Remote IT ሪሞት አይቲ
2.03K subscribers
975 photos
18 videos
26 files
557 links
✔️በቻናላችን✔️

💫ሰለ ክርፕቶ ካረንሲ
📲 የAndroid መተግበሪያ
💻 የPC SoftWare
📌 ስለ ኮምፒዩተር እና ፕርንተር


👉ለአስተያየትና ሌሎች ፕሮግራሞችን ለማግኘት ይቀላቀላሉ

@remoteict
Download Telegram
የቴሌግራም ፕሪሚየም ምንድን ነው እንዴትስ ይከፈላል
~
የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ቁጥር በፍጥነት እያደገ ነው:: በጣም ታዋቂም እየሆነ ነው:: በአሁኑ ወቅት የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ቁጥር 900 ሚሊዮን አልፏል:: በዓመታዊ የአዳዲስ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከWhatsApp ቀጥሎ ሁለተኛ ነው - ቴሌግራም::

ቴሌግራም የብዝሃ-ፕላትፎርም (Multi Platform) አገልግሎቶች መስጫ ነው:: የቪዲዮ ኮንፈፍረንስ ለማካሄድ፣ በድምጽ ብቻ በቡድን ወይም በግል ለመወያየት፣ የጽሁፍ መልእክት ለመለዋወጥ፣ የቀጥታ ወይም የተቀረጸ የቴሌቭዥን ስርጭት ለማካሄድ፣ ገንዘብ ለመላላክ፣ ግዢ ለማካሄድ፣ ክፍያዎችን ለመፈጸም፣ ማናቸውም ፋይል ለመላላክ፣ ክለውድ ላይ የተፈለገውን ያህል የግል ፋይል ለማስቀመጥ (Saved Messages)፣ ቴሌግራም የተሰራበትን ጨምሮ የበርካታ WebApps #Code በነጻ ለመጠቀም (Open Source ነው) . . . ያስችላል:: ብዙ ሰዎች የማያውቁትና የማይጠቀሙበት ደግሞ ልክ እንደ #googleplay እና #Apple_Store ራሱን የቻል #የWebApp Store ያለው መሆኑ ነው:: (ማስፈንጠሪያ link 👇
https://www.tapps.center/ ነው፤ አስፈንጥራችሁ እዩት፤ Webapp ስለሆኑ በስልክም ሆነ በኮምፒዩተር ላይ ይሰራሉ)::
~~

ቴሌግራም ፕሪሚየም ገደቦችን በእጥፍ ያሳድጋል። ለምሳሌ በመደበኛው Telgram 11 Username መያዝ ወይም 11Channels/Groups መክፈት ይቻላል፤ #በPremium Telegram ግን 21 Username መያዝ ወይም 21 Channels/Groups መክፈት ይቻላል፤ በተመሳሳይም በመደበኛው መላክ (Upload) ማድረግ የሚቻለው ፋይል 2GB ሲሆን #በpremium 4GB ፋይል #upload ማድረግና ለሌላሎች መላክ ይቻላል። #Upload እና #Download ሲደረግም ከመደበኛው የበለጠ ፈጣን ነው። ሌሎችም በርካታ በመደበኛው የሌሉ አገልግሎቶች አሉት። በመሆኑም ሰዎች #Premium_Telegram ቢጠቀሙ ይመረጣል። (እኔ አገልግሎቱ ከተጀመረበት አንስቶ ያሉኝን ሁለት የቴሌግራም አካውንቶች #Premium ነው የምጠቀመው)

በአሁኑ ወቅት የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ቁጥር 900 ሚሊየን ያለፈ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የቴሌግራም ፕሪሚየም የሚጠቀሙት አምስት ሚሊዮን የሚሆኑት ናቸው።

