🌼Buee prep academy🌼
216 subscribers
335 photos
11 videos
78 files
71 links
One of The Best Ethiopian Educational And Informational Channel in Telegram


Share this channel to your friends
❤️The time is now not today❤️

https://telegra.ph/BUEE-PREP-ACADEMY-11-01


መረጃና ጥያቄዎች በ comment ላይ ጻፉልን
Download Telegram
#Remedial

ለማካካሻ (ለሪሜዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች በአገር አቀፍ የሚዘጋጅ ፈተና በበይነመረብ (Online) እንደሚሆንና ፈተናውም ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ባሳወቀው መሠረት በዝግጅት ላይ መሆናችሁ ይታወቃል፡፡

ይሁንና ትምህርት ሚኒስቴር ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ለተቋማችን በላከልን መልእክት በኢንተርኔት እና ተዛማጅ በሆኑ ጉዳዮች ምክንያት የፈተና ፕሮግራሙ ላልተወሰነ ጊዜ #መራዘሙን አሳውቆናል፡፡

ይህ በመሆኑ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች (ተማሪዎች) ዝግጅታችሁን በመቀጠል የፈተና ፕሮግራሙን በተመለከተ በቀጣይ ከትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን ውሳኔ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባን፡፡

መረጃውን ያገኘነው ከዩንቨርሲቲው የቴሌግራም ገፅ ነው።

@prep34
👍3
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የቅደመ ምረቃ (ፍረሽ) ተማሪዎችን በውድድር ብቻ እንደሚቀበል ገለጸ! like AASTU and ASTU

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን በውድድር መሆኑን አስታወቀ። ዩኒቨርስቲው ክፍያ የሚፈጸሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን “በልዩ” ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይህንን ያስታወቀው የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ መሆኑን አስመልክቶ ማክሰኞ ነሐሴ 16፤ 2015 በዋናው ቅጥር ግቢ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።መግለጫውን የሰጡት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር ስር ያሉ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ የተዘጋጀው አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው ባለፈው ግንቦት ወር ነበር።የዚህን አዋጅ መውጣት ተከትሎም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ያስቻለው ደንብ፤ ከሶስት ሳምንት በፊት ሐምሌ 28፤ 2015 በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቋል።የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት በዛሬው መግለጫቸው፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር “ሁለት ዓመት ባልሞላ” ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን አስታውቀዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
👍2
🌼Buee prep academy🌼
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የቅደመ ምረቃ (ፍረሽ) ተማሪዎችን በውድድር ብቻ እንደሚቀበል ገለጸ! like AASTU and ASTU አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው…
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበልበት መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል፡-

1. እንደማንኛውም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ወጪያቸውን በመንግስት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎችን ፈትኖ ይቀበላል፣

2. በአሁኑ ሰዓት በማታው ክፍለ ጊዜ (Extension) በግል እየተማሩ እንደሚገኙ ተማሪዎች በመደበኛው ክፍለ ጊዜም (Regular) ተመሳሳይ ተማሪዎችን ተቀበሎ በመጠነኛ ክፍያ የሚያስተምር ይሆናል፣

3. ዩኒቨርሲቲው በፊት ከነበረው ከትምህርት ሚኒስቴር ከሚላክለት የተማሪዎች ቅበላ ውጭ በልዩነት ፈትኖ ተማሪዎችን ቢቀበልም ከዚህ በፊት በመንግስት ከሚመደብለት የተማሪዎች ቁጥር ያነሰ አይሆንም፤

4. አዋጁ በግልጽ እንዳስቀመጠው ሁሉንም የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ የትምህርት ተቋም እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል

ይሁንና በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ድህረ-ገፆች ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሐብታሞች መማሪያ ብቻ ይሆናል ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰተኛና የህግ አግባብነት የሌለው መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡

በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መዳረሻ ፣ የእውቀት መገብያ መናኸሪያ እንዲሆን እንጂ ራስ ገዝ አስተዳደር ያስፈለገው የገንዘብ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን ብቻ ተቀብሎ የሚያስተምር ተቋም እንዳይሆን ታስቦ እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ይህ ማለት አንድ ተማሪ ወደ ተቋሙ ለመማር አስቦ ሲመጣ እንደማንኛውም ተማሪ ከክፍያው በፊት የተቋሙን የትምህርት መመዘኛ መስፈርቶች (Admission paper) ሲያገኝ ብቻ ይሆናል::

