በዐማራ ክልል የሚገኙ 10 ዩኒቨርስቲዎች አሁን ላይ ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ አስታወቁ❗❗
በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን እንዳሉት የክልሉ ጸጥታ እስኪሻሻል ድረስ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ፣ የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱ ገልጸዋል፡፡
ተለዋዋጭነት ባለው የክልሉ ጸጥታ ምክንያት መንገድ እየተዘጋ ነው። ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ግጭት ቢነሣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ሓላፊነት መውሰድ አይችሉም።ከምግብ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ያቀርቡ የነበሩ አካላት፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደተቸገሩ ነግረውናል።በዚህ መነሻ ፎረሙ ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል።የፎረሙን ውሳኔ ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች እንደሚጋሩት ጠቅሶ ቪኦኤ ዘግቧል።

👍2🔥1
ትግራይ❗❗
በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና 69.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል።
ከተፈተኑ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት 657 መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
ከትግራይ ክልል ውጪ ያሉ ተፈታኞች 3% ብቻ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል።
ከትግራይ ክልል 657 የ2015 12ተኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ሆኗል‼

👍6😁1
ሰው ሰራሽ ፀሀይ❗️❗️
ቻይና የሰራችውን ሰው ሰራሽ ጸሀይ ወደ ትግበራ ልታስገባ መሆኗን ገለጸች❗️❗️
ከፈረንጆቹ 2018 ዓመት ጀምሮ ሰው ሰራሽ ጸሀይ ለመስራት ሙከራ ላይ የነበሩት የቻይና ተመራማሪዎች የመጨረሻ ሙከራቸውን እንዳካሄዱ ሽንዋ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ይህች ሰው ሰራሽ ጸሀይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙቀት ማመንጨት መቻሏ የተረጋገጠ ሲሆን ይህብሙቀትም ከካርበን በካይ ጋዝ ነጻ እንደሆነም ተገልጿል።
ቻይና ሰታሿ ጸሀይም በደቡብ ምዕራብ ብሔራዊ የኑክሌር ተቋም ተመራማሪዎች ተሰርታለች የተባለ ሲሆን ብርሀን እና ሙቀትን ማመንጨት ጀምራለች ተብሏል።

👍2
🌼Buee prep academy🌼
Photo
🎂🎂 2nd years of Anniversary to channel 🎉🎈🎉🥳
📌410+ members 🙏 another years with u all we admins & owner

🎉4
🌼Buee prep academy🌼
በዐማራ ክልል የሚገኙ 10 ዩኒቨርስቲዎች አሁን ላይ ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ አስታወቁ❗❗ በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን እንዳሉት የክልሉ ጸጥታ እስኪሻሻል ድረስ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ፣ የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱ ገልጸዋል፡፡ ተለዋዋጭነት ባለው የክልሉ ጸጥታ ምክንያት መንገድ እየተዘጋ ነው። ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ግጭት ቢነሣ…
#Kebridehriuniversity
በ2016 ዓ.ም የተብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ አንደኛ አመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ፡፡
በ 2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ: : በሪሚዳል (Remedial Program) ትምህርታችሁ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ዉጤት ያመጣችሁ እና በ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አንደኛ ሴሚስተርን ጀምራችሁ በጤና እና በቤተሰብ እንዲሁም በተያያዥ ችግሮች ምክንያት ዊዝድረዋል ((withdrawal) በመሙላት ያቋረጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ህዳር 13 እና 14፣ 2016 ዓ.ም (November 23 and 24፧2023) መሆኑን በአክብሮት እየገለፅን ፤በተጠቀሱት ቀናት በዩኒቨርሲቲዉ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታዉቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
☞ ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲዉ የማያስተናግድ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
በዩኒቨርሲቲዉ የሪሚዳል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ የሞላችሁትን የወጪ መጋራት እና ክሊራንስ ፎርም ቀሪ ይዛችሁ እንድትመጡ ልናስታዉሳችሁ
እንወዳለን፡፡
በ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አንደኛ ሴሚስተር ጀምራችሁ በጤና እና በቤተሰብ እንዲሁም በተያያዥ ችግሮች ምክንያት ዊዝድረዋል ((withdrawal) በመሙላት ያቋረጣችሁ ተማሪዎች የሞላችሁትን የዊዝድረዋል ቀሪ ፎርም ይዛችሁ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን።

