ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂
Photo
#አራቱ የሰው ባህሪ አይነቶች
t.me/psychoet
በዛሬው ርዕስ ለሰው ልጆች ተግባቦትና የቀን ተቀን መስተጋብር ወሳኝ ስለሆነው አመል ( Temperament) እንመለከታለን፡፡ እንደሚታወቀው ማንኛውም ባህሪ መነሻ ምክኒያት አለው ፡፡ ምክንያቶቹ ደግሞ #ተፈጥሮአዊ ወይም #አካባቢያዊ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡
1. ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ :- ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ ስንል በዘር ከወላጆቻችን የምንወርሰው ሲሆን
ለምሳሌ ፦ አንድ ልጅ እናቱ ወይም አባቱ ያላቸውን ባህሪ ሲወርስ
2. አካባቢያዊ :- ከቤተሰብ ጋር ባለ ግንኙነት ፣ በጓደኛ ተፅዕኖ ፣ በትምህርት ቤት ቆይታና በምንኖርበት ባህል የምንወርሳቸውን ባህሪያቶች ያጠቃልላል
ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው በጣም ተሳዳቢ ቢሆን ( ያን ስድብ የወረሰው በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አልያም ከሰዎች በተለያዩ መንገድ ከተመለከታውና ከሰማው ሊሆን ይችላል )
የስነልቦና ተመራማሪዎች የሰውን ተፈጥሮአዊ አመል (Temperament ባህሪ) በአራት በመክፈል ያስቀምጡታል
1 .📌ሳንጊዊን (Sanguine)
ሳቂታና ተጫዎች ...
#ተግባቢና ምክኒያታዊ ናቸው
2.📌ኮለሪክ (Choleric)
ተነጫናጭ/ አዛኝና አኩሪፊ ...
#ተግባቢና ስሜታዊ ናቸው
3 .📌ሜላንኮሊክ (Melancholic)
አይናፋር ...
#ጭምቶችና ስሜታዊ ናቸው
4. 📌ፊላግማቲክ (Phlegmatic)
ግትር...
#ጭምተኛና ምክኒያታዊ ናቸው
እነዚህ አራት የሰው አመሎች የየራሳቸው መገቸጫ አላቸው
📌ሳንጊዊን
❇️አየር ⭕️ማሕበራዊ ሰዎች
ሳንጊዊን አመል ያላቸው ዋናው መገለጫቸው አብዝቶ ተጫዎችና ወሬኛነት ፣ ነገሮችን ለመስራት ፈጣንነት ፣ ማሕበራዊነት ይገኙበታል ፡፡ ሳንጊዊኖች በጣም ተግባቢና የሕብረት ነገር የሚወዱ ናቸው፡፡ ይህ አመል ያላቸው ሰዎች ሁልጊዜም ለራሳቸው ሳይሆኑና ምንም ሳይሰሩ ኑሮአቸውን የግል ሳይሆኖ የጋራ ያረጋሉ፡፡
📌ኮለሪክ
❇️ እሳት ⭕️አስተዳዳሪዎች
ኮለሪኮች በጣም ተግባቢ ሲሆኑ የሚገለፁበት ባህሪ በውሳኔ ሰጭነታቸው ፣ በግብ ተኮርነታቸው ፣ በምኞታቸው ፣ በኢጥገኛነታቸው ነው፡፡ በተጨማሪም ኮለሪኮች ቁጡዎች ቂም የሚይዙ ለስሜት ቅርቦች ናቸው፡፡
📌ሜላንኮሊክ
❇️መሬት ⭕️ሰዎችን ከሕይወታቸው አግላይ
ሜላንኮሊክ ሰዎች አስተዋያዮችና ዝርዝር ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጪዎች ደግሞም ጥልቅ አሳቢዎችና ጭምቶች ናቸው ፡፡ ከዛ በተጨማሪ ራሳቸውን ብዙ ሰዉ ካለበት ቦታ ማግለል / ማሸሽ የሚመርጡ ናቸው ፡፡ እነዚህ አይነት ሰዎች ሁሌም ፍፁም ለመሆን የሚሞክሩና የሚፈልጉ ናቸው፡፡ይህ ባህሪ ሰዎችን ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ የሚገፋፋ ፣ ቁጥብ እንዲሆኑ የሚያረግ ነው ፡፡
📌ፊላግማቲክ
❇️ውሀ ⭕️ሰዎችን ከወደሕይወታቸው አቅራቢ
ፊላግማቲክ ሰዎች ረጋ፣ ፈታ ያሉና ከሁሉ ጋር እንደውሀ የሚራመዱ ናቸው ፡፡ ለሌሎች በጣም የሚያዝኑ ግን የራሳቸውን ስሜት በማፈን የማይገልፁ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሰዎች የተለያዩ ሀሳቦችን እና ችግሮችን ወደአንድ በማምጣት ለመፍታት የሚሞክሩ ናቸው ፡፡
✍
አንዳንድ ሰዎች ከነዚህ ባህሪያት ሁለቱን ወይንም ከዛ በላይ ሊያሳዩ ይችላሉ ፡፡ በቅርብም የተጠኑ ጥናቶች ከ4ቱ አመሎች ላይ አንድ ጨምረው 5 አድርሰውታል ፡፡ አምስተኛው ደግሞ የሁሉም ቅልቅል ያለበት ከሁሉም መሀል የሆነ ሲሆን (SUPINE )ብለው ጠርተውታል፡፡
የናንተ ባህሪ ከየትኛው ይመደባል ? በ #Comment አሳውቁኝ ?
