የብዕር ዕንባ 🀄️📝
92 subscribers
13 photos
1 video
3 files
38 links
👉ግጥም
👉ልብወለድ
👉 ፍልስፍና
👉ሀገርኛ ብሂል
👉የሙዚቃ ግጥም
👉ቁም ነገር ለመሸመት
👉ይቀላቀላሉ @poem06
👉አልፎ አልፎ ጥያቀዋችን በመጠየቅ ካርድ እናmb የምሸልም ቻናል ነው።
#join
@poem06
@poem06
@poem06
👉#contact
@Ayo11bot
@Historyoflegend
Download Telegram
ከፍሰሃ ጋር መወለድ

ሰዎች ግራ እስከሚገባቸው ድረስ እጅግ በጣም ደስተኛ የነበረ አንድ ቅዱስ ሰው ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ሰው አዝኖ ስለማያውቅ ሰዎች በጣም ግራ ይጋቡ ነበር፡፡ ይህ ሰው የመሞቻው ጊዜ እንደቀረበ «በሶስት ቀናት ውስጥ እሞታለሁ፡፡ ስለዚህ ስሞት እንዳታለቅሱ፡፡ እድሜ ልኩን ሲስቅ ለኖረ ሰው አይለቀስም፡፡ ይህንን የማሳውቃችሁ በዚህ ጎጆ ውስጥ ምንም አይነት ሃዘን እንዳይኖር ነው፡፡ ይቺ ጎጆ ሁልጊዜ ደስታ እንደተሞላች ነው፡፡ ስለዚህ ሞቴን ክብረ-በዓል እድርጉት፡፡ ሞቴን ሃዘን አታድርጉት” አላቸው፡፡

ሰዎቹ ግን በጣም አዘኑ፡፡ ሰውዬው ግን በጣም አስገራሚ ሰው ነበር፡፡ ሰውዬው አስገራሚነቱ ጥልቅ በሆነ ቁጥር ግን ሰዎቹ በሃዘን ተሞሉ። ብዙ የሚወዱት ሰዎች ነበሩ። ለሦስት ቀናትም ዙሪያውን ከበቡት እስኪሞትም ድረስ ለሰዎቹ ቀልዶቹን ይነግራቸው እና በፍቅር ያዋራቸው ነበር፡፡ ከመሞቱ በፊት ጧት ላይ መዝሙርን ዘመረ እና መዝሙሩን ከጨረሰ በኋላ ለተሰበሰቡት ሰዎች “አስታውሱ ስታቃጥሉኝ ልብሶቼን አታውልቋቸው፡፡ ሬሳ ማቃጠያው ስታስቀምጡኝ ከእነዚህ ልብሶች ጋር አስቀምጡኝ፡፡ ገላዬንም አትጠቡኝ” አላቸው፡፡ እነዚህም የመጨረሻ ትእዛዞቹ ነበሩ፡፡ እናም ሞተ። በሬሳ ማቀጣጠያው ላይ አስቀምጠው ሬሳውን ከነልብሱ ሲያቃጥሉት ስዎች በማዘን የሚቃጠለውን ሬሳ ቆመው እና ከበው እያዮ ነበር፡፡ በድንገት ግን ደነገጡ፡፡ ቅዱሱ ሰው በኪሶቹ ርችቶችን ደብቆ ነበር እና ርችቶቹ መፈንዳት ጀመሩ፡፡የሬሳ ቃጠሎው ወደ ክበረ-ባዓል ተቀየረ! ሰዎቹም መሣቅ ጀመሩ፡፡ “በህይወት እያለ ሲያስቀን ነበር ፤ ሞቶም አሣቀን” አሉ፡፡

ሕይወት ወደ ክብረ-በዓል መሽጋገር አለባት፡፡ ህይወት ፍስሃ መሆን አለባት። ሞት እንኳን ክብረ-በዓል መሆን አለበት፡፡ እናም ይህንን በማድረግ የሚሣካለት ሰው ደግሞ የተባረከ እና በምስጋና የተሞላ ይሆናል።

