Research-ሪሰርች(ጁፒተር-Jupiter)
16K subscribers
34 photos
2 videos
305 files
430 links
🔷 Business proposal
🔷 Proposal(Masters)
🔷 Research ማማከር
🔷 survey questionnaire ለማዘጋጀት እናማክራለን
🛑 ለተመራቂዎች ተማሪዎች ጥሩ ርዕሰ እንዴት መምረጥ እንዳለባችሁ እናማክራለን!
Download Telegram
Paradigm
በዚህ ጽሁፍ ስለሪሰርች ፓራዳይም በአጭሩ ለመግጽ እሞክራለሁ
ይጥናት ፓራዳይም ማለት አንድ ጥናት አጥኚ ጥናቱን ለማጥናት የሚመርጠው ወይም የሚያምነበት ፍልስፍና ነው፡፡አለምን ለማየት የምንመርጠው ፓራዳይም ጥናታችን ላይ የራሱ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡
ፓራዳይም የሚመነጨው ከፍልስፍና ነው፡፡በፍልስፍናው ዘርፍ ስለ እውነት እና ስለ እውቀት የሚያጠኑ ሁለት ዘርፎች አሉ፡፡እነሱም ኦንቶሎጂ እና ኢፒስትሞሎጂ ይባላሉ፡፡
ኦንቶሎጂ እውነት ምንድነው ብሎ ይጠይቃል ለዚህም የተለያዩ መልሶችን ያስቀምጣል፡፡ከመልሶቹ መሀከልም ሶስት ዋና ዋና መልሶችን የሚከተሉትናቸው፡፡
1.ለአንድ ጥያቄ አንድ መልስ ነው ያለው፡፡ እውነት አንድ ነው፡፡
2.ለአንድ ጥያቄ ከአንድ በላይ መልስ ሊኖር ይችላል፡፡በዙ እውነቶች አሉ ፡፡
3.ለአንድ ጥያቄ አንድ ወይም ብዙ መልስ ሊኖር ይችላል፡፡እውነት አንድ ሊሆንም ይችላል ብዙ እውለቶችም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡
ኢፒስቲሞሎጂ እውቀት እንዴት ነው የምናገኘው የሚለውን ለመመለስ የተለያዮ መልሶችን ያስቀምጣል ዋና ዋና መልሶቹ የሚከተሉት ናቸው
1.እውቀት በትክክል መለካት የሚችል ነገር ነው፡፡አለም አቀፍ መለኪያዎችን ተጠቅመን እውቀትን በትክክል መለካት እንችላለን፡፡
2.እቅቀት ይተረጎማል ወይንም ይብራራል እንጂ በትክክል አይለካም ፡፡እንደ ሰዉ አተያይ ይለያያል፡፡
3.እውቀት እንደ ሁኔታው ሊለካ ወይም ሊተረጎም ይችላል፡፡
ከላይ የተገለጹትን የኦንቶሎጂ እና ኢፒስቲሞሎጂ አስተሳሰቦች ስናጣምር የጥናታችንን መነጽር ወይም ፓራዳይም እናገኛለን
ለምሳሌ
1.እውነት አንድ ነው የሚለውን የኦንቶሎጂ ሀሳብ እና እውቀት በትክክል መለካት ይችላል የሚለውን የኢፒስቲሞሎጂ ሀሳብ ስናጣምር ፖዘቲቪዝም የሚባል የጥናት ዕይታ ወይም ፓራዳይም እናገኛለን፡፡በፖዘቲቪዝምን የጥናታች መንገድ የተቃኘን ከሆነ ጥናታችን ሙሉ ለሙሉ ወደሂሳብ ያጋደለ ብዙ ቁጥራዊ መረጃዎችን የያዘ(quantitative) ይሆናል፡፡
2.በዙ እውነቶች አሉ የሚለውን የኦንቶሎጂ ሀሳብ እና እውቀት ይተረጎማል ወይንም ይብራራል እንጂ በትክክል አይለካም የሚለውን የኢፒስቲሞሎጂ ሀሳብ ስናጣምር ኮንስትራክቲቪዝም የሚባል የጥናት ዕይታ ወይም ፓራዳይም እናገኛለን፡፡በኮንስትራክቲቪዝም የጥናታች መንገድ የተቃኘን ከሆነ ጥናታችን ቁጥሮች ላይ ብዙ ጥናትችን ገለጻ ላይ ያተኮረ(qualitative) ይሆናል፡፡በማህበራዊ ሳይነሱ አካባቢ በብዛት የሚሰራበት ነው፡፡

3.ለአንድጥያቄ አንድ ወይም ብዙ መልስ ሊኖር ይችላል የኦንቶሎጂ ሀሳብ እና እቅቀት ይተረጎማል ወይንም ይብራራል እንጂ በትክክል አይለካምእውቀት እንዱሁኔታው ሊለካ ወይም ሊተረጎም ይችላል የሚለውን የኢፒስቲሞሎጂ ሀሳብ ስናጣምር ፕራግማቲዝም የሚባል የጥናት ዕይታ ወይም ፓራዳይም እናገኛለን፡፡በፕራግማቲዝም የጥናታች መንገድ የተቃኘን ከሆነ ጥናታችን እንደሁኔታው ቁጥር ላይ ወይም ደግሞ ገለጻ ላይ ሊያተኩር ይችላል፡፡የምንከተለው የጥናት ዘዴ(mixed) ቅይጥ ይሆናል::
የእናንተ ፓራዳይም የትኛው ነው?
👍53👎2🔥2👏2🥰1
Action Research Module1.pdf
2.3 MB
Action Research Training Module

Written By Genene Abebe (PhD)
👍19
Action research process.pptx
390.2 KB
Action research
Genene Abebe (PhD)
Research and Community Service
Director
👍13
ቻናላችን?
Anonymous Poll
95%
👍
5%
👎
👍152
​​The structure

There are some conventions that guide the structuring of dissertations in different disciplines. You should check departmental and course regulations.

