ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂
Photo
ሱሰኝነትን እንዴት መከላከል ይቻላል?
#Share በማረግ ሌሎችን እናስተምር
ሱስ ስንል ማንኛውም ነገር በሰዎች ላይ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥገኝነት ስሜት በመፍጠር ሰዎች ለመነቃቃት ፤ ድብርትን ለማስወገድ ፤ ጀብዱ ለመስራት፤ ህመምን ለማስታገስና ከፍተኛ የደስታ (Euphoria) ስሜትን ለመጎናጸፍ ብለው የሚያጨሷቸው፤ የሚቅሟቸው በአፍንጫ የሚስቧቸውንና በደም ስር የሚወስዷቸውን ነገሮች በሙሉ ሲያካትት ያለ እነኚህ ሱሶች/ዕፆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴአቸውን ማከናወን ሲሳናቸው ሱስ ወይም የሱሰኝነት ጠባይ እንዳለባቸው ይገለጻል፡፡
ሰዎች ምንም እንኳን ሱስ የሚያሲዙ ነገሮችን በመጀመሪያዎቹ አካባቢ በራሳቸው ተነሳሽነት የሚወስዱና የሚጠቀሙ ቢሆንም እየዋለ ሲያድር ግን በሚያስከትለው ጥገኝነት ሱስ የሚያሲዙ ንጥረ ነገሮችንና አደንዛዥ ዕጾችን መጠቀም የግድ እየሆነ ይመጣባቸዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ በሱስ መጠመድና ተጋላጭ መሆን የአእምሮ ጉዳት ፤ የማስታወስ ክህሎት ማሽቆልቆል ፤ ተስፋ መቁረጥ ፤ እራስን መቆጣጠር አለመቻልና ሌሎች ተጓዳኝ የአካልና የስነ-ልቦና ቀውሶችንና ብሎም ሞትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በሱስና በአደንዛዥ ዕፅ ጥገኝነት የሚመጡት የጤና እክሎች በሱስ የተጠመዱ ሰዎች ሱሰኝነትን ማቆም እንዳልቻሉ የሚያመለክቱ ሲሆን ይህንን የጤና እክል ለማስወገድ የሚደረገው ህክምና አካልና አእምሮን ከሱስ ከማጽዳት አንጻር ትልቅ ጥረትና ክትትልን ይጠይቃል፡፡ ሱስና አደንዛዥ ዕፅ በሰዎች አካል ፤ አእምሮና ስነ-ልቦና ላይ ትልቅ ተጽእኖ ስለሚኖረው የሚሰጠው ዕርዳታና ህክምና በሱስ ምክንያት የተከሰቱ አሉታዊ ተጽእኖዎችን በሙሉ ያካተተ መሆን እንዳለበት ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በማስከተል ሱሰኝነትን ለመከላከል የሚያስችሉ ስልቶችን እንመለከታለን፡፡
1. መጠንን መቀነስ (Reducing dosage)
በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሱሰኝነትን ቀስ በቀስ ወይም በሂደት ለመተው እንዲችሉ የሚወስዱትን ሱስ የሚያሲዙ ነገሮችን መጠን መቀነስ ይኖርባቸዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ሱሰኝነትን ለመተው ያስቡና ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ለማቆም ይሞክራሉ፡፡ ይህ እርምጃ ምንአልባት ለአንድና ለሁለት ቀን ያገለግል እንደሆን እንጂ ዘለቄታዊ መፍትሄን ማምጣት አይችልም፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱሰኝነት በሰውነት አካል ውስጥ በደንብ የተሰራጨ ከሆነ በአንድ ጊዜ ለመተው ማሰብ ህይወትን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ ሱሰኝነትን በአንድ ጊዜ ወይም በቅጽበት ለመተው ከማሰብ ይልቅ መጠንን እየቀነሱ ለዘለቄታው እስከመተው መድረስን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
2. ውጫዊ ተጽንኦዎችን መቋቋም
ሱሰኝነት በተለያዩ ውጫዊ ተጽእኖዎች ሊባባስ ይችላል፡፡ እነዚህን ተጽእኖዎች ለመቋቋም ሱስ ከሚያሲዙ አካባቢዎች መራቅ አንዱ መፍትሄ ሲሆን ይህ የማይቻል ከሆነ ዳግመኛ በሱስ ተጽእኖ ስር ላለመውደቅ አመለካከትን መቀየር ያስፈልጋል፡፡
በአጠቃላይ ሱሰኝነትን ለማስወገድ የሚደረጉ ዕርዳታዎች ሰዎች ከአካላዊና ስነ-ልቦናዊ የሱስ ጥገኝነት ተላቀው ጤናማ ህይወት እንዲኖሩ ማስቻል ነው፡፡ በሱስ ለተያዙ ሰዎች ከሌሎች የሚደረግላቸውን እንክብካቤና ድጋፍ ማስተናገድ ቀላል ቢሆንም ከሌሎች ዕርዳታ ተላቀው እራሳቸውን ከሱሰኝነት ለማላቀቅ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ትልቅ ተግዳሮት ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም ከሱስ የሚያገግሙ ሰዎች የሱስን አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና የውስጠ ስሜት (emotional) ቁርኝነት ከልብ በመረዳት የሱሰኝነትን ስሜት በአወንታዊ መልኩ ለመግታት መታገል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሰዎች ሱሰኝነትን ካቆሙ በኋላ የድብርት ፤ የንዴትና የብስጭት ስሜት በሚሰማቸው ወቅት ከእነዚህ ስሜቶች ለመውጣት ወደ ተዉት የሱስ ህይወት ለመመለስ ያላቸው ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ እነዚህን አጋጣሚዎች በብልሃት ማስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡ መልካም ጊዜ!
