Prince Faysul
6.87K subscribers
5.74K photos
31 videos
33 links
:¨·.·¨: ❀
 `·. @Princ_Faysul
Download Telegram
እዚህ ጋር ሁሉም ነገር ያልቃል...
ዝና ..ገንዘብ..ስልጣን..ስራ ብቻ ይቀራል
Prince Faysul
Photo
part ......2


ከትንሽ ደይቃ ብኋላ ብስራቱ መጣ
ጤንነቴ ተስተካክሎ በጥሩ ሁኔታ ሴት ልጅ ወለድኩኝ ። ነርሷም ሂሳቦን እንድንከፍላት መጠበቅ ጀመረች...

ባልተቤቴም በህይወት አስካለሁ ድረስ የልፍትሽን ዋጋ ለኔ ከአንገቴ ስር ያለ እዳ ነው አሁን ገንዘብ የለኝም አሟልቼ እከፍላለሁ አላት ... ነርሷም አዝናልን ችግር የለውም ብላ ሄደች።

በዚህ መሀል የመጨረሻ ጊዜ የት ነበር የሄድከው ስል ጠየቁት ባልተቤቴም ...? ቤተሰቦቼ ጋር ነበር የሄኩት ... እና አይኖችህ በእንባ ተሞልቶ ለምን ተመለስክ ?

ወደ ፀሀፊው ቢሮ ሄኩኝና ያለውን ነገር አስረድቼ ትንሽ ብር ከደመወዜ ላይ እንዲያበድሩኝ ጠየኩ.....?

ስለ ሰራተኞች ብድር ጉዳይ እኔን አይደለም። ከገንዘብ ጋር ግንኙነት የለኝም አለኝ ፀሀፊው....  ብር ቸግሮህ ከሆነ ወደ ገንዘብ ሹም ሂድ  ወደ ገንዘብ ሹም ሂጄ ያለውን ነገር አስረዳሁት እሱም ስራ አስኬጅ ሳይፈቅድ ምንም ማድረግ እንደማይችል ነገረኝ።

ስራ አስኬጁን እፈልገው ጀመር በሩቅ ተመለከትኩት ወደ አጠገቡ ስደርስ በመኪና ሄደ በጣም እየጮህኩ ተጣራሁ ሊሰማኝ ግን አልቻለም!

ወደ ቢሮው ተመልሼ በጣም እያለቀስኩ ለመንኳቸው ሊተባበረኝ ፍቃደኛ የሆነ ሰው አጣሁ ። ልቤ ተሰብሮ አዝኜ ወደ ቤት ከእንባወቼ ጋር ተመለስኩ ...

አብሽር ባሌ ምጤም አላህ ገር አድርጎት በጤና ወልጃለሁ ሁሉም አለፈ አልኩት


በሁለተኛው ቀን ባልተቤቴ ወደ ቤተሰቦቼ ጋር ሂጄ አልሰራም ብሎ ሌላ ስራ ለመፈለግ ከቤት ወጣ...

ከሰዓታት ብኋላ ከሁሉም አይነት አትክልት ለልጃችን የሚሆን ብዙ ልብሶችን ለልጆች የሚያስፈልጉ የተለያዩ ነገራቶችን ይዞ ባልተቤቴ መጣ ።

በጣም ደስተኛ ሁኖ ነበር ለተመለከተው ለይለተል ቀድር የወረደበት ይመስል ነበር ደስታውን ስመለከት የደስታ አለቀስኩ ይህንን ደስታ ተመልክቼ ስለማላቅ ከዚህ በፊት...

ምግቦቹን ከተመገብን ብኋላ ቀንህ እንዴት ነበር ስራ አገኘህ እንዴ..? ከየት እንዳመጣው ጠየኩት ...

ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ታሪኩን ልንገርሽ ብሎ ያጋጠመውን ይነግረኝ ጀመር......!

በጣም ስራ እየፈለኩ ላገኝ አልቻልኩም ነበር ተስፍ ቆርጫ  ወደ አትክልት ሰፍራ ሄድኩኝ ...!