በዚህ ቦታ ውስጥ ወደ ተመስጥኦ የሚገባ ሰው አንድ ሰው ማሰብ ከሚችለው በላይ በሆነ ፍጥነት መጓዝ ይችላል። ልክ እንደ ቀስትም ይሆናል። ሸክም በበዛበት አእምሮ ጋር ታስሮ ወደ ተመስጥኦ የሚገባ ሰው ቀስት ላይ ድንጋይ አስሮ እንደሚወረውር አይነት ሰው ነው፡፡ ከዚያስ ቀስቱ ምን ያህል ርቆ ይጓዛል? በፍጥነት ለመጓዝ በፈለጋችሁ ልክ አእምሯችሁ የበለጠ ግድ የለሽ እና ቀላል መሆን ያስፈልገዋል፡፡ቀስቱ በፍጥነት ይጓዝ ዘንዳ በፈለጋችሁት ልክ ቀስቱ ቀላል መሆን አለበት፡፡ ከፍ ያለን ነገር ለመንጠላጠል በፈለጋችሁት ልክ ብዙ ኮተቶችን ታች ላይ መተው ይኖርባችኋል፡፡ እናም ታላቁ ሸክማችሁ ደግሞ መከራችሁ፣ ሐዘናችሁ፣ ጥላቻችሁ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ ሌላ ሸክም የለም፡፡ ሰዎችን አልተመለከታችሁምን? ሲራመዱ ጭንቅላታቸውን ሸክም ያጎበጣቸው ነው የሚመስሉት። ይህንን ሽክም አስወግዱት እና ደስታን ተቀበሉ! ምንም አይነት ህይወት ይኑራችሁ ወደ መዝሙር ሊቀየር ፣ በፍስሃ ሊሞላ እንደሚችል ለአለም ንገሩ፡፡ ህይወት ሙዚቃ መሆን ትችላለች።

ኦሾ


join
@poem06
@poem06
@poem06
Forwarded from ቃላዊ
━━━━━✦✦━━━━━

...ለመኮብለል ፡ ስታስብ ፡ ከሃሳቧ ፡ ሃሳብ ፡ ገባኝ። በቃል ፡ ታጥራ ፡ እስከ ፡ አፅናፍ ፡ድረስ ፡ ርቃ ፡ ብትሄድ ፡ አይደንቀኝም ። አይገርመኝም። ቃሏን ፡ በልታ ፡ የልቤን ፡ ፅገረዳ ፡ እንፍጭ ፡ ስታስመስለው ፡ እንግዲህማ ፡ ባይገርመኘ ፡ ይገርመኛል ። በሰበብ ፡ መሽመድመድ ፡ ምክንያታዊ ፡ ያደረጋት ፡ ይመስል ፡ አሁን ፡ ላይ ፡ ለመዝነብ ፡ ሰሞኑን ፡ ቀዝቃዛው ፡ ፀብ ፡ ካፊያ ፡ ሆኖ ፡ ቀርቶ ፡ ነበር። ውርጭ ፡ ቅርንጫፎቼን ፡ እንዳይመታ ፡ በብዙ ፡ ሰግቼ ፡ ነበር ፡ ግን ፡ አልቀረልኝም ፡ ቅርንጫፎቼን ፡ ሰባበረና ፡ ድኩም ፡ አደረገኝ። የህልሜን ፡ ውጥን ፡ ፍሬ ፡ ስቃኝ ፡ የተጨራመተ ፡ እህል ፡ መስሎ ፡ ታየኝ። የከርሞ ፡ መንገድን፡ ሳስበው ፡ የዘንድሮው ፡ ተከርችሞ፡ ይታየኛል። መንገዱን ፡ ጨርቅ ፡ ያርግልሽ ፡ ከምለው ፡ ምርቃት ፡ ይልቅ ፡ በአሜከላ ፡ ይታጠር ፡ ብሎ ፡ መራገም ፡ ድርሻዬ ፡ ይመስለኛል። እርግጥ ፡ ነው ፡ መቁሰሏን ፡ አልሻም ፡ ግን ፡ ካሰበችው ፡ የድሎት ፡ ጠዛ ፡ እና ፡ የግዞት ፡ ጥዝጣዜ ፡ ኑሮ ፡ መቅረቷን ፡ እናፍቃለሁ።
ቅፅበት ፡ ሳይነፍስ ፡ መውደድ ፡ እየነጠፈ ፣ እየተነነ ፡ በትዝታ ፡ ሰንሰለት ፡ የሁዋሊት ፡ ፊጥኝ ፡ ልያስረኝ ፡ ያወዛውዘኛል። የውበት ፡ ጮራ ፡ ድምቀት ፡ ቀትር ፡ የግለት ፡ ውህደት፡ ሙቀት ፡ ነው። ሰው ፡ በመነሻው ፡ አይፀናም። ፀባየ፡ ሰናይ ፡ ያልከው ፡ ቀርበህ ፡ ስትረዳው ፡ እንደ ፡ ዕይታህ ፡ ሳይሆን ፡ እንደተረዳሄው ፡ ይሆናል። የቅርበ ፡ ያልኳቸው ፡ ሁሉም ፡ ስርቁ ፡ የማላውቀው ፡ ሀገር ፡ ሩቁ ፡ ይናፍቀኝ ፡ ጀመር ፤ ስለ ፡ ምድሩ ፡ መጨነቅ ፡ ተወት ፡ አድርገው ፡ በሩቅ ፡ ለምታየው ፡ ስለ ፡ ሰማዩ ፡ እያሰብኩ ፡ ህይወትን ፡ ሽቅብ ፡ በዳዴ ፡ እዳክራለሁ።
ወዲህ ፡ ብሉት ፡ ወዲያ፡ የማይቀያየር ፡ ሰማይ ፡ ነው። ዥንጉርጉር ፡ ምድር ፣ ጉራማይሌ ፡ አፈር ፡ ምን ፡ ይፈይዳል? በጉራማይሌነቱ ፡ መከባበር ፡ ስገባው ፡ መነሻውን ፡ ይስታል። ከሄዋን ፡ አስቀድሞ ፡ መነሻ(ችን) ከአፈር ፡ ነው። ለፍቅር ፡ መነሻ[ዬ] ፡ አንቺ ፡ አይደልሽም።ራሱን ፡ የሰዋው ፡ እሱ ፡ ራሱ ፡ ፍቅር፡ ነው። እኛማ ፡ እሱነቱን[ፍቅርን] ፡ ማወቅ ፡ ተስኖናል። ከአንድም ፡ ሁለት ፡ ሆነናል። መነሻችን ፡ ጠፍቶን ፡ ዳግም፡ ከአፈር ፡ መፈጠር ፡ እንሻለን።
.
.
.
@ቃልኪዳን [አዮነት]
አርባምንጭ, ጦብያ
━━━━━✦✦━━━━━


