✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
40.8K subscribers
92 photos
8 videos
54 links
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
➜ መዝሙር ➜የቅዱሳን ታሪኮች
➜ስብከት
✞ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ
https://t.me/Orthodox_tewahdo_nen
Https://YouTube.com/tomi_8019
Https://www.tiktok.com/@tomi8019
Https://www.Instagram.com/@tomi801977
Download Telegram
ሸባ ጌቴሴማኒ ወ መዝገበ ምህርት ቅ/ማርያም ገዳም እና ደብረ ብርሃነ ቅድስተ ስላሴ ካዴድል

የእናንተን ደብር በ @tomi8019 ላኩልን
⛪️ መልካም የጥምቀት በአል ይሁንላችሁ ⛪️

ያሳለፋችሁትን የጥምቀት በአል ማጋራት ከፈለጉ በ
@tomi8019 መላክ ትችላላቹ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
#ጥር_ወር_በገባ_በ14_አቡነ_አረጋዊ_ልደታቸው_ነው

#ወቶ_ከመቅረት_ካልታሰበ_አደጋ_ከክፉ_ነገር_ሁሉ #ይሰውረ🥰🙏🥰

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
#ጥር_ወር_በገባ_በ14_አቡነ_አረጋዊ_ልደታቸው_ነው። #ወቶ_ከመቅረት_ካልታሰበ_አደጋ_ከክፉ_ነገር_ሁሉ #ይሰውረ።🥰🙏🥰 ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                    •➢ ሼር // SHARE      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥ 💚@Orthodox_tewahdo_nen💚      💛@Orthodox_tewahdo_nen💛 ❤️@Orthodox_tewahdo_nen❤️       ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
"በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

          #ጥር ፲፬ (14) ቀን።

እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አንድ የወይራ ዛፍ ተደግፈው 40 ዓመታት ለጸለዩ #ለአቡነ_አካለ_ክርስቶስ_ዘቤጌምድር ለበዓላቸው መታሰቢያ በዓል፣ #ከዘጠኙ_ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት #ለዘሚካኤል በሚሰሩት ስራቸው አረጋዊ ለተባሉት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አረጋዊ_ለልደታቸውና ወደ ደብረ ዳሞ ለወጡበት ቀን ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ለቊስጥንጥንያ ንጉሥ ለቴዎዶስዮስ ልጅ ለሙሽራወ #ለቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ_ለበዓሉ መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                           
#አባ_ዘሚካኤል_አቡነ_አረጋዊ_ታሪክ_ልደት
የጻድቁ የአቡነ አረጋዊ አባታቸው ቅዱስ ይስሐቅ እናታቸው ቅድስት እድና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩና በሮም አገር የሚኖሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የተባረከውን ልጅ ሰጣቸው፤ ይህም የሆነው በጥር ፲፬ ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሕገ ኦሪትን ትምህርተ ነቢያትንና ቅዱሳት መጽሕፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየጸና እየበረታ አደገ፡፡ ሚስት ያገባ ዘንድ አጩለት፡፡ ጻድቁ አባታችን አቡነ ዘሚካኤል (አረጋዊ) ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡

                                
                            
#አቡነ_አካለ_ክርስቶስ_ዘቤጌምድር፦ ከአባታቸው ከገላውዴዎስ ከእናታቸው ወለተ አዳም ጌታችን በተወለደበት ዕለት ታኅሣሥ 29 ቀን ተወለዱ። በተወለዱም ጊዜ ሙት አስነሥተዋል። የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሲሆኑ በ21 ዓመታቸው ነው በሐይቅ እስጢፍኖስ ገዳም የመነኰሱት። ዘገብርኤል የተባለ በስሙ አሳሳች የሆነ ጣዖት አምላኪ ለጣዖት አልሰግድም ቢሉ ወስዶ በእጅጉ አሠቃቷቸዋል። በ6 ችንካሮች ቸንክሮ ሲያሠቃያቸው ጌታችን ተገልጦላቸው እንደ ጊዮርጊስ ጽና ብሎ ተስፋውን ሰጥቷቸዋል።

ጻድቁ አገራቸው ጋይንት ሲሆን በዚሁ አካባቢ ምዕራፈ ቅዱሳን በተባለው ቦታ አንድ የወይራ ዛፍ ተደግፈው ሳይንቀሳቀሱ 40 ዓመት ቆመው የጸለዩበት ወይራ ዛፍ ዛሬም በገዳሙ ተከብራ ትኖራለች። ቤተ መቅደሱ ሳይታጠን የቀረ እንደሆነ ወይም ዲያቆኑ መብራት ሳያጠፋ የሄደ እንደሆነ የጻድቁ መቋሚያቸው እንደ ሰው አፍ አውጥታ ታቃጭላለች። ያበደ ሰው በመቋሚያዋ 7 ጊዜ ቢተሻሽባት ይድናል። በአካባቢው ብዙ መርዛማ እባቦች ቢኖሩም የአቡነ አካለ ክርስቶስን ስም ከተጠራባቸው ምንም ጉዳት አያደርሱም። በሌላም ቦታ ሆኖ እባብ የነደፈው ሰው እምነታቸውን ከተቀባ ጸበላቸውን ከጠጣ ፈጥኖ ይድናል።

ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
ጥር 16/2016 #ቅድስት_ኪዳነ_ምህረት

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በምስጋና ከፍ ለምናደርግበት እናታችን #ኪዳነ_ምህረትን በቃል ኪዳኗ እንድትጠብቀን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው

👉 #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ #ክርስቶስ_መካነ_መቃብር_ጎለጎታ እየሔደች ትፀልይ ነበር ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ #የምህረት_ቃል_ኪዳንን ሰጣት

👉እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ #ቃል_ኪዳን አደረገ

👉"ከመረጥሁት ጋር #ቃል_ኪዳኔን አደረግሁ" መዝ፣89፦3

👉ስሟን ለሚጠሩ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት #ቃል_ኪዳን ሰጥቷታል

👉በታላቁም መፅሐፍ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም #ቃል_ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ ኦሪት ዘፍ፣9፣16

👉በዚህም መሠረት #ቃል_ኪዳኗን ምክንያት በማድረግ #ኪዳነ_ምህረት እያልን እንጠራታለን የከበረዉ ቃል ኪዳኗ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
ጥር 18/2016 #ዝርወተ_አፅሙ_ለቅዱስ_ጊዮርጊስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቱ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ከሃዲው ንጉሥ ዱድያኖስ እጅግ አሠቃቂ በሆኑ ብዙ መከራዎች እያሠቃየ ሦስት ጊዜም ቢገድለው ጌታችን ግን ቅዱስ #ጊዮርጊስን ከሞት እያስነሣው ከሃድያንን ያሳፍራቸው ነበር

👉ንጉሥ ዱድያኖስ የሚያደርገው ቢያጣ ጭፍሮቹን በመንኰራኩር ፈጭታችሁ አጥንቱን ደብረ ይድራስ ተራራ ላይ ወስዳችሁ ዝሩት ብሎ አዘዛቸው ጭፍሮቹም የቅዱስ #ጊዮርጊስን ሥጋ በመንኰራኩር ፈጭተው ወስደው በተራራው ላይ ቢረጩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ #ጊዮርጊስ_ቅዱሱ_ለእግዚአብሔር ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር እያሉ አመስግነዋል

👉አሁንም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነሣውና ሥጋውን
ፈጭተው በተራራም ላይ ሥጋውን በትነውት ወደ ንጉሡ የሚመለሱትን ወታደሮች በመንገድ ከኋላቸው ሄዶ ደረሰባቸውና #ቆዩኝ_ጠብቁኝ አላቸው እነርሱም እጅግ ደንግጠው ይህ
እንዴት እንደሆነ ሲጠይቁት #አምላኬ_ከሞት_አዳነኝ አላቸው

👉ጭፍሮቹም እጅግ ደንግጠው ከእግሩ ስር ወድቀው ‹‹ይቅር በለን›› ብለው በአምላኩ እንደሚያምኑ መሰከሩለት ቅዱስ #ጊዮርጊስም ከመሬት ላይ ውሃ አመንጭቶ በጸሎት ጌታችንን
ቢጠይቅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ አጥምቋቸዋል እነርሱም በንጉሣቸው ፊት ሄደው ስለጌታችን #በመመስከር በሰማዕትነት ዐርፈዋል

👉 #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ዐፅሙ ተቃጥሎ አጥንቱ ተፈጭቶ #በደብረ_ይድራስ_ተራራ ላይ የተበተነው በዚህች በጥር 18 ዕለት ነው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም
አገልጋይ ብርቱዉንም ደካማዉንም ፍጥረት ኹሉ ፈጥነህ የምትረዳ ሊቀ ሰማዕታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሆይ እንደ እመቤትህ ቅድስት ድንግል ማርያም አንተም ከበቀልና ቂም የተለየህ ርኅሩኅ ልብና ለሰዎች ኹሉ የምታዝን ደግ ሰማዕት ነኽ

👉አማላጅነትህን በመታመን ለሚጠራህ ኹሉ ከነፋስ ዐውሎ ይልቅ ፈጥነህ የምትደርስ ሊቀ ሰማዕታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሆይ የርሕሩሕ አምላክ #እግዚአብሔር ርህራሄን ተጎናጽፈኻልና በዚህ ሰአት በጭንቅ ያሉ የወዳጆችህን ልመና ስማ

