Research-ሪሰርች(ጁፒተር-Jupiter)
16K subscribers
34 photos
2 videos
305 files
430 links
🔷 Business proposal
🔷 Proposal(Masters)
🔷 Research ማማከር
🔷 survey questionnaire ለማዘጋጀት እናማክራለን
🛑 ለተመራቂዎች ተማሪዎች ጥሩ ርዕሰ እንዴት መምረጥ እንዳለባችሁ እናማክራለን!
Download Telegram
RESEARCH DESIGN

There are four main types of Quantitative research: Descriptive, Correlational, Causal-Comparative/Quasi-Experimental, and Experimental Research. attempts to establish cause- effect relationships among the variables. These types of design are very similar to true experiments, but with some key differences.

አራት ዋና ዋና የቁጥር ምርምር ዓይነቶች አሉ::
👉 ገላጭ ፣
👉 ተዛማጅ ፣
👉 የምክንያት-ንፅፅር / የኳሲ-ሙከራ እና
👉 የሙከራ ምርምር ፡፡

ከተለዋዋጮች መካከል መንስኤ-ተጽዕኖ ግንኙነቶችን ለመመስረት ሙከራዎች ፡፡ እነዚህ ዓይነቶች ንድፍ ከእውነተኛ ሙከራዎች ጋር በጣም ተመሳሳይ ናቸው ፣ ግን ከአንዳንድ ቁልፍ ልዩነቶች ይንራቸዋል ።
👍81
Researcher Academy_Nov 2019.pptx
6.1 MB
Authors workshop presentation on how to publish on international journals.
👍4🤔1
doc.pdf
70.6 MB
Qualitative Research and Evaluation Methods.
ቻናላችን
Anonymous Poll
96%
4%
5👍3👏1
Presentation For Proposal.pptx
99.1 KB
please use the following template for your presentation
👍9
ለምርምር ወይም ለጥናት ስራ (Research )የመነሻ ሀሳብ ከየት እናገኛለን?
...................................................
የምርምር ስራ በዋናነት በአንድ ዘርፍ ላይ እውቀትን ለማዳበር እና ሁኔታወችን ከመሰረታቸው ለመረዳት ወይም ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ሊሰራ ይችላል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ላይ ያሉ ተማሪዎች እንዲሁም በስራ ላይ ያሉ ባለሞያዎች በምርምር ስራ ላይ ሊሳተፉ ይችላሉ፡፡

በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ላይ የምርምር ሀሳብ እንዴት እናግኝ ወይም እንወስን የሚለው ጥያቄ ብዙ ጊዜ ይነሳል፡፡ የምርምር ሀሳብ ለማግኘት ወይም ለመምረጥ የሚከተሉት ነጥቦች ሊያግዙ ይችላሉ፡፡
...................................................
1. Observation (አካባቢን ማየት) :- በአካባቢያችን፣ በስራ ቦታ እንዲሁም በመኖሪያ አካባቢ፣ የምናያቸው ችግሮች ወይም ሂደቶችን ለምርምር ስራ ሀሳብ ልናገኝባቸው ይችላሉ፡፡
በቀላሉ ለምሳሌ አንድ መምህር የተማሪዎቹ ውጤት ቢቀንስበት ለምን ቀነሰ ብሎ ችግሩንና የችግሩን መንስኤ ሊያጠና ይችላል፡፡ በተመሳሳይ የተማሪዎቹን ውጤት እንዴት መጨመር ወይም ማስተካከል ይቻላል የሚለውንም ሊያጠና ይችላል፡፡

2. Literature review (ማንበብ):- አንድ ተመራማሪ ወይም ተማሪ ሁልጊዜም እንደልምድ መያዝ ያለበት ነገር ሳይንሳዊ እና ትምህርታዊ ጆርናሎችን መከታተልና ማንበብ ነው፡፡ በየአመቱ በየዘርፉ በሺ የሚቆጠሩ የምርምር ስራ ውጤቶች በጆርናሎች ይታተማሉ፡፡ የምርምር ስራዎችን ማየትና ማንበብ በቀጣይ ለሚሰራ ምርምር መነሻ ሀሳብ ይገኝበታል፡፡
ለምሳሌ የተማሪዎችን ውጤት እንዴት መጨመር እንደሚቻል የተሰራን ጥናት ፅሁፍ ያነበበ መምህር እሱ ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች አንፃር ወይም በተለየ እይታ ሊሰራው ይችላል፡፡

3. የምርምር እና ትምህርታዊ ኮንፈረንሶችን፣
ሴሚናሮችን እና ፕረዘንቴሽኖችን መከታተል:- በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚደረጉ የምርምር ስራ የሚቀርቡባቸው ፕሮግራሞች ለምርምር ስራ ሀሳብ ከማግኘት ባለፈ በአጠቃላይ ስለምርምር ስራ ሂደት መማር ይቻላል፡፡
👍10
ለተመራቂ ተማሪዎች
ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ቀርቦላችኋል!