◌◉◎◦◈◦◎◉◌
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
comment
@kaliye06
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
Forwarded from ቃላዊ
🍁ሙሉጌታ ተስፉዬ የተባለ ገጣሚ
ምን ይላል መሠላችሁ! አለም ላይ ስትኖር ሁለት እድል አላችሁ ወይ ራሣችሁን ችላችሁ መቆም አለበለዚያ መቃብራችሁን ቆፍራችሁ መግባት። ሌላ አማራጭ የላችሁም ይላል..... የአለም ቁጥር አንድ ጀግና ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ጀግና ማለት ጦር ሜዳ ብዙ ገድሎች የሰራ አይደለም። ሠው መግደል ጀግንነት ሣይሆን ሠይጣናዊት ነው። ጀግና ማለት ብዙ ብሮች ያሉት ሀብታም አይደለም ጀግና ማለት ጫካ ውስጥ የሠራውን ገድል ከተማ ውስጥ መጥቶ እየተኮፈሰ ይህን አደረኩኝ የሚል አይደለም!
ትልቅ እውነተኛ ጀግና አምባገነን መሪ ፊት አንዳችም ሣይፈራ እውነቱን የተናገረ እና ውስጡ ያለውን ስንፍና ያሸነፈ ብቻ ነው።

የቆሸሹ ሳቆች
(አዘርግ)


◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
Forwarded from ቃላዊ
🍁ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደለም።ድህነትም የባከኑ ዕድሎች ና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ የአርባ ቀን ዕድል አይደለም "ህይወት ረቂቅ ሚስጢር ናት"። አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህቺን ሚስጢራዊ ሕይወት ዕድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት አደለን። ይህቺም ከረጢት በውስጧ ዕድል በተሠኙ ፈርጦች ተሞልታለች ከረጢቷን እንዳትሰረቅና ያለጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጪ እንዳትሆን ኋላፊነቱን ፈጣሪ ለእኛው ነው የሠጠን በከረጢቷ ውስጥ ያሉትም ፈርጦች አንድ በአንድ እያብለጨለጩ ከባለ ከረጢቱ እጅ ላይ ይፀድቃሉ። ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜው ያልተጠቀምንባቸውን ዕድሎች ከጊዜ ጋር ላይመለሡ ትዝታቸውን አስታቅፈውን ይነጉዳሉ። ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደለም። ድህነትም የባከኑ ዕድሎችን ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ የአርባ ቀን ዕድል አይደለም።


የተቆለፈበት ቁልፍ
( ምህረት ደበበ) ዶ/ር


◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
Forwarded from ቃላዊ
🍁.... ወጣነት ማለት ፉሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ ማለት አይደለም ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አንደለም።
"ወጣትነት ውቂያኖስ ነው" ወጣነት ማለት አድማሠ ሀላፊነት
ነው ... ወጣትነት እውቀት ለማስፉት የምንጋደልቀበት ሠአት ነው ወጣትነት
ከፍርሀት፣ አይቻልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ
ነው።ወጣትነትለ አንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው።

ከ ኤጭ መፅሀፍ የተቀነጨበ ( አዘርግ)

◈◈Join us n share◈◈
◌◉◎ ◎◉◌
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
Forwarded from ቃላዊ
እኔና አንቺ!
( በረከት በላይነህ).

በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።

ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።

ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።

በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።

‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
◈◈ Join ◈◈
👇👇👇
@Write_Event
@Write_Event
@Write_Event
🀄️
🕊 ቸር ያሰማን 🕊
◌◉◎◦◈◦◎◉◌
ሶሊያና

(ኤፍሬም ስዩም)
-----------------------------------

እኔን ከወንበር ላይ
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ
ወረቀት ላይ ወስዶኝ
……
እርሷን ካልጋችን ላይ
እንቅልፍ አሽኮርምሟት
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት ……
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ
ከደጋው ሃሳቤ በረሃ ስሰደድ
እንባን በፊደላት …
ፊደልን በቃላት…
ቃላትን በሃሳብ ወረቀት ላይ ልወልድ
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ …
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
‹‹ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋየ ላይ
አንተን በመናፈቅ በስሜት ስሰቃይ ››
ቀ…ና ብየ ባያት እውነት አለው ቃሏ
ፍም መስሏል አካሏ
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል
እኔን በመጓጓት ደሟ ጠቆጥቶ
ፍቅሯ ተሰውቶ
ስሜቷ ተጎድቶ
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ህፃን
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉራ ሲበታተን …
ካ,ልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን
ፍ...ቅ...ሬ ሶ...ሊ...ያ...ና አወራችኝ መሰል
በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ …
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰትህ አለም
የሰዎች ጥላ እንጅ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ
በሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ
እኔ ውበቱ ነኝ በፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም . . . ወዲህ እንዳትመጣ
በሌሊት ትጋትህ ሃዘን ሳይቀጣ
በ,ኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ
ከየሰው አለም የሚመሳሰሉ
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፍ
ይህ ሁሉ ቢሆንም …
የሰወችን እንባ አትፃፍ ግዴለም
የፍጥረትን ሃዘን ስለህ አትዘልቅም
እውነት አለው ብለህ ሃዘንን አታልም
((ያለቀሱም ሰዎች ሃቀኞች አይደሉም ))
ይልቅ የኔን ስሜት ያንተንም እንባዎች
ሁለቱን አሳየኝ
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ !
እኔን ብቻ ፃፈኝ !
‹‹ያልተደሰተች ሴት›› በሚል መፅሃፍህ
ዘ...ላ...ለ...ም አሻግረኝ
ዘ...ላ...ለ...ም ውሰደኝ
ዘ...ላ...ለ...ም አኑረኝ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
ከበደ ሚካኤል
'
ዝ ን ጀ ሮ
🦧 🦧
አንዲት ዝንጀሮ ናት
የምታስደንቀን፣
ሥራዋን ስናስብ
ዘዴኛ ናት ብለን።
አንድ ቀን ስትሄድ
ጥቅጥቅ ባለው ጫካ፣
በመላው አካሏ
ብዙ እሾህ ተሰካ።
እንዳትቀመጥም
ወይም እንዳትቆም፣
ወግቶ አስጨንቋት
ተጠምቃ በደም።
አንድ ሰው አየና
ቀርቦ ጠየቃት፣
'የቱን ልንቀልልሽ
ንገሪኝ' አላት።
'ሁሉንም ለማውጣት
አልተቻለኝም፣
ቸኩያለሁና
ጊዜ አላገኝም'።
'ከነቀልህልኝስ'
አለችው 'ጌታዬ፣
መጀመሪያ ይውጣ
የመቀመጫዬ፤
ቂጤ መሬት አርፎ
ትንፋሼን ካገኘሁ፣
የቀረውን ሁሉ
እኔ አወጣዋለሁ'።
ይህንን ተናግራ
ዝንጀሮ አረፈች፣
እሾሁን በተራ
እያወጣች ጣለች።
👇
የመቀመጫችን
የአገር ነገር፣
ከሌላው ጣጣችን
ይቅደም ይጀመር።
በጣም ቢቸግረን
በጣም ቢከፋን፣
ይኽንን ታግሰን
ለአገር ከለፋን፣
ኋላ ደስ ይለናል
አንቁረጥ ተስፋን።
--------------------------
ኢትዮጵያ ትቅደም 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
📖 📖 📖 📖 📖
@poem06

❝የመምህርንትን ሙያ አቤት ስወደው! ለምን መሰለህ? ሽኩቻህ፣ ጥልፊያህ ከማወቅና ካለማወቅ ጋር ነው። እምትመቀኘው ሌላን ሳይሆን ድንቁርናን ነው።❞
ስብሐት ገ/እግዚአብሔር


❝በአንድ የአፍሪካ መንደር የሚኖር ሽማግሌ ሞተ ማለት፤ አንድ ሙሉ ቤተ መጻሕፍት ተቃጠለ ማለት ነው።❞
እምቦዋ


❝ምስጢርህ በልብህ ውስጥ እስካለ ድረስ በፈቃድህ የታሰረ ይሆናል። ከአፍህ ከወጣ ግን አንተ በማሰሪያው የታሰርህ ትሆናለህ።❞
ወልደ ሕይወት


