✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
40.7K subscribers
91 photos
8 videos
54 links
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
➜ መዝሙር ➜የቅዱሳን ታሪኮች
➜ስብከት
✞ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ
https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen
Https://YouTube.com/tomi_8019
Https://www.tiktok.com/@tomi8019
Https://www.Instagram.com/@tomi801977
Download Telegram
✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
Photo
ታህሳስ 28/4/2016 ልደተ ክርስቶስ

👉በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በአለ ልደት አደረሰን አደረሳችሁ

👉 ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባህሪውን ዝቅ አደረገና መጥቶ በድንግል ማሕፀን አደረ ከብቻዋ ከኃጢያት በስተቀርም እንደኛ ሰው ሆነ ነቢያት ትንቢት እንደተናገሩለት በቤተልሄም_ተወለደ ፈፅሞም አዳነን ወገኖቹም አደረገን

👉የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት ተወለደ እግዚአብሔር ሰውን የስሙ ቀዳሽ የርስቱ ወራሽ ይሆን ዘንድ ከምድር አፈር አበጅቶ የሕይወት እስትንፋስ እፍ ብሎበት በአርአያውና በአምሳሉ በዕለተ ዓርብ ፈጠረው ዘፍ1፥26-28 ዘፍ 2፥7

👉በፀጋ የከበረ ሆኖ ፈጣሪውን እያገለገለ የተፈጠረበትን ዓላማ ለ7 ዓመታት በመጠበቅ እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት ኖረ በ7ኛው ዓመት በሰይጣን ምክር አማካኝነት የተሰጠውን ሕግ አፍርሶ ዕፀ በለስን በላ በዚህም ከክብሩ ተዋርዶ ከገነት ተባሮ በምድረ ፋይድ ተጣለ ዘፍ 2፥16-17

👉ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ ተፈረደበት ባሕርይው ጎሰቆለ አዳምና ሔዋን የዲያብሎስ አገልጋይ ሆኑ በእንዲህ ያለ ጽኑ ፍርድ ውስጥ እያሉ አዳም ስለበደሉ አዘነ አለቀሰ ፈጣሪውንም ይቅርታ ጠየቀ እግዚአብሔርም በፈጠረው ፍጥረት ሳይጨክን ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል የምሕረት ተስፋ ሰጠው አዳምም ተስፋውን እየጠበቀ 5500 ዘመን ያህል ምሕረትን ሲናፍቅ ኖረ ዘፍ 3፥1-24

👉ቀጠሮውም ሲደርስ የተናገረውን የማያስቀር የምሕረት አምላክ 5500 ዘመን ሲፈጸም ለአዳም አባታችን የገባውን ቃል ለመፈጸም ትንቢቱ ሲደርስ ምሳሌው ሲፈጸም ብርሃነ ዓለም ቅዱስ_ጳውሎስ የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከው ገላ 4፥4 እንዳለው ለመዳናችን ምክንያት ከሆነችው ከቅድስት_ድንግል_ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በቤተልሔም በከብቶች በረት #ተወለደ ማቴ 1፥19-23 ፣ ኢሳ 7፥14 ፣ መዝ 2፥7 ፣ ሉቃ 2፥1-18

👉ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅም ድንግል_ፈጣሪዋን_ወለደችዉ እርሱም የፈጠረውን_ሥጋ_ተዋሐደ ሲል በሃይማኖተ አበው ገልጾታል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ_ክርስቶስ በመልአኩ በቅዱስ_ገብርኤል_ብሥራት መጋቢት 29 ቀን ተፀንሶ ታኅሣሥ 29 ቀን ተወለደ።

👉አካላዊ ቃል ኢየሱስ_ክርስቶስ በቤተልሔም በከብቶች በረት በተወለደ ጊዜ እንስሳት ትንፋሻቸውን ገብረውለታል ሰብዐ ሰገልም የጥበብ_ሰዎች ወርቁን ለመንግሥቱ ዕጣኑን ለክህነቱ ከርቤውን ለሞቱ እንዲሆን እጅ መንሻ አድርገው ገብረውለታል የተናቁ ኖሎት #እረኞች የመልአኩን የምሥራች ቃል ሰምተው በአዲስ ምስጋና አመስግነውታል ቅዱሳን መላእክትም በላይ በአርያም በዙፋኑ ፍፁም ክብሩ አይተውት ስብሀት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሠላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ ብለው አመስግነዋል ስለ ሰብዐ_ሰገል ማቴ፤ም፣2 ያንብቡ

👉 ቅዱስ_አትናቴዎስም አምላክ ሰው ሰው አምላክ የሆነበት ይህ ምሥጢር ፍሬ ተዋሕዶ በእውነት እፁብ ድንቅ ነው ማናቸውን አስቤ ላድንቅ መለኮታዊ ባህርይ ባለመመርመር ቅዱስ_ቅዱስ_ቅዱስ ተብሎ በመመስገን ከባሕርይ አባትህ አብ ጋር በቅድምና መኖርህን ላድንቅን ወይስ በአምሳለ ሕፃን ተገልጸኽ በግዕዘ ሕፃናት ሆነህ በእናትህ_እቅፍ መያዝኽን እያለ የወልድን ከድንግል መወለድ ገልፆታል ለወልድ ሁለት ልደት እንዳለው በቀዳማዊ ልደቱ ዘመን እንደማይቆጠርለት በደኃራዊ ልደቱም ዘመን እንድንቆጥርለት አደረገን

