Plus photographs
24 subscribers
166 photos
5 videos
1 file
5 links
We are plus arts voluntars creww
Download Telegram
ሰላም የፕላስ ቤተሰቦች እንዴት አረፈዳቹ የክበባት ጥምረቱ ስራ ጀምሯል ዛሬ 2/13/2014 ዓ.ም ፕላስ የኪነጥበብ እና የበጎ-አድራጎት ማህበርና ሲዳማ ሰርከስ እና የባህል ቡድን የአዲስ አመት የወዳጅነት እግር ኳስ ጨዋታ በኮንቦኒ ሜዳ ሊያደርጉ ነው።

የጨዋታውን ሁኔታ በቀጣይ እናሳውቃለን

የክበባት አንድነት ለዘላቂ ብልፅግና!!!!!!

ፕላስ አርትስ
ሀዋሳ
ጨዋታው ተጠናቋል

በፕላስ የኪነ-ጥበብ እና የበጎ-አድራጎት ማህበር እና በሲዳማ ሰርከስና የባህል ቡድን በተደረገው ጨዋታ ፕላስ በፔናሊቲ 5 ለ 3 አሸናፊ ሆኗል።

በመጀመሪያው ግማሽ 3 ለ 1 በፕላስ መሪነት የተጠናቀቀ ሲሆን ከዕረፍት መልስ ተከታታይ 2 ጎል በማግባት አቻ ሆነው ውድድሩ ተጠናቋል ።

ሁለተኛው ግማሽ ተጠናቆ ተጨማሪ በተደረገው ጨዋታ ሰርከስ ተከታታይ ሁለት ጎል ሲያስቆጥር ፕላሶች በመልስ ምት በየደቂቃው ልዩነት 3 ተከታታይ ጎሎችን አስቆጥረው እየመሩ በደቂቃዎች ማብቂያ ላይ ሰርከሶች ያገኙትን ፔናሊቲ በመጠቀም 6 አቻ ጨዋታው ተጠናቋል።

በፔናሊቲ መለያም ፕላስ 5ቱንም ኳሶች ሲጠቀምበት ሰርከሶች 2 ኳስ አባክነው 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ፕላስ አርት አሸናፊ ሆኗል።

የተደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ አንድነታችንን እሚያጠነክር የክበባት እና የማህበራትን ወዳጅነት የሚያጎለብት አባላትንም በይበልጥ የሚያቀራርብ ነው። ብለን አምነናል በቀጣይም ሁሉም ማህበራት እና ክበባት አንድነታቸውን ለከተማቸው እድገት እና ብልፅግና ያስተሳስሩታል።

plus art for peace ✌️

ፕላስ አርት
ሀዋሳ
ውቅሮ 404 ወጣቶች ዛሬ ትለዩ ነበር 🙏🙏🙏

ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ምስራቅ ክ/ከ ውቅሮ ቀበሌ ወጣቶች መስቀል በአልን ምክንያት በማድረግ ለሌሎች አርአያ በሚሆን መልኩ በ1 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ድጋፍ በማሰባሰብ ያላቸውን የሰው ፍቅር እና ተግባቦት በመጠቀም ለተማሪዎች መማሪያ ቁሳቁስ እና ለተቸገሩ ደጋፊ ለሌላቸው እናቶች 5ኪሎ ሩዝ፣5 ኪሎ ዱቄት፣2ሊትር ዘይት፣ሽንኩርት እንዲሁም ፓስታ ድጋፍ አርገዋል።

ዛሬ የውቅሮ ወጣቶች ለማህበረሰባቸው ለአከባቢያቸው ነዋሪዎች ላሳደጓቸው እናት አባቶች አለኝታ ሆነው ለቀጣዩ ትውልድ ሰው በሚታየው ሳይሆን በልቡ በሚያስበው ቅንነት እንደሚለካ አስተምረዋል።

ውቅሮ 404 በርቱልን

ፕላስ የኪነ-ጥበብ እና የበጎ-አድራጎት ማህበር
ሀዋሳ
15/01/2015 ዓ.ም