This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንድን ሰው መጥቀም ባትችል አትጉዳው!!
•ማስደሰት ባትችል በአንተ ምክንያት እዲያዝን አታድርገው!!
በችግርጊዜ ከጎኑ መቆም ባትችል በመቸገሩ አትደሠት!!
መልካምነገር በማግኘቱ ባትደሠት ምቀኛ አትሁነው!!
መልካምስራውን ለሠወች ማወደስ ባትችል አታጠጥለው!!
@phillosophy @phillosophy
•ማስደሰት ባትችል በአንተ ምክንያት እዲያዝን አታድርገው!!
በችግርጊዜ ከጎኑ መቆም ባትችል በመቸገሩ አትደሠት!!
መልካምነገር በማግኘቱ ባትደሠት ምቀኛ አትሁነው!!
መልካምስራውን ለሠወች ማወደስ ባትችል አታጠጥለው!!
@phillosophy @phillosophy
የማይቆም ወንዝ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል፤ በጉልበቱ ሳይሆን በጽናቱ!
.......... ................ ........... .......
የተፈጥሮአድናቂ ከሆነን የወንዝን ውበት በህሊናችን ለመሳል ባልተቸገርን። ወንዝ ውብት ብቻም ሳይሆን ከሰው ልጅ ህይወት ጋርም ጥልቅ ግንኙነት አለው። ወንዝ የብዙ ስልጣኔዎች ምንጭ፤ የስነጽሁፎች መጠንሰሻ፤ የፍቅር መጎንጫ ሆኖ በየስነጽሁፉ ተከትቦ እናገኘዋለን። የሰው ልጅ ህይወት በወንዝ ተመስሎ ሲታይ የኑሮዋችን ፍሰት እንዴት እንደሆነ በሶስተኛ አይን ያስመለክተናል።
ስለወንዝ የተለያዩ ድንቅ አባባሎች ተነግረዋል። ለዛሬ መነቃቂያ የመረጥኩት “የማይቆም ወንዝ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል” የሚልውን ነው። አስቡት ከድንጋይ እና ከውሃ የቱ ይጠነክራል?በውሃ የተቦረቦሩ ስንት የድንጋይ አለቶችን አይተናል?ውሃ በምን አቅሙ ድንጋይን ያህል ነገር በስቶ ያልፋል?እውነት ነው ውሃ ድንጋይን የመሰንጠቅ ሃይል አለው። ከድንጋዩ በርትቶ ወይም ከድንጋዩ በላይ ጉልበት ኖሮት ሳይሆን ከድንጋዩ የበለጠ ጽናት ስላለው ብቻ ነው።
ህይወታችንም ልከ እንደወንዝ ነው፤ በየመሃሉ የሚገጥሙን አለቶች እና ድንጋዩች ምንም እንኳን ሊታለፉ የማይችሉ ቢመስሉም ያለማቋረጥ ከተጋፈጥናቸው እና ጉዞዋችንን ካልገታን ግን እየተቦረቦሩ መንገድ ይከፍቱልናል። ብዙዏቻችን ግን የወንዙን ያህል ጽናት የለንም ፤ በትንሹም በትልቁም እንቅፋት ጉዞዋችንን እንገታለን። የስኬት ትልቁ ቁልፍ ያመንበትን ነገር ያለማቋረጥ መከወን ነው። ሁላችንም አላማ እና ግብ ሊኖረን ይችላል፤ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው ግባቸውን አንግበው እረጅም መንገድ የሚጓዙት። እነሱም ጽናት ያላቸው ብርቱዎች ብቻ።
አብዛኛዎቻችን አንድ በር ሲዘጋብን ሁለተኛውን ለማንኳኳት እንፈራለን። በዚህ ምድር ላይ ያለተቃውሞ እና ውድቀት ያሰበበት ስፍራ የደረሰ አንድም ሰው የለም። አሁን ከፍ ብለው የምናያቸው ሰዎች ሲጀምሩ እንደሁላችንም ሰዎች ተራ ነበሩ። ዛሬ ብዙዎች የሚያጨበጭቡላቸው ሰዎች ሀ ብለው ደረጃውን መውጣት ሲጀምሩ ከራሳቸው በቀር ያጨበጨበላቸው ሰው አልነበረም። አንድን ነገር ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብንም፤ ትልቅ ለመሆን ግን መጀመር መቻል ግዴታችን ነው። የዛሬው ስራችን የብዙ ሰዎችን አይን አልሳበም ማለት የነገ ስራችንም እንደዛው ነው ማለት አይደለም። ህልማችን ለሌሎችም ሰዎች እንዲታያቸው መጠበቅ ትልቁ እንቅፋት ነው፤ አንዳንዴ የስኬትን ጎዳና ስትመርጥ ግብህ ለሌሎች አይታያቸውም። ሌሎችን ለማሳመን መጣሩ ጊዜህን እንዳያባክንብህ ተጠንቀቅ።
ከላይ እንዳልኩት ወንዝ ድንጋይን ያህል ነገር አልፎ መጓዝ የሚችለው ከድንጋዩ የበለጥ ጉልበት ኖሮት ሳይሆን፤ የማይበገር ጽናት ስላለው ነው። አዎ በመንገዳችን ብዙ አለቶች ይኖራሉ፤ ብዙ በሮች ይዘጉብናል ብዙ እንቅፋቶች ይፈጠራሉ። ምንም እንኳን የማይታለፉ ቢመስሉም፤ ተስፋ ባለመቁረጥ እና ጉዞን ባለማቆም የማይታለፍ ምንም እክል የለም።
ሌላ ጽናትን በተመለከተ የተረተ አንድ ተረት ላካፍላችሁ እና ጽሁፌን ልቋጭ። ሁለት ዝንቦች መውጫው ጠባብ የሆነ የወተት ጠርሙስ ውስጥ ይሰምጣሉ። አንደኛው ዝንብ ትንሽ ከተንፈራገጠ በኋላ መውጣት ሲያቅተው ተስፋ ቆርጦ ሰምጦ ሞተ።ሁለተኛው ዝንብ ግን ያለማቋረጥ ወተቱ ላይ ሲንፈራገጥ፤ ብዙ ከመንፈራገጡ የተነሳ ወተቱን ንጦ ወደቂቤነት ለወጠው። ቂቤው ላይ ቆሞም ከጠርሙሱ ለመወጣት ቻለ። ተረቱ ቀልድ ቢመስልም እወነታ አለው። ያለጽናት ስኬት የለም። ጽናት የሚፈተነው ደግሞ ምንም እንኳን የሚያበረታታን ብናጣም ጉዞዋችንን መቀጠል ስንችል ነው።
ያለጭብጨባ የሚጽፉ፤ ያለዝና የሚዘፍኑ፤ ያልደሞዝ የሚያገለግሉ፤ ያለሽልማት የሚለፉ ጽኑዏች ናቸው የነገ ስኬታማ ሰዎች። ዛሬ ያለንበት ቦታ የነገም ቦታችን ነው ማለት አይደለም፨ እናስታውስ አንድን ነገር ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብንም፤ ትልቅ ለመሆን ግን መጀመር መቻል ግዴታችን ነው
Join us
👇👇
@phillosophy @phillosophy
ለሃሳብ አስተያየታችሁ ደሞ
👇👇👇
@SSR60 ይጠቀሙ

ዛሬ እኛው እንፈላሰፍ እስኪ...
