Forwarded from ✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞ (◦•●◉✿ T҈ o҈ m҈ a҈ s҈ ✿◉●•◦)
መስከረም 16/2018 #የመስቀል_ደመራ_በዐል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሠላምና በጤና ጠብቆ ለ2018 #የመስቀል_ደመራ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ደመራ ደመረ ከሚለው መነሻ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም መሰብሰብ ማከማቸት እንደማለት ነው ከዚህ ተነስተን ደመራ ማለት የመሰብሰብ ወይም የመደመር ሂደት (ደመራ፤ ድመራ ) ልንለው እንችላለን፡፡
👉ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሁሉንም ከፈፀመ በኋላ እንደ ወንጀለኛ በእንጨት መስቀል ተሰቅሎ ሞተ መስቀል የወንጀለኛ መቅጫ ነበር ጌታ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ የተሰቀለበትን መስቀል አይሁድ እንደ ተራ ነገር አውላላ ሜዳ ላይ ጣሉት
👉ከጊዜ በኋላ ግን ወደ አይሁዳዊያን ጆሮ አንድ ነገር መጣ እንደ ቀልድ የጣሉት #የክርስቶስ_መስቀል ህሙማንን እየፈወሰ እውራንን እያበራ ድንቅ ታእምራትንም እያደረገ እንደሆነ ሰሙ በዚህ ጊዜ ክርስቶስን ከከተማው አውጥተው እንደሰቀሉት ሁሉ መስቀሉንም እንዲሁ ከከተማ ውጭ አውጥተው በተራሮች መካከል ቀበሩት ቆሻሻም መጣያ አደረጉት
👉 #እግዚአብሔር ግን ነገርን የሚያከናውንበት ጊዜ አለውና ደግ ዘመን መጥቶ በእስጢፋኖስ ሞት የተበተነው የክርስትናው ዘር ማፍራት ጀመረ በሮም ነግሰው የነበሩት መክሲሚያኖስ እና ዲዮቅልጢያኖስ ክርስቲያኖችን እንደ ሰም እያቀለጡ እንደ ገል እያደቀቁ ከነፍሰጡሮች ማህፀን ሽል አውጥተው በሰይፋቸው እየሰነጠቁ በስቡ ጎራዲያቸውን በሚወለውሉበት አስከፊ ዘመን ነበር
👉በዚያ አስደንጋጭ የዘመነ ሰማዕታት የስቃይ ጊዜ በነገራችን ላይ #ቤተክርስቲያን በዚያ ዘመን ከደረሰባት መከራ የበለጠ እስካሁን አልደረሰባትም ወደፊትም ይደርስባታል ተብሎ አይገመትም ብዙ #ክርስቲያኖች ዋሻ ውስጥ ገብተው ትውፊት ቁሳዊንና ትውፊት መንፈሳዊውን እየጠበቁ በብዙ መከራ የተስፋይቱን ቀን ሲናፍቁ ነበር
👉በዚያ #የክርስቲያኑ ስደት በተጀመረበት ጊዜ አንዲት ሴት ከነዚህ መከራ ከወረደባቸው ስለ #ክርስቶስ መከራ የሚቀበሉት ጋር አብራ ገፈት ቀማሽ ነበረች ስሟ እሌኒ ይባላል በኋላ የመከራው ዘመን ሲያልፍ ንጉስ ቆንስጣን አግብታ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ወልዳለች #ንግስቲቱ_እሌኒ በመከራ ውስጥ እግዚአብሔር የለያት ሴት በንግስትነት ስትኖር ቤተ መንግስቱ ስለተመቻት ክርስቶስን አረሳችውም
👉ይልቁንም የጌታ ፍቅር እንደ እግር እሳት ስለሚያንገበግባት እሱን በአይነ ስጋ ባላገኘውም እንኳን #መስቀሉን አግኝቼ ገላው ያረፈበትን አቅፌ ተሳልሜ ብላ ፍቅሯን ለመወጣት #መንፈስ_ቅዱስ አነቃት ወደ #ኢየሩሳአሌምም መጣች
👉 #የክርስቶስ_መስቀል የተቀበረበት አካባቢ ማንም አያውቅም ያገኘችው አረጋዊ ሰው #ኪሪያኮስ እንኳን አካባቢውን ከመገመት ዉጪ አባቶቻችን ከነዚያ ተራሮች በአንዱ ነው ይላሉ ከማለት የዘለለ ሊነግራት አልቻለም ክርስቲያን ነገር ሲከብደው የሁሉ ነገር መፍትሔ ወዳለው ጌታ ይፀልያልና ንግስት እሌኒና አረጋዊ ክሪያኮስ ሱባዔ ይዘው ወደ ፈጣሪያቸው ማመልከት ጀመሩ
👉በመንፈስ እንደተረዱት እንጨት ሰብስበው ደመራ ደምረው እሳት ሲያነዱ ከእሳቱ ላንቃ በላይ ተምዘግዛጊ ጢስ ወጣ (ጢሰ ቅታሬ) እንደ #ጦር_ቀስት_ምልክት ያለው ታየ
👉ጢሱም በአንድ ተራራ አናት ላይ ተተከለ ሰው #እግዚአብሔርን ማገልገል ሲያቅተው ግዕዛንና እንስሳት ያገለግሉታል የቢታንያ ዲንጋዮች የሰባ ሰገል ኮኮብ የበልአም አህያ የገሊላ ባህር አሁን ደግሞ #የደመራው_ጢስ በአይሁድ በላይ ሆነ ጢሱም ያረፈበት ቦታ የመስቀሉ መገኛ መሆኑን ስላወቁ ደመራውን በደመሩበት ማግስት መስከረም 17 ቀን ቁፋሮ ተጀምሮ #ቅዱሱ_የጌታ_መስቀል መጋቢት 10 ቀን ተገኘ
👉 #የመስቀል_ደመራ በአል ለሀገራችን ሠላም የምናገኝበት ህዝባችን በፍቅር በአንድነት የሚኖርበት በአል ይሆንልን ዘንድ የአምላካችን የመድኃኒታችን #የኢየሱስ_ክርስቶስ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
መስከረም 16/2018 ዓ/ም
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤18🕊1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤13🥰2
Forwarded from ✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10🥰4
Forwarded from ✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙏8❤7
Forwarded from ✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤14🙏2
Forwarded from ✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞
ቤተ-ክርስቲያኗ በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማትን ሀዘን ገለፀች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማትን ጥልቅ ኀዘን ገልፃለች፡፡
ቤተ-ክርስቲያኗ ባስተላለፈችው የሀዘን መግለጫ፤ የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ዜና እረፍት የሰማነው በታላቅ ኀዘን ነው፤ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የሰላም የፍቅር፣ የአንድነት ተምሳሌት አባት ነበሩ ስትል ገልጻለች።
በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተወደዱና የተከበሩ የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ፤ በመላው ኢትዮጵያን ዘንድ በመልካም ስብእናቸውና በርሕራሔያቸው በታሪክ ሲታወሱ እንደሚኖሩም አመልክታለች።
ቤተ-ክርስቲያኗ በእኒህ የኢትዮጵያውያን ሁሉ አባት በነበሩት በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ዕረፍት የተሰማትን ጥልቅ ኀዘን ገልጻ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ መጽናናትን ተመኝታለች፡፡
📱 JOIN 📱 JOIN -📱 JOIN 📱 JOIN
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማትን ጥልቅ ኀዘን ገልፃለች፡፡
ቤተ-ክርስቲያኗ ባስተላለፈችው የሀዘን መግለጫ፤ የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ዜና እረፍት የሰማነው በታላቅ ኀዘን ነው፤ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የሰላም የፍቅር፣ የአንድነት ተምሳሌት አባት ነበሩ ስትል ገልጻለች።
በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተወደዱና የተከበሩ የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ፤ በመላው ኢትዮጵያን ዘንድ በመልካም ስብእናቸውና በርሕራሔያቸው በታሪክ ሲታወሱ እንደሚኖሩም አመልክታለች።
ቤተ-ክርስቲያኗ በእኒህ የኢትዮጵያውያን ሁሉ አባት በነበሩት በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ዕረፍት የተሰማትን ጥልቅ ኀዘን ገልጻ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ መጽናናትን ተመኝታለች፡፡
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤13
Forwarded from ✞ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነን✞ (◦•●◉✿ T҈ o҈ m҈ a҈ s҈ ✿◉●•◦)
ጥቅምት 14/2018 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ
▶️ በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ አባታችን #አቡነ_አረጋዊ ከዚህ አለም ለተሠወሩበት አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
▶️ በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ፃድቅ ናቸው የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው #ንጉሥ_ይስሐቅና_ቅድስት_እድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው
▶️ ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ
▶️ .በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል #የቤተ_መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል
▶️ የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም #ቅዱስ_መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ
▶️ በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን #አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል
▶️ ለሥራ በተለያዩ ጊዜም #አቡነ_አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን #ደብረ_ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል
▶️ እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ #ደብረ_ሃሌ_ሉያ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል
▶️ ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም የኢትዮጵያ መነኮሳት አባት ተብለዉ ይጠራሉ #አቡነ_አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል
▶️ #ቅዱስ_ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው #ንግስት_እድና ሁናለች
▶️ .ፃድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈፅመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው #ብሔረ_ሕያዋን ገብተዋል ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር #የምሕረት_ቃል_ኪዳን ሰጥቷቸዋል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን
▶️ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል ፃድቅን በፃድቅ ስም የሚቀበል #የፃድቁን_ዋጋ_ይወስዳል ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም ማቴ.10፥41
👉የፃድቁ አባታችን #አቡነ_አረጋዊ ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
📱 JOIN 📱 JOIN -📱 JOIN 📱 JOIN
👉የፃድቁ አባታችን #አቡነ_አረጋዊ ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤7🙏5😱1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤36👍6🙏1