Quantum Computer Technology
94 subscribers
13 photos
2 files
14 links
ወቅታዊና አዳዲስ የቴክኖሎጂ መረጃዎች እንዲደርሶ ይህንን ቻናል በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Download Telegram
Channel photo updated
#HackingAlert

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ በርካታ ጋዜጠኞች እና ሌሎች የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች በብዛት ሀክ እየተደረጉ ነው!

በተለይ ለአለም አቀፍ ሚድያዎች የሚሰሩ ጋዜጠኞች ላይ ያተኮረ የሚመስለው ይህ ሀኪንግ የተከሰተው በፅሁፍ መልእክት የሚላክ ኮድን በመቀያየር ምክንያት እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ ተረድቷል።

ከሚያውቁት ሰውም ቢሆን ምንም አይነት ኮድ ባለመቀያየር ጥንቃቄ ያድርጉ።

@quantum_tech5
#ኢትዮ ሳትን መጠቀም ምን ጥቅም አለው ጉዳቱስ?
*********
ኢትዩ ሳት አሁን ላይ ሲጠቀሙ አሁን ናይል ሳት ላይ የማታገኟቸውን አማርኛ ቻናሎች ያገኛሉ ለምሳሌ ebs cinema ebs musica ,Soder, Jtv እና ሌሎችም እናም ተጨማሪ የኳስ ቻናሎችን ያገኛሉ ከናይል ሳት የጠፉ የአማርኛ ቻናሎችን ያገኛሉ ሰህንዎን ወደ ኢትዮ ሳት ሲገለብጡ የሚያጧቸው ቻናሎችም አሉ ለምሳሌ,Kana tv, Asham Nahooእንዲሁም ሀይማኖታዊ ቻናሎችን ያጣሉ ይህም ማለት ኢስላማዊ ቻናሎችን Africa tv, zawya tv, nesiha tv, minber tv, BST tv.... ከኦርቶዶክስ Eotc from protestant christarmy marciltv, beteltv, araratv....ያጣሉ ሀይማኖታዊ ቻናሎች ወደ ኢትዮ ሳት ይገባሉ የሚል ተስፋ አለን!! እናም ስሀንዎን ከማስገልበጥዎ በፊት በደንብ ሊያስቡበት ይገባል!!።
HD /SD= HD ሪሲቨር ካለው ኢትዮ ሳትን ሙሉ በሙሉ መጠቀም ይችላሉ አንዳንድ ካጋጠሙኝ | ነገሮች ሪሲቨራቸውን HD ካደረጉ የሀይማኖት ቻናሎችን በኢትዮ ሳት መግኘት የሚቻል የሚመስላቸው አሉ ይህ ስህተት ነው!! የሀይማኖታዊ ቻናሎች በኢትዮ ሳት ስርጭት ስላልጀመሩ ሪሲቨርዎ HD ቢሆንም የሀይማኖት ቻናሎችን(ኢስላማዊ) ማግኘት አይችሉም ግን የኳስ የዜና እና የፊልም ቻናሎችን ያገኛሉ mbc bollywed, mbc2, B4U Aflam
ZEE Aflam. የዜናም BBC, CNN,
Al-Jazeera, እነዚህን ቻናሎች በ HD ማግኘት ይችላሉ፡፡
SD? ሪሲቨርዎ SD ከሆነ ደግሞ ኢትዩ ሳት ላይ መጠቀም የሚያስችልዎት 14 ቻናሎችን ብቻ ነው ከዚያ ውጭ በፍፁም አይገባለዎትም አንዳንድ ሰዎች ዝም ብለው ይገለብጡና እንደገና ሀሳባቸውን ይቀይሩና ወደ ናይል ይመለሳሉ። ማለትም ለሁለት ጊዜ ለወጪ ይዳረጋሉ ማለት ነው።
በ SD የኳሶቹንም የፊልሞቹንም የዜናዎቹንም ማግኘት አይችሉም ማግኘት የሚችሉ ከታች የተዘረዘሩትን ቻናሎች ብቻ ነው እናም ዲሽዎን ሲያስገለብጡ የዲሽ ባለሙያዎ በቂ ማብራሪያ እንዲሰጥዎ ይጠይቁ ሁሉንም ነገር አምነዎበት ቢሰራልዎ የተሻለ ይመስለኛል።
ኢትዮ ሳት ላይ በ SD ሪሲቨሮች የሚሰሩ 14 ቻናሎች
ETV News SD
ETV ENT SD
ETV Languages SD
Amhara TV SD
Balageru SD ARTS SD
EBS SD Ahadu SD
FANA TV SD
Walta Tv SD
Afri Health SD
Arts Tv
Ahadu Tv
South Tv SD
ETHISAT DEMO SD
OBN SD