👉አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ_ክርስቶስ ከልደቱ በዐል እረድኤት በረከት ያሣትፈን ሀገራችንን ህዝባችንን አለማችንን በቸርነቱ ይጎብኝልን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እናታችን_ማርያም ስለ ዐለሙ አንድነትና ሠላም ፍቅር መጠበቅ ከአንድዬ ልጇ ከክርስቶስ ታማልደን ታስታርቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥

✍️comment
@tomi8019
ይች ናት ተወህዶ 🥰 🙏

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
የጥምቀት መዝሙራት እና ሌሎችም ቆየት ያሉ እና አዳዲስ መዝሙራት የምታገኙበት ቻናል 👇ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይቀላቀላሉ 👇

👉 https://t.me/+tvR3rXUqr5hlY2Jk
👉 https://t.me/+tvR3rXUqr5hlY2Jk
ጥር 5/2016 #ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ (የለዉጥ በዐል)

👉#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ #የልደታቸዉ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ጥር 5 በዚህች ዕለት #የአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ የልደታቸው መታሰቢያ #የለውጥ_በዓል ነው ትውልድ ሀገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው

👉የአባታቸው ስም #ቅዱስ_ስምዖን እናታቸው ቅድስት #አቅሌስያ ይባላሉ ወላጆቻቸው #በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች

👉ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም #እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ የሚል ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ #መልከፀዴቅ ንጽሕናው እንደ #ነቢዩ_ኤልያስ እንደ መጥምቁ #ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ አሏት

👉ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡

👉ቅድስት #አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ ወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን አላት

👉ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ ዳግመኛም ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ #ለአብ_ለወልድ_ለመንፈስ_ቅዱስ ምስጋና ይሁን አለ

👉 #የአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ በዓለ ልደት ታህሳስ 29 #በጌታችን_ልደት ነው ነገር ግን ዕለቱ ትልቅ ሚስጥር የያዘ ነውና አባቶቻችን የጌታ ልደት ዘምረው ጣዕሙ ሳያልቅ #ቅዳሴ ይገባሉ

👉ስለዚህ #የአባታችን_አቡነ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ በዐል ከሚቀር ልደታቸው ጥር 5 እንዲከበር ስርዓት ሰርተዋልና በዓለ #ልደታቸው በዚህች ቀን ተከብሮ ይውላል

👉የፃድቁ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የምናስባቸዉ #ብርሐናተ_አለም_ቅዱስ_ጴጥሮስና_ጳዉሎስ ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
ጥር 10/2016 #ጾመ_ገሃድ /ጾመ ጥምቀት/

👉 #ጾመ_ገሃድ (ጋድ)፦ የቃሉ ትርጕም «ገሃድ» ሲል መገለጥ፥ «ጋድ» ሲል ለውጥ ማለት ነው ይኸውም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን #የኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ መገለጥን የምናስብበት ነው አንድም ጋድ ተብሎም ይጠራል ጥምቀት ረቡዕ፣ ዓርብ ቢውል በዚያ ለውጥ ማክሰኞና ሐሙስ ይጾማልና

👉ጋድ #ጾመ_ጥምቀት ፦ ይህ ጾም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችንን #የኢየሱስ_ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነ የጥምቀት /ዋዜማ/ ጾም ነው

👉 #የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ዕለት በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማክሰኞንና ሐሙስን በመፆማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል በዚህም የፆምና የበዓል ማክበር ይከናወንልናል

👉 #የጥምቀት ዋዜማ ሰኞ፣ ማግሰኞ፣ ሐሙስ ከሆነ ጾም ነው፤ በአጋጣሚ ደግሞ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ከጥሉላት ምግቦች ብቻ ይጾማል ሆኖም ጥምቀት በየትኛውም ዕለት ቢውል በየዓመቱ ሁልጊዜ የጥምቀትን ዋዜማ እስከ ምሽት #ዕርበተ_ፀሐይ እንጾም ዘንድ አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብንና ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ይሆን ዘንድ ሥርዓትን ሠርተውልናል

👉ስለሆነም በ2016 ዓ.ም የጌታችን በዓለ ጥምቀት ጥር 11 ቀን በዕለተ ቅዳሜ ስለሆነ #ጾመ_ጋድ /ገሃድ/ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም #በዕለተ_አርብ ይሆናል ማለት ነው ዕለተ አርብ ራሱን የቻለ የጾመ ድኅነት ቀን ሲሆን በዚህ ዓመት ጾመ ገሃድ በዚህ ዕለት ውሏልና ዕለቱ #ጾመ_ድኅነትና_ጾመ_ገሃድ የተገጣጠሙበት ዕለት ሆኗል

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
እንኳን ለብርሀነ በጥምቀቱ በሰላም አደረሳቹ እያልን በየአድባራቱ የሚካሄዱ የጥምቀት የጥምቀት በአል ሁነቶችን ፎቶ በማንሳት በቻናላችን እንዲላክልዎት ከፈለጉ በ @tomi8019 ላኩልን እናመሰግናለን 🙏

መልካም በአል


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
ከበቆጂ

የእናንተን ደብር በ @tomi8019 ላኩልን
ከኮተቤ ኪዳነምህረት እና መዳህኒአለም ደብር

የእናንተን ደብር በ @tomi8019 ላኩልን
ሸባ ጌቴሴማኒ ወ መዝገበ ምህርት ቅ/ማርያም ገዳም እና ደብረ ብርሃነ ቅድስተ ስላሴ ካዴድል

የእናንተን ደብር በ @tomi8019 ላኩልን
⛪️ መልካም የጥምቀት በአል ይሁንላችሁ ⛪️

ያሳለፋችሁትን የጥምቀት በአል ማጋራት ከፈለጉ በ
@tomi8019 መላክ ትችላላቹ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