👍1
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር 6 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሬሜዲያል ተማሪዎችን እንደማያስተናግዱ አሳወቀ‼️
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲያስተካክሉ ተብሏል።
ሚኒስቴሩ፦
1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ
6. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም የማያስተናግዱ መሆኑን አሳውቋል።
remidial ሊጠፋ የተቃረበ ሀብታችን😏😲

👍3🔥2
ከወደ ሶማሌ ፈገግ የሚያስብል ዜና😁
"የኢትዮጵያን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ"
"የኢትዮጵያውን ጠ/ሚ አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" ያሉት በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ኢሳቅ አህመድ ሀሰን በሶማሊያ ሶሻል ሚዲያዎች የእለቱ ሳቅ የሚጭር መነጋገሪያ ሆኗል ሲል ሶማሊ ፈጣን መረጃ ዘገባ ያሳያል።
ሰውዬው በሶሻል ሚዲያ ብቅ ብለው በአፍ ሶማሊ ቋንቋ "አብይን ትመስላለህ እያሉ ህይወቴን አደጋ ውስጥ የከተቱብኝ ሰዎች አሉ። እኔ ሳልሆን አብይ ነው እኔን የሚመሰለው። በዚህ ምክንያት ለህይወቴ ሰለሰጋሁ ያለጠባቂ መንቀሳቀስ አቁሜለሁ። በዛ ላይ የአባቱ እና አባቴ ስም አንድ ነው። ወደ ኢትዮጵያ የሄድኩት በመለስ ዘመን ነው አሁን መሄድ ብፈልግም ለደህንነቴ ስጋት ስላለብኝ ጠባቂ ያስፈልገኛል።" ብለዋል።
በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ይህን መልእክት ያስተላለፉት ለቀልድ ይሁን የምራቸውን ግን የታወቀ ነገር የለም ሲል ከሶማሌ ክልል የወጣው መረጃ ያመላክታል።

👍3
breaking news‼️ 1/100 ያመጣው ተማሪ አስተማሪውን በመደብደቡ የተነሳ ነስምንት ወር እስራት ተፈረደበት።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር የዕውቀት መምህሩን የመምታት ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ8 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የቡኢ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታውቋል ።
ተከሳሽ ተማሪ ሳሙኤል ሰምረ ትምህርቱን ችላ በማለት ያመጣው ውጤት ዝቅተኛ በመሆኑ ሃምሌ 12 / 2015 ዓ/ም የማስታወቂያ ቦርድ ላይ ውጤት እየለጠፈ የነበረው መምህር ሰለሞን ገ/ወልድን ከኃላ በኩል ቀኝ እጁን እና የጆሮ ግንድን ይመታል ፣ በወቅቱ በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ የነበሩ መምህራኖች ገላግለው ጉዳዩን ለቡኢ ከተማ ፓሊስ ጽ/ቤት አቤቱታ አሰምተዋል ።
አቤቱታውን ቀርቦ ሲያጣራ ቆይቶ ጥቅምት 23 /2016 ዓ/ም ወደ ከተማው ፍትህ ጽ/ቤት ልኳል ፣ ጉዳዩ የተመራለት ዓቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ ተገቢውን የወንጀል ህግ ቁጥር 441(1)(ለ) በመጥቀስ ተከሳሽ የዕውቀት አባቱ ላይ የሃይል ድርጊት ተፈጽሟል ሲል የወንጀል ክስ መስርቶ ለፍርድ ቤት አቅርቧል ።
ተከሳሽ በችሎት ቀርቦ የወንጀል ድርጊቱን መፈጸሙን ያመነ ሲሆን ውጤት ሲሰጠኝ 1/100 ተሰቶኝ ተናድጄ መትቼዋለሁ በማለት የእምነት ቃሉን ሰጥቷል ። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን የቀረበውን የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ከመረመረ በኋላ ተከሳሹን የሚያርም እና መላው ማህበረሰብን ያስተምራል በሚል የተከሳሽ እጅ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ በ8ወር ቀላል እስራት ይቀጣ ሲል ህዳር 10 / 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል የቡኢ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