ለሌሎች እንዲደርስ # ሼር ያድርጉ

@quantum_tech5
የቡዙ ሰው ጥያቄ የሆነው
📡የኢትዮ ሳት (nss12 57°e) አሰራር እና የቻናሎቹን ዝርዝር ከነፍሪከኴንሲያቸው ዘርዘር አርገን አቅርበንላቹኋል።
እንናተም ለወዳጆቻቹ ሁሉ #ሼር በማረግ አብሮነታቹን አሳዩን።
👇👇 ዝህ👇👇👇
በመጀመሪያ ፋይንደር ወይም ሪሲቨራችን ላይ
11105 H 45000 tp
እንሞላለን!!! በመቀጠል
የዲሻችንን የፊት አቅጣጫ ልክ ከናይል (nilesat7°w) አቅጣጫ ተቃራኒ በማረግ እናስተካክላለን! ከዛ ከ50 እስከ 60 ዲግሪ ከፍ እና ዝቅ በማረግ በጣም በትንሹ ወደ ግራ ዞሮ ስናደርግ Q መግባት ይጀምራል!
ከዛ ዲሻችንን አጥብቀን LNBውን ዞር ዞር ስናደርግ Q በደንብ መግባት ይጀምራል ማለት ነው።
📺TV ቫርዚሽ ላላቹ ደሞ በቀላሉ አንድ ተጨማሪ LNB ከላይ በመደረብ ብቻ ኳሊቲ በቀላሉ ይገባላቹኋል።
ይህም ማለት የእግር ኳስ እና የሀገርኛ ቻናሎችን ያለተጨማሪ የዲሽ ጋጋታ በአንድ የዲሽ ሳህን ብቻ ማግኘት ትችላላቹ ማለት ነው።
📡ኢትዬ ሳት ወይም (NSS 57) ላይ የሚገብ የቻናል ዝርዝሮች
11105
H
45000
👆በዚህ👆 Tp
ቀኑን ሙሉ አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ሀገርኛ ፊልሞችን የምታገኙባቸው
📺SODERE TV
📺EBS cinima
ቀኑን ሙሉ ሀገርኛ ዘፈኖችን
📺EBS muzika
እና ሌሎች ሀገርኛ
📺Tv ethiopa
📺EBS HD
📺walta tv
📺afri Health
📺Balageru
📺Fana tv HD
📺Asham tv
📺Ahadu tv
📺Tv 9 HD
📺dire tv
💏Ethiopan lijoch
👇ፕሮቴስታንት
📺Amaniload tv
📺presence tv
📺Evangelical tv
📺Moaa
📺CM TV
📺7 spirits tv
🌱 የሞባይል ሃርድዌር ክፍል

ለመሆኑ ሃርድዌር ማለት ምን ማለት ነዉ ?

#ሃርድዌር ፦ ማለት በዓይናችን ማያት የምንችለው የሞባይል ክፍል ነዉ በተጨማሪ በእጃችን መዳሰስ መንካት የምንችለው ክፍል ነዉ ።

እሺ በእጃችን መደሰስ የምንችለው የሞባይል ክፍሎች እነማን ናቸዉ አንድ በአንድ የተወሰኑትን እንዳስስ እስክ ....

🙏 1ኛ ቻርጀር ኮኔክተር ፦ ማለት ስልካችንን ከመብራት ጋር የምያገናኝ ስልካችን ቻርጅ እንድያደርግ የምያደርግ የሞባይል ሃርድዌር ክፍል ነዉ
ቻርጅ ኮኔክተር ከተበላሸ ስልካችን ቻርጅ አያደርግም በተጨማሪ ስልካችን ቻርጅር እያመርጠ ያስቸግርናል......

🙏 2ኛ ባቲር ኮኔክተር ፦ ማለት ባቲሪያችን ከሞባይሉ ተገጣጥሞ እንድዝ የምያደርግ ጥርስ ነዉ ይህ ማለት አንደንዴ በአንደንድ ስልኮች ጥርሶቹ አራት ይሆናል አብዛኞቹ ስልኮች ግን በለ ሦስት ጥርስ ነዉ በአጭሩ ሞባይላችን የለባቲር ኮኔክተር አይሰራም....

🙏 3ኛ ጆሮ ማይክ ፦ ማለት ደግሞ በስልካችን ሰዉ ስደዉልልን እኛ አንሲተን ሲናዉራ የደዋዩን ድምፅ ለእኛ የምያሰማን ጆሮ ማይክ ነዉ
ጆሮ ማይክ ከተበላሸ የደዋዩ ድምፅ አይሰማም ሲናገር ....