❖__________________________________❖
ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

👍1
የማስታወስ አቅምን መጨመር! /Memory /
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)
ብዙ ጊዜ ሁላችን በተለያዩ የሕይወት መስተጋብሮች "የመርሳት" ገጠመኝ አለን ፡፡ነገሮችን ማስታወስ አለመቻል በዙሪያችን ባሉ ሰዎች መካከል እንደግዴለሽ የመታየት ፣ በስራችን አመኔታ ማሳጣት ፣ በትምህርታችን ደግሞ ያጠናነውን ያለማስታወስ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ በእርግጥ ነገሮችን መርሳት ሲበዛ እንደ ህመም ይታያል ፡፡ ለዚህም ነው በተለምዶ "የመርሳት ህመም " የሚባለዉ ፡፡ ነገሮችን አለማስታወስ ብዙ ማህበራዊ ጉዳት ካስከተለ ታዲያ እንዳንረሳ ምን እናርግ የሚለው ትልቅ ሙያዊ መልስ ያሻዋል፡፡
______________________________
ማስታወስ / ትዝታ በብዙ መንገዶች መጨመር እንችላለን በዋነኛነት የሚመጡት ግን እነዚህ ናቸው ፡፡ መፍትሔዎች ፦
✍Pay attention (ለነገሮች ትኩረት መስጠት ) : ከዚህ ክፍል 4 እና 5 እንዳስተማርኩት አንድ መረጃ ወደ አዕምሮአችን ገብቶ ለረጅም ጊዜ የሚቀመጠው በስነስርአቱ መረጃው ሲገባ ነው ስለዚህ ነገሮችን ለማስታወስ መጀመሪያውንም ወደ ውስጥ ስናስገባው በጥንቃቄና በአትኩሮት መሆን አለበት ፡፡ በብዛት የሚረሱ ሰዎች መጀመሪያውኑም ለፈተና ከላይ የሚያጠኑ ፣ የምንላቸውን ከላይ ከላይ / በግዴለሽነት የሚሰሙ ናቸው ፡፡
✍Add meaning ፦የምንሰማውን ፣ የምናየውን ነገሮች እንዳንረሳ ከዚህ ቀድም ከምናውቃቸው ጋር ማቆራኘትና ከመሸምደድ ይልቅ ትርጉሙን መረዳት ፡፡
✍Take your time ፦ በአንድ ጊዜ ነገሮችን ለመያዝ / ለማገባት ከመሞከር ጊዜ ወስደን እያረፍን ወደ አዕምሮአችን እናስገባ ፡፡
✍over learn፦ አንድን ነገር እንደምናውቀው ብናውቅም ደጋግሞ ማንበብ ፣ መስማት ፣ ማየት ለብዙ ጊዜ እንዳንረሳው ይረዳል ፡፡
✍Monitor your learning ፦ ያወቅነውን እንዳንረሳ ደጋግሞ በቃል ማለት በጥያቄ መፈተሽ ፡፡ በተለይሞ ተማሪ የሆናችሁ አንድን ነገር ስላነበባችሁ ብቻ በቂ አይደለም ይልቁንስ ያነበባችሁትን ወረቀት ዘግቶ ማሰብ እንዲሁም እውቀታችንን / ትውስታችንን በተለያዩ መንገዶች መመዘን ፡፡ አርቲስቶችን ብንመለከት (በቲያትር / ሙዚቃ ሙያ ያሉ ሰዎች) አንድን ገፀ ባህሪ አንብበው ያወቁ ቢመስላቸውም ከመድረክ በፊት ግን ብዙ ጊዜ ደጋግመው ይሉታል ይለማመዱታል ፡፡ ይህን የሚያረጉት የሚናገሩት ከራሳቸው ጋር እንዲዋሀድ እና እንዳይረሱት ነው፡፡
_______________________________
እንዲሁም መርሳትን ለመቀነስ ባለፈው ትምህርት እንደተመለከትነው በተጨማሪ *
★የግል ምክር ነገሮችን እየረሳችሁ ላላችሁ !