👉ኅዘንን የምታረጋጋ አባቴ ፍጡነ ረድኤት ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ #ጊዮርጊስ ሆይ ለጠላት መሣቂያ ለጠላቶቻችን መዘባበቻ እናድንሆን በገዳም ያሉ የእናቶቻችንን የአባቶቻችንን የጩኸት ድምፅ ሰማ

👉ከሃዲው ንጉሥ ዱድያኖስ ሰባው ነገሥት ስለ #ክርስቶስ ሰለመሠከረ አካላቱ እየቆራረጡ በሥጋው የአሠቃዩት የልዑል #እግዚአብሔር ወታደር ፍጡነ ረድኤት ኃያል ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ እንሆ የተጋድሎ ዝናውን ስንሰማ ግርማ
ሞገስህ ከሰማዕታት ኹሉ ይበልጣል

👉ለሰባት ዓመታት ትእግሥትን በማዘወተር አስጨናቂዎች መከራዎችን ለተሸከመ ትከሻህ ሰላምታ የሚገባህ የአስጨናቂዎች የሥቃይ ሰባት ዓመታትን የታገሥህ ሊቀ ሰማዕታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሆይ የድል በተርህን ይዘህ ኹልጊዜ እደሚገሰግስ አርበኛ የኢትያጵያ ጠላቶች ትመታልን ዘንድ ፈጥነህ ገሥግሰህ ናልን

👉አቤቱ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ አምላክ እዘንልን ራራልን ይቅርም በለን የሰማእቱ ረድኤትና በረከት አይለየን ምልጃ ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
ጥር 21/2016 #አስተርእዮ_ማርያም (እረፍታ ለሶልያና)

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለእናታችን #ሶልያና_ለአስተርእዮ_ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን

ሞት ለሚሞት ሰዉ ይገባዋል #የማርያም ሞት ግን
እጅግ ያስገርማል

👉 #አስተርእዮ ማለት መታየት #መገለጥ ማለት ነው ቃሉ አስተርአየ ታየ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው

👉ከጌታችን የልደት በዓል ጀምሮ እስከ ጥር መጨረሻ ያለው ጊዜ ዘመነ #አስተርእዮ በመባል ይታወቃል

👉የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር #አስተርእዮ_ማርያም ተብሏል

👉እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ /21/ በእሑድ ቀን ነብሷ ከስጋዋ ተለየች

👉ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች #ወላዲተ_አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ” "የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ" ብሏታል መኃ. ፪፥፲ /2፥10/

"ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዴት ያስገርማል
የማርያም ነገር"

👉እመቤታችን ሆይ #ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
የካቲት 18/2016 #ፆመ_ነነዌ

👉#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆም እና በፀሎት ለምንማፀንበት ሀገር እና ህዝብ ከጥፋት ለዳኑበት ትንሽ ቀን ሆና በስራዋ ግን ታላቅ ታምር ለተፈፀመባት #ፆመ_ነነዌ እንኳን አደረሰን

👉ነነዌ ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ፆሙ ሶስት ( 3 ) ቀን ብቻ ነው ቀኖቹም በየዓመቱ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ናቸው #የነነዌ_ፆም በመባቻ ሐሙስ( አቆጣጠር ) ከፍ እና ዝቅ ስለሚል አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል ።

👉እናም የ2016 #ፆመ_ነነዌ የካቲት 18 ሰኞ ይጀምራል የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን ፆም የወሰኑት ልትጠፋ የነበረች ነነዌን በፆም ምክንያት #እግዚአብሔር ይቅር ስላላት ይህን አምላካዊ ይቅርታውን ለዘለዓለም ለማሰብና ዛሬም በዚህ ዓለም ከነነዌ የከፋ ርኩሰትንና ኃጢያትን ስላለ የነነዌ ሕዝብ ይቅር ያልክ አምላክ ዛሬን #ይቅር_በለን ለማለት ነው

👉የነነዌ ሰዎችም #እግዚአብሔርን አመኑ ለፆም አዋጅ ነገሩ ከትልቁም ጀምሮ እስከ ትንሾቹም ማቅ ለበሱ ወሬውም ለነነዌ ንጉስ ደረሰ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናፀፊያውን አውልቆ #ማቅንም_ለበሰ_አመድ ላይም ተቀመጠ አዋጅንም አስነገረ

👉በነነዌም ውስጥ የንጉሱንና የመኳንቱን ትእዛዝ አሳወጀ እንዲህም አለ #ሰዎችም_እንስሶችም አንዳችም እንዳይቀምሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ ሰዎችና እንስሳትም #በማቅ ይከደኑ ወደ #እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩሁ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።