🙏 4ኛ እስፒከር ኮኔክተር ፦ ማለት ሰዉ ደዉሎልን ሲናዉራ የእኛን ድምፅ ለደዉዩ የምያሰማ የሞባይል ክፍል ነዉ
ጓደኞቼ እንደይምታታባቹ ጆሮ ማይክ እና እስፒከር
እስፒከር ከተበለሸ እኛ ደዉለን ሲናዉራ ምንም አይሰማም ለደዉልንት ሰዉ

🙏 5ኛ ርንገር ኮኔክተር ፦ ማለት ሙዚቃ ቪድዮ በስልካችን ሲናጫዉት ድምፅ የምያሰማን ክፍል ነዉ ርንገር ኮኔክተር ከተበላሸ ስልካችን የፈለግነዉን ነጋር ሙዚቃ ድርማ ወዘተ ቢናጫዊተዉ ድምፅ አያሰማም
ጓደኞቼ እንዳትወዛገቡ ድምፅ ማሰማት ምናምን እስፒከር ኮኔክተር እንዳይመስላችሁ ርንገረ ኮኔክተር ነዉ እንጅ......

🙏 6ኛ ካሜራ ኮኔክተር ፦ ማለት ድግሞ በስልካችን ፎቶ ለማንሳት የምጠቅም በስልካችን የተገጠመ ፎቶ ማንሻ ወይም ቪድዮ መቅርጫ ኮኔክተር ነዉ

🙏 7ኛ ሲም ኮኔክተር ፦ ማለት ደግሞ ስልካችንን ከሲም ካርድ ጋር የምያገናኝ የሞባይል ክፍል ነዉ ሲም ኮኔክተር ከተበላሸ ወይም ከተሰበር ሲም ካርድ ቀፎዎችን ሲም አይሰራም .....

8ኛ ሚሞር ኮኔክተር ፦ ማለት ሚሞረወን ከስልካችን ጋር የምያገናኝ የሞባይል ክፍል ነዉ ሚሞር ኮኔክተር ከተበላሸ ስልካችን ሚሞር አይሰራም.....

🙏 9ኛ ኔቶርክ ኮኔክተር ፦ ማለት ስልካችን ኔቶርክ እንድሰራ የምያደርግ ክፍል ነዉ አንዳንዴ ኔቶርክ ኮኔክተር በላይም ከሰፈለገም ከውስጥም የምገጠምበት አጋጣሚ አለ...

🙏 10ኛ ኤርፎን ኮኔክተር ፦ ማለት ድግሞ ስልካችን ድምፁን ከርንገር ወጪ የምያደርግ ክፍል ነዉ ኤርፎን ኮኔክተር ከተሰበር ስልካችን ኤርፎን አይሰራም ....