3. ስነ-ልቦናዊ ህክምና (Psychotherapy)
ሰዎች ሱስና ሱሰኝነትን ከሚያሲዙ ድርጊቶች እንዲላቀቁ የስነ-ልቦና ህክምና ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ ከሱስ አካላዊ ጥገኝነት ይልቅ ስነ-ልቦናዊ ጥገኝነት ስለሚበልጥ ሰዎች በመጀመሪያ ከሱስ ነጻ መውጣት እንደሚችሉ እራሳቸውን ማሳመን ካልቻሉ ሌሎች የሚደረጉ ህክምናዎችና ዕርዳታዎች ውጤታማ መሆን አይችሉም፡፡ ማንኛውም ለውጥ ከአእምሮ ይጀምራል እንደሚባለው በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች በምክር አገልግሎት ሰጪ ባለሙያ(counselor) በመታገዝ ከሱስ ለመውጣት ስነ-ልቦናዊና አእምሮአዊ ዝግጅትና ቁርጠኝነት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሰዎች የመንፈስ ጥንካሬ አእምሯቸውን ለማዘዝ የሚያስችል አቅም ሲሰጣቸው በአንጻሩ የአልችልም ባይነትን ስነ-ልቦና ከተላበሱ አእምሮአቸው ያለመቻልን ስሜት በውስጣቸው ይዘው እንዲዘልቁ ያስገድዳቸዋል፡፡ ስለዚህ ስነ-ልቦናዊ ህክምና በሱስ የተያዙ ሰዎችን ስነ-ልቦና በማጠንከር የሱስ ጥገኝነትን ለማስወገድ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡
4. የመድኃኒት ህክምና
በአደንዛዥ ዕፅና ነጥረ ነገሮች ሱስ የተያዙ ሰዎች ሱሰኝነትን እንዲያቆሙና ከሱስ የጸዳ ህይወት እንዲመሩ ለማስቻል ከሚሰጡ ዕርዳታዎች መካከል አንዱ የመድኃኒት ህክምና ሲሆን ይህም የተለያዩ መድኃኒቶቸን በመጠቀም በሱስ የተያዙ ሰዎች ሰውነት ውስጥ የተከማቹትን መርዛማ ኬሚካሎችን ማስወገድን ያካትታል፡፡ ከሱሰኝነት ጋር በተያያዘ አብዛኛውን ጊዜ የመድኃኒት ህክምናዎች ለብቻቸው ዘላቂ መፍትሄ የመስጠት ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡
5.ሌሎች አማራጮችን መጠቀም
ሱሰኝነት በሰዎች አካላት ውስጥ አንዴ ከተሰራጨ መጠንን በመቀነስ ብቻ በቀላሉ ማስይወገድ ስለማይቻል መጠንን በመቀነስ ለመተው በሚደረገው ጥረት ከዚህ ቀደም ሰውነት የተላመደውን መጠን መጠቀም ስለሚፈልግ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ግድ ይላል፡፡ ሱሰኝነትን በአወንታዊ መልኩ በትክክል የሚተካው ባይኖርም ሱሰኝነትን ለመተው በሚደረገው ጥረት የሚከሰቱትን (withdrawal symptoms) እንደ ድብት ፤ ማቅለሽለሽ ፤ ትኩረት ማጣት፤ ራስ ምታት ፤ አለመረጋጋት ፤ የእንቅልፍ ሰዓት መዛባትና እንቅልፍ ማጣትን ለማስተካከል የማነቃቃት ባህርያ ያላቸውን ትኩስ ነገሮችን መውሰድ ፤ ማስቲካ ማኘክና እንደየአስፈላጊነቱ በተደጋጋሚ ጸጉርን መታጠብ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
(አንቶኒዮ ሙላቱ ©ዘ-ሳይኮሎጂስት)

የአመለካከት / ሃሳብ ልኬት
በመጀመሪያ ሰው ላመነበት ነገር ባሪያ ነው አራት ነጥብ፡፡ ምንም ብትተቸው ብትነቅፈው አመለካከቱ/እይታው በእራሱ መነጸር ትክክል ነው ለድርድር አይቀርብም (ትክክል አለመሆኑን ህሊናው ነግሮት ወይም በነጽሮት እራሱን ለለውጥ እስካላዘጋጀ ድረስ)፡፡ (ለዚህም ነው በህክምና ዘርፍ የአእምሮ ህሙማን በጥንቃቄ ሊያዙና እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ምክር የሚለገሰው፡፡ ምክንያቱም ባጋጠማቸው የጤና መታወክ ደረጃ አስተሳሰባቸው እራሳቸውንና ሌላውን እስካልጎዳ ድረስ ጤናማ ናቸው ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ልብ ይሎአል፡፡ ግን በጣም ታመውም ምንም አንዳልሆኑና እንዳልታመሙ ሆነው ሊከራከሩና ከህክምና ሊርቁም ስለሚችሉ የሌሎች ዕርዳትና እገዛ የሚያስፈልጋቸው፡፡ እንደው በአጋጣሚ አነሳውት እንጂ ሃሳባችንና ትኩረታችን “ጤናማ ሰው” ብለን የምናስበውን ነው፡፡) ይህ ማለት ግን የአንዱ እውነት ወይም የሌላው ምልከታ በሌሎች አረዳድና ግንዛቤ ትክክልና ቀቡል ነው ማለት አይቻልም ሊሆንም አይችልም፡፡ እዚህ ጋ የአንዱ እውነት/ሐሰት ለሌላው ሐሰት/እውነት ሊሆን የሚችለው በንጽጽር መልኩ ካየነው ብቻ ነው፡፡ ያለ ንጽጽር እውነትም ሐሰት ነው ሐሰትም እውነት ነው፡፡ ለብቻው ቀጥ ብሎ የሚቆምና የሚኖር እስካልሆነ ድረስ፡፡
ታዲያ እኔ ከአንተ በሃሳብ ልስማማምና ላልስማማም እንደምችል ካወቅህ አንተም በራስ መንገድ አሸናፊ ነህ እኔም እንደዚያው፡፡ ግን የአንድን ነገር እውነታ በንግግርና በክርክር እንግለጸው ካልክ ሁለታችንም እውነት ነው ብለን ካመንበትና ከተነሳንበት የእይታ ስፍራ ያደረግነውን መነጽር ማውለቅ አለብን፡፡ ምክንያቱም አሁን ልንነጋገር እየተንደረደርን ያለነው ስለ አንጻሪዊ እውነትነት ወይም ሐሰትነት ሳይሆን በሁለታችን መሃል ስላለው ተቀባይነት ነው፡፡ ስለዚህ በሃሳብ መቀመሪችን እንነጋገራለን እንፋጫለን (ከስሜት በጸዳ መልኩና በምክንያት) ልኬቱ በተስተካከለ ፤ በሰከነ ፤ በአስተዋይነት ፤ ዕውቀትንና ቅንነትን መሰረት ያደረገ አመለካከት ከሆነ መቁረጫው ቀላል ነው የሚሆነው፡፡ የሃሳቡን መቁረጫ ልኬት ወደ አወንታዊነት ስለሚቀይረው፡፡ እንደ እኔ እይታና አረዳድ አወንታዊነት (positivity) የአንድን ነገር መልካም ጎን ብቻ መመልከት ሳይሆን ደካማውን አካቶ ሚዛናዊ የሆነውን መያዝ ነው፡፡ የአወንታዊ ምልከታው በሃምራዊ መነጸር እይታ የተጋረደ መሆን የለበትም፡፡ መነጽሩ የሚያሳየን ማየት የምንፈልገው ነገር ብቻ ስለሆነ:: በአስቀመጥነው የሃሳብ/አመለካከት ልኬት ለመቁረጥ መነጽሩ መውለቅ አለበት በሁሉም አቅጣጫ ለማየት እንዲያስችለን፡፡ ከዚያ በኋላ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ሁለታችንም አሸናፊዎች ስለሆንን በልዩነትና በመከባበር እናልፈዋለን፡፡ ለዘለፋና ለትችትም አጋልጦ አይሰጠንም፡፡ ስለዚህ የእኛ የሃሳብ ልኬት በእራሳችን ወይስ በሌሎች ንጽጽር መለካት/መቆረጥ ያለበት? በሁለቱም እንደ ነገሮች ሁኔታ ቢለያይም፡፡
(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©zepaychologist

የካንሰር ተጋላጭነትን መቀነስ
#Share
በካንሰር ህመም ምክንያት በዓመት ውስጥ በመላው ዓለም የበርካታ ሰዎች ህይወት ያልፋል፡፡ ድሮ ድሮ የካንሰር በሽታ የአደጉት አገሮች ችግር ብቻ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡ በአሁን ወቅት ግን አድማሱን በማስፋት በታዳጊ አገራት ላይም ትልቅ ተጽእኖን በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ የአገራችንን ኢትዮጵያ ሁኔታ እንኳን ብንመለከት በእርግጠኝነት ያለውን ቁጥር ማስቀመጥ ባይቻልም ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በዓመት ውስጥ 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ወገኖቻችን ለጋንሰር ተጋላጭ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡ ካንሰርን የሚያድን መድኃኒት እስካሁን ባይገኝም አስቀድሞ ተጋላጭነትን ግን መከላከል ይቻላል፡፡ እንዴት?
