መምህር ዲያቆን ሃይሌ ከእኛ ከአዋቂዎቹ ማን በእሱ አመነ? ብለው ሊያሸማቅቋቸው ሞከሩ፡፡
ይህን ሁሉ ሲሆን የማታው ተማሪ የአይሁድ መምህር ኒቆዲሞስ እዚያ ቆሞ ነበር፡፡ ከአለቆች መካከል በጌታ ያመነ የለም ሲባል እየሰማ ነው፡፡ አሁን ክርስትናው ልትፈተን ነው፡፡ ደፍሮ እኔ አምኜአለሁ ብሎ መናገር ባይችልም ፈራ ተባ እያለ እንዲህ አለ ‹‹ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው።›› እነሱ በተናገሩት ብቻ ለምን ትፈርዳላችሁ? እሱን ሳትሰሙ መፍረድ ተገቢ ነው ወይ? ማለቱ ነበር፡፡ አይሁድ እንደ ሎሌዎቹ ሁሉ ኒቆዲሞስን ማቃለል እንዳይችሉ የተከበረ መምህር ሆነባቸው፡፡ ስለዚህ ‹‹አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ አሉት። እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ሄደ።›› ጌታችን ከገሊላ ናዝሬት መምጣቱን በመጥቀስ መሲህ ከገሊላ አይነሣም ብለው ሊያስተባብሉ ሞከሩ፡፡ ይህ ግራ መጋባት በሐዋርያው ናትናኤልም የታየ ነበር እርሱ ‹‹ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?›› ብሎ የጠየቀው መሲሁ ከይሁዳ ቤተ ልሔም እንደሚነሣ የተነገረውን ትንቢት በማየት ነበር፡፡ ጌታችን የተወለደው ከቤተ ልሔም ነው ያደገው ግን በገሊላ ናዝሬት በመሆኑ ነው ይኼ ሁሉ ውዥንብር፡፡ ኒቆዲሞስ ክርስትናውን በሌሊት ፈርቶ ጀመረ፡፡ አሁን ሙሉ በሙሉ ክርስቲያን ነኝ ብሎ መመስከርና መግለጥ ባይችልም ቢያንስ አይሁድ ከአለቆች ማን በእርሱ አመነ? ብለው ሲዘብቱ ቢያንስ ድምፁን ለማሰማት ሞከረ፡፡ በጥያቄ አስጨንቆም በዚያች ዕለት ስብሰባውን በተነው፡፡
ፍጹማዊው ኒቆዲሞስ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል መከራ ዓለምን የማዳን ሥራውን ፈጸመ፡፡ በዚህ የመከራ ወቅት በዋለበት የዋሉ ባደረበት ያደሩ ደቀ መዛሙርቱ ከዮሐንስ በቀር በፍርሃት ተበተኑ፡፡ ነፍሱን ከሥጋው ተለይቶ ከመስቀሉ ሲወርድም አንድም ሐዋርያ አብሮት አልነበረም፡፡ በዚህ ወቅት ኒቆዲሞስ እንደ ቀድሞው ሌሊት እስኪሆን አልጠበቀም፡፡ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ ከአርማትያው ዮሴፍ ጋር ሆነው የጌታችንን ሥጋ ወሰዱ፡፡ እንደ አይሁድ የአገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት፡፡ ሲገንዙት እያለቀሱ ነበር ‹‹ሞትከኑ መንሥኤሆሙ ለሙታን ፤ ደከምከኑ መጽንኤሆሙ ለድኩማን›› ‹‹ሙታንን የምታስነሣ ሆይ ሞትክን? ደካሞችን የምታጸናቸው ሆይ ደከምክን?›› እያሉ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ጌታችን በመለኮቱ ሕያው እንደመሆኑ አነጋገራቸው፡፡ በነገራቸው መሠረት ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት…›› የሚለውን በኪዳን ወቅት የምናደርሰውን ዓለም አቀፋዊ ጸሎት እያደረሱ ገነዙት፡፡
ኒቆዲሞስ ሲፈራ ፣ ቀስ እያለ ሲናገር የነበረውን ክርስትናውን በአደባባይ ገለጠ፡፡ ‹‹ልቡ ለጻድቅ ውኩል ከመ አንበሳ›› ‹‹ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ሳይፈራ ይኖራል ›› እንዲል ጠቢቡ በጌታ የደረሰ መከራ ቢደርስብኝ ሳይል ሥጋውን ተሸክሞ ገነዘ፡፡ ከምኩራብ ያስወጡኛል ብሎ የፈራው ኒቆዲሞስ ቤተ ክርስቲያን እንዳለች ስለተረዳ በድፍረት ክርስትናውን መሰከረ፡፡ ከሦስቱ የኒቆዲሞስ ክርስትና ደረጃዎች እኛ በየትኛው ላይ ነን? ስለ ሃይማኖታችንስ በየትኛው ደረጃ እንመሰክራለን፡፡ በጨለማ ነው? ፈራ ተባ እያልን ነው ? ወይንስ ያለ ፍርሃት?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 2006 ዓ ም

❤1👍1
+ ያልተናገረችው አህያ +
ነቢዩ በለዓም በአህያ ላይ ተጭኖ ሲሔድ አህያው የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፡፡ በለዓም ተናድዶ መታት፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ አህያይቱ ድጋሚ መልአኩን አየች፡፡ ከበለዓም በታችም ተኛች፡፡ በለዓም ተበሳጭቶ አህያይቱን በበትሩ ደበደባት፡፡