@quantum_tech5
WinRar ምን ጥቅም ላይ ይውላል?
WinRar ተጠቃሚዎች ትላልቅ ፋይሎችን ወደ የታመቀ ቅርጸት እንዲያስተላልፉ ፣ እንዲያጋሩ ወይም በማህደር እንዲያስቀምጡ የሚያስችል የውሂብ መጭመቂያ (data compression) መሳሪያ ነው ፡፡ መሣሪያው ተጠቃሚዎች ከመጀመሪያው የፋይል ቅርጸቶች ያነሰ ማከማቻ የሚወስድ በርካታ ፋይሎችን ወደ .rar ወይም .zip ቅርጸት እንዲለውጡ ያስችላቸዋል።
WinRar በኮምፒተር ማከማቻ ላይ ትልቅ ቦታ ለሚይዙ መልቲሚዲያ ፋይሎች በደንብ ይሠራል ፡፡ በተጠቃሚው ፋይል ውስጥ ብዙ ፋይሎችን እንዲልክ ስለሚያደርግ ፕሮግራሙን በመጠቀም መረጃን ማጋራትም ቀላል ነው ፣ ይህም በፖስታ እንደ አባሪ ሊሄድ ይችላል ፡፡ ፕሮግራሙ ፋይሎችን ከተጨመቀ ቅርጸት ለማውጣት እና በተመረጠው የፋይል መድረሻ ላይ ለማስቀመጥ ሊያገለግል ይችላል ፡፡ WinRar እንዲሁ መዝገብ ቤቶችን በመከፋፈል እና በትክክል በማውጣቱ ተጠቃሚዎች በአግባቡ እንዲመዘገቡ ያስችላቸዋል።
WinRar ን በመጠቀም ፋይሎችን እንዴት ማውጣት እንደሚቻል ፕሮግራሙ በዊንዶውስ ሲስተም ላይ ከወረደ በኋላ ወደ ቀለል በይነገጽ ይከፈታል ፡፡ የላይኛው ፓነል አማራጮችን ያሳያል ይጨምሩ ፣ ያውጡ ፣ ይፈትሹ ፣ ይመልከቱ ፣ ይሰርዙ እና ተጨማሪ አማራጮችን ይጨምሩ ፡፡ የማውጫውን አማራጭ በመጠቀም ተጠቃሚዎች በዝርዝሩ ቅርጸት ወደ መስኮቱ የሚከፍቱ የተጨመቁ ፋይሎችን መክፈት ይችላሉ ፡፡ ዘ. rar ወይም. የዚፕ ፋይሎችን በቀኝ-ጠቅ ሲያደርጉ እና በዊን ራር የመክፈት አማራጭን ሲከተሉ ከመድረሻው ራሱ ሊከፈት ይችላል ፡፡ የዝርዝሩ እይታ አንድ ወደ ተመረጠው መድረሻ ከማምጣቱ በፊት አንድ ሰው በራሱ በፕሮግራሙ ውስጥ ያሉትን ፋይሎች እንዲያይ ያስችለዋል።
WinRar ን በመጠቀም ፋይሎችን እንዴት እንደሚጭመቅ WinRar ተጠቃሚዎች የተለያዩ ፋይሎችን ወደ አንድ የተጨመቀ ፋይል እንዲጭኑ ያስችላቸዋል ፡፡ ይህ ብዙ ፋይሎችን ማስተላለፍ እና መጋራት በቀላሉ ያደርገዋል። አዲስ የራራ ፋይል ሲፈጥሩ ተጠቃሚዎች በአንዱ ፋይል ውስጥ ለመጭመቅ የመረጡትን ማንኛውንም የፋይሎች ቁጥር ለመጨመር ፣ የአክል ፋይሎችን አማራጭ ማመልከት አለባቸው ፡፡
የመጨረሻዎቹ ቅርጸቶች ራሪ ፣ ራራ 4 ወይም ዚፕ ሊሆኑ ይችላሉ ፣ ተጠቃሚው አማራጩን እንዲሁም ፋይሉ መቀመጥ ያለበት መድረሻውን መምረጥ ይችላል።
WinRar ከምን ጋር ተኳሃኝ ነው? WinRar በዋነኝነት ከዊንዶውስ ጋር ተኳሃኝ ሲሆን አሁን ለ Androidም ይገኛል ፡፡ ለ Macs ወይም ለ Apple መሣሪያዎች ኦፊሴላዊ የተለየ ስሪት የለም ፣ ግን WinRar መተግበሪያ ፋይሎችን ለማውጣት ፣ ለማስመዝገብ ወይም ለመጭመቅ በማክ ዴስክቶፖች ላይ ይሠራል ፡፡
WinRar እንደ .rar ያሉ የፋይል ቅርፀቶችን እንዲሁ መፍጠር ይችላል ፡፡ ዚፕ ፣ በ .rar ቅርጸት የተጨመቁ ፋይሎችን መፍጠር የሚችል ብቸኛው ፕሮግራም ይህ ነው። ሌሎች እንደ WinZip ወይም 7zip ያሉ ፕሮግራሞች ከ .rar ፋይል መረጃን ማውጣት ይችላሉ ፣ ግን በዚያ ልዩ ቅርጸት ፋይል መፍጠር አይችሉም።
🔶 ሶፍትዌሩን ማውረድ ለምትፈል 👇👇👇 https://www.winrarfree.net
የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ቻናሎች ወደ ኢትዮ ሳት መቀየራቸው ተከትሎ የዲሽ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል !

ከሰሞኑ በርካታ የቴሌቪዥን ቻናሎች ወደ ኢትዮ ሳት መቀየራቸው ተከትሎ የዲሽ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተነገረው፡፡

እንደማሳያ ከአንድ ወር በፊት ኤች ዲ ላይፍ ስታር ከ650 እስከ 700 ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ እስከ 1000 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

እንዲሁም ሱፐር ስታር ኢሮ ቦክስ እና ኤል ኢጂ 700 የነበረ ሲሆን አሁን እስከ 1 ሺህ 100 ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

የዲሽ ዋጋ በተመለከተም ባለ 60 ሳህን 600 ብር የነበረ ሲሆን አስከ 850 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ባለ 90 ሳህን ደግሞ 700 የነበረ ሲሆን አሁን ላይ እስከ 1 ሺህ አንድ መቶ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ኢትዮ ኤፍ ኤም መታዘብ ችሏል፡፡

እንደዚሁም የዲሽ ዋጋም በተመለከተ ከዚህ በፊት 20 ሜትሩ አንድ መቶ ብር የነበረ ሲሆን አሁን በሜትር እስከ 600 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