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
1st semister fresh man courses👇🏾👇🏾👇🏾
🌼Buee prep academy🌼
Psychology Module.pdf
በቀጣይ ግቢ ፍረሽ ተማሪ የ ሆናችሁ ውድ የ ቀድሞ remidial ያሁኑ freshmanoch endihum ዘንድሮ የ 12 ተፈታኝ የነበራችሁ


📚 የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምትወስዷቸው ኮርሶች ማብራሪያ👇


📌 MATHEMATICS ( for natural science)

📌 GENERAL PHYSICS

📌 GEOGRAPHY

📌 LOGIC & CRITICAL THINKING

📌 COMMUNICATIVE ENGLISH SKILL I

📌 PSYCHOLOGY

📌 PHYSICAL FITNESS

🥺 እስኪ አሁን ደግሞ እያንዳንዱን ኮርሶች እንመልከት።

📌 MATHS

📚 11 ኛ እና 12 ኛ ክፍል የተማራችሗቸው ናቸው አብዛሀኞቹ ፡ የተወሰነ ለውጥ( modification) ነው ያለው።

📚 በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::

📌 Logic and critical thinking

📚 ይህ course ለእናንተ አድስ ነው። ምክንያታዊነት እና ፍልስፍስና የትምህርቱ መሰረት ናቸው። የ concept ተማሪ ከሆናችሁ ትሰሩታላችሁ። ይህ ኮርስ በዋናነት የእናንተን የመረዳት ክህሎት ይጠይቃል ፡ እጅግ በጣም በጣም በጣም ደስ የሚል ኮርስ ነው🙈። ነገር ግን ጥልቅ ንባብ እና መረዳት ይጠይቃል ። ላይ ላዩን ማንበብ የለባችሁም☹️

📚 ለማንኛውም ለ logic and critical thinking የሚያግዝ እጅግ በጣም ምርጥ አጋዥ መፅሀፎች አሉ።

1ኛ) Concise introduction to logic

2ኛ) freshman logic

📌 Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ በጣም አሪፍ አድርጎ ያስረዳል። በጣም አሪፍ አሪፍ የሚባሉ እና ከበድ ያሉ ጥያቄዎችም አሉት😴። የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎቹን ገብቷችሁ በአግባቡ ከሰራችሁ ፡ በእርግጠኝነት ግቢ ላይ የሚወጣውን ፈተና ትሰሩታላችሁ😸 ምክንያቱም የከባድ ጥያቄዎች ጣሪያ የሚባሉ ጥያቄዎች መፅሀፉ ላይ አሉ። ኸረ እንዳውም ከመፅሀፉ Exercise ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ፈተና ላይ ቀጥታ ያወጡታል🙈🙈። የግቢ መምህሮች በጣም የሚጠቀሙት መፅሀፍ ነው👏👏

📌 Freshman logic የሚለው መፅሀፍ ደግሞ የ logic and critical thinking ትምህርትን በቀላሉ እንድትረዱት ያደርጋል ምክንያቱም በ አማርኛ እየተረጎመ ስለሚያስረዳ👏😘። የትምህርቱን ፅንሰ ሀሳብ ( concept) በቀላሉ ለመረዳት freshman logic የሚለው መፅሀፍ በጣም ምርጥ ነው። በዛ ላይ እጅግ በጣም ደስ ደስ የሚሉ የ concept ጥያቄዎችም አሉት😴😍። ስለዚህ እኛ የምንመክራችሁ

1ኛ) መምህሩ የሚሰጣችሁን ኖት ፡ ፒዲኤፍ ማንበብ ፡መምህሩ ሲያስተምር በ ደንብ መከታተል። ጥሩ አድርጎ የማያስተምር መምህር ሊያጋጥማችሁ ስለሚችል ነባር ተማሪዎችን ጠይቆ መረዳት። A+ tutorial Class ላይ ትምህርቱ ግልፅ በሆነ መንገድ ስለሚሰጥ እዛ ላይ ተመዝግባችሁ መማር።

2ኛ) freshman logic የሚለውን መፅሀፍ ማንበብ ምክንያቱም መፅሀፉ ላይ የቀረቡት ኖቶችን በቀላሉ ስለምትረዷቸው።

3ኛ) Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ ላይ ሂዳችሁ ጥያቄ መፍለጥ🕺 ፡ የሚገራርሙ ጥያቄዎች አሉት😴። ከዛ A ታመጡና መቀወጥ🕺💃🕺💃😁😁

