Abraham media
127 subscribers
15 photos
1 video
16 links
Spiritual scripts
Download Telegram
ህይወት አላማ ናት። የምንኖረውን ህይወት ከውስጣችን የጀመረ ከሆነ በእዉነት ህይወተ አላማ ናት የሚለው መርህ ገቡቶናል።ንጉሱ ዳዊት ይህ የገባው ይመስለኛል ለልጁ ለጠቢቡ ሰለሞን ሲመክረው ሰው ሁን አለው
ሰው መሆን ማለት ህይወትን ከውስት መጀመር ማለት ነው።
ህይወታችን ከውስጥ መጀመሩ ቀርቶ ከምናየው ነገር ከሆነ የሚጀምረው ሰው መሆናችን ይቀርና እንስሳ እንሆናለን እንስሳ የሚመራው በአላማ ሳይሆን በስሜት ነው ስሜት ደግሞ ከውጭ ወደውስጣችን የማገባ ነገር ነው።
ህይወታችን በአላማ የማንመራ ከሆነ ሰው መሆን አንቺልም ሰው መሆን የሚለካው በአላማና በስሜት ነው አንጂ በማግኘትና በማጣት አይደለም
"የሰው ልጅ ትልቁ ድል
ራስን ማሸነፍ ነው!
አቅምን መገንባት፣ፍላጎትን መገደብ ፣ስሜትን መቆጣጠር ፣ ሀላፊነት መውሰድ መቻል አለብን ፤ይህንን ማድረግ ስንጀምር በራስ መተማመናችን ይጨምራል ፤ በራሱ ሚተማመን ሰው ራሱን ይመራል ፤ ራሱን በራሱ መምራት የሚችል ሰው ካለመው ቦታ ይደርሳል፡፡"
የአይሁድ ጠላቶች ሊሠለጥኑባቸው በነበረው ቀን፥ አይሁድ በጠላቶቻቸው ላይ እንዲሠለጥኑ ነገሩ ተገለበጠ እንደሚል የእግዚአብሔር ቃል:- ዛሬም በእናንተ ነገር ላይ ጠላት ያወጣው የትኛውም አዋጅ በኢየሱስ ስም ይገልበጥ!!
( #ታካች_አትሁን )

(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 6)
----------
6፤ አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን።

👉ጥበብ የምትሸጥ አይደለችም። ጥበብ #ስጦታ ናት!❤️

ጉንዳን ዝናብና ጭቃ በሚሞላው የክረምት ወር ከጉድጓዱ መውጣትና እንደ ልብ መንቀሳቀስ ስለማይችል ነው በቀላል በጋው ፥ ለከባድ ክረምቱ ስንቅ የሚያከማቸው። 'ነገ' የሚባል ቅዠት አዕምሮውን አስጨንቆት ግን አይደለም ከነግህ እስከ ሰርክ ይታትራል። እግረመንገድ የዛሬ ትጋቱ የነገን ጨለማ ያጸኸያል። ከዚህ ምን እንማር? ቀን ሳለ፣ ጉልበትህ ሳይከዳህ ፣ ሰማያዊ #መዝገብ ታከማች ዘንድ ይገባሀል!. ምንም ልትሰራባት የማትችልበት #ግዜ በህይወትህ ይመጣልና።
#ዛሬ_የትላንት_ዘር_ውጤት ሲሆን #ነገ_የዛሬ_ዘር_ፍሬ ነው!! ዛሬ ላይ ምን እያከማቸህ ነው? #ገንዘብ ነው? ፣ #ጥላቻ ነው? #ተንኮል ነው? ፣ #ጥልን ነው? #ዘረኝነት ነው? እነዚህ ሁሉ እጥፍ ሆነው #ነገ ላይ ታጭዳቸዋለህ!. #መዝራት_ማጨድ እ/ራዊ መርህ ነውና!. የምትፈልገውን ለማግኘት፥ የምትፈልገውን ያንን ዐይነት #ዘር መዝራት አለብህ! ፥፣፣ በአጭሩ ለ #መንፈሳዊ ዕድገት ፥ #ስጋዊ ነገሮችን መዝራት የለብህም። ይህ ጉንዳን #ክረምትን survive ማረግ ስለፈለገ ፥ በጋ ላይ #አልተኛም!. #በጋ ላይ #እንቅልፍን ቢዘራ ፥ #ክረምት ላይ #ረሀብን እንደሚያጭድ ያውቃልና!. 👉አንተም #ቀን ሳለ በጉብዝናህ ወራት #ግዜህን መንፈሳዊ ነገር ላይ #ዝራ ፥ ለዚህኛው አለም ፥ ለሚመጣውም #ስንቅ ይሆንሀልና!!
🔘መልካም ነገሮች እንዲሆኑ አድርጉ🔘

መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።
እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ (ማቴዎስ 12፡35-36)

✔️በምሳሌ 16፡29-30 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ግፈኛ ሰው …
ዓይኑን የሚዘጋ ጠማማ አሳብን ያስባል ከንፈሩን የሚነክስ ክፋትን ይፈጽማል። ይላል፡፡ አስቡት እስቲ! ግፈኛ ሰው ዓይኑን ዘግቶ ጠማማ አሳብን ያስባል፤ ከንፈሩን የሚነክስ ክፋትን ይፈጽማል ይላል፡፡ በሌላ አነጋገር፣ ክፋትን ለማቀነባበር ሃሳቡን ይጠቀማል፤ ከንፈሩን በመጠቀም
ደግሞ እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡ እየተናገረ ያለው የማሰላሰልን መርህ ነው፤
ይህ ደግሞ ለመልካምም ነገር ለክፋትም ይሰራል፡፡

✔️እግዚአብሔር ክፉ ሃሳብ እንዴት እንደሚሰራ እያሳየን ነው፤ በዚያውም ደግሞ መልካም ስራም እንዴት እንደሚሰራ እያሳየን ነው፡፡
ክፉ ሰው ይህንን መርህ በመጠቀም ውጤትን እንደሚያመጣው ሁሉ፣ መልካምም ሰው ይህንኑ መርህ በመጠቀም መልካም ውጤትን ማምጣት ይችላል፡፡ ይህንን ለማድረግ ሃሳባችሁን መጠቀም ትችላላችሁ፤ ዓይናችሁን በመዝጋት አስደናቂና አስገራሚ ነገሮችን አቀነባብሩ፡፡

✔️ይህንን ተለማመዱ፡፡ የማሰብ ኃይላችሁ፣ የመፍጠር ችሎታችሁ ነው። ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ፣ ዓይናችሁን ዘግታችሁ አሰላስሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል መሰረት በማድረግ ታላላቅ ነገሮችን አቅዱ እና ስለእነሱ ተናገሩ፡፡ ይህንን መርህ በመጠቀም፣ ለራሳችሁና ዙርያችሁ ላሉ ሰዎች የተዋበ ህይወትን ፍጠሩ፡፡

✔️ከበርካታ የጸሎት ጠቀሜታዎች አንዱ ይህ ነው፤ ምክንያቱም ስትጸልዩ በመንፈስ ራእይን ታያላችሁ፡፡ የዚህ አይነቶቹን ራእዮች ጻፏቸው፤
ከዛም በእምነት ንግግራችሁ እውን አድርጓቸው፡፡ በመክፈቻ ጥቅሳችን መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል ብለናል፡፡
በህይወት የምትፈልጓቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ውስጣችሁ ነው ያሉት፡፡
እይዋቸውና በቃላቶቻችሁ እውን አድርጓቸው፡፡ በመንፈስ አለም ውስጥ አስቀድመው አሉ፤ እውን የሚያደርጓቸው ቃላቶቻችሁ ናቸው፡፡


🗣የእምነት አዋጅ🗣

የማሰብ ሀይሌ የምፈልገውን ነገር የምፈጥርበት ብቃቴ ነው፤ ስለሆነም በመንፈስ በምጸልይበት ጊዜ በክርስቶስ የሆነውና ክብር የሞላበት ህይወቴ አይምሮዬን ያጥለቀልቀዋል ቃል በማወጣበትም ጊዜ እውን ይሆናል፡፡
አይቻልም የሚባል ነገር በእኔ ዘንድ የለም፡፡ በክርስቶስ ክብር የሞላበት የድል ህይወት እኖራለሁ፡፡ ሀሌሉያ!
🔅 መረረብክ ስትበላው? 🔅