Below is the commonly used structure
🔹Title page
🔹Abstract
🔹Acknowledgements
🔹Contents page(s)

1️⃣ Introduction
2️⃣ Literature review
3️⃣ Methodology
4️⃣ Results/ Findings
5️⃣ Discussion
6️⃣ Summary, Conclusion and Recommendation

N.B. The main body of the thesis (i.e. Introduction, Literature Review, Methodology, Results, Discussion and Conclusion) shall be broken into Chapters

🔷 References
🔷 Appendices (if any)
🔷 Glossary (if any)
👍28👎42👏2😁1
📣📣 GOOD NEWS‼️📣
❇️ በማንኛውም የትምህርት መስክ በማስተርስና የመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው፣ #የመመረቂያ_ፅሑፍ ለመስራት ልዩ ድጋፍና እገዛ ለሚፈልጉ ተመራቂ ተማሪዎች ሁሉ፥ ያሉበት ቦታ ሳይገድበን #ጥራት ያለው አገልግሎት #በተመጣጣኝ ክፍያና #በተፈለገው_ጊዜ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
👇👇👇Contact us👇👇👇
@rese1000arch
@rese1000arch
@rese1000arch
@rese1000arch
@rese1000arch
👉👉 +251954539905
👍9
የጥናትና ምርምር ሥራ ከመጀመሩ በፊት ልብ ሊባሉ የሚገቡ 2 ነጥቦች

ጥናትና ምርምር በትምህርት ተቋማት፣ በበጎ አድራት ድርጅቶች፣ በንግድ ተቋማት እንዲሁም በግለሰቦች እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡ የጥናትና ምርምሩ እንደተመራማሪው ፍላጎት የተለያየ ቢሆንም በዋንኛነት ግን ጥናት አድራጊው ወጭ ቆጣቢና ዉጤታማ አሰራር እንዲኖር ፤ ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን የሚያስችሉ አሰራሮችን ለመፍጠርና ለመተግበር ጥናቶችን ምርምሮች ይሰራሉ፡፡
ታዲያ አንድ የጥናትና ምርምር ፕሮጀክት ሲዘጋጅ ልብ ሊባሉ የሚገቡ ጉዳዮች አሉ፡፡በዚሁ መሰረት ጥናትና ምርምሩ ከመጀመሩ በፊት ጥናት አድራጊው አካል ትኩረት ሊያደርግባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል ዋንኞቹን መጥቀስ ይቻላል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ጥናቱ ወይንም ፕሮጀክቱ በምን አይነት ሁኔታ/መልክ ሊሠራ እንደሚገባ በመቀጠልም የጥናቱ ፕሮጀክት ዶክመንት የሚያካትታቸውን ርዕሶችና ንዑስ ርዕሶች እንዲሁም በውስጣው ሊካተቱ የሚችሉ ፍሬ ሀሳቦችን በቅድሚያ መወሰን ይገባል፡፡ የጥናትና ምርምርም ሥራን ማቀድና መተግበር በአንድ ሌሊት የሚጠናቀቅ ነገር ባይሆንም ከላይ የተጠቀሱ ጉዳዮችን ግን ቀደም ብሎ ማሰብ ሥራችንን ፍሬያማ ሊያደርገው ይችላል የሚል እምነት አለን:
👍30👏2
#የጥናት_ርዕስ_እንዴት_ይመረጣል ?
*
ለ Research (ለመጀመሪያ ድግሪ/BA/BSc), ለ Thesis
(ለሁለተኛ ድግሪ/MA/MSc), ለ Dissertation (ለሶስተኛ
ድግሪ/ PhD), ለ Article (Journal Publication) ጥናት
ጽሁፍ የርዕስ አመራረጥ/አቀማመጥ ላይ እንዴት ጥንቃቄ
ማድረግ ይገባል?
*
ለተራቂዎች የመጨረሻ ዓመት የሚያቀርቡትን የጥናት ርዕሰ
ሃሳብ ፈልጎ ማግኘት ፈተና እንደሆነ ግልጽ ነው! በተለይ ደግሞ
መስራት የሚያስቡትን ሃሳብ በተገቢው አገላለጽ ርዕስ
መስጠትም ሌላኛው ችግር ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ሰዎች
የጥናቱ ውስጣዊ ሃሳብ እና የሰጡት ርዕስ የማይመሳሰል
ይሆንና ለትችት ሲዳረጉ ይታያል፡፡ ስለዚህ….
ልዩ/ያልተሰራበት ርዕስ ለመፍጠር መሞከር አስቸጋሪ
በሚሆንበት ወቅት በሌሎች የተነሱ ሃሳቦችን ጥራት ባለው
እውነተኛ/በቂ ዳታ በመጠቀም፤ ትክክለኛ ሞዴል እና ቴስት
በመጠቀም፤ ተጨማሪ መለኪያ (Variables) በማካተት፣
የተለያዩ ሌሎች አጥኚዎች በተለያየ ወቅት የሰሯቸውን ጥናቶች
በማነጻጸር (Meta Analysis) መስራት፣ ወዘተ በማድረግ
ለሰዎች እና ለእውነት የቀረበ የጥናት ጽሁፍ ማቅረብ ይቻላል፡፡
# ለምሳሌ ሲጋራ በማጨስ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን በጥናት
ለማረጋገጥ የፈለገ አንድ አጥኚ ርዕሱን በሚከተሉት መልኮች
ማቅረብ ይችላል…..
1. Smoking Cigarette and Its Socio-Economic
Effect.
2. The Impact of Smoking Cigarette on Health.
3. Determinants for Smoking Cigarette.
4. Challenges to Stop Smoking Cigarette.
5. The Assessment of Smoking Cigarette and
Social life.
6. Smoking Cigarette and its Drawback on Health.
በጥናት ውስጥ ማረጋገጥ የፈለግነው ጉዳይ (Dependent
Variable) እና ለማረጋገጥ በማስረጃነት የምንወስዳቸው
ሃሳቦች (Independent/Explanatory Variables) መለየት
መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ ብድግ እያደረግን
Determinant, Impact, Effect, Challenge,
Drawback, Assessment በማለት ብቻ ማስቀመጥ ሳይሆን፤
መረጃ አሰባሰብ ላይ ትኩረት በማድረግ፤ ለሞዴል አጠቃቀም
በሚያመች መልኩ፤ Variables አወሳሰድን በመወሰን፤
የመስራት አቅምን መሰረት በማድረግ፤ ወዘተ መሆን አለበት፡፡
👍362
የትኛው አይነት የሪሰርች ጥያቄ (research question) ወይም Dependent Variable ምን አይነት Analysis ያስፈልጋል ብለን ስንመለከት ፣

1. Dependent Variable በቁጥር የሚገለጽ(Numerical variable) ከሆነ በብዛት የሚንጠቀምበት Analysis models:-
🔢 bivariate correlation (Pearson, partial etc..)
🔢 Linear regression( simple, multiple LR)
🔢 t- tests (one sample, paired, independent t test)
🔢 ANOVA (one way, two way, ANCOVA, MANOVA...) የሚባሉ ሞዴሎች ስሆን እያንደንዱን በስፈት እንመለከታለን ፣

2. Dependent variable Categorical ከሆነ
chi square test
Logistic regression( BLR, MLR, OLR)
በአብዛኛው ጊዜ የሚንጠቀምባቸው ናቸው፣
👍23👎1
SAMPLE SIZE CALCULATION


በዚህ ጽሑፍ sample size manually calculate ለማድረግ የሚረደንን formula እና ተያያዥ assumption ለመደሰስ እንሞክራለን። ነገር ግን በዚህ ጊዜ በsoftwar በቀላሉ calculate ማድረግ ስለሚቻል፣ manual ብዙም አሳሳብ አይደለም፣ ነገር ግን ጽንሳ ሀሳቡን ለመረደት ያስችላል።