በጣም ብዙ ሰዎች ሳማክር አንዱ የሚነግሩኝ ችግራቸው የመርሳት ጉዳይ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የመርሳት (የአለማስታወስ) ችግር ቢኖርም በወጣቶች/ታዳጊዎች ላይም በተለያዩ ምክንያቶች መርሳት ያጋጥማል፡፡
ስለዚህ በመርሳት ለተቸገራችሁ ምክሬ እነሆ ፡- ነገሮችን መርሳት መጀመራችሁን ስትረዱ / የቅርብ ሰው ሲነግራችሁ መጀመሪያ ተረጋግታችሁ ለራሳችሁ ግዜ በመውሰድ እነዚህን አርጉ
1. በወቅቱ በብዙ ስራ / ተግባር ተወጥራችሁ ከሆነ ሀሳባችሁን በመሰብሰብ የምትሰሩትን ስራ ለመቀነስ ሞክሩ ከቻላችሁም ዋና መስራት ካለባችሁ 1/2 ስራ በስተቀር ሌሎቹን ተዋቸው ምክንያቱም መርሳት አንዱ ምክንያት በብዙ ስራ / ሃሳብ መወጠር ነው፡፡
2. ለጊዜው ለውጥ እስክታሳዩ ድረስ መስራት/ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች በሙሉ አንድ በአንድ ወረቀት ላይ በመጻፍ ተከታተሉ ፡፡በሀገራችን "በቃል ያለ ይረሳል በፅሁፍ ያለ ይወረሳል" የሚባለውን እንደምሳሌ እንኳን ብንወስድ እንኳን ተማሪዎች የሆናችሁ ክፍል ውስጥ የምትማሩት አልቆ ስትወጡ የምታስታውሱት 50% ነው ከአንድ ቀን በኀላ ደግሞ ወደ 10% ይወርዳል ፡፡ይህም ማለት የምንማረውን ሳይቀር በአንድ ቀን 90% እንረሳለን ማለት ነው ስለዚህ ነገሮችን መጻፍ ለማስታወስ ዋነኛ መሳሪያ ነው ፡፡
3. በአንድ ጊዜ አንድ ብቻ ስራ ስሩ ይህም ማስተዋላችሁን (Concentration ) ስለሚጨምር የመርሳት ችግር ይቀንሳል ፡፡
4. (Quantity) በአንዴ ጥቂት ነገር ብቻ ይማሩ / ያጥኑ ፡ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለተከታታይ 5 ሰአት ከሚያጠና ሰው ይልቅ በቂ እረፍት በየመሀሉ እየወሰደ 3 ሰአት የሚያጠና ሰው የበለጠ የማስታወስ / ያለመርሳት አቅሙ ይጨምራል ፡፡
5. ለብቻችሁ በየቀኑ በቂ እረፍት ውሰዱ ፦ ይህ እረፍት ወደ አዕምሮአችን የሚገባውን መረጃ ፍሰት ለጊዜው ስለሚቀንሰው አዕምሮአችን እንዳይጨናነቅ ይረዳል፡፡
ሌላውና ዋነኛው ነገር #በጣም እየረሳችሁ ከተቸገራችሁ ከአዕምሮ ጤና ጋር ሊገናኝ ስለሚችል ወደ ህክምና ጣቢያ እንድትሄዱ እመክራለሁ ምክንያቱም የዚህ አይነች ችግር የሚታከመው በመድኃኒትም ጭምር ነው ፡፡
፠፠______________________________፠፠
ቴሌግራም ቻናሌ t.me/psychoet
ምንጭ ፦ ካለኝ ዕውቀት ማለትም ከዚህ በፊት ከሰማኀቸው ፣ ከተማርኩት እንዲሁም ከማሰለጥነው ስልጠና ለአንባቢ እንዲቀል አድርጌ በዐማረኛ የጻፍኩት ነው ።
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛
መልካም ቀን

#ተስፋ_መቁረጥ_ከየት_ይመጣል ?
በጣም ጠቃሚ ስለሆነ #ሼር አድርጉት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)
ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ሁነው ተስፋ የለኝም ፣ ተስፋዬ ተሟጧል ፣ የመሳሰሉትን ቃላት በቀን ተቀን ሕይወታቸው ይጠቀማሉ ፡፡
ተስፋ መቁረጥ ወደ ግባችን / ፍላጎቶቻችን እንዳንደርስ የሚያረገን ባህሪ ነው ፡፡ በሕይወቱ ብዙ ጊዜ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ወደግቡ/እቅዱ የመድረሱ እድል በጣም አነስተኛ ነው ፡፡ ወደ ጠቃሚ የሕይወት ግባችን አለመድረስ ደግሞ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት ፣ የበደለኝነት ስሜት ያመጣብናል ፡፡
ሳይኮሎጂ ችግር የመፍቻ ዋና መንገዱ የችግሩን ምክንያት መረዳት እንደሆነ ያትታል ፡፡ስለሆነም የተስፋ መቁረጥ ዋና ዋና ምክንያቶች እንመለከታለን፡፡
_______________________
1.Environmental Factor (አካባቢያዊ ምክንያት)
በአካባቢያችን ያሉ የተለያዩ ሁኔታዎችና ገጠመኞች ፍላጎቶቻችንንና እቅዳችንን እንዳናሳካ ይከለክሉናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ማድረግ የምንፈልገውን ነገሮች " አትችለውም ፣ ይከብድሀል ፣ ከዚህ በፊት አልተሞከረም ፣ ሰው ምን ይልሀል" በማለት ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ያደግንበት ባህል ፣ የምንኖርበት አካባቢ ለማድረግ ያቀድነውን ነገር እንዳናሳካ በራሱ ሊይዘን ይችላል ፡፡ ይሄ በሕይወታችን ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል ፡፡
2.Personal inadequency Factor (ግላዊ ብቃት/ክህሎት ማጠር )