Automatic References
Automatic List of tables
Automatic List of figures
Citation እንዴት እንሰራለን?
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/VujbubSHkZs

ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
✔️ Automatic Tables of Content.
✔️ Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/aB-z5uKq75U
~~~><~~~~~~~~~~
የYouTube ቻናሉን Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርቶችን ይማሩ!
የ YouTube ቻናል ሊንክ
👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
👍4
Qualitative vs. quantitative research
Quantitative research
Quantitative research is expressed in numbers and graphs. It is used to test or confirm theories and assumptions. This type of research can be used to establish
generalizable facts about a topic.
Common quantitative methods include experiments, observations recorded as numbers, and surveys with closed-ended questions.
Qualitative research
Qualitative research is expressed in words. It is used to understand concepts, thoughts or experiences. This type of research enables you to gather in-depth insights on topics that are not well understood.
Common qualitative methods include interviews with open-ended questions, observations described in words, and literature reviews that explore concepts and theories.
The differences between quantitative and qualitative research
Quantitative and qualitative research use different research methods to collect and analyze data, and they allow you to answer different kinds of research questions.
Quantitative research
🔷 Focuses on testing theories and hypotheses
🔷 Analyzed through math and statistical analysis
🔷 Mainly expressed in numbers, graphs and tables
🔷 Requires many respondents
🔷 Closed (multiple choice) questions
🔷 Key terms: testing, measurement, objectivity, replicability
Qualitative Research
🔷 Focuses on exploring ideas and formulating a theory or hypothesis
🔷 Analyzed by summarizing, categorizing and interpreting
🔷 Mainly expressed in words
🔷 Requires few respondents
🔷 Open-ended questions
🔷 Key terms: understanding, context, complexity, subjectivity
Data collection methods
Quantitative and qualitative data can be collected using various methods. It is important to use a data collection method that will help answer your research question(s).
Many data collection methods can be either qualitative or quantitative. For example, in surveys, observations or case studies , your data can be represented as numbers (e.g. using rating scales or counting frequencies) or as words (e.g. with open-ended questions or descriptions of what you observe).
However, some methods are more commonly used in one type or the other.
🔷 Quantitative data collection methods
🔶 Surveys : List of closed or multiple choice questions that is distributed to a sample (online, in person, or over the phone).
🔶 Experiments: Situation in which variables are controlled and manipulated to establish cause-and-effect relationships.
🔶 Observations: Observing subjects in a natural environment where variables can’t be controlled.
🔷 Qualitative data collection methods
🔶 Interviews : Asking open-ended questions verbally to respondents.
🔶 Focus groups: Discussion among a group of people about a topic to gather opinions that can be used for further research.
🔶 Ethnography : Participating in a community or organization for an extended period of time to closely observe culture and behavior.
🔶 Literature review : Survey of published works by other authors.
👍4
Organizing Academic Research Papers: Purpose of Guide


https://library.sacredheart.edu/c.php?g=29803&p=185901
👍1
Variables!

