Procurement Insights Ethiopia
1.22K subscribers
92 photos
3 videos
53 files
43 links
Join us for expert insights, best practices, updates, and advisory on procurement of Local and International market.

ይህ ቻናል በኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ የግዢ ሂደት ላይ በማተኮር መረጃ የሚሰጥ ሲሆን፦ ሙያዊ እይታዎች፣ ምርጥ ተሞክሮዎች ፣ መረጃዎችና ምክረ ሃሳቦች ይቀርቡበታል። ቤተሰብ ይሁኑ!

ያግኙን: @Procinsight_bot
Download Telegram
Channel name was changed to «Procurement Insights Ethiopia»
Channel photo updated
ጨረታ ፀንቶ የሚቆይበት ቀን/Bid Validity Period

ለጨረታ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፕሮፓዛል አዘጋጅተን መርሳት ከሌለብን ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ጨረታ ፀንቶ የሚቆይበትን ቀን / Bid Validity Period/ ማስቀመጥ ነው።
አላማው ምንድነው/ ህጉስ ምን ይላል?

The Bid Validity Period is the time frame stated in the bidding documents, during which the bidders’ submitted proposals remain binding and enforceable. It typically starts from the bid submission deadline and lasts until the expiry date specified in the bidding documents.

Purpose:

1. Time for Bid Evaluation: Allows the procuring entity sufficient time to evaluate the technical and financial aspects of the bids.

2. Contract Finalization: Provides the procuring entity time to process approvals, conduct negotiations (if applicable), and finalize contract awards.

3. Bidder Commitment: Ensures that bidders do not withdraw their offers during the validity period, maintaining fairness and competition.

4. Prevention of Price Volatility: Protects the procuring entity from price changes or other alterations by bidders during the evaluation period.

Legal Provisions:

As per Ethiopia’s  Federal Public Procurement Proclamation No. 649/2009, the following provisions are generally observed:

1. The Bid Validity Period must be clearly stated in the bidding documents.

2. Procuring entities can request an extension of the bid validity period if evaluation and award processes are delayed. However, bidders have the right to accept or reject the extension.

3. If bidders agree to an extension, they may be required to extend their bid security (if applicable) for a corresponding period.

4. Bids that fail to remain valid for the specified period are considered non-responsive.

Join Us: https://t.me/procinsightet
👍6
📆በግንባታ ግዥ ዘርፍ ስራ ልምድ ወይንም ዓመታዊ ተርን ኦቨር አላሟላም ብለው ከጨረታ ተሳትፎ ለመውጣት ከመወሰኖ በፊት ይህንን ይንብቡ?

በፌደራል መንግስት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥ መመሪያዎች ላይ ከተቀመጡ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል በግንባታ ግዥ ጨረታ ውድድር ላይ የስራ ልምዱ እና  ዓመታዊ ተርን ኦቨር ላይ በዶላር ምንዛሬ ለውጥ መሰረት የሚደረግ ማስተካከያ መኖሩ ሲሆን ይህም እንደሚከተለው ይሰላል።

1) ለጨረታ ግምገማ ዓላማ የሥራ ተቋራጩ በስራ ልምድነት እንዲያዝለት በሚያቀርበው የግንባታ ውለታ ዋጋ ላይ ማስተካከያ የሚደረግለት ሲሆን ይህም የሚሰላው ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ  ቀን 28 ቀናት በፊት የነበረው የምንዛሪ ምጣኔን ውሉ በተፈረመበት  ጊዜ በነበረው የምንዛሪ ምጣኔ በማካፈል ከተሰላ በኋላ በሚገኘው ውጤት በማባዛት ነው።

2)በተመሳሳይም በጨረታ ግምገማ ጊዜ ለሚደረግ ማስተካከያ አላማ ለተርን ኦቨር ስሌት የሚወስደው ሥራ ተቋራጩ ያቀረበው አመታዊ የግንባታ ሥራ ተርን ኦቨር መጠን' ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ ቀን 28 ቀን በፊት የነበረውን የምንዛሪ መጠን በእያንዳንዱ በጀት አመት የመጨረሻ ቀን ላይ ባለው የምንዛሪ መጠን በማካፈል ነው።

3) ሁለቱም ማስተካከያዎች የሚሰሉት የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ የሚሰጠውን የውጭ አገር ገንዘብ መሸጫ ዋጋ መረጃ መሠረት በማድረግ ይሆናል።

Join Us: https://t.me/procinsightet
👍5
📌  ማንኛውም ጨረታ ቴክኒካል እና ፋይንናሻል ፕሮፖዛል ከማዘጋጀት በፊት የሚከተሉትን ማድረግ እጅግ ጠቃሚ መሆናቸውን ልብ ይበሉ👇👇

🔵 1. ጨረታውን  ያወጣው ተቋም ያዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ በጥልቀት ማንበብና መረዳት