🤔መማር ያለንን ለማውጣት ወይስ ባለን ላይ ለመጨመር..?
ሶቅራጥስእንዲህ ብሎ ነበር...
"እኔ ማንንም ስለምንም ማስተማር አልችልም!እኔ ማድረግ የምችለው ማሰብ እንደሚችሉ ማሳየት ነው ። "
🗒 እኛ የምንማረውም ወይም መማር ያለብንስ ማሰብ እንደምንችል ለማወቅ አይመስላችሁም?እኛ የምንማረው የሆነ የምንወደውን ሰው ለመምሰል ወይም ለመተካት ከሆነ ወይም የመምራኖቻችንን አሳብ እንደወረደ የምንቀበል ከሆነ እኛ የነሱን አስተሳሰብ እንደወረደ የምንሸከም የአስተሳሰብ ወዛደሮች እንጂ ተማሪዎች መባል ይገባናል ብዬ አልልም ።
🗒 ቢላ የሚሞረደው ቅድሚያ የነበረውን ስለት ለማውጣት እንጂ አዲስ ስለት ለመስጠት አይደለም ። የትምህርት አላማውም አእምሮን ለመሳል እና ንቁ ለማድረግ እንጂ የሰውን አስተሳሰን እና እይታ እኛ ላይ ለመጫን መሆን የለበትም ።
እስቲ የናንተንም ሃሳብ አካፍሉን..
ለምንእንማራለን...
፨ያለንን ለማውጣት ????
፨ባለን ላይ ለመጨመር ???
ወይስ
፨ በሌላ ምክንያት.. ???
ለሃሳብአስታየት
👇👇👇
@SSR60
ወይም
@abdu23
ይጠቀሙ !!!!
📝የናንተን አስታየቶች ሌሎችም ይማሩባቸው ዘንድ ቻናሉ ላይ ሥለምንለቃቸው በአማርኛ ብትፅፉልን ስንል በማክበር እንጠይቃለን ።
@phillosophy @phillosophy
.
Copy direct from @ከፍልስፍና አለም 🙏🙏

ለመወደድ ብለህ አታስመስል ምክንያቱም ማስመሰል አስፈላጊ ሆኖ የሚገኘው አንዴ ብቻ ነው ። ከዛ ቦሃላ ይነቃብሀል ። አንተ አስመስለህ እንደምትናገረው ሁሉ ሌላውም የሚሰማህ እያስመሰለ ነው፡፡ ሰዎች እንዲያከብሩህ አትኮፈስ ። ሰዎች ሊያከብሩህ የሚችሉት አንተ እነሱን ባከበርካቸው ደረጃ ነው። ክብር አስፈላጊ ከሆነ ለሌሎች ክብርን መስጠት የአስፈላጊነት ስሜት መፍጠሪያ መንገድ ነው።
ሰዎች እንዲያዝኑልህ ችግርህን አጉልተህ አታሳይ !!ይሄ ያስፈላጊነት ስሜት አይፈጥርም ። የሚፈጥረው አንተ እነሱን እንደምትፈልጋቸው የሚያሳይ ያለመፈለግ ስሜት ነው ።
ሰዎች እንዲያዝኑልህ ችግር ማጉላት ማለት በዚህ ጉድለት ፈላጊ ስላጣሁ እናንተ ፈልጉኝ አይነት ልመና ነው። ሰዎች እንዲያከብሩህ ብቃትህም ከመጠን አሳልፈህ እንዲያውቁ አታድርግ ። የሌለህን እንዳለህ ከማስመሰል የተሻለ የአስፈላጊነት ስሜት መፍጠር የሚችለው ያለህን ብቃት በመደበቅ እየቆጠቡ መስጠት ነው።

የሰዎችን ስሜት አትካድ
📖🗒🗒📖
ሰዎች በተለያዩ ጊዜአት ስሜትን የሚጎዳ ገጠመኞችን ይጋፈጣሉ ። የእነሱን ልምምድ በእነሱ ሁኔታ ሊያየው የሚችል ሰው ተፈልጎ አይገኝም ። አመጣጣቸውና አመለካከታቸው ለችግሩ የተለየ "ኬሚስትሪ" ስለሚሰጠው ማለት ነው ። ለሰዎች ከምናደርግላቸው ትልቅ ውለታ አንዱ በስሜታቸው ላይ ከመፍረድ ይልቅ ስሜታቸውን በመረዳት አብሮ መቆየትና ማገዝ ነው ። አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የተሰማቸውን ስሜት የሚገነዘብላቸውና የሚያደምጣቸው እንጂ ሃሳብ የሚያዘንብላቸው ሰው አይፈልጉም ። የራሱን ችግር ሳይፈታ በሌላው ሰው ሁኔታ ላይ ሃሳብ ሰጪው ብዙ ነውና ።
🗒🗒🗒
ለምሳሌ ፣ አንድ ሰው በጣም አዝኖ ሲያለቅስ ብታገኘው ፣ " ምን ያስለቅስሃል?ይህ ነገር አሁን የሚያስለቅስ ነገር ነው?" ከማለት ይልቅ ፤ " ስለደረሰብህ ሁኔታ በጣም አዝናለሁ ፣ ላግዝህ የምችለው ነገር አለኝ?" ማለት የበለጠ የስሜትና የማህበራዊ ብልህነት ነው ። የማዘንም ሆነ የማልቀስ ስሜት የማንነታችን አካል የመሆኑ ምክንያት እነዚህ ስሜቶች ሲመጡ በቅጡ እንድንገልጣቸውና ከውስጣችን በማስተንፈስ እንድናወጣቸው ነው ። ለዚህ ነው ሰዎች የሚያልፉበትን ስሜት ጊዜ ወስደው እንዲያልፉበት በመፍቀድ ለማገዝ ራሳችንን ማቅረብ ይገባናል የምንለው ።
🗒 🗒 🗒
ምንጭ 📖የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence )ገጽ 66-67
✍ ዶክተር ኢዮብ ማሞ