ፈጽሞ ትምባሆና የትንባሆ ውጤቶችን አለማጨስ፡፡
ቤታችንና አካባቢያችንን ከትንባሆ ጢስ ነጻ ማድረግ፡፡
ዘውትር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ
ጤናማ የአመጋገብና የኑሮ ዘይቤ በመከተል፡፡
የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም ወይም መጠንን መቀነስ፡፡
ከፍተኛ የሆነ የፀሐይ ብርሃን ተጋላጭነትን መቀነስ ወይም የፀሐይ ብርሃን መከላከያ መጠቀም፡፡
ጡት ማጥባት የእናቶችን ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
ህጻናትን የሄፓቲቲስ ቢና ኤችፒቪ ክትባቶችን (Hepatitis B and HPV) ማስከተብ፡፡
በየጊዜው ምርመራ ማድረግ…ወዘተ
©Zpsychologist
#Share
@Psychoet

ያዘነን ሰው ማጽናናት
#Share አርጉት
ደስታና ሃዘን የአንድ ሳንቲም ገጽታዎች ናቸው፡፡ በህይወታቸን ውስጥ ደስታ እንዳለ ሁሉ በተለያየ ምክንያት ሃዘን ሊያጋጥመን ይችላል፡፡የምንወደው ሰው መታመም ወይም ሞት፤ ያፈቀርነውን ማጣት፤ የህልማቸን አለመሳካት፤ በህይወታችን ውስጥ ትካዜን ከሚፈጥሩ ጉዳዮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ አብዛኞቻችን በራሳችን የህይወት ልምድ ውስጥ ማዘንን ብናውቀውም ያዘኑ ሰዎች ሲያጋጥሙን እንዴት ማጽናናት እንዳለብንና ምን ማድረግ እንዳለብን ለማወቅ እንቸገራለን፡፡ መባል የሌለበትን ነገር በማለት ያዘኑ ሰዎችን ሃዘን ልናባብስ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፡-
ሃዘን ቤት ሄደን የሟች ቤተሰብን ያጽናናን መስሎን “የታመመው ምን ነበር? ህክምና ወስዳቹሁት ነበር?… ከስቃዩ ማረፉ ይሻለዋል፤ በዚህ ዕድሜው ተቀጨ…እንግዲህ ፈጣሪ ካመጣው ምን ይደረጋል….” የሚሉ ሃሳቦች በተደጋጋሚ ሲሰነዘሩ እንሰማለን፡፡ እነዚህ ነገሮች ቤተሰብን በማሰልቸትና ሟቹን እንዳይረሳ በማድረግ ሃዘንን ያባብሳሉ፡፡ ለምን ይህ ሃዘን በእኔ ላይ መጣ የሚል ስሜት በመፍጠር ሃዘንተኛውን ጸጸትና ድብርት ውስጥ ሊከቱ ይችላሉ፡፡
በጣም ደክሞ ሊሞት የሚያጣጥር ሰው ቤት ሄደን በቤተሰቡ ፊት “እንግዲህ የሚመጣውን ለመቀበል መዘጋጀት ነው… ተስፋ ያለው አይመስልም….ዛሬን የሚያድር አይመስልም” ብንል የቤተሰቡን ጭንቀት እናባብሳለን፡፡
በፍቅረኛዋ መከዳት ልቧ የቆሰለን ሴት “ቀድሞውንም ሰውየው እንደማይረባሽ ነግሬሽ ነበር….እንዴት ከዚህ ዓይነት ሰው ጋር እስካሁን ቆየሽ…” እና የመሳሰሉትን ሃሳቦች ማንሳት ለተጎጅዋ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል
የሃዘን ደረጃዎችን መረዳት፡- ሰዎች በሃዘን ወቅት የሚያልፉባቸው 5 ደረጃዎች አሉ፡፡
ደረጃ 1፡ ሰዎች ሃዘን ሲያጋጥማቸው የመጀመሪያ ምላሻቸው ችግሩን መካድ (Denial) ነው፡፡ የቤተሰባቸው አካል መሞቱን አምኖ መቀበል ይከብዳቸዋል
ደረጃ 2፡ ከፈጣሪ ጋር መደራደር (Bargaining)፡-ሃዘን ውስጥ ያሉ ሰዎች ለምን ይህ ችግር በእኔ ላይ መጣና ጥፋቴ ምንድን ነው… የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ፈጣሪያቸውን ይሞግታሉ
ደረጃ 3- ቁጣ (Anger)፡ ያዘኑ ሰዎች በትንሹም በትልቁም ሊነጫነጩና ሊቆጡ ይችላሉ
ደረጃ 4- ድብርት (Depression)፡ ያዘኑ ሰዎች ተገቢውን ድጋፍና ዕርዳታ ካላገኙ በከፍተኛ ድብርት ውስጥ ይገባሉ
ደረጃ 5-ማጣትን መቀበል (Acceptance)፡- በጊዜ ሂደት ውስጥ ያዘኑ ሰዎች ያጡትን ነገር ለመቀበል ውስጣቸውን ያሳምናሉ
ያዘኑ ሰዎችን ለማጽናናት ማድረግ የሚገቡን ጉዳዮች፡-
ስሜትን መጋራት፡- ራሳችንን ባዘነው ሰው ቦታ ማስቀመጥና ስሜቱን እኔ ብሆንስ በሚል መንፈስ መረዳት፡፡ ለምሳሌ፡- አባትህ በሞት በመለየታቸው ሃዘን ተሰምቶኛል፤ ፍቅረኛሽ ትቶሽ በመሄዱ ምን ሊሰማሽ እንደሚችል እረዳሻለሁ፡፡
ማዳመጥ፡- ሰዎች ሃዘን ውስጥ ሲሆኑ ብዙ ማውራት፤ ብሶታቸውን ማካፈል ይወዳሉ፡፡ ስለዚህ ጥሩ አድማጭ መሆን ሃዘንን የመካፈል ሂደት ነው፡፡ ነገር ግን ማውራት የማይፈልጉትን ነገር እንዲነግሩን መወትወት አይገባም፡፡
ለዕርዳታ ዝግጁ መሆንን መግለጽ፡-“ወንድምህን እያስታመምክ እንደሆነ አውቃለሁ…እኔ ልረዳህ የምችለው በምን መልኩ ነው?” እና የመሳሰሉ ሃሳቦችን በማንሳት ሃዘንተኛው ከጎኑ መሆናችንን እንዲያውቅ ማድረግ፡፡
ማቀፍ፡-አንዳንዴ ያዘነን ሰው ምን ማለት እንዳለብን ሲቸግረን አላስፈላጊ ቃላት ከመሰንዘር ይልቅ ዝም ብሎ በማቀፍ ሃዘንን መጋራት ይቻላል፡፡
ሃዘንን ለመርሳት በቂ ጊዜ እንደሚያስፈልግ መረዳት፡- ሰዎች ከሃዘን ለመውጣት መጠኑ የተለያየ ጊዜ ያስፈልጋቸውል፡፡ አንዳንዶች በቀላሉ አገግመው ወደ ዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሲመለሱ ሌሎች ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ ከሃዘን ጋር ሲታገሉ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ይህ የሚወሰነው በሃዘኑ ዓይነትና በተጎጂው የስነ-ልቦና ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ስለሆነም በተቻለ መጠን ላዘኑ ሰዎች በቂ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት “ሃዘኑ ይበቃሃል…. ራስሽን በጣም እየጎዳሽ ነው…በአንተ ላይ ብቻ የተከሰተ ችግር አደረግከው” እና የመሳሰሉትን ቃላት በማውጣት ሃዘንተኛውን ከመወትወት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡
(በሰብለወንጌል አይናለም)
©Zepsychologist

👍2
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂ pinned «ያዘነን ሰው ማጽናናት #Share አርጉት ደስታና ሃዘን የአንድ ሳንቲም ገጽታዎች ናቸው፡፡ በህይወታቸን ውስጥ ደስታ እንዳለ ሁሉ በተለያየ ምክንያት ሃዘን ሊያጋጥመን ይችላል፡፡የምንወደው ሰው መታመም ወይም ሞት፤ ያፈቀርነውን ማጣት፤ የህልማቸን አለመሳካት፤ በህይወታችን ውስጥ ትካዜን ከሚፈጥሩ ጉዳዮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ አብዛኞቻችን በራሳችን የህይወት ልምድ ውስጥ ማዘንን ብናውቀውም ያዘኑ ሰዎች ሲያጋጥሙን…»
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂
Photo
የሶሻል ሚዲያ ጥቆማ
ይህን ፔጅ ገብታችሁ Like & Follow ብታረጉ ብዙ ቁም ነገር ትገበያላችሁ !
