15 ወርቃማ #አባባሎች! ሼር
ቴሌግራም ቻናል - @PSYCHOET
1) ምቀኞች መብዛታቸው በስኬት መንገድ ላይ የመሆንህ ምልክት ነው!
…
2) #ወንድ #ልጅ እናቱ በሕይወት እስካለች ድረስ #ሕፃን ነው..ለእናቱ!
…
3) በፈተና ላይ አለመታገስ ሌላ #ፈተና ነው!
…
4) #ፈገግታ ቃላት የሌለው መልካም ንግግር ነው!
…
5) ካንተ የባሰ አለና አመስግን ፈገግ በል!
…
6) ትንሽን ለመስጠት አትፈር ምንም አለመስጠት ከሱ የባሰ ነውና!
…
7) የተሸናፊዉ #ፈገግታ ያሸናፊውን #ደስታ ይቀንሳል!
…
8) የሁሉን #ሰው ውዴታ ማግኘት ሊደረስበት የማይቻል ግብ ነው!
…
9) #ነፍስ በኩራት ስትሞላ ጎደሎ የመሆኗ መገለጫ ነው!
…
10) ኩራተኛ ሰው ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ ሌሎችን ትንሽ አድርጎ እንደሚያይ ነው ነገርግን እሱንም ትንሽ አድርገው እንደሚያዩት አያውቅም!
…
11) ብዙ ጊዜ በጉጉት ከምንጠብቀው ይልቅ ድንገት የምናገኛቸው ነገሮች ውብ ናቸው እኛ ከለፋነው ጌታ የፃፈው መልካም ነውና!
…
12) ግኡዝ የሆኑት ውሃና አፈር ለእፅዋት አግልጋይ ናቸው ፤ እፅዋቶች ደግሞ ለእንስሳት ያገለግላሉ እንስሳት ፣እፅዋትና ግኡዛን ደግሞ የሰውን ልጅ ያገለግላሉ ... በተቃራኒው የሰው ልጅ ወደታች ወርዶ ለግኡዛን አገልጋይ (አምላኪ) መሆን ከጀመረ ያኔ ከነሱ የባሰ ይሆናል።
…
13) ብዙ ሰው ልጅ ለዘለዓለም እንደሚኖር ሆኖ ይለፋል አንድ ቀን ሳያልፍለት ይሞታል!
…
14) በሕይወት ትልቁ ስኬት የሕይወትን ትርጉም ማግኘትና አላማ ያለው ኑሮ መኖር ነው፡፡
…
15) በዚህ ቦታ .... ካነበባችሁት ፣ ከሰማችሁት ፣ ከምትከተሉት እምነት የምትወዱትን አባባል በcomment አሳውቁኝና ሌሎችም ያንብቡት፡፡
ሜሎሪና መጽሐፍ♥
#Share ይደረግ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

👍35❤13
#ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
መልዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ #Share ያድርጉት
(Social Rules ተብለው የተዘረዘሩ የማኅበራዊ ሕይወት ሕግጋትን ስመለከት ለኛስ አትጠቅምም ወይ ብዬ ነው ወዲህ ማምጣቴ)
==================
1. ይሰለቹሃል
አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!
2. 'ሼም ነው' ነው
የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!
3. አይባልም
"... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።
4. ክፈል
አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።
5. ነውር ነው
ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።
============
6. አታቋርጥ
ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።
7. አታብሽቅ
ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።
8. አመሥግን
ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።
9. ያለስስት አድንቅ
ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።
10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ
ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።
===================
11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ
ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።
12. ስነ ስርዓት
ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።
13. ክብር ለሁሉም
ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።
14. ስልክህን አስቀምጥ
ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።
15. አድብ
ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።
==========================
16. ተቆጠብ
ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።
17. መነጽርህን አውልቅ
ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!
18. አትሳሳት
በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።
19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት
በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።
20. ዕቃ መልስ
የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።
21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ
የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!
ሳይኮሎጂ ፔጅን #Like በማድረግ ቤተሰብ ኹኑ
@psychoet
©Abraham Tsehaye

👍54❤13😁1
ሀምሌ 3፣ 2015
ሜሎሪና መጽሐፍ ከወጣ ዛሬ ድፍን 3 ዓመት ኾነው።😃
በመጀመሪያ፥ በብዙ ሰዎች በመነበቡ እግዚአብሔርን አመሠግናለሁ። በመቀጠልም፥ አንብባችሁ መልካም አስተያየትና ትችታችሁን ለለገሳችሁኝ በሙሉ እግዚአብሔር ክብረት ይስጥልኝ ማለት እፈልጋለኹ።
በቀረው፥ ሜሎሪና ቁጥር ሦስትን በዚህ ዓመት ክረምት ላይ የማውጣት እቅድ እንደነበረኝ በተለያዩ ሚዲያዎች ስገልጥ የነበረ ቢኾንም፣ በተለያዩ ከመጽሐፋ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ግላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ምክንያት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ወደ ቀጣዩ ዓመት ከገና በዓል አካባቢ ለማውጣት ወስኛለሁ። እወዳችኋለሁ ❤️