ለ Cross sectional/ prevalence/ study እንዴት እንደሆነ እንመልከት ፣

Sample Size ለሁሉም specific objectives በተናጠል ተሰልቶ በመቀመጥ ይኖርበታል ፣

♐️ነገር ግን በስተመጨረሻ ከሀሉም ትልቁን ቁጥር የጥናታችን sample saze ነው ብለን መውሰድ ይኖርብናል ማለት ነው።

ለምሳሌ objective of the study: Prevalence and Assiciated factor of coronovirus ብሆን፣

OBJECTIVE 1
prevalance የሚለው objective 1 ስሆን Single proportion method በመጠቀም sample size calculate ማድረግ ይቻላል ።

Assumptions
Z= 1.96( 95%CI)

P- proportion of the event ስሆን፣ ከየት እናገኛለን?
ከዚህ በፊት ከተሰሩ ተመሳሳይ ጥናቶች
ምንም ጥናት ከሌላ 0.5 መውሰድ
Expert guess(በዘርፉ ብዙ ጥናት ከሰሩ ሰዎች)
pilot study ( ትንሽ ጥናት በማድረግ ማውሰድ ይቻላል።

d- ማለት margin of error ስሆን፣ ይህን በአብዛኛው 0.05 (5%) ስሆን፣ ሁልጊዜ ግን አይደለም።

Formula

n= Z²xP(1-p)/D²

SAMPLE SIZE CALCULATION

Double population proportion
ይህ formula ለ cross sectional study( factor) እና Cohort study samples size calculation እንጠቀመለን።

Sample size for Objective 2(associated factors)

✳️ Associated factors የሚለው በ cross section study ሁለተኛ objective ስሆን Double population method በመጠቀም ለተመረጡ factors Calculate መድረግ ይኖርብናል።

ℹ️ ይህ መንገድ ለ Cohort studyም ጭምር ልያገላግል ይችላል።

💹 በዚህ መንገድ ለብዙ variables (associated factors) ወይም factors for exposed vs unexposed( cohort study) calculate ማድረግ ያስፈልጋል።
ለ Double population የተለያዩ Formula ስኖር proportion ወይም Standard deviation (mean) በመጠቀም calculate መድረግ ይቻላል።


Formula using proportion እና Assumption ከላይ ፎቶ ላይ ይመልከቱ።

ለ case control የሚሆን formula ያውቃሉ??

ለ case control እና ለ experimental study የሚሆን sample size calculation method ይዤ እመለሰለሁ።
👍27
❇️ምርምር / Research / ምንድን ነው?❇️

ከጽሑፍ መረጃዎች መገንዘብ እንደሚቻለው ምርመር /Research/ ለሚለው ቃል አንድ ወጥና የማይለዋወጥ ትርጉም አልተገኘለትም፡፡ ምክንያቱም መስኩ ሰፊና በተለያዩ ምሁራን የተለያየ ማብራሪያ ሲሰጥበት የቆየ በመሆኑ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአንዳንድ ምሁራን እጅግ በጣም ቀለለ ያለ ትርጉም ሲሰጠው በሌላ ጊዜና በሌሎች ምሁራን ደግሞ ላቅ ያለና ውስብስብ የሆነ ትርጉም ሰጥተውታል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ ምርምር አዲስ ዕውቀትን ለማግኘትና የተገኘውንም እውቀት እውነተኛነት ለማረጋገጥ ወይም በእለት ተእለት እንቅስቃሴ የሚያጋጥመንን ችግር መፍትሄ ለማበጀት ሲባል ሥርዓት ባለው ሁኔታ የተቀነባበረና ሆን ተብሎ የሚከወን የሰው ልጅ የተግባር
እንቅስቃሴ ነው፡፡

በዚህም መሠረት በምርምሩ ሂደት ውስጥ የችግሩ ምንነት ይለያል፣ ስልት ይቀየሣል፣ይቀነባበራል፣ መረጃ ይሰበሰባል፣ ይገመገማል፣ ይተነተናል፣ ብሎም የተገኘው ውጤት በተቀነባበረ መልክ ይገለፃል፡፡ ከዚህም ሂደት በመነሳት ምርምር ሳይንሳዊ ይዘት አለው ማለት ይቻላል፡፡

❇️የምርምር /Research/ ዓይነቶች❇️

ልዩ ልዩ የምርምር ዓይነቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ለዚህ ጽሑፍ አስፈላጊ ናቸው የተባሉትንና ዋና ዋናዎቹን በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

1️⃣. ታሪክ ነክ ምርምር / Historical Study/

በዚህ የምርምር ዓይነት ተማራማሪው ያለፈን ታሪክ በማጥናትና በመመዝገብ ዕውቀቱን ያዳብራል፡፡ ይህ ዓይነት ምርምር ሲያዩት ቀላል ይመስላል፡፡ ሆኖም ግን ተማራማሪው የተነሳበትን መላምት ለማረጋገጥ የተለያዩ መረጃዎችን አሰባስቦ ማስረዳት መቻል ይኖርበታል፡፡

📌 ለምሳሌ አንድ ተመራማሪ ስለ ኢትዮጵያ ትምህርት ታሪክ ሲያጠና ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ከንግሥት ዘውዲቱ ይልቅ አጼ ምኒሊክ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አድርገዋል የሚለውን ሃሳብ ይዞ ቢነሳ ሐሳቡ እውነት ወይም ሀሰት መሆኑን በተለያዩ ዘዴዎች መረጃዎችን ሰብስቦ በማገናዘብ አሳማኝ ውሳኔ ላይ መድረስ ይኖርበታል፡፡

2️⃣. ገላጭ ምርምር

ይህ የምርምር ዓይነት የአንድን ሁኔታ ትክክለኛ ገጽታ ለማወቅ ወይም በትክክል ለመግለጽ ሲባል መረጃዎችን ከመጽሐፍትና ከሌሎችም ጥናታዊ የጽሑፍ ምንጮች በማሰባሰብና የምልከታ መረጃዎችን በማጠናቀር ትንተና በማድረግ የሚያጠና ሲሆን ውጤቱን በስድስት ንዑስ ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
እነሱም፡-
❇️ ሀ/ ውሱን ጥናት /Case study/
❇️ ለ/ አወዳዳሪ ጥናት /Comparative Study Study/Studies/
❇️ ሐ/ ዕድገት ተኮር ጥናት/developmental
❇️ መ/ ተከታታየነት ያለው ጥናት/follow up studies/
❇️ ሠ/ ተዛምዶን የሚያሳይ ጥናት /correlational/
❇️ ረ/ አሣሽ ጥናት/Survey Study/