fb.com/SafeLightMovement
t.me/safelightofficial
አራት ነገሮች ድባቴን ለማስወገድ፥
1. የፀሐይ ብርሃን (SUN)፦ የፀሐይ ብርሃን የሴሮቶኒን (Serotonin) መጠንን በመጨመር ካለንበት የድባቴ ወይም ከአሉታዊ ስሜት (Negative Energy or Pessimistic) እንድንወጣ ያደርጋል:: በቀን ከ15-20 ደቂቃዎች የፀሐይ ብርሃንን ብንወስድ ድባቴን ልናስውግድ እንችላለን።
2. ሰውን ማዋራት (TALK)፦ ይህ ሁለተኛው መንገድ ሲሆን ድባቴ በዋነኝነት ከሚያስከትለው የብቸኝነት እና ከሰው ጋር ያለመቀላቀል ስሜት ለማስወገድ ‘’ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው።’’ እንደሚል ፈሊጡ ለሰው ማካፈል አስፈላጊ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የህብረተሰብ ክበቦች (Social Clubs) ላይ መሳተፍ ድባቴው መተንፈሻ ያገኛል።
3. የራስን ግፅታ ማሳመር (GROOM):- በድባቴ ወቅት የራስን ግፅታ ማሳመር ውሰጣዊን እርካታ ይጭራል፡፡ ይህም ሰዎች ለእናንተ ያላቸውን አስታየት እንዲቀይርና አዎንታዊ አስታየቶችን በመሰንዘር ከነበራችሁበት የድባቴ ስሜት እንድትወጡ ይረዳል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የራስ መተማመናችሁን እንዲሁም የስራ ምርታማነታችሁን በመጨመር ረገድ ትልቅ አስተዋፆ አለው፡፡
4. ማንነትን ማስታወስ (IDENTITY)፡- ሁሌም ልታስታውሱት የሚገባው ዋናው ነገር በድባቴ ወቅት በሽታ አይደላችሁም፡፡ ማርቲን ሉተር አንድ ጊዜ እንደተናገረው ‘’ጨለማን ጨለማ ሊያሸንፈው አይችልም ብርሃኑ እንጂ፡፡’’ ስለዚህ በሽታን በሽታ ሳይሆን ግለሰቡ ብቻ ሊያሸንፈው የሚችለው፡፡ እናንተ አልማዝ በጭቃ ተለውሶ ከመሬት በታች እንደሚገኘው ሁሉ እናንተም በድባቴ ተከባችሁ የከበረ ማንነት እንዳላችሁ አስታውሱ፡፡
ተስፋ እነኝህን ጥቆማዎች እንድትወስዷቸው የሚያደርግ መሳሪያ ነው፡፡ ተስፈኛ ሰው መንፈሰ ጠንካራ ነው፡፡ መንፈሰ ጠንካራ ችግር የማያጋጥመው ሳይሆን ችግርን የሚያይበት መንገድ የተለየ መሆኑ ነው፡፡
ይህን መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ በማስተላለፍ ሌሎችም እንዲጠቀሙ ያድርጉ፡፡
#SafeLightRecommendation
#InspireEmpowerTransform
ይህን ፅሑፍ የወሰድኩት በአነቃቂ ንግግሮቹና በሕይወት ክህሎት ስልጠናዎቹ ከሚታወቀዉ ስለሺ (ሳልስ) ሴፍ ላይት ፔጅ ነው ፡፡ በተጨማሪ ለወጣቶች በነፃ የተለያዩ የስልጠና እድሎችን የሚያመቻች መልካም ራዕይ ያለው ወጣት ነው ፡፡
Facebook ፔጁን Like & follow አርጉት
fb.com/SafeLightMovement
በ Telegram
t.me/safelightofficial ታገኙታላችሁ ፡፡
መልካም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችንን ማበረታታቴን እቀጥላለሁ ፡፡

#ክፍል_10
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE
#LOVE_Styles / #የፍቅር_አይነቶች
_______________________
ዛሬ የሳይኮሎጂ 10 ኛ ትምህርታችንን ወጣ ባለ ርዕስ ላይ ነገር ግን ለሁላችን አስፈላጊና ወሳኝ ስለሆነው ስለ ፍቅር እንወያያለን ፡፡
ፍቅር በተለያዩ ሙያዎች አንፃር በተለያየ መንገድ ተተርጉሟል ፡፡ Social psychology (በማህበራዊ ሳይኮሎጂ ) አንዱን ትኩረቱን በዚህ ላይ በማረግ የተለያዩ የፍቅር ትርጉም ፣ አይነት ... ላይ ያተኮሩ ጥናቶችን ያበረክታል ፡፡
በአጠቃላይ ስናየው ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ቶሎ በፍቅር ይወድቃሉ ሴቶች ደግሞ ተግባራዊ ጓደኛነትን መሰረት ባደረገ ፍቅር ይሳባሉ ፡፡ ፍቅር በብዙ መንገድ ተተርጉሟል ። ከነዚህ በጥቂቱ
*ለሰው ከዝምድና / ከቅርበት የተነሳ ያለን ጥልቅ ስሜት
*ከፆታዊ ፍላጎት ምክንያት ያለ መሳሳብ ወዘተ ......
_______________________
ይህ ብዙ ትርጓሜ ያሉት ፍቅር ስድስት አይነት የፍቅር አይነቶች /ዘይቤዎች / እንዳሉት ማህበራዊ ሳይኮሎጂስቶች ይናገራሉ ፡፡ እነዚህም
1.Eros-ኤሮስ ፦ለኛ ልዩ ውበት ያለውን ሰው በማየት የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ።
በዚህ ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ገና እንዳዩ የሚሰማ ጥልቅ የፍቅር ስሜት ነው ፡፡
2.Storge-ስቶርጄ :- ይህ ደግሞ ከጓደኛነት የተነሳ የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር የሚመነጨው በመለማመድ ፣ በመቀራረብ ፣ አብሮ ጊዜ በማሳለፍ ነው ፡፡
3. Ludus-ሉደስ ፦ ፍቅርን በጨዋታ መልክ የሚገለፅበት ዘይቤ ነው ፡፡
በዚህ #ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር በብዛት በማማለል የሚፈጠር ሲሆን ስራዬ ተብሎ ያልተያዘ ፍቅር ነው ፡፡
4. Mania-ማኒያ ፦ እጅጉን በኔነት ስሜት የሚያፈቅሩና ፍቅራቸውን በብዙ መከራ ራሱ የማይጥሉበት የተወሰነ ጊዜ የተቆጠረበት የፍቅር ግንኙነት ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።
5. Pragma- ፕራግማ ፦ ይሄ ደግሞ በምክንያት የተደገፈ ፍቅር ሲሆን በባሕሪ ፣ ባስተሳሰብ የሚመስለንን ሰው የምናፈቅርበት ዘይቤ ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።
6. Agape- አጋፔ፦ይህ የፍቅር አይነት ያለአንዳች ምክንያት የምናፈቅረውን ሰው ከራሳችን በላይ የምናስቀምጥበት ነው ፡፡
ይህ የፍቅር ብዙ ጊዜ ከእምነት ጋር ይያያዛል ፡፡ እንደዚህ የሚያፈቅሩ ሰዋች ፍቅረኛዬ ከሚጎዳ እኔ ልጎዳ ፣ ከሚቸገር እኔ ልቸገር የሚሉ ናቸው ፡፡
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !
