ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
10.7K subscribers
629 photos
4 videos
20 files
403 links
| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!


የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai


Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc
Download Telegram
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_9
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)
#SHARE አድርጉት ብዙ ሰው ያስተምራል #Like
#Frustration / #ተስፋ_መቁረጥ_ከየት_ይመጣል ?
___________________________

ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ሁነው ተስፋ የለኝም ፣ ተስፋዬ ተሟጧል ፣ የመሳሰሉትን ቃላት በቀን ተቀን ሕይወታቸው ይጠቀማሉ ፡፡

ተስፋ መቁረጥ ወደ ግባችን / ፍላጎቶቻችን እንዳንደርስ የሚያረገን ባህሪ ነው ፡፡ በሕይወቱ ብዙ ጊዜ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ወደግቡ/እቅዱ የመድረሱ እድል በጣም አነስተኛ ነው ፡፡ ወደ ጠቃሚ የሕይወት ግባችን አለመድረስ ደግሞ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት ፣ የበደለኝነት ስሜት ያመጣብናል ፡፡

ሳይኮሎጂ ችግር የመፍቻ ዋና መንገዱ የችግሩን ምክንያት መረዳት እንደሆነ ያትታል ፡፡ስለሆነም የተስፋ መቁረጥ ዋና ዋና ምክንያቶች እንመለከታለን፡፡
___________________________
1.Environmental Factor (አካባቢያዊ ምክንያት)

በአካባቢያችን ያሉ የተለያዩ ሁኔታዎችና ገጠመኞች ፍላጎቶቻችንንና እቅዳችንን እንዳናሳካ ይከለክሉናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ማድረግ የምንፈልገውን ነገሮች " አትችለውም ፣ ይከብድሀል ፣ ከዚህ በፊት አልተሞከረም ፣ ሰው ምን ይልሀል" በማለት ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ያደግንበት ባህል ፣ የምንኖርበት አካባቢ ለማድረግ ያቀድነውን ነገር እንዳናሳካ በራሱ ሊይዘን ይችላል ፡፡ ይሄ በሕይወታችን ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል ፡፡

2.Personal inadequency Factor (ግላዊ ብቃት/ክህሎት ማጠር )

ይህ ደግሞ ፍላጎቶቻችንን እንዳናደርግ የሚገድበን አለመሙላት (ብቃት አልባነት) ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድን እቃ በጣም ወደነው ለመግዛት ስንፈልግ ከተወደደብንና ያለን ገንዘብ አነስተኛ ከሆነ ተስፋ ቆርጠን ላንገዛ እንችላለን ፡፡ እዚህ ጋር ነገሩን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አለመኖር የራሳችን የሆነ ጉድለት ይሆናል፡፡ ሌላው አንድን ነገር ለመስራት አስበን የግል ችሎታ / ብቃት/ ክህሎት ሲያንሰን እሱ " በቃ አልችልም " በማለት ተስፋ ለመቁረጥ መንስኤ ይሆነናል ፡፡

3. Conflict of interest ( የፍላጎት ግጭት )
የመጨረሻው የግላዊ ፍላጎቶች/ ግቦች እርስ በእርስ ሲፃረሩ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችላል ፡፡ ተስፋ መቁረጡ የሚመጣዎ ሁለቱንም ግቦቻችንን ልናሳካ ባለመቻላችን ነው ፡፡ አንዱን ግብ ብናሳካ ራሱ ሌላውን ስላላሳካን የመወላወል ተስፋ የመቁረጥ ( የማዘን ) ስሜት ይሰማናል፡፡


ከነዚህ ሶስቱ ዎና ዎና ምክንያቶች እግጅ በጣም ብዙ ሰው የሚያጋጥመው የመጨረሻው (.Conflict of Motives / የፍላጎት ግጭት ) እንደሆነ ሳይኮሎጂ ይጠቁማል፡፡
__________________________________
እነዚህ Conflict of motives ( የፍላጎት ግጭት ) ደግሞ በ አራት ይከፈላሉ ፡፡
__________________________________
ሀ. Approach - Approach Conflict
(ፍላጎት ፥ ፍላጎት ግጭት)

ይህ ግጭት ሁለት ነገሮችን በእኩል ፈልገን ነገር ግን መምረጥ የምንችለው አንዱን ብቻ ሲሆን ማለት ነው ፡፡ ለምሳሌ :- ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኅላ Department ሲመርጡ ብዙ ተማሪዎች በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ የdepartment ምርጫዎች ይወጠራሉ ነገር ግን መምረጥ የሚችሉት የወደዱትን ሁሉ ሳይሆን አንዱን ብቻ ስለሚሆን ግጭት ውስጥ ይገባሉ ፡፡ ሌላው ገበያ ሂደን ሁለት ሱሪዎች በጣም ወደናቸው ነገር ግን መግዛት የምንችለው አንዱን ብቻ ከሆነ ይህ አይነት ግጭት ከራሳችን ጋር ይገጥመናል፡፡


ለ. Avoidance - Avoidance Conflict (የማስወገድ ፥ የማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ ከሁለት የማንፈልጋቸው ነገሮች የግድ አንዱን መምረጥ ግድ ሲለን ነው ፡፡
ለምሳሌ ፦ ልጃችን በሰዎች ታግቶ ብር ካልከፈላችሁ ይገደላል ቢሉን ፤ እዚህ ጋር ልጁ እንዲሞትም አንፈልግም ለአጋቾቹ ብር መክፈልም አንፈልግም ፡፡ ግን አንዱን መምረጥ ግድ ይለናል ፡፡ ሌላ ምሳሌ ፦

ሐ. Approach - Avoidance Conflict (የፍላጎትና ማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ በአንድ ግብ ላይ የፍላጎትም የማስወገድም ስሜት ሲሰማን ነው ፡፡

መ. Multiple Approach - Avoidance Conflict (ብዙ የፍላጎት ማስወገድ ግጭት)

ይህ ሁላችንም በሕይወት ቆይታችን የሚያጋጥመን የለት ተለት ግጭት ነው ፡፡ እያንዳንዱ የሚገጥመን ነገር #ብዙ_አወንታዊና_አሉታዊ ነገሮች ይይዝና እሱን #መምረጥና #አለመምረጥ ችግር ይሆናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው መልኩን ፣ ገቢውን ወደን ፀባዩ አመለካከቱ ካላማረን ይሆነኛል አይሆነኝም ብለን ከራሳችን እንጋጫለን ፡፡ሌላው አንድን ስራ ስንሰራ በዉስጡ ያሉ የተለያዩ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ስገፉን ሲስቡን እንደዚህ አይነት ግጭት ውስጥ እንገባለን ፡፡



፠፠______________________________፠፠
ምንጭ ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ Introduction to psychology lecture notes

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 t.me/Psychoet 👍


ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠______________________________፠፠
የሳምንት ሰው ይበለን!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «#ክፍል_9 (በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE አድርጉት ብዙ ሰው ያስተምራል #Like #Frustration / #ተስፋ_መቁረጥ_ከየት_ይመጣል ? ___________________________ ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ሁነው ተስፋ የለኝም ፣ ተስፋዬ ተሟጧል ፣ የመሳሰሉትን ቃላት በቀን ተቀን ሕይወታቸው ይጠቀማሉ ፡፡ ተስፋ መቁረጥ ወደ ግባችን / ፍላጎቶቻችን እንዳንደርስ የሚያረገን ባህሪ ነው…»
ቅናት
መቅናትን ማስቀረት እንችላለን!!!