@quantum_tech5
SDና HD ሪሲቨር ልዩነት ምንድን ነው?
በሁለቱ መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት
Standard Definition (የመደበኛ ጥራት) (ኤስዲ) ወይም High Definition (ከፍተኛ ጥራት (ኤች ዲ)) ያላቸውን የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለማሳየት መቻላቸው ነው ፡፡
የኤስዲ(SD) ሪሲቨር ሣጥን መደበኛ ጥራት(Standard Definition) የቴሌቪዥን ቻናል ስርጭቶችን ብቻ ማሳየት ይችላል።
ኤችዲ(HD) ሪሲቨር High Definition (ከፍተኛ ጥራት) ደግሞ ሁለቱንም መደበኛ ጥራት እና ከፍተኛ ጥራት ቻናሎችን ያሳያል ፡፡ ኤችዲ ሪሲቨር እንደ HDTV ማሳያ እንዲጠቀሙባቸው ከኮምፒዩተር ማሳያዎች(ሞኒተር) ጋር ማያያዝም ይቻላል ፡፡
◄◄◄◄◄◄🔹🔹🔹▻▻▻▻▻▻▻▻
ሪሲቨር ስንገዛ ምን ምን ነገሮችን ማየት አለብን ☜
መጀመሪያ ድ ሪሲቨር ለመግዛት ወደገበያ
ስንወጣ ማየት ያለብን ብዙ ነገሮች አሉ
አለበለዚያ በቸልተኝነት ያገኘነዉ ሪሲቨር ገዝተን
ሪሲቨሩ ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ የሚፈልጉት
ነገሮች ባይሰራ ወይም ሪሲቨሩ ብዙም
ሳይጠቀሙበት ቢበላሽ በተጨማሪ ወጪ
መጋለጦ አይቀሬ ነዉ፡፡
1. መጀመሪያ ሪሲቨሮን ከሶኬት
ጀምሮ ማየት ነዉ የሪሲቨሩ
ስኬት ቶሎ ሚቆረጥ ሊሆን
ስለሚችል ነዉ
2. በመቀጠል ሪሞቱን እናያለን
እቤታችን ዉስጥ ህፃናት ካሉ
ሪሞት አይበረክትም ስለዚህ
የሪሞቱን ጥንካሬ ልብብሎ
ማየት ነዉ ሪሞቱ ቢበላሽ ገበያ
ላይ በቀላሉ ማግኘት
መቻሎትንም ማረጋገጥ አለቦት
3. ሪሲቨሩ በአሁን ሰአት በሪሲቨር
ቴክኖሎጂ ዉስጥ ያሉትን
አዳዲስ ነገሮች መያዙን ማየት
ወይም መጠየቅ ነዉ
✿ለምሳሌ በቤትዎ ነፃ የኳስ
ቻናል ማየት ቢፈልጉ በቀላሉ
ያለ ሶፍትዌር biss key , .
pow
erVU
Tandbrge
የመሳሰሉትን ያለ ሶፍትዌር
ማየት አለቦት
4. ሌላኛዉ ነገር ሪሞታችን
ባይሰራ ሪሲቨሩ ላይ ሙሉ
በተን አለዉ ወይ ?ብላችሁ
ማየት ጠቃሚ ነገር አለያቸዉ
ላይ ምንም በተን የላቸዉ
✿ለምሳሌ እርሶ ቻናል
ለመቀየር ወይም ድምጽ
ለመጨመር ፈልገው ሪሞቱ
ምንም አልሰራ ቢለዎትስ
ሪሲቨሩ ምንም በተን ባይኖረዉ
በሰአቱ በጣም ይናደዳሉ በተን
ካለዉ ግን ሪሞት እስክንገዛ
ሪሲቨሩ ላይ ባለዉ በተን
እየነካን እንጠቀማለን
5. እንደዚሁም ሪሲቨሩ
ሚያጫዉታቸዉ የvideo
format ማየት ነዉ፡፡
✿ለምሳሌ FLV ,
MPGMPG4 ,3GP , ETC
የመሳሰሉትን SUPPORT
ማድረጉን ማየት
6. ሌላኛዉ በተለያዩ ጊዜዋች
አዳዲስ ነገሮች የመጡ
ሶፍትዌሮች ቶሎ ሚለቀቅለት
ሪሲቨር መሆን አለበት
7. የሪሲቨሩ ግራፊክስ ማየት
አለብን
ሌሎች መረጃዎች እንዲደርስዎ ፔጁን like ያድርጉ