በተጨማሪ አንድን ሰው እንደምናፈቅረውና እንደማናፈቅረው የምናውቅበት የሳይኮሎጂ መለኪያ መስፈርት በቴሌግራም ላይ አያይዤላችኀለሁ!
______________________________
🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉
ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ የመጀመሪያ አመት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚማሩበትን ሳይኮሎጂ መጽሐፍ ቴሌግራሜ ላይ POST ስላረኩኝ DOWNLOAD ማረግ ትችላላችሁ፡፡ በግሌ የይዘቱ ስፋት ላይ ጥያቄዎች ቢኖሩኝም GENERAL PSYCHOLOGY መጽሐፍ ለጠየቃችሁኝ ግን እንደመጀመሪያ ጥሩ መሳሪያ ነው፡፡
ቴሌግራም ሊንክ 🚙 t.me/Psychoet 👍
፠፠______________________________፠፠
ምንጭ ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማስተማሪያ መሳሪያዎች (ለማደንቀው የማህበራዊ ሳይኮሎጂ መምህሬ ዴቭ )
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛
በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 t.me/Psychoet 👍
ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂ pinned «#ክፍል_10 (በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE #LOVE_Styles / #የፍቅር_አይነቶች _______________________ ዛሬ የሳይኮሎጂ 10 ኛ ትምህርታችንን ወጣ ባለ ርዕስ ላይ ነገር ግን ለሁላችን አስፈላጊና ወሳኝ ስለሆነው ስለ ፍቅር እንወያያለን ፡፡ ፍቅር በተለያዩ ሙያዎች አንፃር በተለያየ መንገድ ተተርጉሟል ፡፡ Social psychology (በማህበራዊ ሳይኮሎጂ ) አንዱን ትኩረቱን በዚህ…»
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂
Photo
መጥረቢያህን ሳለው!!
በአንድ ከተማ ውስጥ የሚኖር እንጨት ፈላጭ ነበር፡፡ ሆኖም ቋሚ የሆነ ስራ ስለሌው ገቢው እየዋዠቀበት ለመኖር እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጠረበት ስለሆነም ወደ አንድ የጣውላ መሰንጠቂያ ድርጅት በመሄድ ባለቤቱን ስራ እንዲቀጥረው ጠየቀው ኃላፊውም የስራ ፈላጊውን የሰውነት ፈርጣማነት እና የስራ ተነሳሽነቱን በማድነቅ ከሚሰራበት ደን ውስጥ የተወሰነ ቦታ በመከለል ዛፎችን የመቁረጥ ስራ ሰጠው፡፡ በመጀመሪው ቀን 18 ዛፎችን ቆረጠ፤ በዚህ የተደሰተው አለቃም እጅግ በጣም ጥሩ ስራ እንደሰራና እንደሱ ዓይነት ዛፍ ቆራጭ አይቶ እንደማያውቅ እንዲሁም በዚሁ እንዲቀጥልበት አበረታታው፡፡ በአለቃው የማበረታቻ ቃላት የተነሳሳው ዛፍ ቆራጭም በሁለተኛው ቀን በበለጠ ተነሳሽነት ወደ ስራው መጣ ሆኖም ግን የቆረጠው ዛፍ 15 ነበር፤ በሶስተኛው ቀን ደግሞ 10 ዛፎችን ቆረጠ፡፡ ቀናት አልፈው ቀናት በተተኩ ቁጥር የሚቆርጠው የዛፍ ቁጥር እያነሰ እያነሰ እንደውም ከሁሉም ዛፍ ቆራጮች ዝቅተኛ የሆነ የዛፍ ቁጥር የሚቆርጠው እሱ ሆኖ አረፈው፡፡ አለቃውም ይህን የማያሻሽል ከሆነ ከስራው እንደሚያባርረው ነገረው በዚህ የተደናገጠው ዛፍ ቆራጭም የዕረፍት ሰዓቱን ጭምር በመሰዋት ቢሰራም ጠብ የሚል ነገር ጠፋ፤ ጥንካሬዬን አጥቻለው ሲልም ደመደመ፡፡ በመጨረሻም አለቃው መጥቶ ከስራው እንደተባረረ ነገረው፤ በሁኔታው ግራ የተጋባው ዛፍ ቆራጭም የተቻለውን ሁሉ ቢጥርም ምን የሚፈይደው ነገር ማጣቱን ምን እየተፈጠረ እንዳለ ግራ እንደገባው ነገረው፡፡ ሁኔታው የገባው አለቃም መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ መጥረቢያህን የሳልከው ብሎ ሲጠይቀው ዛፍ ቆራጩም መጥረቢያዬን ለመሳል ጊዜ አልነበረኝም አለው፡፡ ስለዚህ የችግሩ ምንጭ የነበረው የሰውየው ጥንካሬ ማጣትና የስራ ተነሳሽነት ሳይሆን የመጥረቢያው አለመሳል ነበር፡፡
ከላይ ካነበብነው አጭር ታሪክ ውስጥ ራሳችንን አስገብተን ካየነው ለስራ ከመነሳታችን በፊት ወይም በስራ ላይ እያለን እረፍት ማድረግና አዕምሮን እንዲሁም አካልን ማሳረፍ ለሚቀጥለው ስራ አብዝቶ እንደሚያዘጋጀን ነው፡፡ ይህ የማይሆን እንደሆነ እና ሁልጊዜ ስራችንን ብቻ አትኩረን የምንሰራ ከሆነ ውጤታማነታችን እየቀነሰ ወይም እዛው ባለበት ይቀጥላል ስለዚህ ውድ የ ዘሳይኮሎጂስት ቤተሰቦች ሁላችንም መቼም አንድ ዓይነት ነገርን ዐዕምሮን የማሳረፊያ መንገድ አንጠቀምም ሆኖም ግን በራሳችን መንገድ የሚያዝናንን ነገር እየመረጥን አዕምሮና አካላችንን ለሚቀጥለው ውጤታማ ስራችን ማዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ እስኪ እነዚህን ጥቂት አዕምሮን እና አካልን የማሳረፊያ መንገዶችን አብረን እንዝለቃቸው ፡-
#ከቤተሰብ ጋር ጊዜን ማሳለፍ
ስንቶቻችን ነን ጠዋት ወተን ማታ የምንገባው ? ከልጆቻችንን ጋር በቂ ጊዜ የምናሳልፈው? ከትዳር አጋራችን ጋር ወጣ ብለን እራት የምንገባበዘው? ቤቱ ይቁጠረው ፡፡ እንደውም እንዳንዶቻችን ወደ ቤት የምንገባው በስራ ከመወጠራችን የተነሳ እራት በልቶ ለመተኛት ነው፡፡ ግን ይሄ እየቆየ ውጤታማነታችንን እየሸረሸረ እንዲሁም ከቤተሰባችን እያራቀን ስለሚሄድ ትኩረት መስጠት ወሳኝ ነው፡፡በህይወታችን ከገንዘብ በተጨማሪም ሌሎች ወሳኝ ነገሮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡
#የተለያዩ መጽሕፍትን ማንበብ