❝ትምህርት ያገኘን ሕዝብ በቀላሉ ይመሩታል። ሊነዱት ቢፈልጉ ግን እጅግ አስቸጋሪ ዳገት ይሆንባቸዋል። የተማረን ማስተዳደር ቀላል ነው፤ እንደ ባሪያ መግዛት ግን ከቶም አይቻልም።❞
ሎርድ ብሮዋም


❝ጥቁር የበላይ የሆነባት ብቸኛዋ ሀገር ማኪያቶ ናት።❞
ይስማዕከ ወርቁ

┈•✦•┈,
ጥ ቅ ሶ ች
"የሰው ልጅ ራሱን መካድ ሲጀምር ባህልና ስልጣኔን አመጣ... እንዲሁ መቀጠል ቢፈቀድለት ደግሞ ዓለማችን ላይ ከፍ ያለ ዋጋ የምንሰጠውን ነገር ሁሉ እንዲያበቃለት ማድረግ ይቻለዋል ። ስለሆነም በዚህ የባርነት ሞራላዊ አስተሳሰብ ልንቀጥል አይገባንም ።"

#ኒቼ
የመሻገር_ሲቃ
ደራሲ- ኢቫን ካንኪር (ዩጎዝላቪያ)
ተርጓሚ- ያዕቆብ ብርሃኑ

በእያንዳንዱ ምሽት ታዳጊዎቹ ወደ መኝታቸው ከመሄዳቸው በፊት ሰብሰብ ብለው ማውጋት ይወዳሉ፡፡ በሰፊው ምድጃ አጠገብ ተቀምጠው ወደ አዕምሮአቸው የመጣውን ነገር ሁሉ ያንሾካሹካሉ። በደብዛዛው መስኮት በኩል ወደ ክፍሉ የሚያጮልቁትን የምሽት ፍዝ አንጸባራቂ ብርሃናት ህልም በተሞሉ ዓይኖቻቸው ይመለከታሉ፡፡ በእያንዳንዷ ጥጋጥግ የፀጥታ ጥላዎች ግር የሚሉ እንግዳ ተረቶችን ተሸክመው ይገዝፋሉ፡፡

ወደ አዕምሮአቸው የመጣውን ነገር ሁሉ ቢናገሩም ቅሉ ወደ አዕምሮአቸው የሚመጡት የጸሐይ ብርሃንና ግለት (የስሜት) ከፍቅርና ተስፋ ጋር የተጠላለፉባቸው ታሪኮች ናቸው፡፡ ለእነሱ የሚቀጥለው ጊዜ በሙሉ አንድ ረጅም የደመቀ ክብረ በዓል ነው፡፡ በገና እና በፋሲካ በዓል መካከል እንኳን የሁዳዴ ጾም የለም፡፡ እዚያ የሆነ ቦታ በአበቦች ካሸበረቀው መጋረጃ ጀርባ የምልዓተ ሕይወት እርግብግቢት፣ ትርታ ሁሉ በጸጥታ ከብርሃን ወደ ብርሃን ይንቆረቆራል፡፡

ቃላት በለሆሳስ ይነገራሉ፤ በከፊል ብቻ ግንዛቤ መረዳት ይወሰድባቸዋል። የትኛውም ተረት መነሻም ሆነ ቅርጽ፣ የትኛውም ተረት መቋጫ የለውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአንድ ጊዜ አራቱም ልጆች ያወራሉ። ሆኖም ማንኛቸውም አይደናገሩም፡፡ ሁሉም ዓይኖቻቸውን ትኩር አድርገውና ተመስጠው የእያንዳንዱን ቃል ግልጽና እውነተኛ መሆን፣ የእያንዳንዱ ተረት ጉልህና ሕይወታዊ መልክ፣ የእያንዳንዱ ተረት ሞገስ ያለው አጨራረስ በብሩህና በጣም አስደሳች በሆነው ጸዳል በኩል መንፈሳቸውን ሰብስበው ይመለከታሉ፡፡

የምሽቱ የሰከረ ድንግዝግዝ ብርሃን መልካቸውን ከማመሳሰሉ የተነሳ የአራት ዓመቱን ታዳጊ ቶንቼክ ከታላቋና አስር ዓመቷ ሎይዝካ መለየት አይቻልም፡፡ ሁሉም ቀጭን ጠባብ ፊቶችና ትላልቅ የተበለጠጡ ወደ ውስጥ የሚመለከቱ ዓይኖች አሏቸው፡፡

በዚያ ምሽት ግን የሆነ ያልታወቀ ነገር ካልታወቀ ቦታ ከሀይለኛና ቁጡ እጆቹ ጋር ወደ ብሩህና አስደሳቹ ብርሃን ገብቶ በተረቶች፣ በበዓላትና በአፈ ታሪኮች መካከል ጨካኝ ሆኖ ታየ፡፡ ደብዳቤው (ፖስታው) አባትዬው በኢጣሊያ አፈር ላይ መውደቁን የሚገልጽ ዜና አስከትሎ መጣ። የሆነ የማይታወቅ፣ አዲስ፣ እንግዳ የሆነ፣ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት የሚያስቸግር ነገር ገጠማቸው፡፡ እዚያው ቆሟል፤ ረጅም ሰፊ ቢሆንም፣ ነገር ግን ዓይን፣ ፊትም ሆነ አፍ የለውም፡፡