ይህ ደግሞ ፍላጎቶቻችንን እንዳናደርግ የሚገድበን አለመሙላት (ብቃት አልባነት) ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድን እቃ በጣም ወደነው ለመግዛት ስንፈልግ ከተወደደብንና ያለን ገንዘብ አነስተኛ ከሆነ ተስፋ ቆርጠን ላንገዛ እንችላለን ፡፡ እዚህ ጋር ነገሩን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አለመኖር የራሳችን የሆነ ጉድለት ይሆናል፡፡ ሌላው አንድን ነገር ለመስራት አስበን የግል ችሎታ / ብቃት/ ክህሎት ሲያንሰን እሱ " በቃ አልችልም " በማለት ተስፋ ለመቁረጥ መንስኤ ይሆነናል ፡፡
3. Conflict of interest ( የፍላጎት ግጭት )
የመጨረሻው የግላዊ ፍላጎቶች/ ግቦች እርስ በእርስ ሲፃረሩ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችላል ፡፡ ተስፋ መቁረጡ የሚመጣዎ ሁለቱንም ግቦቻችንን ልናሳካ ባለመቻላችን ነው ፡፡ አንዱን ግብ ብናሳካ ራሱ ሌላውን ስላላሳካን የመወላወል ተስፋ የመቁረጥ ( የማዘን ) ስሜት ይሰማናል፡፡
ከነዚህ ሶስቱ ዎና ዎና ምክንያቶች እግጅ በጣም ብዙ ሰው የሚያጋጥመው የመጨረሻው (.Conflict of Motives / የፍላጎት ግጭት ) እንደሆነ ሳይኮሎጂ ይጠቁማል፡፡
______________________________
እነዚህ Conflict of motives ( የፍላጎት ግጭት ) ደግሞ በ አራት ይከፈላሉ ፡፡
______________________________
ሀ. Approach - Approach Conflict
(ፍላጎት ፥ ፍላጎት ግጭት)
ይህ ግጭት ሁለት ነገሮችን በእኩል ፈልገን ነገር ግን መምረጥ የምንችለው አንዱን ብቻ ሲሆን ማለት ነው ፡፡ ለምሳሌ :- ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኅላ Department ሲመርጡ ብዙ ተማሪዎች በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ የdepartment ምርጫዎች ይወጠራሉ ነገር ግን መምረጥ የሚችሉት የወደዱትን ሁሉ ሳይሆን አንዱን ብቻ ስለሚሆን ግጭት ውስጥ ይገባሉ ፡፡ ሌላው ገበያ ሂደን ሁለት ሱሪዎች በጣም ወደናቸው ነገር ግን መግዛት የምንችለው አንዱን ብቻ ከሆነ ይህ አይነት ግጭት ከራሳችን ጋር ይገጥመናል፡፡
ለ. Avoidance - Avoidance Conflict (የማስወገድ ፥ የማስወገድ ግጭት)
ይህ ደግሞ ከሁለት የማንፈልጋቸው ነገሮች የግድ አንዱን መምረጥ ግድ ሲለን ነው ፡፡
ለምሳሌ ፦ ልጃችን በሰዎች ታግቶ ብር ካልከፈላችሁ ይገደላል ቢሉን ፤ እዚህ ጋር ልጁ እንዲሞትም አንፈልግም ለአጋቾቹ ብር መክፈልም አንፈልግም ፡፡ ግን አንዱን መምረጥ ግድ ይለናል ፡፡ ሌላ ምሳሌ ፦
ሐ. Approach - Avoidance Conflict (የፍላጎትና ማስወገድ ግጭት)
ይህ ደግሞ በአንድ ግብ ላይ የፍላጎትም የማስወገድም ስሜት ሲሰማን ነው ፡፡
መ. Multiple Approach - Avoidance Conflict (ብዙ የፍላጎት ማስወገድ ግጭት)
ይህ ሁላችንም በሕይወት ቆይታችን የሚያጋጥመን የለት ተለት ግጭት ነው ፡፡ እያንዳንዱ የሚገጥመን ነገር #ብዙ_አወንታዊና_አሉታዊ ነገሮች ይይዝና እሱን #መምረጥና #አለመምረጥ ችግር ይሆናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው መልኩን ፣ ገቢውን ወደን ፀባዩ አመለካከቱ ካላማረን ይሆነኛል አይሆነኝም ብለን ከራሳችን እንጋጫለን ፡፡ሌላው አንድን ስራ ስንሰራ በዉስጡ ያሉ የተለያዩ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ስገፉን ሲስቡን እንደዚህ አይነት ግጭት ውስጥ እንገባለን ፡፡
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው

Melorina.bin
8.6 MB
ከሜሎሪና መጽሐፍ የተቀነጨበ ንባብ
በአጭር ጊዜ በአንባቢያን የተወደደው የታሪክና የሳይኮሎጂ መጽሐፍ "ሜሎሪና- ስውር ጥበብ " ንባብ
"ሜሎሪና" መጽሐፍ በሑሉም መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል ፡፡
ደራሲ ናሁሰናይ ፀዳሉ
አንባቢ ዘላለም ሸምሱ
@psychoet

ራስን በመቆጣጠር ድብርትን መከላከልና መጋፈጥ
ይህን ጠቃሚ መልዕክት #Share እናድርግ
የራስ ቁጥጥርና (self-regulation) የድብርት ስሜት ተዛማጅና ግንኙነት ያላቸው የስነ-ልቡና ክስተቶች ናቸው፡፡ ራስን መቆጣጠር ማለት አንድን ነገር ከግብ ለማድረስ ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብንና ጠባይን መግራት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራስን መቆጣጠር ከግብ ወይም አላማችን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ለምሳሌ ግባችን መማር፤ጥሩ ስራ መያዝ፤ የፍቅር ጓደኛ መያዝ፤ትዳር መመስረትና ልጆች ማፍራትና የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል፡፡ እናም አላማችን ከትናንሽ የዕለተለት ግቦች እስከ ላቅ ያሉ ለህይወታችን ከፍተኛ ትርጉም ያላቸው ግቦች ድረስ ሊሆን ይችላል፡፡
ራስን መቆጣጠርና የድብርት ስሜትን ምን አገናኛቸው?
