ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
10.7K subscribers
629 photos
4 videos
20 files
402 links
| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!


የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai


Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc
Download Telegram
ክፍል 5
ደስተኛ ሕይወት ለመኖር እነዚህን ተግባሮች ልምዳችን እናድርግ

10. ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ለደስተኛ ሕይወት

ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ደስተኛ እንደሚያደርጉ በጥናት ጭምር ተረጋግÚል፡፡ ሃይማኖት ያለን እንደየቤተ እምነታችን፣ መንፈሳዊ ብቻ ነን የምንልም እንዲሁ የመንፈስ ፍሬዎች የሚባሉ ተግባራትን በማከናወን ጎጇችን በደስታ ጸዳል የደመቀ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን፡፡

11. አካላችንን መንከባከብ ለደስተኛ ሕይወት

አእምሮአችን ከአካላችን ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም የአካላችን ደህንነት የአእምሮአችም ደህንነት ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል፡፡ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፤ ስፖርት መስራት ወዘተ የአካላችንን ጤና በመጠበቅ የአእምሮችንም ጤና ይጠብቃል፡፡ “Take care of your body. It’s the only place you have to live.” ይባላል፡፡ “አካላችሁን በሚገባ ተንከባከቡ፡፡ ብቸኛው የምትኖሩበት ስፍራ እሱ ነውና” እንደ ማለት ነው፡፡ አበቃሁ!

መልካም የደስታ ሕይወት!
መልካም የደስታ ቀን!

ተጠናቀቀ
#Share #Like
@psychoet
👍1👏1
ወላጆች በልጆቻቸው ፊት መጠቀም የማይገባቸው ቃላት
#Share

ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደ መሆናቸው መጠን የዕለት ተዕለት ዕድገታቸውን የሚያቀላጥፍ ማንኛውም ነገር ችላ ሊባል አይገባም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ወላጆች በልጆቻቸው ፊት አስተውለው ፤ መርጠውና ተጠንቅቀው የማይጠቀሟቸው ጸያፍና ባዕድ ቃላት በሂደት የልጆቻቸው በራስ መተማመን እንዲያሽቆለቁልና ስለዓለም የሚኖራቸው እይታ እንዲንሸዋረር ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ከዚህ በታች ወላጆች በልጆቻቸው ፊት ማለት የማይገባቸውን 9 ቃላት እንመለከታለን፡፡

1. ዝጋ! በስነ ምግባር የታነጸ ልጅን ማሳደግ ቀላል አይደለም ነገር ግን ወላጆች ስሜታቸውን ሳይቆጣጠሩ በብስጭትና በንዴት ልጃቸውን ማናገር አይጠበቅባቸውም፡፡ ልጆች ወላጆቻቸው በቃላት እየነገሩ ከሚያስተሙሯቸው ነገረ ይልቅ የእነሱን ምግባር አይተው የሚማሩት ነገር ይበልጣል፡፡

2. ትምህርት ይደብራል፡፡ ወላጆች የልጆቻቸው የመጀመሪያዎቹ መምህራን እንደመሆናቸው መጠን ልጆቻቸው በምንም ዓይነት መልኩ ትምህርት መጥላት የሚችሉበትን ቀዳዳ መክፈት የለባቸውም፡፡ ልጆቻቸው መምራኖቻቸውን በማመን ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር ተላምደው እንዲሄዱ ማድረግ ግድ ይላል፡፡ ወላጆቻቸው የጠሉትን ነገር ልጆቻቸውም ይጠላሉ፡፡

3. ሞት እንቅልፍ አንደ መተኛት ነው፡፡ ልጆች ከዕድገታቸውና ከዕድሜአቸው አንጻር አንዳንድ ጉዳዮችን በቀላሉ ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ልጆቻቸውን ለማስፈራራትም ይሁን በእነሱ ጥያቄ መሠረት ሞትን ከእንቅልፍ ጋር አመሳስለው ከነገሯቸው ልጆች በሚመሽበት ሰዓት ወደ መኝታ ቤት መሄድን ስለሚፈሩ ወላጆች ለልጆቻቸው የማይመጥናቸውን ነገር ባይነግሯቸው ይመረጣል፡፡

