠይቃል:: እርሱ የተሰበረውን መንፈስ ይሻል እውነተኛነትንም ይሻል::
3: በምህረቱ መተማመን
ንስሃ ፍፁም የሚሆነው እውነተኛ ንሰሃ እውነትኛና ፍፁም የሆነ ይቅርታን እንደሚያስገኝ ስናምን ነው::
"እጠበኝ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ!" (7)
አንድ ወዳጄ እንዳለው "እውነተኛ ንሰሃ ገብተን ይቅርታ እንዳገኘን የማይሰማን ከሆነ: የእየሱስን ደም የማንፃት ሃይሉን እየተጠራጠርን ነው"
በምህረቱ ሃይል እንተማመን:: እርሱ በደላችንን ዳግም ላያስብ ያነፃናል::
4: ተሃድሶን መናፈቅ
ምህረትን እንዳገኘን ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም:: እውነተኛ ንሰሃ ፍሬው ሃጢአትን መራቅና ፅድቅን መናፈቅ ነው:: ለቀጣዩ መንገድ ግልፅ አቋም ማግኘት ነው:: ሃጢአትን ለመበቀል ሃይልን መቀበል ነው::
"ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ ቀና የሆነውን መንፈስ በውስጤ አድስ...እኔም ለህግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ...ወዳንተ ይመለሳሉ" (8-19 ተመልከቱ)
ቀጣይ "የበደሉንን ይቅር እንድንል..." ይቀጥላል
Please share&join 👉🏿@samitadele

"እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል..."
-እግዚአብሄር የይቅርታ አምላክና በፊቱ በእውነተኛ ንሰሃ የሚመጡትን ይቅር እንደሚል አውቀናል::
- ከዚህ የተነሳ የርሱ የሆኑቱ የርሱን ምሳሌ ተከትለው ምህረት የሚያደርጉ ሊሆኑ ይገባቸዋል::
- ይቅርታን ተቀብሎ የማያስተላልፈው ሃጢያቱ ይቅር እንደተባለለት የማያምን ሰው ነው::
-ታዲያ እንዴት ይቅር እንበል? እርሱ ይቅር እንዳለን!
በእግዚአብሄር ቃል ስለ እግዚአብሄር መሃሪ ባህርይ ከሚያስረዱ ብዙ ክፍሎች ውስጥ ጠፍቶ (እጅጉን አዋርዶት) ጠፍቶ የነበረውን ልጅ ሊቀበል ስለወጣው አባት በምሳሌ እናያለን:: ልጁ በቁሙ "ሙት" ብሎ ንብረቱን ተካፍሎ ሲሄድ ከተዋረደው ይልቅ በማህበረሰቡ የተከበረ አባት ሊሆነው በማይገባ መንገድ ያዋረደው ልጁን ሊቀበል ሲሮጥ የተዋረደ የሚባል ስራ ሰርቷል::
-ገና ከሩቅ ሲያየው ሮጠ... አቀፈው... ሳመው (ከአሳማ ጋር የከረመው ልጁን... አሳማ በአይሁድ ማህበር እርኩስ ተደርጎ ይቆጠራል)...ምርጡን ልብስ አለበሰው ቀለበት አደረገለት... የደስታ ግብዣ አደረገ::
-ይህ ምሳሌ ስለ እግዚአብሄር የምህረት ስራና የርሱን ምህረት ያገኙ ሰዎች ሊያሳዩት የተጠሩትን የይቅርታ ህይወት የሚያሳይ ነው::
-ይቅር ማለት: በደለኛውን ዝም ብሎ መታገስ ሳይሆን እንደ አዲስ መቀበል ነው::
-አዲስ እድል መስጠት ነው::
-በዚህም ይቅርታ ሃጢያትን አይቆጥርም... (አይደምርም አያባዛም አይመዘግብም!
- ይቅርታ የሰዎችን ሁኔታ መረዳት ነው:: "የሚያደርጉትን አያውቁምና..." ሊበድሉን ያበቃቸውን ውስጣዊና ውጫዊ ግፊት ለመረዳት መጣር ነው::
-ይቅርታ በተግባርና በእውነት መልሶ መውደድ ነው:: "እንደራስህ ውደድ..."
ተግባራዊ የይቅርታ ሂደት ለበደሉን ከመፀለይ እንጀምር:: በሁዋላም የኛን መልካምነት በሚያስፈልጋቸው ሁሉ በመግለጥ እንገኝ::
እውነት ነው ይህን ስናደርግ የመዋረድ ስሜት ይመጣል:- ለዚህ ሁሉ በምን አይነት መንገድ ምህረት እንደተቀበልን እናስብ:: እሱን መምሰል መዋረድ አይደለም!
@samitadele

"ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉው አድነን እንጂ"
የምንኖርበት አለም በክፋት የተከበበ ነው:: የሰው ልብ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ክፋት ያዘነበለ ነው:: የሰጠኸውን ሁሉ ተጠቅሞ ለክፋት ሲያውለው የምድር ህይወት የግፍ: የመከራ የሞት አውድማ አድርጎታል::
ይህ ብቻ አይደለም ዲያብሎስና ጭፍራው የአንተ ፈቃድ ተቃራኒ አጀንዳና ሃይል አሰማርቶ ምድርን ይዘዋወራታል:: መሳርያውም ሽንገላ ማታለል: መፈተን ... እና የመሰለውን ነው:: በዚህ ሁሉ አላማው ፍጥረትን ካንተ ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ነው:: ይህን ለማሳካት ያለው ጊዜ አጭር እንደሆነም አውቆ በቁጣ ከፊትህ ከወጣባት ሰአት ጀምሮ ከጭፍራው ጋር ሳይታክት የክፋትን ሰይፍ ይስላል:: ያገኘውንም ሳይራራ በመርዛማው ጦር ወግቶ ገድሏል::
ታድያ ልዑል ሆይ በዚህ ክፉ አለም በየእለቱ በወጥመዱ አንቆ ይዞ እስከወዲያኛው ሊያጠፋን በተዘጋጀው ክፉ ፊት ተስፋችን ምንድን ነው?
ተስፋችንማ አንተ ነህ! አንተ ራስህ ይህን በክፋት የተሞላ አለም አሸንፈኸዋል :: ዲያብሎስና ፈተናውንም አሸነፍክ:: ስለዚህ አንተን ተገን ለሚያደርጉህ ፅኑ ተገን ነህ:: "ወደ እኔ የመጡትን ወደውጭ አላወጣም" ብለሃል:: ደግሞም "ማንም ከእጄ አይነጥቃችሁምም" ብለሃል::
ታዲያ ዛሬም የእምነት ፀሎታችን አድነን ነው:: ክፋው የሚውጠውን ፈልጎ እያገሳ ሌት ተቀን ይዞረናል:: የድፍረቱ ድፍረት ደቀመዛሙርትህን "እስቲ እንደ ስንዴ ላበጥራቸው " ያሉበትንም የእምነት ደረጃ ልፈትንልህ ብሎ ይለምናል:: አቤቱ አንተ ግን ለኬፋ እንደማለድክ ማልድልን!
አዎን አንተ ከተሰወረው: እሩቅ ተሸብቦ ከተወጠረው ወጥመድ ታድነናለህ:: ስለዚህም ባንተ ተማምነን "በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሄድ አንተ ከኔ ጋር ነህና አልፈራም!" እንላለን
Join the page for more👉🏿