ℹ️ 2.1. ውሱን ጥናት /case Study/

ይህ ዓይነቱ ምርምር የአንድን የተወሰነ ሁኔታ የአለፈ ታሪክ ጨምቆ በማጥናት አሁን ላለው ይዘትና ጠባይ በማብራሪያነት መጠቀምን ይመለከታል፡፡
📌 ለምሳሌ ተማራማሪው ስለ አንድ ተማሪ ጠባይ ማጥናት ይፈልጋል እንበል፡፡ ተማሪው በት/ቤቱ አስቸጋሪ
ፀበይ/ባህሪ ቢኖረው የጥናቱ ትኩረት በዚሁ በተማሪው ጠባይ ላይ ይሆናል፡፡ በጥናቱ ሂደት ሊነሳ የሚችለው ዋናው ጥያቄ ይህ ተማሪ ለምን እንዲህ ሆነ የሚለው ነው፡፡

በዚህ መሠረት ሊሰጡ ከሚችሉ መልሶች አጥኚው መላ መምታት ይችላል፡፡ ከመላ ምቶቹ ውስጥ፡-
ከመምህራንና ተማሪዎች፣ የተቀባይነትና ጥሩ አመለካከት በማጣት፣ በትምህርቱ ውጤት ተስፋ በማጣት፣ ከቤተሰቦቹ አያያዝና አስተዳደግ የተነሳና ሌላም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

እንግዲህ የተማራማሪው ተግባር በልዩ ልዩ የምርምር ዘዴዎች ተጠቅሞ በየትኛው ምክንያት ተማሪው ለረብሻ እንደተገፋፋ ማወቅና መንስኤውን ካወቀ በኋላም ልጁ መልካም ጠባይ እንዲኖረው የተጠቀመባቸውን ዘዴዎች የጥናቱና ምርምሩ ውጤት ያደርጋቸዋል፡፡

ℹ️ 2.2. አሣሽ ጥናት / Survey study/

እንደዚህ ዓይነቱ ምርምር ስለአንዳንድ ማህበራዊ ክስተቶች መረጃዎችን አሰባስቦ በመተንተን ስለተጠናው ጉዳይ እውነተኛ ገጽታ መናገር የሚያስችል ነው፡፡
📌 ለምሳሌ ከአንደኛ ደረጃ ትም/ቤቶች ተማሪዎች በየጊዜው እየወጡ የሚቀሩት በምን ምክንያት ነው
በሚል ጥያቄ መነሻ ምርምር ማካሄድ ይቻላል፡፡

ውሱን ጥናት በተወሠነ ጉዳይ ላይ ጠለቅ ያለ ምርምር ማካሄድ ሲሆን አሣሽ ጥናት ደግሞ ሠፋ ባለ ርዕስ ጉዳይ ላይ በማተኮር አጠቃላይ መፍትሔ ለመሻት ነው፡፡

ℹ️ 2.3. አወዳዳሪ ጥናት /Comparative study/

ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ሁኔታዎችን ወስዶ ስለእያንዳንዱ ጉዳይ በጥልቀት በማወቅ አንዱ ከሌላው የሚለይበትንና አንድ የሚሆንበትን ሁኔታ በግልጽ ማሳየት የሚቻልበት የምርምር ዓይነት ነው፡፡

📌 ለምሳሌ ለአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን ሥልጠና የተሻለው ፕርግራም የቱ ነው በዲግሪ ወይም በዲፕሎማ ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሁለቱን
ፕሮግራሞች ደካማና ጠንካራ ጎን ለመለየት ከዚህ በፊት በሁለቱም ፕሮግራሞች የሰለጠኑና በሥራ ላይ ያሉትን መምህራን የሥራ ውጤት በጥንቃቄ በመገምገም፣ የተሻለውን ፕሮግራም ማወቅ ያስችላል ማለት ነው፡፡

ℹ️ 2.4. ዕድገት ተኮር ጥናት / Developmental Studies/

ይህ ጥናት በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ሕፃናት፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች በየእርከኑ የሚያሳዩት የባሕሪይ ለውጥ ወይም የአስተሳሰብና የአእምሮ ዕድገት ለውጥን የማጥናት ሥልት ነው፡፡
ተማሪው በየክፍል ደረጃው በአንድ ወይም ከአንድ በላይ ባሉ የትምህርት ዓይነቶች የሚያስመዘግባቸውን ውጤቶች ተከታትሎ ማጥናትን እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል፡፡

ℹ️ 2.5. ተከታታይነት ያለው ጥናት / Follow-up studies/

ይህ ሥልት አንድ የትምህርት መርሃ ግብር ውጤታማ ስለመሆኑ ለአንድ ሙያ የሰለጠኑ ሰዎች በመስክ የሚያሳዩትን ለውጥ ወዘተ የምንገመግምበት ዘዴ ነው፡፡ በአዲሱ የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ወቅት በሙከራ ት/ቤቶች በ1ኛ እና 5ኛ፣ በ2ኛ እና 6ኛ፣ በ3ኛ እና 7ኛ
በ4ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ሲካሄዱ የነበሩ ሂደታዊ ግምገማዎች እንደምሳሌ ሊጠቀሱ
ይችላሉ፡፡

ℹ️ 2.6. የተዛምዶ ጥናቶች /correlational studies/

የዚህ ዓይነቱ ሥልት
✳️ 1. ዕድሜ ከአእምሮ ጋር ያለውን ግንኙነት
✳️ 2. የአጠናን ሥልት ከትምህርት ውጤት ጋር ያለውን ዝምድና
✳️ 3. የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ውጤት ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት የሚኖረውን ዝምድናና
የመሳሰሉትን የምንዳስስበት ዘዴ ነው፡፡

3️⃣. የሙከራ ምርምር /Experimental Study/

ይህ እይነቱ ምርምር አንድን ሁኔታ በሙከራ አረጋግጦ ማየትን የሚመለከት ምርምር ነው፡፡

📌 ለምሳሌ በአፀደ ሕፃናት ፕሮግራም ውስጥ ካለፉና በቀጥታ ከቤታቸው ወደ አንደኛ ክፍል ከገቡ ሕፃናት ሒሣብን፣ አማርኛን፣ ሣይንስን፣ ወይም ሌላ ትምህርት የትኞቹ በይበልጥ እንደሚከታተሉ ሕፃናቱን ለይቶ በጥንቃቄ በመከታተል ማወቅ ይቻላል፡፡
ጥናቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ መረጃዎችን በጥንቃቄ መያዙ ለውጤቱ ትክክለኛነት እጅግ በጣም ወሳኝ ነው፡፡

📌 ለምሳሌ ከትምህርት ቤት ውጪ ተጨማሪ እገዛ ማግኘት አለማግኘታቸውን፣ የቤተሰብ ልዩነት አለመኖሩንና የቤተሰብ የኑሮ ሁኔታ ልዩነት ሁሉ መጤን ያለባቸው ነገሮች ናቸው፡፡