[ምንም እንኳ አብዛኛው ተቋም PPA 2011 Standard Bidding Document ተጠቅሞ ወይም እንደ ግዥው በጀት ምንጭ አለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ስታንዳርድ ጨረታ ሰነዶችን ተጠቅሞ የሚያዘጋጅ ቢሆንም እንኳ በጨረታ ሰነዱ የሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች እንደየፕሮጀክቱና ተቋሙ ሁኔታና መረዳት የሚሞሉ እንደመሆናቸው የተዘጋጀውን ሰነድ ገዝቶ በግዥ ላይ በሰሩና ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች በዝርዝር ማየት አስፈላጊ ነው]

🟢 2. የጨረታ ሰነዱን ገዝተን በዝርዝር ካየን በኋላ አሻሚ የሆኑ፣ ግልጽ ያልሆኑ እና መካተት የነበረባቸው የቀሩ ሰነዶች  አሉ ብለን ካሰብን፤ ጨረታውን ላወጣው ተቋም ማብራሪያ መጠየቅ አለብን

[ ማብራሪያን በተመለከተ እንዴት እና የት እንደሚጠየቅ የጨረታ ሰነዱን ክፍል አንድ ወይም ሁለት ላይ መመልከት ይኖርብናል። ይህንን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ጨረታውን ያወጣው ተቋም ማብራሪያ መስጠት ይኖርበታል]

🟡 3. በግዥ/ጨረታ ላይ ልምድ ያለው ባለሙያ  የቴክኒካልና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ዝግጅቱን እንዲያከናውን ማድረግ፤

🔴 4. ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉን ቅጾች/forms/ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን በማረጋገጥ እነሱን ተጠቅሞ ማዘጋጀት ይገባል። ከዚህ በፊት ከተጠቀምናቸው ቅጾች ሊለዩ ስለሚችሉ በጥንቃቄ መረዳትና ማየቱ ተገቢ ነው።

Join Us: https://t.me/procinsightet
👍4
🌐በአለም አቀፍ ግዥ እቃዎችን ለመግዛትና ለማስመጣት ሲያስቡ ስለ Incoterms® (International Commercial Terms/ዓለም አቀፍ የንግድ ቃላት)  ማወቁ የግድ ይሆናል። 

አጭር ስዕላዊ  መግለጫ 👆👆

🌐 Incoterms® (International Commercial Terms) are standardized trade terms published by the International Chamber of Commerce (ICC). These terms define the responsibilities of buyers and sellers in international and domestic trade, ensuring clarity in the delivery of goods, allocation of costs, and transfer of risk. The latest version, Incoterms® 2020, was introduced on January 1, 2020, and includes updates to meet the evolving needs of global trade.

Join Us: https://t.me/procinsightet
Procurement Tips:

📌 እንደ ዓለም ባንክ ከመሳሰሉ  አበዳሪ ተቋማት ጋር የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት ለሚያደርግባቸው ፕሮጀክቶች የጨረታ ሂደቱን የሚመሩት ህጎች የትኞቹ እንደሆኑ ያውቃሉ?

💼 የፌደራል መንግስት የግዥ አዋጅ 649/2001፣   አንቀጽ 6 (1) መሰረት:
ይህ የግዥ አዋጅ የፌደራል መንግስት ከአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ መንግስታት ወይም ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ባደረገው ስምምነት ወይም ከስምምነቱ የመነጨ ግዴታ ጋር የማይጣጣም ከሆነ በስምምነቱ የተመለከተው እንደሚጸና ይገልጻል።
🛠ለምሳሌ፡  ከዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበር  ፕሮጀክት በፋይናንስ ስምምነቱ ላይ ግዥዎች በምን መልኩ እንደሚከናወኑ እና የትኛውን የባንኩን መመሪያ እንደሚከተሉ የሚገልጽ ሲሆን፤ ሂደቶቹን የሚመሩ መመሪያዎች፣ Standard Bidding Document በባንኩ ድህረገጽ የሚገኙ ናቸው።

🔍የምንሳተፍባቸው ጨረታዎች የገንዘብ ምንጩንና የሚከተሉትን መመሪያዎች የትኞቹ እንደሆኑ ማወቁ መሰረታዊ  ጉዳይ ነው። ይህም በአሰሪው መስሪያ ቤት ጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ መቀመጥ ይኖርበታል።

🔗 Channel: https://t.me/procinsightet

💬 Contact Us: @Procinsight_bot
Procurement_News:

መንግሥት በራሱና በውጭ ተቋራጮች ግንባታዎችን በመቆጣጠሩ የግል ሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ።

🏗️ መንግሥት የመንገድና የሕንፃ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የራሱን የግንባታና የዲዛይን ድርጅቶች በማቋቋም፣ ፕሮጀክቶችን መያዙና የተቀረውን ለውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች እየተሰጠ መሆኑ፣ የአገር ውስጥ የግል የሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ።