7: “መንግስት: ሃይል: ክብርም: ለዘላለሙ ያንተ ነውና: አሜን::"
ፀሎታችንን ስንደመድም ለፀሎታችን ብቃትና ትርጉም በሰጠው እውነት እንደመድማለን::
አቤቱ መንግስት ሁሉ ያንተ ሊሆን አዲስን መንግስት በልጅህ መምስረትህን: እንዲሁም ይህች መንግስት ለፍጥረት ታሪክና ህልውና ፍፁም ትድግና የተገኘበት እንደሆነ ስንረዳ...
"መንግስትህ ትምጣ" ብለን አዘውትረን እንፀልያለን:: መንግስትህ አገዛዝህ ነው:: አንተ የምታስተዳድረው ብቻ በረፍትህ: በተትረፈረፈው ዘላለማዊ ህይወትና ሰላም ያርፋል:: ስለዚህም "አቤቱ ገዢ ፈቃድህ በሰማይ ፍፁም አስተዳደር እንዳለው... በምድር በቤተሰብ በቤተክርስቲያን ይሁን" ብለን እንፀልያለን::
ሃይል ሁሉ የአንተ እንደሆን ስናውቅ "ከክፉው ሁሉ" "ከፈተናውም ሁሉ" እንደምንድን ባንተ እናምናለን:: የሃጢያት ይቅርታና ከበደል መንፃትን እንደምናገኝ ለዕለት እንጀራም ለሚያስፈልገንም ሁሉ ልንደገፍህ እንደምንችል እናውቃለን::
ክብር ሁሉ ያንተ ስለሆነም...ስምህን በመካከላችን እንቀድሳለን:: ስምህን (ማንነትህን) ስንሻ ክብርህን በመካከላችን እናኖራለን:: የበደሉንን ይቅር ስንል ክብርህን እናሰፋለን እንገልጣለን::
በመጨረሻም ይህን መደምደሚያ ስንፀልይ; ተልእኮአችንን እናስባለን መንግስት ተኮር ህይወት: ለክብር ግብ አድርጎ መኖር:
ሃይልህን ማወቅና መተማመን ይብዛልን!
አሜን!
ይቀላቀሉ👉 @samitadele

በረከትና መታዘዝ
ውድ የዚህ ገጽ/channel ቤተሰቦች፣ አለፍ አለፍ እያሉ በሚተላለፉት መንፍሳዊና መጽሃፍ ቅዱሳዊ ምልከታዎች እየተጠቀማችሁ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ከዚህ በመቀጠል፡ በረከትና መታዘዝ ስላላቸው ትስስር መጽሃፍቅዱስ የሚያስተምረንን እንመለከታለን፡፡
የእግዚአብሔርን በረከት የምናውቀውም የምንለማመደውም በኪዳን ውስጥ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ሁሉና ለማዳን መሳሪያ ሊሆኑ ከተጠሩት ጋር የግንኙነት ስምምነት ይገባል፡፡ ይህ የሁለትዮሽ ስምምነት፣ ከእርሱ የበረከት ማረጋገጫን ሲሰጥ ከፍጥረቱ የመገዛት/የመታዘዝን ሃላፊንት ያስቀምጣል፡፡
ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የኪዳን ህብረት ውስጥ ሲገቡ በርሱ በረከት ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ይህም የርሱን ጥበቃ፣ አቅርቦት፣ ትድግናና ትርጉም ያለው ህይወት ለመቀበል ነው፡፡ በሌላው የዚህ ውል ገጽታ ደግሞ የሰዎችን/ የፍጥረቱን ሃላፊነት እናገኛለን፡፡ የፍጥረቱ ምላሽ ለፈቃዱ፣ ለተገለጡት ትዕዛዞቹና ለባህርዩ መታዘዝ/ መገዛት ነው፡፡
ይህ ምላሽ በአንድ ጎኑ የበረከቱ አካል ወይም መንገድ ሲሆን በሌላ በኩል በረከትን መጠበቂያ/ መያዣ (ማቆያ) ነው፡፡ ማለትም ፍጥረቱ በበረከት ቀጠና ውስጥ የሚሆነው በኪዳን ቀጠና ውስጥ እስከሆነ ድረስ ሲሆን በኪዳን ቀጠና ውስጥ መሆናችን የሚረጋገጠው እስከታዘዝን ብቻ ነው፡፡ በቀጣይ ይህ ትስስር እንዴት በቃሉ እንደተገለጠና የእውነተኛ በረከትና መታዘዝ መገለጫዎችን እንመለከታለን፡፡
ለሌሎች ለማጋራት (Share) ይህን ማስፈንጠሪያ (link) ይጠቀሙ 👉 @samitadele