@quantum_tech5
Channel photo updated
በIDM download ስታደርጉ ለተቸገራችሁ ምርጥ መፍትሄ
ይህ IDM ማንኛውን በኮምፒውተር ላይ በመጫን የፈለጉትን
የአጫጫን Steps
1ኛ idman629build2.exe ይጫኑ
2ኛ Patch የሚለውን ፎልደር ውስጥ በመግባት የኮምፒውተር OS bit 32 ከሆነ 32 Bit patch build 2.exe
64 ከሆነ ደግሞ በተመሳሳይ ይጫኑበት
በይበልጥ ግን How to install የሚለውን ያንብቡት።
Serial number አይጠይቃችሁም ከዚህ በኋላ
4_5972280010818455892.zip
10.1 MB
በIDM download ስታደርጉ ለተቸገራችሁ ምርጥ መፍትሄ
ይህ IDM ማንኛውን በኮምፒውተር ላይ በመጫን የፈለጉትን
የአጫጫን Steps
1ኛ idman629build2.exe ይጫኑ
2ኛ Patch የሚለውን ፎልደር ውስጥ በመግባት የኮምፒውተር OS bit 32 ከሆነ 32 Bit patch build 2.exe
64 ከሆነ ደግሞ በተመሳሳይ ይጫኑበት
በይበልጥ ግን How to install የሚለውን ያንብቡት።
Serial number አይጠይቃችሁም ከዚህ በኋላ