👉እኛ እንዳንጠፋ #እግዚአብሔር ተመልሶ ይፀፀት እንደሄነ ከፅኑ ቁጣውስ ይመለስ እንደሆነ ምን ይታወቃል በማለትም አሳሳበ #እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸውም እንደተመለሱ በስራቸውም አየ #እግዚአብሔር_አምላክም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተፀፀቶ አላደረገውም ት;ዮናስ 3፤5-10

👉 #የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸሩ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንንም በምህረት አይኑ ይጎብኝልን ቸርነቱን ያብዛልን ፆሙንም ለጥያቄያችን መልስ የምናገኝበት የበረከት ፆም ይሆንልን ዘንድ የአምላካችን #ቅዱስ_ፈቃድ ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ፲፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ እንኳን አደረስዎ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
ይቅርታ!! 🙏

◈ ከአብይ ፆም በፊት እያወኩ በድፍረት ሳላውቅም በስህተት ያስቀየምኳችሁ የማውቃችሁንም ሆነ የማላውቃችሁ በሙሉ በእግዚአብሔር ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ።🙏

◈ ለ 7 ሰው እናንተም ይህንን ሼር በማድረግ የምታውቋቸውንም የማታውቋቸውንም ሰዎች ይቅርታ በመጠየቅ አብይ ፆምን በይቅርታ በንፁህ ልብ እንጀምር አላለሁ 🙏

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት

ዘወረደ (ጾመ ሕርቃን)
"ዘወረደ" ማለት "የወረደ" ማለት ነው፡፡  አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው።
ይህም  ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤  ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት  የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ዮሐ፫፥፲፫

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት "የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ" እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ። 

ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ”ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭  ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው፡፡

ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም  ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው ፡፡

ዘወረደ ማለት?
የምስጢረ ሥጋዌ(የአምላክ ሰው መሆን) ትምህርት ነው፡፡ ዘወረደ ስንል አምላክ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ ፤ በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆነ ማለታችን ነው ፡፡ 

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ሲሆን ሞቶ በመብል ምክንያት የሞተው አዳምን  ሕያው አደረገው ፡፡ አምላክ ወልደ አምላክ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ሞቶ ለአዳም ያለውን ታላቅ ፍቅር ገለጸ፡፡

"ጠላቶቹ ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን ፥ ይልቁንም ከታረቅን በኃላ በሕይወቱ እንድናለን፡፡"ሮሜ፭፥ ፲ ፡፡ በዚህም ትህትናን ፍቅርን አስተማረን ፡፡

የመጀመሪያ የዐብይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ስያሜውም፤ በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡

በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡

የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡

የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡

ጾም ሥጋችንን ለነፍሳችን የምናስገዛበት ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት የጽድቅ መንገድ ለሥጋ ጤንነትም ቢሆን አስፈላጊያችን የሆነ አንዱና ዋነኛዉ የጽድቅ እቃ ጦራችን ነዉ፡፡

ሆኖም የጾም ወቅት ሲመጣ አቀበት የሚወጡ ይመስል የሚፈሩትና የሚያማርሩት ሳይሆን እንኳን መጣልን ተብሎ  በጉጉት የሚናፈቅ መሆን አለበት፡፡ስለሆነም ማንኛዉም ሰዉ ጾሙን ሲጀምር የሚከተሉትን ጉዳዮች በደንብ ሊያጤናቸዉ ይገባል፡፡

የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስየተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅም በፆም ድል ማድረግን ለእኛ አስተምሮናል።

እኛም በዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀርእንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ።

በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳን እናቶች እንዳሉን እናስተውል። በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ በሚታየው አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ፆም በመፆም ልዑል
እግዚአብሔር የፀሎታችንን ምላሽ እንዲሰጠን እንማፀን።

ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን።
"ወስብሐት ለእግዚአብሔር"

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​​​ቅድስት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)

«ቅድስት» ማለት የዘይቤ ፍችው « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው። ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2

ቅድስት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው። ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ ክቡር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው። መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ቅዱስ፡ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡ ( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡

የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ቅዱስ ›› የሚለው ቃል ለሰዎች ፡ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ: ለዕለታት … ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም
ይህንን ሲያስተምረን ነው። ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃይማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፡ ጽድቅ ከኃጢአት፡ ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡

ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣ በማኅበራዊ ኑራአችን ፣በምንበላው ምግብ ፣በምንለብሰው ልብስ ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል (ዕብ 12፡1)።

ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
Photo
የፆመ ኢየሱስ ሦስተኛ ሳምንት #ምኩራብ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ፆም ፀሎታችንን ይቀበልልን