>>በረከትና መታዘዝ<<
በረከት የኪዳን አካል ነው::
እግዚአብሄራዊ በረከት የቃልኪዳን አካል ነው:: ይህም ማለት በረከት የተገለጠው በያህዌና በፍጥረት/በሰው መካከል በተደረጉ ቃልኪዳኖች መካከል ነው::
1. ቃል ኪዳን ውል ነው::
በሁለት አካላትና ከዛ በላይ የሚገባ ስምምነት: እግዚአብሄር ከፍጥረቱ ጋር በገባቸው ስምምነቶች የርሱንም የፍጥረቱንም ሃፊነት እና ግዴታ አስቀምጧል:: እርሱ ፍጥረቱን ሊባርክ ቃል ሲገባ ፍጥረቱ ደግሞ እንዲታዘዝለት ሃላፊነት ያስቀምጣል::
2. እግዚአብሔርአዊ/ ቃልኪዳናዊ በረከት ምንድን ነው?
እግዚአብሄር በቃልኪዳን ያስቀመጠው ውል (ከፍጥረት ጋር ኪዳን ሲገባ) ሊባርክ ነው:: ይህ በረከት ከዘፍጥረት ጀምሮ ባሉት ታኮችና መፅሐፍት የተገለጠው በዋናነት አቅርቦትንና ጥበቃን/ ትድግናን (provision and protection) በመግለጥ ነው::
ማለትም እግዚአብሄር ይባርካል ማለት አቅርቦትን ያዘጋጃል ያድናል/ይጠብቃል ማለት ነው::
እግዚአብሄር ለፍጥረቱም ሆነ ለህዝቡ የገባው ቃል በኪዳን ውል ውስጥ የርሱ ድርሻ ለአካልም ለመንፈሳዊም የሚያስፈልግን ማቅረብ እና ከጉዳት መጠበቅ/በአዳጋ ውስጥ ማዳንንም ያካትታል::
በቀጣይ በዝርዝር እውነተኛ, ቃልኪዳናውዊና እግዚአብሔርአዊ በረከት ምንእንደሆነ: እንዲሁም እነዚህ የበረከት አካላት እንዴት በቃሉ እንደተገለጡና የሰዎች/ፍጥረት ድርሻ ምን እንደሆነ እንመለከታለን::
ጌታ ይባርካችሁ!
ለማጋራት 👉@samitadele
ክፍል 1. በረከት የኪዳን አካል ነው::

https://youtu.be/IOKra4tiqfU
ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች፡ ይህን የዩቲዩብ ቻናል subscribe በማድረግ ልዩልዩ መንፈሳዊና ስነመለኮታዊ
አጫጭር ቪድዮዎችን ይመልከቱ!
አመሰግናለሁ!