ሁኔታው ከምንም የማይመሳሰል፣ ጩኸት ከበዛበት ሕይወትም ሆነ ከቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከመንገድ ላይ፣ ከምድጃው ወጋገንም ሆነ ከተረቶቹ የማይገጥም ነገር ነበር፡፡
ምንም የማያስደስት በተለየ ሁኔታ የማያሳዝን ሙት ነገር ይመስላል፡፡ ምንም ዓይኖች ስለሌሉት ከየት እና መቼ እንደመጣ ሊያብራራ የሚችል አንደበት የለም፡፡ ልክ ከግዙፍ ግንብ ፊት እንደቆሙ ሁሉ ከዚያ አንድስ የሚያህል ጣዕረ ሞት እንግዳ ሁነት ፊት ትሁትና አይናፋር መስለው ያለ ንቅናቄ ቆሙ፡፡
‹‹ግን መቼ ነው የሚመለሰው?›› አለ ቶንቸክ በመገረም፡፡

ሎይዝካ ጎንተል አድርጋውና በቁጣ ስሜት ተመልክታው፤
‹‹ከወደቀ እንዴት ተመልሶ ሊመጣ ይችላል?›› አለችው፡፡
ሁሉንም ዝምታ ዋጣቸው፡፡ እዚያ ግዙፍ ጥቁር ግንብ ፊት ቆሙ፡፡ ከግዙፉ ነገር ባሻገር ምንም ማየት አልቻሉም፡፡
‹‹እኔም ወደ ጦርነት እሄዳለሁ›› ሳይጠበቅ የሰባት ዓመቱ ማቲቼ አሳወቀ፡፡ ሁኔታው ልክ ትክክለኛውን ሀሳብ እንዳገኘ ሰው ነበር።
‹‹በጣም ትንሽ እኮ ነህ!›› የአራት አመቱ ቶንቼክ ገሰጸው፡፡

ደቃቃዋና ህመምተኛዋ ሚልካ በእናቷ ግዙፍ የአንገት ልብስ ተውጣና የመንገደኛ ሻንጣ መስላ ከሆነ የጨለማው ጥግ በዚያ ስስ ቀጭን ድምፅዋ፤
‹‹ጦርነት ግን ምን ይመስላል? ማቲቼ ንገረን? ታሪኩን ንገረን?››
ማቲቼ አብራራ፡፡
‹‹ደህና፣ ጦርነት ማለት እንዲህ ነው። ሰዎች በጩቤ ይወጋጋሉ፤ በሰይፍ ይሞሻለቃሉ፤ በጠመንጃ ይገዳደላሉ። የበለጠ ሰው መውጋትሽ፣ መቆራረጥሽ ስኬት ነው፡፡ ይህን ስላደረግሽ ማንም ምንም አይልሽም፡፡ ምክንያቱም የሚደረገው እንዲያ ነው፡፡ ጦርነት ማለት ይሄ ነው፡፡››

‹‹ግን ለምንድን ነው እርስ በእርስ የሚቆራረጡት የሚሞሸላለቁት?›› ሚልካ ነበረች፡፡
‹‹ለንጉሱ ነዋ!›› አለ ማቲቼ… ሁሉም በዝምታ ተሸበቡ፡፡
በደብዛዛው ርቀት በፈዘዙ ዓይኖቻቸው ስር የሆነ ግርማ ያለው አንፀባራቂ ነገር ድንገት ብልጭ አለ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ቡራኬ ላይ እንዳሉ ሁሉ ትንፋሻቸው እንዳይሰማ ሆነው ደንዝዘው ተቀመጡ፡፡ የተጫናቸውን ከባድ ዝምታ ለመስበር በሚመስል ሁነት ማቲቼ በፍጥነት ሀሳቡን ሰብስቦ፤
‹‹እኔም ወደ ጦርነት እሄዳለሁ፡፡ ጠላቶቼን እፋለማቸዋለሁ፡፡›› አለ፡፡
‹‹ጠላት ግን ምን ይመስላል? ቀንድ አለው እንዴ?›› ድንገት ሚልካ በቀጭን ድምፅዋ ጠየቀች፡፡