ራስን መቆጣጠር ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብና፣ጠባይንና ከአላማነችን አንጻር መግራት ነው በሚለው ከተስማማን፤ የግባችን የስኬት መጠን ከድርጊታችን በኋላ ለሚሰማን ሰሜት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ያሰብነውና ያቀድነው ነገር በተሰካ ጊዜ ደስታ፣እርካታ፣ተሰፋና ለነገ የተነሳሽነት ስሜት ይፈጥርልናል፡፡ ያሰብነውና ያለምነው ነገር ሳይሳካ ሲቀር በተቃራኒው የድብርተና ተዛማጅ አሉታዊ ስሜቶች ሊፈራረቁ ይችላሉ፡፡ በዚህም ምክኒያት ራስን መቆታጠርና ድብርት የጠለቀ ግንኙነት አላቸው፡፡
የድብርት ስሜት ለራስ ቁጥጥር ያለው እንድምታ
ምንም እንኳን የድበርት ስሜት ምችት የማይሰጥ ቢሆንም ሳይንሳዊ መላምቶችና ምርምሮች እንደሚያመላክቱት ከሆነ እራሳችን ለመቆጣጠር የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ለምሳሌ ለፍቅረኛችን ታማኝ መሆን ሲገባን በስህተት ተማኝነታችንን ብናጎድል ከፈጸምነው በኋላ የድብርት ስሜት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ነገ ተደጋጋሚ ስህተት ላለመፈጸም ለእራሳችን ግበረ-መልስ (feedback loop) ነው:: ስለዚህ አላማችን ያማረ የፍቅር ህይወት መመስረት ከሆነ ለዚህ አላማችን መሳካት የእራሳችንን ጠባይ እንድንቆጣጠር የድብርት ስሜቱ አስተዋጽኦ ያበረክታል ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ሁሌም ታማኝነታችንን እያጎደልን ከፈጸምነው በኋላ ፌሽታና ደስታ የሚሰማን ከሆነ በዛው እምነት አጉዳይነታችን የመቀጠላችን እድል የሰፋ ነው፡፡ በተመሳሳይም በትምህርታችን ጥሩ ውጤት የማስመዝገብ አላማ ቢኖረንና ጊዜያችንን በአግባቡ ሳንጠቀም የፈለግነው ውጤት ባይመጣ አሁንም የድበርት ስሜት ሊከስት ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ለእራሳችን ጠባይ ከሰነቅነው አላማ አንጻር ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ አእምሯችን እራሱን የሚገመግምበት ግብረ-መልስ ሲሆን፤ ለወደፊት ይህ እንዳይከሰት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ በአጭሩ በዚህ የአረዳድ ድባብ መሰረት የድብርት ስሜት መፈጸም በምንፈለግገውና በፈጸምነው መካከል ልዩነት ሲፈጠር የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡
ተደጋጋሚ ውድቀትና ድብርት
በተደጋጋሚ ያሰብነውና ያቀድነው ነግር በማይሳካ ጊዜ የድብርት ስሜቱም እየጠነከረ በተደጋጋሚ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት፣መንስኤና ውጤት አትኩሮት ሰጥተን እንድናሰላስል በር ይከፍታል፡፡ ይህም ክስተት rumination በመባል ይታወቀል፡፡ ይህ አጥብቆ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት ማንሰላሰል ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ አብዛኞቹ በዚህ ዙሪያ የሚያጠኑ የስነ ልቡና ጠበብቶች አጥብቆ ከልክ በላይ ማሰቡ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አጽኖት ሰጥተው ይናገራሉ፡፡
ስለዚህ ከድብርት እራሳችን ለመካከልና ለመቋቋም ምን እናደርግ?