📖 ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

የንባብ ቅምሻ
📜📜📖📜📜
ነፍስህ በመኖር ጥማት ተፈረካክሳ ሳለች የሕይወትን ችግር በሎጂክ ድራድር ትተበትበዋለህ ። ቦቅቧቃነትህን በዓይናውጣነት አንቀልባ አዝለህ ፣ የባጥ የቆጡን በመቀባጠርህ ትኩራራለህ ። እፍረተቢስ ነገር ታወራና ወዲያው በፍርሃትና በሰበብ ትከልሰዋለህ ። የምፈራው የለም ስትል ቆይተህ ዞር ብለህ ደግሞ ትለማመጣለህ ።
📖📖📖
በሰቆቃ ጥርሴን አፋጫለሁ ብለኸን ፣ ኋላ ደግሞ እየቀለድክ ሳቁልኝ ትለናለህ ። ቀልዶችህ ጣዕመቢስ መሆናቸውን ስታውቅ ፣ በስነፅሁፍ ዋጋቸው ትመፃደቃለህ ። መከራ ደርሶብህ ብታውቅም እንኳን ለስቃይህ ቅንጣት ዋጋ አትሰጠውም ። ከምትቀባጥረው አንዳንዱ እውነት ቢሆንም ፣ ይሉኝታ ቢስነትህ መጠን የለውም ። ከግብዝነት የተነሳ ሐቅህን አደባባይ አውጥተህ ታረክሰዋለህ ። በርግጥ ማለት የምትሻው ነገር አለ ፣ እቅጩን እንዳትናገር ግን ፍርሃት ጠፍሮ ይዞሃል ፤ ለመናገር የሚያበቃህ ድፍረት አጥሮሃል ።
📖📖📖
የፈሪ ባለጌ ነህ ። በአእምሮህ ንቃትህ እየተኩራራህ ሳለ ትወላውላለህ ። ምክንያቱም አእምሮህ ብሩህ ቢሆንም እንኳን ፤ ልብህ በልክስክስነት ፅልመት ተወርሷል ። ንፁህ ልቦና በሌለበት ደግሞ ምሉዕ ንቃተ-ኅሊና ሊኖር አይችልም ።....
📖📖📖
ምንጭ📖 የስርቻው መጣጥፍ (Notesfrom Underground)
ደራሲ🖋 ፊዮዶር ዶስቶዬቭስኪ
ትርጉም ✍ ፋሲል ይትባረክ
፨ እንዴት ልክ ልካችንን የሚነግረን መጽሐፍ መሰላችሁ አንብቡትማ...

በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ የእድል ፋይዳ ምንድን ነው?
(ክፍል ፩ )
📜📜📜
የእድልምንነት ብቻ ሳይሆን እራሱ እድል የሚባለው ነገር መኖሩም ጭምር ብዙዎቹን ፈላስፎች ሊያስማማ አልቻለም ። ይህ አለመስማማት እንዳለ ሆኖ ሁሉም በአንድ ቃል የሚናገሩት ግን እድልን በተመለከተ የሰው ልጅ እርግጠኛ መሆንም ሆነ መቆጣጠር አለመቻሉን ነው ። " እድለኛነት በእቅድ ውስጥ የሚገባም ሆነ እርግጠኛ የሚኮንበት ነገር አይደለም " ሲሉ ይስማማሉ ።
የጥቂቶቹ ፈላስፎች የእድልንና የተርታ ተግባርን ክንውን የሚለዩበት የራሳቸው መስፈርት አላቸው ። ከእድል ውጭ የሆነ ውጤት ታቅዶ ፣ ታስቦበትና አስፈላጊነቱ ታምኖበት ከሞላ ጎደል በቋሚነት ከሚከናወን ተግባር የሚገኝ ነው ። በአጠቃላይ የሰው ልጅ የአእምሮውን ችሎታ ተጠቅሞና ይሁነኝ ብሎ በመስራት የሚያገኛቸው ትሩፋቶች ከእድል የሚቆጠሩ አይደሉም ። በተመሳሳይ ሁኔታ የሰው ልጅ ገና ከመጀመሪያው ሟች መሆኑ ይታወቃል ። ስለዚህ መሞቱ እርግጠኛ ነገር ነው ። የፀሐይ ብርሃን ያረፈበት የውሃ ጥርቅምም መትነኑ የማይቀር ነው ። እነዚህ ነገሮች በተፈጥሮ ነባራዊ ሁኔታ አስገዳጅነት የሚሆኑ እንጂ በእድል የሚከናወኑ አይደሉም ። ነገር ግን ይሆነኝ ብዬ ወደ አንድ የገበያ ማዕከል በመሄድ ላይ ሳለሁ ቦታውና ጊዜው ተገጣጥሞ አንድ ወዳጄን እዚያ ባገኘው እንዲህ ያለውን ገጠመኝ አርስቶትል የእድል ውጤት ነው ይለዋል ።
የጥንቶቹ ፈላስፎች እድልን "ዕጣ ፈንታ" ሲሉም ይጠሩታል እጣ ፈንታም ልክ እንደ እድል ሁሉ በአጋጣሚዎች መከሰት የሚገኝ ውጤት አለው ። ሐብትንና ስመጥርነትን ፣ ክብርንና ስልጣንን የእጣፈንታ ፀጋዎች አድርገው ይመለከቷቸዋል ። እነዚህን ፀጋዎች ማግኘትም ሆነ ማጣት ከእውቀትና ስነ ምግባር ጋር የሚያያዝ የጥረት ውጤት ሳይሆን የእድል ጉዳይ ነው ይሉታል ። አርስቶትል እነዚህን የዕጣ ፈንታ ፀጋዎች ለሰው ልጅ ደስታ አስፈላጊ ነገሮች አድርጎ ያስባቸዋል ። የስቶይሲዝም ፍልስፍና ተከታዮች (Stoicism)ደግሞ በሌላ አንፃር ነው ይሄንን የእድል ጉዳይ የሚረዱት ። ከኛ ቁጥጥር ውጭ ለሆነ ጉዳይ ቁብ የማይሰጥ ሰው ሊከበርና ሊደነቅ ይገባዋል ባይ ናቸው ።
ጥቂት የማይባሉ ፈላስፎች እድል የተባለ ነገር እስከመኖሩም የማይቀበሉ ናቸው ።...
