የፍልስፍና አለም The World of philosophy
255 subscribers
54 photos
7 videos
85 files
20 links
ፍልስፍናዊ ዘውግ ያላቸው መፅሐፍትና ፅሁፎች የሚቀርቡበት
Download Telegram
if you can look at all things without allowing pleasure to creep in - at a face, a bird, the colour of a sari, the beauty of a sheet of water shimmering in the sun, or anything that gives delight - if you can look at it without wanting the experience to be repeated,then there will be no pain, no fear, and therefore tremendous joy.

source  "freedom from the known"
What is fear?
how does it arise?
what do we mean by word fear by it self?
Ask yourself what fear is not what you afraid of.
የፍልስፍና አለም The World of philosophy
What is fear? how does it arise? what do we mean by word fear by it self? Ask yourself what fear is not what you afraid of.
The first thing to ask ourselves is what is fear and how does it arise? What do we mean by the word fear itself? I am 
asking myself what is fear not what I am afraid of. 

I lead a certain kind of life; I think in a certain pattern; I have certain beliefs and dogmas and I don't want those patterns of existence to be disturbed because I have my roots in them. I don't want them to be disturbed because the disturbance produces a state of unknowing and I dislike that. If I am torn away from everything I know and believe, I want to be reasonably certain of the state of things to which I am going. So the brain cells have created a pattern and those brain cells refuse to create another pattern which may be uncertain. The movement fromcertainty to uncertainty is 
what I call fear. 

At the actual moment as I am sitting here I am not afraid; I am not afraid in the present, nothing is happening to me, nobody is threatening me or taking anything away from me. But beyond the actual moment there is a deeper layer in the mind which is consciously or unconsciously thinking of whatmight happen in the future or worrying that something from the past may overtake me. So I am afraid of the past and of the future. I have divided time into the past and the future. Thought steps in, says, Be careful it does not happen again', or Be prepared for the future. The future may be dangerous for you. You have got something now but you may lose it. You may die tomorrow, your wife may run away, you may lose your job. You may never become famous. You may be lonely. You want to be quite sure of tomorrow.'

Source "freedom from the know"
Relationship between human beings is based on the image forming, defensive mechanism. In all our relationships each one of us builds an image about the other and these two images have relationship, not the human beings themselves. The wife has an image about the husband - perhaps not consciously but nevertheless it is there - and the husband has an image about the wife. One has an image about one's country and about oneself, and we are always strengthening these images by adding more and
more to them. And it is these images which have relationship. The actual relationship between two human beings or between many human beings completely end when there is the formation of images.

Relationship based on these images can obviously never bring about peace in the relationship because the images are fictitious and one cannot live in an abstraction. And yet that is what we are all doing: living in ideas, in theories, in symbols, in images which we have created about ourselves and others and which are not realities at all. All our relationships, whether they be with property, ideas or people, are based essentially on this image-forming, and hence there is always conflict.
We don't know how to live, therefore we don't
know how to die.

As long as we are frightened of life we shall be
frightened of death.

Krishnamurti
የህይወት ፈተናዎች

ያጋጠሙህ ውጣ ውረዶች እውነተኛ ጠላቶች አይደሉም፣ ነገር ግን ፍፁም እንድትሆኑ ይረዱሃል።
ሥር የሰደዱህ ይመስላል፣ ግን እነሱን በመታገል ነው ሥርህ እየጠነከረ የሚሄደው።

አንድ ዛፍ ግምት ውስጥ ያስገቡ ዛፉን ወደ ክፍሉ ማምጣት እና ነፋሱ በማይደርስበት መንገድ ሊከላከሉት ይችላሉ:: አውሎ ነፋሶች ከቤት ውጭ ሲነፉሱ የእርስዎ ዛፍ በአደጋ ላይ አይደለም ነገር ግን ምንም ተጨማሪ ፈተናዎች አይኖሩም እና ሁሉም ነገር የተጠበቀ ነው::