❖ተግባራዊ ግብ
በተደጋጋሚ ነገሮች ሳይሳኩ ሲቀሩ የድበርት ስሜት የሚከሰት ከሆነ፣ በተደጋጋሚ ላለመውደቅ ሊተገበር የሚችል ግብ ማውጣት፡፡ የነገሮች አለመሳክት ሁልጊዜ የችሎታ ማነስ፣እድለቢስነትና የሌሎች ተዛማጅ ነገሮች እጥረት ሳይሆን፤ በህይወታችን የምንሰነቃቸው ግቦች ሊተገበሩ የማይችሉና የራስ ቁጥጥራችን ደካማ ስለሆነ ሊሆን ይችላል፡፡
❖ግባችን ለመምታት አስፈላጊ ግብዓቶቸን ማፈላለግ
ተግባራዊ እቅዶችን ከነደፍን በኋላ ወደዚያ ጎዳና ለመድረስ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ከእራሳችንንና ከአካባቢያችን ማፈላለግ፡፡ ተሰጥኦቻችንን ማበልጸግ፤ ድክመታችንን ማሻሻልና የሚጎድለንን መሙላት፡፡
❖ጽናት
ተግባራዊ ግቦችን ካስቀምጥንና ወደ አላማችን የሚያደርሱንን ግብዓቶችንን ካመቻቸንን፤ ቀጣዩ የአላማ ጽናት (persistence) ነው፡፡ ሁሌም አዲስ ነገር ሲጀመር በወረትና በመነሳሳት መንፈስ ማደርግ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ድርግጊቱ መሃል ሲገባና ጫና ሲበዛ መፍረክረክ ግባችንን እንዳናሳካ ያደርገናል፡፡ ፈተና ሊበዛ ይችናል፡፡ ነገር ግን ካለ ተግዳሮትና ፈተና የሚገኝ የቤተሰብ ውርስ ብቻ ነው፡፡ የራሳችን ነገር፣ በእራሳችን ብርታት የምንፈልግ ከሆነ ፈተናና ተግዳሮት አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም ከፈተናና ተግዳሮት ልምድ መቅሰምና እራሳችንን እንዲጠቅመን መቀየር ነው፡፡ ለዚህም ራስን ማዘጋጀት፡፡ ሁሉም ነገር አልጋባልጋ ይሆናል ብለን ከተነሳን፤ በኋላ ተግዳሮቶች ሲከሰቱ የመንፈስ ስበራቱ ያለምነው ግባችን ላይ እንዳንደርስ መሰናክል ይሆናል፡፡ ስለዚህ ለተግዳሮቶችና ፈታናዎች ራስን በማዘጋጀት የአይበገሬነት መንፈስ መቀናጀት፡፡
❖አንዴ አልተሳካም ማለት ህይወት አከተመላት ማለት አይደለም
ህይወት መስመሯ አባ ጎርባጣ እነደመሆኑ መጠን ዛሬ ያቀድነው ነገር አልተሳካም ማለት አጠቃላይ ህይዎታችን አለቀላት ማለት አይደለም፡፡ እንደዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ለድበርት ስሜትና ለሌች የስነ ልቡና ችገሮች መከሰት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ምክኒያታዊ ያልሆነ አስተሳሰብ (irrational belief) ነው፡፡ ዛሬ ያፈቀርካትን ልጅ ስላላገኘሀት አጠቃላይ የፍቀር ህይዎትህ ዜሮ ሆነ ማለት አይደለም፡፡ ዛሬ የፈለግኸውን ስራ ስላላገኘህ የነገ መንገድህ ተቆረጠ ማለት አይደለም፡፡ ያለተሳካው ከብዙ የህይወት ግብ ውስጥ እንዱ ወይም የተወሰኑት ናቸው፡፡ ህይወት ደግሞ በአንድና ሁለት እቅድ አትመዘነም፡፡ ይህም የህይወትንና የተፈጥሮን ታላቅንት ማሳነስ ነው፡፡
❖ራስን መቆጣጠር ልምምድ ይፈልጋል
እንግዲህ ተግባራዊ ግብ ማስቀመጥና አስተሳሰባችንን፤ውስጠ ስሜታችንንና ጠባይያችንን ከዚህ ግብ አንጻር መግራት የራስ ቁጥጥር አንኳር መገለጫዎች ናቸው፡፡ የማይተገበር ግብ ማስቀመጥም ለውድቀት ይዳርጋል፤ ተግባራዊ ግብ ቢኖረንም በጽናት ጠባይያችንንና nአስተሳሰባችንን ካልገዛነውም ለውድቀት እንዳረገልን፡፡ ስለዘህ እራሳችንን የመቆጣጠር ክህሎት ለመካን ከትናንሽ ነገሮች ጀምረን እንለማመደው፡፡ ያኔ የስብእናችን ዋነኛ ምሰሶ ይሆናል፡፡
(በአሸናፊ ካሳሁን)
©Zepsychology

እንኳን ለ 2013 ዐዲስ አመት አደረሰን!