Variables:- ማንኛውንም ጥናታዊ ስራ ለመስራት በምናስብበት ወቅት ስለ ምናጠናው ሃሳብ ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች፤ በጥናት ልናረጋግጠው በፈለግነው ሃሳብ ላይ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ተጽኖ የሚፈጥሩ ጉዳዮች ወይም ሃሳቦች ማለት ነው።

ለምሳሌ:-

በግለሰብ ደረጃ ሲጋራ ለማጨስ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን ለማጥናት ብናስብ፣ ቀጥተኛ ሆነ ተዘዋዋሪ ተጽኖ የሚፈጥሩ ሃሳቦችን መጀመሪያ እንለያለን፣ እነሱም ጾታ፤ እድሜ፤ የትዳር ሁኔታ፤ የስራ በሃሪ፤ ገቢ፤ የመኖሪያ አካባቢ፤ ወዘተ ሲጋራ ማጨስን ጨምሮ Variables ይባላሉ። የምንመርጣቸውን Variables ከTheory አንጻር፤ ከሌሎች ጥናታዊ ግኝቶች አንጻር እና ከልምድ አንጻር በመመስረት መምረጥ ይይቻላል።

ለምሳሌ:-

ወጣትነት ለማጨስ እንደሚገፋፋ ከልምድ በመነሳት፤ የገቢ ማነስ በብስጭት ምክንያት ለማጨስ እንደሚዳርግ የተረጋገጠ ጥናት ካለ በመውሰድ፤ ሌሎቹንም በምክንያት በማስደገፍ መርጦ መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን ከላይ ከተጠቀሱት ምክያቶች ውጪ ምክንያት አለኝ ወይም ማረጋገጥ እፈልጋለው ለሚል አጥኚ የራሱን ሃሳብ በማቅረብ ማጥናት ይችላል።

ለምሳሌ:-

በግለሰብ ደረጃ ሲጋራ ለማጨስ የኢንተርኔት መጥፋት ምክንያት ነው የሚል Variables ቢመረጥ ስህትት አይደለም ነገር ግን በመረጃ በመነሳት ግንኙነት እንዳለው እና እንደሌለው ማረጋገጥ ብቻ ነው የሚጠበቅበት።

በግለሰብ ደረጃ ሲጋራ ለማጨስ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን ለማጥናት ብናስብ በጥናት የሚረጋገጠው ሲጋራ ማጨስ (Dependent ወይም Outcome Variable) ይባላል። ምክንያቱም ሲጋራ ማጨስ በጾታ፤ በእድሜ፤ በትዳር ሁኔታ፤ በስራ በሃሪ፤ በገቢ፤ በመኖሪያ አካባቢ፤ ወዘተ ተጽኖ ስለሚያድርበት በነሱ ላይ ጥገኛ ነው።

ነገር ግን በራሳቸው ቆመው በሲጋራ ማጨስ ላይ ተጽኖ የሚፈጥሩት ጾታ፤ እድሜ፤ የትዳር ሁኔታ፤ የስራ በሃሪ፤ ገቢ፤ የመኖሪያ አካባቢ፤ ወዘተ (Independent ወይም Explanatory Variables) ይባላሉ። ምክንያቱም ሲጋራ ማጨስ በተቃራኒው የግለሰቡ ጾታ ላይ ተጽኖ መፍጠር አይችልም (ሰው ስላጨሰ ጾታው አይለወጥም ነገር ግን ጾታው እንዲያጨስ ተጽኖ ሊፈጥርበት ይችላል

ለምሳሌ:- ወንዶች ከሴቶች በላይ አጫሽ ሊሆኑ ይችላሉ።

Y(ሲጋራ ማጨስ) = f(ጾታ + እድሜ + የትዳር ሁኔታ + የስራ በሃሪ + ገቢ + የመኖሪያ አካባቢ + ወዘተ + Error Term)

በተለይ የEconometrics Model በመጠቀም ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ለሚያስቡ አጥኚዎች የምንመርጠውን Variables በጥንቃቄ መምረጥ የማንችል ከሆን የመጨረሻ ውጤቱን ሊያዛባው ይችላል። በተለይ የመረጥነው Independent Variable በተቃራኒው በራሱ በIndependent Variable ላይ ተዘዋዋሪ ተጽኖ የሚፈጥር ከሆን በጣም ክፍተኛ ስህተት የሆነ ውጤት ነው የምናገኘው። የዚህ አይነቱ ችግር Multicolinearity Effect ይባላል። ስለዚህ በቅድሚያ Variables በጥንቃቄ በመምረጥ እንዲሁም