👉 የምትበላውን ፍሬ ካልወደድከው እና ከመረረክ አስተውል ችግሩ ያለው የሆነ ጊዜ የዘራከው ዘር ላይ፡፡
👉 ፍሬውን ለመቀየር ያለክ አማራጭ ምትዘራውን መቀየር ነው፡፡
👉 ስንዴ ዘርተክ በቆሎ እንደማታጭድ ያለዘራከውን ለማጨድ መሞከር ሞኝነት ነው፡፡
👉 ዛሬ በምትወስደው ውሳኔህ፣በምትመርጠው ምርጫህና በምትዘራው ዘር የነገህን በትክክል መተንበይ ትችላለክ፡፡
ነገህ ያለው ዛሬክ ላይ ነው ዛሬ ላይ ምታበስለው ከሌለ ነገ ላይ የምትበላው አይኖርክም፡፡
👉 ነገህን ዛሬክ ላይ ስራውውውውውውውው ዘርህን ቀይረው ፍሬህ ይቀየራል፡፡
👉 ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል አንተም
እንደዛው፡፡
#በህልውና_መቆየት

👉አሳ ከውሀ ውጪ መኖር የማይችለው ስሪቱ ለውሀ ስለሆነ ነው #ክርስቲያን ስርይቱ ለመንፈስ ቅዱስ ነው ከመንፈስ ቅዱስ ውጪ መኖርም መሰንበትም አይችልም።
👉በምድር ላይ አለ እግዚአብሔር መገኘት መኖር የማይቻልበት ብቸኛው ህይወት የክርስትና ህይወት ነው።ክርስትያን የሞተው ትንቢት መናገር ሲያቆም ሳይሆን ከመገኘቱ የራቀ ቀን ነው።የክርስትና ኑሮ የሚጣፍጠው መኖር መኖር የሚለው በመገኘቱ ውስጥ ብቻ ሲኖር ነው።የክርስትያን ደስታው፣ርካታው በመገኘቱ መኖር ነው።
🙏የአበቴ መገኘት ሁል ጊዜ ከአንተ/ከአንቺ ገሪ ይሁን
🔆 #ውበት_ብቻውን_በቂ_አይደለም....
____
አንድ ቀን ልጅ ለእናቱ "እናቴ በጣም ቆንጅዬ የሆነች በጣም የምወዳትን ፍቅረኛዬን ዛሬ ላስተዋውቅሽ እፈልጋለሁ" አላት። እናቱም በጣም ደስ ብሏት እሺ የኔ ልጅ ገበያ ደርሼ እመጣለሁ ብለው ወደ ገበያ ሄዱ።
:
ልጁም ለፍቅረኛው ስልክ ደውሎ ዛሬ እንደበፊቱ ተደብቀሽ አትሄጅም ከእናቴ ጋር አስተዋውቅሻለሁ ብሏት ቶሎ ነይ አላት። እሺ ብለ ታጥባ ለባብሳ እራሱዋን በመስተዋት እያየች "ዋውውውው በጣም ቆንጆ እኮ ነኝ። እንደዚህ አይነት ቆንጆ ሴት አግኝታ ለልጁዋ እምቢ የምትል እናት አትኖርም" እያለች ከቤት ወጣች። ከዛም ባስ ውስጥ ገባች።
:
አንዲት እናት ብዙ እቃ ተሸክመው መጡና እባክሽን ልጄ እኔ መስኮት የሌለበት ቦታ መቀመጥ አልወድም ወደዛ ጠጋ በይልኝ አሏት። "አቦ አልፈልግም እኔ እኮ ነኝ ቀድሜ የተቀመጥኩት ስለዚህ አይሆንም" አለች። እሺ ልጄ ይቅርታ ብለዉ ዝም አሉ። ከዛ ከባስ ውስጥ አብረው ወጥተው ታክሲ ጠበቁ አንድ ታክሲ መጣና ለአንድ ሰው የሚሆን ቦታ ብቻ ነው ያለው አለ።
:
ሴትዮዋም "እባክሽ ልጄ በጣም አጣዳፊ ችግር አለብኝ ቶሎ እቤትም መድረስ አለብኝ በዛ ላይ እቃዬ በጣም ከብዶኛል። እኔ ልግባ አንቺ ሌላ ታክሲ ጠብቀሽ ነይ ሲሏት "አቦ ምንም አይነት አሮጊት ናት ታዲያ ይሄ የኔ ችግር ነው እንዴ" ብላ ታክሲ ውስጥ ገብታ ሄዳች።
:
ቤት እንደገባች "እናትህ የት አሉ?" አላች አይ ገበያ ሄዳለች አሁን ትመጣለች ሲል "ዋውውውው እንደዚህ ቆንጆ የሆንኩኝ ልጅ አገኝተው በጣም ነው ደስ የሚላቸው" አለች። እሱም ትክክል ነሽ እርግጠኛ ነኝ እማ በጣም ትወድሻለች አለ።
:
እናቲቱም በሌላ ታኪስ ትንሽ ቆይተው ቤት ሄዱ ቤት ሲሄዱ መንገድ ላይ እንደዚህ እየሰደበቻቸውና እያዋረደቻቸው የነበረችውም ሴት እቤት አገኟት "ልጄ እቺ እርኩስ ሴት እዚህ ቤት ምን ትሰራለች?" አሉ "እማ ኢች እኮ የኔ ፍቅረኛ ናት" አለ ከዛ እናቱ የሆነውን ሁሉ ነገሩት እሱም እውነት ነው ወይ ብሎ ጠየቃት "አዎ ግን የአንተ እናት መሆኑዋን አላውቅም ነበራ!" አለች። እናት ያው እናት ናት የለም የእኔን እናት ወዶ የሌላውን እናት መጥላት ግብዝነት ነው።" ብሎ አባራረት።
