Quantum Computer Technology
94 subscribers
13 photos
2 files
14 links
ወቅታዊና አዳዲስ የቴክኖሎጂ መረጃዎች እንዲደርሶ ይህንን ቻናል በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Download Telegram
ኮምፒውተራችን በቫይረስ የተጠቃ መሆኑን በቀላሉ ማወቅ የምንችልባቸው መንገዶች👇

#1. ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ:-

ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡

#2. የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም /Slow System/:-
በሲስተም ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን (applications)
ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን ሊያመለክት ይችላል።

#3. ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ:-
እንቅስቃሴ( 3. Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃት የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

#4. ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ:-
ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች /drive/ ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

#5. የተለዩ መልእክቶች:-
በተለያዩ መልእክቶች ወደ እርስዎ የመልእክት መለዋወጫዎች ሲገቡ እና ፋይሎችን በሚከፍቱበት ጊዜ ካልተከፈተ የተፈጠረ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

#6. መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ:-
ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመክፈት እየሞከረ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡

#7. የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ /Random Network Activity :-
ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

#8. የተሳሳቱ የኢሜይል መልእክቶች:-
እርስዎ ለማንም ኢ-ሜይል ባይልኩም ከእርስዎ የኢሜይል አድራሻ ለእርስዎ ኢ-ሜይል መልእክት ከደረስዎ የእርስዎ ስርዓተ ኮምፒውተር ተጥሷል (ወይም የኢ-ሜይል የይለፍ ቃልዎ እንደተሰረቀ የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው)

#9. የአይፒ አደራሻዎ በበይነመረብ ፕሮቶኮል አድራሻ በጥቁር መዝገብ ከተቀመጠ/
Blacklisted IP Address/ :-
የእርስዎ የአይፒ አድራሻ በጥቁር መዝገብ መያዙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከደረሰዎት ኮምፒተርዎ በጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት፡፡

#10. ያልተጠበቀ የፀረ-ቫይረስ አገልግሎት መቆም:-
ብዙ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር /malware/ ፕሮግራሞች ፀረ-ቫይረስ አገልግሎት የማስተጓጎል ወይም ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተልእኮ በመያዝ የተቀየሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ቫይረስ ስርዓትዎ በድንገት የማይሠራ ከሆነ የኮምፒውተር ስርዓቱ ትልቅ ችግር ላይ መውደቁን የሚያሳይ በመሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል፡፡
@quantum_tech5
ኦሪጅናል እና fake ሳምሰንግ ስልኮችን እንዴት መለየት እንችላለን ????
***************************
#1 መጀመሪያ የ ስልኮትን imei number ከ ስልኮት ላይ ያወጣሉ (ስልክ መደወያ ላይ ገብተው *#06# ይንኩ )
#2 ከዛ የሚመጣላችሁን 15 ዲጂት ቁጥር በ ወረቀት ይጻፉ
#3 www.imei.info የሚል ዌብሳይት ላይ ይግቡ ከዛ የሚመጣላችሁ box ላይ የ ቅድሙን 15 ዲጂት ቁጥር ያስገቡ
#4 ከዛ ዌብሳይቱ እራሱ ስለ ስልኩ በቂ መረጃ ይሰጣችኋል።
Variables!

Variables:- ማንኛውንም ጥናታዊ ስራ ለመስራት በምናስብበት ወቅት ስለ ምናጠናው ሃሳብ ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች፤ በጥናት ልናረጋግጠው በፈለግነው ሃሳብ ላይ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ተጽኖ የሚፈጥሩ ጉዳዮች ወይም ሃሳቦች ማለት ነው።

ለምሳሌ:-

በግለሰብ ደረጃ ሲጋራ ለማጨስ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን ለማጥናት ብናስብ፣ ቀጥተኛ ሆነ ተዘዋዋሪ ተጽኖ የሚፈጥሩ ሃሳቦችን መጀመሪያ እንለያለን፣ እነሱም ጾታ፤ እድሜ፤ የትዳር ሁኔታ፤ የስራ በሃሪ፤ ገቢ፤ የመኖሪያ አካባቢ፤ ወዘተ ሲጋራ ማጨስን ጨምሮ Variables ይባላሉ። የምንመርጣቸውን Variables ከTheory አንጻር፤ ከሌሎች ጥናታዊ ግኝቶች አንጻር እና ከልምድ አንጻር በመመስረት መምረጥ ይይቻላል።

ለምሳሌ:-

ወጣትነት ለማጨስ እንደሚገፋፋ ከልምድ በመነሳት፤ የገቢ ማነስ በብስጭት ምክንያት ለማጨስ እንደሚዳርግ የተረጋገጠ ጥናት ካለ በመውሰድ፤ ሌሎቹንም በምክንያት በማስደገፍ መርጦ መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን ከላይ ከተጠቀሱት ምክያቶች ውጪ ምክንያት አለኝ ወይም ማረጋገጥ እፈልጋለው ለሚል አጥኚ የራሱን ሃሳብ በማቅረብ ማጥናት ይችላል።

ለምሳሌ:-

በግለሰብ ደረጃ ሲጋራ ለማጨስ የኢንተርኔት መጥፋት ምክንያት ነው የሚል Variables ቢመረጥ ስህትት አይደለም ነገር ግን በመረጃ በመነሳት ግንኙነት እንዳለው እና እንደሌለው ማረጋገጥ ብቻ ነው የሚጠበቅበት።

በግለሰብ ደረጃ ሲጋራ ለማጨስ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን ለማጥናት ብናስብ በጥናት የሚረጋገጠው ሲጋራ ማጨስ (Dependent ወይም Outcome Variable) ይባላል። ምክንያቱም ሲጋራ ማጨስ በጾታ፤ በእድሜ፤ በትዳር ሁኔታ፤ በስራ በሃሪ፤ በገቢ፤ በመኖሪያ አካባቢ፤ ወዘተ ተጽኖ ስለሚያድርበት በነሱ ላይ ጥገኛ ነው።

ነገር ግን በራሳቸው ቆመው በሲጋራ ማጨስ ላይ ተጽኖ የሚፈጥሩት ጾታ፤ እድሜ፤ የትዳር ሁኔታ፤ የስራ በሃሪ፤ ገቢ፤ የመኖሪያ አካባቢ፤ ወዘተ (Independent ወይም Explanatory Variables) ይባላሉ። ምክንያቱም ሲጋራ ማጨስ በተቃራኒው የግለሰቡ ጾታ ላይ ተጽኖ መፍጠር አይችልም (ሰው ስላጨሰ ጾታው አይለወጥም ነገር ግን ጾታው እንዲያጨስ ተጽኖ ሊፈጥርበት ይችላል