እዛም በፊት ላይ የማቀው አንድ ጓደኛየን አገኘሁ ። በአትክልት ስራ ላይ የተሰማራ ነበር

ሰላም ተባብለን ያለሁበትን ሁኔታ እያለቀስኩ ነገርኩት ። ስራም እንደተውኩና ቤተሰቦቼ ያደረጉኝን አስረዳሁት... በጣም ቸግሮኝ አልተባበርም እንዳሉኝ ነገርኩት ።

በጣም ተቆጣ ምን አይነት ልብ ነው ያላቸው
እኔ ጋር መተህ በነበር በገንዘብ ሳይሆን በነፍሴ ፊዳ መስዋእትነት እከፍልልህ ነበር ።

ወረቀትና እስክርቢቶ ያዝ ብሎኝ ማፃፍ ጀመረ
ከዛሬ ጀምሮ ስራ ትጀምራለህ እዚህ አለኝ

ስራውም እንዳለቀ የሚያስፈልጉህን ከሁሉም አይነት አትክልት ለሰራተኞቹ እንዲያዘጋጁልኝ ነገራቸው ።

እንደጨረሱም መኪናው ውስጥ አስገባኝና
ወደ ሱቅ ሄድን የተለያዩ ልብሶችና ለህፆናት የሚያስፈልጉ ነገራቶችን ገዝቶ ይህ ለልጅህ ስጧታየ ነው ብሎ ሰጠኝ።

ወደ ቤት አደረሰኝና በኪሴ ብዙ ብር አስገባልኝ
ነገ ጧት በጊዜ እጠብቅሀለሁ ዛሬ ጥሩ ሰርተሀል ጥሩ ጅማሮ ነበር አለኝ።


በሁለተኛው ቀን ወደ ስራ ሂዶ ብዙ መልካም ነገራቶችን ይዞ ተመለሰ ። ምሳ ከበላን ብኋላ ይህንን ብር ለሀኪሞ እንሰጣታለን አለኝ ።

ገንዘብ ግን ከትክክለኛው ክፍያ ይበልጥ ነበር
ወደ ነርሷ ሂጄ ብሩን ስሰጣት አልቀበልም አለች ። ይህ ያንቺ ሀቅ ነው መውሰድ አለብሽ እያልኩ ለመንኳት ...

ነርሷም እያለቀሰች ወላሂ ከእናንተ ቤት በዛች ለሊት ስወጣ  ለአላህ የልፍቴን ዋጋ ላንተ መልካምነት ስል ትቻለሁ መልካምነትህን አሳይኝ አልኩት... ለአላህ ስል የዛኑ ጊዜ አውፍ አልኩ ።

ከዛም  ወደ ቤት ስመለስ  የማላቀው ስልክ ተደወለ ...

ከተማ ያለ ትልቅ ሆስፒታል ነበር የደወሉት ከዚህ በፊት ማመልከቻ አስገብቼ ነበር ስራ ለመግባት
መረጃወቼን አስቀምጫ ነበር እንደውልልሻለን ብለውኝ ነበር ... ረጂም ጊዜ ስለነበር ተስፍ ቆርጫ በትንሽ ክሊንክ ስራ ጀምሬለሁ

ከእናንተ ጋር ስመለስ ጥያቄየን ተቀብለው ስራ መጀመር እንደምችል ነግረውኝ አሁን እዛ ባለ ሆስፒታል ውስጥ አዋላጅ ሀኪም ሁኛለሁ አለች ።

እኔም የአላህ መልካምነት አስገረመኝ ለአላህ ስትል ተወች አላህ በመልካምነቱ አስደሰታት

አላህ ግን ምን ያህል ከሪም ነው....

እኔም ወደ ቤት ተመልሼ ለባሌ ሁኔታውን አስረዳሁት ። ባሌ ግን በሌላ ደስታ ነበር የተቀበለኝ እቃወቻችን ሰብስቢና ወደ ከተማ ለመኖር  እንገባለን አለኝ ።

ለምን ስል ጠየኩ..?