:
ሴቶችዬ ውበት እና ደም ግባት ብቻውን በቂ አይደለም የሴት ልጅ ውበቷ ውስጥ ያለው በተግባር የሚገለጠው ስብናዋ ነው።
አስተማሪ ሆኖ ካገኙት #ሼር(Share) በማድረግ ለወዳጅዎ...
LAW AND GRACE
The Law is a mirror so what a mirror does is it shows where there is imperfection but it can't remove or make right the imperfection. So the law is like a mirror it's a showing instrument, nothing more than that.
Grace is the hand that takes away what the mirror shows you. Or it's the perfectly of the image shown by the mirror. Grace is like a medicine for a rush, if some person has a rush on there face nd rubs ointment on it they get healed. They see the rush in the mirror but the mirror can't take away the rush it can only show it. But the moment the ointment is applied the rush goes away.
The Law preceded the grace of God so that we can see that we needed saving, if a person doesn't know that they need saving then the medicine is insignificant for that person.
So we understand that the law by it self isn't active but makes the person active by showing their imperfection nd demanding a perfection.
GRACE is active Grace takes away the imperfection from us and makes us perfect in the right of God, Grace is active but the person doesn't need to work to earn it.
“For it is by free grace (God's unmerited favor) that you are saved (delivered from judgment and made partakers of Christ's salvation) through faith. And this is not of yourselves , but it is the gift of God;”
— Eph 2:8 (AMP)
ENJOY AND LIVE IN ND BY THE GRACE OF GOD.
የሰው ጥንካሬ የምለካው በደረሰበት መከራ ልክ ነው።
ሰው ምንም ችግር ወይም ጫና ሳይደረስበት ጠንካራ ነኝ ማለት በፍጹም አይችልም።
#ወደ ክርስትያን ስንመጣ እግዚአብሔር ለምወዳቸው ብቻ ያዘገጀው መከራ ወይም ቅጣት አለ።
ይህንን ቅጣት ሁላችንም ተካፍለናል በትንሹም በትልቁም በትልቁ የእግዚአብሔርን መከራ የተካፈለ መንፈሳዊ ሰው ይባላል።
መንፈሳዊ ሰው መከራ ስደርስበት እንደ ሙሉ ደስታ ይቆጥራል ወደ እግዚአብሔር የምያስጠጋውም ያ መከራ መሆኑን ስለምያውቅ በመከራው ይመካል።
#እግዚአብሔር መከራውን እንድያነሳለት ሳይሆን መከራውን ማለፍ የምችልበትን አቅም ይጠይቃል።
#አለት ላይ የቆመ ክርስቲያን አሻዋ ላይ ከቆመው ሰው ይልቅ ብዙ ችግር ይደርስበታል ነገር ግን የቆመው አለቱ(ክርስቶስ) ላይ ስለሆነ አይነቃነቅም።