👉 #ጌታ_ክርስቶስ ለደካሞች እጅግ ያዝን ነበር ከተናቁት ጋር መአድ ላይ ቀርቦ ተመልክተነዋል ከተጠሉት ጋር አብሮ መቀመጡንም አልጠላም ለደካሞች ቃሉን አያጠነክርም የቁጣ ጅራፉን አያነሳም

👉 #ምኩራብ በገባ ጊዜ ምን እንዳደረገ ለአፍታ እናስታውስ አይሁድ የጸሎት ቤተ የተሰኘውን ምኩራብ ሲሸጡበት ሲለውጡበት ተመለከተ ጅራፍ አበጅቶም ገበያቸውን ፈታባቸው ለሁሉ ጅራፉን ሲያነሳ ርግቦች ላይ ግን ከማንሳት ወደ ኋላ አለ ምክንያቱም  ርግብና መሰል እንስሳት አካላቸው ዱላ አይችሉም ለሞት ይሆናሉ

👉 #ጌታ_ክርስቶስ ምን እንዳደረገ ተመልከቱ ለቤቱ ቢቀናም ደካሞችን ሊጎዳ  ጅራፍ ሊያነሳባቸው አልወደደም ሲሸጡ ሲለውጡ የነበሩት ላይ ቢሆን ይህን ያደረገው ለትምህርት እንዲሆናቸው እንጂ ሊጎዳቸው አልነበረምና ሊያጠፋቸው ቢወድ በአንድ ቃል ምድር ተከፍታ በዋጠቻቸው ነበር

👉እርሱ ግን ቁጣው #ለትምህርት እንዲሆናቸው ብቻ ወደደ የኛ ቁም ነገር ግን ይህ ነው በአማኞች መካከል እንደ ርግብ የዋህ የሆኑ አሉ በጠንካራ ቃላቶች የሚደነግጡ ብዙ ናቸው በጥቂቶች በደል የተያዙ ገር አማኞች በየስፍራው ይገኛሉ

👉ጅራፍ ስናነሳ ምናሳርፈው ማን ላይ ነው አንድ አንድ ወቅቶች አሉ #ለቤተክርስቲያን ቀንተን ምናወጣቸው ቃላቶች ከሩቅ ያሉ አማኞችን ያስደነግጣል ዘለፋዎቻችን ያደክማቸዋል

👉በትጋት ያሉትን ሳየቀር ያስደነግጣል #መቅናታችን የዋሀኑን እንዳይጎዳ በማሰብ ቢሆን እንዴት መልካም ነው ቅጣታችን በጥቂቶች ኃጢአት የተያዙ ሃይማኖታዊ ሰውነታቸው ስስ የሆነባቸውን አማኞች እንዳይጎዳ እናስተውል አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከሰንበት ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​መጋቢት 22/2016 #የፆመ_ኢየሱስ ፬ኛ ሳምንት #መፃጉዕ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና ፀሎት ለምንማፀንበት ለ4ተኛ የፆም ሳምንት #መፃጉዕ በሰላም አደረሰን

👉 #መፃጉዕ ማለት የወደቀ የተጨበጠ የሰለለ መነሣት መቀመጥ የማይችል ሽባ ጎባጣ ሕመምተኛ ማለት ነው በዚህ ሳምንት በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5 የተዘገበውን ታሪክ የሚታሰብበት ነዉ

👉ለ38 ዓመታት የደዌ ዳኛ የአልጋ ቁራኛ ኹኖ የሚኖር አንድ ሰው ነበር በመጠመቂያ ስፍራ ሕመምተኞች በዚያ ተሰልፈው በዓመት 1 ጊዜ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሲነካው ቀድሞ የገባ ይፈወስ ነበር በዚህ ኹኔታ ሕመምተኞች ባሕሩ ከበው ሲጠብቁ አስታማሚ ያለው ቀድሞ በመጠመቅ ይፈወስ ነበር

👉ይህ #መጻጉዕ በዚህ ኹኔታ አሰታማሚ ዐጥቶ ለ38 ዓመት ኖረ ጌታ ቀርቦ ልትድን ትወዳለኽ አለው አዎ ጌታዬ ሰው የለኝም ውሃው ሲታወክ ወደ ጥምቀት የሚያገባኝ በማጣቴ አለው፡፡

👉 #መጻጉዕ ጌታን ሲያየው የ30 ዓመት ወጣት ነውና አንስቶ ተሸክሞ ይወሰደኛል ብሎ አስቦ ነበር ነገር ግን ባልጠበቀው ልትድን ተወዳለህ ብሎ ጠየቀው አዎን አለ እንግዲያው ተነሥና አልጋኽን ተሸክመኽ ኺድ ብሎ በቃሉ ተናግሮ ከበሽታው አዳነዉ ፈወሰዉ