4. እስቲ አየዋለሁ፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው ማድረግ የማይችሉትን ነገር በቀጥተኛ ንግግር ሊነግሯቸው ይገባል፡፡ እሺም እንቢም ሊሆን የሚችል ነገር መናገር በወላጆችና በልጆች መካከል ሊኖር የሚገባውን መተማመን ይቀንሳል አልያም ያጠፋል፡፡ ስለዚህ እንዳንዴ እቅጩን መናገር ትልቅ ጠቀሜታ ስለሚኖረው ልጆች አንድን ነገር የተከለከሉበትን ምክንያት በቀላሉ እንዲረዱ ያስችላቸዋል፡፡

5. ወይኔ ወፍሬአለሁ! ወላጆች በልጆቻቸው ፊት ስለ ውፍረትና ክብደት መጨመር እያነሱ የሚጨነቁ ከሆነ በልጆቻቸው ጤናማ አመጋገብ ላይ ተጽእኖ ይፈጥራሉ፡፡ ወላጆቻቸው ብዙ በመብላት ነው የወፈሩት ብለው ስለሚያስቡ እንደ ወላጆቻቸው ላለመሆን ሲሉ የተዛባ የአመጋገብ ስርዓት እንዲከተሉ ማለትም ከምግብ እንዲታቀቡ ይገፋፋቸዋል፡፡

6. አትፍራ! ልጆች ደፋርና አካባቢያቸውን በደንብ እንዲያውቁ አድርጎ ማሳደግ ትልቅ ችሎታ ነው፡፡ ነገር ግን ወላጆች በደፈናው ልጆቻቸውን ምን መፍራት እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው ሳያሳውቋቸው በደፈናው አትፍሩ ማለት ልጆችን ወደ አደጋ ቀጠና እንደመገፋፍት ስለሚቆጠር አግባብነት ያለው ድፍረት ልጆችን ከአደጋና ለአደጋ ተጋላጭ ከመሆን ይታደጋቸዋል፡፡

7. ወይኔ በትኩሳት ነደሃል/ነደሻል፡፡ ልጆች ከአዋቂዋች ጋር ሲነጻጸሩ በቀላሉ ለበሽታ ተጋላጭ ናቸው፡፡ ስለዚህ ወላጆች ልጆቻቸው በሚታመሙበት ወቅት በፍጹም ስለ በሽታቸው መጠን መንገር አይጠበቅባቸውም ምክንያቱም ህክምና ከተከታተልን ህመማችን ይባባሳል ብለው ስለሚያስቡ፡፡ አልያም ከበሽታው ይልቅ ስነ-ልቦናዊ ጫናው ያይልባቸዋል፡፡

8. የብልግና ቃላትን መጠቀም፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው ጸያፍና የብልግና ቃላትን እንዳይጠቀሙ ከፈለጉ በመጀመሪያ ወላጆች እራሳቸው አንደበታቸውን ከጸያፍ ቃላት መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስም ይነሳል ከቤት ይደርሳል ጎረቤት እንደሚባለው፡፡

9. ደደብ ነህ/ሽ፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን በቁመት ያነሱ በአእምሮ ግን ትልልቅ ሰዎች አድርገው የሚስሏቸው ከሆነ ልጆቻቸው ስህተትን በሚሰሩበት ሰዓት ዘለፋና ወቀሳ ያወርዱባቸዋል፡፡ ልጅነት ወድቆ መነሳት ስለሆነ ልጆችን ደደብ ብሎ መሳደብ በፍጹም አያስፈልግም፡፡ እንዲሁም ልጅ ተሳስተው እየተማሩ ሲያድጉ ነው ደስ የሚለው ፍጹምነትን ከመጠበቅ ይልቅ፡፡


እንግዲህ ከላይ የተመለከትናቸው ወላጆች በልጆቻቸው ፊት መጠቀም የማይጠበቅባቸውን ቃላት ከብዙ ጥቂቱን ነው፡፡ እኔ መንገድ ካሳየዋችሁ እናንተ ደግሞ በየቤታችሁ አዳብሩት፡፡

#Share #Like
©zepsychologist (በአንቶኒዮ ሙላቱ)
@psychoet
1
#ክፍል_3
JOIN MY TELEGRAM CHANNEL t.me/psychoet

ነገሮችን የመረዳት ችሎታ! /Perception/
ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አርጉት !