ቅናት መጠኑ ይለያይ እንጅ በአብዛኛው ሰው ላይ የሚታይ ባህርይ ነው፡፡ እኛ ሰዎች በሁለቱም ማለትም ባለንም በሌለንም ቁሳዊም ሆነ ስነ-ልቡናዊ ጥቅሞች ባላቸው ነገሮች ላይ እንቀናለን፡፡ በሌለን ነገር ላይ የምንቀናው ቅናት (Envy) ሰዎች የሚፈልግቱንና እኛ የሌለንን ሲያገኙ ፣ ሲያሳኩ ወይም የሚያሳኩበትን የተስተካከለ መስመር ሲይዙ የሚሰማን ምቾት የማጣት ስሜት ሲሆን፤ ባለን ነገር ላይ ቅናት (Jealousy) ማለት ደግሞ ሌሎች እኛ ያለንን ቁሳዊ አካል ወይም የስሜት ግኙነት የመሰረትንበትን ሰው ሊያሳጧችሁ የሚመስል መጥፎ ስሜት በውስጣችሁ ሲፈጠር ነው፡፡

በምሳሌ ለማስቀመጥም የፍቅር አጋርህን ሌላ ወንድ ሲያናግራት ብታይ እና ሰላም የማጣት ስሜት ሲሰማህ ቅናት (Jealousy) ሸነቆጠህ ማለት ነው፡፡ አልያም ህፃናት አዲስ በተወለደው ወንድም ወይም እህት ምክንያት የሚሰማቸው እናቴን ወይም አባቴን ተነጠኩኝ ዓይነት ስሜት እና ባህርይ እንደ አብነት ማየት ይቻላል፡፡ ቅናት ገደቡን ካለፈ በእኛም ላይ ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ ስነ ልቡናዊ እና አካዊ ጉዳቶችን ይፈጥራሉ፡፡ ሆኖም ግን ቅናትን በበጎ መልኩ የምንጠቀምበት ከሆነ መልካም የሆነ ግንኙነትና እኛ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ወደተሸለ ደረጃ ወይም የምንቀናባቸው ሰዎች ወዳሉበት የስኬት ማማ ላይ ለመድረስ መንገዱን ይጠርግልናል፡፡

ከላይ እንደተገለጸው ቅናት የተለያዩ ስነ-ልቡናዊ እና አካላዊ ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡ ቅናት ቤተሰብን ይበትናል፣ ፍቅረኞችን ያለያያል፣ የስራ ባልደረቦችን ያጋጫል፣ ሰላማዊውን የሰው ልጆች መስተጋብር ያፋልሳል …ባስም ሲል ቅናት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትን ያስጠፋል (የዴዝዴሞና ታሪክ ትዝ አላችሁ?) ስለዚህ መፍትሔው ምንድን ነው ?? መቅናትን እንዴት ማቆም እንችላለን??? እስኪ እነዚህን የመፍትሔ አቅጣጫዎች አብረን እንዝለቃቸው……….

በጾታዊ ፍቅር ምክንያት ከሆነ ቅናት የሚይዘን በግልጽ መነጋገር፡፡ ይሄ ደርጊትሽ(ህ) ጥሩ ያልሆነ ስሜት እየፈጠረብኝ ስለሆነ መስተካከል ይኖርበታል ማለት አለብን፡፡ ማስተዋል ያለብን ቀንቻለው ማለት የተሸናፊነት ምልክት ሳይሆን ግንኙነቱን ዘላቂና ሰላማዊ ማድረግ እፈልጋለሁ ማለት እደሆነ ነው፡፡( መተማመን) በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ዋናው የግንኙነት መሰረቱ መተማመን ነው፡፡ የማይተማመን ባልንጀራ ካብ ለካብ ይማማላል እንዲሉ አበው፤ መተማመን የሌለው  ጾታዊ ፍቅርም ለቅናት የተጋለጠ ነው፡፡ ሌላው መቼም የምንቀናበት ሰው ፍጹም አይደለም፡፡ እሱ የሌለው እኛ ግን ያለን ሌሎች ነገሮችም እንዳሉ መገንዘብ፡፡ሁልጊዜ ራስህን በጥረት ውስጥ ማሳለፍ ይኖርብሃል፡፡ ምክንያቱም የቻልከውን ያህል ስለታተርክ በቅናት ፋንታ እርካታን ታገኝበታለህ፡፡ ከምንቀናባቸው ሰዎች ልምድ መቅሰም አለብን፡፡  ይህም ማለት የቀናህበትን ነጥብ ነቅሰህ አውጣ በዚህም አንተ ማግኘት ያቃተህ ሌሎች ግን ያሳኩት ከሆነ እንዴት እንዳሳኩት በማወቅ ራስህን እንድታሻሽል ይረዳሀል፡፡ በመጨረሻም ሌሎች ሰዎች ላይ እና ያላቸው ነገሮች ላይ ያለህን ፅንፍ የያዘ ትኩረትህን ቀንስ፡፡ ምክንያቱም የአዕምሮህን የትኩረት አቅጣጫ በማስቀየር አቅምህን ያሟጥብሀል፡፡ ስለሌለህ ሳይሆን ስላለህ ነገር በማሰብ ለእራስህ እውቅና ስጥ በዚህም በጊዜ ሂደት በራስ መተማመንን አዳብረህ ቅናትን ታስወግዳለህ፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ……

– ቁምላቸው ደርሶ
@zepsychologist
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ተመስጦ/Meditation
ከራስ ጋር የሚወሰድ ድንቅ ጊዜ
#Share #Like
ብዙ ሰው ከራሱ ጋር የግል ጊዜ ስለማይወስድ ሂወቱ የተረጋጋ አይደለም!