ለምሳሌ:- ወንዶች ከሴቶች በላይ አጫሽ ሊሆኑ ይችላሉ።

Y(ሲጋራ ማጨስ) = f(ጾታ + እድሜ + የትዳር ሁኔታ + የስራ በሃሪ + ገቢ + የመኖሪያ አካባቢ + ወዘተ + Error Term)

በተለይ የEconometrics Model በመጠቀም ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ለሚያስቡ አጥኚዎች የምንመርጠውን Variables በጥንቃቄ መምረጥ የማንችል ከሆን የመጨረሻ ውጤቱን ሊያዛባው ይችላል። በተለይ የመረጥነው Independent Variable በተቃራኒው በራሱ በIndependent Variable ላይ ተዘዋዋሪ ተጽኖ የሚፈጥር ከሆን በጣም ክፍተኛ ስህተት የሆነ ውጤት ነው የምናገኘው። የዚህ አይነቱ ችግር Multicolinearity Effect ይባላል። ስለዚህ በቅድሚያ Variables በጥንቃቄ በመምረጥ እንዲሁም የዚህ አይነቱን ችግር መኖሩን የሚያረጋግጠውን Multicolinearity Test ለማድረግ የተለመደው variance-inflating factor (VIF) ስልት ሲሆን በVIF የሚገኘው አማካይ ውጤት ከ10በታች ከሆነ የወሰድናቸው Independent Variables ትክክለኛ ወሆናቸውን ያሳያል። ለዚህ የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች E-View፤ Stata፤ SPSS፤ Sas፤ ወዘተ) በመጠቀም ችግሩን መቅረፍ ይገባል።

© The Ethiopian Economist View
ስኬት ምንድን ነው?"

ብዙ አዋቂዎች የሚስማሙበትን አጠር ስናደርገው እነዚህን እውነታዎች እናገኛለን፡፡

1. ማንነትንና ብቃትን ማወቅ

፦ አንድ ሰው ማንነቱን በቅጡ ሲያውቅና በዚህ ዓለም ላይ በሕይወት የሚኖርበትን ዘመን ምን ሠርቶ ማለፍ እንዳለበት ሲገባው የስኬት መስመር ውስጥ የገባ ሰው ነው ማለት ነው፡፡

" ሁሉም ሰው ብልህ ነው፡፡ ነገር ግን፣ አሳን ዛፍ ላይ በመውጣት ችሎታውን ከመዘንከው ይህ አሳ እድሜውን በሙሉ ደደብ ነኝ ብሎ በማመን ይኖራል፡"
#Albert #Einstein

ስለዚህ አንተ ውስጥ አስገራሚ ብቃትና የእውቀት ዝንባሌ አለ፤ ለመሆንና ልትችለው የተፈጠርክለትን ማንነት! ችላ ብለህ ለአንተ ያልተሠጠውን ማንነት ሆኖ ለመገኘት እና ከሆንከው ማንነትህ ጋር የማይሄደውን ለማወቅና ለማድረግ መሞከር ማለቀቂያ የሌለው ጉዞ ይሆንብሃል፡፡ ስለዚህ በዛ በተሰጠህ ነገር ላይ ልፋ ስኬታማ ትሆናለህ፡፡

2. እምቅ ብቃትህን መፍታት

ራስህን አሁን ካለህበት ሁኔታ በበለጠ ማየት ካልጀመርክ በሁኔታህ እንደታሰርክ ትኖራለህ፡፡ ራስህን ማየት ያለብህ መሆን ከምትችለውና ከምታውቀው ብቃትህ አንፃር ነው፡፡ ይህንን ብቃትህን ለማወቅ ያለመርካት ስሜቶችህን አዳምጣቸው፡፡ ( ያለመርካት ስሜት ማለት ነገሮችን ስታከናውን ቅር የሚልህን ቦታ ትኩረት ሰተህ እየው ማለት ነው፡፡ ) በተጨማሪም ከዚህ የተሻለ ማድረግ ይቻላል ብለህ የምታስባቸውን ጉዳዮች አጢናቸው ታገኘዋለህ! አሁን ካለህበት ሁኔታና ከምትሄድበት አቅጣጫ የተሻለ ነገር እንዳለና አንድ ቀን እዚያ ደረጃ መድረስ እንዳለብህ ውስጥህ ከናፈቀ፣ የእምቅ ብቃትህን ቁልፍ አግኝተህዎል፡፡

"ሰውን አሁን ካለበት ሁኔታ አንፃር ስናስተናግደው፣ ካለበት ሁኔታ የበለጠ እናወርደዋለን፡፡ ያለውን እምቅ ብቃትና ወደ ፊት መሆን የሚችለውን አይተን እንደዚያ ስናስተናግደው፣ መሆን የሚገባውን እንዲሆን መንገድ እንከፍትለታለን፡"
#Johann #Wolfgang #Von #Goethe

3. ለሌሎች የሚተርፍን ዘር መዝራት

ብልፅግና፣ ሃብት፣ እውቀት፣ ዝናና ኀይል ለሌሎች ካሉበት መነሳት ላቃታቸው ሰዎች ጥቅም እስኪውል ድረስ ከስኬት ጋር በፍፁም ሊያያዝ አይችልም፡፡ ለሌሎች የመትረፍህን መጠን ለማወቅ፣ ወደ እጅህ በገባውና ከእጅህ በወጣው መካከል ያለውን ልዩነት ተመልከት፡፡ የገባው ብዙ፣ ለሌሎች ጥቅም የዋለው ደግሞ ጥቂት ከሆነ ከስኬት ጎዳና ውጪ ነህ፡፡ አንተ የደረስክበት ደረጃ ላይ የደረስከውና ያገኘህውን መልካም ነገር ያገኘህው በሰው በኩል መሆኑን አትዘንጋ! ከመወለድና ለመራመድ ከመብቃትህ ጀምሮ፡፡ አንተ በፍፁም ልትጠቀምበት የማትችለውን ዛፍ ትከል፡፡

" ታላቅነት ማለት አንተ ካለፍክ በሃላ ለሌሎች አልፎ የሚሄድና የሚዘልቅን ነገር ጀምሮ ማለፍ ማለት ነው፡፡ "

#William #James

ለራስ በልቶ መኖርና መሞት የታናሽነት ሁሉ ታናሽነት ነው፡፡ ታላላቆች ከእነሱ ለሚበልጥና ለሌላው ለሚተርፍ ነገር የሚኖሩና የሚሰሩ ናቸው ።
©goferebusiness