ዛፉን በሞቃት ክፍል ውስጥ ማስቀመጥ ይችላሉ ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቅጠሎቹ ቀለም ያጣሉ እና አረንጓዴ አይሆኑም:: በዛፉ ውስጥ አንድ ነገር ይሞታል, ምክንያቱም ህይወትን የሚቀርጸው በፈተና እና በትግል ነው::
አውሎ ነፋሶች እንዳይደርሱባቸው እና እንዳያጠፋቸው ስርዎን ወደ ጥልቅ ትልካላችሁ።

ፀሀይ በጣም ሞቃታማ እና የዛፎቹን ቅጠሎች የሚያቃጥል ይመስላል, ነገር ግን ዛፎቹ እራሳቸውን ከፀሀይ ሙቀት ለመጠበቅ ብዙ ውሃ ይወስዳሉ በዚህም ምክንያት አረንጓዴ እና አረንጓዴ ይሆናሉ::
ከተፈጥሮ ኃይሎች ጋር በመዋጋት ዛፉ ልዩ ስሜት ላይ ይደርሳል.
ነፍስም የምታድገው በትግል ብቻ ነው። ሁሉም ነገር በጣም ቀላል እና ቀላል ከሆነ ይጠወልጋሉ እና ደካማ ይሆናሉ::
በተደጋጋሚ ይወድቃል; ምክንያቱም ሁሉም ነገር ቀላል በሚሆንበት ጊዜ ፍጽምና አያስፈልግም:: ስለዚህ ችግር በሚፈጠርበት ጊዜ በድፍረት ይጋፈጡ::
እኛ  ማታለያ ፣ ማረሳሽያ ፣ ማፅናኛ ነገርን እንወዳለን። መከራ ያለበትን ,ጭንቀት , ውጥረት , ጥበት መዘንጋት እንፈልጋለን ።

ለዚህም ነው። አለም ላይ ትልልቅ የሚባሉት ኢንዱስትሪዎች ( መጠጥ፣ ፊልም ፣ ሙዚቃ፣ ጊም ፣  ኳስ ...እንዲሁም. የሀይማኖት ተቋማት ) ትርፍማ የሆኑበት ትልቁ ስራቸው ይህ ነው። ማረሳሳት

አብዝሀኛው ለምን እንደሚሰቃይ ለምን እንደሚጨነቅ ለምን እንደሚፈራ አያውቅም ። ለሱ normal ነው (የዕለት ተዕለት መጨናነቁ ፣ መረበሹ ፣ ፍርሀቱ፣ ግጭቱ፣ ውጥረቱ ፣ ትርምሱ ) ለነዚህ ነገሮች እንዴት መቆጫ ማበጅት እንዳለበት አያውቅም ። ከዛ ይልቅ  ለአፍታ መዘንጋት፣ ማምለጥን እንዲመርጥ ተደርጎ  ተሰናድቱል። ከዛ ውጭ ምንም አይነት ምርጫ እንደሌለው እንዲያምን ተደርጎ ተቀርጿል።


ውዶች እኔ ግን....
ምርጫ አላችሁ መምረጥም ትችላላችሁ
እላችኃለሁ። አሁንን !! ምረጡ
[ ካለ መረጋጋት መማር ]
~ኦሾ
ሰላም ቤተሰቦቼ
ህይወትን እያጣጣማችሁ እየመረመራችሁ ነው?
ከሆነ ደስ ይላል። ግን ለምን? ለምን መመርመር አስፈለገ ለምንስ ማጣጣም አስፈለገ? መመርመር የተሻለና ውብ ህይወት እንድትኖሩ ስለሚረዳችሁ? ለምን የተሻለ ህይወት አስፈለገ? ለምን ውብ የሆነ ነገር አስፈለገ?