@quantum_tech5
YouTube ላይ ቪዲዮ ዳውንሎድ ማድረግ
ከ YouTube ላይ ቪዲዮችን ዳውንሎድ ለማድረግ የሚያገለግሉ ብዙ ሶፍትዌሮች ኢንተርኔት ላይ ይገኛሉ፡፡ አንዳዳቹን በነፃ ሌሎቹን ደግሞ በክፍያ ነው ዳውንሎደ የሚደረጉት፡፡ ቪዲዮችን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት ዳውንሎድ የምናደርግበትን ሶፍትዌር እራሱ ዳውንሎድ ማድረግ ወይንም ከሌላ ኮምፒውተር ላይ ኮፒ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
ዳውንሎድ ማድረግ ወይንም ማውረድ ማለት ምን ማለት ነው?
ማንኛውንም አይነት ፋይል (ቪዲዮ፤ድምጽ፤ጽሁፍ፤ስእል ….) ከኢንተርኔት ላይ ወደ ኮምፒውተራችን ኮፒ የምነዳርገበት መንገድ ዳውንሎድ ይባላል፡፡ ምሳሌ፡ ከ YouTube ላይ ቪዲዮ ስናወርድ/ዳውንሎድ ስናደርግ ቪዲዮውን ከ ዌብሳይት ላይ ወደ ኮምፒውተረችን ኮፒ አደረግን ማለት ነው በተመሳሳይ መጽሀፍት፤ፊልሞች ወይንም ጌሞችን ከኢንተርኔት ላይ ወደ ኮምፒውተራችን ኮፒ ስናደርግ ዳውንሎደ አደረግን ማለት ነው፡፡
ከ YouTube ላይ ቪዲዮችን ለማውረድ/ዳውንሎደ ለማድረግ ተጨማሪ ለዳውንሎድ ማድረጊያ ተብለው የተዘጋጁ ሶፍተትዌሮች ያስፈልጉናል፡፡ ከ ለማውረድ ከሚያገለግሉ ሶፈትዌሮች መከካል Internet Download Manager (IDM) በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ ነው። ግን እሱ ብቻ ነው ዳውንሎደ ማድረጊያ ማለት አይደለም፡፡ በዛሬው ቱቶሪያላችን ከ ደውንሎደ መማድረጊያ ሶፍትዌሮች ሶስቱን እናያለን፡፡
Internet Download Manager (IDM)
በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ እና ተወዳጅ ነው ፡፡ከቪዲዮ ባሻገር የተለያዩ የፋይል አይነቶችን ዳውንሎድ ማድረግ ይችላል፡፡ ነፃ ሶፍትዌር አይደለም ፡፡ይህን ሶፍትዌር የሚያመርተው ድርጅት ሶፍትዌሩን ለ 30 ቀን የሙከራ ጊዜ ይሰጠናል ከተባለው ቀን በኋላ ከተመቸን እንድንገዛ ካልተመቸን ደግሞ ከኮምፒውተራችን እንድናሰስወግደው አድርጎ ነው የሚሰራው፡፡እንደ ሶፍትዌሩ አምራች ከሆነ ኮምፒውተራችን ላይ ከተጫነ ከ 30 ቀን በላይ አያገለግለንም ማለት ነው፡፡ በእኛ ሀገር ሁኔታ በኢንተርኔት አማካኝነት መገበያየት ስለማንችል ያለን አማራጭ ሶፍትዌረን ለ 30 ቀን ተጠቅመን ማስወገድ ወይንም ሶፍትዌሩን ክራክ በማድረግ የአግልግሎት ጊዜውን ማስቀጠል ነው፡፡እዚህ ጋር ክራክ ማድረግ ማለት ሶፍትዌሩን ሳንገዛው አንደ ገዛነው ማድረግ ማለት ነው፡፡
የ IDM አጫጫን
1. መጀመሪያ IDM ዳውንሎድ ያድርጉ (IDM የሚለውን ክሊክ በማድረግ ዳውንሎድ ያድርጉ)
2. ብራውሰራችንን እንዝጋ
3. ዚፕ ፈይሉን ይክፈቱት ከዛም ኤክስትራክት የድርጉት
4. Setup የሚለውን አቃፊይክፈቱ
5. idman615 የሚለውን እንደገና ይክፈቱ
6. Accept ሚለውን ይምረጡ
7. ኢንስታሌሽኑ አስኪያልቅ ድረስ Next የሚለውን መጫን
* ክራክ እንዴት እንደምናደርግ Installation የሚለውን በመክፈት ማንበብ ይቻላል
ዳውንሎድ አደራረግ
የተለያዩ አይነት ፋይሎችን ማውረድ እንደሚችል ጠቅሰናል እንደ ምሳሌ ግን የምናየው ቪዲዮ ፋይሎችን እንዴት እንደምናወርድ ነው፡፡
1. YouTubeን እንከፍታለን
2. የምንፈልገውን የቪዲዮ ስም በመፈለጊያ ሳጥን ውስጥ እንፃፍለት ቀጥሎም Search ውይንም ኢንተርን መጫን
3. ከሚመጡት የቪዲዮ ዝርዝሮች መካከል የምንፈልገው ላይ ክሊክ በማድረግ መክፈት
4. ቪዲዮው ሎድ አድርጎ መጫወት ሲጀምር ከቪዲዮው ማጫወቻ ሳጥን ከላይ በቀኝ በኩል Download video የሚል ይመጣልናል ቀጥሎም የምንፈልገውን የፋይል አይነት በመምረጥ Start now ማለት ነው
5. ዳወነንሎድ አደርጎ እስኪጨርስ እንደ ፋይሉ መጠን እና እንደ ኢንተርኔቱ ፍጥነት ጊዜ ይወስዳል
6. ዳውንሎደ አድርጎ ሲጨርስም መጨረሱን ይገልጽልናል
7. እኛ ካልቀየርነው በስተቀር ዳውንሎድ የሚያደርጋቸውን ፋይሎች በ Downloads ፎልደር ውስጥ ነው የሚያስቀምጠው ፤ ለጊዜው ዳውነሎደ ያደረግነው ቪዲዮ ስለሆነ ዳውንሎደ የደረግነውን ፋይል የምናገኘው Downloads ---> Videos የሚለው ፈልደር ውስጥ ይሆናል ማለት ነው፡፡
Free Download Manager (FDM)
FDM እንደ IDM ዳውንሎደ ለማድረጊያ ሶፍትዌር ነው፡፡ በነፃ ደውንሎድ የሚደረግ ሲሆን እስከፈለግነው ጊዜ ድረስ ክራክ ማድረግ ሳያስፈልገን የምንጠቀምበት ሶፍትወዌር ነው፡፡
FDM ከ IDM የሚለየው በነፃ የሚገኝ መሆኑ እና በተጨማሪ የ ቶረንት ፋይሎችን ማውረድ መቻሉ ነው፡፡
FDMን ከ www.freedownloadmanager.com ላይ በቀጥታ በመግባት Download የሚለውን ታብ በመጫን የምንፍልገውን ቨርሽን ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን፡፡ ዳውንሎደ አድርገን ከጨረስን በኋላ ከላይ ለ IDM በተጠቀምነው መንገድ በተመሳሳይ ሁኔታ ኢንስታል ማድረግ፡፡ ኢንስታል አድርገን ከጨረስን በኋላ ልክ እንደ IDM፤ YouTube በመክፈት የምፈልገውን ቪዲዮ ከከፈጥን በኋላ ከቪዲዮ ላይ በግራ ጠርዝ በኩል Download የሚል ያመጣልናል እሱን ክሊክ በማድረግ ዳውነሎዱን ማስጀመር፡፡፡ ዳውንሎድ አድርጎ ሲጨርስ በተመሳሳይ መልኩ ዳውኖዳችንን መጨረሱን ይገልጽልናል፡፡
XiloSoft YouTube Downloader
ይሄኛው ሶፍትዌር ስራው YouTube ብቻ ቪዲዮችን ዳውንሎደ ማድረግ ነው፡፡ በነፃ ዳውንሎድ የሚደረግ ሲሆን ከተጫና በኋላ እንደ ቀደምቶቹ ቨዲዮችን በብራውሰራችን ፈልገን ሳይሆን የምናወርደው በራሱ በሶፍትወሩ በመጠቀም ነው፡፡
XiloSoft YouTube Downloader (ክሊክ ያድርጉት ) ዳውንሎደ በማድረግ ከላይ በተጠቀሱት መንገድ ኢንታል ማድረግ፡፡ ዴስክቶፓችን ላይ የተፈጠረውን XiloSoft YouTube Downloader ሾርትከት መክፈት ወይንም በተለመደው አካሄድ All Programs በመግባት መክፈት የቻላል ፡፡ ቀጥሎም ሶፍተዌሩ ውስጥ በሚገኘው የመፈለጊየ ሳጥን ውስጥ የምንፈልገውን ቪዲዮ ስም በመፃፍ ቪዲዮችን መፈለግ፡፡ የምንፈልገውን ቪዲዮ መርጠን ማጫወት ስንጀምር ከለያ ሜኑ ባር ላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል መጀመሪያ ላይ የሚገኘውን የወደታች ቀስት መጫን ቅስቱን ስንጫን በቀጥታ ዳውንሎድ ማድረግ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ የዳውንሎዳችንን ሁኔታ ለማየት በግራ በኩል ከተዘረዘሩት ሜኑዎች ውስጥ Downloads የሚለውን በመጫን ምን ላይ እንደ ደረሰ ማወቅ ይቻላል ሲጨርም መጨረሱን ይነግረናል፡፡ በተጨማሪ አንዱ ዳውነሎድ ሳያልቅ ሌሎችን ማሰጀመርም ይቻላል
ከF1 እስከ F12 ያሉ #የኪቦርድ ቁልፎች አገልግሎት