ጓደኛየ ወደ ከተማ ከቤተሰብህ ጋር ግባና እኔ አትክልቶችን አመጣልሀለሁ አንተ ለነጋዴወች ታከፍፉላለህ ስላለኝ ከተማ መግባት አለብን አለ።

በሚቀጥለው ቀን እቃችንን ይዘን ከተማ ገብተን የተሻለ ቤት ተከራየን ።

ከዚህ ጀምሮ ህይወት ለኛ መሳቅ ጀመረች በእየቀኑ ህይወታችን እየተሻሻለ መጣ ከሶስት አመታት ብኋላ ባልተቤቴ ሀብታም ሆነ የራሱ የንግድ ሱቅ ኑሮታል አልሀምዱሊላህ

በአላህ ፍቃድና በእኛ ትግስት ህይወታችን ተሻሻለ!!

ታሪኩ እንዴት ነበር......?
ጁመዓ ነው ፈገግ በሉ...😂

አንዷ ናት አሉ...

ዩሱፍና አብደረህማን የሚባሉ ሁለት ልጆች አሉኝ ። ተኮርፈው  አብደረህማንን ዩሱፍን ሲያሰግደው

ሁሌም ይህንን አያ መቅራት ያበዛል

اقتلوا يوسف أو أطرحوه أرضا" 😁
ዮሱፍን ግደሉት ወይም መሬት ላይ ጣሉት”
የሆነ ነገር ከመጀመርህ በፊት
እንዴት መጨረስ እንዳለብህ እሰብ!
ይህንን ሰፊ አለም ተመለከታችሁት
በውጭ ባለው ነገር በውስጥ ባለው ነገር
ሁሉንም የያዘውን ነገር  አንዲትም ጉንዳን አታገኙም አላህ የሷን ሲሳይ የሰጣት ቢሆን እንጂ .....
አትፍራ  አላህ እኮ አንተንም ጠባቂ ነው
ሁሉም ነገር ጊዜያዊ ነው"
ችግሮቻችንም ጭምር።
=
#የማለዳ_መልዕክቶች
የወደፊቱን ህይወት ለማሻሻል የሚሞክርን ሰው ያለፈውን ነገር አታንሳበት."
አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ሌሎች ስህተት እንደሠሩ እንዲያውቁ ለማድረግ ምርጡ መንገድ ነው። !
አንዲት ሴት ባሏ ይሞትባትና ሰደቃ መስጠት ትፈልጋለች...

ጁመዓ ማታ ምግብ ሰርታ በሰፈራቸው ላሉ የአንድ ሚስኪን ቤት እንዲያደርስ የቲሙ ልጇን ላከቺው። ልጇም እናቱ የሰራቺውን ይዞ ሄደ መንገድ ላይ ግን በጣም ራበው ራሀቡን ተቋቁሞ አድርሶ ተመልሶ ቤት ገብቶ ተኛ እየራበው ።

በሁለተኛው ሳምንት ጁመዓ ማታ እናቱ ለባሏ ሰደቃ መሰደቅ ፈልጋ ምግብ ሰርታ ለልጇ ላከች አሁንም በተመሳሳይ እየራበው ልጇ አድርሶ ተመልሶ ራቱን ሳይበላ ተኛ

በሶስተኛው ጁመዓ በተመሳሳይ እናቱ ሰደቃ መስጠት ፈልጋ ለልጇ ምግብ ሰርታ ለሚስኪኖች ላከች ልጇም ምግብን ይዞ ሲሄድ ረሀቡን አልቻለም ነበርና ለሚስኪኖቹ የተዘጋጀውን ምግብ በልቶ ወደ ቤት ተመልሶ ገባና ተኛ ።

የዛች ምሽት ለሊት እናቱ በህልሞ ባሏ ይመጣና የምሰጪው ሰደቃ ዛሬ ገና ደረሰኝ አላት ። እናቱ ስትነቃ ልጆን ጠየቀቺው የማታውን ሰደቃ የት ነው ያደረስከው ..? ልጁም ሁለቱ ሳምንታትን ራሀብን ተቆቁሜ ሰደቃውን ላልሺኝ ሚስኪን አደረስኩ የማታው ግን ከአቅሜ በላይ ነበርና ሚስኪኑ ቤት ስደርስ በጣም ራበኝ መቋቋም አቃተኝና በላሁትና ወደ ቤት ተመልሼ ጠግቤ አደርኩ አላት...