ይቀጥላል...

(ክፍል ፪ )
ካለፈውየቀጠለ....
📜📜📜
ጥቂትየማይባሉ ፈላስፎች እድል የተባለ ነገር እስከመኖሩም የማይቀበሉ ናቸው ። እንደነሱ እምነት እድል እያልን የምንጠራው ለክስተቶች ምክንያታዊነት ያለንን አላዋቂነት ነው ። ነገሮች እንዴት እንደተፈፀሙ መረዳት ሲሳነን ያንን "እድል" እንለዋለን ። ስፒኖዛ የተባለው ፈላስፋ ምንም ነገር በእድል አይሆንም ሲል ይከራከራል ። ሁሉም ነገር መሆን እንደሚገባው ነው የሚሆነው ይላል ። ብዙ የክርስቲያን እምነት ሊቆች ከመለኮታዊው ፈቃደኝነት አንፃር በማየት የድንቢጥ ወፍ ጉዳይ እንኳን በእግዚአብሔር ዘንድ እንደማይዘነጋ ሁሉም ከእርሱ በእርሱ እንደሆነ ያስረዳሉ ። በዚህም << በዚህ ዓለም ውስጥ በዘፈቀደ የሚከናወን አንዳችም ነገር የለም >> ከሚለው ከፈላስፋው አውጉስቲን ጋር ይስማማሉ ። ሁሉም ነገር እንደ እድል የታየውን ነገር ጨምሮ በአምላክ ፈቃድ የሚከናወን ነው ሲሉም ይደመድማሉ ።
ዊልያም ጀምስ ደግሞ ዓለም ሙሉ በሙሉ በተረጋገጠ ሁኔታ ስርዓት በሚለው የስፒኖዛ ድምዳሜ አይስማማም ። አንዳንድ ጊዜ አገናዝበን የማንወስንባቸው ጉዳዮች የአማራጭነት ባህርይ ይዘው ያጋጥሙናል ። እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ሲያጋጥሙን ውሳኔያችን የግድ ከሆነ በመሳሳታችን ቆርጠን ያንን ወይም ይሄንን በጭፍን እንመርጣለን ። በምርጫችን ያጋጠመንን ሁኔታ ካየን በኋላ ነገሮችን በማመዛዘን ሌላ ውሳኔ የማሳለፍ እድሉ ይኖር ይሆናል ። ጀምስ እንደሚለው ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች መረጃዎች ሁሉ ተጠቃለው ሳናገኛቸው በእርግጠኝነት ልንወስን አንችልም ። በአማራጭ ትክክል ወይም ስህተት መሆን እንዳለ አውቀን ግን ሁኔታዎችን ልናከናውን እንገደዳለን ።
ይቀጥላል...
ለማንኛውምሃሳብ አስተያየት
👇👇👇👇
@SSR60 ይጠቀሙ
,,,,,,

Share it
#መራር_እውነታዎች
• ምንም ነገር ለዘላም አይቆይም፡፡ ችግሮችህ፣ የከበቡህ ሰዎች፣ ስራህ፣ ትዳርህና ግንኙነቶችህ ሁሉ ለጊዜዉ ነዉ፡፡ የሁሉም ነገር ፍፃሜ የሆነ ቀን ላይ ሲሆን ታየዋለህ፡፡ በህይወቴ ሁሉ አብረዉኝ ይኖራሉ ያልካቸዉ ነገሮች እንኳን ሳይቀሩ ሲፈረካከሹ ታያቸዋለህ
• ለሁሉም ነገር ተራ አለዉ፡፡ ሰዉን ብትጠቅም ጊዜዉን ጠብቆ አምላክህ ይከፍልሃል፡፡ ብትጎዳም እንዲሁ...በሰፈርከዉማንነት ጊዜዉ ሲደርስ ትሰፈራለህ
• ማንም ሰዉ ስላንተ አይጨነቅም፡፡ 20 ፐርሰንቱ ብቻ ስላንተ ሲጨነቁ (እነሱምየቅርብ ጓደኞችህና ቤተሰቦችህ መሆናቸዉን አትዘንጋ)80 ፐርሰንቱ ግን ኑር አትኑር አንዳች ቅንጣት ስላንተ አያስቡም፡፡ ችግሮችህን ለነዚህ ለ 80 ፐርሰንት መናገር እራስህን ማባከን ነዉ ምክንያቱም ችግርህ ለነሱ ምናቸዉም አይደለምና!የራሳቸዉ ጉዳይ ብቻ ያሳስባቸዋልና ቆጠብ በል
• ሰዎች በህይወትህ ይመጣሉ ደግሞም ይሄዳሉ፡፡ አንድ ቀን ለብቻህ ሰዉ በሌለበት ልትሞት ትችላለህና ሰዎችን #አትደገፍ
• ከ5-6 የልብ የምትላቸዉ ሰዎች በቀር ፌስቡክ ላይ ያሉት የጓደኛ ጋጋታ ምንም አይጠቅሙህም፡፡ ብትሞት እንኳ ቀብርህ ላይ የማይመጡ ብዙዎች መሆናቸዉን እወቅ
• የስራ አለቃህ እንድታድግና የተሻለ ቦታ እንድትይዝ ሊመኝ ይችላል ግን መቼም እንድትበልጠዉ አይፈልግም፡፡ ምንም ሽልማትና ጭብጨባ ቢበዛልህ ከሱ እንደምትበልጥ ካሰበ አንተን ለመገፍተር ወደኋላ አይልም
• 98 ፐርሰንቱ ሰዉ መቼ እንደተወለድክ እንኳን አያዉቅም(2ፐርሰንቱ መቼም እነማን እንደሆኑ መገመት አያቅትህም)፡፡ካላመንከኝ ሞክረህ እየዉ!