ማንበብ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማፍለቅ እንደ ግብዓት ሆኖ ያገለግላል፤ እንዲሁም አዕምሮን ለማሰረፍ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ታዲያ መጽኃፍት ስንል ልብ ማለት የሚገባን ከስራችን ጋር የተገናኙ መጽሀፍትን ማንበብ እሰየው የሚያስብል ቢሆንም ቅሉ ግን ታሪካዊ፣ ኃማኖታዊ ፣ ፖለቲካዊ ………ወዘተ እንደምርጫችን ማካተትም ይኖርብናል፡፡
#ሙዚቃ፣ ስዕል ፣ ፊልም ቲያትር…. ላይ ጊዜን ማሳለፍ
በህይወታችን ላይ ጥብብን እንደ አንድ የማስከኛ እና የማደሻ መንገድ በመጠቀም የደከመን አዕምሮ እና አካልን እንደገና በማነቃቃት እና ለሚቀጥለው ስራ ማዘጋጀት ይመከራል፡፡
#ኃይማኖታዊ ህይወት ማዘውተር
የዕረፍት ጊዜን ከማሳለፊያ መንገዶች አንዱ የኃይማኖት ተቋማትን በማዘውተር ከፈጣሪ ጋር ግንኙነትን ማጠናከር እና የተለያዩ ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች ላይ መሳተፍ ይበረታታል፡፡
#የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ማዘውተር
በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅሰቃሴዎች ላይ መሳተፍ እና በቀዝቃዛ ውኃ ሰውነትን መታጠብ ህይወታችን ላይ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰራተኞች ከማያደርጉት የበለጠ በስራቸው ውጤታማና ቀልጣፋ ሆነው ተተገኝተዋል፡፡
#ከጓደኞቸ ጋር ሰብሰብ ብሎ መሳቅ መጫወት
መቼም በጉጉት ከሚጠበቁትት የእረፍት ማሳለፊያ ነገሮች መካከል ከአብሮ አደግ ጓደኞች፣ ከቢሮ የስራ ባልደረቦች እንዲሁም ከልባዊ ወዳጆች ….ወዘተ ጋር ተሰብስቦ ስለ ተለያዩ ነገሮች እያወሩ መሳቅ እና መጫወት አንዱ ነው፡፡ ይህ ክዋኔም አዕምሮን በማደስ አካልን ያነቃቃል፡፡
#ቀናችንን በፕሮግራም መምራት
በቀን ውስጥ የምንሰራቸውን ስራዎች በቅደም ተከተላቸው መሠረት እና የሚወስዱበትን ጊዜ ጨምረን ፕሮግራም እናውጣ ከስራችን መኃልም የእረፍት ጊዜን ማካተት እንዳንረሳ፡፡
#አጭር የዕንቅልፍ ሠዓት ይኑረን
በቀን ውስጥ ሲበዛ ለ20ደቂቃ እንቅልፍ ማሸለብ ውጤጣማ እና ቀልጣፋ እንደሚያደርግ ብዙ ጥናቶች አመላክተዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህን የእንቅልፍ ሰዓት ማራዘም በራሱ ጉዳት እንዳለው ልብ ይለዋል፡፡
ውድ ቤተሰቦች ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገውና በግሌ የተሳሳተ አባባል እና አመለካከት የሚመስለኝ አንድ አቢይ ጉዳይ አለ፤ ይህም ብዙዎቻችን እረፍትን ጊዜ ማሳለፊያ ብቻ ነው እንጂ የምንለው እና የምንቆጥረው እንጂ በህይወታችን ላይ ዓይነተኛ ሚናን እንደሚጫወት ድረጊት አይደለም፡፡ ግና ወዳጆጄ ይህን ጉዳይ በደምብ ማጤን አለብን ይህንም ስል እረፍት በራሱ እንደ አንድ ዓቢይ ነገር በመያዝ የህይወታችን አንድ አካል ማድረግ እንዳለብን ነው፡፡ ጠንካራ፣ ጎበዝ እና ለውጤት የሚታትር ሰው መሆን እጅግ የሚበረታታ ሰብዕና እና ባህርይ ነው ሆኖም ግን ይህ ነገር ገደቡን አልፎ ስራ ብቻ ላይ ከሆነ ትኩረታችን አዕምሮኣችንን እያደነዝንና አካላችን እያደከምን መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዕረፈትም ጊዜ በመስጠጥ ልክ እንደመጥረቢያው እኛም ሁልጊዜ አዕምሮአችንን መሳል ይኖርብናል፡፡ ጽሁፌን በአብርሃም ሊንከን አባባል ልቋጨው ዛፍ ቁረጥ ብለህ 6 ሰዓታትን ብትሰጠኝ 4ቱን የምጠቀምበት መጥረቢያዬን በመሳል ነው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ…. መልካም ሳምንት
#Share
©(ቁምላቸው ደርሶ ©ዘ-ሳይኮሎጂስት)

ከኢንተርኔት ሱሰኝነት ነጻ መውጣት
ክፍል 1 #Share
የኢንተርኔት ሱሰኝነት ምንድነው?
ከኢንተርኔት መስፋፋት ጋር በተያያዘ ሁኔታ በዓለም ላይ ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡፡ በተለይ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ኢንተርኔት መጠቀም ከተቻለ ወዲህ ብዙ ኮምፕዩተር የሌላቸው ሰዎች የተለያዩ ድረ-ገጽችን ለማሰስ ዕድል አግኝተዋል፡፡
ኢንተርኔት መጠቀም ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በርካታ ጥቅሞች እንዳለው የታወቀ ነው፡፡ ኢንተርኔት ለመረጃ፣ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ፣ ለንግድ፣ ከሰዎች ጋር ግንኙነት ለማድረግና ለሌሎችም ነገሮች ከፍተኛ ጥቅም አለው፡፡ ሆኖም ሰዎች በተገቢ ሁኔታ ካልተጠቀሙበት ወደ ሱስነት ደረጃ በማደግ ህይወትን ሊጎዳ የሚችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው በራሱ ክፉ ባይሆንም የአጠቃቀም ሁኔታው ስርዓት ባለውና በገደብ ካልሆነ ወደ አሉታዊ ውጤት ሊያመራ ይችላል፡፡
የኢንተርኔት ሱሰኝነት ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ የመጣ ችግር ነው፡፡ ይህም በኢንተርኔት ላይ በሚደረጉ በማንኛውም ነገሮች ደስታንና እርካታን ለማግኘት ከመጠን በላይ በኢንተርኔት ላይ ጊዜ ማባከን ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ የተለመደውን መልካም ህይወት መምራት ሲያቅትና በተለያዩ የህይወት ገጽታዎች ላይ አሉታዊ ጫና ሲፈጠር እንዲሁም መተው ፈልጎ መተው ያለመቻል ስሜት ሲፈጠር ሱሰኝነት ውስጥ ተገባ ማለት ነው፡፡