የሰው ልጅ ዕለት ተዕለት በሚኖረው ኑሮ ውስጥ ሲደክመው ዕረፍት ማድረግን ፤ የሰውነት ክፍሎቹን ለማፍታታት መንጠራራትንና ማፍታታትን ፤ የድብርት ስሜት ሲሰማው ማፋሸግንና ሲጨንቀው ስሜቱን ለማረጋጋት ዓየር በደንብ ወደ ውስጥ አስገብቶና ወደ ውጭ በረጅሙ መተንፈስን በተፈጥሮ የታደላቸው ገጸ በረከቶች ናቸው፡፡ ከፍ ሲልም መንፈሱን ወደ ትልቁ ማማ ሰማየ ሰማይ በመውሰድና በመመሰጥ አእምሮውንና መንፈሱን ያድስበታል፡፡

ተመስጦ ሰዎች ከጥንት ጊዜ ጀምሮ አእምሯቸውንና ህይወታቸውን የሚቆጣጠሩበት እንዲሁም እራሳቸውን ፈልገው የሚያገኙበት የአእምሮ ፤የአካልና የመንፈስ እንቅስቃሴ ነው፡፡ በተጨማሪም ተመስጦ ሰዎች አእምሯቸውን እንደ ኤሌክትሪክ ማብሪያና ማጥፊያ ባሻቸው ሰዓት ማሰብ የሚፈልጉትን እንዲያስቡ ማሰብ የማይፈልጉትን ደግሞ ከአእምሮአቸው ውስጥ በቀላሉ የሚያጠፉበት ተፈጥሯዊ የአእምሮ ቁልፍ ነው፡፡

በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በዓለም ላይ በሚገኙ ባህሎች ውስጥ ተመስጦና መመሰጥ አለ፡፡ ነገር ግን ተመስጦ በተደራጀና በተዋቀረ መልኩ የተጀመረው በሂንዱ ሸለቆ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ5000 እስከ 3500 ዓመተ ዓለም አካባቢ መሆንኑን የአርኪዮሎጂ ጥናቶችና ግኝቶች ያስረዳሉ፡፡ በሂንዱ ሸለቆች የተገኙ የግርግዳ ላይ ስዕሎች ከላይ ከተጠቀሰው ዓመተ ዓለም ጀምሮ ሰዎች ቁጭ ብለው እግራቸውን አመሳቀለው ተመስጦን ሲያከናውኑ እንደነበር ማስረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ እንዲሁም በህንድ መጻሕፍት ውስጥ ከ3000 ዓመታት በፊት የተመስጦና መመሰጥ ዘዴዎች ተመዝግበው እንደሚገኙ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፡፡

ሁሉም ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች በውስጣቻው ተመስጦን ይዘው ይገኛሉ፡፡ በሃይማኖታዊ ስርዓት ምዕመናን ሲጸልዩ ፤ ሲያመሰግኑና ሲሰግዱ ወደ አምላካቸው ይመሰጣሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ስለተመስጦና መመሰጥ ሲነሳ ሰዎች ወደ አእምሮአቸው የሚመጣው የቡድሃ ወይም የሂንዱ እምነት ነው፡፡ ምንም እንኳን እነኚህ ሃይማኖቶች በሃይማኖታዊ ክንዋኔአቸው ለተመስጦ ትልቅ ትኩረት ቢሰጡም በዘመናዊው እይታ ተመስጦና መመሰጥ ከየትኛውም ሃይማኖት ጋር አይያያዝም አልያም ዘውትር መመሰጥንና ተመስጦን ማከናወን የቡድሃ ወይም የሂንዱ እምነት ተከታይ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ለመነሻ ያህል ይህን ካልን የመመሰጥና የተመስጦን ጥቅም ከብዙ በጥቂቱ እንመለከታለን፡፡

1. ውጥረትን ይቀንሳል

መመሰጥና ተመስጦ ከማንኛውም አካላዊ እንቅስቃሴ በላይ ውጥረትን የመቀነስ አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ መመሰጥ ውጥረትን መቀነስ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በነርቭ ስርዓት ላይ ውጥረትን የሚያመጣውን ኮርቲሶል የሚባለውን ኬሚካል በመቀነስ በምትኩ ሰዎች ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርገውን ሴሮቶኒን የተባለውን ኬሚካል አንጎላችን እንዲያመነጭ ያነሳሳል፡፡

2. ጤናን ያሻሽላል

ተመስጦ የበሽታ መከላከል ኃይልን በማደርጀት፤ የደም ግፊትና የኮለስትሮል መጠንን  በመቀነስ ጤናን ያሻሽላል፡፡ በተለይ በማይድን ጽኑ ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች ህመማቸውን ለማስታገስና ለማገገም ከተመስጦ ብዙ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ በእርግጥ ተመስጦን ለመጠቀም የግድ ጽኑ ህሙማን መሆን አይጠበቅብንም ከጉንፋንና እራስ ምታት ለመታቀብና ለመዳን ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

3. ለእንቅልፍ

በስራ ጫና ብዛትና በውጥረት ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እንቅልፍ ላይዛቸውና በቶሎ በመተኛት ከድካማቸው ፋታ ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ወቅት መመሰጥት ችግራቸውን  ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ በቀላል እንዲፈቱ ይረዳቸዋል፡፡

4. እርጅናን ይከላከላል

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አዘውትረው የሚመሰጡ ሰዎች ከማይመሰጡት ጋር ሲወዳደሩ ቀናቸውን በተመስጦ የሚያሳልፉ ሰዎች ከዕድሜቸው አንጻር ቶሎ የማያረጁና ረጅም ዕድሜ የሚኖሩ ሆነው ተገኝተው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት መመሰጥና ተመስጦ እርጅና የሚያስከትሉ ቲሹዎችንና በሽታዎችን መግታት በመቻሉ ነው፡፡

5. ለውስጠ ስሜት መረጋጋትና አወንታዊ አስተሳሰብ

መመሰጥ ጭንቀት ውስጥ ለገቡ፤ በቶሎ ለሚናደዱ፤ ስሜታቸውን መቆጣጠር ለሚቸገሩና ድብርት ለሚያጠቃቸው ሰዎች እንደ ተፈጥሯዊ መከላከያ መድኃኒት ተደርጎ በባለሙያዎች ይታዘዝላቸዋል፡፡ በተጨማሪም መመሰጥ የአሉታዊ አስተሳሰቦችንና ስሜቶችን ከሰዎች አእምሮና አካላት ውስጥ አጥርቶ በማውጣት በአወንታዊ አስተሳሰብ እንዲገነቡ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ በአጠቃላይ ከጭንቀትና ተያያዥ ጉዳዮች ባሻገር ተመስጦን የሚያዘወትሩ ሰዎች ጥሩ ስሜት የሚሰማቸውና ደስተኞች ናቸው፡፡

ለተመስጦ የሚረዱ ጥቆማዎች

*ዘውትርና በተመሳሳይ ሰዓት መመሰጥን ልምድ ማድረግ ይመከራል

*ከመመሰጥ በፊት የማነቃቃት ባህሪይ ያላቸውን ትኩስ ነገሮች አለመውሰድ

*ከምግብ በኋላ አለመመሰጥና በቀን ውስጥ ሙሉ ኃይል የለኝም ብለው በሚያስቡበት ሰዓት መመሰጥ

*መመሰጥ የሚፈልጉበትን ስፍራ ማዘጋጀትና በቂ ዓየር እንዲገባው መስኮት መክፈት

*በጣም ደማቅ ብርሃን የሌለውን ስፋራ መምረጥና ሰፋ ያለ ልብስ መልበስ

*ጸጥ ያለ አካባቢን መምረጥና በተመስጦ ጊዜ ሊረብሹ የሚችሉ ነገሮችን እንደ ስልክ ፤ ሬዲዮ ፤ ቴሌቪዥንና የመሳሰሉ ነገሮን ድምጽ ማጥፋት