ማንኛውም ሰው በአካባቢው ያሉትን ሁኔታዎች/ ክስተቶች የሚረዳው /የሚገነዘበው የተለያዩ ሁኔታዎችን አልፎ ነው ፡፡ ሰዎች እርስ በእርስ የሚለያዩበት አንዱ ነገር ስለ አካባቢያቸው ባላቸው ግንዛቤ ነው ፡፡
ለምሳሌ አንድ ቀን ለሁለት ሰዎች ጥሩ ነገር ብናረግ አንዳንዱ በቀና ተገንዝቦት ሲያመሰግነን ሌላው ደግሞ በክፉት ተመልክቶት ሊያጠፋኝ ነው ፣ ከኔ የፈለገው ነገር ቢኖር ነው ወዘተ ... በማለት እርዳታችንን በቀና መንገድ ከመረዳት በተሳሳተ መንገድ ይተረጉመዎል ፡፡
ታዲያ ለነዚህ ሰዎች ያደረግነው ተመሳሳይ መልካምነት መልሳቸው ለምን ተለያየ ስንል መልሱ ስለ ነገሩ ያላቸው መረዳት/ግንዛቤ ይሆናል ፡፡ ሳይኮሎጂ ደግሞ ስለ ሰዎች ነገሮችን አረዳድ ብዙ መልስ አለዉ ፡፡ በጣም አሳጥሬ እንደሚከተለው አቀርበዎለሁ ፡፡ በደንብ አንብቡት!

(Perception) ፐርሰብሽን ማለት በዙሪያችን ስላለው አለም ያለን መረዳት / ግንዛቤ ነው ፡፡

ፐርሰብሽን (መረዳት / መገንዘብ) ሶስት ሂደቶችን ያካትታል ፡፡ እነርሱም :-
1. መምረጥ / ማተኮር( Selection / Attention )
2.የተመረጠውን ማደራጀት (Organization)
3.መተርጎም ናቸው ( Interpretation )

[ ] 1.መምረጥ / ማተኮር( Selection / Attention ) ማለት ሁላችንም በቀን ተቀን እንቅስቃሴያችን በስሜት አካላቶቻችን መርጠን የምንቀበላቸውና የምናስገባቸውን (Stimuli) ድምፆች ፣ ምስሎች ፣ ጣዕሞች ... ናቸው ፡፡ እነዚህ በስሜት አካላቶቻችን ተመርጠው ከገቡ በኀላ ወደ አዕምሮአችን በነርቮቻችን አማካይነት ይደርሳሉ ፡፡ ነገር ግን ማንኛቸውም የምንሰማቸው ወይም የምናያቸው ነገሮች ወደ አዕምሮአችን አይደርሱም ፡፡ መርጠን ያተኮርንበት ነገር ብቻ ነው የሚደርሰው ፡፡
* ለምሳሌ ከቡድን ፎቶ ውስጥ አብዛኛው ሰው ቀድሞ የሚፈልገው የራሱን ምስል ከዛ ግን ወደ አዕምሮው የሚደርሰው ቀድሞ ፈልጎ አስተውሎ የተመለከተው የራሱ ምስል እንጂ የሁሉም ሰው አይደለም ፡፡
*ሌላም በታክሲ ተሳፍረን ስንሄድ ከውጭ የመኪና ድምፅ ፣ የተለያዩ ክላክሶችና ድምፆች ከውስጥ ደግሞ አንዳንድ ታክሲ ውስጥ ጮክ ብለው ከጎናቸው ካለው ሰው ወይም ከውጭ ሰው ጋር በስልክ ሲያወሩ ፣ በመኪና ውስጥ ከፍ ተደርጎ የተከፈተ ሙዚቃ እነዚህን ሁላ እንሰማለን ነገር ግን ይህ ሁሉ ድምፅ ወደ ጆሮአችን ቢገባም መርጠን የምናስገባው ግን የረዳቱን "ሂሳብ " የሚል ድምፅ ነው 😂😉 ፡፡ ለዚህም መሰለኝ ከመስማት ማዳመጥ ... ከማየት መመልከት የሚባለው ፡፡