🏷 በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው
የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function
Key እንላቸዋለን፡፡
በዋናነትም ከሌሎች #ቁልፎች ጋር
በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ
ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና
ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው
ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡

◽️F1
ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው
ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን #የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ
Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡
◽️F2
#የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር
F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt
+ Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡
◽️F3
ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift +
F3 መጫን #የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን
አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን
ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡
◽️F4
አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 #መጫን
ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ
አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን
ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ
#የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን
ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን
ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ
ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4
ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt +
F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት
ነው፡፡
◽️F5
አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5
መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ
Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት
ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡
◽️F6
በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን
አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው
ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ
ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን #ወደቀጣዩ
የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡
◽️F7
ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ
#Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም
ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡
◽️F8
ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ #Startup menu
ለመግባት የጠቅማል፡፡
◽️F9
በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን
በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን
#Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { }
ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት
CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ
ለማጥፋት
◽️F10
አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ
ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን #ራይት ክሊክ
እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
◽️F11
በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን
የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን
ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡
◽️F12
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ #የ Save as ማስኮትን
ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም አዳዲስ ቪዲዮችን እየሰራሁ ስለሆነ #Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ telegram ቻናል ሊንክ 👇👇👇
@quantum_tech5
እንዴት አድርገን በCBE ሞባይል ባንኪንግ ብር መላክ እንችላለን?
1ኛ *889# በመጫን
~~~~~~~~~~~~~~~~~
2ኛ Welcome to CBE Mobile Banking. Press * to navigate back any time, select one
of the following options below:
1: Login
2: Exit
👉 1ን ይጫንኑ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
3ኛ Please enter your PIN to login: 👉 የPIN ቁጥር ያስገቡ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~
4ኛ Welcome to CBE Mobile Banking
1: My Accounts
2: Transfer to CBEBirr Wallet
3: Make Payment to Beneficiary
4: Payment to others
5: More options
👉 4ን ይጫኑ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
5ኛ Payment to others
1: የአካውንት አይነት- ETB - 7000
👉1ን በማስገባት Send የሚለውን ይጫኑ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
6ኛ Refine
Please enter Account No
የሚላክለንትን የአካውንት ቁጥር ያያገቡ ለማስሌ(100000000000)
ከዛም Send የሚለውን ይጫኑ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
7ኛ Payment to other
1: MUHAMMED
AMIN YASIN-ETB-0797(ይህ ስም የሚላክለት ሰው ስም ነው)
👉1ን ያስገቡ ከዛም Send የሚለውን ይጫኑ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
8ኛ የላኪ ስም
Request Debit Acc: የላኪ ስም Credit Acc: የተቀባይ ስም-ETB-0797
Please enter Amount
8000(የሚላከውን የብር ብዛት ያስገቡ)
ከዛም 👉Send የሚለውን ይጫኑ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~
9ኛ Please enter Reason
የሚላክበትን ምክንያት ይጻፉ
ከዛም 👉Send የሚለውን ይጫኑ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~
10ኛ Confirm request for የተቀባይ ስም
Request Debit Acc: የላኪ ስም Credit Acc: የተቀባይ ስም ... Press any key except 1
and 2 for more
👉1ን በመጫን
👉Sendን ይጫኑ
👉1ን ከተጫኑ ብር ልከዋል ማለት ነው መላክ ካልፈለጉ ደግሞ 2ን ይጫኑ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~
ከተመቻችሁ ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር ይደረግ!

@quantum_tech5