@quantum_tech5
Malicious Software ምንድን ነው?
⚠️ #Malicious_Software ለሚለው አጭር ስያሜ ሲሆን Virus, Worm, Trojan Horse, Spyware, Adware የመሳሰሉትን አካትቶ በውስጡ የያዘ ሰፊ ቃል(term) ነው።

▪️የኮምፒውተር ስራን በማዛባት ለ ሀከሮች ትልቅ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።
✴️ #Worm

▪️ እነዚህኞቹ ደግሞ ከ ቫይረስ ጎራ የሚመደቡ ናቸው። ልክ እንደ ሌሎች ቫይረሶች ሁሉ እራሳቸውን በማባዛት ጉዳታቸውን የሚያደርሱ ሲሆኑ በአንድ ኔትወርክ ላይ በሚገኙ ኮምፒዩተሮች እራሳቸውን በ #email, በተበከሉ ድህረ-ገፆች እና በመልዕክቶች አማካኝነት በመላክ አደገኛ መሆናቸው ግን ለየት ያደርጋቸዋል።

✴️ #Trojan_Horses

እኚህ ፕሮግራሞች ሲታዩ ጠቃሚ ቢመስሉም ጎጂ የሆነ ኮድ በውስጣቸው የያዙ ናቸው።
ብዙውን ጊዜ በ #email አልያም ደግሞ የተለያዩ ጌሞች ወይም ፊልሞች download በምናደርግበት ሰዓት ወደ ኮምፒዩተሮቻችን የሚገቡ ናቸው።
በመሰረቱ እራሳቸውን ስለማያባዙ ቫይረሶች አይደሉም ግን ብዙ ቫይረሶች እና ዎርሞች የ #trojan_virus ታክቲክን በመጠቀም ጉዳት ያደርሳሉ።

✴️ #Spyware

ይኼኛው ደግሞ ጎጂ የሆነ የ ኮምፒዩተር ፕሮግራም ሲሆን ልክ እንደ ስሙ የ #spy (ስለላ) ተግባርን የሚፈፅም ነው።
▪️ በከፈታችሁት email ፤ በጎበኛችሁት website ወይም ደግሞ download ባደረጋችሁት ፕሮግራም አማካኝነት ራሱን ወደ ኮምፒዩተራችሁ በማስገባት የግል መረጃዎቻችሁን ይሰርቃል። አንድአንድ የ #spyware ፕሮግራሞች የተለያዩ ዌብሳይቶችን ስትጠቀሙ የምታስገቧቸውን እንደ :-
🔹 #username
🔹 #password
🔹 #credit_card_information እና
🔹 #email_address
ያሉ የግል መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚያስችል #keylogger የሚባል ፕሮግራም ይጫንባቸዋል።

✴️ #Adware

#Adware ኮምፒዩተራችሁ ላይ የሚጫን software ሲሆን አንዴ ከተጫነ በኋላ የኢንተርኔት ልምዳችሁን በማጥናት ብዙ ጊዜ የምትጎበኟቸውን ድህረ-ገፆች መረጃ የያዘ ብቅታዎችን ያሳያቹሃል።
ስታስቡት ምን ችግር አለው ትሉ ይሆናል ፤ ነገር ግን የኮምፒዩተራችሁን እና የኢንተርኔታችሁን ፍጥነት ከመቀነስም አልፎ የግል መረጃዎቻችሁን በውስጣቸው ሊይዙ በሚችሉት የ #spyware ፕሮግራም አማካኝነት በቀላሉ መውሰድ/መስረቅ/ ይችላሉ።
"ፌስቡክ እና ኢንስታግራም የተቋረጠው ከእኔ እውቅና ውጭ ነው" - ኢትዮ ቴሌኮም

ከትናንት ምሽት ጀምሮ ተቋርጦ ስለነበረው የፌስቡክ እና ኢንስታግራም አገልግሎት ኢትዮ ቴሎኮም ምላሽ ሰጥቷል።

የአገልግሎቶቹን መቋረጥ በተመለከተ በአል ዓይን ዜና ማሰራጫ የተጠየቀው ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶቹ ከኩባንያው እውቅና ውጭ መቋረጣቸውን አሳውቋል።

ከትላትን ምሽት ጀምሮ የተቋረጠው የፌስቡክ እና ኢንስታግራም አገልግሎት ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ መስራት መጀመሩ ያታወቃል።
#EthiopiaCheck Telegram Poll Result

ኢትዮጵያ ቼክ በትናንትናው እለት "አጠራጣሪ ምስሎችን ተመልክተው በመተግበርያዎች አማካኝነት ማጣራት አርገው ያቃሉ? ከሆነ የትኛውን ተጠቅመው ያውቃሉ?" የሚል ጥያቄ ለቴሌግራም ተከታታዮቹ አቅርቦ ነበር።

በውጤቱም 72% በመተግበርያዎች አጣርቼ አላውቅም፣ 17% Google Reverse Image Search፣ 14% Google Images፣ 4% TinEye፣ 4% Search by Image App፣ 1% PicSearch እንዲሁም ሌላ 1% Yandex የሚል መልስ ሰጥተዋል።

መልስ በመስጠት 1,195 ሰዎች በተካፈሉበት በዚህ መጠይቅ እጅግ የሚልቁት መላሾች (861 ሰዎች) መተግበርያዎችን በመጠቀም አጠራጣሪ ምስሎችን አጣርተው እንደማያውቁ ገልፀዋል።

ይህም በግልፅ የሚያሳየው በርካታ የሀገራችን ማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ሶሻል ሚድያ የሚለቀቁ ምስሎች ላይ በራሳቸው ማጣራት እንደማያደርጉ ነው፣ ይህም በራሱ ለሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አስተዋፅዖ እንደሚያደርግ አመላካች ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች በግላቸው ምስሎችን ማጣራት አስፈላጊ እንደሆነ ያምናል። ከዚህ በታች እነዚህን የማጣርያ መተግበርያዎች ይጠቁማል:

TinEye
https://tineye.com/

Google Reverse Image Search
https://lens.google/

Search by Image App
https://play.google.com/store/apps/details?hl=en&id=com.palmteam.imagesearch

