Psychology Spotlight
507 subscribers
193 photos
15 videos
72 files
3 links
🌟 Welcome to Psy-COOL-ogy!
A destination for students and psychology enthusiasts. Enhance your understanding of psychology. Get study guides, short videos, and practice questions for an enjoyable learning experience. 🌟
Download Telegram
ቀናችን ውስጥ ውሳኔዎች እየወሰንን ሄደን ሄደን ቀስ በቀስ ጥሩ ውሳኔ የመወሰን አቅማችን እየተዳከመ ሲሄድ decision fatigue ይባላል።

💥 ይህም የሚፈጠረው ብዙ ውሳኔዎች በመወሰናችን ምክንያት exhaust
ስለምናደርግ ነው።

💥የውሳኔ quantity ሲጨምር quality እየቀነሰ ይሄዳል። ቀላል እና ፈጣን ወደሆነው ውሳኔ እንድናዘነብልም ይሆናል።

💥 እንደ መፍትሄም የውሳኔዎችን ቁጥር መቀነስ፣ እረፍት መውሰድ፣ በቅደም ተከተል መስራት፣ በጋራ መወሰን እና ለሌሎች መወከል decision fatigue ለመቀነስ ይረዳሉ።

💥 እንዲሁም በእረፍት ቀን- ለምሳሌ አንድ ሰው ሳምንቱን ሙሉ ብዙ ውሳኔዎችን ሲሰራ ቆይቶ እሁድ ጠዋት ምን እንደሚበላ፣ ምን እንደሚለብስ ለመወሰን ሲሞክር እንኳን decision fatigue ሊገጥመው ይችላል።

💥ይሄ ሲከሰት አንዳንድ ጊዜ ለራሳችን እረፍት ለመፍቀድ እና ትንንሽ ለሆኑ ውሳኔዎች እራስን ላለማጨናነቅ decision fatigue እንዳለ ማስታወስ ይጠቅማል።

💥 the late Steve Jobs, Barack Obama,  Mark Zuckerberg, የአይምሮ ኢነርጂያቸውን ለአስፈላጊ ውሳኔዎች ለመጠቀም  የቀን ውሎዋቸውን(አለባበሳቸውን...) ቀለል  በማድረግ decision fatigue ከሚቀንሱት ውስጥ እንደሚጠቀሱ የ behavioral economics ጥናቶች ያሳያሉ።
👍10
ይ ቻ ላ ል 👉 brain plasticity

💥 የህይወት እስትንፋስ እስካለን ድረስ አይምሮአችን አዳዲስ neural connections በመፍጠር እና የነበሩትን በማስተካከል እራሱን እንደገና ማቀናጀት እና ለውጥን adapt ማድረግ ይችላል
—
brain plasticity (neuroplasticity)

💥 አእምሮአችን ከልምድ፣ ከመማር፣ ከእድገት ወይም ከጉዳት ጋር በተያያዘ  በ structure እና function እራሱን መለወጥ ይችላል።

💥 ለምሳሌ ታዋቂው የማጓየር ጥናት እንደሚያሳየው የለንደን የታክሲ አሽከርካሪዎች በስራቸው ምክንያት በጣም ውስብስ የሚባለውን የከተማዋን ማሳለጫ አቅጣጫዎች የእጃቸው መዳፍ ያክል ያውቁታል። ይሄ ልምምዳቸው spatial ሚሞሪን የሚያካትተው hippocampus መጠኑ እንዲጨምር አድርጎታል።

💥 አንድ ሰው እይታውን ቢያጣ, visual cortex ከሌሎች የስሜት ህዋሳት ለምሳሌ በድምጽ መረጃን መሰብሰብ ይለማመዳል። ይሄም ማየት ለተሳነው ሰው የሌሎቹን የስሜት ህዋሳት ችሎታ ከፍ እንዲል ያደርግለታል።

💥 ስለዚህ አእምሮ plasticity ስላለው, rewire ስለሚያደርግ ተስፋ አለ።

💥 በ dedication እና በጊዜ ውስጥ አዲስ ቋንቋ መማር፣ አዲስ ችሎታ ማግኘት፣ ከ trauma መዳን ፣ ጤናማ አስተሳሰብን, ባህሪን መገንባት፣ መማር፣ መለወጥ almost ብዙ ነገር ይቻላል.....

Let's train our brain
❤5👍4💯2
በዚ መንገድ ማሰቤ፣ እንደዚ ማሰቤ ለምን ይጠቅማል? ውጤቱስ? ብለን የምናስብበት ሳምንት ይሁንልን

ተያይዘን የምንድንበት ሳምንት ይሁንልን!