*በረጅሙ ዓየር ወደ ውስጥ ማስገባት

*ያስገቡትን ዓየር ለጥቂት ሰከንዶች ሳይተነፍሱ ማቆየት

*ከዚያም በረጅሙ መተንፈስ

በሚተነፍሱበት ወቅት ለሚሰማዎት ስሜት ትኩረት መስጠት፤ ዓየር በአፍንጫ ቀዳዳዎ ሲገባ ፤ ዓየሩን ለተወሰኑ ሰከንዶች ሲይዙት በመላ አካላቶ እየተሰራጨ እንደሆነና ሰውነቶን አዝናንቶ በአፍዎ እንደሚወጣ ማሰብ በቀላሉ የተረጋጋ ስሜትንና መዝናናትን አእምሮአችንና አካላችን እንዲሰማው ያደርጋል፡፡ ሰላም!

(በአንቶኒ ሙላቱ)
©Zepsychologist
በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ፥

ሰውን ሁሉ ለመውደድ ጣሩ!

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ሱሰኝነትን እንዴት መከላከል ይቻላል?
#Share በማረግ ሌሎችን እናስተምር

ሱስ ስንል ማንኛውም ነገር በሰዎች ላይ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥገኝነት ስሜት በመፍጠር ሰዎች ለመነቃቃት ፤ ድብርትን ለማስወገድ ፤ ጀብዱ ለመስራት፤ ህመምን ለማስታገስና ከፍተኛ የደስታ (Euphoria) ስሜትን ለመጎናጸፍ ብለው የሚያጨሷቸው፤ የሚቅሟቸው በአፍንጫ የሚስቧቸውንና በደም ስር የሚወስዷቸውን ነገሮች በሙሉ ሲያካትት ያለ እነኚህ ሱሶች/ዕፆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴአቸውን ማከናወን ሲሳናቸው ሱስ ወይም የሱሰኝነት ጠባይ እንዳለባቸው ይገለጻል፡፡

ሰዎች ምንም እንኳን ሱስ የሚያሲዙ ነገሮችን በመጀመሪያዎቹ አካባቢ በራሳቸው ተነሳሽነት የሚወስዱና የሚጠቀሙ ቢሆንም እየዋለ ሲያድር ግን በሚያስከትለው ጥገኝነት ሱስ የሚያሲዙ ንጥረ ነገሮችንና አደንዛዥ ዕጾችን መጠቀም የግድ እየሆነ ይመጣባቸዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ በሱስ መጠመድና ተጋላጭ መሆን የአእምሮ ጉዳት ፤ የማስታወስ ክህሎት ማሽቆልቆል ፤ ተስፋ መቁረጥ ፤ እራስን መቆጣጠር አለመቻልና ሌሎች ተጓዳኝ የአካልና የስነ-ልቦና ቀውሶችንና ብሎም ሞትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በሱስና በአደንዛዥ ዕፅ ጥገኝነት የሚመጡት የጤና እክሎች በሱስ የተጠመዱ ሰዎች ሱሰኝነትን ማቆም እንዳልቻሉ የሚያመለክቱ ሲሆን ይህንን የጤና እክል ለማስወገድ የሚደረገው ህክምና አካልና አእምሮን ከሱስ ከማጽዳት አንጻር ትልቅ ጥረትና ክትትልን ይጠይቃል፡፡ ሱስና አደንዛዥ ዕፅ በሰዎች አካል ፤ አእምሮና ስነ-ልቦና ላይ ትልቅ ተጽእኖ ስለሚኖረው የሚሰጠው ዕርዳታና ህክምና በሱስ ምክንያት የተከሰቱ አሉታዊ ተጽእኖዎችን በሙሉ ያካተተ መሆን እንዳለበት ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በማስከተል ሱሰኝነትን ለመከላከል የሚያስችሉ ስልቶችን እንመለከታለን፡፡

1. መጠንን መቀነስ (Reducing dosage)

በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሱሰኝነትን ቀስ በቀስ ወይም በሂደት ለመተው እንዲችሉ የሚወስዱትን ሱስ የሚያሲዙ ነገሮችን መጠን መቀነስ ይኖርባቸዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ሱሰኝነትን ለመተው ያስቡና ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ለማቆም ይሞክራሉ፡፡ ይህ እርምጃ ምንአልባት ለአንድና ለሁለት ቀን ያገለግል እንደሆን እንጂ ዘለቄታዊ መፍትሄን ማምጣት አይችልም፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱሰኝነት በሰውነት አካል ውስጥ በደንብ የተሰራጨ ከሆነ በአንድ ጊዜ ለመተው ማሰብ ህይወትን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ ሱሰኝነትን በአንድ ጊዜ ወይም በቅጽበት ለመተው ከማሰብ ይልቅ መጠንን እየቀነሱ ለዘለቄታው እስከመተው መድረስን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

2. ውጫዊ ተጽንኦዎችን መቋቋም

ሱሰኝነት በተለያዩ ውጫዊ ተጽእኖዎች ሊባባስ ይችላል፡፡ እነዚህን ተጽእኖዎች ለመቋቋም ሱስ ከሚያሲዙ አካባቢዎች መራቅ አንዱ መፍትሄ ሲሆን ይህ የማይቻል ከሆነ ዳግመኛ በሱስ ተጽእኖ ስር ላለመውደቅ አመለካከትን መቀየር ያስፈልጋል፡፡

በአጠቃላይ ሱሰኝነትን ለማስወገድ የሚደረጉ ዕርዳታዎች ሰዎች ከአካላዊና ስነ-ልቦናዊ የሱስ ጥገኝነት ተላቀው ጤናማ ህይወት እንዲኖሩ ማስቻል ነው፡፡ በሱስ ለተያዙ ሰዎች ከሌሎች የሚደረግላቸውን እንክብካቤና ድጋፍ ማስተናገድ ቀላል ቢሆንም ከሌሎች ዕርዳታ ተላቀው እራሳቸውን ከሱሰኝነት ለማላቀቅ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ትልቅ ተግዳሮት ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም ከሱስ የሚያገግሙ ሰዎች የሱስን አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና የውስጠ ስሜት (emotional) ቁርኝነት ከልብ በመረዳት የሱሰኝነትን ስሜት በአወንታዊ መልኩ ለመግታት መታገል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሰዎች ሱሰኝነትን ካቆሙ በኋላ የድብርት ፤ የንዴትና የብስጭት ስሜት በሚሰማቸው ወቅት ከእነዚህ ስሜቶች ለመውጣት ወደ ተዉት የሱስ ህይወት ለመመለስ ያላቸው ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ እነዚህን አጋጣሚዎች በብልሃት ማስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡ መልካም ጊዜ!