እናትም የአባቱ ሰደቃ በቅድሚያ ለየቲሙ ልጁ እንደሚገባ አወቀች

አህባቢ ቤት የተራበ ሰው እያለ ውጭ ሂደን አንሰድቅ ሰደቃ የሚጀምረው ከቤት ነው..
Prince Faysul
Photo
አንድ ወንድም አጋጣሚውን እንዲህ ይተርክልናል ።

  የሆነ ጊዜ ወንድሜ አዲስ ቤት ሰራና ለመዘየር ሄኩኝ በአዲሱ ቤቱ ወንድሜም በጥሩ መስተንግዶ ተቀበለኝና ጥሩ ጊዜ አሳለፍኩ ወደ ሰዓቱ ስመለከት ለኢሻ ሶላት ግማሽ ሰዓት ይቀር ነበር ...!

ለወንድሜ ወደ መስጂድ መሄድ እንደምፈልግ ስነግረው ገና ነው አዛን አልተባለም አለ...?

ሶላት እስኪደርስ ድረስ ቁርዓን እየቀራሁ እጠብቃለሁ ልሂድ ብየ ሄኩኝ ...

ወደ መስጂድ ስደርስ  መስጂዱ ባዶ ሁኖ አገኘሁት ቁርዓን አንስቼ መቅራት ጀመርኩ..!

ከትንሽ ደቂቃ ብኋላ አንድ ልጅ ወደ መስጅድ በመግባት ሰላምታ አቀረበልኝና ሶላት ቆመ ሁለት ረከዓ ሰገደ አሰላመተ በድጋሜ ሶላት ቆመ ሱጁድ ላይ በጣም ይቆይ ነበር ....

በሶላቱ በጣም ተገረምኩ በዚህ እድሜው በዚህ ልክ ኹሹእ ሲያደርግ አላህ ጋር ያለው ግንኙነት አስቀናኝ ። ሱጅድ ላይ ሲቆይ ምን እያለ ነው ብየ ጠጋ ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ ...

ወደ ልጁ ተጠግቼ ሳዳምጠው ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ማልቀስ ጀመርኩ ጌታውን እንዲህ እያለ ሲጣራ ነበር...

ያረቢ አባቴ የሆነ ነገር ሲቸግረን ወደዚህ እንድመጣ አደራ ብሎኛል..

እኔም ኢሄው እጅህ ላይ የተናነሰ ደካማ ራሀብተኛ  የተቸገረ ሁኜ ቀርቤለሁ....

ያረቢ ትናንት ጀምሮ ምንም እንዳልበላን አንተም ታቃለህ .. ያረቢ ትናንሽ ወንድሞቼና እህቶቼ ረሀብን መቋቋም አይችሉም .. እኔና እናቴ ግን መቋቋም እንችላለን ...

ነገር ግን ታናናሾቼ በረሀብ ምክንያት ሲያለቅሱ ሳይ ወደ አላህ ሂጄ  የሚበላ እንዲሰጠን እጠይቀዋለሁ አልኮቸው!

አባቴ እንዳስተማረኝ  ያረቢ እባክህን እናቴና ታናናሾቼ ዘንድ አታሳዝነኝ እባክህን

አንተ እኮ አሸናፊ ሀብታም አዛኝ በጣም ሩህሩህ መልካም ነገሮች በሙሉ በእጅህ ነው አንተም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ ያረቢ

የዱዓ አደራረጉ በጅጉ ልብ ይነካል እድሜው ገና አስር ቤት  ቢሆንም ሁኔታው ልብ ይነካል አላህን ደጋግሞ ይለምናል ሱጁድ ላይ እያለ  ታናናሾቹን አላህ ምግብ እንዲሰጣቸው እያለቀሰ ይማፀናል ።

ሰወች መተው ኢሻን እስክንሰግድ ድረስ ተከታተልኩት ።  ኢሻን ሰግደን ስንጨርስ ወንድሜን አገኘሁትና  ይህ ልጅ ማነው ታቀዋለህ ወይ ስል ጠየኩት...?