Google Images
https://images.google.com/

PicSearch
https://www.picsearch.com/

Yandex
https://yandex.com/images/touch/
ኮምፒተር ከመግዛታችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ የኮምፒተር ባህርያት እና የኮምፒተር ክፍሎዎች እነማን ናችው ? በአጪሩ እንያቸው !
👉1ኛ ፡- ራም (RAM(Random Access Memory)) - በጣም ወሳኝ የሆነ የኮምፒተር ክፍል ሲሆን ይህም ጊዜያዊ የዳታ ማከማቻ ነው በሶፍትዌር ይሁን በሲስተም የሚፈጠሩ ጊዜያዊ ዳታዎች ራም ላይ ይጠራቀማሉ ማለትም ስራ ላይ በመሆኑበት ጊዜ ከዛም ቆሚ ዳታዎች ወደ ስቶሬጅ ይላኩሉ ፡፡
👉2ኛ:-ፕሮሰሰር (Processor) ስራ በፍጥንት የምሰራት ፕሮሰስ የማደረግ አቅም በፕሮሰሰር ይወሰናል ለምሳሌ የፕሮሰሰር አይነቶዎች core i 3, core i 5, core i 7 .
👉3ኛ ማከማቻ(Storage): - ዳታዎችን በቆሚነት የሚከማቹበት ቦታ ስቶሬጅ ይባላል::
👉4ኛ Screen Size (ስክሪን ሳይዝ) :- ዲስፕለይ ስክሪን አጠቃላይ የኮምንፒተር የሚወጡ ውጤቶዎችን የምናይበት ነው ለምሳሌ 14 ኢንች፣17 ኢንች ፣19 ኢንች .
👉5ኛ ጥራት (Resolution) : - ከኮምፒተሩ የሚፈጥርው ውጤቶዎች ጥራት የሚለካበት መንገድ ነው ቪድዮ፣ካሜራ የሚፈጥሩት ውጤት ጥራት ምን ያህል እንደሆን ይለካል ለምሳሌ 1080p፣4k ወ.ዘ.ተ
👉6ኛ Size and weight (መጠን እና ክብድት) :- ቀላል ነው ወይ ? ውፍረቱ ክብድቱ ለመያዝ ይምቻል ወይ ? ይዞ ለመንቀሳቀስ አመችነቱን ማየት ያስፈልጋል::
👉7ኛ ኦፕሬቲንግ ሲስተም( Operating system ) :- የትኛው ኦፕቲንግ ሲስተም ቢጫንበት ይመከራል ታስቦ የተሰራ ከየትኛው ኦፕቲንግ ሲስተም ጋር ነው ፡፡
👉8ኛ ዋጋ(cost) :- እንደ ግዢ ዋጋውን ግምት ውሰጥ ማስግባት ይኖርብናል ማለትም ከምንፈለገው አላማ ጋር ማስተሳሰር ስራው ግድ የተሻለ አቅም የሚፈልግ ከሆነ መልካም ነው አልያ ለቀላል ስራ እና ለመዝናኛ ከሆነ ትንሽ ቆየት ያሉትን ኮንፒተር ብንገዛ የዋጋ ቅናሽ ይኖራል እና በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ግዴታ በቀር ይቅርብ ምርት መያዝ አይጠበቅብንም ፡
ማጠቃለያ - ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶዎች ኮንምፒተር ስፔክ ወይም ማብራርያ ወረቀት ላይ ማግኘት ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ የዋለ ወይም ያገለገለ ከሆነ ደሞ ሻጪ እና ባለሙያ በመጠየቅ ማውቅ ይቻላል ፡፡
ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን ላይ Sleep, Hibernate, Shutdown ልዩነታቸው ምንድን ነው?

ኮምፒውተርም እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትም ከተለመደው ፍጥነቱ ዘግይቶ መንቀራፈፍ ይጀምራል። በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ በተለያዩ መንገዶች ኮምፒውተራችን ማጥፋት ወይም ማሳረፍ ያስፈልጋል።

ኮምፒውተራችን “ተርን ኦፍ”፣ “ስሊፕ” አልያም “ሀይበርኔት” በማድረግ እረፍት እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን። ይሁን እንጂ የትኛው የተሻለ መንገድ ነው የሚለው የሚያከራክር ጉዳይ ነው። እናም ከዚህ በታች ስለ ሶስቱ ኮምፒውተር ማሳረፊያ ዘዴዎች ጥቅሞች እና ጉዳቶች በዝርዝር እንመለከታለን።

♐️“ስሊፕ”

በቀደሙ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ “ስታንድ ባይ” የሚል ስያሜ የነበረው “ስሊፕ” የኮምፒውተራችን የሀይል ፍጆታ የሚቀንስ ነው።

ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ሞድ ላይ ስናደርገው ከራሙ በስተቀር ወደ ሁሉም የኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚሰራጨው ሀይል ይቋረጣል። የስሊፕ ሌላኛው ጥቅሙ ኮምፒውተራችን ከመዝጋታችን በፊት የተከፈቱ ስራዎችን ሴቭ ማድረጉ ነው። ከዚህም ባሻገር ያቆምነውን ስራ በፍጥነት ለመጀመር ይረዳል።

ይሁን እንጂ ስሊፕ ማድረግ ከሸት ዳውን እና ሃይበርኔት የበለጠ ሀይል ይወስዳል። በመሀል የሀይል መቋረጥ ከተከሰተም ሴቭ ሳናደርግ የተውናቸው ስራዎች ሊጠፉ ይችላሉ። በመሆኑም ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ከማድረጋችን በፊት የተጀመሩ ስራዎችን ሴቭ ማድረግ ተገቢ ነው።

♐️“ሸት ዳውን”
ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን የምናጠፋው “ሸት ዳውን” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ነው። በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር ይዘጋል፤ የራም (ራንደም አክሰስ ሚሞሪ) ሚሞሪም ይጠፋል፤በአጠቃላይ ኮምፒውተሩ ምንም እንቅስቃሴ አይኖረውም። በ”ሸት ዳውን” የተዘጋ ኮምፒውተር ምንም ሀይል አይጠቀምም። ይሁንና ኮምፒውተራችን በድጋሚ ስንከፍት ዘለግ ያለ ጊዜ (ከ“ስሊፕ” አንፃር) ይወስዳል።

♐️“ሀይበርኔት”

ይህ አማራጭ ደግሞ በ”ስሊፕ” እና በ”ሸት ዳውን” መሀል የሚገኝ ነው። “ሀይበርኔት” ስናደርግ እያከናወንናቸው የነበሩ ስራዎች በራም ሳይሆን በኮምፒውተራችን ሀርድ ድራይቭ ላይ ይቀመጣሉ። ኮምፒውተራችን ስናስነሳም ሴቭ ሳናደርግ ትተናቸው የነበሩ ስራዎችን የምናገኛቸው ሲሆን፥ ከ“ስሊፕ” አንፃር አነስተኛ ሀይል ይወስዳል። ነገር ግን ስሊፕ ያደረግነውን ኮምፒውተር ስንከፍት ከሚወስደው ጊዜ ዘግየት የማለት ባህሪ አለው። በሀይበርኔትም ሆነ “ሸት ዳውን” ኮምፒውተራችን ስናጠፋ እና ስንከፍት የምንጠቀመው ሀይል ተመሳሳይ ነው።

ኮምፒውተራችን ሀይል በመጨረስ ላይ ከሆነ “ሀይበርኔት” ተመራጭ ነው።

መቼ ነው “ስሊፕ”፣ “ሸት ዳውን” ወይም “ሀይበርኔት ማድረግ የሚኖርብን?