ለማንኛውም ሁሉንም መጠየቅ አትርሱ ብዙ ትክክል ያልሆኑ አመለካከቶች ባህሎች የህይወት ልምድ እንዲፈርስ ከፈለጋችሁ መጠየቅ መቀጠልን አትርሱ

ስለምትበላው ምግብ ጠይቅ
ስለጓደኛ ጠይቅ
ስለማንነትህ ጠይቅ
ስለጊዜ ጠይቅ
ስለህይወት ጠይቅ
ስለትዳር ጠይቅ
ስለነገሮች ጅማሮና አፈፃፀም ጠይቅ
ስለትንሻ ጠይቅ ስለትልቁም ጠይቅ

በዙሪያ ያለውን ነገር ምንም ሳታውቅ ለምን ትኖራለህ

ማወቅ ግን አስፈላጊ ነው?
መኖር ግን አስፈላጊ ነው?
ግን እየኖርን ነው?
በህልም አለም ብንሆንስ?
ሁሉም ነገር እኛ አዕምሮ ውስጥ ቢሆንስ?


መልካም የጥያቄ ህይወት ይሁንላችሁ።
ከመኝታህ እንደነቃህ ከዚህ በፊት በአዕምሮህ ውስጥ ስታስባቸው የነበሩ ነገሮች በሙሉ በመኝታ ክፍልህ ግድግዳ ዙሪያ መታየት ይጀምራሉ እናም ሀሳብህ በሌሎች ዘንድ በግልፅ መታየት መጀመሩ ድንጋጤን ይፈጥርብሀል

ከመኝታ ክፍልህ ስትወጣ ሌሎችም እንዳንተ ሀሳባቸው ከፊት ለፊት ባለ ነገር ላይ ተንፀባርቆ ይታያል እና ሌላውም እንዳንተ ተደናግጧል በሂደት ግን ድንጋጤው እየተለመደ ይመጣል

ከንግዲህ በኃላ በውስጥ ሰው ሳያይህ ማሰብ ማስታወስ ቀርቷል የራስህ ክፍል ገብተህ ካልሆነ በቀር

ከመኝታ ስትነቃ የክፍልህ ግድግዳ በስክሪን መልክ ሆኖ ሀሳቦችህን በፎልደር በፎልደር አድርጎ ይደረድርልሀል እናም ታገላብጣለህ ሁሉም ፎልደሮች ራሳቸውን በሚገባ ያስተዋውቁሀል(advertise ያደርጋሉ) ምርጫው ግን ያንተ ነው። ስትመርጥ ግን ለመረጥከው ፎልደር(የትውስታ ወይም ሀሳብ አይነት) ከህይወትህ ቀንሰህ ትከፍላለህ።

በቃ ተኝተህ መመልከት ነው፣ በመኝታ ክፍልህ ብቻ አይደለም በሄድክበት ቦታ ሁሉ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሁነህ ከህይወትህ እየከፈልክ ማየት ትችላለህ።

#አንተ_አዕምሮህን_አይደለህም
Channel name was changed to «የፍልስፍና አለም The World of philosophy»
መንጋነትን ተፀየፍ

ሲግመን ፍሮይድ፣ አርኪመድስ፣ ኒቼ፣ ቻርለስ ዳርዊን፣ ጋሊሊዮ፣ ሶቅራጥስ፣ ቡድሃ፣ ቶማስ ኤዲሰን፣ ቫን ጎ፣ የእኛው ሀገር ፈላስፋ ዘርዓያዕቆብ ... ሌሎችም ሌሎችም በየስርቻው በየጉራንጉሩ በእኛም ሀገር ጭምር አሉልህ፡፡ አብዛኞቹ በዘመናቸው የተወገዙ ወይ አድማጭ ያጡ  ነበሩ፡፡ ዛሬ እግርህን በጀብደኝነት አንፈራጠህ ቆመህ ሰልፊ (ራስ በራስ ፎቶ) የምትነሳበትን ስልጣኔ የመሰረቱት ግን እኔው ዘመንን የቀደሙ የትናንት መሰሎችህ ነበሩ፡፡ ካምቤል ኢጁጋርጁክ የተሰኘ የካናዳ ካሪቦ ኢስኪሞ ጎሳዎችን መንፈሳዊ መሪ አባባል ይጠቅሳል፡፡ ኢጁጋርጁክ እንዲህ አለ....