.....እምቢ ሚል ቃል ልብህ እና አፍህ ውስጥ እስከሌለ ድረስ የውነቴን ነው ምነግርህ በያዝከው መንገድ 200 ሜትር እንኳን በስርአት አትሄድም ምክንያቱም 10ሜትር እንደሄድክ ዙሪያህ በሙሉ አብረን እንሂድ በሚሉ ሰዎች ይሞላል። እሽ ስለሆነ ምላሽህ የሌሎች ሰዎች ጉዞ አጃቢ እንጅ ሂያጅ አትሆንም።
#ሙሴ እምቢን ባያውቅ ኖሮ ታሪክ እሱን ሚያወቀው በፈርኦንነቱ ነበር። እምቢ ያለው ፈርኦን (ንጉስ) መሆንን ነበር።
#ሊያነግሱህ የሚፈልጉትን በሙሉ እምቢ የሚል ልብ ይኑርህ።
.....ሰይጣን ትንቢት ሲነገርህ ምንም አይልህም። መራመድ ስትጀምርም ምንም አይልህም። ነገር ግን እግዚአብሔር ያሰበልህ ፍፃሜ ሲቃረብ የመጣህበትን መንገድ እንዲሁ በከንቱ እንደደከምክ እየነገረክ ከፍፃሜ ያስቀርሀል። ይህም ካልሆነለት ፍፃሜህ ጋር እንዳትደርስ ሌላ መንገድ እና ሌላ ሰው ሰጥቶህ መንገድህን ካዲስ ያስጀምርሀል። እሱ መሄድ እና መጓዝ የጀመርክ ሰአት አይፈራህም ነገር ግን ከንአን ውስጥ ልትገባ እንደሆነ ያወቀ ሰአት የዛኔ ጦሮቹን አንስቶ ከፊትህ ይቆማል። ሰይጣን መንገደኛ ሰዎችን አይፈራም። ነገር ግን ለፍፃሜያቸው የቆረጡ እና በራሳቸውም ጭምር ላይ ለመወሰን ማይከብዳቸውን ጨካኝ እና የቆረጡ ሰዎችን ያየ ሰአት መንገድ ይለቅላቸዋል። ምክንያቱም እነሱን ከማቆም ፀሀይን ከከዋከብት ጋር ማውጣት : ጨረቃን ደሞ በቀን እንድትወጣ ማድረግ ይቀላል። እነሱን ከማቆም ደመናን እግርስር : የምድርን አፈር ላይ መስቀል ይቀላል። ደግሜ እላለሁ እነዚህን ሰዎች ከማቆም የወንዝን ጅረት ከታች ወደላይ እንዲፈስ ማድረግ : ተፈጥሮን መቀያየር ይቀላል።
#ላየሀው_ነገር_ጨካኝ_ሁን
#እምቢ_በል
.....ሰይጣን ትንቢት ሲነገርህ ምንም አይልህም። መራመድ ስትጀምርም ምንም አይልህም። ነገር ግን እግዚአብሔር ያሰበልህ ፍፃሜ ሲቃረብ የመጣህበትን መንገድ እንዲሁ በከንቱ እንደደከምክ እየነገረክ ከፍፃሜ ያስቀርሀል። ይህም ካልሆነለት ፍፃሜህ ጋር እንዳትደርስ ሌላ መንገድ እና ሌላ ሰው ሰጥቶህ መንገድህን ካዲስ ያስጀምርሀል። እሱ መሄድ እና መጓዝ የጀመርክ ሰአት አይፈራህም ነገር ግን ከንአን ውስጥ ልትገባ እንደሆነ ያወቀ ሰአት የዛኔ ጦሮቹን አንስቶ ከፊትህ ይቆማል። ሰይጣን መንገደኛ ሰዎችን አይፈራም። ነገር ግን ለፍፃሜያቸው የቆረጡ እና በራሳቸውም ጭምር ላይ ለመወሰን ማይከብዳቸውን ጨካኝ እና የቆረጡ ሰዎችን ያየ ሰአት መንገድ ይለቅላቸዋል። ምክንያቱም እነሱን ከማቆም ፀሀይን ከከዋከብት ጋር ማውጣት : ጨረቃን ደሞ በቀን እንድትወጣ ማድረግ ይቀላል። እነሱን ከማቆም ደመናን እግርስር : የምድርን አፈር ላይ መስቀል ይቀላል። ደግሜ እላለሁ እነዚህን ሰዎች ከማቆም የወንዝን ጅረት ከታች ወደላይ እንዲፈስ ማድረግ : ተፈጥሮን መቀያየር ይቀላል።
#ላየሀው_ነገር_ጨካኝ_ሁን
#እምቢ_በል. @proabraham
​​​​.
አንብበው አሰላስለው ተናገረው

"፤ ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው።"
(መጽሐፈ ምሳሌ 3: 3)

" Gaarummaa fi amanamummaan sittii hin fagaatin! Morma keetti isaan hidhadhu, gabatee garaa keettis isaan caaffadhu!"
(Macaafa Fakkeenyaa 3: 3)

" ሕያውነትን ሓቅን ካባኻ ኣይፈለያ፡ ኣብ ክሳድካ እሰረን፡ ኣብ ጽላት ልብኻውን ጽሐፈን።"
(መጽሓፍ ምሳሌ 3: 3)