‹‹አለው! አለው እንጂ ከሌለውማ ምኑን ጠላት ሆነ፡፡›› የተበሳጨ በሚመስል ጉልህ በሆነ ድምጽ ቶንቼክ መለሰላት፡፡ ሆኖም ማቲቼ ራሱ ትክክለኛውን መልስ አላወቀውም፡፡
‹‹ቀንዶች… ያለው አይመስለኝም፡፡›› በሚርበተበትና ዝግ ባለ በሚቆራረጥ ድምጽ መለሰ፡፡
‹‹እንዴት ቀንድ ሊኖረው ይችላል፡፡ ጠላት እኮ እንደኛው ሰው ነው፡፡›› ሎይዝካ ባለመቀበል ድምጽዋን አሰማች፡፡ መልሳ አሰብ አድርጋ ሌላ ሀሳብ ጨመረች፤
‹‹ብቻ ነፍስ የለውም!››

ረዘም ካለ ዝምታ በኋላ ቶንቼክ ጥያቄ አቀረበ፤
‹‹ግን ሰዎች በጦርነት ላይ እንዴት ነው የሚወድቁት? ልክ እንደዚህ ወደ ኋላ?›› አወዳደቁን አሳየ፡፡
‹‹ይገድሉታል!›› ማቲቼ አብራራ፡፡
‹‹አባቴ ጠብመንጃ ሊያመጣልኝ ቃል ገብቶልኛል፡፡››
‹‹ከወደቀ እንዴት ጠብመንጃ ሊያመጣልህ ይችላል?›› ሎይዝካ ለዘብ ባለ ቁጣ መልስ ሰጠችው፡፡
‹‹እና እንዲሞት አድርገው- ገደሉት?››
‹‹ገደሉት!››
የማይታመን ዝምታና ሀዘን በሰፊው በተበለጠጡ የታዳጊ ዓይኖቻቸው በኩል ወደ ጨለማው፣ ወደ ሆነ የማይታወቅ ነገር፣ ወደ ልብ፣ ወደ አዕምሮ አፈጠጠ፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ከጎጆው በር ውጭ አግዳሚ ወንበር ላይ ወንድና ሴት አያቶቻቸው ቁጭ ብለው ነበር፡፡

የመጨረሻዎቹ የምሽት ደማቅ ቀይ ጸዳል የተላበሱ የፀሐይ ጨረሮች ጨለምለም ባለው የግቢው መናፈሻ ቅጠላቅጠሎች ላይ አብረቅራቂ ጨረሮቻቸውን ፈንጥቀዋል፡፡ ከፈረስ ጋጣው በኩል ከሚሰማው መጎርነን የጀመረ፣ ጉርምርምታ የሚመስል፣ የተራዘመ፣ የታፈነ የመንሰቅሰቅ ልቅሶ በስተቀር ምሽቱ ፀጥ ያለ ነበር፡፡ ይሄው ልቅሶ እንስሳቱን ለመንከባከብ በሚል ወደ ጋጣው የሄደችው የልጅ እግሯ እናት የሀዘን እንጉርጉሮ መሆኑ የሚጠረጠር አይደለም፡፡ ሁለቱ እድሜ የተጫናቸው ሰዎች ልክ ከዚህ በፊት ለዓመታት፣ ለረጅም ዘመናት አድርገውት የማያውቁ ይመስል አንዱ የሌላውን እጅ አጥብቆ ይዞ ጭብጥ፣ ኩርምትና ጥግትግት ብለው፣ ምንም ሳይናገሩ እንባ በሌላቸው በተራቆቱ ዓይኖች ደንገዝገዝ ያለው ወገግታ ላይ አፍጥጠው ተቀመጡ፡፡
____ተፈፀመ___




#join
@poem06
@poem06
@poem06
"በዚህ ምድር ላይ ሦስት ዓይነት ሰዎች አሉ፤ የመጀመሪያዎቹ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉና እሱንም ያገኙ ሲሆኑ፤ ቀጣዮቹ ደግሞ እሱን በመፈለግ የሚደክሙና ነገር ግን ያላገኙት ናቸው፤ የመጨረሻው ዓይነቶች እሱን ሳይፈልጉ የሚኖሩ ነገር ግን ያገኙት ናቸው። የመጀመሪያዎቹ አዋቂና ደስተኞች ሲሆኑ ሁለተኛዎቹ ሞኞችና በመከራ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፤ በመጨረሻ የምናገኛቸው ደግሞ ደስተኞች ያልሆኑ ነገር ግን አዋቂዎች ናቸው።
አንድ ቀን ከደቀ መዝሙራቸው አንዱ ወደ ሱፊው መምህር በመምጣት፦ "መምህር ሆይ የሚያፈቅራትን ሴት ማግባት ከቻለ ሰው በላይ ደስተኛ አይገኝም?" በማለት ይጠይቃል። "አለ እንጂ፤ ያገባትን ሴት ያፈቀረ እሱ የበለጠ ደስተኛ ነው" በማለት መለሱለት። ፍቅር ከመቀበል ይልቅ በመስጠት ላይ የተመሰረተ ልምምድ መሆኑን የምታሳየን ነች።
አንድ ጠያቂ የሱፊውን መምህር ሙዛፊርን በዓይናቸው የማያዩትን ነገር "አምላኬ ነው" በማለት እንዴት ሊያመልኩት እንደቻሉ ጠየቃቸውና እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ "በበረሃ ስትሄድ የግመል ዱካ በረዥሙ ተዘርግቶ ብታይ በዚያ ቦታ ግመል ማለፉን ትጠራጠራለህን!" አሉ። ጠያቂውም "ዱካውን ካየሁማ እንዴት እጠራጠራለሁ!" አለ። መምህሩም "እንግዲያውስ የአምላካችን ዱካዎች ደግሞ እኛ ብሎም ይኸ ዓለም ነውና ለእምነቴ የግድ እሱን ማየት የለብኝም" አሉት።