📌 Communicative English skill I

ይህ ኮርስ ላወቀበት ተማሪ የሚሰራ ኮርስ ነው፡🙈። በውስጡ ምን ምን ይዟል መሰላችሁ🤔

📚 Speaking skill ( ራሳችሁን በ እንግሊዝኛ ማስተዋወቅ🙈 ፡ ከዛ መምህሩ የሆነ ርዕስ ይሰጣችሁ እና ስለዛ ነገር በ እንግሊዝኛ presentation ማቅረብ (የሆነ ማርክ%)

📚 Reading skill ( አንድ passage ይሰጣችሗል ፡ በዛ መሰረት ጥያቄ ይሰጣችሗል( የሆነ ማርክ%)

📚 Writing skill ( letter , descriptive , narrative,argumentative , expository ከነዚህ ባንዱ ትፅፋላችሁ( ከዛ የሆነ ማርክ)

📚 Grammar ( Tense , Active and passive voice , conditional sentence, reported speech ... እነዚህ ነው የምትማሩት ፡ ደግሞ ቀላል ናቸው ፡ Concise ላይ የተለቀቁ ኖቶችም ሊጠቅማችሁ ይችላል።)

📌 Geography

ለ Geography ም አዲስ አይደላችሁም። ነገር ግን ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አደለም በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል 🤷‍♂️ ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Note ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባቹ ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም PPT እንደ Apetizer ውሰዱ 😂 እንዳልኳቹ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ Module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል Note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቡን አንብቡ 👍::

📌 Psychology

📚ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል:: ይህ ትምህርት ለየትው የሚያረገው በደምብ መረዳትን ይጠይቃል Module ካነበባችሁ በቂ ቢሆንም Module በደምብ የማያብራራው ሀሳብ ስለሚኖር Google ማድረግ በጣም ተመራጭ ነው በይበልጥ ከ ምዕራፍ 3 ጀምሮ የ Case ጥያቄ ስለሚበዛ በደም Exercise መስራት ይጠቅማቹሀል በቀላሉ Google ላይ በ Topicu ርዕስ worksheet search ብታረጉ ከፈተናው ተመሳሳይ ጥያቄ ታገኛላቹ።
ሌላኛው አማራጭ YouTube ነው እኛ ሀገር በስፋት ባይለመድም በአጭር ግዜ Concept ለመረዳት ፍቱን ነው ሞክሩት ።
11 ምዕራፎች ሲኖሩት ቢበዛ እስከ ምዕራፍ 8 ብትማሩ ነው አታስቡ A+ የናንተ ናት 👍

📌 General Physics

General physics የምትማሩት ከ 11 እና 12 የተለየ ነገር የለውም ከናንተ የሚጠበቀው Module ማንበብና የተወሰነ Refer አድርጋቹህ ጥያቆዎችን መስራት ነው እንጂ የተለየ አዲስ ነገር የለውም::

📌 Physical fitness

ሜዳ ወጥታችሁ ሱምሶማ መስራት መሮጥ ነው😁። ስለዚህ የ ስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል ፡ እንዳትረሱ😂። ይህ ኮርስ ውጤት የለውም ማለቴ ውጤት አይሰራለትም:: pass or fail ነው የምትባሉት።


♻️Share and Support Us.
═══════════════════
Join us 👇👇
👍3
🎬 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸው ኮርሶች👇

📌 Communicative English Skill I

📌 Economics

📌 Geography

📌 Maths(Social)

📌 Civics and Moral Education

📌 Global Trends

📌 Physical Fitness

🙌 አሁን ደግሞ ስለ እያንዳንዱ ኮርስ መጠነኛ የሆነ ገለፃ ወይም ጅንጀና እናድርግ።

🎯 Communicative English Skill I

ይህ ኮርስ የብዙ ተማሪዎችን ውጤት የሚያነሳ ነው እንግሊዝኛ ሞካሪ ከሆናችሁ። ነገር ግን የአምና ተማሪዎች ውጤታቸውን ዝቅ አድርጎባቸዋል። በዚህ ኮርስ በዋናነት የምትማሩት