ወንድሜም አዎ አቀዋለሁ የመስጅዳችን ኢማም ልጅ ነው አባቱ ሙቷል አላህ ይዘንለት አለኝ ።

የት እንደሚኖር ልጠቁመኝ ትችላለህ አልኩት ወንድሜም ታሪኩ ምንድን ነው አለኝ..?

ምንም የለም ዝም ብለህ ቤቱን  አሳየኝ  ....!

ከመስጅድ ወተን የልጁን ቤት አሳየኝ ወደ ሱቅ ሂጄ በርካታ የሚበላ ምግብና በርከት ያለ ገንዘብ በውስጡ አስቀምጫ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ቆሮቁሬ ቶሎ ተደበኩኝ!

ልጁም ወደ ውጭ ወጣና ቀይና ግራውን ሲመለከት ማንም የለም ወደ ታች ሲመለከት ምግቡን አየው የተቆጠሩትን ምግቦች እየነካካ እንዲህ ሲል ጮሀ እናቴ ሆይ በርካታ ምግብ አገኘሁ አላህ አመጣልን ....

በጣም ደስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ለአላህ ሱጁድ አደረገ .....
Prince Faysul
Photo
በጀናዛ በማጠብ ላይ የተሰማራ አንድ ወንድም የሆነን አጋጣሚ እንዲህ ይተርክልናል..

ከእለታት አንድ ቀን አርባወቹ ያልደረሰ ወጣት ሙቶ ከጓደኞቹና ከቤተሰብ ጋር ታጥቦ እንዲሰገድበት ወደ መስጅድ መጣ..

ከመጡት ሰወቹ መሀል አንድ ወጣት በልዩ ሁኔታ ትኩረት ሳበኝ ወጣቱ የሞቹ አይነት እድሜ ውስጥ ያለ ወጣት ነው  ። በጣም ያለቅሳል በየመሀሉ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ቃልን ይደጋግማል ራሱን ለመቆጣጠር ድምፁን ዝቅ ለማድረግ ቢሞክረም አልቻለም በጣም እያለቀሰ ነበር።

  ከኔ ጋር ወደ ማጠቢያ ክፍል ገባ ወጣቱ
በየመሀሉ  በጣም ሲያለቅስ አብሽር ታገስ ትግስት ማድረግ እንዳለበት እነግረዋለሁ ።

   ምላሱ ይህን ቃል ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ደጋግሞ ይል ነበር ። ይህንን ቃል ስሰማ እኔ እርጋታ ይሰማኛል ለቅሶው በጣም ስራውን እንዳልሰራ እያደረገኝ ስለነበር ።

     ለወጣቱም ወንድምህን አላህ ይማረው ካንተ በላይ አላህ ለሱ አዛኝ ነው ። ትግስት ማድረግ አለብህ አልኩት.... ወጣቱም ወደኔ እየተመለከተ ወንድሜ አይደለም አለኝ !

በጣም ተገረምኩ ይህ ሁሉ ለቅሶ ይህ ሁሉ እዝነት እንዴት አልኩ በውስጤ ...

  ወጣቱም ከወንድሜ በላይ የሆነ ውድ የሆነ ጓደኛየ ነው ።  የልጅነት ጓደኛየ..የትምህርት ቤት ጓደኛየ ክፍል ውስጥ አብረን ተቀምጠን በረፍት ሰዓትም አብረን አሳልፈን ...በሰፈር ውስጥ አብረን ተጫውተን...አብረን አድገን ግንኙነታችንም አብሮ አድጎ አብረን ዩኒቨርስቲ ገብተን አብረን ተመርቀን አንድ አይነት ስራ ይዘን እህትማማቾች አግብተን ወንድና ሴት ወልጄ እሱም በተመሳሳይ ወንድና ሴት ወልዶ በአንድ አከባቢ ቤት ተከራይተን እየኖርን ደስታችንንም ሀዘናችንንም አብረን እያሳለፍን
አብረን ደስታ ሲኖር ደስታው እየጨመረ ስንገናኝ ሀዘኑ እየቀነሰ  በሁሉም ነገር አብረን ነበር የምንኖረው ...