ቅንነት ፊቱን ታየዋለች
🙏6🥰3
የ Gen Z እና Gen Alpha የጋራ ነገራቸው

በ2024 Oldest የሚባለው የ Z ጀነሬሽን አባል 26 እድሜ  ሲሆን የ Gen alpha ደሞ 12 ነው።

እነዚ ጀነሬሽኖች

💥 ቴክኖሎጂ ላይ fluent ናቸው።
They are of screen age.

💥ተግባር ተኮርና ችግር ፈቺ የሆነ የትምህርት መንገድን ይመርጣሉ።

💥  ከቾክና ቦርድ፣ ከመጽሃፍ እና ከlecture አጥር በላይ የሆነ የትምህርት approach ይፈልጋሉ።  ለዚህም አንዱ ምክንያት short attention span ነው ያላቸው።

💥 ነጻነትንና ግለሰባዊነትን ያስቀድማሉ።

💥 Entrepreneurial-minded ናቸው። የስራ ፈጠራ ችሎታ አላቸው።

💥 ገንዘብ መስራትን early age ነው የሚጀምሩት።

💥Global perspective አላቸው።  ከተለያየ ባህልና ህዝብ ጋር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግንኙነት የመፍጠር ችሎታ አላቸው።

💥በማህበራዊና አከባቢያዊ ጉዳይ, ለምሳሌ የአየር ንብረት ለውጥ, environmental conservation ላይ ንቁ ተሳትፎና እይታ አላቸው።

💥 ስለ አይምሮ እና ስነልቦናዊ ጤና ለማወቅ እና እርዳታ ለማግኘት የተሻለ ፍላጎት አላቸው።

💥 Generation Z ከታላቆቻቸው Millennials ወይም Gen Y ጋር የሚመሳሰሉበትም የሚለያዩበትም መገለጫ አላቸው።

💥 Gen Alpha ከመወለዳቸው ጀምሮ በቴክኖሎጂ የተጠመቁ የመጀመሪያዎቹ ትውልዶች እየተባሉ ይገለጻሉ። 

💥 በ 2025 ከአለም ህዝብ ሩብ ያህሉ Gen alpha ይሆናል።

💥 42% የ tik tok ማህበረሰብ Gen Z ነው።

ይሄ ትውልድ የተሻለ ነገር ይገባዋልና ፓሊሲዎች በተለይ የትምህርት ፣
ከዛ ደሞ ችግርና ጠባሳ የሚጥስ ትውልድ ቢፈጠርስ ብለው የሚሰጉ አካላት ይሄን ትውልድ እንዴት ያዩት ይሆን?
💯5❤3👍1
በየጊዜው የተለያዩ ተቋሟት የሃገራትን የአስተውሎት ደረጃ (intelligence level) report ያወጣሉ


💥 ሳይኮሎጂስቱ James Flynn, ፍሊን ኢፌክት (Flynn effect)  የተባለው ክስተት አሳይቶናል።

💥 በዋናነትም አስተውሎት በህዝብ ደረጃ ሊሻሻል እንደሚችል ያሳየ ጥናት ነው።  ለምሳሌ  በ አሜሪካ ከ 1970 ጀምሮ ህዝቡ በየ 10 አመቱ የ3 ነጥብ IQ score ማሻሻል እያሳየ ቀጥሏል።

💥 በተለያዩ ሃገራት በ standardized የአስተውሎት ፈተናዎች analysis መሰረት ቀጣይነት ያለው average IQ score ጭማሪዎች በህዝብ ደረጃ እንደተመዘገቡ የሚያሳዩ ጥናቶች አሉ።

💥 በገጠራማው የኬኒያ አከባቢ ባሉ ልጆች ላይ ለ 14 አመታት በተሰራው ጥናት — ልጆቹ በየአመቱ በ average የ 1 ነጥብ Flynn effect (ጭማሪ) አሳይተዋል።

💥 exact የሚባለው ምክንያት እስካሁን አከራካሪ ቢሆንም;  አመጋገብ፣ ትምህርት፣ የተሻሻለ የኑሮ ሁኔታ እና access to resources ለነዚ መሻሻሎች ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸው ባለሙያዎች ያሳያሉ።

💥 እነዚ ጥናቶች አስተውሎት በ genetics ብቻ ይወሰናል የሚለውን ሃሳብ የሞገቱ ናቸው። የ cognitive እድገትን የሚያፋጥን አከባቢ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም አስገንዝበዋል።

💥 አንድን ምግብ ለመስራት recipe ግድ ነው።
የአብሳዩ ሙያ ደሞ የሚወጣውን ሰሃን ይወስነዋል።

የ Genetics እና Environment ሚና

የ Recipe እና Chef ያህል ወሳኝ ነው
❤6👍4
IKEA

💥 ሰዎች የተሳተፏበትን፣ ያዘጋጁትን ወይም የገጣጠሙትን ነገር የበለጠ የሚወዱበት ፣ ምርጥ እንደሆነ የሚቆጥሩበት እና ዋጋ የሚሰጡበት ምክንያት IKEA effect (አይኪአ ኢፌክት) ይባላል።