🗞 Reading skill ( ልክ Entrance እንደተፈተናችሁ አይነት የ passage ጥያቄ ትፈተናላችሁ።)

🗞 Grammar( Tense , conditional sentence, Modal Verbs etc ትማራላችሁ።) mid exam, final exam እና CoC exam ላይ passive and active voice እና conditional sentence ብዙ ጥያቄ ስለሚወጡ ትኩረት ሰጥታችሁ በማንበብ ተረዱት።)

🗞 Vocabulary - ከ አውዱ ተነስታችሁ የቃላቶችን ተመሳሳይ ና ተቃራኒ ትርጉም መፈለግ ነው። ብዙ ተማሪዎች ለመስራት ይቸገራሉ። ነገር ግን ወደ 5 የሚሆኑ ዘዴዎች አሉ በእነሱ መሰረት መስራት ነው። ፈተና ላይ በብዛት ይወጣል። ኮርሱ A+ tutorial class ላይ ግልፅ በሆነ መንገድ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

🎯 Economics

📚 ግቢ ላይ ብዙ ሰቃይ ተማሪዎች Economics ን አይሰሩትም🙇‍♂️። 3.7 or 3.8 ያላቸው ልጆች Economics ን B- ምናምን ነው የሚያመጡት። ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው ግቢ ላይ የ Economics ትምህርት ፈተናዎች ወይም ጥያቄዎች conceptual ናቸው። ስለዚህ Economics ን ስታነቡ አትሸምድዱ። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ሞክሩ ፡ ተግባራዊ እውነታውን ተረዱ። ለዚህ ኮርስ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ቲቶርያል ልጠቁማችሁ። በርግጠኝነት A+ ነው የምታመጡት። Fortino Academy ይባላል። በ አማርኛ እያብራራ ያስረዳል። እጅግ በጣም ሲበዛ ግልፅ ና ለፈተና የሚያዘጋጁ ትምህርቶች ይቀርቡበታል። You tube ላይ ገብታችሁ ተከታተሉት። ማየት ምስክር ነው።

🎯 Geography

📚 ግቢ ላይ የምትማሩት የ Geography ትምህርትም አዲስ አይደለም። በዋናነት የኢትዮጵያን እና የምስራቅ አፍሪካን መልክአምድራዊ ገፅታ ነው በዚህ ኮርስ የምትማሩት ። ነገር ግን ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አደለም በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል 🤷‍♂️ ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Note ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባቹ ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም PPT እንደ Apetizer ውሰዱ 😂 እንዳልኳቹ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ Module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል Note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቡን አንብቡ 👍:: 🎯 Maths (Social)

ከ መጠነኛ ለውጥ ( modification) ውጭ 11 እና 12 የተማራችሁት ነው። 📚 በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::

🎯 Civics and Moral Education

📚 ዩኒቨርሲቲ ላይ የሚሰጠው የ Civics and Moral Education ኮርስ ፤ Highschool ና pre paratory ከሚሰጠው ኮርስ ጋ በፍፁም አይገናኝም። ግቢ ላይ ያለው የ Civics ኮርስ ለተማሪዎች የሚያስቸግር ከባድ ኮርስ ነው። ይህ ኮርስ በተለይ ስለ Ethics ና Morality ምንነት በስፋት ያትታል። ከ Ethics ጋ የተያያዙ የ ሞራል ፍልስፍናዎችን ና ንድፈሀሳቦችን በስፋት ይዳስሳል። በተለይ ስለ Normative ና non-normative Ethics, Teleological Ethics, Ethical Egoism and psychological Egoism, Altruism, Utilitarianism, Quality over quantity Ethics, Quantity over quality Ethics, Act and Rule Utilitarianism, Virtue Ethics, Meta Ethics በጣም በስፋት ይዳስሳል። እንዲሁም ደግሞ ስለ state, government ና citizenship ምንነት በስፋት ያጠናል በተለይ ስለ pluralist state, capitalist state, Leviathan state, Patriarchal state, minimal state, developmental state,social-democratic state, collectivized state, totalitarian state, religious state ና ስለ Citizenship በጣም በስፋት ያጠናል። A+ Tutorial Class ላይ በጣም ደስ በሚል ለመረዳት ምቹ ና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