ይህ የተገለጸው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከግሉ የግንባታ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ባለፈው ሳምንት ባደረገው የምክክር ጉባዔ ላይ ነው።

ሚኒስቴሩ የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች በአሥር ዓመታት ውስጥ በአገር ውስጥ ያላቸውን የገበያ ድርሻ ወደ 75 በመቶ፣ በቀጣናው ደግሞ የ25 በመቶ ድርሻ እንዲያሳድጉ ዕቅድ ቢይዝም፣ የሥራ ተቋራጮች በበኩላቸው መንግሥት በውጭ ተቋራጮች ላይ ያለውን ከፍተኛ ጥገኝነት፣ የክፍያዎች መዘግየት፣ በቅርብ የተካሄደው የኢኮኖሚክ ሪፎርም በኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረውን ጫናና ሌሎችም ማነቆዎችን በማንሳት፣ መንግሥት በእርግጥ ኢንዱስትሪውን ያውቀዋል ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

ዘገባው የሪፖርተር ነው። ዝርዝሩን ያንብቡ👇
http://bit.ly/3PlqSd5

🔗 Join Us: https://t.me/procinsightet

💬 Contact: @Procinsight_bot
👍4
Procurement and property proclamation1333.2024-.pdf
1.7 MB
📰 ከ2001 ዓ/ም ጀምሮ ለ16 ዓመታት በስራ ላይ የነበረውን የፌደራል መንግስት  ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ  649/2001ን በመሻር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተጸደቀውን አዲሱ የፌደራል መንግስት  ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/2016 እነሆ አያይዘንላችኋል።👆

Key Note:

🔴 ይህ አዋጅ ከመፅናቱ በፊት ተጀምረው አዋጁ በፀደቀበት ዕለት ያልተጠናቀቁ የመንግሥት የግዥ እና የንብረት አስተዳደር ሥራዎች ወይም
ክርክሮች በመንግሥት የግዥና የንብረት
አስተዳደር 649/2001 እና በአዋጁ መሠረት በወጡ መመሪያዎች መሠረት ፍፃሜ ያገኛሉ፡፡

🟡 ይህ አዋጅ ምን አዳዲስ ነገሮችን ይዟል። በቀጣይ በዝርዝር እናቀርብላችኋለን!

🔗 Join Us: https://t.me/procinsightet

💬 Contact: @Procinsight_bot
3👍3
2017 2nd QUARTER CONSTRUCTION WORKS (ONLY DIRECT COST).pdf
20 MB
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በየሩብ ዓመት የሚያወጣው የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት ከላይ ተያይዟል ☝️

🔗 Join Us: https://t.me/procinsightet

💬 Contact: @Procinsight_bot
👍2
Procurement_Directive_Amharic.pdf
2.1 MB
📌 የፌደራል መንግስት የግዥ አፈፃፀም ረቂቅ መመሪያ ከላይ ተያይዟል።የፌደራል ግዥና ንብረት ባለስልጣን ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ግብአት እያሰባሰበበት ይገኛል።

📌 ከረቂቅ መመሪያው መረዳት እንደሚቻለው የውለታ ጊዜያቸው 18 ወራትና ከዚያ በላይ ለሆኑ የግንባታ ሥራዎች ብቻ የዋጋ ማስተካከያ እንደሚደረግ የሚገልፀውና ማስተካከያው ተፈጻሚ የሚሆነው ከአስራ ሁለት ወራት በኋላ መሆኑን የሚያስቀምጠው የዋጋ ማስተካከያ አንቀፅ ማሻሻያ አልተደረገበትም።

🔗 Join Us: https://t.me/procinsightet

💬 Contact: @Procinsight_bot
1
Procurement Insights Ethiopia
Procurement_Directive_Amharic.pdf
አዲሱ የፌደራል መንግስት የግዥ አፈፃፀም ረቂቅ መመሪያ

📌 ከላይ በተያያዘው አዲሱ የፌደራል መንግስት የግዥ አፈፃፀም ረቂቅ መመሪያ ላይ ከተካተቱ አዳዲስ ጉዳዮች መካከል የግዥና ንብረት ባለስልጣን በቀጣይ በዝርዝር የሚያሳውቃቸው በተመረጡ የዕቃ እና ግንባታ ግዥዎች ላይ የሕይወት ዘመን ወጪ (Life Cycle Cost) ታሳቢ ያደረገ የጨረታ ውድድር  አንዱ ነው።

📌 ይህም በሚከተለው መልኩ እንደሚሰላ አስቀምጧል።

የሕይወት ዘመን ወጪ (Life Cycle Cost)= የመጫረቻ ዋጋ + የሕይወት ዘመን ወጪዎች ድምር (ማለትም የስራ ማስኬጅ ወጪ+ የጥገና እና መለዋወጫ ወጪ+ የማስወገጃ ወጪ)

🔗 Join Us: https://t.me/procinsightet

💬 Contact: @Procinsight_bot