• የዉሸት ጓደኞችህ የተሻለ ህይወት እንድትመራ በፍጹም አይፈልጉም፡፡ ነገሮች መልካም ሲሆኑ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሊያስገርምህ አይገባም!አንድ ቀን ህልምህ 'ወለም' ብሎ ካዩ እጃቸዉን ቀስረዉ ይስቁብሃል፡፡ የዛኔ ያልሳቁብህን የልብ ጓደኞችህ አድርጋቸዉ
• ገንዘብ ያለዉና ፀዳ ብሎ የሚመላስን ሰዉ ብዙዎች ሲያከብሩት ትመለከታለህ ፡፡ የማያዉቅህ እንኳን ቢሆን ፀዳ ካልክበት ሊያከብርህ ሲዳዳዉ ታየዋለህ
• ለሰዎች ምክር መስጠት በጣም ቀላል ነዉ ነገር ግን ምክርን ወደተግባር መቀየር ከባዱና አስቸጋሪዉ ነገር ነዉ፡፡ አንዳንዴ ሰዉን ካለበት ማጥ ለማዉጣት ካሰብክ ከምክር በላይ የሆነ ስብዕና ሊኖርህ ይገባል፡፡
• አንድ ዉሸታም ጓደኛህ ከ 100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል፡፡ ጠላቶችህን ተከታተላቸዉ ጓደኞችህን ደግሞ በጣም ተከታተላቸዉ
• ነገሮች መልካም እንዲሆኑና እንዲሳኩ ያለ የሌለ ጥረትህን አድርገህ ሳይሳካልህ ቀርቶ ይሆናል፡፡ ይሄ ያንተ ደካማነት ሳይሆን ህይወት እንዲህ አይነት ገፅታም ስላላት ነገሩን ተቀበለዉ፡፡
• ለመወደድ ልዩ ሰዉና ሁሉንም ሞካሪ መሆን አይጠበቅህም፡፡ እንዳንዴ ሰዉ ሁሉ ባይወድህ እንኳን ይሄ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተረዳ፡፡
በሰዎች መጠላትንም ቀለል አድርገህ ዉሰደዉ ምክንያቱም እንዴት እራስህን ማሳደግ እንዳለብህ ማጤን ወሳኙ ነገር ሲሆን የሰዎችን ስሜት እያዳመጥክ ከፍና ዝቅ እያልክ መኖር አይጠበቅብህም፡፡
• የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎችበሀሳብህ አለመስማማታቸዉ አንተነትህ ላይ የሚያመጣዉ ነገር የለም፡፡ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትዉጣ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ
• ይቺ አለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነዉ፡፡ ባጠቃላይ አለም እራስ ወዳድ ናት
• ሰዎች ስለ ደስታ አጋነዉ ሲያወሩ ትሰማ ይሆናል፡፡ በኣጭሩ ደስታ ማለት ስሜትህ ሳይሆን አእምሮህ ያለበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ደስተኛ ሆነህ በሰዎች ልትጎዳ ትችላለህ፡፡
• ህይወት እኩል አይደለችም፡፡በሆነ ነገር ጎበዝ ብትሆን ካንተ የበለጠ በጣም ጎበዝ ሰዉ አለ...እኩልነትዉሸት ነዉ፡ ስለዚህ በመኖርህ ብቻ ተደሰት፡፡
አመሰግናለሁ
#ቅን_ከሆኑ_ለሎሎችም_ያጋሩ
ለማንኛውም ሃሳብ አስተያየት
👇👇👇👇👇
@SSR60
ወይም
@abdu23 ይጠቀሙ
ቻናላችንን join

📝📝📝የስርቻው መጣጥፍ 📝📝
………ለሰው የሚበጀው ደህነኛውና ገንቢው ነገር ብቻ ነው ብለው አጥብቀው በአርምሞ የሚለፍፉት ለምንድነው?
አይምሮይበጃል ብሎ በሚገምተው ነገር ሊሳሳት አይችልም?
ሰውየሚወደው ደህንነትን ብቻ ሳይሆን መከራን ጭምር ቢሆንስ?
ስቃይምእንደ ደህንነት ይበጃል ብሎ ቢያስብስ?
አንዳንዴኮ ሰው መከራን እጅግ ይወደዋል። ይህንን ስላልኩዎት የአለምን ታሪክ መመርመር አያስፈልግዎትም።በእርግጥ ሰው ከሆናችሁና የኑሮን ፅዋ ከቀመሳችሁ ራሳችሁን ጠይቁት።
እንደኔ ከሆነ ግን ደህንነትን ብቻ መውደድን ከነውረኝነት እቆጥረዋለሁ። ቢበጅም ቢከፋም አንዳንዴ ሆን ብሎ መስታዎት ማድቀቅና የክት ለብሶ ከጭቃ መርመጥመጥም ድንቅ ነገር ነው።
📖📖📖
በእውነቱ ለመከራ ጠበቃነት አልቆምም፣ የደህንነትም አፈ ቀላጤ አይደለሁም፣ የምቆምለት ነገር የራሴ ቅፅበታዊ ፈቃድና ፍላጎት፣ እርሱንም ለማድረግ ያለኝን የግል መብት ነው።
፧
ሁሉ ነገር በሰመረበት አገር ለምሳሌ መከራ ዝር አይልም። በእንከን አልባው የመስታወት ቤት ስቃይ ጭራሹን አይታሰብም።ስቃይ ማለት ጥርጣሬ ነው፤ አፍራሽ ሀይል። ጥርጣሬና እንከን አልባነት ደግሞ አብረው አይኖሩም። ሰው ግን ስቃይን እርግፍ አድርጎ አይተውም። ስቃይን፣ ውድመትንና ምስቅልቅልን። ምክንያቱም መከራ የንቃተ ህሊናው መሰረት ነውና። የሰው የስቃይ ምንጩ ንቃተ ህሊናው ነው። ይህን ንቃተ ህሊናውን በምንም ርካታ እንደማይለውጠውም አውቃለሁ። ንቃተ ህሊና ከ"ሁለት ጊዜ ሁለት አራት" እጅጉን የላቀና የከበረ ነው። ከ "ሁለት ጊዜ ሁለት" በኋላ ሊማሩትም ሆነ ሊያደርጉት የሚቀር ነገር የለም። አንድ የሚተርፍ ነገር ቢኖር፣ አምስቱት የስሜት ህዋሳትዎን ደፍነው ትርጉምና ቅርፅ በሌለው ባዶነት መዋዠቅ ነው። በንቃተ ህሊናዎም አማካኝነት መድረሻዎ ይሄው ምንም የማይፈፅሙበት ማሰላሰል ቢሆንም፣ ሌላው ቢቀር ቢያሰኝዎ ራስዎን እዬጠበሱ ይዝናናሉ። አዎ፣ ይህ ጠማማነት ነው። ግን ከምንም ይሻላል።
📖📖📖
በመስታዎት ቤት ህንፃ ዘላለማዊነትን ያምናሉ እንበል።በውስጡ የሚኖር ሰው ተደብቆ ምላሱን ማውጣትም ሆነ ከኪሱ ውስጥ እንኳን ጡጫ መጨበጥ በማይችልበት ህንፃ። በበኩሌ የዚህ ህንፃ ቋሚነት ሳይሆን በድብቅ እንኳ ምላሴን ልጎለጉልበት ባለመቻሌ እፈራዋለሁ።
፧
አዩ በተንጣለለ ውብ ቪላ ፋንታ የዶሮ ቤት ቢኖርና፣ዝናብ መጣል ቢጀምር፣ እጠለል ዘንድ ወደዚህ የዶሮ ቤት ተንፏቅቄ ብገባ፣ከዝናብ ስላዳነኝ የዶሮ ቤት ከቪላ ይቆጠራል ብዬ ራሴን አልደልልም። እንደሚስቁብኝ ይሰማኛል። በዚሁ አጋጣሚ የዶሮ ቤት ከቪላው ምን ለየው ይሉኛል። ምንም። የኑሮ ሚስጥሩ ከዝናብ ከመራስ ለመዳን ከሆነ።
📖📖📖
ለኔ ይህ የመኖር ትርጉሙ አይደለም። ከኖሩ አይቀር በቪላ መንፈላሰስ ይሻላል ብዬ የማምን ከሆነ ምን ያደርጉታል?