3. ስነ-ልቦናዊ ህክምና (Psychotherapy)

ሰዎች ሱስና ሱሰኝነትን ከሚያሲዙ ድርጊቶች እንዲላቀቁ የስነ-ልቦና ህክምና ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ ከሱስ አካላዊ ጥገኝነት ይልቅ ስነ-ልቦናዊ ጥገኝነት ስለሚበልጥ ሰዎች በመጀመሪያ ከሱስ ነጻ መውጣት እንደሚችሉ እራሳቸውን ማሳመን ካልቻሉ ሌሎች የሚደረጉ ህክምናዎችና ዕርዳታዎች ውጤታማ መሆን አይችሉም፡፡ ማንኛውም ለውጥ ከአእምሮ ይጀምራል እንደሚባለው በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች በምክር አገልግሎት ሰጪ ባለሙያ(counselor) በመታገዝ ከሱስ ለመውጣት ስነ-ልቦናዊና አእምሮአዊ ዝግጅትና ቁርጠኝነት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሰዎች የመንፈስ ጥንካሬ አእምሯቸውን ለማዘዝ የሚያስችል አቅም ሲሰጣቸው በአንጻሩ የአልችልም ባይነትን ስነ-ልቦና ከተላበሱ አእምሮአቸው ያለመቻልን ስሜት በውስጣቸው ይዘው እንዲዘልቁ ያስገድዳቸዋል፡፡ ስለዚህ ስነ-ልቦናዊ ህክምና በሱስ የተያዙ ሰዎችን ስነ-ልቦና በማጠንከር የሱስ ጥገኝነትን ለማስወገድ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡

4. የመድኃኒት ህክምና

በአደንዛዥ ዕፅና ነጥረ ነገሮች ሱስ የተያዙ ሰዎች ሱሰኝነትን እንዲያቆሙና ከሱስ የጸዳ ህይወት እንዲመሩ ለማስቻል ከሚሰጡ ዕርዳታዎች መካከል አንዱ የመድኃኒት ህክምና ሲሆን ይህም የተለያዩ መድኃኒቶቸን በመጠቀም በሱስ የተያዙ ሰዎች ሰውነት ውስጥ የተከማቹትን መርዛማ ኬሚካሎችን ማስወገድን ያካትታል፡፡ ከሱሰኝነት ጋር በተያያዘ አብዛኛውን ጊዜ የመድኃኒት ህክምናዎች ለብቻቸው ዘላቂ መፍትሄ የመስጠት ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡

5.ሌሎች አማራጮችን መጠቀም

ሱሰኝነት በሰዎች አካላት ውስጥ አንዴ ከተሰራጨ መጠንን በመቀነስ ብቻ በቀላሉ ማስይወገድ ስለማይቻል መጠንን በመቀነስ ለመተው በሚደረገው ጥረት ከዚህ ቀደም ሰውነት የተላመደውን መጠን መጠቀም ስለሚፈልግ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ግድ ይላል፡፡ ሱሰኝነትን በአወንታዊ መልኩ በትክክል የሚተካው ባይኖርም ሱሰኝነትን ለመተው በሚደረገው ጥረት የሚከሰቱትን (withdrawal symptoms) እንደ ድብት ፤ ማቅለሽለሽ ፤ ትኩረት ማጣት፤ ራስ ምታት ፤ አለመረጋጋት ፤ የእንቅልፍ ሰዓት መዛባትና እንቅልፍ ማጣትን ለማስተካከል የማነቃቃት ባህርያ ያላቸውን ትኩስ ነገሮችን መውሰድ ፤ ማስቲካ ማኘክና እንደየአስፈላጊነቱ በተደጋጋሚ ጸጉርን መታጠብ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

(አንቶኒዮ ሙላቱ ©ዘ-ሳይኮሎጂስት)
የአመለካከት / ሃሳብ ልኬት

በመጀመሪያ ሰው ላመነበት ነገር ባሪያ ነው አራት ነጥብ፡፡ ምንም ብትተቸው ብትነቅፈው አመለካከቱ/እይታው በእራሱ መነጸር ትክክል ነው ለድርድር አይቀርብም (ትክክል አለመሆኑን ህሊናው ነግሮት ወይም በነጽሮት እራሱን ለለውጥ እስካላዘጋጀ ድረስ)፡፡ (ለዚህም ነው በህክምና ዘርፍ የአእምሮ ህሙማን በጥንቃቄ ሊያዙና እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ምክር የሚለገሰው፡፡ ምክንያቱም ባጋጠማቸው የጤና መታወክ ደረጃ አስተሳሰባቸው እራሳቸውንና ሌላውን እስካልጎዳ ድረስ ጤናማ ናቸው ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ልብ ይሎአል፡፡ ግን በጣም ታመውም ምንም አንዳልሆኑና እንዳልታመሙ ሆነው ሊከራከሩና ከህክምና ሊርቁም ስለሚችሉ የሌሎች ዕርዳትና እገዛ የሚያስፈልጋቸው፡፡ እንደው በአጋጣሚ አነሳውት እንጂ ሃሳባችንና ትኩረታችን “ጤናማ ሰው” ብለን የምናስበውን ነው፡፡) ይህ ማለት ግን የአንዱ እውነት ወይም የሌላው ምልከታ በሌሎች አረዳድና ግንዛቤ ትክክልና ቀቡል ነው ማለት አይቻልም ሊሆንም አይችልም፡፡ እዚህ ጋ የአንዱ እውነት/ሐሰት ለሌላው ሐሰት/እውነት ሊሆን የሚችለው በንጽጽር መልኩ ካየነው ብቻ ነው፡፡ ያለ ንጽጽር እውነትም ሐሰት ነው ሐሰትም እውነት ነው፡፡ ለብቻው ቀጥ ብሎ የሚቆምና የሚኖር እስካልሆነ ድረስ፡፡
ታዲያ እኔ ከአንተ በሃሳብ ልስማማምና ላልስማማም እንደምችል ካወቅህ አንተም በራስ መንገድ አሸናፊ ነህ እኔም እንደዚያው፡፡ ግን የአንድን ነገር እውነታ በንግግርና በክርክር እንግለጸው ካልክ ሁለታችንም እውነት ነው ብለን ካመንበትና ከተነሳንበት የእይታ ስፍራ ያደረግነውን መነጽር ማውለቅ አለብን፡፡ ምክንያቱም አሁን ልንነጋገር እየተንደረደርን ያለነው ስለ አንጻሪዊ እውነትነት ወይም ሐሰትነት ሳይሆን በሁለታችን መሃል ስላለው ተቀባይነት ነው፡፡ ስለዚህ በሃሳብ መቀመሪችን እንነጋገራለን እንፋጫለን (ከስሜት በጸዳ መልኩና በምክንያት) ልኬቱ በተስተካከለ ፤ በሰከነ ፤ በአስተዋይነት ፤ ዕውቀትንና ቅንነትን መሰረት ያደረገ አመለካከት ከሆነ መቁረጫው ቀላል ነው የሚሆነው፡፡ የሃሳቡን መቁረጫ ልኬት ወደ አወንታዊነት ስለሚቀይረው፡፡ እንደ እኔ እይታና አረዳድ አወንታዊነት (positivity) የአንድን ነገር መልካም ጎን ብቻ መመልከት ሳይሆን ደካማውን አካቶ ሚዛናዊ የሆነውን መያዝ ነው፡፡ የአወንታዊ ምልከታው በሃምራዊ መነጸር እይታ የተጋረደ መሆን የለበትም፡፡ መነጽሩ የሚያሳየን ማየት የምንፈልገው ነገር ብቻ ስለሆነ:: በአስቀመጥነው የሃሳብ/አመለካከት ልኬት ለመቁረጥ መነጽሩ መውለቅ አለበት በሁሉም አቅጣጫ ለማየት እንዲያስችለን፡፡ ከዚያ በኋላ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ሁለታችንም አሸናፊዎች ስለሆንን በልዩነትና በመከባበር እናልፈዋለን፡፡ ለዘለፋና ለትችትም አጋልጦ አይሰጠንም፡፡ ስለዚህ የእኛ የሃሳብ ልኬት በእራሳችን ወይስ በሌሎች ንጽጽር መለካት/መቆረጥ ያለበት? በሁለቱም እንደ ነገሮች ሁኔታ ቢለያይም፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©zepaychologist
የካንሰር ተጋላጭነትን መቀነስ
#Share
በካንሰር ህመም ምክንያት በዓመት ውስጥ በመላው ዓለም የበርካታ ሰዎች ህይወት ያልፋል፡፡ ድሮ ድሮ የካንሰር በሽታ የአደጉት አገሮች ችግር ብቻ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡ በአሁን ወቅት ግን አድማሱን በማስፋት በታዳጊ አገራት ላይም ትልቅ ተጽእኖን በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ የአገራችንን ኢትዮጵያ ሁኔታ እንኳን ብንመለከት በእርግጠኝነት ያለውን ቁጥር ማስቀመጥ ባይቻልም ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በዓመት ውስጥ 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ወገኖቻችን ለጋንሰር ተጋላጭ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡ ካንሰርን የሚያድን መድኃኒት እስካሁን ባይገኝም አስቀድሞ ተጋላጭነትን ግን መከላከል ይቻላል፡፡ እንዴት?