ኢትዮጵያ ውስጥም ብዙ ሰዎች የቴሌግራም ፕሪሚየም መጠቀም ይፈልጋሉ:: የመክፈል አቅምም አላቸው:: ነገር ግን እንዴት መክፈል እንዳለባቸው አያውቁም:: ቴሌግራም ያለንበት #Location ስለሚያውቅ #Premium መክፈያ ብር መጠን ያሳያል:: ሆኖም አይሰራም:: መክፈል የሚቻለው #በUSD ወይም #በTON (የቴሌግራም ዲጂታል ገንዘብ) ነው:: በቴሌግራም አካውንታችሁ በኩል የሚከፈለ #በUSD ብቻ ሲሆን በየጊዜው ቅናሽ ስለሚደረግ ከ48-60 USD ይደርሳል::

በጣም ርካሹ የክፍያ መንገድ #በToncoin ሲሆን ወደ #USD ሲቀየር $29 አካባቢ ነው:: ስለሆነም የዚህ አከፋፈል #በScrreshot ቅደም ተከተል አስቀምጬላችኋለሁ::

1. Tonkeeper wallet ከGoogleplay መጫን (https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ton_keeper ወይም የደስክቶፕ/ላፕቶፕ https://www.tapps.center/ ላይ ታገኛላችሁ)
#ጥንቃቄ - ስትጭኑ 24 ቃላት ይሰጣችኋል:: በጥንቃቄ አስቀምጧቸው:: #Signout ካላችሁት ወይም ፓስወርድ ከጠፋባችሁ ያለእነዚህ ቃላት መግባት አትችሉም::

2. https://fragment.com/ በማንኛውም #Browser ስትከፍቱት ከታች #ScreenShot - 1 ላይ የተመለከተው የቴሌግራም Username እና Anonymous ቁጥር መሸጫ ድረገጽ ይመጣላችኋል:: በስተቀኝ Connect Ton የሚለውን ስትነኩ ከTonkeeper ጋር የምትገናኙበትን ሂደት ይጀምራል:: የሚጠይቃችሁን በማድረግ ታገናኙታላችሁ:: በመቀጠል በዚህ ስክሪንሾት የተሰመረበት #Premium የሚለውን ትነካላችሁ:: #ScreenShot - 2ን ያመጣላችኋል:: Buy Premium for a User የሚለውን ትጫናላችሁ:: #ScreenShot - 3 ይከተላል:: ከሚመጡት የዓመት፣ የስድስት ወር ወይም የሦስት ወር አንዱን ትመርጣላችሁ። ለራሳችሁ ከሆነ Buy for myself የሚለውን ትነካላችሁ። (አካውንታችሁ Username ሊኖረው ይገባል)።

የምትገዙት ለሌላ ሰው ከሆነ ግን የሰውዬውን Username copy አድርጋችሁ በተከበበው ቦታ ላይ Past ታደርጋላችሁ። . . . የክፍያ ሂደቱ ይጀመራል። Tonkeeper ላይ ክፍያ accept እስክታደርጉ ድረስ ትቀጥላላችሁ። ሁሉም ሂደት ከክፍያ መፈጸም ጋር ይጠናቀቃል። (በጣም ቀላል ሂደት ነው)።

ምናልባት Toncoin ከየት ነው የምናመጣው የምትሉም አትጠፉም። መቼስ ከሰማይ እንዲዘንብ መጠበቅ የለባችሁም። በቴሌግራም ዋሌታችሁ ባለው የግብይት መንገድ #USD ገዝታችሁ እዛው ወደ TON Exchange በማድረግ ወደ Tonkeeper መላክ ትችላላችሁ::

#ማሳሰቢያ
እኔ የማጋራው ለግንዛቤ ነው:: ከመወሰናችሁ በፊት የራሳችሁን ጥናት ማድረግና አዋጪ መንገድ መምረጥ የራሳችሁ #ፋንታ ነው:: በተለይም በሂደቱ የምትፈፅሙት ትንሽ ስሕተት የማይመለስ ጉዳት ሊያስከትልባችሁ እንደሚችል ብጽሞና ልትገነዘቡ ይገባል::
.
.
.
የቴሌግራም ቻናሌን join አድርጉ👇👇
https://t.me/remoteict