"እውነተኛ ጥበብ ከሰው ልጅ ተሰውራ ትገኛለች፡፡ በታላቅ ሕመምና የብቻ አርምሞ ካልሆነ የሚደረስባት አይደለችም፡፡ ፈተናን መጋፈጥና ብቻነት ግን ወደዚህ ድብቅ ዕውቀት መገኛ ስውር ቦታ አዕምሮን ይመራሉ፡፡"

የምንኖረው ግን በጅምላ በሚመለክበት፣ በጅምላ በሚወገዝበት፣ በጅምላ በሚኮነንበት፣ ሽያጩም፣ ዘረፋውም፣ ግድያውም፣ ቀብሩም ጅምላ ሆኖ ተነጥሎ መቆም ወንጀል በሆነበት ማኅበረሰብ ውስጥ ነው፡፡

እናስ በዚህ ሂደት ከመንጋው የመነጠል፣ ከዘመን የመጣላት፣ ከትውልድ የመኳረፍ አዝማሚያ የሌለው ጠቢብ የመንጋውን መፈክር በውብ ቃላት ሸላልሞ ከማተም በስተቀር ረብ ያለው ሀቲት ሊወጣው ይችላልን? ምንኖረውን የሆነውን ለመጻፍ፣ ለመዝፈን፣ ለማቅለም፣ ለማሰማመር ብዙ መጣር አርቲስት መሆን ያስፈልጋል እንዴ? በየትኛውም ዘመን ተወለድ (በእኛም ዘመን ይሁን) ብዙዎች ከሚስማሙበት ከተለየህ፣ ብዙዎች የሚያደንቁት ካልመሰጠህ፣ ብዙዎች በጅምላ የሚጠሉትን ካልጠላህ ውግዘት ውርደት፣ ግዞት ይደርስብሃል፡፡ ምክንያቱም አንተ የሚቀጥለው ትውልድ አባል ነህ፡፡

የእኛን ነገር እንኳን ተውት፣ ተውት አዲስ አተያይ ማመንጨቱን፣ የሚቀጥለውን ትውልድ ትልም የማርቀቅ ቅብጠቱን ተውት... ተውት፡፡ እኛ ከዘመንና ከትውልድ መኳረፍ ያቃተን፣ ዘልማዳዊ የነተበ ሕይወት የማይሰለቸን፣ አንሰን አንሰን የምናሳንስ፣ በአጥንት እንደሚጣሉ የተራቡ ውሾች እርስ በእርስ የምንናከስ ሕዝቦች ነን፡፡

ለብቻ መቆም መቻል ግን ውበት ነው፡፡ ፅናት ነው፡፡ ጥንካሬ ነው፡፡ ለብቻ መቆም(solitude) መሟላት እንጂ መነጠል (isolate) አይደለም፡፡ መነጠል ብሎ ነገር የለም፡፡ የምትነጠለው ጉልህ ስብዕና አጥተህ ተጀምለህ  የተቆጠርክ ዕለት ነው፡፡ እንደ ጉሬዛ ከዛፍ ዛፍ እየዘለልክ ብትኖር እንኳን ከሰው እንጂ ከምልዓተ ዓለሙ መነጠል አትችልም፡፡ ማንም ሁን ከየትም ና አንተ የምልዓተ ዓለሙ የልብ ትርታ ነህ። አንተ አንተን መሆን ከቻልክ ያለ አንተ ዓለሙ ይጎድላል፡፡

ተደርቦ ተጀምሎ መቆጠርን ተፀየፍ፡፡ በስብዕናህ ራስህን ችለህ ስትር ብለህ መቆምን ቻልበት፡፡ ሰዎችን በሙሉ ልብህ ተቀበል፡፡ ለመሸኘትም ግን ምንጊዜም ዝግጁ ሁን፡፡ በጊዜ ውስጥ አስቀድሞ ያልሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ መወለድህም፣ መሸለም መጋዝም በጊዜ ውስጥ ቀድሞውኑ የታሰበ ነው፡፡ ይኼንን ማሰብ መቀበል ስለማትፈልግ ዘወትር ለእያንዳንዷ የሕይወት እርምጃ እንግዳ ትሆናለህ፡፡ ቀላል እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡

ይኼንን የምነግርህ እኔ እንኳን ዘወትር እንደ ተማሪ ነኝ፡፡ ከሰው ልትደበቅ ትችላለህ፡፡ ማንም ግን ከራሱ መደበቅ አይችልም፡፡ በራስህ ምላስ መቅመስ ካልቻልክ አንተ ጣዕምን አታውቃትም፡፡ ብቻህን መቆም ከቻልክ አንተ ነፃ ወጥተሃል፣ ክንፎችህን ሰርተሃል፡፡ ነፃ በወጣህ ጊዜ ሕይወትን በምልዓት ትኖራታለህ፡፡ ሁልጊዜ ከራሳቸው መታረቅ ተስኗቸው ቀላሉን መንገድ በመሻት እንደሚማስኑ ደካሞች አትሆንም፡፡

ግለሰቦች ሲሳሳቱ ስህተቱ ከራሳቸው ወይም በጣም ከጥቂቶች የተሻገረ ጥፋትን አያስከትልም፡፡ መንጋው ከተሳሳተ ግን አያድርስ ነው፡፡ የመንጋው፣ የጅምላው ስህተት የሚያደርሰውን የጥፋት መጠን ለማወቅ ሩዋንዳን መጥቀሱ ብቻ ይበቃል፡፡ መንጋው እንዲያውም ልክ ሆኖ አያውቅም ማለት ይቻላል፡፡ አንተ የዚህ የጅምላ ስህተት አካል መሆንን ተጸየፍ፡፡


አስቀድሜ እንዳወጋሁህ ዛሬ ዘመናዊው ዓለም የደረሰበትን የኑረት ቅኝት የቀረጹት ሺኅ እንኳን የማይሞሉ በራሳቸው መሻት ወይም በመንጋው ግፊት ተገልለው ማሰብ የቻሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ሌላው ግብስብሱ ለድምቀት ለጭብጫባ ብቻ የሚፈለግ የቤተሙከራ አይጥ ሆኖ አልፏል፡፡ ያልፍማል፡፡ አንተም በፊናህ ጥቂት ስንኝ ቋጥረህ በብዙ የምታቧትር፣ በርካታ የግል አድናቂዎችን ቤት ለቤት እየዞርክ ለመፍጠር የምትማስን ሆነህ ባየሁ ጊዜ ግን አዘንኩልህ፡፡ አንተ ግን ከሰው ይልቅ ሰዎች በልጠውብህ ተቧድነህ ባሩድ ስታሸት ስትወራወር ባየሁህ ጊዜ አነባሁ፡፡

አንተ እኮ አንተ ነህ፡፡ በሰዎች መካከል ስትሆን ደቃቅ አሸዋ ላይ እንደወደቀች አንዲት የጤፍ ዘር ታንሣለህ፡፡ ምርጫህ በሌሎች ምርጫ ይወሰናል፡፡ ድምጽህ በሌሎች ጩኸት ይሸፈናል፡፡ ቁጣህ በሌሎች ግድየለሾች ፌዝ ይከለላል፡፡ ሕማም፣ ሕመምህ በሌሎች ለዛየለሾች ሁካታ ይጨፈለቃል...

ግለሰባዊነት ይለምልም!

ምንጭ-ከባዶ ላይ መዝገን
ደራሲ- ያዕቆብ ብርሀኑ
ሰው ከእንስሳ በምን ይለያል?

ምንጭ ፦ የፍልስፍና አፅናፍ
ፀሀፊ    ፦ አለማየሁ ገላጋይ

የሰው ልጅ ከእንስሳት ሁሉ የሚለይበት መሰረታዊ አፈጣጠር አለው የሚለውን አመለካከት መጠራጠር የጀመሩት አንዳንድ የቅርብ ጊዜ ፈላስፎች ናቸው፡፡ ከፕሌቶ አንስቶ እስከ አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተዋረድ የተዘረጋ የምዕራባውያን የእሳቤ ባህል ውስጥ ሰውና ሰው ብቻ ምክንያታዊ እንስሳ ነው በሚል ተደምድሞ ቆይቷል፡፡ ይሄ ሰውን ከእንስሳት ሁሉ የተለየ አድርጐ የሚያስቀምጠው ፍልስፍና ሰው ብቻ በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን ከሚያስተምረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር የተስማማ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡

በእንግሊዛዊው የተፈጥሮ ሳይንስ ሊቅ ቻርልስ ዳርዊን ዘመን ተቃራኒው አመለካከት ብቅ ማለት ጀመረ፡፡ አመለካከቱ ከሳይንሱ ቤተሰብ ወጥቶ እስከ ልሂቃኑ ድረስ የተዛመተ ነበር᎓᎓ የዳርዊን አስተምህሮት ንድፈ ሀሳብ አንተም እንደምታውቀው የሰው ልጅ እና የዝንጀሮ የዘር ግንድ አንድ ነው ብሎ ደምድሟል፡፡ ድምዳሜው ወዴት እንደሚያመራ ግልፅ ነው፡፡ የሰው ልጅ ስር መሰረታዊ የዝግመተ ለውጥ ምርምር ሰው ከአጥቢ እንሰሳት ሁሉ የሚለየው በአስተሳሰብ ደረጃው ብቻ እንደሆነ ያስተምራል፡፡ የዝግመተ ለውጥ ተመራማሪዎቹ ሰው ብቻ ምክንያታዊ እንስሳ ነው ለሚለው የቀድሞ ድምዳሜ ሌላ የምርምር መዳረሻቸውን ይዘው ብቅ ብለዋል፡፡ በሰውና በተቀሩት እንስሳት መካከል ያለው አስተሳሰብ አንድ ነው፡፡ ሰው ግን ላቅ ያለ የአስተሳሰብ ደረጃ አለው ይላሉ፡፡

የሰው ልጅ ሌሎች እንሰሳት የሌላቸው ኃይል እንዳለው ማረጋገጫ የሚሆነን አንዳንድ ምሳሌዎችን መጥቀስ እንችላለን፡፡ የሰው ልጅ በአግባቡ የሚያከናውናቸው እንስሳት ግን ጨርሶ የማይሞክሩት ነገር አለ፡፡ እሱም
አንዳንድ የሚያበጃጃቸው ነገሮቹ ናቸው፡፡

እርግጥ ነው ንቦች ? ፎ እንደሚሰሩ አውቃለሁ:: ወፎች ጎጆአቸውን፤ ፍልፈሎች ጉድጓዳቸውን ያበጃሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ የእንስሳቱ ተግባር በደመነፍሳዊ ግፊት የሚከናወኑ ናቸው᎓᎓ ወፎች ሁሉ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተቀባበሉ የሚሰሩት ያንኑ ተመሳሳይ ጎጆ ነው። ይሄ የሚያሳየን የወፍ ጐጆ የደመነፍስ ግፊት እንጂ በአስተሳሰብ መዳበርና በነፃነት የሚገኝ የጥበብ ውጤት አለመሆኑን ነው። ቤት መገንባት፣ ድልድይ ማበጀትና በመሳሰሉት ተግባራት ላይ የሰው ልጆች የፈጠራ ችሎታቸውን ያውላሉ፤ አንዱን ከሌላኛው ይመርጣሉ፤ በዚህም ሌሎች እንሰሳት የሌላቸው ትክክለኛ የጥበብ ተስዕጦ ባለቤት እንደሆኑ ይመሰክራሉ፡፡

የሰው ልጅ ብቻ ነው የማምረቻ ማሽኖችን የሚሰራው፡፡ ልብ በል ሰው የሚፈልገውን ነገር የሚሰራት ማምረቻ። ሌሎቹ እንሰሳት ባገኙት መሳሪያ ይጠቀሙ እንዳደሆን ነው እንጂ ጥሬ እቃውን ወዳለቀለት ምርት እየቀየረ በፍጥነት የሚስራ ሌላ ማሽን አይሰሩም፡፡ ይህም ሰውን ከሌሎች እንሰሳት ሁሉ የበለጠ ነገሮችን የማበጃጀት ልዩ ችሎታ እንዳለው የሚያመላክተን ምሳሌ ነው፡፡