ለምሳሌ: አንድ እናት ቤት ውስጥ ያዘጋጀችው ቅመማ ቅመም ወይም የምግብ ግብአት በፋብሪካ ከተቀነባበረውና ገበያ ላይ ካለው የሷ በጣም ጣፋጭ እና የተመጠነ እንደሆነ ታምናለች።

💥ወይም አንድ ሰው በጣም ጥሩ ባይሆን እንኳን እራሱ የሰራው ወይም ያደሰው ጠረቤዛ የተሻለ quality እንዳለው ያስባል።

💥 ህጻናትም ዝግጅቱ ላይ የተሳተፏበትን ምግብ በደስታ ይበላሉ።

💥 አንዳንድ አምራቾች IKEA effectን ለመፍጠር ደንበኛቸው እራሱ የሚገጣጥመውን ምርት ያመርታሉ፣ ሰዎች ፋብሪካቸውን እንዲጎበኙላቸው፣ አንዳንዴም ስራው ላይ እንዲሳተፏ ይጋብዛሉ።

💥 አይኪአ ኢፌክት, DIY (do-it-yourself) ስራዎች የሚወደዱበትም ምክንያት ነው።

💥 IKEA effect እንስሳትም ላይ ይሰራል። ለምሳሌ- አይጦች የነሱ ጥረት ያለበትን ምግብ መመገብ ይመርጣሉ።

💥 IKEA effect ከ ታዋቂው የ ሲውዲሽ ያልተገጣጠመ furniture አምራች የተወሰደ ስም ነው።
👍6❤1
Sunday night syndrome

እሁድ ማታ ላይ ምነው አርብ ከእንደገና ቢመጣ ብሎ መመኘት ፣ ከቀጣይ ቀን ጀምሮ የስራ ሳምንት መሆኑን በማሰብ ጭንቀት፣ብስጭት፣ መነጫነጭ ፣ የተረበሸ እንቅልፍ የመሳሰሉ ነገሮች ከ "Sunday night syndrome" ጋር ይያያዛሉ

ምን ማድረግ ይሻላል?

💥 ከእረፍት ቀን በፊት ለቀጣዩ የስራ ሳምንት አቅዶ መጨረስ
(ለምሳሌ:  አርብ ከሰዓት ማቀድ)

💥 የእረፍት ቀኔ ላይ መስራት አለብኝ ወይስ የለብኝም የሚለውን መወሰን። መስራት ካለብን መቼ እንደሚሰራ ሰዓት መወሰን። ይሄንንም  ከእረፍት ቀን በፊት ባለው የመጨረሻ ቀን መወሰን ይመከራል።

💥 አስቸኳይ ካልሆነ በእረፍት ቀን ላይ የስራ ጉዳይ አለማስኬድ (ሰኞ እንዲ እንድታደርጊ/ግ ብሎ email አለመላክ/ አለመቀበል) ያጨናንቃልና

💥 ብዙ ነገር weekend ላይ ማድረግ እንደምንችል በማሰብ እቅዶችን አለማብዛት።

💥 ሌላ ቀን ላይ ከለመድነው pattern ብዙም ያልተለየ መንገድ weekend ላይም መጠቀም። ሌላ ጊዜ ጠዋት የምንነሳ ከሆነ እሁድም በተቻለ ያንኑ መድገም

💥 Mindfulness እና relaxation ዘዴዎችን ማዳበር

💥 የእረፍት ቀን ላይ የግል እና ከሌሎች ጋርም ጊዜ እንዲኖረን ማመቻቸት። ዘና የሚያደረጉ ነገሮች ማድረግ።

💥 Sunday night syndrome በጣም የሚረብሽ አይነት ከሆነ እርዳታ ማግኘት ይመከራል።
❤5
Gaslighting

💥 አንድ ሰው ሃሳቡ፣ ምላሹ፣ ስሜቱ እና ትውስታው ትክክል እንዳልሆነ እንዲያስብና የራሱን ጤነኛነት እስኪጠራጠር ድረስ ማድረስ ነው።

💥Gaslighters ከእውነታው በተቃራኒ እናንተ ትክክል እንዳልነበራቹ ያሳምኗችኋል።

💥Gaslighting በራስ መተማመንን፣ የመወሰን አቅምን የሚጎዳ manipulation ነው።

💥 በተደጋጋሚ ለ gaslighting መጋለጥ, በጊዜ ውስጥ እንደ brain fog ላሉ ለከፋ የስነልቦና ቀውስ አይነቶች ሊያጋልጥ ይችላል

💥 Gaslighting የሃሳብ ልዩነት አይደለም። Intentional distortion መፍጠር ነው።

Don't buy their lie with inaccurate self-doubt
👍5