#ሜሎሪና መጽሐፍ ለዐዲሱ አመት ስጦታ፡፡
በብዙ አንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሜሎሪና ልብወለድ መጽሐፍ ለአንባቢያን በቀረበ በኹለት ወር ውስጥ ሦስተኛ ህትመት የተሰጠና ብዙዎች አንባቢዎችን ቀጣዩን በጉጉት እንዲጠብቁ ያደረገ መጽሐፍ ነው፡፡
መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው ሥነልቡናዊ ልቦለድ ሲሆን የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው የማያቋርጥ ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበባዊ ሚና የሚተርክና ከፍተኛ የአስተሳሰብ ልዕልናችንን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው ፡፡ አቀራረቡም አስተማሪ የሥነልቡና ምክሮችንና ሀሳቦችን ከታሪካዊ ክስተቶች ጋር ደምሮ የያዘ ነው፡፡
|ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብ ወለድ|
ከመጽሐፉ የተወሰዱ ሀሳቦች
~~~~~~~~~~~~~~~
‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››
______
‹‹ኢትዮጵያዬ ቅደሚ፣ አንቺ ስትቀድሚ ልጆችሽ ደስ ይለናል፡፡ አንቺ ስትለሚ ከስደታችን እናርፋለን፤ አንቺ ስትበለጽጊ ዓለም ሁሉ ወዳንቺ ይመጣል›› እያለች ስታለቅስ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ታቤል በልጅነት አእምሮው ‹ኢትዮጵያ› የሚለውን ስም የያዘው፡፡ ታቤልም ‹‹እንዲህ የምትወድድ፣ የሚታዘንላትና የሚለቀስላት ኢትዮጵያ ማን ነች?›› እያለ መጠየቅ የጀመረው ከዚያ በኋላ ነው፡፡
______
‹‹ዐይን አላችሁ? ተመልከቱ! ጆሮ አላችሁ? እንግዲያውስ ስሙ! ልብ አላችሁ? አስተወሉ! ገንዘብ ምድራዊ ሕይወት እንጂ እውነተኛን ደስታን አይገዛላችሁም፡፡ ደስታን የሚገዛላችሁ እረፍት የሚሰጣችሁ ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ የሌለው ላይመጣ ያለው ላይሄድ ዕድሜያችሁን ሙሉ ከመባዘን ተጠበቁ!›› ይሉ ነበር አበምኔቱ፡፡
_____
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~
በተለያዩ ሚዲያዎች የቀረቡ የመጽሐፉ ዳሰሳ
በEBS ቅዳሜን ከሰዓት
https://youtu.be/pCMLIRgFKdM
በETV ፈታኝ ሳጥን
https://youtu.be/XNBsOMgrd4o
በNahoo መዝናኛ
https://youtu.be/hb_7RyK203c
በአሐዱ ራዲዬ ፍኖተ ጥበብ ፕሮግራም
https://youtu.be/ULetSbHlRSI
https://youtu.be/DZWWNEP1Po4
በFana ራዲዬ ጥበባት ፕሮግራም
https://youtu.be/I07rjVHMKM0
በመጽሐፍ መደብሮችና አዟሪዎች እጅ ይገኛል!
_____________________________
በዐዲስ አበባ
ለገሀር ✿ጃፋር (ኖክ አጠገብ - ተወልደ ህንጻ)
ሜክሲኮና ስታዲየም ናሽናል ታወር ✿ሀሁ (ደብረ ወርቅ ህንፃ አጠገብ)
ጥቁር አንበሳ ✿እነሆ (ትራኮን ታወር)
ካዛንቺስ ✿ጦቢያ መጽሐፍ ቤት
ቦሌና አራት ኪሎ ✿BOOK LIGHT
በተጨማሪም ከሌሎችም መጽሐፍ መደብሮችና መጽሐፍ አዟሪዎች ላይ ታገኙታላችሁ
_____________________________
በክልሎች
በአዳማ +251923736714
በአዋሳ +251916617743
+251940479245
በሌሎች ችልሎች የምትገኙ አንባቢያን መጽሐፉን ከየመደብሩ ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡
_____________________________
ከኢትዮጵያ ውጭ
አሜሪካ +12022947117
ኢንግላድ +447577009720
_____________________________
በዐዲስ አበባ ሜሎሪና ቤታችሁ ድረስ እንዲመጣ ከፈለጋችሁ +251939115238 ደውላችሁ እዘዙ ።
መጽሐፉን በብዛት ማከፋፈል የምትፈልጉ 0912664084 መደወል አሳታሚውን ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡
መልካም ንባብ !