የዚህ አይነቱን ችግር መኖሩን የሚያረጋግጠውን Multicolinearity Test ለማድረግ የተለመደው variance-inflating factor (VIF) ስልት ሲሆን በVIF የሚገኘው አማካይ ውጤት ከ10በታች ከሆነ የወሰድናቸው Independent Variables ትክክለኛ ወሆናቸውን ያሳያል። ለዚህ የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች E-View፤ Stata፤ SPSS፤ Sas፤ ወዘተ) በመጠቀም ችግሩን መቅረፍ ይገባል።

© The Ethiopian Economist View
👍7
የጥናት ርዕስ እንዴት ይመረጣል

ለ "Research" (ለመጀመሪያ ድግሪ/BA/BSc)፣ ለ "Thesis" (ለሁለተኛ ድግሪ/MA/MSc)፣ ለ "Dissertation" (ለሶስተኛ ድግሪ/ PhD) እና ለ "Article" (Journal Publication) የጥናታዊ
ጽሑፍ ርዕስ አመራረጥ/አቀማመጥ ላይ እንዴት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል?

ለተመራቂዎች የመጨረሻ ዓመት የሚያቀርቡትን የጥናት ርዕሰ ሃሳብ ፈልጎ ማግኘት ፈተና እንደሆነ ግልጽ ነው። በተለይ ደግሞ መስራት የሚያስቡትን ሃሳብ በተገቢው አገላለጽ ርዕስ መስጠትም ሌላኛው ችግር ነው። ምክንያቱም ብዙ ሰዎች የጥናቱ ውስጣዊ ሃሳብ እና የሰጡት ርዕስ የማይመሳሰል ይሆንና ለትችት ሲዳረጉ ይታያል።

ስለዚህ ልዩ/ ያልተሰራበት ርዕስ ለመፍጠር መሞከር አስቸጋሪ በሚሆንበት ወቅት በሌሎች የተነሱ ሃሳቦችን ጥራት ባለው እውነተኛ/ በቂ ዳታ በመጠቀም፣ ትክክለኛ ሞዴል እና ቴስት በመጠቀም፣ ተጨማሪ መለኪያ (Variables) በማካተት፣ የተለያዩ ሌሎች አጥኚዎች በተለያየ ወቅት የሰሯቸውን ጥናቶች በማነጻጸር "Meta Analysis" መስራት እና ወዘተ በማድረግ ለሰዎች እና ለእውነት የቀረበ የጥናት ጽሁፍ ማቅረብ ይቻላል፡፡

ለምሳሌ:-

ሲጋራ በማጨስ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን በጥናት ለማረጋገጥ የፈለገ አንድ አጥኚ ርዕሱን በሚከተሉት መልኮች ማቅረብ ይችላል።

1. Smoking Cigarette and Its Socio-Economic Effect.

2. The Impact of Smoking Cigarette on Health.

3. Determinants for Smoking Cigarette.

4. Challenges to Stop Smoking Cigarette.

5. The Assessment of Smoking Cigarette and Social life.

6. Smoking Cigarette and its Drawback on Health.

በጥናት ውስጥ ማረጋገጥ የፈለግነው ጉዳይ (Dependent Variable) እና ለማረጋገጥ በማስረጃነት የምንወስዳቸው ሃሳቦች (Independent/Explanatory Variables) መለየት መሰረታዊ ጉዳይ ነው።

ስለዚህ በቀላሉ ብድግ እያደረግን "Determinant"፣ "Impact"፣ "Effect"፣ "Challenge"፣ "Drawback"፣ "Assessment" በማለት ብቻ ማስቀመጥ ሳይሆን መረጃ አሰባሰብ ላይ ትኩረት በማድረግ ለሞዴል አጠቃቀም በሚያመች ሁኔታ ማስቀመጥ፣ "Variables" አወሳሰድን በመወሰን፣ የመስራት አቅምን መሰረት በማድረግ እና ወዘተ መሆን አለበት፡፡

© The Ethiopian Economist View
👍13
Plagiarism

⁉️ምን ማለት ነው?

