Psychology Spotlight
507 subscribers
193 photos
15 videos
72 files
3 links
🌟 Welcome to Psy-COOL-ogy!
A destination for students and psychology enthusiasts. Enhance your understanding of psychology. Get study guides, short videos, and practice questions for an enjoyable learning experience. 🌟
Download Telegram
ይ ቻ ላ ል 👉 brain plasticity

💥 የህይወት እስትንፋስ እስካለን ድረስ አይምሮአችን አዳዲስ neural connections በመፍጠር እና የነበሩትን በማስተካከል እራሱን እንደገና ማቀናጀት እና ለውጥን adapt ማድረግ ይችላል
—
brain plasticity (neuroplasticity)

💥 አእምሮአችን ከልምድ፣ ከመማር፣ ከእድገት ወይም ከጉዳት ጋር በተያያዘ  በ structure እና function እራሱን መለወጥ ይችላል።

💥 ለምሳሌ ታዋቂው የማጓየር ጥናት እንደሚያሳየው የለንደን የታክሲ አሽከርካሪዎች በስራቸው ምክንያት በጣም ውስብስ የሚባለውን የከተማዋን ማሳለጫ አቅጣጫዎች የእጃቸው መዳፍ ያክል ያውቁታል። ይሄ ልምምዳቸው spatial ሚሞሪን የሚያካትተው hippocampus መጠኑ እንዲጨምር አድርጎታል።

💥 አንድ ሰው እይታውን ቢያጣ, visual cortex ከሌሎች የስሜት ህዋሳት ለምሳሌ በድምጽ መረጃን መሰብሰብ ይለማመዳል። ይሄም ማየት ለተሳነው ሰው የሌሎቹን የስሜት ህዋሳት ችሎታ ከፍ እንዲል ያደርግለታል።

💥 ስለዚህ አእምሮ plasticity ስላለው, rewire ስለሚያደርግ ተስፋ አለ።

💥 በ dedication እና በጊዜ ውስጥ አዲስ ቋንቋ መማር፣ አዲስ ችሎታ ማግኘት፣ ከ trauma መዳን ፣ ጤናማ አስተሳሰብን, ባህሪን መገንባት፣ መማር፣ መለወጥ almost ብዙ ነገር ይቻላል.....

Let's train our brain
❤5👍4💯2
በዚ መንገድ ማሰቤ፣ እንደዚ ማሰቤ ለምን ይጠቅማል? ውጤቱስ? ብለን የምናስብበት ሳምንት ይሁንልን

ተያይዘን የምንድንበት ሳምንት ይሁንልን!

ቅንነት ፊቱን ታየዋለች
🙏6🥰3
የ Gen Z እና Gen Alpha የጋራ ነገራቸው

በ2024 Oldest የሚባለው የ Z ጀነሬሽን አባል 26 እድሜ  ሲሆን የ Gen alpha ደሞ 12 ነው።

እነዚ ጀነሬሽኖች

💥 ቴክኖሎጂ ላይ fluent ናቸው።
They are of screen age.

💥ተግባር ተኮርና ችግር ፈቺ የሆነ የትምህርት መንገድን ይመርጣሉ።

💥  ከቾክና ቦርድ፣ ከመጽሃፍ እና ከlecture አጥር በላይ የሆነ የትምህርት approach ይፈልጋሉ።  ለዚህም አንዱ ምክንያት short attention span ነው ያላቸው።

💥 ነጻነትንና ግለሰባዊነትን ያስቀድማሉ።

💥 Entrepreneurial-minded ናቸው። የስራ ፈጠራ ችሎታ አላቸው።

💥 ገንዘብ መስራትን early age ነው የሚጀምሩት።

💥Global perspective አላቸው።  ከተለያየ ባህልና ህዝብ ጋር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግንኙነት የመፍጠር ችሎታ አላቸው።

💥በማህበራዊና አከባቢያዊ ጉዳይ, ለምሳሌ የአየር ንብረት ለውጥ, environmental conservation ላይ ንቁ ተሳትፎና እይታ አላቸው።