ፈጽሞ ትምባሆና የትንባሆ ውጤቶችን አለማጨስ፡፡

ቤታችንና አካባቢያችንን ከትንባሆ ጢስ ነጻ ማድረግ፡፡

ዘውትር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ

ጤናማ የአመጋገብና የኑሮ ዘይቤ በመከተል፡፡

የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም ወይም መጠንን መቀነስ፡፡

ከፍተኛ የሆነ የፀሐይ ብርሃን ተጋላጭነትን መቀነስ ወይም የፀሐይ ብርሃን መከላከያ መጠቀም፡፡

ጡት ማጥባት የእናቶችን ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡

ህጻናትን የሄፓቲቲስ ቢና ኤችፒቪ ክትባቶችን (Hepatitis B and HPV) ማስከተብ፡፡

በየጊዜው ምርመራ ማድረግ…ወዘተ

©Zpsychologist

#Share

@Psychoet
ያዘነን ሰው ማጽናናት
#Share አርጉት
ደስታና ሃዘን የአንድ ሳንቲም ገጽታዎች ናቸው፡፡ በህይወታቸን ውስጥ ደስታ እንዳለ ሁሉ በተለያየ ምክንያት ሃዘን ሊያጋጥመን ይችላል፡፡የምንወደው ሰው መታመም ወይም ሞት፤ ያፈቀርነውን ማጣት፤ የህልማቸን አለመሳካት፤ በህይወታችን ውስጥ ትካዜን ከሚፈጥሩ ጉዳዮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ አብዛኞቻችን በራሳችን የህይወት ልምድ ውስጥ ማዘንን ብናውቀውም ያዘኑ ሰዎች ሲያጋጥሙን እንዴት ማጽናናት እንዳለብንና ምን ማድረግ እንዳለብን ለማወቅ እንቸገራለን፡፡ መባል የሌለበትን ነገር በማለት ያዘኑ ሰዎችን ሃዘን ልናባብስ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፡-

ሃዘን ቤት ሄደን የሟች ቤተሰብን ያጽናናን መስሎን “የታመመው ምን ነበር? ህክምና ወስዳቹሁት ነበር?… ከስቃዩ ማረፉ ይሻለዋል፤ በዚህ ዕድሜው ተቀጨ…እንግዲህ ፈጣሪ ካመጣው ምን ይደረጋል….” የሚሉ ሃሳቦች በተደጋጋሚ ሲሰነዘሩ እንሰማለን፡፡ እነዚህ ነገሮች ቤተሰብን በማሰልቸትና ሟቹን እንዳይረሳ በማድረግ ሃዘንን ያባብሳሉ፡፡ ለምን ይህ ሃዘን በእኔ ላይ መጣ የሚል ስሜት በመፍጠር ሃዘንተኛውን ጸጸትና ድብርት ውስጥ ሊከቱ ይችላሉ፡፡

በጣም ደክሞ ሊሞት የሚያጣጥር ሰው ቤት ሄደን በቤተሰቡ ፊት “እንግዲህ የሚመጣውን ለመቀበል መዘጋጀት ነው… ተስፋ ያለው አይመስልም….ዛሬን የሚያድር አይመስልም” ብንል የቤተሰቡን ጭንቀት እናባብሳለን፡፡

በፍቅረኛዋ መከዳት ልቧ የቆሰለን ሴት “ቀድሞውንም ሰውየው እንደማይረባሽ ነግሬሽ ነበር….እንዴት ከዚህ ዓይነት ሰው ጋር እስካሁን ቆየሽ…” እና የመሳሰሉትን ሃሳቦች ማንሳት ለተጎጅዋ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል

የሃዘን ደረጃዎችን መረዳት፡- ሰዎች በሃዘን ወቅት የሚያልፉባቸው 5 ደረጃዎች አሉ፡፡

ደረጃ 1፡ ሰዎች ሃዘን ሲያጋጥማቸው የመጀመሪያ ምላሻቸው ችግሩን መካድ (Denial) ነው፡፡ የቤተሰባቸው አካል መሞቱን አምኖ መቀበል ይከብዳቸዋል

ደረጃ 2፡ ከፈጣሪ ጋር መደራደር (Bargaining)፡-ሃዘን ውስጥ ያሉ ሰዎች ለምን ይህ ችግር በእኔ ላይ መጣና ጥፋቴ ምንድን ነው… የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ፈጣሪያቸውን ይሞግታሉ