ይህየኔ መሻት ነው፣ ፍላጎቴ። ከውስጤ ፍቀው ሊያወጡት የሚችሉት ፍላጎቴን መቀዬር ሲቻልዎት ብቻ ነው። ታዲያ ምን ያዘዎት?ያው፣ፍላጎቴን ይቀይሩት፤በሌላ ነገር ይደልሉኝ ድንቅ ነገር ያቅርቡልኝ።
እስከዛ ድረስ ግን የዶሮ ቤትን ከቪላ አልቆጥረውም። ይህ የመስታዎት ቤት ህንፃ የሀሳብ ውላጅ ቢሆንም እንኳን፤ ከድንቁርናዬ የመጣ፣ የተፈጥሮ ህግ የማይፈቅደው የህልም እንጀራ። ታዲያ ተፈጥዎ ባይፈቅደው እኔን ምን ሲገደኝ?
የምኖረውበምኞት ውስጥ ሆነ፣ወይም የህንፃው መኖር ምኞቴ እስከሆነ ድረስ፣ እኔ ምን ቸገረኝ?
📖📖📖
አሁንምእዬሳቁ ነው?
እንዳሻዎት፣ይሳቁ። ቢሳለቁብኝም እየራበኝ ጠግቤያለሁ አልልም። በእርግጥ ስለኖረና የተፈጥሮ ህግ ስላነገሰው ብቻ ለፍፃሜ አልባ ባዶነትና ለተልካሻ ስምምነት እጄን አልሰጥም። ቪላ እያለ፣የሺህ አመት ውል የተፈረመበት ዛኒጋባ የፍላጎቴ ምንጭ አይሆንም። ፍላጎቶቼን ደምስሰው፣ክቡር መመሪያዎቼን ነቅለው፣ የተሻለ ነገር ሲያሳዩኝ ያኔ እከተልዎታለሁ። ላንተ ማን ግድ ይሰጠዋል ካሉኝም፣እኔም እርስዎን ጉዳይ አልልዎትም። የምናወጋው ከልብ ነውና ትኩረትዎን ሊሰጡኝ ካልፈቀዱ እኔም እርስዎን ደጅ አልጠናም። ወደ ስርቻዬ አዘግማለሁ።
📖📖📖
ግን በህይወት እስካለሁና መሻቴ እስካላከተመ ድረስ ይህን ለመሰለ ቤት አንዲት እንኳን ጡብ ባበረክት ክንዴ ሽባ ይሁን!
የመስታዎቱንቤት ህንፃ የናቅኩበት ምክንያት ሰው በውስጡ ምላሱን ማውጣት ስለማይችል በመሆኑ ብዙ አይደነቁ። ያንን ያልኩትም ምላስ በማውጣት ፍቅር ተለክፌ አይምሰልዎ። የነገሮች ሁኔታ የምላስ ማውጣት ፍላጎቴን እንዲያጠፋ ሆኖ ቢገኝ ኖሮ ከደስታዬ ብዛት በፈቃዴ ምላሴን ባስቆረጥኩ ነበር። መሻቴና ምኞቴ ለምን ተፈጠሩ?