መምረጥ ላይ ተፅእኖ የሚያረጉ 3 ሁኔታዎች አሉ
1.የድርጊቱ ሁኔታ (Environmental )
ለምሳሌ የነገሩ መጠን ፣ መደጋገም ፣ ትልቅነት ፣ እንቅስቃሴ
2.ሥነልቦናዊ ሁኔታ (Psychological ) ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚያስደስተንን የምንወደው ነገር ልብ እንሰጣለን ፡፡
3.አካላዊ(Physiological) አዕምሮአችን ውስጥ የሚገኙ ልዩ ጠቋሚዎች ወደ አንድ ነገር (ወደሚለዩት ነገር ) እንድናተኩር ሊያረጉን ይችላሉ

እሺ የመጀመሪያው ሂደት ይህ ከሆነ በተለያየ መንገድ የገባው መረጃ ምን ይሆናል ...

[ ] 2.የተመረጠውን ማደራጀት (Organization)
በዚህ ሂደት አዕምሮአችን ተመርጠው የገቡትን መረጃዎች በምንረዳበት መልኩ በቅርፅ በቅርፅ አርጎ ያስቀምጣል ፡፡
በዚህ ሂደት አዕምሮአቸን በተለያዩ መንገዶች መረጃዎችን ያደራጃል ፡፡ ዝርዝሮቹን ከታች ባስቀመጥኩት PDF ማንበብ ይቻላል፡፡
[ ] 3.መተርጎም ናቸው ( Interpretation )
ይህ የመጨረሻው ነገሮችን የምንረዳበት ሂደት ነው ፡፡ አንድ ተመርጦ የገባ መረጃ በስነስርአቱ ከተደራጀ በኀላ ካለን የሕይወት ልምምድ አንፃር ትርጉም ይሰጠዋል ፡፡ ልብ በሉ ይህ ሂደት ነገሮች ላይ ምን ያህል ተፅእኖ እንደሚያመጣ ? አዕምሮአችን ማናቸውንም የገቡ መረጃዎች ከቀድሞ ልምምድ (experience ) ትውስታ (Memory) አንፃር እየተረጎመ ያወጣቸዋል ፡፡

ይህ የመተርጎም ሂደት በተለያዩ ሁኔታዎች ተፅእኖ ይደረግበታል እነዚህም :-
*ስለ ነገሮች ያለን እምነት
*በወቅቱ የነበረን ስሜት (ተናደን ፣ ተደስተን ፣ አዝነን ...ነገሮችን የምንተረጉምበት ነገር ይለያያል)
*ግምት (ምከላ ) እኛ ወደምንፈልገው (ወደምንጠብቀዉ ) የመተርጎም ሂደት ነው ናቸው ፡፡

ይህ ሁሉ እኛ የማንቆጣጠረውና በማይክሮ ሰከንዶች የሚከናወን ሂደት ነው ። Telegram ላይ አንብቡት post ያረኩትን PDF . t.me/psychoet

❖❖______❖______❖❖
Source:- personal knowledge from different text books
#Addis Ababa University teaching material
ምንጭ ፦ ካለኝ ዕውቀት ማለትም ከዚህ በፊት ከሰማኀቸው ፣ ከተማርኩት እንዲሁም ካነበብኩት ለአንባቢ እንዲቀር አድርጌ በአማረኛ የፃፍኩት ነው ። ጥሩ መጸሐፎች የሚፈልግ #Telegram ቻናሌን Join አርጉ ፡፡

በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል፡፡ ማንኛውም ጥያቄ / ተጨማሪ ሀሳቦች Comment ማረግ ይቻላል ፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት እንዚህን እናያለን ፦
እንዴት ነገሮችን እንደምናስታውስና እንደምንረሳና ከዚህ ጋር ተያይዞ መርሳት የሚባል ነገር በሥነ ልቡና አለ ወይ ?


ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የTelegram ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!

THIS IS MY TELEGRAM CHANNEL :- YOU CAN Join and get BOOKS there .
🚗 @Psychoet👍
🚕 @Psychoet👍
🚙 @Psychoet👍
ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ አሥር የሕይወት መርሆች አውቅ ከሆኑ የሳይኮሎጂ መፅሀፍቶች የተወሰደ እና ከሳይኮሎጂ ባለሞያዎች/አማካሪዎች የተገኘ መረጃ!

#ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን #ሼር በማድረግ ይጀምሩ፡፡

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።

2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡

4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡

6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡

7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።

8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡

9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡

11. የአዲስ መረጃ ቤተሰቦች፣ ሼር ማድረግ ምን ያህል ደስ እንደሚያሰኝ ስለሚያውቁ ቀናቸውን የሚጀምሩት የኛን መረጃ ሼር በማድረግ ነው፡፡

ደስተኛ ህይወትን ለሁላችንም ይስጠን ! መልካም የጤና ጊዜ!!!

----------------------

ምንጭ - (ቶማስ እንደፃፈዉ፣ ፅሁፉ ከዶክተር አለ የተወሰደ)

🎡@🎡መልካም ቀን
#Join #Join #Join
🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
🚗 @Psychoet👍
🚕 @Psychoet👍
🚙 @Psychoet👍
ምድር
እሾህ🌵 🦠🦠🦠 🌵
ይዛ ብትቀበላችሁ እናንተ ግን
አበባ💐🌷🌹🥀🌺
ተክላችሁ ማለፍ ትችላላችሁ ፡፡
ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች!
"ሜሎሪና" መጽሐፌን ምን ያህሎቻችሁ አንብባችሁታል?

ያነበባችሁ 1⃣ ያላነበባችሁ 2⃣
👉ጠቃሚ ምክሮች👈

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

#መልካም_ቀን !
#Share #Like
@Psychoet
በምትኖሩት ኑሮ/ሕይወት ደስተኞች ናችሁ? መልሳችሁን አሳውቁን?
Anonymous Poll
25%
በጣም ደስተኛ ነኝ
30%
ደስተኛ ነኝ
20%
አላውቅም
18%
ደስተኛ አይደለሁም
8%
በጣም ደስተኛ አይደለሁም
የተፈጠርንበትን አላማ (ወደ እዚች ምድር የመጣንበት ምክንያትን) ምን ያህል እናውቃለን?
ከታች ከተዘረዘሩት አንዱን ምረጡ፡፡
Anonymous Poll
41%
በደንብ አውቃለሁ
32%
በትንሹ አውቃለሁ
21%
ምንም አላውቅም
6%
ማወቅ አልፈልግም
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «የተፈጠርንበትን አላማ (ወደ እዚች ምድር የመጣንበት ምክንያትን) ምን ያህል እናውቃለን?
ከታች ከተዘረዘሩት አንዱን ምረጡ፡፡
»
የደስታ ቀን ይኹንላችሁ
ለሰው የምትነግረውን ሚስጥር በደንብ አስብበት!

የዛሬ የቅርብ ጎደኛህ የነገ ዋናው ጠላትህ ሊሆን ይችላል፡፡
@psychoet
#ይቻላል
JOIN TELEGRAM t.me/psychoet

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©ZePsychology

መልካም ቀን!
#Share_it
ከእለታት በአንዱ ቀን ሁለት በእድሜ የገፉ አዛውንት ባለትዳሮች አንድ ቀን ድብር ይላቸውና....