ደረጃ 3- ቁጣ (Anger)፡ ያዘኑ ሰዎች በትንሹም በትልቁም ሊነጫነጩና ሊቆጡ ይችላሉ

ደረጃ 4- ድብርት (Depression)፡ ያዘኑ ሰዎች ተገቢውን ድጋፍና ዕርዳታ ካላገኙ በከፍተኛ ድብርት ውስጥ ይገባሉ

ደረጃ 5-ማጣትን መቀበል (Acceptance)፡- በጊዜ ሂደት ውስጥ ያዘኑ ሰዎች ያጡትን ነገር ለመቀበል ውስጣቸውን ያሳምናሉ

ያዘኑ ሰዎችን ለማጽናናት ማድረግ የሚገቡን ጉዳዮች፡-

ስሜትን መጋራት፡- ራሳችንን ባዘነው ሰው ቦታ ማስቀመጥና ስሜቱን እኔ ብሆንስ በሚል መንፈስ መረዳት፡፡ ለምሳሌ፡- አባትህ በሞት በመለየታቸው ሃዘን ተሰምቶኛል፤ ፍቅረኛሽ ትቶሽ በመሄዱ ምን ሊሰማሽ እንደሚችል እረዳሻለሁ፡፡

ማዳመጥ፡- ሰዎች ሃዘን ውስጥ ሲሆኑ ብዙ ማውራት፤ ብሶታቸውን ማካፈል ይወዳሉ፡፡ ስለዚህ ጥሩ አድማጭ መሆን ሃዘንን የመካፈል ሂደት ነው፡፡ ነገር ግን ማውራት የማይፈልጉትን ነገር እንዲነግሩን መወትወት አይገባም፡፡

ለዕርዳታ ዝግጁ መሆንን መግለጽ፡-“ወንድምህን እያስታመምክ እንደሆነ አውቃለሁ…እኔ ልረዳህ የምችለው በምን መልኩ ነው?” እና የመሳሰሉ ሃሳቦችን በማንሳት ሃዘንተኛው ከጎኑ መሆናችንን እንዲያውቅ ማድረግ፡፡

ማቀፍ፡-አንዳንዴ ያዘነን ሰው ምን ማለት እንዳለብን ሲቸግረን አላስፈላጊ ቃላት ከመሰንዘር ይልቅ ዝም ብሎ በማቀፍ ሃዘንን መጋራት ይቻላል፡፡

ሃዘንን ለመርሳት በቂ ጊዜ እንደሚያስፈልግ መረዳት፡- ሰዎች ከሃዘን ለመውጣት መጠኑ የተለያየ ጊዜ ያስፈልጋቸውል፡፡ አንዳንዶች በቀላሉ አገግመው ወደ ዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሲመለሱ ሌሎች ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ ከሃዘን ጋር ሲታገሉ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ይህ የሚወሰነው በሃዘኑ ዓይነትና በተጎጂው የስነ-ልቦና ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ስለሆነም በተቻለ መጠን ላዘኑ ሰዎች በቂ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት “ሃዘኑ ይበቃሃል…. ራስሽን በጣም እየጎዳሽ ነው…በአንተ ላይ ብቻ የተከሰተ ችግር አደረግከው” እና የመሳሰሉትን ቃላት በማውጣት ሃዘንተኛውን ከመወትወት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡

(በሰብለወንጌል አይናለም)
©Zepsychologist
#Share
👍2
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ያዘነን ሰው ማጽናናት #Share አርጉት ደስታና ሃዘን የአንድ ሳንቲም ገጽታዎች ናቸው፡፡ በህይወታቸን ውስጥ ደስታ እንዳለ ሁሉ በተለያየ ምክንያት ሃዘን ሊያጋጥመን ይችላል፡፡የምንወደው ሰው መታመም ወይም ሞት፤ ያፈቀርነውን ማጣት፤ የህልማቸን አለመሳካት፤ በህይወታችን ውስጥ ትካዜን ከሚፈጥሩ ጉዳዮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ አብዛኞቻችን በራሳችን የህይወት ልምድ ውስጥ ማዘንን ብናውቀውም ያዘኑ ሰዎች ሲያጋጥሙን…»
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
የሶሻል ሚዲያ ጥቆማ

ይህን ፔጅ ገብታችሁ Like & Follow ብታረጉ ብዙ ቁም ነገር ትገበያላችሁ !
fb.com/SafeLightMovement
t.me/safelightofficial

አራት ነገሮች ድባቴን ለማስወገድ፥

1. የፀሐይ ብርሃን (SUN)፦ የፀሐይ ብርሃን የሴሮቶኒን (Serotonin) መጠንን በመጨመር ካለንበት የድባቴ ወይም ከአሉታዊ ስሜት (Negative Energy or Pessimistic) እንድንወጣ ያደርጋል:: በቀን ከ15-20 ደቂቃዎች የፀሐይ ብርሃንን ብንወስድ ድባቴን ልናስውግድ እንችላለን።

2. ሰውን ማዋራት (TALK)፦ ይህ ሁለተኛው መንገድ ሲሆን ድባቴ በዋነኝነት ከሚያስከትለው የብቸኝነት እና ከሰው ጋር ያለመቀላቀል ስሜት ለማስወገድ ‘’ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው።’’ እንደሚል ፈሊጡ ለሰው ማካፈል አስፈላጊ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የህብረተሰብ ክበቦች (Social Clubs) ላይ መሳተፍ ድባቴው መተንፈሻ ያገኛል።

3. የራስን ግፅታ ማሳመር (GROOM):- በድባቴ ወቅት የራስን ግፅታ ማሳመር ውሰጣዊን እርካታ ይጭራል፡፡ ይህም ሰዎች ለእናንተ ያላቸውን አስታየት እንዲቀይርና አዎንታዊ አስታየቶችን በመሰንዘር ከነበራችሁበት የድባቴ ስሜት እንድትወጡ ይረዳል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የራስ መተማመናችሁን እንዲሁም የስራ ምርታማነታችሁን በመጨመር ረገድ ትልቅ አስተዋፆ አለው፡፡

4. ማንነትን ማስታወስ (IDENTITY)፡- ሁሌም ልታስታውሱት የሚገባው ዋናው ነገር በድባቴ ወቅት በሽታ አይደላችሁም፡፡ ማርቲን ሉተር አንድ ጊዜ እንደተናገረው ‘’ጨለማን ጨለማ ሊያሸንፈው አይችልም ብርሃኑ እንጂ፡፡’’ ስለዚህ በሽታን በሽታ ሳይሆን ግለሰቡ ብቻ ሊያሸንፈው የሚችለው፡፡ እናንተ አልማዝ በጭቃ ተለውሶ ከመሬት በታች እንደሚገኘው ሁሉ እናንተም በድባቴ ተከባችሁ የከበረ ማንነት እንዳላችሁ አስታውሱ፡፡
ተስፋ እነኝህን ጥቆማዎች እንድትወስዷቸው የሚያደርግ መሳሪያ ነው፡፡ ተስፈኛ ሰው መንፈሰ ጠንካራ ነው፡፡ መንፈሰ ጠንካራ ችግር የማያጋጥመው ሳይሆን ችግርን የሚያይበት መንገድ የተለየ መሆኑ ነው፡፡
ይህን መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ በማስተላለፍ ሌሎችም እንዲጠቀሙ ያድርጉ፡፡
#SafeLightRecommendation
#InspireEmpowerTransform