👍29❤5
………✍ በጣም ገራሚ ታሪክ
😍 ትንሿ ቆንጅዬ ልጅ ሁለት አፕል እንደያዘች እናቷ መጣች ።
እናትም " የኔ ጣፋጭ አንዱን ለኔ ለእናትሽ ትሰጪኛለሽ ?" ስትል በትህትና ትጠይቃታለች ።
ልጅም ትኩር ብላ ከተመለከተቻት በኋላ አንዱን አፕል ግምጥ አደረገችው ። ቀጠለችና ሁለተኛውንም ደገመችው 😳 እናት በልጇ ሁኔታ ደንግጣ ፍዝዝ ብላ ቀረች ።
ስሜቷን በቁጣ ልታሳያት ብትሞክርም ድንጋጤው ከለከላት ☺️እንዴት በእኔ በእናቷ ትጨክናለች …? ብላ አሰበች ።
በዚህ መሀከል ልጅ የገመጠችውን አንዱን ለእናቷ እያቀበለቻት "እንኪ ማሚ ይበልጥ የሚጣፍጠው ይሄኛው ነው ።" አለቻት ። እናት ያልጠበቀችውን ክስተት በማየቷ ልጇን አቅፋ ተንሰቅስቃ አለቀሰች 😍
መልካም ቀን 💕
@psychiet

❤41👍23
አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ⛔️⛔️⛔️
ሁላችሁም በየግሩፑ #ሼር አድርጉት
በእነዚህ ሳምንታት በጓደኞቻችሁ ወይም በግሩፕ የሚላኩ ይሄን የመሰሉ መልዕክቶች ቴሌግራማችሁን ከሚጠልፉ ሰዎች የሚላኩ ሲኾን Linkun ከፍታችሁ ከገባችሁ የእናንተንም ቴሌግራም ጠልፈው ለሌሎች ወዳጆቻችሁ መልዕክት ይልካሉ። ስለዚህ እንደዚህ አይነት መልዕክት ከደረሳችሁ
1. Linkun እንዳትከፍቱት
2. የላከውን ሰው ካወቃችሁት ደውላችሁ ቴሌግራሙ እንደተጠለፈ ንገሩት
እባካችሁ ብዙ ሰው በዚህ እየተሸወደ ስለኾነ ይሄንን ማስጠንቀቂያ በየግሩፑ #ሼር አድርጉ።

👍22❤5
ግጭትን ማስተናገድ መቻል
“እኔ ከማንም ሰው ጋር መጣላትም ሆነ መቀያየም አልፈልግም!” ሲሉ የምንሰማቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከሰዎች ጋር አብረን እስከኖርን ድረስ ደግሞ ከግጭት መራቅ አንችልም፡፡
ግጭት እንዳይፈጠር ከመታገል ይልቅ ግጭትን የምናስተናግድበትን አቅም መፍጠር ነው ያለብን፡፡
ግጭት ለምን ያስፈልጋል?
1️⃣ ግንኙነትን ለማደስ ያስፈልጋል፡፡
2️⃣ ልዩነትን ለማወቅና ለማክበር ያስፈልጋል፡፡
3️⃣ ያመንበትን ነገር እንድናሳይ እድል ይሰጠናል፡፡
4️⃣ መተማመንን ይፈጥርልናል፡፡
5️⃣ አቅማችንን ለመፈተሸ ይረዳናል፡፡
6️⃣ ሁሌም የሚፈጠር ጉዳይ መሆኑን እንድንረዳ ይጠቅመናል፡፡
ከግጭት ለመሸሽ ከመመሞከር ይልቅ ያመንበትን ነገር ለማሳየት መሞከር የተሻለ ደስታን ይፈጥርልናል፡፡
ግጭት ሁሌም ያለ መልካም ነገር ነው፡፡
ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት!
ተመስገን አብይ Psychologist

👍32❤6👏1
#በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።
መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል። ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። አጋጣሚ ነው ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።
ብዙ ጊዜ ሰዋች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።
ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር።
© ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ

👍56❤25
‹‹ በዚኽች ምድር በቢሊዮን የሚቈጠር ሰው አለ፤ ፈጣሪ አንዱንም ሰው ያለ ምክንያት አልፈጠረም፡፡ ኹሉም ሰው በዐላማ መልካም ሥራ እንዲሠራ በዚኽም ምድር ላይ ተደስቶ እንዲኖር ተፈጥሯል፡፡ ሕይወታችንም የሚለካው በኖርንበት ዐላማ እንጂ በኖርንበት ዕድሜ ብዛት አይደለም፡፡››
ሜሎሪና ቴሎስ
አንተ የአላማ ሰው ነህ!
አንቺ የአላማ ሰው ነሽ!
"... የህይወትን አላማ የተረዳ ሰው የሚኖረው ለመብልና ለመጠጥ ሳይሆን ለህሊናው ነው።
ብዙ ሰው #ህሊናውን_ሸጦ #ለሆዱ_ያድራል።
በዚህ አለም የሚኖርበትን አላማ የተረዳ ሰው ህሊናውን ከሆድ ፣ ከስልጣን ፣ ከዝና ጋር አያወዳጅም ።
ህሊናው የሚገዛው ስለተፈጠረለት አላማ ፣
#ለእውነትና_ለፍትህ ብቻ ነው ። ..."
ሜሎሪና - ቴሎስ
መልካም ቀን 💚
መልዕክቱን ቢያንስ ለ5 ጓደኞቻችን እናጋራ

👍27❤12👏3
እኔ: ጌታዬ ጥያቄ ልጠይቅህ?
ፈጣሪ: ትችላለህ፤ ጠይቀኝ ።
እኔ: ዛሬ ይሄ ኹሉ ችግር እንዲደርስብኝ ለምን ፈቀድክ? ዛሬ እንደማትወደኝ ገባኝ
ፈጣሪ: ልጄ፣ ዛሬ ምን መጥፎ ነገር ደረሰብህ?
እኔ: ዛሬ ስንት የስራ ቀጠሮ እያለኝ አርፍጄ ተነሳሁ ይሄ ሳያንስ እየሮጥኩ ታክሲ ለመያዝ ስከቹል መኪና ጭቃውን ረጭቶኝ ልብሴ ተበላሸ፡፡ በፍጥነት ወደ ቤት ተመልሼ ልብሴን ቀይሬ ስመጣ ደግሞ የታክሲው ሰልፍ እረጅም ኹኖ ጠበቀኝ ።
ፈጣሪ: እሺ ሌላስ?
እኔ: በመንገድ እያለሁ ስልኬ ዘጋ?
ፈጣሪ : እሼ ልጄ አሁን ሁሉንም ላብራራልህ ፡፡ ዛሬ ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ የሞት መልአክ በቤት መጥቶ ነበር እኔ ግን በሕይወት እንድትኖር አንዱን መልአኬን ልኬ ላንተ እየተዋጋልህ ነበር፡፡ ይሄ እስኪያልፍ እንቅልፍ ጣልኩብህ
እኔ : እሺ 😔
ፈጣሪ፡ ታክሲ ቶሎ እንዳትይዝ ያረኩት ደግሞ የምትሄድበት ቦታ ቀድመክ ከደረስክ ሊደበድቡህ ስለነበር ያስረፈድኩህ ብዙ ሰዎች እስኪሰበሰቡ ድረስ ነው፡፡
እኔ : እሺ 😔
ፈጣሪ: ስልክህ እንዲዘጋ ያረኩት ደግሞ ለአንተ በሀሰት ደውለው ከዛ ንግግርህን በመቅዳት በፍርድ ቤት ሊከሱህ የፈለጉ ሰዎች ስለነበሩ ከነሱ ልጠብቅህ ነው፡፡
እኔ: ጌታ ሆይ እባክህ ይቅር በለኝ😢
ፈጣሪ: እሺ ልጄ ግን በማረገው ነገር ኹሉ እኔን እመነኝ ፡፡ ላንተ የማደርገው ኹሉ ለመልካም ነው፡፡
እኔ: አምንሀለው ጌታዬ
ፈጣሪ: እኔ ላንተ ያለኝ ሀሳብ ካንተ ሀሳብና እቅድ በላይ እንደሆነ አትጠራጠር፡፡
እኔ: አልጠራጠርም ጌታዬ ዛሬ ስለሆነው ነገር ኹሉ አመሠግናለሁ ፡፡ እንደምትወደኝ አሁን አወኩ።
ስለመልካምነቱ ፈጣሪያችንን እናመስግን!
መልዕክቱን ለሌሎችም እናጋራ
t.me/psychoet

👍34❤10