እንስሳት ምክንያታዊነት እንዳላቸውም ጠቆም አድርገሃል፡፡ እኔ እንደሚገባኝ የተሻለ ትክክል የምንሆነው እንሰሳት ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ ከችግር የሚወጡበት ተፈጥሯዊ ግፊት እንዳላቸው የተናገርን እንደሆነ ነው፡፡ ወይም የሚፈልጉትን ለማግኘት እንደዚያው የተፈጥሯዊ ግፊት ዘዴ እንደሚዘይዱ ያሰብን እንደሆነ ነው፡፡ የእንስሳትን «አስተሳሰብ» ሁሉ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ልናየው ይገባል። የትኛውም እንስሳ ለማሰብ ቁጭ አይልም፡፡ ፈላስፎች ሆነ የሂሳብ ሊቶች የሚያከናውኑት ነገር ሁሉ ለህይወት ከሚያስፈልግ የተፈጥሮ ደመነፍሳዊ ግፊት ነፃ ነው፡፡

የሰው ልጅ አስተሳሰብ በዙሪያ ጥምጥም የሚከናወን ግራ ፈትልና ቋንቋ የተቀላቀለበት መሆኑ እንሰሳት ከሚጠቀሙበት ችግር መፍቻ የተለየ ያደርገዋል። በእርግጥ እንሰሳትም ስሜታቸውን የሚገላለጡበት የእርስ በእርስ መግባቢያ ድምፅ ያወጣሉ፡፡ ነገር ግን በሃሳብ መካፈል ደረጃ ተግባቦት ያላቸው እንስሳት የሉም፡፡ የነገሮችን ትክክለኛነት ለመተማመን የእሰጥ-አገባ ሙግት የሚገጥሙ እንሰሳት እስካሁን አልታዩም። ይሄንን ለማድረግ የሚችለው አመክኑያዊ እንስሳ ሰው ብቻ ነው::

እንዲህ ያሉ ብዙ መረጃዎችን መስጠት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሰው ከእንስሳት ሁሉ በላይ በተፈጥሮ የተቀባ መሆኑን የሚያመላክት አንድ ማስረጃ አቅርቤ ነገሬን በዚሁ በአቅብ ነው የመረጥኩት፡፡

በታሪካዊ ሂደት እራሱን እያጐለበተና ልምዱን እያዳበረ የመጣ እንስሳ ሰው ብቻ ነው᎓᎓ የተቀሩት እንስሳት በተፈጥሮ ሂደት በመቶ ሺህ ትውልድ ውስጥ የራሳቸውን የአካል ለውጥ አግኝተው ይሆን ይሆናል እንጂ የታሪካዊ ሂደት ለውጥ ተጠቃሚዎች አይደሉም፡፡ ምክንያቱም በደመነፍስ ከሚወርሱት የአኗኗር ዘዬ ውጭ በትውልድ ቅብብል እያሳደጉ የመጡት እውቀት የላቸውም፡፡ ሰውን ያየን እንደሆን ልምዶቹንና ባህሎቹን ከአንዱ ትውልድ ወደሌላው በማሸጋገር ሀሳቦችንና ተቋማቶቹን በማሻሻል እያደረጀ እዚህ እንደደረሰ ከታሪኩ እንረዳለን፡፡

በእኔ ሐሳብ የሰው ልጅ በአፈጣጠሩ እንደማንኛውም እንሰሳ ይሁን እንጂ በምክንያታዊነቱ ግን ከተርታዎቹ እንስሳት እራሱን ነጥሎ ልዩ ቦታ የተቀመጠ አስደናቂ ፍጡር ነው፡፡ በዚህና በሌላ ምክንያቶች የዳርዊንን የሰው ልጅ ዝግመተለውጣዊ ንድፈ ሐሳብ የምናጣጥልበትን አቋም እናገኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ስለንድፈ ሐሳቦች መያዝ ያለብን አንድ እውነታ አለ፡፡ ንድፈ ሀሳቦች ሐቅን ፈልፍሎ ለማውጫ እንጂ ሐቅን ለንድፈሐሳብ ማዳበሪያ ብቻ መጠቀም እንደሌለብን ነውና፡፡