ምርጥ የResearch ቻናል።
https://t.me/researchRC
👍7313👎2
CHARACTERISTICS OF A GOOD ESSAY

A good essay will have the following characteristics:

Content

• A clear theme with evidence of background research
• A well organised structure with
📌o a clear introduction
📌o a well-structured argument
📌o a clear conclusion

• Good use of paragraphs
• Use of a range of discourse markers
• Good use of sources in the text including use of summary, paraphrasing or quotation
• Evidence of a critical approach to the reading sources


Language

• A good range of lexis
• Accurate use of lexis
• A good range of grammatical and sentence structures
• Accurate use of grammatical and sentence structures
• Appropriate use of a suitable formal academic style
• Avoidance of redundancy

Presentation
• Suitable layout and presentation, including:
📌o cover page:
▪️ module name & number
▪️ tutor name
▪️ student number (not name)
▪️ date of submission
▪️ word count o page numbers
📌o student number (not name) on every page
📌o use of paragraphs, not headings, bullet points or numbering o double line spacing o maximum font size 12
• Acknowledgement of sources in the text (in-text referencing)
• Accurate list of references at the end of the essay

PLEASE NOTE THE GIVEN INSTRUCTION AS WELL AS THE REQUIRED REFERENCES STYLE ALWAYS OVERRIDE THE PRESENTATION
👍103
1. Essay Structure

Writing an academic essay means putting a coherent set of ideas into an argument. Academic essays are linear—they offer one idea at a time—so you need a structure that presents your ideas in an order that makes the most sense to a reader. The structure of the essay is often determined by the topic of the essay. The topic dictates the information the reader needs to know and the order in which they need to receive it. Thus your essay's structure is unique to the main claim you're making.

Some essential elements of an essay include: introducing the argument, analyzing data, raising counterarguments, concluding. The introduction and conclusion have fixed places, but the other parts don't. A counterargument, for example, may appear within a paragraph, as a free-standing section, or before the ending. Background material (i.e: historical context, a summary of relevant theory or criticism, the definition of a key terms) often appears at the beginning of the essay, between the introduction and the first analytical section, but might also appear near the beginning of the specific section to which it's relevant. There is no set structure for an essay. Take your time, plan your argument, and the logical flow of your essay. Making an outline is the first step to getting the structure right.

2. Essential Elements
While there is no set structure for an academic essay, there are some essential elements that you need to include in your essay.

2.1: A clear, concise, and defined thesis statement that occurs in the first paragraph of the essay

Your thesis needs to present a focused and argumentative expression that avoids generalization and vagueness, while being defined enough to state your position on the topic. You are taking a position and defending it, not just summarizing what other people have written. The first goal of a thesis statement is to establish a position, the second is to explain how that position will be argued.

2.2: A well-defined and organized introduction that clearly shows the reader what your argument is

In the first paragraph of the essay, you should set the context by reviewing the topic in a general way. It is essential that the thesis statement be narrowed down to follow the guidelines of the essay topic. In some cases, the introduction paragraph can also be used to present why this topic is important, or why readers should care.

2.3: Clear and logical transitions between the introduction, body paragraphs, and conclusion

Transitions are the glue that holds the essay together. Without a logical progression, the reader is unable to follow the essays argument and the structure of the essay will collapse. Transitions should connect the content of the paragraph above and below. Without transitions, your essay is simply a series of unrelated arguments.

2.4: Body paragraphs that include evidence. Each paragraph is limited to the discussion of one idea/argument that supports the thesis of the essay

It must be clear how each paragraph and argument supports the thesis with the evidence collected during research. Do not simply restate what others have said. Your evidence is there to support your thesis, claims and your argument. It is not necessary to prove that your idea is the only “right” idea. Know what the research says and explain how these different ideas/positions are understood through the research. Each body paragraph should include:
• topic sentence
• evidence that will support your thesis/stance
• an explanation of the evidence and why it is important for your argument, and
• conclusions that can be drawn from the analysis of the evidence

2.5: A conclusion that does not simply restate the thesis, but readdresses it in light of the evidence provided

The conclusion of the essay leaves the most immediate impression on the mind of the reader. It must be effective and logical. Restate why the topic is important, review the main points of your essay, and review your thesis.
👍92
Don’t simply cut and paste from what you’ve already written; review your essay in a fresh way with new sentences and tone. It is okay to include a short discussion of additional research that may need to be done in light of what you found; but avoid asking unanswerable questions, or making broad sweeping statements that cannot be answered or accounted for.

3. Consider These Elements

A typical essay contains many different kinds of information, which can be located in many different places throughout the essay. These are not individual paragraphs, but elements that can come up throughout the essay. It's helpful to think of the different essay sections as answering a series of questions your reader might ask when encountering your thesis. Again, these are NOT separate sections, but questions that can guide your outline and writing.

3.1: "What?"

The first question to anticipate from a reader is "what": What evidence shows that the phenomenon described by your thesis is true? This question is usually answered within the first few paragraphs. Tell your reader what to expect by providing enough detail and background on the subject. But be careful: it shouldn't take up too much space of your finished essay. If it does, the essay will lack balance and may read as a mere summary or description of other people’s research.

3.2: "How?"

The follow up question to “what” is "how": How does the evidence support the thesis of the essay? How does the thesis stand up to the challenge of a counterargument? (i.e: are your claims backed by evidence? Are the claims specific enough to be true in the cases you’ve presented?) You could answer the “how” within each paragraph, and next to any claim and evidence that you present. It can appear anywhere in an essay, it does not have to be its own paragraph.

3.3: "Why?"

Your reader will also want to know what is at stake in your claim: Why does your interpretation of a phenomenon matter to anyone beside you? (this is your answer to “why does this matter?”). This question addresses the larger implications of your thesis. In answering "why", your essay explains its own significance. Although you might gesture at this question in your introduction, the fullest answer to it properly comes towards the end of the essay. If you leave it out, your readers will experience your essay as unfinished or insular
👍213🥰1
ጥናታዊ ጽሁፍ(Research) ሲሰራ መገንዘብ ያለብን ጉዳይ
የጥናቱን ዘዴ መለየት

የአንድ ትምህርት ነክ የሆነን ችግር / Educational Problem/ መንስኤ ለማወቅና
መፍትሔውን ለማየት የሚካሄድ ጥናታዊ ምርምር በሂደት ውስጥ ከዚህ ቀደም በመስኩ
የተሰማሩትን ምሁራን የምርምር ሥራ ውጤቶችን መመርመር ስለሚጠናው ችግር
አጠቃላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያግዛል፡፡ ሆኖም በመስኩ ከዚህ ቀደም መሰል ምርምር
ያልተካሄደ ከሆነ አግባብ ያለውን መረጃ በማሰባሰብ አዲስ ጥናት ማካሂድ አስፈላጊ
ይሆናል፡፡
አንድ የምርምር ባለሙያ ለምርምር አስፈላጊ የሆነውን መረጃ ለመሰብሰብ ሲያቅድ
ስለመረጃ ምንነት፣ ስለምንጮቹና ስለአሰባሰቡ ስልትና ስለመጠኑ ትክክለኛ ዕውቀት
እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡

❇️. የመረጃ አሰባሰብ/Data Collection/ ዘዴ
ለጥናቱ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማሰባሰብ መፍትሔ ለማፈላለግም ሆነ ችግሮችን በሂደት
እየፈቱ ለመሄድ ተገቢና በቂ መረጃ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን መረጃ ለማግኘት ደግሞ
ሳይንሳዊ በሆነ በንገድ በጥንቃቄ መሰብሰብ አለበት፡፡ ለዚህም የተለያዩ ዘዴዎች ስላሉ
እንደ ጥናት አይነቱ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

✳️ መረጃ /Data/ ምንድን ነው?
መረጃ ለምርምር ሥራ የሚያስፈልግ መሠረታዊ ጥሬ ሃሣብ ነው፡፡ ተመራማሪዎች
በምርምር ሥራቸው ሂደት ውስጥ ለማሰብ፣ ለመገመት፣ ለመተንበይ፣ አዲስ ንድፈ ሃሣብን፣
አዲስ የአሠራር መርህን ለማፍለቅ የሚችሉት መረጃዎችን መሠረት በማድረግ ነው፡፡
ለጥናታዊ ምርምር የሚቀርብ መረጃ ጥራትና ብቃት ለጥናቱ ውጤትና ከፍተኛ ደረጃ
መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመረጃ አሰባሰብና አጠቃቀም ሂደት ውስጥ የባለሙያው ቅድመ ዕውቀት ግምት፣ ልምድና አመለካከት የመረጃን ትክክለኛ መሆንና አለመሆን ሊጠቁሙ
የሚችሉ ሁኔታዎች ናቸው፡፡
ለምርምር ሥራ የሚሰበሰብ መረጃ ትክክለኛ መልኩን ያልያዘና የተዛባ ከሆነ የጥናቱ
ውጤት የተዛባና የተሳሳተ አቅጣጫ የሚያመላክት ይሆናል እንዲይዝ ያደርገዋል፡፡ ይህም
ለምርት፣ እድገትና አጠቃላይ ልማት አደገኛ ሁኔታን ሊፈጥር ስለሚችል ባለሙያው
ለሚሰበስበው መረጃ ጥራትና ብቃት ልዩ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል፡፡

✳️ የመረጃ ምንጮች /Source of data/
ለጥናታዊ ምርምር የሚያስፈልግ መረጃ ከሁለት ዋና ዋና ምንጮች ሊሰበሰብ ይችላል፡፡
እነርሱም ርቱዕ ምንጭ / primary source/ ኢርቱዕ ምንጭ /Secondary source/ በመባል ይታወቃሉ፡፡
ርቱዕ የመረጃ ምንጭ / primary source/ ለምርምር ሥራ ተፈላጊ የሆነ ጥሬ መረጃ
በጽሁፍ መጠይቅ፣ በቃል መጠይቅ፣ በመስክ ምልከታ ወዘተ… አማካኝነት በቀጥታ የሚገኝ
ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ መረጃ ከሚገኙባቸው ምንጮች ውስጥ፡-
🖍 በቀጥታ ከሚመለከታቸው ሰዎች
🖍 ጥናታዊ ምልከታ የሚደረግበት የመስክ መረጃ /Field Data Source/
🖍 አንዳንድ ደብዳቤዎች፣ ሪፖርቶች፣ ማስታወሻዎች ወዘተ… ከርቱዕ ምንጭ ሊመደቡ
ይችላል፡፡ እነዚህ መረጃዎች ከመጀመሪያ የመረጃ ባለቤቶቻቸው የመነጩ
በመሆናቸው ከኢርቱዕ ይለያሉ፡፡
🖍 ኢርቱዕ የመረጃ ምንጭ (Socondary Source) አንዳንድ መጽሐፍት፣ መጽሔቶችና
የመሳሰሉት በጽሑፍ መልክ የሚገኙ ዶክመንቶች ከኢርቱዕ የመረጃ ምንጮች
ይመደባሉ፡፡ እነዚህ ምንጮች የብዙ ምሁራንና የምርምር ባለሙያዎችን ጥናታዊ
ሪፖርቶች ፍሬ ነገር በማሰባሰብና በመጭመቅ የተዘጋጁ በመሆናቸው ለምርምር
ሥራ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ፡፡ ከኢርቱዕም ሆነ ከርቱዕ ምንጮች የሚገኘው
መረጃ የአዘጋጁን ወይም የመረጃ ሠጭውን መብት በመጠበቅ በትክክል መጠቀስ
ይኖርበታል፡፡ አዘጋጅ ሳይጠቀስ የሚወሰድ ቀጥተኛ ያልሆነ የመረጃ ምንጭ
በምሁራን ዘንድ በግልጽ የሚታይ የሐሳብ ስርቆት /plagiarism/ ይባላል፡፡ ይህም በምርምር ዓለም እጅግ የተወገዘ ድርጊት በመሆኑ ምርምር አድራጊዎች ልዩ
ጥንቃቄ ሊያደርጉበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

✳️ የመረጃ አሰባሰብ ስልት /Techniques of data collection/
ለጥናታዊ ምርምር የሚያስፈልጉ መረጃዎች በተለያዩ ዘዴዎች አማካኝነት ይሰበሰባሉ፡፡
ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
🖍 የጽሑፍ መጠይቅ (Questionnaire)
🖍 የቃል መጠይቅ (Oral Interview)
🖍 የመስክ ምልከታ (Observation)
🖍 የተመረጠ ቡድን ውይይት (Focus Group Discussion)
እነዚህ ዘዴዎች የራሳቸው የሆነ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ስላላቸው የተመራማሪውን
ጥንቃቄና ትኩረት ይሻሉ፡፡