#የኢንተርኔት ሱሰኝነት ምልክቶች
አንድ ሰው የአልኮል መጠጥ ሱሰኛ መሆኑን የምናውቅበት ምልክቶች እንዳሉ ሁሉ፣ የኢንተርኔት ሱሰኛ መሆንም የሚታወቅባቸው መሠረታዊ ምልክቶች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹን እንመለከታለን፡፡
1. በኢንተርኔት ላይ የሚሰሩ ነገሮችን ሁልጊዜ ማሰብ፡- በኢንተርኔት ሱስ የተያዙ ሰዎች ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ጊዜ ብዙ ጊዜ በኢንተርኔት ላይ ሲያደርጉ የቆዩ ነገሮችን ያስባሉ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ በኢንተርኔት ላይ ሲገቡ የሚያደርጉ ነገሮችን ያስባሉ፡፡ በአጠቃላይ በአእምሮአቸው ውስጥ ትኩረት ያለው ነገር እነርሱ በኢንተርኔት ላይ የሚያደርጉአቸው ድርጊቶችና ሊያደርጉ የሚፈልጉአቸው ነገሮች ናቸው፡፡
2. ኢንተርኔትን ለእርካታ መጠቀም፡– ሰዎች ኢንተርኔትን ለተለያዩ ነገሮች ይጠቀማሉ፡፡ በሱስ የተያዙ ሰዎች ግን በአብዛኛው ኢንተርኔትን የሚጠቀሙት ደስታና እርካታ ለማግኘት ነው፡፡ እርካታቸው እንዲጨምርም በዚያ ላይ ብዙ ሰዓታትን ያባክናሉ፡፡ ኢንተርኔት የእርካታ ምንጫቸው ይሆናል፤ በዚያ የሚያገኙትን እርካታ በሌሎች ድርጊቶች እንደማያገኙ ያስባሉ፡፡ ስለዚህ የእርካታ ምንጫቸው ከሆነው መራቅ አይፈልጉም፡፡ ከዚያ ሲርቁ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ትርጉም ማጣት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡
3.መቆጣጠር የሚቻል ነገር እንዳልሆነ ማሰብ፡– በኢንተርኔት ላይ ብዙ ጊዜያቸውን ማጥፋታቸው ተሰምቶአቸው፣ ለመተው ሙከራ ያደርጋሉ፤ ሆኖም አሁንም እዚያው ሲሆኑ ራሳቸውን ያገኛሉ፡፡ ለመተው ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አድርገው በተደጋጋሚ ደግሞ አይሳካላቸውም፡፡ ከቆይታ በኋላ ኢንተርኔትን መጠቀም ማቆም ወይም መቆጣጠር የሚቻል ነገር አይደለም ብለው ወደ ማመን ይደርሳሉ፡፡
4. ሳይፈልጉ በኢንተርኔት ላይ መቆየት፡– ኢንተርኔት ላይ ለመቆየት ካሰቡት ጊዜ በላይ በዚያ ላይ ያባክናሉ፡፡ አሁን አሁን እንደሚተው እያሰቡ ግን በሚያደርጉትና በሚያዩት ነገር እየተወሰዱ ይሄዳሉ፡፡
5. ህይወታቸው ስኬታማ አለመሆን፡– በኢንተርኔት ሱስ መያዝ ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ቀደም ብሎ ዋጋ ያላቸውን፣ ትኩሰረት ይሰጡ ለነበሩ ነገሮች ለምሳሌ ግንኙነት፣ ትምህርት፣ ስራና ሌሎች መልካም ዕድሎችን ችላ ማለት ይጀምራሉ፡፡
6. መዋሸት፡– በኢንተርኔት ሱስ የተያዙ ሰዎች ስለኢንተርኔት አጠቃቀማቸው (ምን ያህል ጊዜ እንደሚጠቀሙ ሲጠየቁ) ትክክለኛውን መረጃ አይናገሩም፡፡ ከዚህም የተነሳ እነርሱን መርዳት የሚችሉ ሰዎችም ተገቢውን እርዳታ ሳያደርጉላቸው ይቀራሉ፡፡
7. ኢንተርኔትን እንደ መሸሻ ስፍራ መጠቀም፡– በህይወታቸው የገጠማቸውን ችግሮች በመጋፈጥ ከመፍታት ይልቅ ጊዜያዊ የሆነ እፎይታ ለማግኘት በኢንተርኔት ውስጥ ይሸሸጋሉ፡፡
(በከበደ በከሬ)
©zepsychologist
ክፍል ሁለት ላይ የኢንተርኔት ሱሰኝነት #መንስኤዎች እና የኢንተርኔት ሱሰኝነት የሚያስከትለው #ጉዳት በተጨማሪም #ነጻ_መውጣት የሚቻልባቸው መንገዶች እናያለን
@Psychoet
ኢንተርኔትን በብዛት ለሚጠቀሙ ጓደኞቻችሁ በመላክ እንርዳቸው ፡፡

እንደምን ከረማችሁ ዛሬ ታክሲ ላይ ሆኜ ትንሽ ጊዜ ሳገኝ እቺን ጽሑፍ ለመፃፍ ተነሳሳሁ ፡፡ ታክሲ የያዝኩት በግፊያ ስለነበር በሌለ ታክሲ ፥ ታክሲ ማግኘቴ ደስ ብሎኛል ፡፡ ጊዜው ጠዋትና ደመናማ ስለነበር አንዳንዱ ከዝናብ ሽሽት ሌላው ደግሞ ስራ ላለማርፈድ ሰልፈኛው ተራውን በጉጉት ሲጠብቅ ሌላው ደግሞ ሲጋፋ ነበር ፡፡ 4ኪሎ ሮሚና ካፌ ጋር ይህ ተግባር በየቀኑ በተለይ ስራ መግቢያና መውጫ ላይ የተለመደ ድርጊት ነው ፡፡
ወደ ዋናው ሀሳቤ ልመለስና አልረፈደም ያልኩበትን ምክኒያት ልንገራችሁ፡፡ እኔ ቀጠሮዬ 3:00 ነበር ነገር ግን እረስቼው 2:30 እንደሆነ በማሰብ ከቤቴ ስጣደፍ 2:20 ነበር የወጣሁት ታክሲ በግፊያ ካገኘሁ በኀላ ግን ታክሲ ውስጥ ሁኜ የቀጠሮዬን ሰአት ከስልኬ Text ላይ ስመለከተው 3:00 ነበር የሚለው ከዛ ተረጋጋሁ ፡፡ ለካ አልረፈደም ብቻ ሳይሆን ገና ነው ፡፡ ደስ አለኝ ፣ የቀጠርኳቸው ሰዋችን አላስጠብቅም ፡፡ ያው ግፊያው ፣ ሩጫው በስንፍናዬ ቢሆንም ቀጠሮው ግን አልረፈደም ፡፡
ይህን ይፃፍኩት ስለኔ ለማውራት ሳይሆን ስለ እኛ ሁላችን ለማውራት ነው ፡፡ ምን ያህሎቻችን ነን በሕይወታችን ብዙ ነገር ለመሞከር ፣ እንደገና ለመጀመር ፣ የምንወደውን ነገር ለመስራት አስበንና ፈልገን እረፍዷል ብለን ተስፋ በመቁረጥ የተቀመጥነው ፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ እንዳይረፍድ የምንጋፋና የምንገፋ ምን ያህሎቻችን ነን ?
እኔ ግን እላችኀለሁ በሕይወታችን " አልረፈደም ! " እንበል ለመለወጥ አልረፈደም ፣ ደስተኛ ለመሆን አልረፈደም ። ከዚህ በፊት በተለያዩ ስንፍናችን አልያም ከኛ በላይ በሆነ ምክኒያን ነገሮችን መስራት ያቃተን ሰዎች አሁንም ተነስቶ ለመስራት አልረፈደም ፡፡ እኔ እንደዚህ አምናለሁ እስካልሞትኩኝ ድረስ አልረፈደም ነገር ግን አንድ ነገር ላይ ችክ አልልም ምክንያቱም ብዙ ተመሳሳይ ነገሮች አሉ ፡፡ ያው ይገባችሁ የለ ፡፡
መልካም ቀን ፡፡
ናሁሰናይ ፀዳሉ
ለማንኛውም ግን አሁን 3:20 ሁኖም የቀጠርኳቸው አልደረሱም ፡፡ እነሱስ እረፍዷል ብለው እየተጋፉ ይሆን ?