👉አይሁድ ግን ለምን በሰንበት አልጋህን ትሸከማል በሚል ክስ አቀረቡበት ታሞ የተነሣ ፈጣሪውን ረሳ እንዲሉ #የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ማድነቅና መመስከር ሲገባው መፃጉዕም ያደነኝ ተሸከም አለኝ በማለት ከአይሁድ ጎራ ተሰልፏል በዕለተ ዐርብም የጌታን ፊት በመምታት በሰንበት ቀን አድኖኛል ብሎ ለአይሁድ እንደመሰከረ ይነገራል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሣምንቱን በሠላም በጤና ያስፈፅመን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​መጋቢት 29/2016 #በዐለ_ደብረ_ዘይት

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የዘንድሮው #ዘመነ_ዮሐንስ መጋቢት 29 አምስት በአላት አንድ ላይ ዉለዋል

1ኛ ዕለተ ሰንበት
2ኛ ደብረ ዘይት ዕለተ ምፅዓት
3ኛ በዓለ ፅንሰት
4ኛ ዓለም የተፈጠረበት
5ኛ ጥንተ ትንሣኤ

👉ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን #ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም ማቴ፤24፣36)

👉 ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ማንም አያውቅም ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ፣ዕለቱ ዕለተ እሑድ፣
ሰዓቱ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ቢታወቅም ብዙ ዘመነ ዮሐንስ፣ ብዙ ዕለተ እሑድ፣ብዙ መንፈቀ ሌሊት አለና ስለዚህ አይታወቅም የሰማይ #መላእክትም አያውቁትም

👉ልጅም አያውቀውም ማለቱ ልጅ ያለው ማንን ነው ከተባለ ፍጥረታትን ሁሉ ማለቱ ነው ኦሪት ዘልደት ሲል ኦሪት ዘፍጥረት ማለት እንደሆነ ሁሉ ልጅም ቢሆን አያውቅም የሚለው ቃል #መላእክትም ሌሎች ፍጥረታትም አያውቁም ማለት ነው

👉 #ከአብ በቀር የሚያውቃት የለም ማለቱ "በቀር" የሚለው ቃል ከፍጡራን ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው አይደለም ይህን የመሰለ አገላለፅ 1ኛ ጢሞ፤1፣17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው ለማይታየውም ለዘለዓለም ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘለዓለም ድረስ ይሁን አሜን የሚል ቃል አለ

👉በዚህ አገላለፅ "ብቻውን" ስላለ አምላክ "አብ" ብቻ ሊመስለን ይችላል ነገር ግን ብቻውን የሚለው ከፍጥረታት ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል ምክንያቱ #ሥላሴ በአብ፤ልብነት ያስባሉ በወልድ፤ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ፤እስትንፋስነት ለዘለዓለም ይኖራሉ

👉 #አጋዕዝተ_ዓለም_ሥላሴ ፤የአለምን መጨረሻ በአብ ልብነት ያውቃሉ፤ በወልድ ቃልነት የሚነገርበት ጊዜ ሲደርስ ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ጊዜው ሲደርስ ዓለምን ያሳልፋሉ ማለት ነው።

👉ሞት በሰዎች ትከሻ ላይ የተሰየመ ነውና ምጽዓተ ክርስቶስን ብቻ አንጠብቅ ሞት ለሰው ልጅ ዕለተ ምጽዓት ነው ምክንያቱም ከሞት በኋላ ጽድቅ ሥራ መሥራት፣መፆም፣ መጸለይ፣ መስገድ፣ ንስሐ መግባት፣ አይቻልምና ስለዚህ ሁል ጊዜ ከኃጢአት ርቀን ሕጉን ጠብቀን ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን ለመኖር ጌታችን ይርዳን

👉እንዲሁም በዚህች ቀን #አለም_የተፈጠረበት ለእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም የከበረ መልአክ #ገብርኤል የጌታን መፀነስ የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል

👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው

👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍፁም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኩር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና

👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን #መጋቢት_ሃያ_ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን ዳግም ሲመጣም ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን የምንሰማዉን የምናየዉን ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ ነገር ይቀይርልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️💒✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 6/2016 #ፆመ_ኢየሱስ_6ኛ_ሳምንት_ገብርሄር

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የአብይ ፆም 6ኛ ሳምንት #ገብርሔር :- ገብር ማለት አገልጋይ፣ሔር ማለት ቸር ማለት ነው

👉በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 25 እንደተገለጸው ቸሩ ፈጣሪ እራሱን እንደ ባለፀጋ ሰይሞ ለሶስት ሰዎች #መክሊት ፀጋና በረከት እንደሰጣቸውና አንድ መክሊት የተሰጠው አንተ ያልዘራኸውን የምታጭድ ጨካኝ መሆንህን ስለማውቅ ደብቄ ያቆየሁትን መክሊትህን እንካ አለው