የሪሚዲያል ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል‼️
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ምደባችሁን ለማየት የቀረቡ አማራጮች፦
በድረ-ገፅ፦
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም ቦት፦
https://t.me/moestudentbot
የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። የተመደባችሁበት የትምህርት ተቋማት ጥሪ በመጠበቅ ትምህርታችሁ መከታተል ትችላላችሁ ተብሏል።

Schaum's Programming with C++ -- 434.pdf
8.3 MB
engineering and technology ተማሪዎች ምርጥ c++ አጋዥ book
📌Only c++ language‼
📌Only c++ language‼
#የሥነ_ዜጋ እና #ሥነ_ምግባር ትምህርት ከ12ተኛ ክፍል #ፈተና እንዲወጣ ተደረገ‼️
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ተኛ ክፍል ፈተና ላይ ከሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር ትምህርትን ሲያስወጣ፣ በአንጻሩ የኢኮኖሚክስ ትምህርት በማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ውስጥ ተካተተ።
በዚህ ዓመት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት መተግበር የጀመረው ትምህርት ሚኒስቴር፤ የ12ተኛ ክፍል የፈተና ዝርዝር ላይ ለውጥ ማድረጉን ያሳወቀው ሐሙስ ጥር 9/2016 በጻፈው ደብዳቤ ነው። በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት ዓይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡
#የተፈጥሮ_ሣይንስ፦ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት
#የማኅበራዊ_ሣይንስ፦ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።
የ12ተኛ ክፍል ፈተና ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ የሚሰጠውን ትምህርት የሚያካትት ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ፈተና የሚወጣው ከ12ተኛ ክፍል ብቻ እንደሆነ ትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጠቅሷል።
ኩረጃን እና የፈተና ስርቆትን ለመከላከል በጥብቅ ቁጥጥር ውስጥ ከ2014 ዓ.ል. ጀምሮ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ መሰጠት የተጀመረው የ12ተኛ ክፍል ፈተና፤ ባለፉት ዓመታት እጅጉን ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች የሚያልፉበት ሆኗል።
የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ፈተና መቼ ሊሰጥ እንደታሰበ ጥያቄ የቀረበላቸው የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ፤ “አሁን ከክልሎች ጋር ምክክር እያደረግን ነው። በቅርቡ እናሳውቃለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#ሰበር
#ፋኖ
ፋኖ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎችን ማስጠንቀቂያ ሰቷል ። ባህር ዳር ዘንዘልማ ካምፓስ ግቢ ውስጥ ድረስ በመግባት ዩኒቨርሲቲውን የሚጠብቁ ፌደራል ፖሊሶችን ተኩስ ከፍቶ በማባረር በጊዜው አግኝቷቸው የነበሩ ተማሪዎችን ማንም እናንተን የሚጠብቅም ሆነ የሚከላከል ሀይል የለም ስለዚህ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው በማለት መልእክት እንዳስተላለፈ ከግቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። ይህንንም መሰረት በማድረግ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎችን መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝሞታል ።
የኢትዮጵያ ተማሪ ግን😭😭