ታሪካቸውን ሲነግረኝ አልቻልኩም በጣም አለቀስኩ...

ያሸይኽ ምድር ላይ እንደኛ አይነት ግን አለ...

ይች ንግግር ልቤን ነካው..
ሩቅ ያለውን ወንድሜን አስታወስኩና የለም አልኩት....

ሱብሐነላህ የሚለውን ቃል እየደጋገምኩ አጥቤው ጨረስኩ ወጣቱም የጓደኛውን ግንባር ሳመና በጣም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ..

  ሰወች ይዘውት ወጡ ሶላቱል ጀናዛ እንድንሰግድበት .... ሰግደን እንደ ጨረስን ጀናዛውን ተሸክመን ወደ ቀብር ቦታ ሄድን ...
ጥግ ላይ ቁሞ ወዳጅ ዘመድ እያፅናናው ቀብረን ጨረስን ሰወች ሲሄዱ ለጓደኛው ዱዓ አርጎ ተመለስን ....

     በሚቀጥለው ቀን አሱር አከባቢ መስጂድ ትናንት የተመለከትኮቸው ሰወች አንድ ጀናዛ ይዘው መጡ.... ትናንት የተመለከትኩትን ወጣት መልክ ያለው አንድ አባት እያለቀሱ ተመለከትኩ ያ ሸይኽ ትናንት እኮ ጓደኛው ጋር ነበር ጓደኛውን ሸኝቶ ዛሬ ተከትሎ ሄደ ትናንት ለጓደኛው ከፈንና መቀስ ሲያቃብል ጓደኛውን እየገለባበጠ ሲነካ ነበር ትናንት በጓደኛው ሞት ልብ ተነክቶ ሲያለቅስ ነበር እያለ አባቱ ስቅስቅ ብሎ አለቀ..

   የተሸፈነበትን ስገልጠው ትናንት በጓደኛው ሞት እያለቀሰ የነበረው ወጣት እንደሆነ አወኩ
  በጣም ደንግጫ እንዴት ሞተ አልኮቸው
ሚስቱ የሚበላ ብታቀርብለት አልበላ አለው  መተኛት ፈልጎ ተኛ አሱር ላይ ሚስቱ ስቀሰቅሰው ሙቶ ተገኘ ...

   በጓደኛው ሞት ድንጋጤ አልቻለም ነበር
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን የሚለውን ደጋግሞ ይል ነበር....

    ጀናዛውን አጥበን ሰግደንበት ወደ ቀብር ቦታ ስንሄድ ሌላ አስገራሚ ነገር አገኘን ከትናንት ሞች ብኋላ ሌላ የሞተ ሰው አልነበረም ይህ ብዙ ጊዜ አያጋጥምም ነበር ከጓደኛው ቀብር ጎን ቀብረነው ተመለስን
እውነትን በቀልድ መሀል ልሰማ ትችላለህ
በደንብ አርገህ አዳምጥ!
አንዳንድ ሰወች አሉ ሲመጡ ዝም እንላለን አክብረናቸው  አይደለም ወሬን ስለሚያመላልሱ እንጂ!
አንበሳ ከታቹ የሚቀመጥበት ዛፍ ላይ ጦጣወች አይንጠላጠሉም
የወንዶች ቤትም እንደዚሁ ነው !
"قُل للتي بلغَ النصاب جمالها
إن الزكاة عن الجمال تَبسُمِ
أدي إليّ زكاة حسنك و اعلمي
إن الأداء إلى سواي مُحرّم.
የሆነ ጊዜ አንድ ሰው ህይወት ያደክመውና ችግሮች በዝተውበት ወደ አንድ ጥበበኛ ሰው ዘንድ ይሄዳል ላለበት ችግር መፍትሄ ፈልጎ  ....

   ጥበባኛው ዘንድ ሂዶ ያለውን ነገር አስረዳው
ምንም መፍትሄ እንዳጣና አቅጣጫ አሳይኝ ሲል ጠየቀው ...  ጥበበኛው ሁለት ጥያቀውን እጠይቅሀለሁ መልስልኝ አለው ...?