🎯 Global Trends

📚ይህ ኮርስ ከስሙ እንደምትረዱት ፤ ፖለቲካዊ ቴክኖሎጂያዊ ና ኢኮኖሚያው አለም አቀፍ ጉዳዮችን ይዳስሳል። በተለይ አለም አቀፍ ግንኙነት(International relation) ሳይንሳዊ ምንነትን ይዳስሳል። ስለ አቀፍ ግንኙነት ንድፈ ሀሳቦችን ይዳስሳል በተለይ ስለ Liberalism, Realism , Marxism ና Constructivism የተባሉ የፖለቲካ ርዕዮቶችን ይዳስሳል። እንዲሁም ስለ Foreign Policy, National interest ና Globalization በሰፊው ይናገራል። 😁ይህ ኮርስ ለተማሪዎች የሚከብድ ኮርስ ነው። A+ Tutorial Class ላይ በጣም ደስ በሚል ለመረዳት ምቹ ና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

🎯 Physical Fitness

📚 ይህ ኮርስ ውጤት የለውም። ማለትም A, B+ ,C ምናምን ተብሎ Grade አይሰራለትም። pass or fail ነው የምትባሉት። ኳስ ሜዳ ወጥታችሁ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ነው የምትሰሩት ፡ ስለዚህ የስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል። attendance ካልቀራችሁ እና መምህሩ የሚያሰራችሁን ስፖርት ከሰራችሁ pass ትባላላችሁ ማለትም ታልፋላችሁ።



♻️ Share and support us
__
jo
in us👇👇
በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በ ኦንላይን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።

ለዚህም ተግባራዊነት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ፤ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ በመጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው በዋል።

በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመጽሐፍት እጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ፤ ችግሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳያጋጥም ቀደም ብሎ ጨረታ በማውጣት መጽሐፍትን በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

መጽሐፍት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቀርቡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
©ትምህርት ምንስቴር
👍1
#ውጤት

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም (15) ድረስ ይፋ ይደረጋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም 2016 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በጥቅምት 2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር ዕቅድ መያዙንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በፀጥታ ችግር ምክንያት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሦስት ፈተናዎች ያልወሰዱ ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።

በ2015 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ሲወስዱ የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች፣ የመጨረሻዎቹን ሦስት ፈተናዎች አለመፈተናቸው ይታወቃል።

እነዚህ ተማሪዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ ፈተናቸውን እንዲያሚያጠናቅቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።
#ጥሪ_ማስታወቂያ

ለነባር የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ ለ2016ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ነባር የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን #መስከረም 18-20 2016 ዓ.ም. መሆኑን አናሳውቃለን።( including freshmans 2nd semister stud)

ማሳሰቢያ፡ በ2ዐ15 ዓ.ም. በRemedial ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ወጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ወደ ፊት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን።
0.5 TRX አንድ ሰው ስትጋብዙ ይሰጣቹሀል 🔥
ቤታችሁ ውስጥ
No Investment 🔥
100% Legit ነው ይከፍላሉ
Minimum Withdrawal 0.05 TRX

⚠️ 3ቱንም Telegram ቻናላቸውን እና Youtube አካውንታቸው Join እና Subscrbe ማድረግ አለባቹ ስራውን ለመጀመር(youtube subscribe batilum chigir yelewim) ከዛ bonus ነክታችሁ getbonus ነኩና active አርጉ

ስራውን ለመጀመር Link👇👇👇 https://t.me/SonicTrxBot?start=1189801869 ke tech channel የተወሰደ
የጥሪ ማስታወቂያ

#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ዲግሪ የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪ የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ምዝገባ መስከረም 07/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት መስከረም 08/2016 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡

(ዩኒቨርሲቲው ያወጣው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)
" ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016  የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር
 
ትምህርት ሚኒስቴር የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 እንደሚሰጥ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ፈተናው በ30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከናወን ይሆናል።

የሚሰጠው ፈተና የማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ  ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከመስከረም 7- 10/2016 ዓ.ም ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና #በወረቀት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50 % በታች ሆኖ ወደከፍተኛ ትምህርት መግባት ያልቻሉ እና በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት የነበራቸው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንድ ሴሚስተር የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸው ይታወቃል።

የማካካሻ  (ሬሜዲያል) ፈተና የሚሰጠው ተማሪዎቹ በተቋማት እና በማዕከል የሚሰጠውን ምዘና ወስደው በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ከ2016 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ጋር የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው።

#Moe