በቀን ውስጥ ለተከታታይ ስአታት ኮምፒውተራችንን የምንጠቀምበት ከሆነ ሙሉ በሙሉማጥፋት (ሸት ዳውን) አይጠበቅብንም። ይሁን እንጂ በቀን ውስጥ ለአንድ ስአት አልያም ለሁለት ስአት የምንጠቀም ከሆነ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋ መልካም ነው።

ካቆምንበት በአጭር ጊዜ ተመልሰን ስራችንን ለመቀጠል “ስሊፕ” ተመራጭ ነው።“ስሊፕ” ስናደርግ ኮምፒውተራችን በፈለግነው ቅፅበት ዝግጁ ይሆናል።

ለስአታት አልያም ለቀናት ኮምፒውተራችን እንዲያርፍ ስንፈልግ ደግሞ “ሸት ዳውን”ማድረጋችን መዘንጋት የለብንም።በርካታ ሰዎች የዘጉት ኮምፒውተር በፍጥነት እንዲከፈት በማሰብ “ሸት ዳውን” ከማድረግ ይልቅ “ሀይበርኔት”ን ይመርጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች እና ሶፍትዌሮች ከ”ሀይበርኔት” መልስ ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወን ሊሳናቸው ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም “ሸት ዳውን” ማድረጉ ተመራጭ ነው።

ከ“ስሊፕ” ይልቅ “ሀይበርኔት” ሀይል በመቆጠብ ረገድ የተሻለ ነው። ረዘም ላለ ስአታት የጀመርነውን ስራ ማቋረጥ ከፈለግን “ሀይበርኔት” ማድረግ ይመከራል። ለምሳሌ ለእንቅፍል ወደ መኝታ ክፍላችን ስናመራ። “ሀይበርኔት” የኤሌክትሪክ ሀይልን እና የኮምፒውተር ባትሪን ሀይል ለመቆጠብ ይረዳል።በአጠቃላይ ኮምፒውተራችን እንደምንጠቀምበት አግባብ የእረፍት ጊዜ እነዲኖረው ከላይ የጠቀስናቸውን ማሳረፊያዎች መጠቀም ይገባል። @quantum_tech5
👍1
ዊንዶዎስ 11 ተለቀቀ
የዊንዶውስ 10 ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይተካል ተብሎ የታሰበው አዲሱ የዊንዶውስ 11 ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይፋ ሁኖል በጣም ብዙ አዳዲስ እና ማራኪ ነገሮዎችን ይዞ የቀረበው ይህ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሰኔ(ጁን) 24 ሙሉ በሙሉ ይለቀቃል፡፡
የዊንዶውስ 11 ኦፐሬቲንግ ሲስተም አዳዲስ ፊውቸሮዎች መካከል
1.አዲስ አንሜሽን አክቶል(New Animation)
2 ብዙ ስራዎችን በቀላሉ እንድንሰራ የሚስችል መልቲ ታስኪንግ(Multi Tasking)
3 ተች ኮንትሮል(Touch Controls)
4. አዲስ እና ምርጥ ሳውንድ(Fresh Sounds)
5.ዳርክ ሞድ (Dark Mode)
6 የጠርዝ እጥፋት (Rounded Corner)
7.አዳዲስ አይከኖዎችን(New Icons)
8.ቨርችዎል ዴስክቶፕ(Virtual Desktop)
9.ዊጀት(Widgets)
10.አክሽን ሴንተር (Action Center)