💢Plagiarism ማለት፣ ምንጩን ሳናመሰግን ወይም ሳንጠቅስ የሌላ ሰው ሀሳብ ወይም ቃላትን እንደ ራስ አድርጎ መጠቀም፣ መስረቅ፣ ወይም የሌላ ሰው ምርት እንደ የራስ ማድረግ”

🚫ብዙ ጊዜ plagiarism የሌላ ሰው ጽሁፍ ወይም ቃላትን መጠቀም ብቻ ይመስለናል ግን አይደለም፣ paraphrase (እንደገነ በሌላ ቃላት መግላጽ) ብንችል እንኳ፣ የሌላ ሰው ሀሳብ ሆኖ ምንጭ ከልተገለጸ(cite ከልተደረገ) plagiarism ነው።


Types of plagiarism

1. Copy past plagiarism

💢also known as direct plagiarism, means using a paragraph from another source without a citation

💢በቀጥታ ምንጩ ሳይጠቀስ የሌላ ሰው ጽኩፍ በከፍል ኮፒ አድርጎ መጠቀም ፣

2. Mosaic plagiarism

💢Copying and pasting different pieces of text together to create a kind of “mosaic” or “patchwork” of other researchers’ ideas is plagiarism.

💢በተላያዩ ሰዎች የተጻፉ ጽሁፎችን ኮፒ በማድረግ ሌላ አድስ የምመስል ጽሑፍ ማዘጋጃት እና አድስ ማስመሰል ፣ በዚህ ጊዜም ምንጭ ከልተጠቀሰ plagiarism ነው፣ ምክንያቱም የሌላ ሰው ሀሳብ እንኳ ማስረቅ አይቻልም ።

3. Self plagiarism

💢When you use parts of your previous work (a paper, a literature review ) without properly citing.

💢ከዚህ በፊት ራሳችን ከሰረነውን ጽሁፍ እንኳን ለሌላ ጽሁፍ cite ሳይደረግ መጠቀም አይቻልም።

💢ማለት ለሌላ አላማ ከጻፍነው ጽሑፍ ላይ አድስ ለምንጽፈው ጽሁፍ ምንጭ ሳንጠቅስ መጠቀም አንችልም።😃😃


4. Global plagiarism

💯When you use someone else’s paper.

💢ሙሉ በሙሉ የሌላ ሰው document የቤተሰብ፣ የጓዳኛ ፣ የፍቅረኛም ይሁን፣ ለራስ መጠቀም plagiarism ነው፣ ለምን የሚስት/የባል አይሆንም😉😉😉😃

How to avoid plagiarism

To avoid plagiarism, simply follow these two steps:

1⃣Quote, paraphrase or summarize the words or ideas

2⃣ have citation in the text and provide the reference list.

💯የግድ ትምርህተ ጥቅስ("quote") ውስጥ ማድረግ ወይም በሌላ አገለላጽ መጻፍ (paraphrase)፣ ወይም አሰጥሮ መግላጽ summarize) እና ምንጭ መጥቀስ (cite) ማድረግ አለብን።

🚫ይህን ሁሉ አድርገን ምንጭ መጥቀስ ካልቸልን አሁንም plagiarism አለ ማለት ነው፣

💢What information needs to be cited?

🔰ሁሉንም ነገር የግድ cite ማድረግ አይጠበቅብንም። አንደንድ መረጃ አብዛኛው ሰው የሚያውቀው (common knowledge) ከሆን cite ላይደረግ ይችላል። ከ common Knowledge ውጪ ሁሉም የራስ ያልሆኑ ጽሁፎች cite ማድረግ አለብን።

©research_con
👍9