✳️. የጽሑፍ መጠይቅ(Questionnaire)
ይህ ዓይነቱ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ከሌሎቹ ዘዴዎች አንፃር ሲታይ አብዛኛውን ጊዜ
አገልግሎት ላይ የሚውል ዘዴ ነው፡፡ የጽሁፍ መጠይቅ ሲዘጋጅ የሚከተሉት ዋና ዋና
ነጥቦች መታወስ ይኖርባቸዋል፡፡
🖍 ብዙ ጊዜ መጠይቆቹ የሚቀርቡት አጥኝዎች በቀጥታ በሌሎበት ሊሆን ስለሚችል
ጥያቄዎቹ በአጫጭር ዓረፍተ ነገሮችና በቀላል ቋንቋ መቅረብ ይኖርባቸዋል፣
🖍 ሁለትና ከሁለት በላይ ጥያቄዎች በአንድ ላይ ባይቀርቡ ይመረጣል፣
🖍 የጥያቄዎቹ አቀራረብ ተገቢ የሆነ ቅደም ተከተል ያለውና ተጠያቂዎች ያለችግር
ተገንዝበው የሚመልሷቸው ዓይነት መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
🖍 ጥያቄዎቹ በተጠያቂዎች ዘንድ ግምታዊ፣ የተዛባና የተሳሳተ መልስ እንዲሰጥ
የሚጋብዙ እንዳይሆኑና በማያሻማ ሁኔታ የተፈለገውን መልስ/መረጃ/ በትክክል እንዲጠቁሙ የሚያስችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
🖍 ጥያቄዎቹ መልስ ሰጭዎቹን የሚያሰለቹና የተንዛዙ መሆን የለባቸውም፡፡ የጽሑፍ
መጠይቆች ለተጠያቂዎቹ እንደፈተና የሚቆጠሩና የሚያስጨንቁ ዓይነት ሳይሆን
ማራኪነት ያላቸውና የሚጥሙ ነገር ግን ማሰብን የሚጠይቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
🖍 የጥያቄዎቹ ይዘት መልስ ሰጭዎቹን የሚያስደነግጡ፣ የሚያንቋሽሹ ወይም
የሚያስወነጅል መሆን የለበትም፡፡ በዚህ አኳያ የመልስ ሰጭዎችን ኢኮኖሚያዊና
ማኀበራዊ ዕድገት ማጤን አስፈላጊ ነው፡፡
🖍 መጠይቆቹን የሚሞሉ ሰዎች ባደረጉት ትብብር ለጥናቱ ጠቃሚ አስተዋጽኦ
ማድረጋ ቸው ተጠቅሶ ለዚህም ምስጋና እንደሚገባቸው በሸኝው ደብዳቤ ወይም
በመጠይቁ ራስጌ ላይ መግለጽ ጠቃሚ ነው፡፡
🖍 መልስ ሰጭዎች በማወቅም ሆነ ባለመወቅ ሊሰጡ የሚችሉትን የተሳሳተ መልስ
ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ጥያቄዎች በመጠይቁ ውስጥ መታከል አለባቸው፡፡
ለምሣሌ
የቤተሰብ የገቢ መጠን በሚመለከተ የቀረበ ጥያቄ ካለ በሌላ ጎን የወጭ መጠንን
የሚጠይቅ ጥያቄ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
🖍 ለጥያቄዎች የሚሰጡ መልሶች በምርጫ መልክ ቢቀርቡ ይመረጣል፡፡ ምርጫ
የሌላቸው
ጥያቄዎች ከሆኑ ደግሞ አጫጭር መልስ የሚሰጣቸው ዓይነት ቢሆኑ የተሻለ ነው፡፡
ለጥናታዊ ምርምር ብቁ መረጃ ለማሰባሰብ የሚያስችል የተሟላ መጥይቅ ለማዘጋጀት
በቅድሚያ የሙከራ መጠይቅ ተዘጋጅቶ መሠራጨት ይኖርበታል፡፡ ከመጠይቁ በሚገኙ
የማሻሻያ ጥቆማዎች አማካኝነት ድጋሚ የሙከራ መጠይቅ ለተመሳሳይ ዓላማ
ይሠራጫል፡፡ መጠይቁን ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ ማሻሻል ራሱን የቻለ አድካሚ ሥራና
👍291
ረጅም ጊዜ የሚፈጅ ቢሆንም ለሥራው ጥራት ሲባል ሳይታለፍ መከናወን ያለበት ተግባር
ነው፡፡
✳️ የቃል መጠይቅ/Interview/
ቃለ መጥይቅ ብዙውን ጊዜ ከጽሑፍ መጠይቅ ጋር አብሮ የሚሄድ ሲሆን በዚህ ዘዴ
አማካኝነት የሚገኝ መልስ እንደጽሑፍ መጠይቅ ውሱን ሳይሆን ሰፋ ያለ ይሆናል፡፡ ሆኖም
ለጽሑፍ መጠይቅ እንደሚደረግ ሁሉ ለቃለ መጠይቅም ዝግጅትና ዕቅድ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ጥያቄዎችም አመክኖን/logic/ በተከተለና ተገቢ በሆነ ቅደም ተከተል
መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
በቃለ መጠይቅ አማካኝነት የሚገኝ መልስ በጠያቂውና በተጠያቂው መካከል በማካሄድ ነፃ
ውይይት ነው፡፡ ለዚህም በሁለቱ መካከል የተቀራረበና መተፋፈር የሌለበት ግንኙነት
እንዲኖር ጠያቂው ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ጠያቂው ሞቅ ያለ ፈገግታና ትህትና
የተሞላበት አቀራረብ ቢኖረው ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ይረዳዋል፡፡ በቃለ መጠይቅ
ወቅት ተጠያቂውን የሚያስከፉ አባባሎች መቅረብ የለባቸውም፡፡ በተጨማሪም ጠያቂው
ግትርነትንና በውይይት ውስጥ የተደጋገመ ጣልቃ ገብነትን ማስወገድ ይኖርበታል፡፡
ከውይይቱ የሚገኙትን መልሶች/ሃሳቦች/ ውይይቱ በሚካሄድበት ወቅት መመዝገብ ወይንም
በቴፕ መቅዳት በተጠያቂው በኩል ጥርጣሬንና ፍርሃትን ሊያስከትልና አንዳንድ ሃሳቦችን
ሊደብቅ ስለሚችል ቢቻል መልሶችን/ሃሣቦችን/ ከውይይቱ በኋላ መመዝገብ ይመረጣል፡፡
✳️ የመስክ ምልከታ (Field Observation)
የመስክ ምልከታ የተቀነባበረ በቅድሚያ ለታወቁና ለታቀዱ ጥያቄዎች መልስ ከማግኘት
አኳያ የጠለቀ ማሰብንና መመራመርን ተመርኩዞ የሚካሄድ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም
በየዕለቱ በዘልማድ ከሚካሄደው ምልከታ በጣም የተለየ ነው፡፡
በመስክ ምልከታ አማካኘነት የሚገኝ መረጃ ሪፖርት ቀደም ሲል በመስኩ ከነበሩ መሪ
ንድፈ ሃሳቦችና ከጥናቱ መነሻ መላምት ጋር ተገናዝቦ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ለጽሑፍና
ለቃለ መጠይቅ እንደሚደረገው ሁሉ የመስክ ምልከታ ሪፖርት በጥንቃቄ ተመዝግቦ
አጥኚው እንደ ማስረጃ ሊያቀርበው ይችላል፡፡
የጽሑፍ መረጃ (Related literature) እና ፈተና (Test) ሌሎች ተጨማሪ የመረጃ
መሰብሰቢያ ስልቶች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡

በቀጣይ የናሙና አመራረጥ (Sampling) ይቀጥላል...........
👍44👎5
ለተመራቂ ተማሪዎች (Research info)፦
#ጥሩ_የጥናት_አቀራሪብ_መረጃ
Good research presentation (Defense)
.
ጥሩ አቀራረብ እንዲያደርጉ የሚረዱዋችሁን አንዳንድ ነጥቦች።
.
ጥናታዊ ጽሑፍን በጥሩ ሁኔታ ለማቅረብ (good presentation) ከሚረዱ ቁልፍ ነገሮች አንዱ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (PowerPoint) ነው። ጥሩ ማብራሪያ ነጥብ (power point) እንዲኖርዎ ደግሞ እነዚህን ይጠቀሙ፦
.
#1ኛ. ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (Powerpoint) ብዙ ስላይድ አይኑረው። በ15 ደቂቃ ለማቅረብ እስከ 15 በዛ ከተባለ ከ20 እስከ 25 ማሳያ (slide) እጅግ በቂ ነው።
.
#2ኛ. ማሳያ (slide) በብዙ ጽሑፍ የተጠቀጠቀ መሆን የለበትም። ፎቶዎችንናቃላት ሰንጠረዦችን የበለጠ በደምብ ይጠቀሙ። "አንድ ፎቶ ወይም ሰንጠረዥ ከ1000 በላይ ገላጭ ነው" የሚለውን አባባል ልብ ይበሉ።
.
#3ኛ. መብራራት የሚፈልጉ ቃላትን ብቻ በርዕስ መልክ ይጻፉ። ማብራሪያቸውን የግድ ማሳያ (slide) ላይ መፃፍ አይጠበቅብዎትም።
.
#4ኛ. የሚቀርበው ጥናት እጅግ ሰፊ ይዘት ያለው ቢሆን ለመመጠን ሳይቸገሩ በማሳያ (slide) ላይ ለመዳሰስ ማሳያዎትን (slide) በክፍል በክፍል (part) ይክፈሉት።
....... Introduction (መግቢያ)
....... Main Body (ሃተታ) as Discussion
....... Conclusion ( መደምደሚያ) ያድርጉት።
.
#5ኛ. ከአንዱ ማሳያ (slide) ወደ ሌላው ሲዘዋወሩ (ሲሸጋገሩ) ጊዜ እንዳይወስድብዎ (እንዳይንቀረፈፍ) Animation ባይጠበሙ ይመረጣል።
.
#6ኛ. በማሳያዎ (slide) ላይ ሚሰፍሩ ጽሁፎች በትንሹ በ24 መጠን (Font Size) መሆን ይጠበቅባቸዋል።
.
#7ኛ. የጽሑፎቹ ቅርጽ አይነት (Font type) "Time new roman" ቢሆን የተሻለ ነው። ከዚህ ካለፉ ግን Nyala እና Countur ይጠቀሙ።
.
#8ኛ. የማሳያ (slide) ጽሑፎች እጅግ ብዙ የቀለም (Font colour) ዝብርቅርቅ የበዛበት ከሆነ አትኩሮትን ግራ ስለሚያጋባ ብዙ ቀለም አይጠቀሙ። ከተቻለ በአንድ አይነት ቀለም ቢሆን ካልሆነ ግን ልዩ ገለጻ የሚፈልጉትን ለማቅለም ሁለት ቀለሞች በቂ ናቸው።
.
#9ኛ. አስተያየት (professional recommendation) በሚለው የጥናት ክፍልዎ ውስጥ ከተማሩበት አንጻር ለደረሱባቸው ችግሮች መንገዶችን ለመጠቆም ይሞክሩ ይንጅ "
#ድርጅቱ_ይህንን_ችግር_ማስተካከል_አለበት " የሚል ደረቅ ትዕዛዝ ከማስገባት ይቆጠቡ። የሚያስተካክለው እንዴት ባለ ዘዴ፤ መቼ፣ በማን፣ የት፣ .. እንደሆነ ሙያዊ ድጋፍ መስጠትዎን አይርሱ።
.
. ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (Power point) እንዲህ ካዘጋጁ በኋላ፦
.
#1ኛ. አለባበስዎን ያስተካክሉ። እርቃንን የሚያሳይ፣ ተመልካችን የሚያሳፍር፣ ለመታደም የመጣን ሰው ሰላም የሚነሳ፣ ማንነትን የማይገልጽ ልብስ ለእርስዎ የሚኖረውን ክብርና ዋጋ በእጅጉ ይቀንሳል። ጥሩ አለባበስ በራስ መተማመንንም ከፍ ያደርጋል። ወንዶች ሙሉ ልብስ (በተለምዶ 'አምባሳደር' የምንለው) ሴቶች ቢያንስ እስከ ጉልበታችሁ የሚዘልቅ የጨርቅ ጉርድ እና ኮት ወይም እጀሙሉ ዠሚዝ የተሻለ ነው። እንደ ገምጋሚው ፍላጎት ሊለይ ይችላል እንጂ ባሕልንና ሀገርን የሚገልጽ ቢሆን በግሌ ደስ ይለኛል።
.
#2ኛ. ለንግግር ቅላጼ (pronounsation) ከመጨነቅ ይልቅ የሚፈልጉትን ሀሳብና ማብራሪያ ለማስረዳት መሞከር የተሻለ ነው። የቋንቋ ተማሪዎች በዋና የቋንቋ መስክ፣ ከዚያ ውጪ ያላችሁት ደግሞ በሚችሉት የእንግሊዘኛ ቃላት ለማቅረብ ይሞክሩ።
.
#3ኛ. ያዘጋጁትን ማሳያ (slide) ከማቅረብዎ በፊት ደጋግመው ያንብቡ።
.
#4ኛ. የማያውቁትን ነገር ከመናገርም ሆነ በየማሳያ (slide) ላይ ከመጻፍ አጥብቀው ይቆጠቡ።
.
#5ኛ. በሚያቀርቡበት ጊዜ በክፍል ውስጥ ያሉትን ሰዎች በአይን ቅኝት መቆጣጠርዎን አይርሱ። ፈጽሞ አይደንግጡ አይፍሩ። የተሰበረቡት ሰዎች ድሮ የነበሩ እንጂ እንደ አዲስ ፍጥረት አያስቧቸው።
.
#6ኛ. ለሚጠየቁት ጥያቄ በተረጋጋ ስሜት ሆነው ከጥናትዎ አንጻር የተደረሰበትን ውጤት አገናዝበው ይመልሱ።

"A good presentation should be like a women's skirt long enough to cover the subject and short enough to create interest" Winston Cherchil
.
.
.
መልካም እድል!!!!
👍525😁1
Research proposal Guideline.PDF
359.1 KB
ሪሰርች Guideline በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ!
👍15