👉 የፊታችን ሰኔ 24 ማይክሮሶፍት በሚዘጋጀው ኢቭንት ላይ ስለ ኔክስት ጀነሬሽን ዊንዶዎስ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮዎች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል መረጃውን እናደረሰዎታለን @quantum_tech5
የነገሮች ኢንተርኔት (The Internet Of Things)
ኢንተርኔት በተለምዶ እንደሚታወቀዉ ኮምፒዉተሮች ብቻ እርስ በእርሳቸዉ ተገናኝተዉ የሚሰሩበት አሠራር ታሪክ እየሆነ ነዉ ቢባል ማጋነን አይሆንም። በ1984 ዓ.ም. ከኢንተርኔት ጋር የተያያዙ ኮምፒዉተሮች 1 ሺህ ብቻ ነበር። ይህ ቁጥር በ1992 ዓ.ም. ወደ 1 ሚሊዮን ማደግ የቻለ ሲሆን በ2006 ዓ.ም. ደግሞ 600 ሚሊዮን መድረስ ችሏል። እድገቱ በሚያስገርም ሁኔታ ጨምሮ በ2008 ዓ.ም. 1 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ እስከ 2014 ዓ.ም. ያለዉ መረጃ እንደሚጠቁመው ደግሞ ከ15 ቢሊዮን በላይ የኤሌክትሮኒክ ቁሶች ከኢንተርኔት ጋር ተገናኝተዋል።
የነገሮች ኢንተርኔት (The Internet Of Things - IoT) የሚባለዉ ክስተት በዛሬ ጊዜ ከኢንተርኔት ጋር ያልተገናኘ ቁስ የሌለ አስመስሎታል። የነገሮች ኢንተርኔት (IoT) ማለት በኤሌክትሮኒክስ፣ በጂ.ፒ.ኤስ (GPS)፣ በአነፍናፊ ቁሶች (Seasors)፣ እንዲሁም በሶፍትዌር በመታገዝና የኢንተርኔት ቴክኖሎጂን በመጠቀም እጅግ በርካታ ቁሶች ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲሰበስቡ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ነዉ። እነዚህን መረጃዎች ለዕለት ተዕለት ኑሯችን በምንጠቀምባቸዉ እንደ ኮምፒዉተር፣ ስልክ፣ ቤት፣ መኪና፣ ፍርጅ፣ ቴሌቪዥን፣ ምድጃ፣ አየር ማቀዝቀዣ፣ የሙዚቃ ማጫወቻ፣ ካሜራ፣ የአየር መቆጣጠሪያ፣ መነጽር፣ ጫማ፣ የስፖርት እቃ፣ የህክምና ቁስ፣ የቢሮ ቁስ፣ የመዝናኛ ቁስ፣ ሰዓት፣ የልብስ ማጠቢያ፣ የቡና ማፍያ፣ ማብሪያ ማጥፊያ፣ አምፖል ባሉ ብዙና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች አማካኝነት በማስተላለፍ እርስ በርሳቸዉ ወይም ማዕከላዊ ከሆነ የኮምፒዉተር መረጃ ቋት (database) ጋር በኢንተርኔት አማካኝነት ተገናኝተዉ በመለዋወጥ ሰፊ አገልግሎትን እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛል።
ከየትኛዉም ቦታ ሆነን የቤታችንን የአየር ሙቀት በእጅ ስልካችን መቆጣጠር፣ መብራት ሳናጠፋ ረስተን ብንወጣ ስልካችንን በመጠቀም ማጥፍት፣ ቤታችን እንዲገባ የምንፈልገዉ ሰዉ ቢኖር ከየትም ሆነን በራችንን መክፈት፣ ብርሃን ከመስጠት አልፈዉ የዋይፋይ አገልግሎት የሚሰጡ የመንገድ መብራቶች፣ እንደ ድልድይ፣ ግድብ፣ ህንጻ፣ ያሉ መሠረተ ልማቶች እክል ሲገጥማቸዉ በተገጠመላቸዉ "sensor" እና የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ አማካኝነት በራሳቸዉ ለተቋማቱ ማሳወቅ የሚችሉ አሠራሮች የነገሮች ኢንተርኔት (IoT) ከሚሰጣቸዉ አዲስ አይነት አገልግሎቶች እጀግ ጥቂቶቹ ናቸዉ። @quantum_tech5
Important shortcut keys for computer CTRL+A. . . . . . . . . . . . . . . . . Select All
CTRL+C. . . . . . . . . . . . . . . . . Copy
CTRL+X. . . . . . . . . . . . . . . . . Cut
CTRL+V. . . . . . . . . . . . . . . . . Paste
CTRL+Z. . . . . . . . . . . . . . . . . Undo
CTRL+B. . . . . . . . . . . . . . . . . Bold
CTRL+U. . . . . . . . . . . . . . . . . Underline
CTRL+I . . . . . . . . . . . . . . . . . Italic
F1 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Help
F2 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Rename selected object
F3 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Find all files
F4 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Opens file list drop-down in dialogs
F5 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Refresh current window
F6 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Shifts focus in Windows Explorer
F10 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Activates menu bar options
ALT+TAB . . . . . . . . . . . . . . . . Cycles between open applications
ALT+F4 . . . . . . . . . . . . . . . . . Quit program, close current window
ALT+F6 . . . . . . . . . . . . . . . . . Switch between current program windows
ALT+ENTER. . . . . . . . . . . . . . Opens properties dialog
ALT+SPACE . . . . . . . . . . . . . . System menu for current window
ALT+¢ . . . . . . . . . . . . . . . . . . opens drop-down lists in dialog boxes
BACKSPACE . . . . . . . . . . . . . Switch to parent folder
CTRL+ESC . . . . . . . . . . . . . . Opens Start menu
CTRL+ALT+DEL . . . . . . . . . . Opens task manager, reboots the computer
CTRL+TAB . . . . . . . . . . . . . . Move through property tabs
CTRL+SHIFT+DRAG . . . . . . . Create shortcut (also right-click, drag)
CTRL+DRAG . . . . . . . . . . . . . Copy File
ESC . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Cancel last function
SHIFT . . . . . . . . . . . . . . . . . . Press/hold SHIFT, insert CD-ROM to bypass auto-play
SHIFT+DRAG . . . . . . . . . . . . Move file
SHIFT+F10. . . . . . . . . . . . . . . Opens context menu (same as right-click)
SHIFT+DELETE . . . . . . . . . . . Full wipe delete (bypasses Recycle Bin)
ALT+underlined letter . . . . Opens the corresponding menu
PC Keyboard Shortcuts
Document Cursor Controls
HOME . . . . . . . . . . . . . . to beginning of line or far left of field or screen
END . . . . . . . . . . . . . . . . to end of line, or far right of field or screen
CTRL+HOME . . . . . . . . to the top
CTRL+END . . . . . . . . . . to the bottom
PAGE UP . . . . . . . . . . . . moves document or dialog box up one page
PAGE DOWN . . . . . . . . moves document or dialog down one page
ARROW KEYS . . . . . . . move focus in documents, dialogs, etc.
CTRL+ > . . . . . . . . . . . . next word
CTRL+SHIFT+ > . . . . . . selects word
Windows Explorer Tree Control
Numeric Keypad * . . . Expand all under current selection
Numeric Keypad + . . . Expands current selection
Numeric Keypad – . . . Collapses current selection
¦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . Expand current selection or go to first child
‰ . . . . . . . . . . . . . . . . . . Collapse current selection or go to parent
Special Characters
‘ Opening single quote . . . alt 0145
’ Closing single quote . . . . alt 0146
“ Opening double quote . . . alt 0147
“ Closing double quote. . . . alt 0148
– En dash. . . . . . . . . . . . . . . alt 0150
— Em dash . . . . . . . . . . . . . . alt 0151
… Ellipsis. . . . . . . . . . . . . . . . alt 0133
• Bullet . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0149
® Registration Mark . . . . . . . alt 0174
© Copyright . . . . . . . . . . . . . alt 0169
Trademark . . . . . . . . . . . . alt 0153
° Degree symbol. . . . . . . . . alt 0176
¢ Cent sign . . . . . . . . . . . . . alt 0162
1⁄4 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0188
1⁄2 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0189
3⁄4 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0190
PC Keyboard Shortcuts
Creating unique images in a uniform world! Creating unique images in a uniform world!
é . . . . . . . . . . . . . alt 0233
@quantum_tech5
É . . . . . . . . . . . . . . . alt 0201
ñ . . . . . . . . . . . . . . . alt 0241
÷ . . . . . . . . . . . . . . . alt 0247
File menu options in current program
Alt + E Edit options in current program
F1 Universal help (for all programs)
Ctrl + A Select all text
Ctrl + X Cut selected item
Shift + Del Cut selected item
Ctrl + C Copy selected item
Ctrl + Ins Copy selected item
Ctrl + V Paste
Shift + Ins Paste
Home Go to beginning of current line
Ctrl + Home Go to beginning of document
End Go to end of current line
Ctrl + End Go to end of document
Shift + Home Highlight from current position to beginning of line
Shift + End Highlight from current position to end of line
Ctrl + f Move one word to the left at a time
Ctrl + g Move one word to the right at a time
MICROSOFT® WINDOWS® SHORTCUT KEYS
Alt + Tab Switch between open applications
Alt +
Shift + Tab
Switch backwards between open
applications
Alt + Print
Screen
Create screen shot for current program
Ctrl + Alt + Del Reboot/Windows® task manager
Ctrl + Esc Bring up start menu
Alt + Esc Switch between applications on taskbar
F2 Rename selected icon
F3 Start find from desktop
F4 Open the drive selection when browsing
F5 Refresh contents
Alt + F4 Close current open program
Ctrl + F4 Close window in program
Ctrl + Plus
Key
Automatically adjust widths of all columns
in Windows Explorer
Alt + Enter Open properties window of selected icon
or program
Shift + F10 Simulate right-click on selected item
Shift + Del Delete programs/files permanently
Holding Shift
During Bootup
Boot safe mode or bypass system files
Holding Shift
During Bootup
When putting in an audio CD, will prevent
CD Player from playing
WINKEY SHORTCUTS
WINKEY + D Bring desktop to the top of other windows
WINKEY + M Minimize all windows
WINKEY +
SHIFT + M
Undo the minimize done by WINKEY + M
and WINKEY + D
WINKEY + E Open Microsoft Explorer
WINKEY + Tab Cycle through open programs on taskbar
WINKEY + F Display the Windows® Search/Find feature
WINKEY +
CTRL + F
Display the search for computers window
WINKEY + F1 Display the Microsoft® Windows® help
WINKEY + R Open the run window
WINKEY +
Pause /Break
Open the system properties window
WINKEY + U Open utility manager
WINKEY + L Lock the computer (Windows XP® & later)
OUTLOOK® SHORTCUT KEYS
Alt + S Send the email
Ctrl + C Copy selected text
Ctrl + X Cut selected text
Ctrl + P Open print dialog box
Ctrl + K Complete name/email typed in address bar
Ctrl + B Bold highlighted selection
Ctrl + I Italicize highlighted selection
Ctrl + U Underline highlighted selection
Ctrl + R Reply to an email
Ctrl + F Forward an email
Ctrl + N Create a new email
Ctrl + Shift + A Create a new appointment to your calendar
Ctrl + Shift + O Open the outbox
Ctrl + Shift + I Open the inbox
Ctrl + Shift + K Add a new task
Ctrl + Shift + C Create a new contact
Ctrl + Shift+ J Create a new journal entry
WORD® SHORTCUT KEYS
Ctrl + A Select all contents of the page
Ctrl + B Bold highlighted selection
Ctrl + C Copy selected text
Ctrl + X Cut selected text
Ctrl + N Open new/blank document
Ctrl + O Open options
Ctrl + P Open the print window
Ctrl + F Open find box
Ctrl + I Italicize highlighted selection
Ctrl + K Insert link
Ctrl + U Underline highlighted selection
Ctrl + V Paste
Ctrl + Y Redo the last action performed
Ctrl + Z Undo last action
Ctrl + G Find and replace options
Ctrl + H Find and replace options
Ctrl + J Justify paragraph alignment
Ctrl + L Align selected text or line to the left
Ctrl + Q Align selected paragraph to the left
Ctrl + E Align selected