ጥበብ ቅጽ ፪ ከጲላጦስ(ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)
"ቀላል፣ የተዋበ፣ ፀጥታ የሞላበት፣ ተደሳችና የተባረከ ሕይወት መኖር የምትሻ ከሆነ የአእምሮን ስግብግብ ጥያቄዎች ጣላቸውና በምትካቸው የልብህ መልሶች ተካባቸው። የአእምሮ ጠቢብነት ነገሮችን እያወሳሰበ ዕለት ተዕለት ጥያቄን መከመር ነውና የሕይወትህ ጌታ ልብህን አድርገው። "

ኦሾ💛💛💛
ሶሊያና

(ኤፍሬም ስዩም)
-----------------------------------

እኔን ከወንበር ላይ
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ
ወረቀት ላይ ወስዶኝ
……
እርሷን ካልጋችን ላይ
እንቅልፍ አሽኮርምሟት
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት ……
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ
ከደጋው ሃሳቤ በረሃ ስሰደድ
እንባን በፊደላት …
ፊደልን በቃላት…
ቃላትን በሃሳብ ወረቀት ላይ ልወልድ
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ …
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
‹‹ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋየ ላይ
አንተን በመናፈቅ በስሜት ስሰቃይ ››
ቀ…ና ብየ ባያት እውነት አለው ቃሏ
ፍም መስሏል አካሏ
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል
እኔን በመጓጓት ደሟ ጠቆጥቶ
ፍቅሯ ተሰውቶ
ስሜቷ ተጎድቶ
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ህፃን
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉራ ሲበታተን …
ካ,ልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን
ፍ...ቅ...ሬ ሶ...ሊ...ያ...ና አወራችኝ መሰል
በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ …
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰትህ አለም
የሰዎች ጥላ እንጅ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ
በሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ
እኔ ውበቱ ነኝ በፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም . . . ወዲህ እንዳትመጣ
በሌሊት ትጋትህ ሃዘን ሳይቀጣ
በ,ኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ
ከየሰው አለም የሚመሳሰሉ
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፍ
ይህ ሁሉ ቢሆንም …
የሰወችን እንባ አትፃፍ ግዴለም
የፍጥረትን ሃዘን ስለህ አትዘልቅም
እውነት አለው ብለህ ሃዘንን አታልም
((ያለቀሱም ሰዎች ሃቀኞች አይደሉም ))
ይልቅ የኔን ስሜት ያንተንም እንባዎች
ሁለቱን አሳየኝ
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ !
እኔን ብቻ ፃፈኝ !
‹‹ያልተደሰተች ሴት›› በሚል መፅሃፍህ
ዘ...ላ...ለ...ም አሻግረኝ
ዘ...ላ...ለ...ም ውሰደኝ
ዘ...ላ...ለ...ም አኑረኝ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
Track 01 16k
Soliana
#_ሶሊያና
( ኤፍሬም ስዩም )
@getem
@getem
@getem
አጀገንኩት ልቤን ተማጠንኩ ፍቅር
የትላንት ህመሜን በፍቅር ልሻገር
የሆንኩትን ቢሆንም
አይበደሉ ቢወጋም
አልኖርም ዘላለም በሽታዬን ሳስታምም

ከፍቅር ወዴት ይሸሻል ?
ተክዶ ማን ሞቷል..?
ቃል ቢታጠፍም በቃል ይታደሳል
የፍቅርም አባዜ በፍቅር ይፈወሳል ።

ማነሽ ልቤን አንኳኪ ? የዛሬ ተረኛ
ሰባራ ነውና ልቤ የትላንት ቁስለኛ
የጠዋቱ ጤዛ ከሆንሽ ቅርብ ወራጅ
አትነካክኝ አልሻም ሸንጋይን ወዳጅ
B
ተሻጋሪ ሆነሽ ተቻችሎ ከራሚ
እንከንም የለብኝ
Check out this Christmas game on Telegram 🎄

If you join, we both get gifts! Then you can decide if you wanna keep playing or not :)

Here’s the link 👇👇👇