#ሰበር #ፋኖ ፋኖ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎችን ማስጠንቀቂያ ሰቷል ። ባህር ዳር ዘንዘልማ ካምፓስ ግቢ ውስጥ ድረስ በመግባት ዩኒቨርሲቲውን የሚጠብቁ ፌደራል ፖሊሶችን ተኩስ ከፍቶ በማባረር በጊዜው አግኝቷቸው የነበሩ ተማሪዎችን ማንም እናንተን የሚጠብቅም ሆነ የሚከላከል ሀይል የለም ስለዚህ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው በማለት መልእክት እንዳስተላለፈ…
ባህርዳር ዩኒቨርስቲ
#አዲስ
ትናንት ማታ(ማክሰኞ) በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሳባታሚት ካምፓስ(ጤና ካምፓስ )በተማሪዎች መኖሪያ አካባቢ ቦንብ ተጥሎና ተኩስ ተከፍቶ ተማሪዎቹ ላይ የአካል ጉዳት ባይደርስም የዶርማቸዉ መስኮት ጉዳት ደርሶበታል!!
😢2
#የኢትዮጵያ_ባንኮች_ሀክ_ተደረጉ‼
በዚ ሁለት ቀናት ጀምሮ ኤትም ባንኮች ያለ ገደብ ብር ሲያወጡ እንደነበር በተለያዩ ዜና ምንጮች መዘገባቸው ይታወሳል፨ እስከ አሁን ከ 1.2 billion ብር በላይ በATM እና በኦንላይን ትራንስፈረ አጥታለች በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየ Atm ባንኮች እየሄዱ ከመጠን ያለፈ ገንዘብ ከ ለሊቱ 8 ሰአት ጀምሮ ሲያወጡ ነበር ቢሆንም ግን 10 ሰአት ለሊት ቢዘጋም ተማሪው ግን የ ዜርፎር ቀን የመሰለ ሰልፍ ተሰልፎ የሀገርን ገንዘብ መዝረፍ ምን ይሉታል ይባስ ብሎማ አንዳንድ ተማሪዎች ባወጡት ገንዘብ ስልክ ሲገዙበት እንደነበር አንዳንዱ ደሞ ገንዘቡን ይዘው ወደ ቤተሰብ ጋ ላጥ ቆይ ጊቢ ተማሪ መሆንክ ምኑ ላይ ነው ፋይዳው ላገርክ ካላሰብክ እስከ አሁን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ የአቢሲኒያ ባንክ፤የአዋሽ ባንክ ገንዘብ ተዘርፈዋል ጥያቄው ግን ማን ሀክ አደረገ ነው እስከ አሁን በ ምርምራ ላይ ነው ጉዳዩ ግን ቢሆንም የመጀመሪያው transaction የተፈጸመው በ ASTU(አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ) ነው በተጨማሪ በኢትዮጵያ በ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ኮምፒውተር ሳይንስ እውቀት የመጠቁ ተማሪዎች በASTU ስለመኖራቸው ጥርጠራውን ያገዝፈዋል፨
በአሁን ሰአት ASTU ከ ጊቢ መውጣትም መግባትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፨ የየጊቢውም ያወጣችሁ ተማሪዎች ገንዘቡን መልሱ እየተባለ ነው😂😂 ግን የተበላ እንዴት ይተፋል🙉
ግን ሌብነት ነውር ነው‼
By the way በዩኒቨርስቲ ብቻ አይደለም በሁሉም ከተማ ATM ያለበት ሁሉ 🤔🤑😳

🫡2👍1
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በአንድ አካል ሁለት ጭንቅላት ያላቸው ልጆች ተወለዱ
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንድ አካል ጭንቅላታቸው የተያያዙ መንታ ልጆች አንዲት እናት መገላገሏን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
በትላንትናው እለት ከምሽቱ 3፡30 ገደማ የወለደችው እናት እድሜዋ 40 ዓመት ሲሆን የአምስት ልጆች እናት መሆኗ ተገልፆል፡፡
ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱት ህፃናቶቹ እና እናትየው በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል
በሆስፒታሉ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ እንደሆነ እና ወደ አዲስ አበባ ሪፈር እንደሚደረጉ ነገር ግን ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ መሆኑን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቨ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
በሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ሁለት እና ሦስት መንትያ ልጆች ተወልደው ቢታወቅም ይህ ክስተት የመጀመሪያ ነው ሲሉ ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በደምቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ሁለት ጭንቅላት ያለላቸው ልጆች መወለዳቸው ይታወሳል፡፡
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