@quantum_tech5
ስልካችን ቢበላሽ እንዴት አድርገን ስልክ ቁጥሮቻችንን እናገኛለን?
ምንጊዜም ስልክ ቁጥሮቻችንን በ Backup መያዝ አለብን
~1ኛ
እንዴት Buckup እንያዝ?
🔶 Step By Step
1:-contact ዉስጥ መግባት
2:-በተለምዶ setting botton የሚባለዉ Back ከማረጊያዉ ተቃራኒዉን መጫን
3:-ከዛ import/export የሚል ሲመጣ
እሱን መጫን\
4:-ከዛ Export to Storage ወይም export to SD Card ሲመጣ የሚል ሲመጣ እሱን
መጫን በቃ በ 5 ሰከንድ ዉስጥ FileManager ላይ Coppy አርጎ ይጨርሳል ከዛ
FileManager መክፈት
5:-Phone Storage ወይም Memory Storage መክፈት
6:- VCard file ወይም ሌላ አይነት ስም ይሰጠዋል በቃ Buckup ያዝን ማለት ነዉ
7:-ከፈለግን ደግሞ ወደ Computer ላይ Coppy ማረግ ይቻላል
8:- Computer ላይ ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ከፈለጋችሁ Coppy ያደረግነዉን በ NotPad
በመክፈት ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ይቻላል
~2ኛ
2:-እንዲሁም እያንዳንዱን ስልክ ቁጥር ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ ሳይጠበቅብን እንዴት
በሰከንድ ዉስጥ ሁሉንም ስልክ ቁጥሮቻችንን ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ እንደምንችል
1:-በመጀመሪያ ከላይ እንዳሳየሁችሁ Memory Card ላይ Coppy ማድረግ አለብን
2:-ከዛ Contact ዉስጥ መግባት
3:-ከዛ setting botton ዉስጥ መግባት
4:-inport/ export ዉስጥ መግባት
5:-Import from Storage ማድረግ
3:-ስልክ ቁጥሮቻችንን SIM Card ሳንይዝ እንዴት በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንደምንችል፡፡ እዚህ ላይ የስልክ አድራሻዎቻችንን በጂሜይል / Gmail / ላይ ማሰቀመጥ ግዴታ ነዉ የአንድሮይድ ስልካችንን ከጂሜይላችን ጋር አገናኝተን የምንጠቀም ከሆነ ሁሉንም የስልክ አድራሻችንን እዛ ላይ ማኖር ያስችለናል።
በዚህ መንገድም የስልክ አድራሻዎቻንን እንዳይጠፉብን ማድረግ የምንችል ሲሆን SIM Card ሳንይዝ በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንችላለን ድንገት ቢጠፉብን እንኳ ከጂሜይል መልሰን ማግኘት ያስችለናል።
ለዚህም ይረዳን ዘንድ የጂሜይል አድራሻችን ውስጥ
~3ኛ~~~~~~~~
1:-ኢንቦክስ / inbox / ውስጥ በመግባት አድራሻ /
2:-Contacts/ የሚለውን መጫን
3:-ከሚመጡንል ምርጫዎች ውስጥ / Restore contacts/የሚለውን በመጫን የስልክ አድራሻችንን ጂሜይል ላይ ማኖር እንችላለን፡፡
@quantum_tech5
ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች።

