Psychology Spotlight
507 subscribers
193 photos
15 videos
72 files
3 links
🌟 Welcome to Psy-COOL-ogy!
A destination for students and psychology enthusiasts. Enhance your understanding of psychology. Get study guides, short videos, and practice questions for an enjoyable learning experience. 🌟
Download Telegram
Addiction/ ሹሾ

ምንድነው?

💥  ሹሾ:— ምንም እንኳን የምናደርገው ወይም የምንጠቀመው ነገር ጉዳትና መጥፎ መዘዞች ቢኖሩትም ያንን ነገር ከማድረግ ወይም ከመጠቀም ራሳችንን መቆጠብ/መቆጣጠር ሳንችል ስንቀር ነው።

💥 ይህ ህመም በግለሰቡ እና ሌሎችም ላይ (ቤተሰብ፣ ጓደኛ..) በተለያየ ደረጃ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል።
👍7
ሱስን በሁለት አይነት ልናየው እንችላለን :

💥 Substance addiction:— በአንድ ንጥረ ነገር ወይም ዕጽ ላይ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥገኝነት ነው። ለምሳሌ የአልኮል፣ ጫት፣ ሲጋራ፣ paff tablet or injection የመሳሰሉ  ሲሆን

💥 Behavioral addiction:– በአንድ ድርጊት ከመጠን ባለፈ መዘፈቅ እና መቆጣጠር አለመቻል  ነው። ለምሳሌ የቁማር፣ የኢንተርኔት፣ ቪዲዮ ጌም፣ shopping (እቃ የመግዛት)፣ workaholic እና sexual related behaviors ይገኙበታል።
👍7
የስፖርት ቁማር

variable interval reinforcer And Gambling.

💥 የተለያዩ ሚዲያዎችና አለም አቀፍ መጽሔቶች አፍሪካ በስፓርት ቁማር wave እንደተመታች ያብራራሉ።

ለምሳሌ ሁላችንም የምናቀው betting አንዱ የስፖርት ቁማር አይነት ነው።

💥 እስቲ ቤቲንግን ጨምሮ የአብዛኛውን የቁማር ሱስ አንዱ ምክንያትን በ variable interval reinforcer እንየው።

variable interval reinforcer
ማለት:—

💥ለአንድ ድርጊት(behavior) ማበረታቻ ወይም ሽልማት የምናገኘው ከማይታወቅ የጊዜ ርዝመት በኋላ ነው።

💥 እናም አንድ ሰው በቁማር ውስጥ ሲሳተፍ ማበረታቻ የሚያገኘው ወይም የሚበላው በማይታወቅ እና ተለዋዋጭ በሆነ የጊዜ gap ውስጥ ነው።

💥 ይህ unpredictability ሰዎች በዛ behavior (ቁማር) ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቆዩ ያደርጋል። ምክንያቱም:

1ኛ ቀጣይ የመብላት እድላችን መቼ እንደሆነ unpredictable መሆኑ በተነሳሽነት እንድንቀጥል ያደርገናል (motivational effect).

2ኛ ቀጣይ እኔ ልሆን እችላለሁ የሚለው ተስፋ ና እምነት በከፍተኛ መሰጠት እና በተደጋጋሚ ተሳትፎ እንድንቀጥል ያደርገናል (behavioral persistence).

3ኛ በተለዋዋጭ እና unpredictable የጊዜ ልዩነት ውስጥ የሚገኘው ሽልማት ጠንካራ የስሜት ምላሽ እንዲኖረን ያደርጋል (emotional effect).

💥 ይሄ አይነቱ የ reinforcement schedule የቁማርን dynamics እንድንረዳ ሲያግዘን በተጨማሪ የ gambling intervention ስንሰራ የ ሳይኮሎጂ መርሆችን ማወቅ እንደሚያስፈልግ ያስረዳናል
👍6❤4