ባልየው <<የወጣትነት ጊዚያችንን ብንመልሰው ምን ይመስልሻል>> ይላታል ሚስትም በጣም ተደስታ <<እሺ>> ትላለች።
ከዛም ባል<< በቃ እኔ ታች ሱቁ ጋር ልውረድና ድንጋዩ ላይ ቁጭ ብዬ አንቺ በዛ በኩል እለፊና ይዤ ላዋራሽ>> ተስማሙና ባል ወደታች ወርዶ ድንጋዩ ላይ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ጀመረ.....
ቢጠብቅ ቢጠብቅ ቢጠብቅ አትመጣም...4 ሰዐት ሙሉ ጠበቃት አልመጣችም። የሆነ ነገር አጋጥሟት ይሆናል ብሎ ወደቤት ሲመለስ ሚስት ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ያገኛታል።
ባል ደንግጦ << ምነው የኔ ውድ ምን ሆንሽብኝ >>
ሚስት ማልቀሷን ሳታቆም
.
.
.
<< እናቴ ከቤት መውጣት ከልክላኝ ነው።>>

😂😂😂

©Nejat Ahmed
@psychoet
👍2😁1
25 ጠቃሚ አባባሎች!!

1. አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡
-ፍራንክ ኦሽን

2. በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሀል፡፡
-ቶማስ ጄፈርሰን

3. ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ፡፡
-ዶናልድ

4. አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው፡፡
-ኢማም አሊ

5. በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው፡፡
-ዋልተር ባግሆት

6. ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው፡፡
-ጂም ዋትኪንስ

7. ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም፡፡
-አርል ኒተንጋል

8. ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው፡፡
-አዚም ፕሪሚጂ

9. ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ፡፡
-ዚግ ዚግላር

10. ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ፡፡
-አልበርት አንስታይን

11. አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም፡፡
-ካርል ጉስታቭ

12. ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ፡፡
-ሪያኖር ሮዝቪልት

13. እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡
-ኮንፊሺየስ

14. ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
-ቲም ኖትኪ

15. ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል፡፡
-ሱዚ ካስም

16. እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር፡፡
-ብሩስ ሊ

17. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
-ካረን ላንብ

18. ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል፡፡
-ስቴፈን ማክክሬን

19.ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው፡፡
-ሮቢን ሻርማ

21. መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል፡፡
-ኤሪክ ቶማስ

22. ፊትህን ወደ ፀሀይ ስታዞር ጥላህ ከኀላህ ይወድቃል፡፡
-የማዎሪ አባባል

23. 99% የሚሆኑ ሰዎች ሀሳብህን ከተጠራጠሩህ ፣ እጅጉን ስተሀል አልያም ታሪክ ልትሰራ ነው፡፡
-ስኮት ቤልስካይ

24. ፈፅሞ አትድከም ምክንያቱም አሁን እጅግ ከባድ የሆነብህ ስራ ከጥቂት ጊዜያት በኀላ ለሌላ ስራ መሟሟቂያ ይሆናል፡፡
-ያልታወቀ ሰው

25. ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ፡፡

@Psychoet
👍21
መልካም ዜና ለኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በሙሉ፡፡

በአይነቱ ልዩ የሆነ የስልጠናና የውድድር መድረክ ተዘጋጅቷላችኀል፡፡ አሸናፊው ወደ ካይሮ የሚሄድበትን ሽልማት የሚያገኝበት ትልቅ እድል!
ለኹሉም ሰልጣኞችና ተወዳዳሪዎች ደግሞ ሰርተፊኬትና ከወጣት መሪዎች ጋር በቅርበት የመወያየትና ልምድ የመቅሰም እድል ያገኛሉ::

The leadership conference and competition we have all been waiting for is here. Take part in this one of a kind event and get a prize.

Registration is open (በዚህ ሊንክ ይመዝገቡ)
https://bit.ly/leadershipconferenceregistration

Account no: 1000437297208 CBE

+251919367159
+251967304100

Detailed information is available via
https://bit.ly/3C7dD7l

Contactlccteam@gmail.com