👉የተሰጠንን ፀጋ በተለይ ካህናት አብዝተን ለጌታ መመለስ እንደሚገባን ሲያስተምረን አንተ በትንሽ ያልታመንክ እንደሌሎቹ አብዝተህ እንኳን ልትሰጠኝ ባትችል ለለዋጮች አደራ ሰጥተህ ልታተርፈው ትችል ነበር አለው  ስለዚህ #መክሊቱን ውሰዱበት  አስር መክሊትም ላለው ስጡት ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታልና

👉ምዕመናን ከዚህ ምን እንማራለን #እግዚአብሔር በሰጠን ፀጋ ጤንነትና እውቀት ተጠቅመን በዚህ ዐቢይ ፆም የሰራዊት ጌታ የሚወደውን መልካም በጎ ምግባር ብቻ አብዝተን በመስራት ፈጣሪን ማስደሰት እንደሚገባን ያስተምረናል

👉እርሱ የሚያተርፈው ይህን ጊዜ ብቻ ነው ሌላውማ ምን ቸግሮት ስለሆነም በአንቃድዎ ልቦናና በሰቂለ ህሊና ትኩረታችንን ወደ ጌታ መልሰንና በንስሐ ታጥበን ሁል ጊዜ ልንፀልይና ልንሰግድ ይገባናል  ቸሩ አንድ አምላክ ለሰው ዘር በሙሉ ምህረቱንና ረድኤቱን ይላክልን እኛም የተሰጠንን #መክሊት አትርፈንበት ታማኝ አገልጋይ ተብለን በጌታችን ታምነን የክብሩ ወራሾች እንድንሆን አምላካችን ይፍቀድልን "አሜን"

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 13/2016 #የፆመ_ኢየሱስ_7ኛ_ሳምንት_ኒቆዲሞስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለፆሙ 7ኛ ሳምንት #ለኒቆዲሞስ መታሠቢያ እንኳን አደረሰን

"ኒቆዲሞስ ይጠራችኋል"

1ኛ.ኢትዮጵያዊ በተወለደበት መንደሩና አፉን በፈታበት ቋንቋው እየተፈረጀ አንተ ከየት ነህ እየተባለ በሚፈናቀልበትና በሚገደልበት ባለሥልጣን የሆናችሁት አለቆች

2ኛ.በሰው ሠራሽ ችግር ብዙ ወገን ትናንት ሰጪ ዛሬ ለማኝ በሆነባት፤ ወደ ሀብት ተጉዛችሁ ሳይሆን እሱ ራሱ ሀብት ድንገት ደርሶባችሁ በድንገቴ ሀብታም የሆናችሁ ባለፀጎች

3ኛ.ያለ ጥም ቆራጭ እውቀታችሁ ራሳችሁን አዋቂና ምሁር ስታደርጉበት ሕዝቡ ምሁራን እያለ የሚጠራችሁ የሀገሬ ምሁራን ሁላችሁ

👉በዛሬው ዕለተ #ሰንበት_ኒቆዲሞስ ይጠራችኋል ወደ እሱ ባትመጡ እንኳን እስኪ እንደው አንድ ጊዜ ባላችሁበት ሁኑና ስሙት

👉እኔ ሦስት ነገሮች የተስማሙልኝ ሰው ነበርኩ ሀብት ሥልጣን ዕውቀት ይሁን እንጂ ጎዶሎ ነበርኩ

👉ጎዶሎዬም #እግዚአብሔር ነበር እሱን የምሞላበት ጊዜ ስፈልግ የራሴን ጊዜ የምተኛበትን እረፍተ ሥጋ የምወስድበትን ጊዜ አገኘሁ እናም ይኼንን ጊዜ ሰዋሁና በጨለማ በሌሊት ከጌታዬ እግር ሥር ቁጭ ብዬ ጎዶሎዬን ሞላሁት

👉ይገርማል ወደ #እግዚአብሔር ስንቀርብ ያለን ምድራዊ ሀብት ሥልጣንና ዕውቀት ሁሉ የሚወሰድብን ይመስለናል ግን እንደምናስበው አይደለም

👉እኔ ራሴ ሦስቱን ምድራዊና ጊዜያዊ ነገሮች ይዤ መጥቼ ሦስት ዘላለማዊና ሰማያዊ ስጦታዎችን ነው ይዤ የተመለስኩት

1ኛ. ምድራዊ ሥልጣን ነበረኝ የሥላሴ ልጅ የመሆን ሥልጣን ገንዘብ አደረኩኝ፤ የጌታዬን ቅዱስ ሥጋ ለመገነዝም በቃሁ

2ኛ. ምድራዊ ሀብት ነበረኝ ሰማያዊዉን የፀጋ ልጅነት ሀብት ርስተ መንግሥተ ሰማያትን የማግኘት ሀብት የዘላለማዊ ሕይወት ሀብት አግኝቼ ተመለስኩ