💥 ስለ አይምሮ እና ስነልቦናዊ ጤና ለማወቅ እና እርዳታ ለማግኘት የተሻለ ፍላጎት አላቸው።

💥 Generation Z ከታላቆቻቸው Millennials ወይም Gen Y ጋር የሚመሳሰሉበትም የሚለያዩበትም መገለጫ አላቸው።

💥 Gen Alpha ከመወለዳቸው ጀምሮ በቴክኖሎጂ የተጠመቁ የመጀመሪያዎቹ ትውልዶች እየተባሉ ይገለጻሉ። 

💥 በ 2025 ከአለም ህዝብ ሩብ ያህሉ Gen alpha ይሆናል።

💥 42% የ tik tok ማህበረሰብ Gen Z ነው።

ይሄ ትውልድ የተሻለ ነገር ይገባዋልና ፓሊሲዎች በተለይ የትምህርት ፣
ከዛ ደሞ ችግርና ጠባሳ የሚጥስ ትውልድ ቢፈጠርስ ብለው የሚሰጉ አካላት ይሄን ትውልድ እንዴት ያዩት ይሆን?
💯5❤3👍1
በየጊዜው የተለያዩ ተቋሟት የሃገራትን የአስተውሎት ደረጃ (intelligence level) report ያወጣሉ


💥 ሳይኮሎጂስቱ James Flynn, ፍሊን ኢፌክት (Flynn effect)  የተባለው ክስተት አሳይቶናል።

💥 በዋናነትም አስተውሎት በህዝብ ደረጃ ሊሻሻል እንደሚችል ያሳየ ጥናት ነው።  ለምሳሌ  በ አሜሪካ ከ 1970 ጀምሮ ህዝቡ በየ 10 አመቱ የ3 ነጥብ IQ score ማሻሻል እያሳየ ቀጥሏል።

💥 በተለያዩ ሃገራት በ standardized የአስተውሎት ፈተናዎች analysis መሰረት ቀጣይነት ያለው average IQ score ጭማሪዎች በህዝብ ደረጃ እንደተመዘገቡ የሚያሳዩ ጥናቶች አሉ።

💥 በገጠራማው የኬኒያ አከባቢ ባሉ ልጆች ላይ ለ 14 አመታት በተሰራው ጥናት — ልጆቹ በየአመቱ በ average የ 1 ነጥብ Flynn effect (ጭማሪ) አሳይተዋል።

💥 exact የሚባለው ምክንያት እስካሁን አከራካሪ ቢሆንም;  አመጋገብ፣ ትምህርት፣ የተሻሻለ የኑሮ ሁኔታ እና access to resources ለነዚ መሻሻሎች ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸው ባለሙያዎች ያሳያሉ።

💥 እነዚ ጥናቶች አስተውሎት በ genetics ብቻ ይወሰናል የሚለውን ሃሳብ የሞገቱ ናቸው። የ cognitive እድገትን የሚያፋጥን አከባቢ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም አስገንዝበዋል።

💥 አንድን ምግብ ለመስራት recipe ግድ ነው።
የአብሳዩ ሙያ ደሞ የሚወጣውን ሰሃን ይወስነዋል።

የ Genetics እና Environment ሚና

የ Recipe እና Chef ያህል ወሳኝ ነው
❤6👍4
IKEA

💥 ሰዎች የተሳተፏበትን፣ ያዘጋጁትን ወይም የገጣጠሙትን ነገር የበለጠ የሚወዱበት ፣ ምርጥ እንደሆነ የሚቆጥሩበት እና ዋጋ የሚሰጡበት ምክንያት IKEA effect (አይኪአ ኢፌክት) ይባላል።

ለምሳሌ: አንድ እናት ቤት ውስጥ ያዘጋጀችው ቅመማ ቅመም ወይም የምግብ ግብአት በፋብሪካ ከተቀነባበረውና ገበያ ላይ ካለው የሷ በጣም ጣፋጭ እና የተመጠነ እንደሆነ ታምናለች።

💥ወይም አንድ ሰው በጣም ጥሩ ባይሆን እንኳን እራሱ የሰራው ወይም ያደሰው ጠረቤዛ የተሻለ quality እንዳለው ያስባል።

💥 ህጻናትም ዝግጅቱ ላይ የተሳተፏበትን ምግብ በደስታ ይበላሉ።

💥 አንዳንድ አምራቾች IKEA effectን ለመፍጠር ደንበኛቸው እራሱ የሚገጣጥመውን ምርት ያመርታሉ፣ ሰዎች ፋብሪካቸውን እንዲጎበኙላቸው፣ አንዳንዴም ስራው ላይ እንዲሳተፏ ይጋብዛሉ።

💥 አይኪአ ኢፌክት, DIY (do-it-yourself) ስራዎች የሚወደዱበትም ምክንያት ነው።

💥 IKEA effect እንስሳትም ላይ ይሰራል። ለምሳሌ- አይጦች የነሱ ጥረት ያለበትን ምግብ መመገብ ይመርጣሉ።

💥 IKEA effect ከ ታዋቂው የ ሲውዲሽ ያልተገጣጠመ furniture አምራች የተወሰደ ስም ነው።
👍6❤1
Sunday night syndrome