@psychoet

ክፍል 2 #Share
የኢንተርኔት ሱሰኝነት መንስኤዎች
ሰዎች ለኢንተርኔት ሱሰኝነት እንዲጋለጡ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡ ለአንዱ እንደ ትልቅ መንስኤ የሚሆን ነገር ለሌላው ላይሆን ይችላል፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ ከዚህ በታች የተጠቀሱ ሃሳቦች ሰዎች በኢንተርኔት ሱሰኝነት እንዲያዙ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡
ሀ. በኢንተርኔት የመጠቀም ዕድል መኖር፡– በኢንተርኔት የመጠቀም ዕድል ማግኘት አስፈላጊ ነገር ቢሆንም ሰዎች በተገቢው መንገድ ካልተጠቀሙበት ለሱሰኝነት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ኢንተርኔትን የማይጠቀሙ ሰዎች በዚህ ሱስ አይያዙም፡፡ በተለይ ‹‹ትርፍ›› ጊዜን በአብዛኛው በኢንተርኔት ላይ ማሳለፍ ለሱሰኝነቱ ያጋልጣል፡፡
በተለይ ብዙ ጊዜያቸውን በሥራ ላይ የማያሳልፉ ሰዎች በቀላሉ ጊዜያቸውን ለማጥፋት ኢንተርኔትን መጠቀም ይጀምራሉ፡፡ በተገቢ ሥራ ያልተያዘ አእምሮ፣ ለኢንተርኔት ሱሰኝነት ያጋልጣል፡፡
ለ. ኢንተርኔትን ለእርካታ መጠቀም፡– እንደ ማንኛውም ሱስ ኢንተርኔት ሰዎች ሊሸሸጉበት የሚችሉት ዋሻ ነው፡፡ በተጨባጭ ነባራዊ እውነታ ያጋጠማቸውን ችግር ከመጋፈጥ ይልቅ በኢንተርኔት ላይ በሚያገኙት እርካታ መያዝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ ውጥረቶች ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ እፎይታ ለማግኘት ብለው ወደ አልኮል መጠጣት፣ ማጨስ፣ አደንዛዥ ዕፅ መጠቀምና ሌሎች ልምዶች ውስጥ እንደሚገቡ፣ አንዳንዶች ደግሞ በኢንተርኔት ላይ ጊዜያቸውን በማባከን ከችግር ለማምለጥ ይጠቀማሉ፡፡
ሐ. በኢንተርኔት አማካኝነት ብዙ ወዳጆችን ማፍራት፡– አንዳንድ ጊዜ በማኅበራዊ ግንኙነት ደካማ የሆኑ ሰዎች በኢንተርኔት አማካኝነት ከብዙ ዓይነት ሰዎች ጋር ጓደኝነትን ይመሰርታሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ውስጥ የሚኖሩ በመሆናቸው ኢንተርኔት ላይ የሚገኙት በተለያየ ሰዓት ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች ለማግኘት የራሳቸውን የሥራ ወይም የእንቅልፍ ጊዜ መቀየር የሚጠይቅበት ጊዜ ይኖራል፡፡
በኢንተርኔት ላይ ካፈሩ ወዳጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት ሲመሠርቱ በአካባቢያቸው ካሉ ሰዎች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ደግሞ እየቀነሰ ይመጣል፡፡ ቀስ በቀስ ‹‹የእኔ›› የሚሉአቸው ወዳጆቻቸው በኢንተርኔት ላይ የተዋወቁአቸው ሰዎች ይሆናሉ፡፡ በእነርሱ እይታ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ብዙ ጊዜ ማሳለፍ፣ አንድ ሰው ከወዳጆቹ ጋር በአካል እንደማሳለፍ እንደሆነ እየተሰማቸው ይመጣል፡፡
መ. በኢንተርኔት ላይ የሐሰት ማንነት መያዝ መቻል፡– በአካባቢያቸው በተለያዩ ምክንያቶች ተቀባይነት ያላገኙ ሰዎች በኢንተርኔት ላይ የሐሰት ማንነት በመፍጠር ከሰዎች ጋር መገናኘት ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የሚፈልጉት ዓይነት ሰው ሆነው ለሰዎች በመቅረብ የሚፈልጉትን ነገር ያወራሉ፡፡ ለአንዳንዶች ይህ ዕድል በሐሰት ማንነታቸው እንዲኖሩ ወይም ይህን በመጠቀም ሌሎች ሰዎችን ለመበዝበዝ መልካም አጋጣሚ ይሆንላቸዋል፡፡
ሠ. የስነ-ልቦና ችግሮች መኖራቸው፡– ከሰዎች ጋር ግንኙነት የመመሥረትና የማቆየት ክህሎት አለመኖር፣ ጭንቀት፣ የሥራ ወይም ሌሎች የህይወት ውጥረቶች መኖር፣ በሌሎች ሱሶች መያዝ ለኢንተርኔት ሱሰኝነት ያጋልጣል፡፡ ለምሳሌ የብቸኝነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ከብቸኝነት ስሜቱ ለመውጣት ብለው ኢንተርኔትን መጎርጎር ይጀምራል፡፡ በዚያው እየጣማቸው ይሄዳል፣ መጨረሻው ሱሰኛ መሆን ነው፡፡
የኢንተርኔት ሱሰኝነት የሚያስከትለው ጉዳት
የኢንተርኔት ሱሰኝነት አንዱ ችግር ብዙ ጊዜን በኢንተርኔት ላይ ማጥፋት ነው፡፡ በዚህ ሱስ የተያዙ ሰዎች ከመጠን ያለፈ ጊዜያቸውን በኢንተርኔት ላይ ስለሚያባክኑ በቤተሰብ ህይወታቸው፣ በሥራቸውና በማኅበራዊ ግንኙነታቸው ላይ ጉዳት እየደረሰ ይሄዳል፡፡
ኢንተርኔት ሰዎች በአካል ከእርስ በርስ በላቸው ግንኙነት ላይ አሉታዊ ጫናን ይፈጥራል፡፡ በኢንተርኔት ሱስ የተያዙ ሰዎች ራሳቸውን ከጠቃሚ ማኅበራዊ ግንኙነት ያገላሉ፡፡ ራሳቸውን ከተገቢ ማኅበራዊ ግንኙነት ማግለል ደግሞ ለብቸኝነት ስሜት ያጋልጣቸዋል፡፡ ቀስ በቀስ ደግሞ ወደ ድብርት/ የመንፈስ መሰላቸት ያመራል፡፡ ባለትዳር ከሆኑ ደግሞ ከትዳር ጓደኛቸው ጋር ተገቢውን ጊዜ እንዳያሳልፉ ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ለትዳር ውስጥ ግጭትና አልፎም ለትዳር መፍረስ ምክንያት ይሆናል፡፡
የኢንተርኔት ሱሰኝነት በትምህርትና በሥራ ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ አለው፡፡ እነዚህ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በኢንተርኔት ላይ ስለሚያጠፉ ለትምህርት ወይም ለሥራቸው ትኩረት አይሰጡም፡፡ በተጨማሪም በቂ እንቅልፍ አያገኙም፡፡ በትምህርት/በሥራ ጊዜ ይፈዛሉ፣ ንቃት የላቸውም፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በተለይ ቁጥጥር የማይደረግባቸው ከሆነ፣ በትምህርት ወይም ሥራ ላይ ሆነው ኢንተርኔትን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ መሥራት የሚገባቸውን ሥራ እንዳይሠሩ እንቅፋት ይሆንባቸዋል፡፡ የኢንተርኔት ሱሰኝነት የምርታማነት ጠንቅ ነው፡፡
በኢንተርኔት ላይ የወሲብ ምስሎች/ፊልሞችን በማየት ወይም በማውራት የተጠመዱ ሰዎች ደግሞ ከትዳር ጓደኛቸው ጋር የሚኖራቸው አካላዊ አንድነት ይቀንሳል፡፡ ቀስ በቀስ ደግሞ የወሲብ ፍላጎታቸውን ለማርካት ከሰው ይልቅ ወደ ኢንተርኔት ይሄዳሉ፡፡

#መልካም_የታህሳስ_ወር !
T.me/psychoet #Share
ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡
ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡
አንድ ቀን ነገር ሁሉ ቀላል ይሆናል ! ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
#እወዳችኀለሁ!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