በዚህተፈጥሮዬ ምክንያት ማንነቴ ከንቱ ነው። ብዬ እንዳስብ ልገደድ ታቅዶ ይሆን?አይመስለኝም።ይህን ግን ይወቁ። እኛ የስርቻ ሰዎች በወጉ ተጠፍረን መያዝ እንዳለብን ተረድቻለሁ። የኔ አይነቱ ሰው አንዲት ቃል ሳይተነፍስ ለአርባ አመታት ጉድባው ውስጥ ተወትፎ ይኖርና አንድ ቀን ወጣ ብሎ አፉን ከከፈተ ማቆሚያ የለውም።
ምንጭ 📖 የስርቻው መጣጥፍ 📖 መጽሐፍ
ደራሲ ✍ ታላቁ ሩሲያዊው ፊዮዶር ዶስቶዬቭስኪ
ትርጉም ✍ ፋሲል ይትባረክ
✍ ፍልስፍናና የህይዎት እውነታ አድሚኖች ✍
📖 ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል 📖

የትናንት ታሪክህ ያስመዘገባቸው ደስ የማያሰኙ ሁኔታወች ከማሰብ ማለፍ ካልቻልክ ከድካም አታርፍም።
ትናንትናን ሳያልፍ ዛሬ ላይ የደረሰ የለም ። ያንታን | ያንችም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም። የትናንትናው ታሪክህ ደግሞ ደስ የሚያሰኝ ትውስታ እንዳለው ሁሉ ለማሰብ የማትፈልጋቸው ትዝታወችንም አቅፏል ። ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ባትችልም በትናንትናው ላይ ያለህን አመለካከት ግን መቀየር ትችላለህ። ካለፈው ታሪክህ ትምህርትን ከመቅሰም ይልቅ ባለፈው እና በከተመለት ውስጥ ከኖርክ ለውድቀት ራስህን ታዘጋጃለህ።
በትናትናው ውስጥ የሚኖር ሰው ሶስት ነገር ኖሮት ሶስቱንም የከሰረ ሰው ነው። በአንድ ጎኑ የትናንት ስህተቱ ታሪኩን እንዳበላሸበት ስለሚያስብ "ትናንቱን" ከስሯል ፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በትናንትናው ላይ የተተከለው ማንነቱ የዛሬን ህይዎት ማጣጣም ስለሚያስቸግረው "ዛሬን" ከስሯል ፡ በመጨረሻም በጸጸት የደከመ ማንነቱና የፈዘዙት አይኖቹ የነገን ራእዩን ስለሚጋርድበት "ነገውን " ከስሯል ።
ትናንት ፥ ዛሬ እና ነገ የተሰኙ ለሁሉም ሰው ካለምንም አድልዎ የተሰጡ ስጦታወች የራሳቸው የሆነ ውበት አላቸው። "" ትናንት " ክፉና ደጉን የለየንበት አስተማሪያችን ነው። ""ዛሬ" ራሳችንን ከትናንትናው የተሻለ ሆኖ ያገኘንበትና ዳግም እድል የተቀበልንበት ታላቅ ስጦታ ነው። "" ነገ "" ደግሞ የትናንትናውን እና የዛሬውን ልምምዳችን ታክሎበት ለአዲስ ራእይ የምንነሳበት ታላቅ ተስፋችን ነው ።
ይቀጥላል

ከሶቅራጠስ እንማር !!!
አንድ ሠው መጥቶ ሶቅራጦስን፡- ‹‹እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ የሠማሁት ደስ
አይልም›› አለው፡፡ ሶቅራጦስ ግን ዝም አለ፡፡ ሠውየውም እንደገና፡- ‹‹ይገርማል
ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› አለው፡፡ ሶቅራጦስም እንደማይለቀው
ስለተረዳ፡- ‹‹ ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን ልሠማው የምችለው ሶስት
ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን ስትመልስልኝ ብቻ ነው›› አለው፡፡ ሠውየውም
ተስማማ፡፡
‹‹የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው፡፡ ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ
እውነት ነው ወይ?›› አለ፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን
አልችልም›› አለው፡፡
ሶቅራጦስም፡- ‹‹ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው፤ ሁለተኛው
ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለው፡፡
ሶቅራጦስም፡- ‹‹አንደኛ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ ሁለተኛ መልካም ያልሆነ ነገር
ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ ሶስተኛ ጥያቄ አለኝ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እሺ›› አለ፡፡
ሶቅራጦስም፡- ‹‹ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹የለም›› ብሎ መለሠ፡፡
ሶቅራጦስም በመጨረሻ፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ፤ ለእኔ
የማይጠቅም ነገር አልሠማም›› አለው ይባላል፡፡
ወዳጆቼ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፣ መልካም ያልሆነ እና በሕይወታችን ላይ ጉልህ
ሚና የሌለው ነገር ላይ ጊዜን ማጥፋት ትልቅ ብክነት ነው፡፡
አንዳንድ ሠዎች በማይመለከታቸው ነገር እድሜአቸውን ይገፋሉ፡፡ በዚህም
መልሠው ማግኘት የማይችሉትን ውዱን ጊዜአቸውን መና ሲያደርጉት ማየት አሳዛኝ
ነው፡፡ ታላቁ ፈላስፋ ሶቅራጦስም ይህን እውነት በሚደንቅ መልሱ አሳይቶናል፡፡
ስለሆነም በጎ ዓላማ በሌለው፣ ሐቅነቱ ባልተረጋገጠና አንዳች ፋይዳ በሌለው
እንቶፈንቶ ሳንባዝን ለሚጠቅም ነገር፣ ለሠናይ ተግባርና ለእውነት እንትጋ መልዕክቴ
ነው።
If you have any comment
@abdu23 and @SSR60

የቀጠለ ,,
,,
,
.
የህይዎት ሙሉ ስእል ያለው የትናንትናው ፥ የዛሬውና የነገው ተደምረው ጤናማ ስሌት ሲሰራላቸው ነው።