1. የሀርድዌር መቃረን ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡

እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ

1.እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ
ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡

2. የተበላሸ ራም ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር ( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡
ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡

3. ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)
እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡
እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡

4. ቫይረስ ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡

5. መጋል በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡ ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል
ወይም ክራሽ ያደርጋል፡፡ @quantum_tech5
የተለያዩ አይሲዎችን ለመለየት የሚጠቅም ዘዴ
1. ሲፒዩ ወርቃማ እግር አለዉ፡፡
2. ቻርጅ አይሲ R22 የሚል አነስተኛ ሬዚስተር አጠገቡ ይገኛል፡፡
3. ዩአይ አይሲ 20እግር አለዉ እግሮቹም ወጣ ወጣ ያሉ ናቸዉ፡፡
4. ቪሲኦ አብዛኛዉን ጊዜ በቆርቆሮ የታሸገ ነዉ፣አልያም በወርቃማ መስመር ብቻዉን የታጠረ ነዉ፡፡
5. ክሪስታል ኦሲሌተር ጠፍጣፋ እና ሬክታንግል መልክ ያለዉ ነዉ፡፡
6. ኔትወርክ አይሲ ከክሪስታል ኦሲሌተር አጠገብ ይገኛል፡፡ ኔትወርክ አይሲ Rx ክፍል ዉስጥ ይገኛል፡፡
7. ፓወር አምፕሊፋየር አብዛኛዉን ጊዜየመጀመሪያው (ከላይ የሚገኝ)አይሲ ነዉ፡፡
8. ኤፍ ኤም አይሲ አጠገብ ባለቀለም ኢንደክተር ይኖራል፣ቀለሙም ደማቅ ወይም ደብዛዛ ሰማያዊ ነዉ፡፡
9. ብሉቱዝ አይሲሬክታንግል ቅርፅ ያለዉ ነጭ፣አነስተኛ ጠፈር ያለ አካል ከአጠገቡ ይገኛል፡፡
10. ፓወር አይሲ አጠገቡ ትንሽና ቀጭን አካል(አርቲሲ)ሁሌም ይኖራል፡፡
11. ባካፕ ባትሪ የሰአት ባትሪ የሚመስል ነዉ፡፡
12. ላይት አይሲ አጠቀቡ ትልቅ ሽቦ (ቡስተር ኮይል) ይኖራል፡፡
13. ሲም አይሲ ትንሽ፣አንጸባራቂ፣ብርማ ከለር ያለዉ ከሲም ማስቀመጫ አጠገብ ወይም ከሲም ማስቀመጫ በስተጀርባ ይገኛል፡፡
14. ኪይ ፓድ አይሲ ከኪይ ፓድ እና ከኮኔክተር አጠገብ ወይም ከሲፒዩ አጠገብ ይገኛል፡፡
15. ካፓሲተር ቀለል ያለ ቡኒ ቀለም ያላቸዉ ናቸዉ፡፡
16. ኢንደክተር ጥቋቁር እና አብዛኛዉን ጊዜ ከካፓሲተሮች በመጠናቸዉ ተለቅ ብለዉ ይገኛሉ፡፡
17. ሬዚስተር ጥቁር እና ትንሽ ክፍሎች ናቸዉ፡፡
18. ዲስፕሌይ አይሲ አብዛኛዉን ጊዜ እስክሪን ኮኔክተር አጠገብ ወይም በስተጀርባ ይገኛል፡፡
19. ሜሞሪ ካርድ አይሲ ከሚሞሪ ካርድ ካርድ ኮኔክተር አጠገብ ይገኛል፡፡
20. ካሜራ አይሲ ከካሜራ አጠገብ ወይም ከካሜራ በስተጀርባ ይገኛል፡፡
21. ኦግዝለሪ ፓወር አይሲ ይህ አይሲ የሚገኘዉ ቢቢ ፍይቭ ስልኮች ላይ ሲሆን አጠገቡ ትልቅ ሽቦ ይኖራል ፡፡
22. ሜሞሪ አይሲ አጠገቡ ብዙም ሬዚስተሮች እና ካፓሲተሮች አይገኙም ፡፡ አንዳንድ ስልኮች 2 እና ከዚያም በላይ ሜሞሪ አይሲ ሲኖራቸዉ ይችላል:: @quantum_tech5
የኮምፒውተራችን እድሜ ስንት እንደሆነ ለማወቅ👇

1. System information በመጠቀም
👉Search bar ላይ System information ብላችሁ ጻፉ

👉 ክሊክ ስትሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version/date ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ

2. CMD በመጠቀም

👉አሁንም Search bar ላይ CMD ብላችሁ ጻፉ

👉 open CMD

👉CMD ሲከፍት systeminfo.exe ብላችሁ ጻፉና ENTER በሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ:: @quantum_tech5
የኮምፒውተር ስክሪን ወደ ፈለጋችሁት አቅጣጫ ለማዞር
🔷 CTRL and ALT keys, press UP ARROW , ትክክለኛ የስክሪን እይታ

🔷 CTRL + ALT + DOWN ARROW
የኮምፒውተር ስክሪን ወደታች ይገለበጣል

🔷 CTRL + ALT + LEFT ARROW
የኮምፒውተር ስክሪን ወደ ግራ ይገለጣል.

🔷 CTRL + ALT + RIGHT ARROW
የኮምፒውተር ስክሪን ወደ ቀኝ ይገለበጣል:: @quantum_tech5
ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን ጋር ተጠቅመን ከጨረስን በኋላ eject ማድረጋችን ምንድን ነው ጥቅሙ? አስበውት ያውቃሉ እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ?
ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መልቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው እንዲወጣ መጫን ነው።
ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርዲ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ? ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋ ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን።
ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስብሰካና ስናስገባ ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል። ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተንና አስገብተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር .......... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብባወጣው። ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች።
ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተር ጋ ተሰክተው እያለ ዝም ብለን የምነቅለው ከሆነ ይህም የመበላሽት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው።
ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋ የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ።
Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው።
ምስሉን ይመልከቱ!⁉️
Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው። እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል።
ሁልጊዜ ተግባራዊ እናድርግ @quantum_tech5