YouTube
Kingdom of God - Part 1: Introduction (የእግዚአብሄር መንግስት፡ ክፍል 1፡ መግቢያ በመጋቢ ሳሙኤል ታደለ) By Samuel Tadele
In this video, Pastor Samuel explores popular conceptions of "Kingdom of God", and debunks some of them as misconceptions ;qualifying others in light of the notions found in both Jewish and Earliest Christian sources.
በዚህ ቪዲዮ፥ መጋቢ ሳሙኤል ሰለእግዚአብሔር መንግስት በብዙዎቻችን…
በዚህ ቪዲዮ፥ መጋቢ ሳሙኤል ሰለእግዚአብሔር መንግስት በብዙዎቻችን…
>>በረከትና መታዘዝ<<
ክፍል 2: እውነተኛና መፅሃፍቅዱሳዊ በረከት ምንድን ነው?
በመግቢያው ክፍል እንደተመለከትነው በረከት በመፅሃፍ ቅዱስ አቅርቦትና ጥበቃ እንደሆነ ተመልክተናል:: ታዲያ እግዚአብሄር በኪዳን ለተጣመራቸው ያቀረበው በረከት ምንድን ነው?
ገና ከፍጥረት ጅምር እንደምንመለከተው እግዚአብሄር ፍጥረታትን በአቅርቦቱ ዘማሪው በ መዝ 104 እንደሚገልፀው ምድርና በውስጧ ያሉ ሁሉ ሳይቀር እርሱን ተስፋ ያደርጋሉ::
የሰው ልጅም በ ዘፍ 1-3 እንደምንመለከተው ህይወትን የጀመረው በበረከት ነው::
1ኛ በረከቱ በአምላኩ አምሳል መፈጠሩ ነው:: የርሱ ወኪል ሆኖ የሚያስተዳድር:: የአምላክ መልክ ነፀብራቅ የፈቃዱ ማሳያ ሊሆን ተጠራ:: ይህ በረከት በቀጣዩ የአብርሃም ጥሪና በ እስራኤል ህዝብ ኪዳን ውስጥ ተገልጧል::
1) ሀ) አዳም በፍጥረት ላይ "እየጠበቀ እየተንከባከበ " እግዚአብሔርን የሚወክል ካህን ሊሆን ከአፈር ተጠራ::
ለ) አብርሀም ተባርኮ ለአህዛብ የበረከት ማሳያና ማስተላለፊያ ሊሆን ከአህዛብ መካከል ተጠራ::
ሐ) እስራኤል ከግብፅ የመንግስት ካህናት ሊሆኑ ተጠሩ::
ለኛም የእውነተኛ በረከት ቁንጮ ይህ ጥሪ ነው:: የእርሱ በመሆን ያገኘነው በረከት የርሱ መሆንን ነው::
"በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ " ከተባረክንበት በረከት የሚልቅ በረከት የለም::
"ቅዱሳንና ነውር አልባ": "ልጆች" "የፈቃዱን ምስጢር ማወቅ" "ለክብሩ ምስጋና" ለመሆን ተጠራን (ኤፌ. 1:2-14) አሜን!
ይቀጥላል...
Join and share
👉 @samitadele

Jacob pursuing meeting with Yahweh, lets go all the possible distructions away. His wives, children and possetions were not evil by themselves, in fact were signs of Yahweh's presence and blessings.
Yet, he was convinced at this critical moment there should be no distrution inorder to have real encounter with the God of his father's .
Abraham did the same thing while he was willingly obeyed to sacrifice his begotten son to show the importance of priority.
That is the holy place where human beings have the intimate aliance with God, where he ultimatly brings all our blessings back to us to have it and enjoy it in a right way.

Engage with your current situations and feelings well, however don't abide with them. Dwell on the concrete hope!
#2
Hope is not self confidence or mere optimism. It is based on faith or certainty. To have Faith is on what has been done or promised from the the ultimate being.
#3
True Faith or certainty only comes if there are true encounters from the ultimate being. When one is certainly encountered with what has been done or being promised with this being will have the necessary trust about the future
#4
To unlock true Faith and hope try to see beyond your available informational knowledge. True trust and hope comes from beyond knowledge. You may know God has done or promised certain things. Yet, do you believe or have hope on them, is the defining question.

ቁርና ዝናብ ሳይበግራቸው አስርም አምስትም ሊለቅሙ ለሊት ከጠባብ መንደር የሚተመውን እመለከትና እንዴት ይህ ሁሉ ህዝብ ሰላምተኛ ሆነ ?...
ሙሉ ቀን በባዶ ሆድ አውራ ጎዳና ላይ የተበተኑትን ጨቅሎች አይና ህይወት ለማስቀጠል አቅም ከየት ተገኘ? እልና... በጭላንጭል ተስፋ ኀይል እደነቃለሁ!

ከራስ በራስ የሆነውን የማይቻል ትግል ለቆ ራስን ለፀጋ መጣል እንዴት ከባድ ነው?
.
.
የትግል አቅጣጫ መቀየር
ከማይቻለው ወደ ቀላሉ መታገል!
.
.
የትግል አቅጣጫ መቀየር
ከማይቻለው ወደ ቀላሉ መታገል!
The renewal of the mind is important to know and rejoice by the will of God.
To know it is one important thing, yet to seek it and rejoice with it is another higher attitude.
"Do not be conformed to this age, but be transformed by the renewing of the mind, so that you may discern what is the will of God—what is good and acceptable and perfect."
Rom. 12:2