ኦርቶዶክስ መረጃ 2
878 subscribers
12 photos
1 video
3 links
Download Telegram
Forwarded from RHOBOTH Online shopping
ሰበር ዜና

ብፁዑ አቡነ ናትናኤል «መንግስት ቃሉን የማያከብር ከሆነ፣ በቤተክርስቲያን ድርድር ስለሌለ ምዕመናን ልጆቻችን በተጠንቀቅ በመቆም አይናቸውን ቤተክርስቲያን ላይ ጆሯቸውን ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ አድርገው የአባቶችን ድምፅ ይጠብቁ» በማለት አሁን ቀጥታ እየተላለፈ ባለው መግለጫቸው አስጠነቀቁ!

ይሄ ነው የምንፈልገው!!! አዛምቱ!!!

@ORTODOX_MERJA
Forwarded from RHOBOTH Online shopping
እኛ ላዘንነው ከጎናችን መሆን ባትችሉ እንኳን ዝምታን ሳትመርጡ በንፁሀን ደም የተሳለቃችሁ ነጭ የለበሳችሁ ሁሉ የቤተክርስቲያንን መከፈል እና መፍረስ የተመኛችሁ ደስም የተሰኛችሁ ሁሉ እንድትፈርስም የአቅማችሁን የጣራችሁ በትንሽ ዳቦ የለወጣችሁ ነገን እጠግብ ብላችሁ ዛሬን በሰው ደም በሺህ አመታት ታሪክ ላይ የተረማመዳችሁ መሸሸጊያ ባጣችሁ ጊዜ ያስጠጋቻችሁን ቤተክርስትያን የገፋችሁ ሀገር ፊደል ቁጥር ቋንቋ ባህል ሰጥታችሁ ሰው ያረገቻችሁን ቤተክርስትያን ላይ ፊታችሁን ያዞራችሁ ሀዘንሽ የግልሽ ያላችሁ ልጆቿ ሲያለቅሱ ማቅ ስተለብስ በየSocial mediaw የተዘባበታችሁ ሀገርን ከነ ክብሯ ጠብቃ በጥቁር ህዝብ ታሪክ የሌለን ጥበብ ለዓለም ያበረከተችን ቤተክርስቲያን ሀዘንሽ ሀዘኔ አደለም ያላችሁ ሁሉ ታሪክሽ ተረት ነው እምነትሽም ጣዖት ነው ያላችሁ ሁሉ ስናዝን አይዟችሁ ያላላችሁ ሁሉ ከዚች ቀን አንስቶ እኔ አላውቃችሁም እናንተም የኔ ሰዎች አይደላችሁም፡፡ ፈጣሪም እምባዋን ቆጥሮ ፍርዱን በህይወት እያላችሁ ይስጣችሁ፡፡
አመሰግናለሁ ፡፡

YILIKAL GETU
@ORTODOX_MERJA
#ሰበር_ዜና

ዛሬ ከምሽቱ 1:30 ላይ በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል የአዲስ አበባ የቀድሞው ስራ አስኪያጅ የነበሩት ሊቀ ጉባኤ ቆሞስ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ እና የመናገሻ አምባ ማርያም እና የጋራው መድኃኔዓለምና ደ/ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አባ ሞገስ ኃ/ማርያም ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሢኖዶስ ለማስረከብ እንዲሁም ቅድስት ቤተክርስቲያንንና ምዕመናንን ይቅርታ ለመጠየቅ በጉዞ ላይ እያሉ በህገ ወጡ ቡድን ግብረ አበሮች ተይዘው ወደ እስር ቤት እንደተወሰዱ ተገለፀ።

መረጃውን ያወጣው 'የሰንበት' ትምህርት ቤት ሚዲያ ማዕከል'' ነው!

@ORTODOX_MERJA
@ORTODOX_MERJA2