👉👉 Add እና DROP 👈👈
📌so,ጊቢ ላይ ሲባሉ ልትሰሙአቸው ከምትችሏቸው ነገሮች ዋነኞቹን ጀባ ልበላችሁ፨
📕ADD ማለት በጣልነው ኮርስ ምትክ ሌላ ተመጣጣኝ credit hour ያላትን ኮርስ ከኛ በላይ ወይም ከኛ በታች ከሚገኙት batch ተማሪዎች ጋር የምንማረው ኮርስ ነው።
📒DROP ማለት ደግሞ F በመምጣቱ ምክንያት ቀጣይ የምንወስደውን ኮርስ ወይም ፍላግ 🏴☠የሰቀልንበት ኮርስ እንዳንማር በሚያደርገን ጊዜ ያንን ኮርስ መጣል(drop)😭ማድረግ ይሆናል ማለት ነው።
ስለዚህ ታሪካዊ ዳራቸውን ካየን በኋላ🤔 እንዴት ይሄንን ማድረግ ይቻላል የሚለውን ለማየት እንሞክር😉
እሺ ምን ይደረጋል መሰላችሁ መጀመሪያ ምን ኮርስ ናቸው የመጣባችሁ የሚለውን መለየት እና ማወቅ ያስፈልጋል😎
ለምሳሌ በምህንድስና ትምህርት👷♂️ ደግሞ Mathematics👺 እና physics
☠ ወሳኝ ትምሮዎች ናቸው።
እናም ከሁለት አንዱ ወይም ሁለቱም ይሁን ፍላግ ብትሰቅሉ😥 በትንሹ እንኳን ከአመት በላይ ትዝጋላችሁ😵💫 ከመዛግም ደግሞ አልፎ እናንተ የምንተፈልጉት ዲፓርትመንት የብዙ ሰው ምርጫ ከሆነ😬 ለምሳሌ አብዛኛው ህዝብ ጊቢ የገባው ሜድስን 👨⚕️፤ፋርማሲ ፤agro-economics ፤management 👨💼፤ሶፍትዌር 👨💻 ለመማር ነው🤐 እናም ሌሎቹ ተማሪዎች እነዚህ ኮርሶቻቸው ካልተበላሹባቸው እነዚህ ዲፓርትመንት የመግባት እድላችሁ የጠበበ ነው የሚሆነው😧🤒 ስለዚህም ይሄንን አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እላለሁ። (ላልመረጣችሁ fresh/remedials)
እነ ሎጂክ👽 እነ ሳይኮ👻 ሌሎችም ትምሮዎች ፍላግ ብትሰቅሉ ሌሎች ተመጣጣኝ የሆኑ ኮርሶችን ከcredit hourቻው አንጻር አይታችሁ ADD እና DROP ተብሎ በተቀመጠላችሁ ቀናት መሰረት እየሄዳችሁ ማስተካከል ትችላላችሁ።
ስለዚህም መግባት የምትፈልጉትን ዲፓርትመንት ቀድማችሁ በማጣራት ፍላግ🏴☠ ከሰቀላችሁበት ኮርስ ጋር ያለውን ቁርኝነት ወይም መስተጋብር ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይኖርባችኋል።
🧰እናም ከእዚህም ጋር አያይዤ ላነሳ የምፈልገው ነገር🙄 ADD እና DROP አድርጋችሁ ከነበራችሁበት ግቢ ልትወጡ ያሰባችሁ ካላችሁ ልትገቡበት ያሰባችሁበት ግቢ መረጃ ከባሌም ከቦሌም ብላችሁ መሰብሰብ አለባችሁ ካልሆነ ግን በጣም እንደምትዝጉ ላይፋችሁ ራሱ ተስፋ መቁረጥ ሊሞላው ስለሚችል አስቡበት❗️
🔱 ይሄንን ስላችሁ ደግሞ አትፍሩ። ያው እኛም ፍሬሽ ተማሪ ሆነን ያየነው ነው😉 እናም F ያመጣንበት ኮርስ ሊኖር ይችላል ይሄ ብርቅ አይደለም በሕይወት ውስጥ መነሳት መውደቅ ያለ ነውና። ስለዚህም ይሄ አንዱ ግቢ እስካለን የሕይወታችን አካል እንደሆነ በመቁጠር ሳትበሳጩ😡 ይሄንን process በመጠቀም ሕይወታችሁን ማሻሻል ነጥባችሁንም ከፍ ማድረግ ትችላላችሁ💪☺️
📌 በመጨረሻም ይሄ ነገር የተናከርኩት በሙሉ ላይገባችሁም(ለ fieldu fresh የሆናችሁ😭😂) ይችላል ስለዚህ ግቢ ስንገባ ሲኒየር ተማሪ ጀለሶቻችሁ ካሉ🤷♂ ወይም ደግሞ የግቢ እናት እና አባት ተብለው የተሰጧችሁ እነሱም ካሉ💁♂ ከእነሱ በበለጠ መልኩ ለመረዳት ሞክሩ🚶♂። በዚህ ዙሪያ የተሻለ መረጃ ካገኘሁ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጽፌ ለማቅረብ እሞክራለሁ💆♂
Join @prep34
🗯The time is now not today🗯