እሁድ ማታ ላይ ምነው አርብ ከእንደገና ቢመጣ ብሎ መመኘት ፣ ከቀጣይ ቀን ጀምሮ የስራ ሳምንት መሆኑን በማሰብ ጭንቀት፣ብስጭት፣ መነጫነጭ ፣ የተረበሸ እንቅልፍ የመሳሰሉ ነገሮች ከ "Sunday night syndrome" ጋር ይያያዛሉ

ምን ማድረግ ይሻላል?

💥 ከእረፍት ቀን በፊት ለቀጣዩ የስራ ሳምንት አቅዶ መጨረስ
(ለምሳሌ:  አርብ ከሰዓት ማቀድ)

💥 የእረፍት ቀኔ ላይ መስራት አለብኝ ወይስ የለብኝም የሚለውን መወሰን። መስራት ካለብን መቼ እንደሚሰራ ሰዓት መወሰን። ይሄንንም  ከእረፍት ቀን በፊት ባለው የመጨረሻ ቀን መወሰን ይመከራል።

💥 አስቸኳይ ካልሆነ በእረፍት ቀን ላይ የስራ ጉዳይ አለማስኬድ (ሰኞ እንዲ እንድታደርጊ/ግ ብሎ email አለመላክ/ አለመቀበል) ያጨናንቃልና

💥 ብዙ ነገር weekend ላይ ማድረግ እንደምንችል በማሰብ እቅዶችን አለማብዛት።

💥 ሌላ ቀን ላይ ከለመድነው pattern ብዙም ያልተለየ መንገድ weekend ላይም መጠቀም። ሌላ ጊዜ ጠዋት የምንነሳ ከሆነ እሁድም በተቻለ ያንኑ መድገም

💥 Mindfulness እና relaxation ዘዴዎችን ማዳበር

💥 የእረፍት ቀን ላይ የግል እና ከሌሎች ጋርም ጊዜ እንዲኖረን ማመቻቸት። ዘና የሚያደረጉ ነገሮች ማድረግ።

💥 Sunday night syndrome በጣም የሚረብሽ አይነት ከሆነ እርዳታ ማግኘት ይመከራል።
❤5
Gaslighting

💥 አንድ ሰው ሃሳቡ፣ ምላሹ፣ ስሜቱ እና ትውስታው ትክክል እንዳልሆነ እንዲያስብና የራሱን ጤነኛነት እስኪጠራጠር ድረስ ማድረስ ነው።

💥Gaslighters ከእውነታው በተቃራኒ እናንተ ትክክል እንዳልነበራቹ ያሳምኗችኋል።

💥Gaslighting በራስ መተማመንን፣ የመወሰን አቅምን የሚጎዳ manipulation ነው።

💥 በተደጋጋሚ ለ gaslighting መጋለጥ, በጊዜ ውስጥ እንደ brain fog ላሉ ለከፋ የስነልቦና ቀውስ አይነቶች ሊያጋልጥ ይችላል

💥 Gaslighting የሃሳብ ልዩነት አይደለም። Intentional distortion መፍጠር ነው።

Don't buy their lie with inaccurate self-doubt
👍5
Self-reflection

የራስን behavior፣ ስሜት፣ ሃሳብና ምክንያት መታዘብ መመርመር ነው።

💥 self– reflect ስለራስ መማር ነው

💥 ማንነታችንን(ጥንካሬያችንን፣ ድካማችንን፣ ፍርሃታችንን፣ ችሎታችንን፣ ጥፋታችንን፣ ትክክላችንን፣ ልዩ የሚያደረገንን..... ፊት ለፊት የመጋፈጥ ድፍረት ነው።
It is not a one-time fix ~ ሂደት ነው

💥 Self-reflect ከእለት ድርጊት እና reaction ሊጀምር ይችላል። ከዛም አልፎ

💥 self-reflect ራስን የማሳደግ ጉዞ ነው።
አንዳንዴ በዚ ጉዞ ከምንሸሻቸው እና ተስፋ ከሚያስቆርጡን ማንነቶቻችን ጋር እንገጣጠማለን።  ይሄን ለብቻ መጋፈጥ ሲከብድ ከማቆም ይልቅ እርዳታ መፈለግ አስፈላጊ ነው።

"The curious paradox is that when I accept myself just as I am, then I can change."  Carl Rogers
💯4❤3