ጤናማውም ሆነ ጤማ ቢሱ የትናንትናው ታሪክ ለዛሬው ውሳኔያችንና ለነገው ዝግጅታችን እጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው። ስለሆነም የትናንትናውን ደስስ የማማያሰኝ ታሪክ ልክ እንዳልተከሰተ ቆጥሮ ለማለፍ መሞከር ሁኔታው ውስጥ ውስጡን እንዲጎዳን ከመፍቀድ ውጭ ሌላ ውጤት የለውም ። በተጨማሪም በሁኔታው ላይ ከልክ ባለፈ መልኩ በማተኮር ሌላ ነገር ማሰብና ወደፊት መሄድ ሲያቅተን ከአጉል ተጽእኖ አናመልጥም። የዚህ አይነቱ የሂዎት ዘይቤ አሉታዊ ተጽእኖው ብዙ ነው።
ከትናንትናው ታሪኩ መውጣት ያስቸገረው ሰው የዛሬን እውነታ የመጋፈጥ አቅሙ ደካማ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በትናንትናው ላይ ብቻ የተያዘው ማንነቱ ነገ ለሚገጥመው ሁኔታ ሊኖረው የሚገባውን ዝግጁነት ስለሚቀማው ገጠመኝ ሲመጣ ድንገት ይሆንበታል ። እስካሁን ያሳለፈው ለምንም ነገር ምንም አይነት መፍትሄ በማይሰጠው የትናንትናው ታሪክ ውስጥ ስለሆነ ፥ የወቅቱን ሁኔታ ለመጋፈጥ የተዘጋጀ አመለካከት አይኖረውም።
ይቀጥላል
ምንጭ
📔 ራስን ማሸነፍ 📔
🖊 ዶ/ ር አዩብ ማሞ🖊
📖 ገጽ 22 📖

የሕይወት ማዕቀፍ
📖📖📖
🗒 ስኬት ሌላ አይደለም ። የህይወት ማዕቀፍን መኖር መቻል ማለት የአንተን ማንነት ከተሳለው መድረኩ ጋር ማጣጣም መቻል ስኬት ነው ። ማንነት የመኖር መሆን ነው ። የተሳትፎ መድረኩ ሕይወት ነው ። ሁለቱ ተመጣጣኝ ሲሆን የሕይወት ማዕቀፍ ነው ። ማንኛውም አይነት ሕይወት ችግር አይደለም ። ችግረኛ የሆነ ነዋሪም የለም ። የሕይወት ችግሩ የሕይወት ማዕቀፍን መኖር አለመቻል ነው ።
🗒 አማራጩ ሁለት ነው ። አንደኛ በልክህ የተሰራ ሕይወት ፈጥረህ ትኖራለህ ወይም በምትፈልገው ሕይወት ለመኖር ራስህን በልክ ታስተካክላለህ ። ልዩነቱ በልክህ ለመኖር ኑሮን ትጠርባለህ ። ያለልክህ ላለመኖር ደግሞ ራስህን ትጠርባለህ ። ሰው የሚኖረው የሕይወት ማዕቀፍ ሁለት አይነት ነው ። አንደኛው ሰው በራሱ ልክ ለክቶ የሰራውን ሕይወት የሚኖርበት ነው ። ሁለተኛው ሕይወት ሰው ራሱን ለክቶ በመስራት የሚኖርበት ሕይወት ነው ። ሕይወት ልክ እንደ ሸሚዝ በልክህ ተዘጋጅታ የምትኖራት ብቻ ሳትሆን ራሷም በልኳ ሰርታህ የምትኖርባት ናት ።
🗒 ሁሉም ሰው ሊኖረው የሚገባ በልኩ የተሰራ ሕይወት ባለቤት ነው ። ልከኛ ኑሮ የሕይወት ማዕቀፍ ነው ። ሁሉም ሰው ለክቶ የሚኖረው የሕይወት ማዕቀፍ አለው ። የምታደርገው ጫማ የሚመችህ በልክህ የተሰራ ከሆነ ብቻ ነው ። በጣም ትልቅ ከሆነ ሸክም ነው በጣም ትንሽ ከሆነ ስቃይ ነው የሕይወት ማዕቀፍም እንዲሁ ነው ። በማንኛውም አኗኗር ውስጥ ብትሆን በልክህ የምትኖረው ሕይወት ማዕቀፍ ካለህ የአንተ ትክክለኛ ሕይወት እሱ ነው ።
🗒 የሕይወት ማዕቀፍ የኑሮ ቀለምና ቅርፅ መርጦ የመናር ጉዳይ ነው ። ለመኖር የማትችለውን ቀለም አትምረጥ ። መኖር የማትችለው የሕይወት ማዕቀፍ ውስጥ እየኖርህ ከሆነ የምትኖረው አንተ ሳትሆን ኑሮ ራሱ እየኖረብህ ነው ።
ምንጭ 📖 ሰው መሆን /ገጽ 83-84/
✍ ቢልልኝ ሀብታሙ
📜 ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

የእለቱ የመጽሐፍ ግብዣ
፧
፨ ሕይወት የምርጫዎችና የስምምነቶች መድረክ ናት ።
በዓለማችን ካሉ ፍጡራን በአጠቃላይ የሰው ልጆችን የሚያክል አካላዊ አፈጣጠሩ ያልተሟላ ፍጡር አይገኝም ። የሰው ልጅ እንደ ወፍ መብረር አይችልም ፤ በሩጫም ከነብር ጋር አይመጣጠንም ፤ የአዞን ያህል መዋኘት ፤ የጦጣን ያህል ዛፍ መውጣት አይችልም ፤ የንስርን ዓይነት የእይታ ችሎታ የለውም ። የሰው ልጅ ከየትኛውም ፍጡር የባሰ ደካማ እንደመሆኑ ትንኝ እንኳን ነድፋ ለሞት ልታበቃው ትችላለች ። ነገር ግን ተፈጥሮ ሚዛናዊ ናትና ለሰው ልጅ የማሰብ ችሎታን ችራዋለች ። ስለዚህ የሰው ልጅ አካባቢውን መፍጠር ሲችል እንስሳት ግን አካባቢያቸውን ተላምደው ለመኖር ይገደዳሉ ።
📖📖📖
ይህንን ታላቅ ስጦታ (የማሰብኃይልን)ሙሉ በሙሉ የሚጠቀሙበት የሰው ልጆች ግን እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው ። ውድቀት ሁለት አይነት ነው ። አንደኛው ድርጊቶችን ያለምንም ጥልቅ ቅድመ እሳቤ በመከወን የሚከሰት ውድቀት ሲሆን ፣ ሁለተኛው መልካም ነገሮችን ለመከወን አስበው ሳይተገብሩት ሲቀሩ የሚከሰት ውድቀት ነው ። በሕይወት ጎዳና ላይ የማሰብ ችሎታን ሳይጠቀሙ መጓዝ ልክ ሳያነጣጥሩ እንደመተኮስ ይቆጠራል ።
📖📖📖
ሕይወት ልክ እንደ ምግብ ቤት ናት ። ሳህናችንን ይዘን ያሻንን የምግብ አይነት እንመርጥና በመጨረሻ እንከፍላለን ። መክፈል እስከቻልን ድረስ በሕይወታችንም የፈለግነውን ነገር ማግኘት እንችላለን ። ምግብ ቤቱ ካለንበት ድረስ እንዲመጣልን የምንጠባበቅ ከሆነ ዕድሜ ልካችንን ላንመገብ እንችላለን ። በሕይወትም ላይ የምትፈልጉትን ከመረጣችሁ በኋላ ለስኬት ለመብቃት ተገቢውን (ተመጣጣኝ)ዋጋ መክፈል ይኖርባችኋል ።
...
ይለናል" ለአሸናፊነት መገዛት " የተሰኘው የቪቭ ኬራ መጽሐፍ ገጽ 55 ላይ ስናነበው ።
ያንብቡት ብዙ ነገር ያገኙበታል
፧
ምንጭ 📖 ለአሸናፊነት መገዛት 📖
✍ ደራሲ - ቪቭ ኬራ
✍ትርጉም - ማኅሌት ጥላሁን