እግዚአብሔርም የአህያይቱን አፍ ከፈተ ፦ ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው፡፡ በለዓምም አህያይቱን ፦ ስላላገጥሽብኝ ነው ሰይፍ በእጄ ቢኖር ኖሮ እገድልሽ ነበር አላት፡፡ አህያይቱም በለዓምን ፦ ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት’’ /ዘኁ 22፡27-30/
ይህንን ታሪክ ባነበብሁ ቁጥር ሁልጊዜም የሚያስደንቀኝ የአህያይቱ መናገር ሳይሆን የበለዓም መልስ መሥጠት ነው፡፡
እግዚአብሔር ያሳያችሁ፡፡ በለዓም መልስ የሠጠው ከሎሌዎቹ ለአንዱ አይደለም፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‘ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን ዕብደት አገደ’ /2ጴጥ 2፡16/ እንዳለው አህያ ስትናገር ታይቶ ተሰምቶ አያውቅም፡፡
መንገድ ላይ እየሔድህ ከሰፈርህ ውሾች አንዱ ‘እንዴት አደርህ?’ ቢልህ እግዚአብሔር ይመስገን ትላለህ? እርግጠኛ ነኝ ራስህን ስተህ ልትወድቅ ትችላለህ፡፡ ከተረጋጋህ በኋላም አእምሮህ ተነክቶ ‘ውሻው ተናገረ እኮ’ እያልክ ትኖራለህ፡፡
በለዓም ግን ተናግራ የማታውቀው አህያ አፍ አውጥታ ስትናገር ሲያይ ትንሽ ደንገጥ እንኳን አላለም፡፡ ሌላ ቀን ሲያናግራት እንደኖረ ሰው ኮስተር ብሎ መመላለስ ጀመረ፡፡ አህያዋ አብረው ስለኖሩበት ዘመን የሥራ ልምድዋና የሥራ አፈጻጸምዋ ‘ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን?’ ብላ ስትነግረው በለዓም ሠራተኛውን እንደሚያናግር አለቃ ተረጋግቶ ያለ ምንም መደንገጥ ራሱን እየነቀነቀ ከሰማ በኋላ ፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም ብሎ ግምገማዋን ተቀብሎ ኂሱን ዋጠ፡፡
የበለዓምን ነገር እንተወውና የተናጋሪዋ አህያውንም ነገር እንርሳውና አንዲት መናገር ሲኖርባት ያልተናገረች አህያ ነገር ግን የበለጠ ይቆጫል፡፡
ይህች አህያ በሆሳዕና ዕለት ጌታችን የተጫነባት አህያ ናት፡፡ ይህች አህያ እንደ በለዓም አህያ ጌታዋ በበትሩ የሚደበድባት ሳይሆን ‘ለጌታ ያስፈልጉታል’ ብሎ ከነ ልጅዋ ያስፈታት አህያ ናት፡፡ የእርስዋ ጌታ በተኛችበት በበትር የሚቀጠቅጣት ሳትሆን እግርዋ መሬት እንዳይረግጥ ጌታዋ ያስነጠፈላት አህያ ናት፡፡
የእርስዋ ጌታ እንደ በለዓም መልአክ መንገድ የሚዘጋበት ሳይሆን መላእክት በፊቱ እየሰገዱ እንደ ሻሽ የሚነጠፉለት ነው፡፡ የበለዓምን አህያ አንደበት የከፈተ ጌታ ምነው የዚህችን አህያ አንደበት በከፈተው ኖሮ! ስንት ነገር በተናገረች ነበር?
የሆሳዕናዋ አህያ አንደበትዋ ቢከፈት እንደ በለዓም አህያ ጌታዋን ከማማረር ይልቅ ከሕዝቡ ጋር አብራ ትዘምር ነበር፡፡ እንደ በለዓም አህያ ‘ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን?’ በማለት ፋንታ ‘ከብዙ ዘመን ጀምሮ ሰው ሲቀመጥብኝ የኖርሁ አህያ ነበርሁ፡፡ በውኑ ንጉሥን እሸከም ዘንድ ልማዴ ነበርን?’ ብላ ታመሰግን ነበር፡፡
ጌታ ሆይ እኛስ ስንት በለዓሞችን ተሸክመን ኖርን? ስንት በለዓሞች በተሸከምናቸው በታግስናቸው ልክ በማመስገን ፈንታ በበትር ደበደቡን? በብሶት በምሬት አፍ አውጥተን ስንናገር እንኳን ትንሽ አይደንቃቸውም፡፡
አንተው መጥተህ ገላግለን፡፡ ለምስጋና ቢስ በለዓሞች ‘ለጌታ ያስፈልጉታል’ ብለህ እንዲፈቱን ንገራቸው፡፡ አንተው ዙፋንህ አድርገን፡፡ አንተን መሸከም አይከብደንም፡፡ አንተን የያዝን እንደሆን መንገዳችን በዝማሬ የተሞላ ይሆናል፡፡ የሚንቁን ሁሉ አንተን ብለው ያከብሩናል፡፡ ምንም እንኳን አንተን ሊይዝህ የሚችል ባይኖርም በደስታ እንሸከምሃለን፡፡
ራስህ እንዲህ ብለሃልና ፦
‘እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ
እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ
ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና
ለነፍሳችሁም ዕረፍትን ታገኛላችሁ
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና’ /ማቴ 11፡28/
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 17 2013 ዓ.ም

❤1