ለምትወዱት ሰው ለዐዲስ ዓመት የምትሰጡት ግሩም ስጦታ
ሜሎሪና 💚💛❤️
መልዕክቱን ለሌሎችም በማጋራት እናድርስ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂ pinned «እንኳን ለ 2013 ዐዲስ አመት አደረሰን! #ሜሎሪና መጽሐፍ ለዐዲሱ አመት ስጦታ፡፡ በብዙ አንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሜሎሪና ልብወለድ መጽሐፍ ለአንባቢያን በቀረበ በኹለት ወር ውስጥ ሦስተኛ ህትመት የተሰጠና ብዙዎች አንባቢዎችን ቀጣዩን በጉጉት እንዲጠብቁ ያደረገ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው ሥነልቡናዊ ልቦለድ ሲሆን የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው የማያቋርጥ ትግል ውስጥ…»
ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ የሕይወት ምክሮችና እውነታዎች
📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡
📕በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡
📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡
📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡
📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡
📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖
ከሜሎሪና መጽሐፍ የተወሰዱ ሀሳቦች
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖
❖አንባቢ እናት ጥሩ ትውልድን ትገነባለችና ይቺን የመሰሉ እናቶች ይብዙልን ፡፡ ፎቶው የተላከልኝ ከወደ አዋሳ ነው ፡፡
መልዕክቱን ለሌሎችም ወዳጆቻችን #Share እናድርግ
"ሜሎሪና" መጽሐፍን በጃዕፈር ፣ በሀሁ ፣ በእነሆ ፣ Book Light ጨምሮ በሀገራችን በኹሉም ክልሎች በሚገኙ የመጽሐፍ መደብሮች ይገኛል ፡፡ ለዐዲስ ዓመት ለወዳጅዎ የሚሰጡት ትልቅ ስጦታ ፡፡ ሜሎሪና ❤️❤️❤️

አንዳንዴ እንዳሰብነው ባይሆን እንኳን እንዳሰበልን አኑሮን ከዘመን ዘመን አድርሶናል መጪውንም እሱ አብሮን ይሁን 😍 ፈጣሪ 🙇🏽
እነዚህ የጳጉሜ ቀናት የይቅርታ ፣ የምስጋና እንዲሁም የሚያልፈውን ዓመት የምንገመግምበት የሚመጣውን የምናቅድበት ቀናት ናቸው ስለሆነም
❣ሳላውቅ በስህተት❤
💙አውቄ በእህል💔
አስቀይሜ
አሳዝኜ
አስከፍቼ
💜ከሆነ ከጉልበቴ
በርከክ ብዬ💗
💞ይ
💞ቅ
💞ር
💞ታ እጠይቃለው💕
🖤በችግሬ በሃዘኔ ስከፋ ተከፋታችሁ ሳዝን አዝናችው💘
💖በደስታዬ ተደስታችው ሃሳቤን በመካፈል መፍትሄ ለሰጣችውኝ❣
💚ስሜታዊ ሆኜም
💙መታገስን ላስተማራችሁኝ💜💗
💖💕💞በዙሪያዬ
💓💗💖ያላችው
💙💜❤ኹሉ
💝አ
💝መ
💝ሰ
💝ግ
💝ና
💝ለ
💝ሁ
❣💝💕💞💓💗 መልካም አዲስ አመት 🌻🌻🌻🌻💐💐💐🌼🌼🌼ላንተ/ቺ ይሁንላችሁ ለጓደኞቻቹ ኣድርሱ እኔም🙋🙌 ከነዛ ውስጥ ከሆንኩ forward ኣድሩጉልኝ😙💕💕💕💕💕💕💕💕💕
@Psychoet

በእንግሊዝና በአሜሪካ ያላችሁ የፔጃችን ቤተሰቦች ሜሎሪናን ስትፈልጉ በእነዚህ ስልኮች በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡
★★★ አሜሪካ
+12022947117
★★★ ኢንግላድ
+447577009720
በአዲስ አበባ ያላችሁ ደግሞ እቤታችሁ ድረስ በዋጋው እንዲመጣ በዚህ +251939115238 ደውሉ ፡፡
በዚህ ፔጅ ከ 16,700 በላይ ቤተሰቦች አላችሁ ፡፡ ምን ያህሎቻችሁ ሜሎሪናን አንብባችኀል?

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂ pinned «በእንግሊዝና በአሜሪካ ያላችሁ የፔጃችን ቤተሰቦች ሜሎሪናን ስትፈልጉ በእነዚህ ስልኮች በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡ ★★★ አሜሪካ +12022947117 ★★★ ኢንግላድ +447577009720 በአዲስ አበባ ያላችሁ ደግሞ እቤታችሁ ድረስ በዋጋው እንዲመጣ በዚህ +251939115238 ደውሉ ፡፡ በዚህ ፔጅ ከ 16,700 በላይ ቤተሰቦች አላችሁ ፡፡ ምን ያህሎቻችሁ ሜሎሪናን አንብባችኀል? @Psychoet»
መነሳሳት
በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡
1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”
3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡
4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡
5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡
6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡
7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡
8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡
9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡
10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡
(በአንቶኒዮ ሙላቱ) ©Zepsychology

ኹል ጊዜ ደጋግሜ ሳነበው የሚያፅናናኝ ቃል
በሕይወታችን አንዳንድ ጊዜ ለፍተን፣ ጥረን፣ ደክመን ምንም ውጤት እናጣለን ፡፡ ይባስ ብሎ በአቅማችን የሰራነው ነገር ደግሞ ወዲያው ሲበላሽ፣ ሲወድም፣ ሲጠፋ እንመለከታለን ፡፡ በሕይወት ትግል ኹል ጊዜ ተሸናፊዎች የኾንን እስኪመስለን ድረስ ተስፋ ቆርጠን ፣ ነገር ጨልሞብን በድንግዝግዝ እንመላለሳለን ፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ ፈጣሪ የሚባል ነገር ራሱ መኖሩን እንጠራጠራለን ፤ በቃ ሕይወት ራሱ ግራ ትገባናለች፡፡
ግን እኔ ይህን አምናለሁ ፡፡ የእኛነታችን ዋንኛው ጥንካሬ የሚፈተሸው በዚህ ስሜትና ኹኔታ ውስጥ ነው ፡፡
መልካም ቀን ይኹንላችሁ ፡፡
ጷግሜ 2 ፣ 2012