    ጥበበኛውም ወደዚህ ዱንያ ስትመጣ ይህንን ሁሉ ችግር ይዘህ ነው የመጣሀው...?

    ሰውየውም አይደለም ሲል መለሰ!

ጥበበኛውም ይችን ዱንያ ትተህ ስትሄድ ይህንን ሁሉ ችግር ይዘህ ነው ወይ የምትሄደው ...?

    ሰውየውም ይዤ አልሄድም አለ!

ጥበበኛውም ይዘሀው ያልመጣሀው ነገር ይዘሀው የማትሄደው ነገር በዚህ ደረጃ ሊያሳስብህ አይገባም ትግስተኛ ሁን በዱንያ ነገራቶች ላይ መሬት ላይ ከምትመለከተው በላይ ሰማይ ላይ የምትመለከትበት ጊዜ ረጂም ይሁን የፈለከው ነገር እንዲሳካ ከፈለክ!

   ሰውየውም ደስ ብሎት ተስፈኛ ሁኖ ልብ ተጠግቦ ሄደ።
ልጃቸው ያገባ ጊዜ አባትና ሙሉ ቤተሰብ በአዲሱ ቤቱ ሊዘይሩት ይሄዳሉ....

አባትም ልጁ ቤት እንደደረሰ ወረቀት ቀለምና ማጥፊያ እንዲያመጣው አዘዘ ....ልጁም ለሰርጌ ሙሉ እቃ አሞልቻለሁ ያልከኝ ግን የለም ከሱቅ ገዝቼ ልምጣ ብሎ ለመግዛት ሄደ ....

ልጁም የተባለውን ገዝቶ መጣና  አባቱ ጋር አጠገብ ቁጭ አለ።
አባቱም ልጁን ፆፍ አለው ልጁም ምን ልፃፍ አለ? የፈለከውን ፆፉ  ...ልጁም ዝም ብሎ ፃፈ አባትም አጥፍው ....  ልጁም የፃፈውን አጠፍው!

    አባት ድጋሜ ፆፍ አለው ልጁም ምን ሲል ጠየቀ አባትም የፈለከውን አለው! ልጁም የፈለገውን ፆፈ... አባትም አጥፍ አለው ልጁ በመገረም አጠፍው ...! አባት ለሶስተኛ ጊዜ ፆፍ አለው.. ልጁም ምን አለ..? አባትም ደስ ያለህን ሲል መለሰለት ልጁም ፃፈ የፈለገውን ...አባትም አጥፍው አለው አጠፍው ...

አባትም የልጁን ትከሻ ያዝ አርጎ ልጄ ትዳር ማጥፊያ ያስፈልገዋል ። አንተ ከሚስትህ አንዳንድ የማትወደውን ሁኔታወች ሊኖሩ ይችላሉ ..... ሚስትህም ካንተ አንዳንድ ደስ የማይላት ሁኔታወች ሊኖሩ ስለ ሚችሉ ትዳራቹህ ላይ ማጥፊያ ከሌለ የትዳሩ ደብተር ጨለማ ሁኖ አስከፊ ሁኔታ ላይ ይደርሳል ።

የትዳር ግንኙነት ልጄ በውዴታ ..በመከባበር ..በይቅርታ  በሁለቱም በኩል በሚኖር መደማመጥ አንዳንድ ትልቅም ትንሽም ስህተቶች ሲፈጠሩ በመተራረም ድጋሜ እንዳይፈጠሩ በጥሩ መልኩ በመወቃቀስ ነው ትልቅ ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችለው  ።

   ይህ ህግ ነው ጥሩ  ትዳር የሚገነባበት
መንገድ ።  ሚስትህን በደንብ ተንከባከባት ለሷ መከታ ሁናት ካንተ ብዙ ነገር ትፈልጋለች ።
አንዳንዴ ሴት ሴትነቶን ለማይገባው ለማገዝ ስትል መስዋእትነት ትከፍለዋለች
እሱ ደሞ ሴትነቶን በሌላ ሴት ውስጥ ይፈልጋል ...