ይህን ፅሑፍ የወሰድኩት በአነቃቂ ንግግሮቹና በሕይወት ክህሎት ስልጠናዎቹ ከሚታወቀዉ ስለሺ (ሳልስ) ሴፍ ላይት ፔጅ ነው ፡፡ በተጨማሪ ለወጣቶች በነፃ የተለያዩ የስልጠና እድሎችን የሚያመቻች መልካም ራዕይ ያለው ወጣት ነው ፡፡

Facebook ፔጁን Like & follow አርጉት
fb.com/SafeLightMovement

በ Telegram
t.me/safelightofficial ታገኙታላችሁ ፡፡

መልካም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችንን ማበረታታቴን እቀጥላለሁ ፡፡
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_10
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE
#LOVE_Styles / #የፍቅር_አይነቶች
_______________________
ዛሬ የሳይኮሎጂ 10 ኛ ትምህርታችንን ወጣ ባለ ርዕስ ላይ ነገር ግን ለሁላችን አስፈላጊና ወሳኝ ስለሆነው ስለ ፍቅር እንወያያለን ፡፡

ፍቅር በተለያዩ ሙያዎች አንፃር በተለያየ መንገድ ተተርጉሟል ፡፡ Social psychology (በማህበራዊ ሳይኮሎጂ ) አንዱን ትኩረቱን በዚህ ላይ በማረግ የተለያዩ የፍቅር ትርጉም ፣ አይነት ... ላይ ያተኮሩ ጥናቶችን ያበረክታል ፡፡

በአጠቃላይ ስናየው ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ቶሎ በፍቅር ይወድቃሉ ሴቶች ደግሞ ተግባራዊ ጓደኛነትን መሰረት ባደረገ ፍቅር ይሳባሉ ፡፡ ፍቅር በብዙ መንገድ ተተርጉሟል ። ከነዚህ በጥቂቱ

*ለሰው ከዝምድና / ከቅርበት የተነሳ ያለን ጥልቅ ስሜት
*ከፆታዊ ፍላጎት ምክንያት ያለ መሳሳብ ወዘተ ......
_______________________
ይህ ብዙ ትርጓሜ ያሉት ፍቅር ስድስት አይነት የፍቅር አይነቶች /ዘይቤዎች / እንዳሉት ማህበራዊ ሳይኮሎጂስቶች ይናገራሉ ፡፡ እነዚህም

1.Eros-ኤሮስ ፦ለኛ ልዩ ውበት ያለውን ሰው በማየት የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ።

በዚህ ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ገና እንዳዩ የሚሰማ ጥልቅ የፍቅር ስሜት ነው ፡፡

2.Storge-ስቶርጄ :- ይህ ደግሞ ከጓደኛነት የተነሳ የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር የሚመነጨው በመለማመድ ፣ በመቀራረብ ፣ አብሮ ጊዜ በማሳለፍ ነው ፡፡

3. Ludus-ሉደስ ፦ ፍቅርን በጨዋታ መልክ የሚገለፅበት ዘይቤ ነው ፡፡

በዚህ #ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር በብዛት በማማለል የሚፈጠር ሲሆን ስራዬ ተብሎ ያልተያዘ ፍቅር ነው ፡፡


4. Mania-ማኒያ ፦ እጅጉን በኔነት ስሜት የሚያፈቅሩና ፍቅራቸውን በብዙ መከራ ራሱ የማይጥሉበት የተወሰነ ጊዜ የተቆጠረበት የፍቅር ግንኙነት ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።


5. Pragma- ፕራግማ ፦ ይሄ ደግሞ በምክንያት የተደገፈ ፍቅር ሲሆን በባሕሪ ፣ ባስተሳሰብ የሚመስለንን ሰው የምናፈቅርበት ዘይቤ ነው ፡፡

በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።

6. Agape- አጋፔ፦ይህ የፍቅር አይነት ያለአንዳች ምክንያት የምናፈቅረውን ሰው ከራሳችን በላይ የምናስቀምጥበት ነው ፡፡
ይህ የፍቅር ብዙ ጊዜ ከእምነት ጋር ይያያዛል ፡፡ እንደዚህ የሚያፈቅሩ ሰዋች ፍቅረኛዬ ከሚጎዳ እኔ ልጎዳ ፣ ከሚቸገር እኔ ልቸገር የሚሉ ናቸው ፡፡

#የሳምንት_ሰው_ይበለን !
በተጨማሪ አንድን ሰው እንደምናፈቅረውና እንደማናፈቅረው የምናውቅበት የሳይኮሎጂ መለኪያ መስፈርት በቴሌግራም ላይ አያይዤላችኀለሁ!
______________________________
🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉
ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ የመጀመሪያ አመት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚማሩበትን ሳይኮሎጂ መጽሐፍ ቴሌግራሜ ላይ POST ስላረኩኝ DOWNLOAD ማረግ ትችላላችሁ፡፡ በግሌ የይዘቱ ስፋት ላይ ጥያቄዎች ቢኖሩኝም GENERAL PSYCHOLOGY መጽሐፍ ለጠየቃችሁኝ ግን እንደመጀመሪያ ጥሩ መሳሪያ ነው፡፡

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 t.me/Psychoet 👍

፠፠______________________________፠፠
ምንጭ ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማስተማሪያ መሳሪያዎች (ለማደንቀው የማህበራዊ ሳይኮሎጂ መምህሬ ዴቭ )

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 t.me/Psychoet 👍

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠______________________________፠፠
ማንን እንደምናፈቅር የምናውቅበት መለኪያ ፡፡ ባሉት ክፍት ቦታዎች የሚሆነውን ስም ብቻ ጻፉና ብዙ ስሙን የጻፋችሁትን ሰው ❤️ አለ ማለት ነው ፡፡
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «#ክፍል_10 (በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE #LOVE_Styles / #የፍቅር_አይነቶች _______________________ ዛሬ የሳይኮሎጂ 10 ኛ ትምህርታችንን ወጣ ባለ ርዕስ ላይ ነገር ግን ለሁላችን አስፈላጊና ወሳኝ ስለሆነው ስለ ፍቅር እንወያያለን ፡፡ ፍቅር በተለያዩ ሙያዎች አንፃር በተለያየ መንገድ ተተርጉሟል ፡፡ Social psychology (በማህበራዊ ሳይኮሎጂ ) አንዱን ትኩረቱን በዚህ…»