3ኛ. ምድራዊ ዕውቀት ነበረኝ ያውም የብሉይ ኪዳን ወደ ጌታዬ ስመጣ ግን ምሁረ ሐዲስ ሆንኩኝ #ምሥጢረ_ሥላሴን ምሥጢረ ጥምቀትን ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን የማወቅ ፀጋ ተጨመረልኝ ይላችኋል

መልካም ዕለተ ሰንበት
❖ ኒቆዲሞስ ❖

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​ሚያዚያ 20/2016 #የፆመ_ኢየሱስ 8ኛ ሳምንት #ሆሣዕና

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንና መድኃኒታችንን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት ስምንተኛ ሳምንት በአለ #ሆሣዕና እንኳን አደረሰን

👉 #ሆሣዕና በአርያም፣ ሆሣዕና በአርያም፣ ሆሣዕና በአርያም

👉 #ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው

👉 #ሆሣዕና ከጌታችን ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው

👉ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከኢየሩሳሌም ወደ ቤተ መቅደስ ለመግባት በፈለገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ፊታችሁ ባለው ሀገር ሂዱና አህያ ከውርጭላዋ ጋራ ታስራ ታገኛላችው ፈታችው አምጡልኝ ምን ያደርግላችኋል የሚላችው ሰው ካለ #ጌታቸው ይፈልጋቸዋል በሉ ብሎ ላካቸው

👉ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ እንዳዘዛቸው ሂደው ፈተው አመጡለት በዚያም የተሰበሰቡት ሁሉ #በአህዮቹ ላይ ልብሳቸውን ጎዘጎዙለት ጌታችንም በሁለቱ አህዮች ላይ ተቀመጠ ከሌሎቹ እንስሳት አህዮችን መርጦ በአህዮች ተቀምጧል

👉 #አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸውና የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች ዘኁ 22 እስከ 28 ጌታችን በተወለደ ጊዜ #አህዮች_ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን አሟሙቀውታል

👉 #የሆሣዕና_አህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል ለምን የተዋረዱት አህዮችን መረጠ?

1 ትሕትናን ለማስተማር

👉የትሕትና ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ ደመና አዞ ነፋስ ጠቅሶ በእሳት መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ነው ነገር ግን የመጣው #ለሰው_ልጅ ትህትናን ሊያስተምር ነውና በአህያ ተቀመጠ

2 ትንቢቱን ለመፈፀም

👉ትንቢት አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሁትም ሁኖ #በእህያም_በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈፀም ነው
ዘካ፣9፥1

3 ምሳሌውን ለመግለጽ

👉ምሳሌ ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና #ጌታችንም_ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል

4 ምሥጢሩን ለመግለፅ

👉ምሥጢር በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል #በአህያይቱ ላይ ተቀምጧል

👉ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ሕግ ናትና በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም #ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው

👉ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ነው 14ቱን ምዕራፍ በእግሩ ሂዶ ሁለቱን ምዕራፍ #በአህያይቱ ሂዷል #በውርጭላይቱ ሆኖ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሱን ዙሯል 14 ምዕራፍ የአስርቱ ትእዛዛትና የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ አስሩ ምዕራፍ የአስርቱ ትአዛዛት አራቱ ምዕራፍ የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ ነው

👉 #አራቱ_ኪዳናት የሚባሉት እነዚህ ናቸው ኪዳነ ኖህ፣ ክህነተ መልከ ጼዴቅ፣ ግዝረተ አብርሀምና ጥምቀተ ዮሐንስ ናቸው

👉 #በአህያይቱ ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ
በአህያዋ ላይ ኮርቻ ሳያደርጉ ልብስ አንጥፈውለታል ኮርቻ ይቆረቁራል ልብስ አይቆረቁርም የማትቆረቁር ህግ ሰራህልን ሲሉ ነው

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ዘወረደ ብለን ጀምረን ሆሣእና ብለን ሱባኤያችንን እንድንፈፅም ስለረዳኸን እናመሰግንሃለን #ሰሙነ_ህማማቱንም በሠላም አስፈፅመህ #ለብርሃነ_ትንሣኤህ በሠላም አድርሰን የተባረከ #እለተ_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
​​በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸ ሥርዓቶች

1, ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                   •➢ ሼር // SHARE

     ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
💚
@Orthodox_tewahdo_nen💚     
💛@Orthodox_tewahdo_nen💛
❤️
@Orthodox_tewahdo_nen❤️
      ✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